cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ብሥራት ሚዲያ

ይህ ቻናል የተከፈተው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መረጃ የምንለዋወጥበት በዓይነቱ፣ በይዘቱ ለየት ያለ ቻናል በይፋ ከፍቻለሁ። በዚህ ቻናል👇👇👇 ✔ ፎቶዎችን ✔ቪዲዮችን ✔መፅሐፍትዎችን ✔ታሪኮችን ታገኙበታላችሁ።👇👇 Http://Telegram.me/Bisrat_Midea Http://tiktok/@bisratman20 https://youtube.com/@BisratTube19?si=3HfoFy4qaLDuC77k

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
341
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
+130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሐምሌ 7 --  በዓለ አጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ሥላሴ የሚለው ሠለሰ - ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት (ሦስትነት ) ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም / አንድነት ሦስትነት ተብሎ ይተረጎማል ። ሦስትነታቸው በስም ፣በአካል፣ በግብር አንድነታቸው በባሕርይ ፣ በህልውና በመለኮት ፣ በሥልጣን በፈቃድ ነው ። ሀ,የስም ሦስትነት - አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ነው ማቴ 28 ፣ 19 ለ, የአካል ሦስትነት - ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው። አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው ። ገጽ ፊት ነው መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር  ያለ ነው አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ መዝ 33 ፥ 15, መዝ 118+73 ኢሳይያስም '' ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ '' ብሏል (ኢሳ 66 + 1 ) ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ። ዘፍ 18+ 1-4, ማቴ 3+16 ሐ, የግብር ሦስትነት፦ የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው ። አብን ወላዲ ፣ ወልድን ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስንም ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደለም አንድ ናቸው ። እንዲህም ማለት ሦስት አማልክት ማለት አይደለም ። አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ የአንድነታቸውስ ነገር እንደምን ነው ? ቢሉ በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ አንድ ናቸው የህልውና አንድነታቸው በአብ ልቡናነት ወልድ መንፈስ ቅዱስም ያስቡበታል፤ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስም ይናገሩበታል ። በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ ወልድም ህልዋን ናቸው  ይተነፍሱበታል ። ቅድስት ሥላሴ የሚል የሴት ቅጽል የተቀጸለላቸው ባሕርያቸውን አይቶ ነው ። ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንዲገኝ ይህም ዓለም ከሥላሴ  ባሕርይ ተገኝቷልና ፤ እናት ለልጅዋ የሚያሻውን አስባ እንድታቀርብለት ሥላሴም ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈለገውን ሁሉ አስቀድመው ያዘጋጁለታል። ማቴ 6 +32 አንድም እናት ልጅዋ ቢያስቀይማት ፈጽማ እንዳትጥለው ሥላሴም ሰርቀው አመንዝረው ቢበድሏቸው ንስሐ ገብተው ቀኖና ይዘው ቢለምኗቸው ይቅር ይላሉና ። ማቴ 6 +32 ይህን የሥላሴ አንድነት ሦስትነት ካልተማሩ ሥርየተ ኃጢአት  ተስፋ መንግሥተ ሰማያት አይገኝምና ፤ ይህንንም ምሥጢር ያፋለሰ  ለየራሳቸው ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ አላቸው ዘጠኝ አማልከት ናቸው ። እንዳለው እንደ ዮሐንስ ተዐቃቢ ፍዳን ይቀበላልና ፈጽሞ ጠንቅቆ መረዳት ይገባል ። ሥላሴ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ካለ መኖር ወደ መኖር አምጥተው የፈጠሩ ድካም የማይሰማቸው በሞት የማይለወጡ ገዥ ፈጣሪ ናቸው ። ሥላሴ እንደዛሬ ሁሉ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ባሕርያቸው ባሕርያቸውን ሲያመሰግን ይኖር ነበር  ኋላ ግን ሰውና መላእክትን ስማቸውን ለመቀደስ ክብራቸውን ለመውረስ ፈጠሩ። ሌላውን ገን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ፈጥረውታል። የበዓሉ ታሪክ አብርሃም ቤቱን ከተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን እንግድነት ሲቀበል ይኖር ነበር ። ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ራሱን ገምሶ አጥንቱን ከስክሶ ከመንገድ ቆይቶ እንግዶቹን ወዴት ትሄዳለችሁ ? ይላቸዋል ። ርቦን ሊያበላን ጠምቶን ሊያጠጣን ከአብርሃም ዘንድ ይሉታል ፤ የወትሮው አብርሃም መሰላችሁን እኔም እንደ እናንተ ርቦኝ ያበላኛል ጠምቶኝ ያጠጣኛል ብዬ ብሄድ ራሴን ገምሶ አጥንቴን ከስክሶ ሰደደኝ ይላቸዋል ፤ እያዘኑ በመጡበት ይመለሳሉ ። እንዲህ አድርጎ 3 ቀን ሙሉ እንግዳ ከለከለበት እሱም ያለምስክር ግብር አላገባም ብሎ ሳይመገብ ቆይቷል ። በሦስተኛው ቀን በቀትር ከድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ ሥላሴ በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ተቀምጠው ታዪት። ( ዘፍ 13 + 18 ) '' ገሀሡ አጋዕዝትየ ቤተ ገብርክሙ አብርሃም '' ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፉ አላቸው ። ደክሞናልና እዘለን አሉት ። አንዱን አዝሎ ቢገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ ገብተው ተገኝተዋል ። እሱም ሦስት እንደሆኑ አውቆ ሣራን 3 መስፈሪያ ዱቄት ወስደሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ ጋግሪው አላት ፤ ጋግራ አቀረበች ፤ እርሱም ወይፈን አርዶላቸው ወተት እርጎ ጨምሮ አቅርቦላቸው ተመግበዋል / አቅረበ ሎሙ ሐሊበ ዕቋነ ወዕጉለ ላሕም / እንዲል ። መብላቸው ግን አሳት ቅቤ በላ እንደ ማለት ነው ። ይህንንም ሲያጠይቅ አርዶ አወራርዶ ያቀረበው ወይፈን ተነሥቶ '' ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ '' ብሎ አመስግኗል ። '' ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤ ዘበኃይልክሙ ሐይወ ላሕም ፤ ሥላሴ ክቡራነ ስም '' እንዳለ ደራሲ። በሚሄዱም ጊዜ ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ቃል አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ ፤ የዛሬ ዓመት እንደዛሬ ወዳንተ እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ብሎ ለጊዜው ልደተ ይስሐቅን ፍጻሜው ግን ሰው ሆኖ የሚያድነው መሆኑን ነግሮታል ። ዘፍ 18 + 1- 14              ምንጭ  ፦ መዝገበ ታሪክ 1 & 2 https://t.me/Bisrat_Midea
نمایش همه...
#ሐምሌ_7 #ቅድስት_ሥላሴ ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት) https://t.me/Bisrat_Midea
نمایش همه...
ብሥራት ሚዲያ

ይህ ቻናል የተከፈተው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መረጃ የምንለዋወጥበት በዓይነቱ፣ በይዘቱ ለየት ያለ ቻናል በይፋ ከፍቻለሁ። በዚህ ቻናል👇👇👇 ✔ ፎቶዎችን ✔ቪዲዮችን ✔መፅሐፍትዎችን ✔ታሪኮችን ታገኙበታላችሁ።👇👇 Http://Telegram.me/Bisrat_Midea Http://tiktok/@bisratman20

https://youtube.com/@BisratTube19?si=3HfoFy4qaLDuC77k

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ሥላሴ 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ሥርዓተ ነግሥ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet ነግሥ ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ: ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ: ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ: ኃይልየ ሥላሴ ወፀወንየ ሥላሴ: በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ። @EOTCmahlet ዚቅ አምላክነሰ ኃይልነ አምላክነሰ ፀወንነ: አምላከ አሕዛብ ዕብነ ወዕፀ ኪነት ኢኮነ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክአ ሚካኤል ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ: ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ: ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ: ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ: አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡ @EOTCmahlet ዚቅ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር: ዘይሴባሕ እምትጉሃን: ወይትቄደስ እምቅዱሳን፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ ተፈሥሒ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ: ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ #ሥላሴ: እንዘ እዘብጥ ከበሮ ቅድመ አዕላፈ ኤፍሬም ወምናሴ: ለተአምርኪ እነግር ውዳሴ: ማርያም እኅቱ ለሙሴ። @EOTCmahlet ወረብ ተፈሥሂ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ ተፈሥሂ ማርያም/፪/ ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ #ሥላሴ ዘጸገይኪ ለነ/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ይሴብሑኪ ወይገንዩ ለስምኪ: ዘእምሥሉስ ቅዱስ ቃል ኃደረ ላዕሌኪ: ወትሰመዪ ማኅደረ መለኮት። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክአ ሥላሴ ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላዌያተ: ለረኪበ ስሙ ኅቡእ አመ ወጠንኩ ተምኔተ: እምግብርክሙ ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ: መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚኣክሙ ገጻተ: እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ: አአትብ ወእትነሣእ: በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ: ሠለስተ አሥማተ ነሢእየ እትመረጎዝ: እመኒ ወደቁ እትነሣእ: ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት: እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet አመላለስ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ/፪/ ሃሌ ሃሌ ሉያ/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለሕጽንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ: ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ: እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ: ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ: ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ በአፍዓኒ አንትሙ: ወበውሣጤኒ አንትሙ: በገዳምኒ አንትሙ: ብርሃኑ ለኢያሱ አንትሙ ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ በአፍአኒ አንትሙ ወበውሣጤኒ አንትሙ/፪/ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለኢያሱ ንጉሠ ነገሥት/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለኅሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ: እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ: ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ: ፫ተ ዕደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ኀይምት ርእየ: ወለ፩ዱ ነገሮ ረሰየ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ወጽአ እምድረ ካራን: ወቦአ ብሔረ ከነዓን: ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር: እንበይነዝ ጽድቀ ኮኖ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ ወጽአ እምድረ ካራን ወቦአ ዝየ ረከብነአ/፪/ ተአመነ "አብርሃም"/፪/በእግዚአብሔር/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለሐቌክሙ ዘቅናተ ኂሩት ቅናቱ: ሊሉያነ ፆታ ሥላሴ እምአምላከ በለዓም ከንቱ: ኀበ መስፈርትክሙ ጽድቅ እስመ ያበጽሕ ትእምርቱ: ተደለዉ ከመ ይሑሩ ምሕዋረ ዕለታት ሠለስቱ: በዓለ መሥዋዕት አብርሃም ወይስሐቅ መሥዋዕቱ።  @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ: አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ: እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ: ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል: አብርሃምኒ ርእዮ በውስተ ምሥዋዕ: ሕዝቅኤልኒ ርእዮ በልዑላን: ሙሴኒ ርእዮ በዓምደ ደመና: በነደ እሳት: ፈያታዊኒ ርእዮ በዲበ ዕፀ መስቀል አምነ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ/፪/ አውረደ ሎቱ "ቤዛሁ በግዐ"/፪//፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ሥላሴ ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ: መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ስብዐተ: ህየንተ ፩ዱ #ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምእተ: ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ: ወዲበ ፲ቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም: ስብሐት ለወልድ ለዘአክበራ ለማርያም: ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኲሉ ዓለም/፪/ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet መልክዐ ተክለሃይማኖት ሰላም ለኅሊናከ ዘኮነ መምለኬ: ሥላሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ: ተክለሃይማኖት ቄርሎስ ዘላፌ ረሲዓን እለ እውጣኬ: ባርከኒ አባ ለወልድከ ዝኬ: እስመ ልማዱ ለመምህር ቡራኬ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ አንትሙሰ ከመ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ: ወለክህነቱ ቅዱስ: ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ ለዘጸውዓክሙ: አባ ባርከኒ ተክለሃይማኖት አባ: ከመ ባረኮ አብርሃም ለይስሐቅ ወልዱ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ አንትሙሰ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ/፪/ ወለክህነቱ ቅዱስ ታዕርጉ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ምልጣን በእምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም። @EOTCmahlet @EOTCmahlet አመላለስ አማን በአማን/፬/መንግሥተ ሥላሴ አማን በአማን/፬/ መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም/፬/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ በእምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም ደብረ ብርሃን/፪/ እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet እስመ ለዓለም ዘሰንበት መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ ፈኑ ሣህለከ ወምህረትከ ዘአንተ ታርኁ ክረምተ በጸጋከ ወትሴሲ እመዝገብከ ስብሐት ለከ ወዓቢይ ኃይልከ ዘሠራዕከ ሰንበተ ለሰብአ ዕረፍተ ዘሠርዓ ለአብርሃም ወመሐለ ለይስሐቅ ወአቀመ ሰምዓ ለያዕቆብ፤ ንስእለከ ወናስተበቁዓከ፤እስመ ኵሉ ዘሥጋ ያንቀዓዱ ኀቤከ 👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet   #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያድርጉ
نمایش همه...
ሁሉም ሰው ተሳትፎ ሊያደርግበት የሚገባ መጠይቅ ስለዚህ ዘመን ምን ያስባሉ?🧨
نمایش همه...
نمایش همه...
በመልዕልተ አድባራት ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት አንቀጸ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርትቤት ስር የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች በዓለማዊ ህይወታቸው ያላቸው የአለባበስ ስርዓት ምን ይመስላል? በሚል ርዕስ የሚሠራ ጥናታዊ ጽሑፍ

የተከበራችሁ የዚህ መጠይቅ መላሾች ሠላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን ይህ መጠይቅ የተነደፈው የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች በዓለማዊ ህይወታቸው ያላቸው የአለባበስ ስርዓት ምን ይመስላል? በሚል ርዕስ ላይ በመልዕልተ አድባራት ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት አንቀጸ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርትቤት የራብዓይ ኮርስ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ነው። ስለ አለባበስ መነጋገር ያስፈለገን እውነተኛ ክርስቲያን በአነጋገሩ፣ በአረማመዱ፣ በአመጋገቡ፣ በአለባበሱ፣ ብቻ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆን ስላለበት ነው። በዚህ መጠይቅ ላይ አለባበስ የሚለው ቃል ክርስቲያናዊ አለባበስ እንደሆነ እንዲሁም አገልጋይ የሚለው ደግሞ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮችን እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን። በመሆኑም እርስዎም ለዚህ ጥናት ግብዓት ይሆን ዘንድ ይህን መጠይቅ እንዲሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን ። የሰጡን ምላሽ ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀና ለዚህ ጥናት ብቻ በግብአትነት የሚያገለግል በመሆኑ በሙሉ ነፃነትና ታማኝነት እንዲሞሉ በአክብሮት እናሳስባለን። ጊዜዎትን ሰጥተው በአግባቡ መጠይቁን እንደሚሞሉ ተስፋ በማድረግና በማመን ይህ ጥናት በእርስዎ ምላሽ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። ለትብብርዎ አስቀድመን በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን። ምናልባት ጥያቄና ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦች ካሉ በሞባይል ቁጥር 0994495268 (ዲን. ብስራት ቦጌ) ወይም 0951068366 (ቤተልሔም ተፈራ) ወይም 0917315958(ዘሪሁን ወልዴ) ይደውሉልን ወይም በTelegram መልዕክት ያስቀምጡልን። አጠቃላይ መመሪያ •ስሞትን መጻፍ አይጠበቅቦትም እንዲሁም የጥያቄ ምላሾች ይህንን ምልክት ( ●)ባለው ክፍት ቦታ በማድረግ መልስዎን ይግለጹ .ዝርዝር ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው ቦታዎች…

Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ ። ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ ። እንዘ ትረውጽ ጥቡዐ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልድ ። አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ ። ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ ። ሰላም ለጳውሎስ ሃይማኖተ ክርስቶስ ዘአግሀደ ። እስከ አቊሰልዎ በሰይፍ ወመተርዎ ክሣዶ ። ከመ ያግብእ ሕዝበ ሀየንተ ቀዳሚ ሰደደ ። በላዕለ አብዳን ተመሰለ አብዶ ። ወለአይሁድኒ ኮኖሙ አይሁዶ ።
نمایش همه...
👍 1 1
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል። በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል። ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5 የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል። በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል። በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል። በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል። ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል። አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9 (#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ) https://t.me/Bisrat_Midea
نمایش همه...
​​እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ #ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6) ¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! ¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ¤ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ¤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል #እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: ¤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: ¤ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ:: ¤እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና #ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ¤ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ:: ¤ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም:: ¤ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና:: ¤ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና:: ¤ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው:: ¤"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው:: ሔሮድስን ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6) ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: #ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት:: ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች:: << አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ (የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች) >> 1.ነቢይ 2.ሐዋርያ 3.ሰማዕት 4.ጻድቅ 5.ካሕን 6.ባሕታዊ/ገዳማዊ 7.መጥምቀ መለኮት 8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ) 9.ድንግል 10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ) 11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ) 12.መምሕር ወመገሥጽ 13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ) ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! https://t.me/Bisrat_Midea
نمایش همه...
نمایش همه...
ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር ዘያበቁል ሣዕረ ውስተ አድባር || ዲን. ለዓለም ብርሃኑ || #ምስባክ

ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር ዘያበቁል ሣዕረ ውስተ አድባር || ዲን. ለዓለም ብርሃኑ || #ምስባክ #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #ወርኃ_ክረምት #ክረምት #ethiopian #ethiopia #mesbak #viral #ethiopiaorthodox #youtube #foryou

ይህን ያውቁ ኖሯል❓ አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን ፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ) ፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ) ፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች። ፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል) ፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል ፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል) ፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል) ፭..ነቢዩ እዝራ ፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል) ፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል) ፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል) ፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል) ፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል) ፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል) ፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል) ፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል) ፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል) በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን! የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን💒♥ https://t.me/Bisrat_Midea
نمایش همه...
ብሥራት ሚዲያ

ይህ ቻናል የተከፈተው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መረጃ የምንለዋወጥበት በዓይነቱ፣ በይዘቱ ለየት ያለ ቻናል በይፋ ከፍቻለሁ። በዚህ ቻናል👇👇👇 ✔ ፎቶዎችን ✔ቪዲዮችን ✔መፅሐፍትዎችን ✔ታሪኮችን ታገኙበታላችሁ።👇👇 Http://Telegram.me/Bisrat_Midea Http://tiktok/@bisratman20

https://youtube.com/@BisratTube19?si=3HfoFy4qaLDuC77k

👍 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.