cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ

أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ የሚፈስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
396
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-230 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
👆     ለጎዳና ኢፍጣር የተነጠፈ ሸራ እንዳይመስልህ   ለአላህ እንግዶች ለሑጃጆች ሂድማ የተዘጋጁ ትራንስፖርቶች ናቸው። 🤲አላህ እናት ሀገር ሳዑዲ, ህዝቦቿ እና መንግስቷን ጠብቅላት!!
380Loading...
02
📣 የ2ዓመት ወንጀል ያሰርዛል!! 🌺 የ"ዐረፋ" ን (የዙል-ሐጅን) 9ነኛ ቀን የፆመ ለሆነ ሰው ትልቅ ምንዳ አለው !!! 🌹ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተረጋግጦ እንደመጣው... 🌴 « (አማኝ) የዐረፋን ቀን ፆም በመፆሙ የተነሳ አላህ የአለፈውን ዓመትና የቀጣዩን ዓመት ወንጀል ይሰርዝለታል። ( ይምርለታል !!! ) » 🤝 ይህም ማለት ፦ በሌላ መረጃ ላይ ግልፅ እንደተደረገው ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅ መስፈርት ማለት ነው !!! 🎙️ ታላቁ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
441Loading...
03
«ጥቆማ፦ ለዒድ ወደ ሰባት ቤት እና ጅማ ተጓዦች እንዲሁም በዛ መንገድ ለምትሄዱ ሁሉ፤ ከሰበታ በታች ባሉ ከተሞች እስከ ወሊሶ መንገድ የፀጥታ ችግር ስላለ ከምሽቱ  12 ሰአት እስከ ጠዋቱ 12 ሰአት መንገድ ዝግ ስለሆነ ከመሸ በደረሱበት ከተማ ስለሚያስቆሟቸው ሰበታ ሲደርሱ 11:00 ከሆነ እዛው ውረድ ብለው ዲማ ፌደራል ኬላ አድረው ጠዋት 12 ሰአት ጉዞዋቸውን መቀጠል ብቸኛው አማራጭ ነው። ከሰበታ ተነስቶ ወሊሶን ለማለፍ በትንሹ  2 ሰአት ስለሚፈልግ እንዲሁመረም ፍተሻ በቅርብ ርቀት ስለሆነ ቀድሞ ማሰብ ያሰፈልጋል። አልፋለሁ ብሎ የገባ ሳያልፍ ሜዳ ላይ ሚሊሻና ፖሊስ የመኪና ቁልፍ ተቀብለውት፣ እዛው ያለ ጥበቃ አድሮ፣ ጠዋት መተው አስፓልት ላይ ቁልፉን በትነውት፣ የራሳችሁን ውሰዱ ብለው ነው የሚሄዱት። ባጠቃላይ ጉዞ የቀን ብቻ ስለሆነ የትራፊኩን ነገር ይታሰብበት ሰምታችኋል ጉራንስና የባድ ወልድ እንዲሁም መሰሎቻቸው!
661Loading...
04
Media files
640Loading...
05
ያረብ እኛንም ወፍቀን
601Loading...
06
"ሀገራዊ የምክክር ኮሚሸኑ የፌደራል መጅሊሰ እና የክልል መጅሊሶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች አለመቀበሉ የሀገሪቱ ግማሸ ህዝብ መናቅ ነው"በድር ኢትዮጵያ ... በድር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫውም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሸኑ የፌደራል መጅሊሰ እና የክልል መጅሊሶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች ተቀብሎ ማሰተካከያ ከማድረግ ይልቅ ንቀት በሚመሰል መልኩ በዝምታ ማለፉ የሀገሪቱ ግማሸ ህዝብ ወኪሎች በማይሳተፉበት ሁኔታ ሀገራዊ መግባባት ሰኬታማ ማድረግ እንደማይቻል መረዳት ይኖርባቸዋል"ብሏል። . ህዝበ ሙሰሊሙ በሀገረ መንግሰት ግንባታና በሀገር የኢኮኖሚ ሰርዐት ውሰጥ ታላቅ እሴት የሚጨምር የሀገር ትከሻ ፣ የማህበረሰባዊ ግብረገብ ጌጥ ፍትህ አበርክቶው ያልተፃፈለት ደማቅ ታሪክ አለው፡፡ በኢትዮጵያ አጨቃጫቂ እና አነታራኪ ጉዳዮች ብዙ ቢሆኑም አይፈቱም አይታረሙም ወይም አይሰተካከሉም ብሎ መደምደም አይቻልም ።ለዚህ ደግሞ ግልፅና ፍትሀዊ የሆኑ ህዝባዊ መድረኮች በቂ የመሸጋገሪያ ድልድዮች ናቸው ቸግሩ ያለው እነዚህን መድረኮች በአግባቡ ያለ መጠቀም እና የመጠቀም ጉዳይ ይመሰለናል። ይሁን እንጂ በጋራ ሀገር ለሚኖሩ ዜጎች ሁሉ ሊሰጥ የሚገባው የኢትዮጵያዊነት ውክልናና ዜግነት ሙሰሊሙ ማህበረሰብ ላይ ሲሆን የጥርጣሬ ሙግት መፍጠሩ የትናንቱ እኩይ ድርጊት ዛሬም እየታየ በመሆኑ በእጅጉ ያሳስበናል ። ባልተረጋገጠ _ ተረት ተረትና ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ የሙስሊሙን የውክልና እሴት መጨፍለቅ ወይም ባላወቀ መዝለል ለምን የሚል መፍትሔ ፈላጊ ጥያቄ ያጭራል።ያለ ሲሆን . በሀገረ መንግሰት ምሰረታ ላይ የጋራ አሻራን ለማሳረፍ ያለመቻል ለተጨማሪ አመታት እርሰ በርሰ መባላቱና የተባባሰ ሀገራዊ ቀውሰ ውሰጥ መገባቱ አይቀሬ ነው።ስለዚህ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ይሣካ ዘንድ ተቋሙ ፍትሀዊ ገለልተኛና ለሀገሩ እና ለህዝቡ በታማኝነት መፍትሔ አምጪ ምክክር ይሆን ዘንድ በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሙሰሊሞች ድርጅት በጥብቅ ያሳስባል።ብሏል በድር ኢትዮጵያ በመግለጫው። .. ሙሉ መግለጪውን ከታች አያይዘናል .
640Loading...
07
Media files
600Loading...
08
Media files
621Loading...
09
📮 ዓረፋ በገነንዳ በምሩ ኽሮት ያነወ📮⤵️ በሚል ርዕስ ወቅታዊ የሆነ መደመጥ ያለበት በጉራጊኛ  ቋንቋ የተደረገ ሙሐደራ⤵️ 📍👇ሙሐደራው ላይ ከተወሱ ነጥቦች ውስጥ በከፊሉ⤵️👇 💥አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ቱሩፋትና በልዩ መልኩ ከዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን። 💥 ኡዱሒያ የተደነገገበት ጥበብ {ሂክማ} እና ሁክሙ ምንድነው? 💥ክፍለ ሀገር ላይ ከዒደል ዓድሀ ዓረፋ ጋር በተያያዘ አንዳንድ  የሚፈፀሙ ሙንከራቶች 💥  የዒድ ቀን ለኡዱሒያ(እርድ) የሚዘጋጀው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ... 💥 ሲታረድም ሆነ ከታረደ በኋላ የሚባል ዱዓ ወይም ሌላ ነገር አለን? 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ሲሄዱ የሚያደርጉት የተለየ ዒባዳ አለን? 💥 ዒድ የሚሰገድበት ሰዓት {ጊዜ} እና የሚያበቃበት ሰዓት {ጊዜ}። 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በምን አይነት ሁኔታ ነው መሄድ ያለባቸው? 💥 የዒድ ሰላት አሰጋገድ ሁኔታ በተግባር ምን ይመስላል ተክቢራስ ስንቴ ነው ሚባለው? 📌  ሌሎችንም ነጥቦች የተዳሰሰበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ የሕያ ኢልያስ ቢን አወል አላህ ይጠብቀው።
580Loading...
10
ለኡዹሕያህ መከተ-ል-ሙከረማህ!
580Loading...
11
~ሂጃብ (ኒቃብ)ሱና ነዉ ለምትሉ ....! 🔖 ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን "አሏህ ይጠብቃቸውና" እንዲህ አሉ። ሴት ልጅ ፊቷን ገልጣ የምትወጣ ቢሆን ኖሮ ሊያጫት ለሚፈልግ ሰው ሂድና ተመልከታት የሚል ፍቃድ ባላስፈለገ ነበር።
974Loading...
12
ትክክለኛ ማንነት የሚታወቀዉ ትዳር ዉስጥ ከተገባ አብሮ መኖር ከተጀመረ በኋላ ነዉ ያኔ ግን ነገሮች ሊቀያየሩ ይችላሉ ብልጥ ሁኖ ነገሮች በመነጋገር እና ትእግስት በማድረግ ማስኬድ እንጅ ሳንጋባ በፊት እንድህ አልነበርሺም አልነበርክም እያሉ መጨቃጨቅ ይሄ ትዳር ለመፍረስ 1ኛ መንስኤ ነው @delilsuleyman @delilsuleyman
980Loading...
13
🌿የማይቀርበት  የሙሀደራ ግብዣ🌿 🎙በኡስታዝ መንሱር ሁሴን 🗓  የፊታችን እሁድ ሰኔ 02 / 2016E.C 🕌 በዓሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ መድረሳ 🕝 አስር ሰላት እንደተጠናቀቀ 📍ሴቶችንም ወንዶችንም ተጋብዛቹሀል❗️❗️❗️ 🔖 አድራሻ :- ሎሚሜዳ ከአሊ መስጂድ ጀርባ
940Loading...
14
ራስህን ያለ ትዳር አተዉ" ኢማመል ብኻሪ እንዲህ ይላሉ ፈተና በበዛበት ዘመን ለወጣቶች ከሀጅ በላይ ትዳር ዋጅብ ነዉ ! ኢብኑ መስኡድም እንዲህ ይላሉ ከእድሜየ አንዲት ለሊት ቢቀረኝ ሚስቴ ጋር መሆንን እመርጥ ነበር"
940Loading...
15
በህይወትህ ውስጥ ጨካኝ ቀናትና ፈታኝ ጊዜያት ይኖራሉ። አንተን የሚሰሩህም እነርሱ ናቸው። በየትኛውም ከባድ የህይወት አጋጣሚ ውስጥ ስታልፍ ትልቅ ትምህርት ትማራለህ። ትምህርቱ ደግሞ አንተን ይቀይርሃል። ቢያንስ ቢያንስ "ሁሉም ነገር ያልፋል" የሚል የህይወት እውነትን ትረዳለህ።
901Loading...
16
ዋናዉ ነገር አበባዉ አይደለም አበባዉን የሚይዘዉ እንጂ በዉስጡ ዉዴታ ካለ ሽታዉ ይጨምራል በዉስጡ ፍቅር ካለ ዉበቱ ይጨምራል ሰላም ለነዛ በልቦቻቸዉ ፍቅርን ተናግረዉ ዉዴታን ለሚያሳዩ ሁሉ
962Loading...
17
Media files
850Loading...
18
ዛሬ ለተጋባቹት ለመሀመድ ከድርና ለዘኪያ ሺፋ ባረከላሁ ለከማ ወባረክ አለይኩማ ወጀማ በይነኩማ ፊ ኸይር
860Loading...
19
ዛሬ ለተጋባቹት ለመሀመድ ከድርና ለዘኪያ ሺፋ ባረከላሁ ለከማ ወባረክ አለይኩማ ወጀማ በይነኩማ ፊ ኸይር🤣
10Loading...
20
ከመጅሊሱ  አጀንዳ 2 የቀጠለ... ለብሄራዊ ምክክር ከተላከ ሰነድ የተወሰደ 2.6 ብሄራዊ መዝሙር የብሔራዊ መዝሙር ይዘት ኢትዮጵያ የብዝሃ ሃይማኖት ባለቤት መሆኗን በሚገልፅ እና በሁሉም ህዝቦች የተገነባች ፤ ሁሉም ህዝቦቿም በጋራ የሚያሳድጓት መሆኗን በሚገልፅ መልኩ መቃኘት አለበት፡፡ በመሆኑም ብሄራዊ መዝሙር አስመልክቶ በምክክር መድረኩ አጀንዳው እንዲያዝልን እንጠይቃለን። 2.7ሀገር ወካይ ምልክቶች የሀገር ወካይ አልባሳት፣ምግቦች፣ ስነ-ጥበባት፣ አርማዎች (ወዘተ): ሀገርን ይወክላሉ ተብለው የሚጠቀሱ ስእሎች፣ እንስሳት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችና አለባበስ የሚባሉት፣ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝት የሚባሉት፣ በካላንደር፣ በብሄራዊ ስጦታዎች፣ በውጭ ሀገራት ኤምባሲዎቻችን በሚወከሉ ምስሎች፣ የሀገር ምልክቶች ሁሉን አቀፍ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም አሁን የሚንፀባረቁ ሀገራዊ ወካይ ምልክቶች ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንና በተለይም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የማይወክሉ በመሆናቸው ሁሉን አካታች በሆነ መንገድ ይቃኙ ዘንድ የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ እንዲሆኑ አቅርበናል፡፡ 2.8ሰንደቅ አላማ ሰንደቅ አለማ የሀገር ትልቁ መታወቂያ አርማ ነው፡፡ ከየትኛውም የባህል፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ ሁሉን ወካይ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም ኣንድ ባህል እና ሃይማኖት በብቸኝነት የኔ ነው የሚለው ሰንደቅ አላማ ሀገርን የመወከልና ህዝቦችን የማስተሳሰር እድል የለውም፡፡ በኢትዮጵያ ካሉ ቁልፍ ብሄራዊ መግባባት ከሚሹ ጉዳዮች አንዱ ሰንደቅ አላማ ሲሆን የሙስሊሙ ማህበረሰብም በአንክሮ የሚከታተለው ነው፡፡ በመሆኑም  ሰንደቅ አላማ አስመልክቶ የብሔራዊ ምክክሩ አንዱ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ እንጠይቃለን፡፡ 2.9ሀገራዊ እሴቶች ሀገራዊ እሴቶች በሀገሪቱ የረዥም ዘመን ታሪክ የተለያዩ ማህበረሰቦች በአኗኗር፣ በትውፊት፣ በአስተምህሮ፣ጠብቀዋቸው የቆዩ መገለጫዎች ናቸው፡፡ እሴቶች ሲጠኑ አንድን ህዝብ የስልጣኔና የትምህርት እሴቱን በማጥናት ስልጡን እንደነበረ፣ ሌለውን በሌላ መልኩ መልካም እሴቶች እንደሌሉት ተደርጎ ከቀረቡ ማህበረሰብን በታቀደ መልኩ የማሞገስ እና የማንኳሰስ ውጤት ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ እሴቶች በትምህርትና በሚዲያ የሚሰራጩ በመሆኑ ማህበረሰብን የመበየን አቅም አላቸው፡፡ በአግባቡ ከተሰሩ ሀገርን ከፍ ሲያደርጉ በአግባቡ ካልተበየኑ ኪሳራቸው ብዙ ነው፡፡ የሙስሊሙና የሌሎች ማህበረሰብ ልዩልዩ እሴቶች በልዩ ጥናት፣ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲለዩ፣ እንዲተዋወቁ፣ እንዲለሙ ለማድረግ የብሔራዊ ምክክሩ አንድ አጀንዳ እንዲሆኑ እና ውይይት እንዲካሄድባቸው እንጠይቃለን፡፡ 2.10የሃይማኖቶች እና የብሄር ብሄረሰብ ምልክቶች ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ሀገር ናት፡፡ ምልክቶቿም እነርሱን ሊመስሉ ይገባል፡፡ የብሔር ምልክቶች በራሳቸው የመወከላቸው ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ሁሉ ከሌሎች ብሔሮች ጋር ያላቸው መስተጋብርም በምልክትነት ሊወከል ይገባል፡፡ ሃይማኖቶችና ብሔሮች በጋራ የሚገለጡባቸው ምልክቶች ሚዛናቸውን ጠብቀው አንዱ አንዱን ሳይሸፍን ሊሰየም ይገባል። በመሆኑም የብሄር ብሄረሰቦች እና ሀይማኖቶች መገለጫ ምልክቶችን በተገቢው ግንኙነታቸውን እና ልዩነታቸውን የሚያረጋግጥ አሰራር ለማስፈን በብሄራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብልን እንጠይቃለን፡፡ 2.11የቀን አቆጣጠር(ካላንደር) የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጣር ተብሎ አሁን በግልጋሎት ላይ የሚገኘው ከኣንድ ሀይማኖት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የኢትዮጵያዊያን ሀይማኖቶችንና ባህሎችን ባካተተ መልኩ ዳግም መከለስ ያሻል፡፡ ዓመተ ምህረት (ዓ.ም) የሚለውን ሃይማኖታዊ ፍች ከሃገሪቷ ሴኩላራዊ ባህርይ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ሊቀየር ወይም ሊከለስ ይገባል። ኢትዮጵያ አማራጭ ካላንደሮች ሊኖሯት ይገባል፡፡ ግሪጎሪያን እና ሎካል እንደሚባለው ሂጅሪያ ካላንደርን በትይዩ ጥቅም ላይ ማዋል ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ በተጨማሪም ባህላዊ የሆኑ ካላንደሮች እንደሚታወቁ እና እንደሚከበሩ ሁሉ የሂጅራ ካላንደርም እንዲታወቅ እና እንዲከበር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በሂጅሪ ካላንደር መሠረት የሚታወቁ ጉልህ ክስተቶች ያሉ በመሆኑ የካላንደሩ እውቅና ማግኘት በሙስሊሙ ማህበረሰብም ሆነ እንደሀገር ወሳኝ ነው። አጠቃላይ የቀን አቆጣጠር በተለይም የሒጅራ ካሌንደር ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ክስተት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመሆኑም የሒጅራ ካሌንደር እንደትይዩ ካላንደር ሆኖ እንዲዘጋጅ የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብልን እንጠይቃለን፡፡
1110Loading...
21
ሰሞኑ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋ በተያያዘ ከመጅሊ በኩል የሚለቀቁት መግለጫዎች በጣም ወሳኝነት አለው እንደ ቀልድ አይታቹ ብቻ አትለፉቱ የበኩላቹን ሀላፊነት ተወጡ
830Loading...
22
በሲዳማ ክልል አንድም ሙስሊም ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ አልተካተተም ተባለ! … በሲዳማ ብሄራዊ ክልል መንግስት ላይ ሙስሊሞች በሀገራዊ ምክክር ተግባር ላይ ምንም አይነት ድርሻ እንዳልተሰጣቸው የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተለያዩ ሥራዎች ሢሠራ ቆይቶ አጀንዳ የመለየት ሥራና ተሳታፊ ልየታ ሥራ ጨርሶ ወደ ውይይት እየገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ይሁንና በሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤት በኩል ለውይይቱ ተሳታፊ ለማቅረብ ያልቻልንና ከሲዳማ ክልል ሙስሊም ሕብረተሰብ የሙስሊሙን አጀንዳ የሚያቀርብ አንድም ሙስሊም ለሀገራዊ ምክክር ያልተሳተፈ በመሆኑ የሲዳማን ሙስሊም ያገለለ ሥራ እንደተሰራ ተገልጿል :: … በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ከሲዳማ አንድም ሙስሊም ለሀገራዊ ምክክር ሂደት ያልተሳተፈ መሆኑን አውቆ ለምክክሩ እንዲያሳትፉን በእናንተ በኩል ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጥያቄ እንዲቀርብልን እየጠየቅን ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሲዳማ ሙስሊም ገለልተኛ የሚሆን ከሆነ ለሀገራዊ ምክክሩ እውቅና የማንሰጥ መሆናችንን በአክብሮት እናሳውቃለን ሲል ለጠቅላይ ምክር ቤቱ አሳውቋል፡፡
840Loading...
23
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ዝግጅት የምሁራን ኮሚቴን አዋቅሮ ሰፋ ያለ ጥናት ሲያስጠና ቆይቶ፤ ለኢትዮጲያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚከተለው መልኩ አቅርቧል።
700Loading...
24
አጀንዳ ②‼ ========= ✍ መጅሊሱ በሁለተኛ ደረጃ ካስመቀመጠው አጀንዳ ውስጥ ሀገራዊና ሕዝባዊ ምልክቶች ምንነት/ አስፈላጊነት አንድን ሀገርና ብሄር ወይንም የተለያዩ የሃይማኖትና የባህል ገፅታዎቹን፣ ስፍራዎችን፣ ታሪክንና ማንነቱን ወክለው ከፍና ጎላ በማለት የሚታዩ፣ የሚደመጡ፣ የሚዳሰሱ ምልክቶች ሁሉን አካታች መሆናቸው የባለቤትነትን ስሜትና የሀገር ፍቅርን የማጎልበት ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ በሀገራችንም ታሪክ ዘርፈ ብዙ ጀግኖች አሉን፡፡ ነገርግን ለእነዚህ ጀግኖች ለተፈለገው ተዘምሮ ላልተፈለገው እምብዛም ቦታ ሳይሰጠው ታልፏል፡፡ 2.1. የሀገር ጀግኖች ሀገራችን የረጅም ዘመን ታሪክ ብቻ ሳይሆን በየዘርፉ የበርካታ ጀግኖች ባለቤትም ናት፤የእነዚህም ጀግኖች ምንጭ የሀገሪቱ ህዝቦችና ሃይማኖቶቻቸው ናቸው፡፡ በጦር ሜዳ ውሎ፣ በጤና፣ በትምህርቱ፣ ትውልድን በማነፅ፣ … ሀገራችንን ከፍ የሚያደርግና ማህበረሰቡም በውስጡ የነበሩ የየዘመናቱ ጀግናዎች ሀገራዊ ጀግና ተደርገው ቢቆጠሩ የሚፈጠርበት የሀገር ኩራትና የራሱ ትውልድ ብሔራዊ ጀግና የመሆን ተነሳሽነትን ይጨምራል፡፡ ሀገራችንም ስለታሪኳ ሲነሳ እንዲሁም የተቀረው ዓለም ስለኢትዮጵያ ሲያስብ በየዘመናቱ የነበሩ የሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች ያፈሯቸውን ብሔራዊ ጀግኖች ሲረዱ ኢትዮጵያ እውነትም በሁሉም ህዝቧ የተገነባችና በጀግኖቿ የታፈረች ሀገር መሆኗን ይረዳሉ፡፡ ስለዚህም በአንድ አካባቢና ባህል ውስጥ ብቻ የታጠረው የሀገር ጀግኖች ሙገሳና በተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች የመዘከር አካሄድ ሀገራችንን በሙሉ ምስሏ ስለማይገልፃት በብሔራዊ ምክክሩ ሊከለስ እንደሚገባ እናምናለን፡፡ በመሆኑም የሀገራችን ጀግኖች ሃይማኖታቸውን ሳያገል የሁሉም ሃይማኖት ተከታይ ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች ስለሆኑ በአንድነት እንዲዘምሩ ቀጣዩ ትውልድም የነርሱን ፈለግ በመከተል በየህይወት ፈርጁ ጀግና እንዲሆኑ ለማስቻል በብሄራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆኖ እንዲያዝልን እንጠይቃለን፡፡ 2.2 ሀገራዊ ታሪካዊ  ክስተቶችና  ቦታዎች የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሰፊ መልከአ ምድራዊ ይዞታዎች ውስጥ በነበሩ የብዙ ህዝቦች የዘመናት መስተጋብር የተፈጠረ ነው፡፡ ሀገር በማፅናት፣ ማህበረሰብን በማነፅና በትምህርት ማእከልነት በማስፋፋት፣ የንግድ ማዕከላት በመሆን፣ የማዕከላዊ መንግሥትና የሱልጣኔት የዋና ከተማና የጦር ሰፈር ሆኖ በማገልገል፣ ወሳኝ የውስጥና የውጭ ስምምነቶች የተፈራረሙባቸው በሀገረመንግስት ግንባታ የተሳተፉ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚታወሱባቸው ሀገራዊ ክስተቶችና ታሪካዊ ቦታዎች አሉ፡፡ ነገርግን በሰነድ የሚታወቁትም ይሁን በብሔራዊ ደረጃ የሚዘከሩት፣ ማስታወሻ የሚቀመጥላቸው፣ ሌጋሲያቸው እንዲቀጥል የሚደረጉት፣ለአሁኑ ትውልድ መማሪያነት የሚተረኩት ስለሀገራችን ሙሉ ምስል የማይሰጡ በሀገራችን የረዥም ዘመን ታሪክ አንፃር የማይመጣጠን ይዘት ያላቸው ሀገራዊ ክስተቶችና ቦታዎች ናቸው፡፡ ስለሆነም ታሪካዊ ክስተቶችና ቦታዎችን አስመልክቶ በብሔራዊ ምክክሩ ህዝባዊ ምክክር እንዲካሄድበት  በአጀንዳነት እንዲያዝ እንጠይቃለን፡፡ 2.3የመንገዶች አሰያያም የመንገዶችና የስፍራዎች ስያሜ በአሁኑና በመጪው ትውልድ ውስጥ ስለሀገርና አካባቢያቸው ዘላቂ ምስል ከሳችና ሀገራዊ ገፅታና መገለጫ እንደሆኑ እንዲረዱ ከሚያደርጉ ክስተቶች ከዋነኞቹ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሰለጠነው ዓለም የመንገድ ስያሜ በህዝበ ውሳኔ እስከመወሰን የሚያደርስ አጀንዳም ጭምር ነው፡፡ በሀገራችን ያሉ የመንገድና የአደባባይ ስያሜዎች ፍፁም ኢትዮጵያን የማይገልፅ፣ የኢትዮጵያን ሙሉ ምስልና ታሪክ የማያሳይ፣ ለትውልዱም ሆነ ለቱሪስት ፍፁም የተዛባ ምስል የሚሰጥ፣ ለከተማነት ስታንዳርድም የማይመጥን አካታችነት የጎደለው አንደኛውን የሚያጎላ ሌላውን የረሳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የረዥም ዘመን ታሪክና ታላላቅ ገድሎች የተፈፀሙባቸው መንገዶች ሳይቀሩ ከታሪኩ ተቃራኒ በሆኑ ስያሜዎች ሲጠሩ ይስተዋላል፡፡ ኢትዮጵያን እና እስልምናን የሚያስተሳስሩ ታላላቅ ታሪኮች እና ስብእናዎች በሌሎች ሀገራት ሳይቀር ተቋምና ጎዳና ሲሰየምላቸው በሀገራችን ግን ይህ ሲሆን አይታይም፡፡ ይህ የሀገር ምንነት ምስል በማህበረሰብ ስነልቦና ላይ ትልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ በመሆኑ በሀገራዊ ምክክሩ መድረክ እንዲቀርብ በአጀንዳነት እንዲያዝልን እንጠይቃለን፡፡   2.4ሕዝባዊ ስፍራዎች እና መጠርያዎች እንዲሁም የከተማ እና መንደሮች ስያሜ ማናቸውም ህዝባዊ ስፍራዎች (Public Sphere) ስያሜዎች እና መጠሪያዎች አካታችና የአንድ ወገን ሃይማኖታዊ መገለጫዎች ከመሆን ነፃ መሆን ነበረባቸው፡፡ ማንኛቸውንም የህዝብ መገልገያ ስፍራዎች (Public Sphere) ፣ አደባባዮች፣ መንገዶች፣ ተቋማት (እንደ ሆስፒታል ፣ ባንኮች ፣ የትምህርት ተቋማት ወዘተ) ሴኩላር ማድረግ አልያም ይህ የማይሆን ከሆነ ማንኛውንም ስያሜ እና አጠራር በሃገሪቱ ያለውን የሃይማኖት ስብጥር ፍትሃዊ በሆነ መንገድ (equitable) የሚያንፀባርቅ እንዲሆን ያስፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በሀገራዊ ምክክሩ ለውይይት እንዲቀርብ በአጀንዳነት እንዲያዝልን እንጠይቃለን፡፡ 2.5ሙዚየሞችና የታሪክ ስፍራዎች ሙዚየሞች በሌላ መጠሪያቸው ‹‹ ትናንሽ ሀገሮች ›› ናቸው፡፡ ለትውልዱና ለውጭ ቱሪስቶች ሀገርን የማስተዋወቂያ ወሳኝ አማራጮች ናቸው፡፡   አንዳንድ ሙዚየሞች የሀገሩን ምስረታታሪክ የሚያሳዩ በሀገር ሀብት የተሰሩ የታሪክ ጥናት፣ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች፣ የረዥም ዘመን ትውስታን የያዙ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ሙዚየሞች የዚያን ሀገር ባህል፣ ሃይማኖት፣ አለባበስ፣ ማምረቻ፣ መገበያያ፣ መማሪያ፣ ስልቶችን የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡ የህዝቦች፣ የቦታና፣ የታሪክ ስያሜዎችና ምስሎችም በጋራ የተገነቡ እሴቶች በመሆናቸው እንደ ሀገር ብዙሃኑን የሚወክል ሆኖ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህና ሌሎች የሙዚየም ይዘቶች ሀገርን ካልወከሉ የሀገሩ ዜጎችም የውጭ ሀገር ጎብኚዎችም ስለሀገሩ የተዛባ መረጃ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ በተለይም ሙዚየሞች በዋነኛነት በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ በመሆኑ መንግስት ከህዝብ በሚሰበሰብ ሀብት የሚያስተዳድራቸው ሙዚየሞች ሀገሪቱን በሙሉ ገፅታ አለመወከሉ ትልቅ ክፍተትን ፈጥሮዋል፡፡ በመሆኑም ሙዚየሞች እና ታሪካዊ ስፍራዎች አካታች እንዲሆኑ በብሔራዊ ምክክሩ ቁልፍ አጀንዳ ተደርጎ እንዲያዝ እንጠይቃለን፡፡
710Loading...
25
ኢትዮጵያ ሃገራችን በሺዎች በሚቆጠሩ ዓመታት የሕዝብና የመንግሥት አደረጃጀት እና አስተዳደር ሂደት ውስጥ ረጅምና ውስብስብ የሆነ ሕብረ ብሔራዊ መስተጋብሮች የነበሩበትን ሂደት አሳልፋለች፡፡ በዚህም ሂደት ሕዝቦች በተለያዩ የአስተዳደራዊ ፣ፖለቲካዊ ፣ ብሔራዊና ፣ ብሔረሰባዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ጭቆናዎች ተካሂደዋል፡፡ እነዚህ መካረሮች ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ተካረው መሳሪያ የሚያስነግቡ ክስተቶችንም ሀገራችን አሳልፋለች፡፡ በኃይማኖት መነሻነት የተለያዩ ችግሮች በአገራችን ሲከሰቱ ይስተዋላሉ፡፡ በተለይም ሙስሊሞች የፀሎት ቦታዎችን እንዳይገነቡ ፣ የቀብር ቦታ የማጣት ባስ ሲልም እስከአሁን ድረስ መስጊዶች የማይገነባባቸው አካባቢዎች መኖር ይስተዋላል፡፡ እንዲሁም ኢስላማዊ አለባበስና ሃይማኖታዊ መገለጫዎች በይፋ እንዳይተገበሩ ይደረጋል፡፡ ሙስሊም ሴት ኢትዮጵያዊያት ሂጃብ ለብሰው የመማር እንዲሁም በትምህርታቸው በሙያቸው በመንግስትና በታላላቅ የግል ተቋማት ሃይማኖታቸው በሚያዛቸው መልኩ ሂጃብ ለብሰው እንዳይሰሩ የቅጥር ክልከላዎች በሰፊው ይስተዋላሉ፡፡ ሀገራዊ ምክክር እና ብሔራዊ መግባባት በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በፊት ጥያቄውን የሚያነሱ አካላትን የሚያሳቅቅ እና በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ ለሀገራችን ዘላቂ የህዝቦች የጋራ አብሮነት ዋስትና ሊሰጥ የሚችለው ሀገራዊ ምክክር በማካሄድ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ መቻል ነው የሚል አቋም የለውጡ መንግስት እንደያዘ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም እነዚህንና ሌሎችንም ሀገራዊ ጉዳዮች በመድረክ ተወያይቶ ለመፍታት ያስችል ዘንድ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2015 መሰረት ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ሆኖ እራሱን የቻለ ነፃ ተቋም ሆኖ ተቋቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች በሙስሊሞች ዙሪያ በሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ለማዘጋጀት እንዲያስችለው ትላልቅ ምሁራንን ያቀፈ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ዝግጅት ኮሚቴ አዋቅሮ ሰፋ ያለ ጥናት አስጠንቷል፡፡ ም/ቤታችን ይህንን ጥናት በማስተባበር የመጨረሻ ውጤት የሆነውን ባለ 9 ዐብይ አጀንዳዎች እና 47 ንዑሳን አጀንዳዎችን ያቀፈ የሙስሊም ኢትዮጵያ ጥያቄዎችን አዘጋጅቷል፡፡ እነዚህኑ አጀንዳዎችን ለኮሚሸኑ እንደሚከተለው አቅርቧል። 1ኛ) የታሪክ ጅማሬን ፣የሀገር ጅማሬን ፣የሀገር አንድነት ጅማሬን፣ የሃይማኖትና የህዝቦች አመጣጥ(ወዘተ) ትርክትን መከለስ፦ የሀገር አመሰራረትና ጅማሬ ታሪክ ህዝቦች የዚያ ሀገር መስራችነትና ባለቤትነት ከመቼ ጀምሮ በምን መልኩ ነው የተጎናፀፉት የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ ባለቤትና መጤ ስያሜም የሚመነጨው ከዚሁ መሰረተ ሀሳብ በመነሳት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ስር ነቀል የትርክት ለውጥ ከሚፈልጉ ጉዳዮች ዋነኛው ይህ የሀገር ጅማሬና አመሰራረት ታሪክ ነው፡፡ በተለያዩ መንገዶች ያሉ ታሪኮችና ትርክቶች ተገቢውን ቦታ ተሰጥቷቸው ሊፈተሹ ይገባል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብም በዚህ ጉዳይ ላይ የህልውና ጥያቄ አለው፡፡ የራሱ ታሪክና ትርክት አለው፡፡ ስለሆነም ሙስሊሙ ማህበረሰብ እኩልነት፤ፍትህን እና ርትዕን መሰረት በማድረግ ታሪኩ የኢትዮጵያ የታሪክ አካል እንዲሆንለት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ የሀገር ምሥረታና ተያያዥ የህዝቦችና የኃይማኖቶች አመጣጥ ታሪክ እንደገና እንዲከለስ ለማስቻል በአጀንዳነት እንዲያዝልን እንጠይቃለን፡፡
710Loading...
26
"ስለ ዙል ሒጃ አስር ቀናቶች ጥቆማ‼️" ________ ✍️በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዛሬ ዕለተ ሐሙስ ነሀሴ 3, 2010 ዓ.ል ነው። በሒጅሪያህ አቆጣጠር ደግሞ ዙል ቂዕዳ 27, 1439 ነው። የዙል ሒጃ ወር ሊገባ ሁለት ወይም ሶስት ቀናቶች ብቻ ይቀራሉ። ስለዚህ ስለነዚህ ቀናቶች አንዳንድ ጥቆማዎችን እንቃኝ። 👉1✔️የዙል ሒጃ የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ታላቅነት✔️ _________ እነዚህ አስርት ቀናቶች አላህ በቁርኣን ላይ የማለባቸው ቀናቶች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፦ "{وَالْفَجْرِ. وَلَيَالٍ عَشْرٍ} [الفجر:1-2]" "በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም።" [አል፡ፈጅር: 1-2] | ታላቁ የቁርኣን ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሢር <<በዐሥር ሌሊቶችም>> በሚለው የተፈለገው የዙል ሒጃን የመጀመሪያ አስርት ቀናቶች ነው በማለት ኢብኑ ዓባስ፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ሙጃሂድና ሌሎችም መናገራቸውን ጠቅሰዋል። {{(ተፍሲር ኢብኑ ከሢር ፥ 4/539-540).}} ከነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከተዘገቡ የሐዲሥ መዛግብቶች ውስጥም የሚከተሉት ይገኙበታል። ( ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر . قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله ، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء ) [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (ቡኻሪ: 2/457) | በተመሳሳይ ገለፃም ከኢብኑ ዓባስ በተወራ ሐዲሥ ስለ ቀናቶቹ ትሩፋትና ታላቅነት ኢማሙ ዳሪሚይ 1/357 በኢስናዳቸው ዘግበዋል። ለተጨማሪ ማብራሪያም ተፍሲር ኢብኑ ከሢር 5/412 ላይ ይመልከቱ። 2✔️"በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሚወደዱ ተግባራቶች" _________ ✔️ሐጅና ዑምራ ✔️ፆም ✔️ ተክቢር፣ ተህሊልና ሌሎች ዚክሮችም ጭምር ✔️ተውበት፣ ከወንጀል መራቅ ✔️መልካም ስራንና ዒባዳን ማብዛት፡ ሶላት ሶደቃ፣ ጅሃድ ✔️የማረጃው ቀንም ኡዱሕያን መተግበርና ሌሎችም 👉كان النبي صلى الله عليه وسلم يصوم تسع #ذي_الحجة ويوم عاشوراء وثلاثة أيام من كل شهر . أول اثنين من الشهر وخميسين " "ነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም #የዙል_ሒጃን ዘጠነኛው ቀን፣ የዓሹራን ቀን፣ ከየወሩ ሶስት ቀናት፣ እንዲሁም በወሩ ውስጥ ሰኞንና ሐሙስን ይፆሙ ነበር።" {{ "ነሳኢይ: 4/205" "ኢማም አልባኒም በሶሒሕ አቡ ዳውድ 2/462 ላይ ዘግበውታል። | 👉( ليشهدوا منافع لهم ويذكروا اسم الله في #أيام_معلومات على ما رزقهم من بهيمة الأنعام ) الحج/28 "ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ #በታወቁ_ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ። " [አል-ሐጅ: 22:28] "أيام_معلومات" <<በታወቁ_ቀኖች>> የሚለውን አገላለፅ ከኢብኑ ዓባስና ኢብኑ ከሢር በተገኘ ዘገባ የዙል ሒጃን አስርት ቀናቶች ለመጠቆም መሆኑ ተዘግቧል። [( الأيام المعلومات : أيام العشر ) ] 👉( ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد ) " ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ ታላቅና አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም። በነርሱም ውስጥ ተክቢር (አላሁ አክበር ማለት)፣ ተህሊልና (ላ ኢላሀ ኢለሏህ ማለት) ተሕሚድን (አልሐምዱ ሊላህ ማለትን) አብዙ።]" [አሕመድ: 7/224] ኢማሙ ጦበራኒይም አል ሙዕጀሙል ከቢር ላይ ዘግበውታል። አላህ ከመልካም ሰሪዎች ያድርገን። ነሀሴ 3, 2010 ዓ.ል
791Loading...
27
የኦሮሚያ መጅሊስ እና የአዲስአበባ መጅሊስ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተገቢውን ውክልና አለማግኘቱን ገለፁ! .. የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለፌደራል መጅሊሱ በፃፉት ደብዳቤ የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ያደረገው የተሳታፊ ልየታ ላይ የሙስሊሙ ተሳትፎ አነሳ በመሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በበቂ ሁኔታ እንዲወከል ይጠይቅልን ሲሉ ለፌደራል መጅሊሱ በፃፉት ደብዳቤ ገልፀዋል። … በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚገባው መጠን እንዲወክል የተነሳ ሲሆን የአዲስ አበባ መጅሊስ እና ኦሮሚያ መጅሊስ ከኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል። …
760Loading...
👆     ለጎዳና ኢፍጣር የተነጠፈ ሸራ እንዳይመስልህ   ለአላህ እንግዶች ለሑጃጆች ሂድማ የተዘጋጁ ትራንስፖርቶች ናቸው። 🤲አላህ እናት ሀገር ሳዑዲ, ህዝቦቿ እና መንግስቷን ጠብቅላት!!
نمایش همه...
1
📣 የ2ዓመት ወንጀል ያሰርዛል!! 🌺 የ"ዐረፋ" ን (የዙል-ሐጅን) 9ነኛ ቀን የፆመ ለሆነ ሰው ትልቅ ምንዳ አለው !!! 🌹ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተረጋግጦ እንደመጣው... 🌴 « (አማኝ) የዐረፋን ቀን ፆም በመፆሙ የተነሳ አላህ የአለፈውን ዓመትና የቀጣዩን ዓመት ወንጀል ይሰርዝለታል። ( ይምርለታል !!! ) » 🤝 ይህም ማለት ፦ በሌላ መረጃ ላይ ግልፅ እንደተደረገው ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅ መስፈርት ማለት ነው !!! 🎙️ ታላቁ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
نمایش همه...
«ጥቆማ፦ ለዒድ ወደ ሰባት ቤት እና ጅማ ተጓዦች እንዲሁም በዛ መንገድ ለምትሄዱ ሁሉ፤ ከሰበታ በታች ባሉ ከተሞች እስከ ወሊሶ መንገድ የፀጥታ ችግር ስላለ ከምሽቱ  12 ሰአት እስከ ጠዋቱ 12 ሰአት መንገድ ዝግ ስለሆነ ከመሸ በደረሱበት ከተማ ስለሚያስቆሟቸው ሰበታ ሲደርሱ 11:00 ከሆነ እዛው ውረድ ብለው ዲማ ፌደራል ኬላ አድረው ጠዋት 12 ሰአት ጉዞዋቸውን መቀጠል ብቸኛው አማራጭ ነው። ከሰበታ ተነስቶ ወሊሶን ለማለፍ በትንሹ  2 ሰአት ስለሚፈልግ እንዲሁመረም ፍተሻ በቅርብ ርቀት ስለሆነ ቀድሞ ማሰብ ያሰፈልጋል። አልፋለሁ ብሎ የገባ ሳያልፍ ሜዳ ላይ ሚሊሻና ፖሊስ የመኪና ቁልፍ ተቀብለውት፣ እዛው ያለ ጥበቃ አድሮ፣ ጠዋት መተው አስፓልት ላይ ቁልፉን በትነውት፣ የራሳችሁን ውሰዱ ብለው ነው የሚሄዱት። ባጠቃላይ ጉዞ የቀን ብቻ ስለሆነ የትራፊኩን ነገር ይታሰብበት ሰምታችኋል ጉራንስና የባድ ወልድ እንዲሁም መሰሎቻቸው!
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ያረብ እኛንም ወፍቀን
نمایش همه...
"ሀገራዊ የምክክር ኮሚሸኑ የፌደራል መጅሊሰ እና የክልል መጅሊሶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች አለመቀበሉ የሀገሪቱ ግማሸ ህዝብ መናቅ ነው"በድር ኢትዮጵያ ... በድር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫውም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሸኑ የፌደራል መጅሊሰ እና የክልል መጅሊሶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች ተቀብሎ ማሰተካከያ ከማድረግ ይልቅ ንቀት በሚመሰል መልኩ በዝምታ ማለፉ የሀገሪቱ ግማሸ ህዝብ ወኪሎች በማይሳተፉበት ሁኔታ ሀገራዊ መግባባት ሰኬታማ ማድረግ እንደማይቻል መረዳት ይኖርባቸዋል"ብሏል። . ህዝበ ሙሰሊሙ በሀገረ መንግሰት ግንባታና በሀገር የኢኮኖሚ ሰርዐት ውሰጥ ታላቅ እሴት የሚጨምር የሀገር ትከሻ ፣ የማህበረሰባዊ ግብረገብ ጌጥ ፍትህ አበርክቶው ያልተፃፈለት ደማቅ ታሪክ አለው፡፡ በኢትዮጵያ አጨቃጫቂ እና አነታራኪ ጉዳዮች ብዙ ቢሆኑም አይፈቱም አይታረሙም ወይም አይሰተካከሉም ብሎ መደምደም አይቻልም ።ለዚህ ደግሞ ግልፅና ፍትሀዊ የሆኑ ህዝባዊ መድረኮች በቂ የመሸጋገሪያ ድልድዮች ናቸው ቸግሩ ያለው እነዚህን መድረኮች በአግባቡ ያለ መጠቀም እና የመጠቀም ጉዳይ ይመሰለናል። ይሁን እንጂ በጋራ ሀገር ለሚኖሩ ዜጎች ሁሉ ሊሰጥ የሚገባው የኢትዮጵያዊነት ውክልናና ዜግነት ሙሰሊሙ ማህበረሰብ ላይ ሲሆን የጥርጣሬ ሙግት መፍጠሩ የትናንቱ እኩይ ድርጊት ዛሬም እየታየ በመሆኑ በእጅጉ ያሳስበናል ። ባልተረጋገጠ _ ተረት ተረትና ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ የሙስሊሙን የውክልና እሴት መጨፍለቅ ወይም ባላወቀ መዝለል ለምን የሚል መፍትሔ ፈላጊ ጥያቄ ያጭራል።ያለ ሲሆን . በሀገረ መንግሰት ምሰረታ ላይ የጋራ አሻራን ለማሳረፍ ያለመቻል ለተጨማሪ አመታት እርሰ በርሰ መባላቱና የተባባሰ ሀገራዊ ቀውሰ ውሰጥ መገባቱ አይቀሬ ነው።ስለዚህ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ይሣካ ዘንድ ተቋሙ ፍትሀዊ ገለልተኛና ለሀገሩ እና ለህዝቡ በታማኝነት መፍትሔ አምጪ ምክክር ይሆን ዘንድ በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሙሰሊሞች ድርጅት በጥብቅ ያሳስባል።ብሏል በድር ኢትዮጵያ በመግለጫው። .. ሙሉ መግለጪውን ከታች አያይዘናል .
نمایش همه...
📮 ዓረፋ በገነንዳ በምሩ ኽሮት ያነወ📮⤵️ በሚል ርዕስ ወቅታዊ የሆነ መደመጥ ያለበት በጉራጊኛ  ቋንቋ የተደረገ ሙሐደራ⤵️ 📍👇ሙሐደራው ላይ ከተወሱ ነጥቦች ውስጥ በከፊሉ⤵️👇 💥አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ቱሩፋትና በልዩ መልኩ ከዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን። 💥 ኡዱሒያ የተደነገገበት ጥበብ {ሂክማ} እና ሁክሙ ምንድነው? 💥ክፍለ ሀገር ላይ ከዒደል ዓድሀ ዓረፋ ጋር በተያያዘ አንዳንድ  የሚፈፀሙ ሙንከራቶች 💥  የዒድ ቀን ለኡዱሒያ(እርድ) የሚዘጋጀው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ... 💥 ሲታረድም ሆነ ከታረደ በኋላ የሚባል ዱዓ ወይም ሌላ ነገር አለን? 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ሲሄዱ የሚያደርጉት የተለየ ዒባዳ አለን? 💥 ዒድ የሚሰገድበት ሰዓት {ጊዜ} እና የሚያበቃበት ሰዓት {ጊዜ}። 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በምን አይነት ሁኔታ ነው መሄድ ያለባቸው? 💥 የዒድ ሰላት አሰጋገድ ሁኔታ በተግባር ምን ይመስላል ተክቢራስ ስንቴ ነው ሚባለው? 📌  ሌሎችንም ነጥቦች የተዳሰሰበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ የሕያ ኢልያስ ቢን አወል አላህ ይጠብቀው።
نمایش همه...
00:15
Video unavailableShow in Telegram
ለኡዹሕያህ መከተ-ል-ሙከረማህ!
نمایش همه...
4.12 MB