cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Lessons by LIFE📋📝

# Spreading motivational lessons of LIFE; # Speakings of many people's; # Useful books and other information and useful thoughts... Join us.... @LivingourLIFE 🙏🙏 please #invite your friends & share

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
290
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#በውስጥህ_ያለውን_አውሬ_ፍታው! በአስራ ዘጠኝ ሃምሳዎቹ በሃርቫርድ ዩንቨርስቲ ውስጥ በአይጦች ላይ የተደረገ ሙከራ ይህን ይመስል ነበር.... ዶክተር ከርት ሬቸተር አይጦችን በውሃ ውስጥ በመጨመር ራሳቸውን ለማዳን ምን ያህል ጊዜ ይፍጨረጨራሉ... ይዋኛሉ የሚለውን አጠኑ። በአማካኝም እነዚህ አይጦች ለ15 ደቂቃዎች ያህል ህይወታቸውን ለማትረፍ ይጥራሉ... ከ15 ደቂቃዎች በኋላ ተስፋ ይቆርጣሉ.... መፍጨርጨራቸውንም ያቆማሉ። ሆኖም ልክ ተስፋ ቆርጠው ሊሰጥሙ ሲሉ፤ ተመራማሪዎቹ አይጦቹን ከውሃ ውስጥ አወጧቸው. .. አደረቋቸውም... ለደቂቃዎችም እረፍት እንዲወስዱ አደረጉ። እንደገናም ለሁለተኛ ጊዜ ውሃ ውስጥ ጨመሯቸው። አስታውስ እነዚህ አይጦች በመጀመርያውን ዙር ራሳቸውን ለማዳን ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነው ሲፍጨረጨሩ የነበሩት.... በሁለተኛው ሙከራ አይጦቹ ህይወታቸውን ለማትረፍ ለምን ያህል ጊዜያት የታገሉ ይመስልሃል? በድጋሜ ለ15 ደቂቃዎች? ለ10 ደቂቃዎች? ለ5 ደቂቃዎች? . . . አይደለም! ለ60 ሰዓታት! ነበር። .... አዎ፤ ድፍን 60 ሰዓታት ያለማቋረጥ ዋኙ። የዚህም ሙከራ መደምደሚያ ይህ ነበር - እነዚህ አይጦች የመዳን ተስፋ እንዳላቸው ሲያውቁ፤ ቀድሞ ከነበራቸው አቅም በላይ ሰውነታቸውን ገፉት.... የማይችሉትንም ቻሉ። በህይወት ላይ ተስፋ መቁረጥ ቀላል ነው። ብዙ ትዳሮች ከጅምራቸው ፈርሰዋል፣ ብዙ እቅዶች ገና በጅምር ቀርተዋል፣ ብዙዎች ሳይታገሉ ተሸንፈዋል..... ነገህ ላይ ብርሃን ካልታየህ፤ ዛሬን ተስፋ ቆርጠህ መስመጥ ትጀምራለህ። ሆኖም ነገ የተሻለ እንደሚሆን ስታምን ራስህን የበለጠ ትገፋዋለህ፤ በሙሉ አቅምህም መታገል ትጀምራለህ። ውስጥህ ያለው አውሬም ይወጣል... መዋኘትህን ቀጥል.... ፍልሚያህን ቀጥል! @LivingourLIFE
نمایش همه...
#አንድ_ሀብታም_ሰው_ነበር። ይህ ሰውዬ በይፋ ለሰው እርዳታ ሲሰጥ ሰው አይቶት አያውቅም። ነገር ግን አንድ ቀን ይህ ሀብታም ሰው ገላዋን በመሸጥ የምትተዳደር ሴት ቤት ሂዶ ብር ሲሰጣት ሰው ያየዋል ። በዚህም ሰዎች በሙሉ በአንድነት ተቹት። <<እንዴት ብር ለዝሙተኛ ሴት ይሰጣል?>> በማለት ተናደዱ በሌላ ቀን ይህ ሀብታም ሰውዬ በመንደሩ ውስጥ በሌብነት ለሚታወቅ ሰው ሄዶ ብር ይሰጠዋል። ሰዎችም ይህን ተመልክተው <<ይህ ሰው ያምዋል! እንዴት ለሌባ ብር ይሰጣል?!>> በማለት የትችት አንደበታቸውን ዘረጉበት። በሌላም ቀን ይህ ሀብታም ሰውዬ ከእርሱ የማይተናነስ ሌላ ሀብታም ሰው ዘንድ በመሄድ.. ለዚያ ሀብታም ሰው እርዳታ ሲሰጥ ሰው ያያል። በዚህ ስራው የተገረሙት የመንደሩ ነዋሪዎች <<ይህ ሰው በርግጥም አብዷል! እንዴት ለሀብታም ሰው ብር ይሰጣል?! >> በማለት ተቹት። ከመሀከላቸውም ሀብታሙን ሰውዬ በሚሰራው ስራ ላይ እንዲያናግሩት ከመካከላቸው ሰዎችን መርጠው ወደ ሀብታሙ ቤት ላኩ። ሰዎቹ ለሀብታሙ ሰው እንዲህ ሲሉ ጥያቄ አቀረቡ <<ሰውን መርዳትህ የተወደደ ነው። ነገር ግን ብር የሚሰጣቸውን መረዳት የሚገባቸውን ሰዎች ያወቅክ አይመስለንም። እንዴት # ለዝሙተኛ # ለሌባና_ሞልቶ_ለተረፈው_ሀብታም_እርዳታ_ትሰጣለህ ? ይህ እብደት ነው>> አሉት። #ሀብታሙ ሰውዬ ለጠየቁት ጥያቄ ማብራሪያ መስጠት ጀመረ ☞ #ለዝሙተኛዋ ሰው የሰጠኋት ያች ሴት ገንዘብ ፍለጋ ነው ለሊት በብርድ ገላዋን እያስመታች ሰውነቷን የምትሸጠው። ያን የምትፈልገውን ገንዘብ ሰጠኋት ከመጥፎ ስራዋ እንድትርቅ። ☞ #ሌባውም የሚሰርቀው ገንዘቡን ፈልጎ ነው። የሚፈልገውን ገንዘብ ሰጠሁት ከስርቆት እንዲቆጠብ። ☞ #ያ_ሀብታም ሰው ብዙ ሀብት አለው። ግን አንድም ቀን እርዳታ ሰጥቶ አያውቅም። እርዳታ ሰጠሁት እርዳታ መስጠት ይለምድ ዘንድ! ይህ ነው እንግዲህ በእናንተ ዘንድ እብድ ያሰኘኝ!>> በማለት ሁሉንም ያስተማረ ምላሽ ሰጣቸው። ይባላል የሰዎችን ስራ አትተች አትንቀፍ ፈጣሪ በነሱ ወንጀል አንተን አይጠይቅህምና ይልቁኑ ለምን እንዳደረጉ ጠይቃቸው ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል። ምክንያቱም #ሁሉን_አዋቂው ፈጣሪ ብቻ ነውና @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
✍ወደ ፈጣሪ ስትቀርብ ከአለም መራቅ አለብህ በ ጊዜአዊ ነገሮች መመካትን ማቆም አለብህ:: ፈጣሪን የምትፈልገው ለአለማዊ ስኬት ብቻ ነው? ገንዘብ እንዲሰጥህ? ዝነኛ እንዲያደርግህ? ትዳርህን እንዲያሰምርልህ? በምድር የሚያስፈልግህን ሁሉ እንዲያሟላ ብቻ ነው? እነዚህ ነገሮችን ከ ፈጣሪ ዘንድ መጠየቅህ ችግር የለውም::እርሱም በመጠየቅህ ቅር አይለውም::ችግሩ የቱንም ያህል አለማዊ ስኬት ብትጎናፀፍ ዘለአለማዊ እረፍት አይሆንህም::እንዲሁም በጊዜ ሂደት ሁሉም ነገር ያስጠላሀል::ከንቱ እንደሆነ ሲገባህ ወደ ጭንቀት እና ትርጉም ወደ ማጣት ይወስድሀል:: ከዛ ይልቅ ፈጣሪን ራሱን ብትፈልግስ? የ ፈጣሪን ህግጋት ጋ በመተግበር ብቻ የሚገኘውን ደስታ እና ሰላም ብታስቀድምስ? በሄድክበት ሁሉ ከምንም ነገር በፊት የምታስቀድመው ቢሆንስ? አሁን ፈጣሪህ በአለም የሚያስፈልግህን አያውቅም? ምን መብላት እና መልበስ እንዳለብህ? ማንን ማግባት እና መቼ መውለድ እንዳለብህ እርሱ ራሱ አይሰጥህም?? አሁን አመለካከትህን ቀይረው::እንደ ብዙ ሰዎች ፈጣሪን ለቁሳዊ ስኬት ብቻ አትፈልገው:: ስታስቀድመው አለም "ሞኝ!" ይበልህ::ማን ሞኝ እንደሆነ ሞት ሲመጣ ይታወቃል::አዳሜ በሚፈርሰው አለም የገነባው ሀብት ሲበሰብስ የማይፈርሰው ፈጣሪ ነፃ ያወጥሀል:: አለማዊ ስኬትህ ምንም ይሁን ምንም የፈጠረህን አመስግን። @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
#የሚቀጥለው_ሳምንት_ትሞታለህ ወደ ጤና ተቋም ብትሄድና ሃኪሙ የአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ እንዳለህ ቢነግርህ ምንድነው የምታደርገው? ሁለት አማራጮች አሉህ፡- አንደኛው ልትሞት እንደሆነ በማሰብ ለስቃይ መዳረግ፣ “ልሞት ነው፣ እዘኑልኝ” እያልክ ለሁሉም ሰው መናገርና የስንብት መተቃቀፍ፡፡ ሌላኛው አማራጭ የሚያስደስቱህን ነገሮች ብቻ በማድረግ እያንዳንዷን ቅፅበት በፌሽታ ማሳለፍ፡፡ የአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ ካለህ ህይወትን አጣጥማት፤ ኑርባት፡፡ “ከዚህ በኋላ ሌሎችን ለማስደሰት ስል የገዛ ህይወቴን አላላሽቅም፤ ከአሁን ወዲያ ሌሎች ስለ እኔ ምን ያስባሉ ብዬ አልብሰከሰክም፤ በአንድ ሳምንት ውስጥ ልሞት ነውና ምንስ ቢያስቡ ምን አስጨነቀኝ? ስለዚህ ራሴን እሆናለሁ፤” ማለት ትችላለህ፡፡ መልዓከ ሞት እያንዳንዷ ቀን የህይወትህ የመጨረሻዋ ቀን እንደሆነችና ነገ የሚባል ቀን እንደሌለ ያስተምርሃል፡፡ እያንዳንዷን ቀን፦ “ነቅቻለሁ የፀሐይንም ብሩህ ጨረሮች አያለሁ፤ እስካሁን ድረስ በህይወት አለሁና ምስጋና እና አክብሮቴን ለፀሐይ፣ ለሁሉም ሰው እና ለሁሉም ነገር እሰጣለሁ፤ ራሴን ለመሆን አንድ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቶኛል” በማለት ጀምር፡፡ @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
✍​​VALENTINE'S DAY የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ??? በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው። የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው። ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት። ይህ የሰይጣን ቀን ነው ይሄን ማውገዝ ይጠበቅብናል። (ሁሉም ቀን የፈጣሪ ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው) ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋጅ ክብረ በአል ነው፡፡ እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው። ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል። ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር። በዚህ ቀን በትንሹ ይህ ይከናወናል 1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗ 2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗ 3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው። Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው እንደኢትዮጵያም ሃገር ቢሆን ተቀባይነት የለውም እና እባካችሁን እራሳችሁን ለሰይጣን ከመሸጥ ተጠንቀቁ ያው አውቃችሁም ላይሆን ስለሚችል ሳታውቁት ልታከብሩ ያሰባችሁ ሰርዙ። share በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ! @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
✍ወደ ፈጣሪ ስትቀርብ ከአለም መራቅ አለብህ በ ጊዜአዊ ነገሮች መመካትን ማቆም አለብህ:: ፈጣሪን የምትፈልገው ለአለማዊ ስኬት ብቻ ነው? ገንዘብ እንዲሰጥህ? ዝነኛ እንዲያደርግህ? ትዳርህን እንዲያሰምርልህ? በምድር የሚያስፈልግህን ሁሉ እንዲያሟላ ብቻ ነው? እነዚህ ነገሮችን ከ ፈጣሪ ዘንድ መጠየቅህ ችግር የለውም::እርሱም በመጠየቅህ ቅር አይለውም::ችግሩ የቱንም ያህል አለማዊ ስኬት ብትጎናፀፍ ዘለአለማዊ እረፍት አይሆንህም::እንዲሁም በጊዜ ሂደት ሁሉም ነገር ያስጠላሀል::ከንቱ እንደሆነ ሲገባህ ወደ ጭንቀት እና ትርጉም ወደ ማጣት ይወስድሀል:: ከዛ ይልቅ ፈጣሪን ራሱን ብትፈልግስ? የ ፈጣሪን ህግጋት ጋ በመተግበር ብቻ የሚገኘውን ደስታ እና ሰላም ብታስቀድምስ? በሄድክበት ሁሉ ከምንም ነገር በፊት የምታስቀድመው ቢሆንስ? አሁን ፈጣሪህ በአለም የሚያስፈልግህን አያውቅም? ምን መብላት እና መልበስ እንዳለብህ? ማንን ማግባት እና መቼ መውለድ እንዳለብህ እርሱ ራሱ አይሰጥህም?? አሁን አመለካከትህን ቀይረው::እንደ ብዙ ሰዎች ፈጣሪን ለቁሳዊ ስኬት ብቻ አትፈልገው:: ስታስቀድመው አለም "ሞኝ!" ይበልህ::ማን ሞኝ እንደሆነ ሞት ሲመጣ ይታወቃል::አዳሜ በሚፈርሰው አለም የገነባው ሀብት ሲበሰብስ የማይፈርሰው ፈጣሪ ነፃ ያወጥሀል:: አለማዊ ስኬትህ ምንም ይሁን ምንም የፈጠረህን አመስግን። @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
ፍጡራን ዘንድ ያለህን ቦታ አትመለከት ይልቁንስ ፈጣሪ ዘንድ ቦታህ የት እንደሆነ ተመልከት። ወንድሜ ማንም እየተነሳ በተንሸዋረረ አእምሮው እየሳለ ቢተችህ ቦታ አትስጥ። ውሻው ይጮሀል ግመሉም ጉዞውን ይቀጥላል እያልክ ወደፊት ቀጥል እንጅ ቦታዬን አሳየዋለሁ ብለህ የቂል ስራ እንዳትሰራ። ይልቁንስ ወደራስህ ተመልከት "ፈጣሪ ዘንድ ያለኝ ቦታስ የት ነው ?" በማለት ጠይቅ። አንተን ዝቅ አድርጎ እርሱ ለመንጠራራት ቢሞክር በተለምዶ "እንቁራሪት ዝሆን አክላለው ብላ ፈንድታ ሞተች" እንደሚባለው ይሰበራል እንጅ ያለ አቅሙ የትም አይደርስ። 👉ፈጣሪ ያላቀውን የማንም ትችት ዝቅ አያደርገውም 👉ፈጣሪ ያዋረደውንም የማንም ሙገሳ ከፍ አያደርገውም። @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...
✍ደስተኛ መሆን ሳይንቲስቶች ጥናት አደረጉ፡፡ሰዎች ሲደሰቱ ሰውነታቸው ውስጥ ምን እንደሚካሄድ መረመሩ፡፡አንድ #ሴራቶኒን የተባለ ኬሚካል ወይም ሆርሞን አለ፡፡በሰዎች ሰውነት ውስጥ እሱ ሲመነጭ ሰዎች በደስታ ያብዳሉ፡፡በጥሩ ስሜት ይፈነጥዛሉ፡፡ሴራቶኒን የደሰታው ወይም የመልካም ስሜቱ ሆርሞን ይባላል፡፡ ይህ ሆርሞን ሙዳችሁን ይጨምራል፣ የማህበራዊ ኑሮ ጠባያችሁን ያሻሽላል፣ የትውስታችሁን አቅም ያበረታል፣ የምግብ ፍላጎትና የአፈጫጨት ጥርዓታችሁን ያስተካክላል፣ ከስንፈተ ወሲብ በሽታም ይታደጋችኋል፡፡ሴራቶኒን ሳይንቲስቶች ያልደረሱበት ሌላ ብዙ ጥቅሞችም አሉት፡፡ የምንደሰተው ሴራቶኒን በሰውነታችን ሲመነጭ ነው፡፡ታዲያ ሴራቶኒን በሰውነታችን እንዲመነጭ የሚያደርገው ነገርስ ምንድን ነው?ይህ የሳይንቲስቶችም ጥያቄ ነበር፡፡ ለሰዎች ደግ መሆን የሴራቶኒን ሆርሞንን በሰውነታችን ከሚያመነጩ ነገሮች መካከል ዋነኛው እንደሆነ ሳይንቲስቶች ደርሰውበታል፡፡የሚገርመው ደግ ለሆነው ሰው ብቻ ሳይሆን ደግነቱ ለተደረገለት ሰውም ይህ የደስታ ሆርሞን በሰውነቱ ይመነጫል፡፡ከዚህም በላይ የሚገርመው የደግነቱን ድርጊት ከውጭ ሆነው በሚመለከቱ ሰዎች ውስጥም ይህ የደስታ ኬሚካል መመንጨቱ ነው፡፡ ደግ ስትሆኑ ከራሳችሁ አልፋችሁ ለብዙ ሰዎች የደስታ ምንጭ ትሆናላችሁ፡፡በአእምሯችሁ የሚንጫጫውን ራስ ወዳድ ማንነታችሁን አሸንፉት፡፡ሰዎችን የሚጠላውን የውሸት ማንነታችሁን ቅበሩት ፤ ግደሉት፡፡ "ደግነት ደካማነት ነው!" ሲላችሁ አትስሙት፡፡ደግነት ሐይል ነው፡፡በዛ ላይ ደግነት ለራስ ነው፡፡ካላመናችሁ ሞክራችሁ እዩት፡፡ደግ በመሆን የሚገኘውን የልብ ስሜት ደግ በመሆን እዩት፡፡በውስጣችሁ የማያቋርጥ የደስታ ዝናብ ይዘንባል፡፡ይህ ደስታ ደግሞ መብል፣ መጠጥ፣ ጭፍራ፣ ፋሽን መከተል ወይም በኢንስታግራም ብዙ ላይክ ማግኘት እንደሚገኘው ደስታ አይደለም፡፡ይህ ደስታ የሰዎችን መረዳት ሁሉ የሚያልፈው የፈጣሪ ደስታ ነው፡፡እውነተኛ ሰላም፣ ነጻነትና እረፍት የሚሰጠው ደግነት ነው፡፡ ስትከፉ ለሆነ ሰው የሆነ ነገር አድርጉ፡፡ያላችሁ ነገር ገንዘብ ሆነ ፣ ሳቅ ሆነ ፣ ጊዜ ሆነ፣ ከልብ ማድመጥ ሆነ፣ እውቀት ሆነ፣ ፍቅር ሆነ ብቻ ደግ ሆናችሁ ለሰዎች ስጡ፡፡በምትኩ ግን ደግ ከሆናችሁላችሁ ሰዎች ምንም አትጠብቁ፡፡even እነዛ ሰዎች መጥፎ ቢሆኑላችሁም አትገረሙ ወይም ደግነታችሁን አታቁሙ፡፡ደግ ስትሆኑ ምላሹን መጠበቅ ያለባችሁ ከ ፈጣሪ ነው፡፡እሱ ደግነታችሁን አይቶ ባላሰባችሁበት መንገድ ይከፍላችኋል፡፡ @LivingourLIFE ON LESSONS BY LIFE
نمایش همه...