ETHIO CRYPTO ™
رفتن به کانال در Telegram
Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟
نمایش بیشتر3 571
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-8230 روز
آرشیو پست ها
3 571
የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪዎች ብሔራዊ የትስስር ምክር ቤት ተመስርቷል።
https://t.me/student_text
3 571
+1
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 5/2016 ዓም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አምስት አመታት በጤና መረጃ ስርዓት ላይ በሠራው ሥራ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር የላቀ አፈፃፀም ተሸላሚ ሆኗል።
የሽልማቱ ስነስርዓት በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው የጤና መረጃ ሳምንት አጀማመር ፕሮግራም ላይ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክዘኩዩቲቭ ዳይሬክተር አለሙ ጣሚሶ (ተባ. ፕሮፌሰር) ከጤና ሚንስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እጅ ተቀብለዋል::
የጤና መረጃ ሥርዓት ላይ የተሰራው ሥራ እንደሀገር ከጤና ሚንስቴር አምስቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ የትኩረት ዘርፎች አንዱ ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ ሞዴል ከሆኑት ሰባት ወረዳዎች ሁለቱን ማለትም ከሲዳማ ክልል የሸበዲኖ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳንኩራ ወረዳዎችን ሞዴል በማድረግ በሠራው ሥራ እና አዳዲስ ምርምሮችን በመሥራት የላቀ አፈፃፀምና የልዩ አፈፃፀም ሽልማት አግኝቷል::
https://t.me/student_text
3 571
+6
የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስራ ሰሃት መግቢይ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ሱፕርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዩ አሰፋ ትምህርትና ለውጥ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በማጠቃለያ መልዕክታቸው የስራ ውጤታማነት ሊመዘገብ የሚችለውና የታለመውን አላማ ከግብ ማድረስ የሚቻለው ተከታታይነት ያለው ለውጥ እንዲመጣ በትኩረት በመስራትና በጋራ በመሰናሰል በመስራት በመሆኑ ሰራተኛው ለዚህ ትኩረት መስጠት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
https://t.me/student_text
3 571
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ ሆነ፣
ግንቦት 04/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለመስጠት የሚያስችል ንቅናቄ ይፋ ሆኗል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ከክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ባደርጉት ውይይት ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተማሪዎች መውደቅ ምክንያት በትምህርት ሚኒስቴር ጥናት መጠናቱን እና ጥናቱን ተከትሎ በቀረቡት ምክረ-ሃሳቦች መሠረት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀትና ለማብቃት የሚያስችል ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት የሚያስችል ንቅናቄ መጀምሩን ገልጸዋል።
የማጠናከሪያ ትምህርቱ ዋና አላማ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት በማሳደግ ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በንቅናቄና ዘላቂነት ባለው መልኩ የራሱ ሥርዓት በማበጀት መተግባር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
በተለይም የማጠናከሪያ ትምህርት መርሃ-ግብሩ በየደረጃው ያለው የትምህርት ዘርፉ አመራር በጥብቅ ዲስፕሊን እየመራ ተማሪዎች ያሉባቸውን የመማር ውጤት ክፍተት በመለየት፤ በክፍተቱ መሠረት የጎደላቸውን ለይቶ በመሙላት ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሥራውን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎቹ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ሃይል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ተቋቁሞ ተናቦ መሰራት እንዳለበትና ለዚህም ያሉ አቅሞችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አስረድተዋል።
ለተፈታኝ ተማሪዎችም የሙከራ ፈተናዎችን በመስጠት ውጤቶችን በመተንተን ክፍተት በሚታይባቸው የትምህርት አይነቶች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ድጋፍ ማድረግ ይገባል ተብሏል።
በመጨረሻም ይህን ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ንቅናቄ የአካባቢውን አቅም ማለትም በጎ ፈቃደኛ የሆኑ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶች ባለሙያዎችን፣ ወዘተ ጭምር እንዲሳተፉ በማድረግ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል፡፡
https://t.me/student_text
3 571
+5
በቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት አተገባበርና በትምህርት መርጃ መሳሪያ አዘገጃጀት ዙሪያ ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም
መርሀ ግብሩ በቢሮው የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን በስልጠናው የሁሉም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ህጻናት በአካል፣አዕምሮና በስነ ልቦና ዳብረው ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁ የሚሆኑበት የትምህርት ደረጃ እንደመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከትምህርቱ አተገባበር ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደተግባር እንዲገቡ ለማስቻል ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ዳይሬክተሯ አክለውም በአዲሱ ስርአተ ትምህርት በተቀመጠው መሰረት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴ ተግባራዊ የሚሆንበት እንደመሆኑ ከአተገባበሩ ጋር በተገናኘ በቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው ከማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ አዘገጃጀትና አተገባበር ጋር በተገናኘም በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።
https://t.me/student_text
3 571
ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና በከተማ አቀፍ ደረጃ ግንቦት 1 ቀን የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የሚሰጠውን ከተማ አቀፍ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ምዘናው መንግስት ለትምህርት ጥራትና መሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው አካላት በመሆናቸው ምዘና መደረጉ ተገቢና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዋነኛው ሂደት ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ፈተናውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው ምዘናው የመምህራንን የሙያ ብቃት ለማሳደግና እውቅና ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሩን በበቂ ስነ-ልቦና ለማስተማርና ለመምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የምዘናውን አካሄድ ውጤታማ ለማድረግም የትምህርት አመራሩና የክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች ለተፈታኞች የሚሰጡ ቅድመ ምዘና ገለጻዎች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው 1:30 ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
https://t.me/student_text
3 571
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት የእውቅና ጥያቄ አቅርበው መስፈርቱን ለአሟሉ የምርምር ጆርናሎች እውቅና ሰጥቷል። ዝርዝሩ በሚከተለው ደብዳቤ ተገልጿል።
https://t.me/student_text
3 571
+1
የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች እየተከበረ ነው
በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት÷ በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፥ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል።
https://t.me/student_text
