Amhara community United Kingdom
رفتن به کانال در Telegram
Build and maintain a strong Amhara community that provide support among each other during good or bad times.To organize social events, trips and workshops that encourages social activities to prevent isolation or loneliness from Amhara community.
نمایش بیشتر216
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ሲባል አገዛዙን በህብረት መታገል ተገቢ እና አስፈላጊ በመሆኑ በያለህበት ትግሉን ፖለቲካዊ እና የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ባሻገር የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ይህን ዘር አጥፊ አገዛዝ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል በባለቤትነት እንድትሳተፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
፫) ጥሪ ለዲያስፖራው
የአማራ ዲያስፖራም ሆነ ህዝባዊው መላው የኢትዮጵያ ዲያስፓራ በሀገር ቤት የሚደረገውን የህልውና ትግል ለመደገፍ ከፍተኛ ጥረት ስታደርጉ መቆየታችሁ ይታወቃል። በዚህም ለትግሉ ትልቅ አቅም ሆናችሁ ቆይታችኋል። ትግሉ ወሳኝ እና አዲስ ምዕራፍ ለመሻገር በሚንደረደርበት በዚህ ወቅት ከቀደመው ድጋፍ የበለጠ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። ከዚህም አንጻር ድርጅታችን ባስቀመጣችው የድጋፍ መስመሮች በመግባት እና በመደረጃት የሚጠበቅባችሁን እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
፬) ጥሪ ለሚዲያ ሰወች
በአማራ ትግል ውስጥ ሚዲያ ትልቅ አቅም በመሆን መረጃ በማድረስ እና ህዝባዊ ንቅናቄ በማነሳሳት አግዟል። ይህ የትግላችን አንዱ መስክ እንደመሆኑ በተደራጀ አኳኀን የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ ሊሰራ ይገባል። ከዚህ አኳያ በቀጠናው ያለው አደረጃጀት አንድነት ከማብሰር ባሻገር አንድነትን የሚያጠናክር ስራዎች በመስራት የበኩላችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን፤ በቀጠናችን ያለውን ልዩ የትግል ባህርይ ያገናዘበ ዘገባዎች እንዲቀርቡም ለማሳሰብ እንወዳለን።
እንዲሁም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ተከታዩን ምስጋና ያቀርባል።
፩) ምስጋና ለድርጅታችን:
እናት ድርጅታችን አፋብን ሁላችንን አሰባስቦ የቀጠናውን ትግል አንድ የሚያደርግ ስራ በመስራት ረገድ ለተወጣው አይተኬ ሚና ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን። በዚህ ስራ ረጅም ጉዞ ተጉዘው በአካል ተገኝተው በማወያየት በትጋት አብረውን ለነበሩት እና በተሳካ መልኩ ግዳጃቸውን ለፈጸሙት የድርጅታችን የፖሊት ቢሮ አባል በልዩ መልኩ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
፪) ምስጋና ለትግሉ ደጋፊዎች:-
የትግላችን ደጋፊዎች ተቀራርበን እንድንነጋገር እና እንድንወያይ በጎ ግፊት ስታደርጉ በመቆየታችሁ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
በመጨረሻም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ቀጥሎ የተቀመጠውን ቃል ይገባል።
እኛ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ ስራ አስፈጻሚ አባላት በቀጣናችን ሲደረግ በቆየው ትግል የተገኙ ድሎችን ለማሳደግ፣ ፈተናዎችንም በጽናት ታግሎ ዕዙን ለቀጣዩ የስራ ሀላፊነት ብቁ ሆኖ እንዲመጣ ለማስቻል በከፍተኛ ጓዳዊ ሞራል በተለይም ቅንነትን፣ የድርጅትን ህገ ደንብ እና ርዕዮተ አለማዊ መስመር ገዢነትን የሚያሰፍን፣ በአጠቃላይ ድርጅታችን አፋብን ያስቀመጠውን ዓላማ የሚያሳካ እና በሂደቱም ሆነ በውጤቱ 'የድርጅትን' አሸናፊነት በማረጋገጥ ለአዲስ የትግል ምዕራፍ የምስራች እንዲሆን፤ የተጣለብንን አደራ ፦ በእውተኛነት፣ በፍትሀዊነት፣ ሀቅ ላይ በተመሠረተ ምክንያታዊነት ለመፈጸም በህዝባችን፣ በጓዶቻችን፣ በተሰውት ሰማዕታት እና በምናምነው እውነተኛ እና ጻድቅ አምላክ ስም ቃል እንገባለን።
በአፋብን የወለጋ-ቢዛሞ አንሻ ሰይድ ዕዝ
ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ የተሰጠ የአንድነት መግለጫ
ለዘመናት የጅምላ ሰቆቃ እና የዘር ማጽዳት ቤተ ሙከራ ሆኖ የባጀው የወለጋ-ቢዛሞ አማራ ራሱን ለመከላከል በተለያዬ ጊዜ እና ሁኔታ ተጋድሎዎች ሲያደርግ ቆይቷል።
የአማራ ህዝብ የመንግስት እና የሀገር ባለቤትነትን መቀማቱ አማራ ክልል ከሚባለው ውጭ ላለው አማራ ማህበረሰብ ከፍተኛ የህልውና ስጋት እንዳመጠበት በተጨባጭ የታዬ ሀቅ ነው። በተለይ በቢዛሞ/ወለጋ ቀጠና ያለው ማህበረሰብ አማራ መሆንን ተከልክሎ ከመኖር ባሻገር ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ከአስተዳደራዊ በደል ጀምሮ ሰፊ የማንነት ጥቃት ተፈጽሞበታል። አማራ ነኝ እና አማራ አይደለህም በሚለው ተቃርኖ ውስጥ በስጋት ሲኖር የቆየው ማህበረሰብ በተለይ ከብልጽግና አገዛዝ መምጣት በኋላ መንግስታዊ እውቅና ባለው ይፋዊ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ተገድለዋል፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ተለያዬ አካባቢ ተፈናቅለዋል፣ ተበትነዋል። ይህን የዘር ማጥፋት አዋጅ መከላከል የህልውና ጉዳይ በመሆኑም የቢዛሞ አማራ ተደራጅቶ ራስን የመከላከል እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።
ይህ እንቅስቃሴ የፋኖነት እና የአማራ ትግል በሀሳብ እና የአላማ አንድነት በማግኘቱ የፖለቲካ መስመር እየጠራ መምጣትን ተከትሎ ደግሞ ትግልን የሚመጥን አደረጃጀት በመፍጠር ከሌላው የአማራ ወገን ጋር ህልውናን መታደግ እና ጠላትን የመመከት አላማን ይዞ እየታገለ ይገኛል። በዚህም ህዝባዊ አቅሞችን በማሰባሰብ እና መሬት የተከለ ትግል በማድረግ ሰፋ ያለ አካባቢ ላይ በመንሳቀስ እና የማደራጀት ስራ በመሰራቱ የጠላትን የማጥፋት አቅም ማዳከም እና በጠላት ላይ ሰፊ ጉዳት ማድረስ ችሏል።
ይሁንና ፈተናው ከምቹ ሁኔታዎች የሚልቅ በመሆኑ በሁለት አደረጃጀቶች የታቀፈውን ሀይል ወደ አንድ በማምጣት ብሎም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አደረጃጀት መዋቅር ውስጥ በመግባት የጋራ ህዝባዊ አቅም በመፍጠር የተቀናጀ ትግል ማድረግ ግዴታ ነው።
እስካሁን ድረስ በአካባቢው የነበረው አደረጃጀት ሁሉንም የአካባቢው የፋኖ ኃይል ማቀፍ ባለመቻሉ ምክንያት የአደረጃጀት ስራችን ሣይጠናቀቅ ቢቆይም እነሆ ዛሬ ድርጅታችን አፋብን ባደረገልን እገዛ እና ክትትል የአማራ ፋኖ ቢዛሞ ቀጠና አንሻ ሰይድ እዝ እና የአማራ ፋኖ በወለጋ በሚል አደረጃጀት ስር የቆዬን ታጋዮች በሁለታችንም የስራ አስፈፃሚ ሙሉ ኮሚቴ ቀናትን በወሰደ የአካል ውይይት በአፋብን የወለጋ-ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝን መስርተናል፤ የእዙ የስራ አስፈፃሚ አባላትንም:-
1. አርበኛ ንጉሴ ዋለልኝ- ሰብሳቢ
2. አርበኛ አደም ተፈራ -ምክትል ሰብሳቢ
3. አርበኛ ሐብታም ጥላሁን -ወታደራዊ አዛዥ
4. አርበኛ አለፈ ሽባባዉ -ምክትል ወታደራዊ አዛዥ
5. አርበኛ ዳዊት አማረ -የሕ/ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
6. አርበኛ ተስፋዬ አቻሜ - የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ
7. አርበኛ ወንድ-ወሰን ተገኑ -የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
8)አርበኛ ምኒበል እንዳለ -አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
8. አርበኛ ክንዱ ስጦታው -ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
9. አርበኛ ክንዱ አቸነፍ -ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
10. አርበኛ ጥላሁን ሰብስቤ -ጤና መምሪያ
11. አርበኛ ታለልኝ ደርሶልኝ -ፅ/ቤት ኃላፊ
12. አርበኛ ሮቤል ወ/ምካኤል -የፋይናንስ እና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
13. አርበኛ አህመድ አበባው - ሎጅስቲክ መምሪያ ኃላፊ
14. አርበኛ አንዳርጌ በለጠ -መካናይዝድ ጦር መምሪያ ኃላፊ
15. ••••መረጃ እና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ
16. አርበኛ እንዳለው ተስፋዬ -ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
17. አርበኛ ዘመን መላክ -ወታደራዊ መረጃ እና መገናኛ ኃላፊ
18. አርበኛ አስናቀው ቸርነት -ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
19. አርበኛ አዲሱ አላምረው -ሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
20. አርበኛ አማረ በለጠ-ህግ እና ስነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ
21. አርበኛ በረከት አይናዬ -ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
22. አርበኛ ካሳሁን ወርቁ -የሰው ኃብት መምሪያ ኃላፊ
23. አርበኛ ሙላት ከፌ -ኢንዶክሪኔሽን መምሪያ ኃላፊ
24. አርበኛ ደረጀ ወርቄ -ሐብት አፈላላጊ መምሪያ ኃላፊ
25. አርበኛ አስማማው ግርሙ-ጥናት እና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
26. አርበኛ አይሸሽም አሞኘ -ወታደራዊ ጥናት እና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
27. አርበኝት ወርቅሰው ጌጤ - የሴቶች ጉዳይ
በማድረግ የስራ ስምሪት እና ምደባ ሰጥተናል።
እንኳን ደስ አላችሁ !
ትግላችን የአማራን ህልውና የመታደግ እና እንደ አማራ በምንኖርበት አካባቢ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የመተዳደር ወይም ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የመጎናጸፍ ነው። ይህ የአማራ የብሔርተኝነት ርዕዮተ አለማዊ የትግል መስመር የአማራ ህዝብ ለዘመናት የተነፈገውን መብት የቦታ ልዩነት ሳይኖረው እንዲከበር የማረጋገጥ ነው። ይህ መብት መከበር እኛ በምንኖርበት አካባቢ ከሚኖረው ወንድም የኦሮሞ ህዝብ እና ከሌላው ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መሠረት ሲሆን የመብት መከበር ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥም ብቸኛው መፍትሔ እንደሆነ እናምናለን። ከዚህም በመነሳት ለህዝባዊ ህልውና መረጋገጥ እና መብቶች መከበር ከኦሮሞ ወንድሞቻችን እና ሌሎች ጎረቤት ህዝቦች ጋር የጋራ መግባባት እየፈጠርን አገዛዙን ከሚታገሉ የኦሮሞ ኃይሎች ጋርም በትብብር በመስራት ቀድሞ የነበሩ ተቃርኖዎች እየፈታን፣ የነበሩ መልካም ግንኙነቶችንም እያጠናከርን መሄድ የትግላችን አካል ነው።
በመሆኑም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ተከታዩን ጥሪ ያቀርባል።
፩) ጥሪ ለሰራዊታችን
የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በቀጠናችን አንድ ትግል አንድ አደረጃጀት መፈጠሩን እያበሰርን በአማራዊ ወንድማማችነት እና በትግል ጓዳዊነት መንፈስ የጀመርነውን የህልውና ትግል የፖለቲካ መስመሩን በማጽናት እና የሚሰጡ ግዳጆችን የአንድነት አቅምን ተጠቅመን በበለጠ ጽናት እንድንፈጽም ለማሳሰብ እንወዳለን። ከዚህ በተጨማሪም በድርጅታችን ካሉ ሌሎች ዕዞች ጋር በሚኖሩ የጋራ ግዶጆች የሚጠየቀውን በቁርጠኝነት እንድትፈጽሙ በድጋሚ እናሳስባለን።
፪) ጥሪ ለአማራ ህዝብ
የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የመጥፋት አደጋ ለመዳን እና ጠላትን ከመመከት ባሻገር ጨርሶ ለማስወገድ ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይ መድረሳችን ይታወቃል። ይህ ምዕራፍ ከቀደሙት የትግል ወቅቶች የበለጠ መራር ትግል የምናደርግበትም ነው። በቀጠናችን በዛሬው ዕለት የተጠናቀቀው አደረጃጀት ደግሞ በነባሩ አቅም ላይ ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ አቅም እንደሚሆን ሙሉ እምነት ያለን ሲሆን ይህን ህዝባዊ ጦርነት በህዝባዊ ውጊያ መክተን ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል በባለቤትነት እንደ እስከዛሬው የሚጠበቀውን ለማድረግ በየአደረጃጀቱ እንድትተጋ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
፫) ጥሪ ለኢትዮጵያዊያን
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራ ህዝብ የተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሦስት አመታት ሰፊ ህዝባዊ ትግል እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የአማራ የህልውና አደጋ የራሱ ልዩ ባህርያት ቢኖሩትም ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ ተመሳሳይ ቅርጽ ያለው የህልውና ስጋት ውስጥ እንዳለ እሙን ነው። ይህ ጸረ ህዝብ የብልጽግና አገዛዙ በተርታ ህዝቦችን ለማጥፋት የጀመረውን ጦርነት በጋራ መመከት ደግሞ የሁሉም ህዝቦች ተፈጥሯዊ ግዴታ እንደሆነ እናምናለን። ስለዚህም የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል መደገፍ ብቻ ሳይሆን ለራስም ህልውና
የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) በሳተላይት ቴሌቪዥን ምስረታ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!
በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ተቋማት፣ የሕዝባችንን የህልውና ትግል፣ ሰብዓዊ መብትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማስከበር የአማራ ሚዲያ ካውንስልን (AMC) በማቋቋም ላለፉት ሁለት አመታት በጋራ ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመሥረት ባለፉት ሁለት ወራት በጠንካራ ዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንገጽ በታላቅ ኩራት ነው።
ይህ ካውንስል ከሁለት ዓመት በፊት ሲመሠረት በተበታተነ መልኩ የሚደረጉ የሚዲያ ሥራዎችን ወደ አንድ ወጥና ጠንካራ የጋራ አጀንዳ (Unified Narrative) ለማምጣት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎችንና ተቋማትን አቅም በማቀናጀት የሕዝብን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የመረጃ አፈና ለመስበር፣ በጨለማው ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ እና ድምፅ ለሌላቸው ኢትዮጲያዊያን ድምፅ ለመሆን፣ በዲጂታልና በሳተላይት አማራጮች አማካኝነት እውነቱን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ የተቋቋመ የሙያና የትግል መድረክ ይሆናል።
ካውንስሉ ካቀዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች መካከል ቀዳሚው፣ የኢንተርኔት መቆራረጥና ሳንሱር የማያግደው፣ ኢንተርኔት በማይደርሰበትና አገዛዙ ኢንተርኔት ለዘጋበት ሕዝብና አካባቢ ለመድረስ፣ በመላው ኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሚሆን "የሕዝብ ድምፅ" የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ መመሥረት ነው። ይህ ጣቢያ የአባል ሚዲያዎችን ሰፊ የሕዝብ መሠረትና አቅም በማቀናጀት፣ የሕዝባችንን የታሪክ፣ የባህል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍላጎቶች የሚወክል ቀዳሚ ተቋም ይሆናል።
ይህ ታላቅ ተቋም በምስረታ ላይ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት አብረውን እንዲቆሙና እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፦
• ለሚዲያ ባለሙያዎችና ተቋማት፦ በካውንስሉ ውስጥ ያልታቀፋችሁ ሚዲያዎች የካውንስሉን አቅም በማጠናከርና የጋራ አጀንዳን በመገንባት ሂደት ውስጥ በሙያችሁ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
• በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እየተሳተፋችሁ ላላችሁ የህልውና ታጋዮች አብረን እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን።
• ለሲቪል ማህበረሰብና ሙያ ማህበራት፦ በዚህ አመራር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ የጣቢያውን ገለልተኝነትና ሕዝባዊነት እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን።
• ለባለሀብቶችና ለደጋፊዎች፦ ይህንን የመረጃ አፈና የሚሰብር የሳተላይት ፕሮጀክት ከሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የታሪክ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ጥሪ እናቀርባለን።
• ለዲያስፖራው ማህበረሰብ፦ የትግሉ የጀርባ አጥንት በመሆን የካውንስሉን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና የፋይናንስ ዘላቂነት፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲኖረው በምትችሉት ሁሉ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።
የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ለፍትሕና ለህልውና የሚደረገውን ትግል በጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ታንጾ ለመዘገብና እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ለማድረስ ቆርጦ ተነስቷል። ይህ የመጀመሪያው እርምጃችን ሲሆን፣ በቀጣይ በዝርዝር የምናሳውቃቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች ታላቅ ተስፋ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠርም።
"የጋራ ድምፅ ለፍትሕና ለእውነት!"
የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC)
ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
