cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ባል እና ሚስት❤👰👳

Fikir❤ .......... he loves death .... &she loves live . ........... then he live for her she die for he😢😢 love is. this. 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFdlSAuUbHgeFtx0Lg @balenamist @balenamist Don`t leive 👹 b\c like it😎

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
413
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ድሮ ሃይስኩል ስንማር ረመዳን በመጣ ቁጥር ክርስቲያን የት/ቤት ጓደኞቻችን ሁለት ቀን ልፁምልህ ሶስት ቀን እያሉ አብረውን ይፆሙ ነበር😍 ይህን ማድረግ የማይችሉ ልጆች ደግሞ ፆመኛ ፊት ምግብ አይበላም በሚል እኛ ፊት ምግብ አይበሉም ዉሃም አይጠጡ ነበር። የእነዚያ ውድ ክርስቲያን ጓደኞቻችንን ውለታ ዛሬ መክፈል ፈለኩ፣ ከዚህ የባሰ ጊዜ ስለማይመጣና ሌላ ሌላውን ነገር ባላውቀውም ይህን በቤተክርስቲያን የታወጀውን የ3 ቀን ፆም አብሬያችሁ በመፆም ውለታ እክፍላለሁ። ያልፋል! enezin yabzalin
نمایش همه...
አምላኬ ሆይ ተስፋ ያደረግሁት ከእኔ ቢርቅም አንተ ግን በአማኑኤል ስምህ ከእኔ ጋር ሁን ። ያከበርኩት ቢያዋርደኝ አንተ ግን በወርቀ ደምህ መገዛቴን ንገረኝ ። አለኝታ ያልኩት ደጁን ቢዘጋብኝም አንተ ግን የጠፋው ልጅ አባት ሁነኝ ። አስታዋሼ ያልኩት ፍጹም ቢረሳኝም አንተ ግን የማትረሳ እምዬ ነህ ። የእኔ ያልኩት እንደ በረዶ ቢሟሟም አንተ ግን የማታልቅ ሀብቴ ነህ ። ይጠግነኛል ያልኩት ቢሰብረኝም አንተ ግን ሐኪሜ ነህ ። ያድነኛል ያልኩት ቍስሌን ቢያድሰውም አንተ ግን አዲስ ራእይ የምትሰጠኝ ነህ ። ይመጣል ያልኩት ቢቀርም አንተ ግን ቀጥረህ የማትቀር ነህ ። ያልታየውን አየሁልህ የሚል ሸንጋይ ቢገጥመኝም አንተ ግን ዓይኔ ነህ ። ላይደርስልኝ ቆይ መጣሁ እያለ ቢያዘናጋኝ አንተ ግን ደመናን ጠቅሰህ ፣ ባሕር ተራምደህ ትመጣለህ ። ለካባ ያሰብኩት ቀሚሴን ቢወስደውም አንተ ግን የጽድቅ ሸማዬ ነህ ። ይሰውረኛል ያልኩት ቢያጋልጠኝ አንተ ግን የመማጸኛ ከተማዬ ነህ ። ይደርስልኛል ያልኩት እልም ቢልም አንተ ግን በረከቴ ነህ ። ለትርፍ ክፍያ ስጠብቅ ደመወዜን ባጣም አንተ ግን መኖሪያዬ ነህ ። በግራዬ ሰዎች ቢከዱኝ አንተ ግን በቀኜ ወዳጆች ታመጣልኛለህ ። ቀኑን ሳልገምት ቢደርስብኝም አንተ ግን ቀድመህ አዘጋጅተህልኛል ። ጉልበቴ የከዳኝ ቀን አንተ ግን ተነጥፈህልኛል ። ልነሣ ስል አልጋ ላይ ስቀር አንተ ግን አስታመኸኛል ። የተንተራስኩት ክንድ ሲዝል አንተ ግን ችለኸኛል ። ይወደኛል ያልሁት ቢጠላኝም አንተ ግን ውዴ ሆነህልኛል ። ያድነኛል ያልኩት ገዳይ ቢሆንም አንተ ግን መርዙን አርክሰህልኛል ። መኖሬን ስጠራጠር አንተ ግን ብዙ ቀን ጨምረህልኛል ። ይሾመኛል ያልኩት ቢያዋርደኝም አንተ ክርስቶስ አክብረኸኛል ። ናልኝ ያልኩት ቢቀርም አንተ ግን ሳትለየኝ ፈጥነህ ደርሰህልኛል ። የከበቡኝ ሲበተኑ አንተ ግን መላእክትን አዝዘህልኛል ። ይለምኑልኛል ያልኋቸው ቢዘርፉኝ አንተ ግን ቅዱሳንን ሰጥተኸኛል ። ያዝንልኛል ብዬ ቍስሌን ያሳየሁት ጥዝጣዜ ቢጨምርብኝ አንተ ግን ዳሰኸኛል ። አለቀ ያልኩት ገና እንጭጭ ቢሆንም አንተ ግን የዳርቻዬ አዛዥ ነህ ። ተስፋዬ ሆይ በእኔ አቆጣጠር ዘገየህ ። ወይ ቶሎ ና ወይ ልቤን ትዕግሥት ሙላ ። ውስጤን ሳስበው ገና በዓለም ለመኖር እከጅላለሁ ። በአፌ ማራናታ ፣ በልቤ ቆይ ጌታ እላለሁ ። ገልብጠህ ስማኝ ፣ እንደ ልቤ ሳይሆን እንደ አፌ አድርግልኝ ። እንደ እኔ ሳይሆን እንደ አንተ ይቅር በለኝ ። አለው ያሉኝን ደግ ነገር እባክህ ጨምረህ ስጠኝ ። አላመኑኝም ብዬ በሰው ከማዝን አምንሃለሁ ብዬ ባንተ መደሰት አብዛልኝ ። ወዳጅ ሆይ በቃልህ ያልተማርን በሬሳ አንማርም ። እኛን ለማስተማር ዘመኑን ብታስጨንቅም ፣ ስትለቀን ያው ነን ። እባክህ ዝም ብለህ ወዳንተ መልሰን ። አሳዳጁን ጳውሎስን ገንዘብ ያደረግህ እኛንም ለክብርህ ለመኖር አብቃን ። እናቱን እንደ ናፈቀ ልጅ መምጫ መምጫህን እያየን እንኑር ። ቀኑ ሳያልቅብኝ ምስጋናዬን ላቅርብልህ ። ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋና ይገባል ። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ። 💚 Orthodox 💚 💛  Orthodox💛 ❤️  Orthodox❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
نمایش همه...
አቤቱ እንደ ሀገር ለኖርኩብህ፣ እንደ ወገን ለኮራሁብህ፣ እንደ ወዳጅ ለተጽናናሁብህ፣ እንደ ትምህርት ቤት ለተማርኩብህ፣ እንደ ዘይት ለለመለምኩብህ፣ እንደ ብርሃን ለታየሁብህ፣ እንደ ጥላ ለአረፍኩብህ የሕይወቴ ሽታ  አምላኬ የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒዓለም ሆይ ከአንተ ውጪ የማምነው የለምና የሀገሬን የቤተክርስቲያኔን የሕዝቤን ነገር አደራ 💚 @Orthodox💚 💛  Orthodox 💛 ❤️  Orthodox❤
نمایش همه...
ተወልደን የተጠመቅንባት(የሥላሴ ልጅነትን ያገኘንባት)፣ በምግባር ታንጸን ያደግንባት፣ በወግ በማዕረግ ጋብቻችንን የፈጸምንባት፣ ወልደን የምናስጠምቅባት! ስንጨነቅ የምንጽናናባት፣ ስንሞትም ማረፊያ የምትሆነን ቤተክርስቲያን ጥቃት ያመናል። #አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ
نمایش همه...
●ባለ ቆብ ሚስማሮች ! ዛሬ መድኃኔ ዓለም ነው::ቀኑም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነገረ ቅንዋት ይነገርበታል።ቅንዋት መድኃኔ ዓለም ለሁላችን ቤዛ ሊሆን የተቸነከረባቸው ችንካሮች(ሚስማሮች) ናቸው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መድኃኔዓለምን መስላ እርሱን ተከትላ በእነዚህ ባለቆብ ችንካሮች ተቸንክራለች። ችንካሮቹ መነቀላቸው አይቀርም። ለጊዜው ግን ሕመሙ ከባድ ነው።ሚስማሮቹ ባለቆብ ናቸውና። የቤተ ክርስቲያንን እግሮቿን ቸንክረው እያደሟት ነው። ለቤተ ክርስቲያን ዛሬ ስቅለት ነው። ስቅለት ደግሞ የትንሣኤ ጎረቤት ነው።ለንጊኖስም የዘረኝነት ዘገሩን ነጥቆ ጎኗን እየወጋት ነው። ከባለቆብ ሚስማሮች ጋር።ዛሬ የፍርድ ፀሐይ ጨልሟል። ስቅለት ነዋ! ነገ ግን በእርግጥ ትሣኤ አለ። ትንሣኤ ብቻ አይደለም እርገትም አለ !! ባለቆብ ሚስማሮች
نمایش همه...
ቢገርፉን ቢገፉን እሰከ ቀራኒዮ እስከ ጎለጎታ ሞት አያስፈራንም ሞቶ ማሸነፍን አስተምሮን ጌታ
نمایش همه...
አስቸኳይ! ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በስናይፐር የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል። የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል። ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል።
نمایش همه...
ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ክቡርነትዎ ስለ ሰሞነኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፈተና የሰጡትን ማብራሪያ ሰማሁት። ከተሾሙበት ዘመን ጀምሮ ያደረጉልንን መልካም ነገሮች ዘርዝረዋል። የውስጥና የውጭ ሲኖዶስ የሚል መከፋፈልን ማስቀረትዎ፣ በአቡዳቢ መቅደስ እንዲኖረን ማድረግዎ በቤተ ክርስቲያን ለዘለዓለም የማይረሳ በጎ ሥራዎ ነው። ነገር ግን የተወረሱ ሕንጻዎችን መመለስ፣ መሬት መስጠት የመሳሰሉ ነገሮች መንግስት ለሚያስተዳድረው ሕዝብ ሊያደርገው የሚችል እንጅ በየቀኑ አመስግኑኝ የሚያስብል ውለታ አደለም። ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ገደለ የሠሩትን ሕንጻ ወረሰ።  የተገደሉ ፓትርያርካችንን መመለስ ባይችሉም ጊዜው ሲደርስ ሕንጻችንን መልሰውልናል። የራሳችንን እንጅ ሠርቶ የሰጠን መንግሥት የለም። ፍርድ መጠንቀቅዎን ብናደንቅም ምጽዋት ተደርጎ እንደ ተሰጠን አድርጎ በየቀኑ ማነሣሣት ግን አስፈላጊ ነው  ብየ አላምንም። ይልቁንም ወሮ በላ ጳጳሳት እየወረሩኝ ነው መንግሥት ሕግ ያስከብርልኝ ብላ በጠየቀች ቤተ ክርስቲያን ፊት ቀርቦ እንዲህ ያለ ንግግር ማድረግ ፍትሕ እየጠበቅን የነበርን እኛን አሳዝኖናል። ተርቦ የሚለምንን ሰው ከዚህ በፊት ስለ ወሰደው እንጀራ እየተረኩ ማዘግየት ችግረኛውን ሰው በረሀብም በነገርም እንዲጎዳ ማድረግ ነው። ከጀ መሩት አይቀር ጉዳታችንንም ቢናገሩልን ኖሮ ደስ ይለን ነበር። => በሃይማኖታቸው ምክንያት የታረዱ ምዕመናን በሐረር፣ በጅማ፣ በወለጋ፣ በአርሲና በሌሎችም ስንት ናቸው? => ታቦት አጅበው የሚሄዱ ወጣቶች በመንግሥት ወታደር አልተገደሉብንም? ታቦቱን ወደ መቅደሱ ማስገባት ተከልክለን የመንግሥት ታጣቂዎች መንገድ ዘግተውብን ከጎዳና አላደርንም? => አርቲስቱ ሲገደል፣ ጃዋር ሲከበብ ለውጥ ተደርገው የታረዱ ምዕመናንስ? እናቶች ሆዳቸው ተቀደደ፤ ጡታቸው ተቆረጠ፤ ወንዶቹ ብልታቸው ተሰለበ፤ ሰው በእሳት ነደደ። => የመስቀል ማክበሪያ ቦታችንን በጴንጤ ሹማንቶችዎ ተቀምተን ሳናከብር የቀረንባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን አያውቁም? የኩራዝን ጭሱን ይከላከሉታል፤ መብራትነቱን ይጠቀሙበታል ብለን እያለፍነው ነው እንጅ ብልፅግና ከጠቀመን ይልቅ የጎዳን ብዙ ነው። በተጨማሪም፦ • የትግራይ ክልል ጳጳሳት በጦርነቱ ወቅት ያወጁትን ዐዋጅ ማነጻፀሪያ አድርገው ማንሣትዎ ተገቢ አደለም። ያ በጦርነት ጊዜ የቀረበ ጥያቄ ነው። ብስጭትና ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ነበሩ። በጦር ተከቦ እየተዋከበ ለነበረ ሕዝብ መግለጫ ማውጣት ነበረብን? ሰልፍ መጥራት ነበረብን? • በዚያውስ ላይ የትግራይ ጳጳሳት ጥያቄ ጦርነቱን አውግዙልን ሕዝብ ተጎዳብን የሚል ነው እንጅ የብሔር፣ የዘር ጥያቄ አልነበረም። ያሁኑ ግን የፖለቲካ እንጅ የሃይማኖት መልክ የሌለው ጥያቄ ነው። ቤተ ክርስቲያን አድርጋው የማታውቀውን ከኔ ወገን ተሹአሚ አንሱአል ይጨመርልኝ የሚል ነው። አባቶቻችን ያቆዩን ጥያቄ አባት አንሶናል ይጨመርልን የሚል ነው መልካሙ ጥያቄ ይሄ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ለብሔር ብሔረ ሰቦች የሚከፋፈሉ መናብርት የሉትም። እንኳን ኢትዮጵያውያኑን ይቅርና ከውጭ የመጡትንም አባት አድርጋ የምትቀበል ቤተ ክርስቲያን ናት። ግልጽ ወረራ በዘመንዎ እየተፈጸመብን መሆኑን ባይሰሙኝም ልነግርዎ እፈልጋለሁ። መንግሥትዎ ጣልቃ ያልገባ ለማስመሰል የሄዱበትን መንገ ድ ሳየው ታዘብሁዎ! - ምነው የጅማ ፖሊስ ለቤተክርስቲያን ቡራኬ የተጋበዙ ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ከተማችን ማንም እንዳይመጣ ብሎ በስልክ መከልከሉን፣ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ከብዙ መንገላታት በሁአላ ከከተማ አስወጥቶ መስደዱን አልሰሙም? -  የጅማ ሀገረ ስብከት ተንቀሳቃሽ ንብረቱን እንዳያንቀሳቅስ መታገዱንስ? አያውቁም? ውጉዛኑ በታጣቂ ታጅበው ወለጋ መግባታቸውንስ አላዩም? ወታደር ቁልፍ ሰብሮ ሲያስገባቸው መረጃ አልደረሰዎትም? ጣልቃ መግባቱንማ አልፈው መንግሥታዊ ኃይማኖት ለመመሥረት እየሠሩ ያሉ ሰዎች ባጠገብዎ አሉ። ሕግን ላስተማረ ሕጋዊ ተቅዋም አቤቱታ መልስ ለመስጠት የኦሮምያ ክልል ፕሬዝደንት ያሳዩት ንቀት እንዳለ ሆኖ ለሕግ አፍራሾች ወታደር ይመደብላቸዋል፤ ለሕጋዊው ሲኖዶስ በር ይዘጋበታል። አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ካቢኔዎች እንዳይረዱን ጩኸታችንን እንዳይሰሙን የሰጡአቸው ማስፈራሪያ የዛሬው መግለጫ ዋና ዓላማ ይመስለኛል። ደኅና አድርገው አሸማቀቁልን! በሌላ ጎን የተሰለፉ  ባለ ሥልጣናትንም እኔ አለሁ በርቱ አሉልን። ስማችንን ለመጥራት ተጸይፎን የሰነበተ የመንግሥት ሚዲያ ሁሉ እየደጋገመ ማስጠንቀቂያዎትን አሰማን። አንቱ ይተዉ እንጅ ለግፍም ልክ አለው!
نمایش همه...
መልካም የብርሃነ ልደት በዓል ይሁንልን ዛሬ አባታችን አዳም ከክርስቶስ ጋር አብሮ ተወለደ። የክርስቶስ ልደት ሕይወቱ ነውና አብሮ ተወለደ። አዳም አባታችን ከሲኦል ማሕፀን ተወለደ ፤ ምንም እንኳ ሞት እና ትንሳዔውን ቢጠብቅም ዛሬ በቤተልሔም በከብቶች ግርግም አብሮ ልደቱን አከበረ ፤ የሕይወቱ ተሥፋ ተፈጽሟልና። ጌታዬ ሆይ እኔስ መቼ ይሆን የሕይወቴ ተሥፋ የሚፈጸመው 😔 ጌታዬ ዛሬ ልደትህ ነው ስለዚህ አላዝንም ፤ ግን በኃጢአት ሕይወት መመላለሱ መሮኛል። ከሁሉም ነገር ያንተ መንገድ ይሻለኛል፤ አውቃለሁ ብዙ እየነገርከኝ ቶሎ እረሳለሁ የቃላትህ መዐዛ ሕይወትን የሚያለመልም የጨለመውን የሚያሳይ ቢሆንም በግብዝነት እርቄሀለው። እኔ ብሸሽህም ትከተለኛለህ። ከዚህ በኋላ ግን  በመረረ የኃጢአት ዓለም ውስጥ መኖር አልፈልግም ፤ ከኃጢአት ጽንስ ውስጥም ከአንተ ጋር መወለድ ፈለግሁ። ስለዚህ ጌታዬ ሆይ ምሕረት ቸርነትህ ፤ ፍቅር አንድነትህ አይለየኝ። ዛሬ ልደቴ ነው😇፤ የእናንተስ? ፈጣሪ በምሕረቱ ከኃጢአት ዓለም ያውጣን ፤ ልምድ ከሆነብን በሥጋችን ላይ ከሰለጠነብን  ከኃጢያት ሱስ ያላቅቀን። ለንስሐ ሕይወት ለሥጋ ወደሙ ያብቃን።
نمایش همه...
ሰው ሁነህ መኖር ሰው ሁነህ ማለፍ ከፈለክ ነባሩ አስተሳሰብ ነባሩ የገቢ ምንጭና የስራ ሲስተም እንድሁም የግዜ አጠቃቀምህን በፍጥነት ቀይር /ቀይሪ  ያለዚያ እውነታው ካለፈው እልቅ እሚመጣው ዘመን ኮስተር ያለ ነው ያለም ገበያ አንድ ሁኗል አለም ወደድጅታሉ ወይም ወደሜታ ቨርስ ከተቀየረች ውላ አድራለች በጣም ለውጥ አለ ሶ አንተም አንቺም የለውጥ ጎዳናን መከተል የውዴታ ሳይሆን አሁን ላይ ግዴታ ነው🙏 @balenamist @balenamist @balenamist
نمایش همه...