cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Shashe Fana 103.4

پست‌های تبلیغاتی
588
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሲዳማ ባንክ በ2015 በጀት ዓመት ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ። ሻሸመኔ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ፋና 103.4)- ሲዳማ ባንክ 2ኛ መደበኛና 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ዕለት አካሄደ። የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብረሃም ማርሻሎ በጉባኤው ላይ ባቀረቡት የባንኩ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጠረውን የፋይናንስ ቀዉስ ተቋቁሞ ባንኩ ትርፋማ መሆን ችሏል ብለዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 60.7 ሚሊዮን ብር ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ በተሰራው የተቀናጀ ስራ 63.9 ሚሊዮን ብብር ትርፍ ማግኘት ተችሏል ነዉ ያሉት። በበጀት ዓመቱ ከ287.9 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 275.8 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 96 በመቶ መከናወን መቻሉን ተናግረዋል። ይህም በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ98.8 ሚሊዮን ብር ወይም 55.8 በመቶ ብልጫ አለዉ ነዉ ያሉት። በዚሁ ዓመት 229.2 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስቧል ብለዋል። ይህም 64.1 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። በብድር አገልግሎት 616 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠቱን የቦርድ ሰብሳቢዉ አቶ አብረሃም ማርሻሎ ጠቁመዋል። በብድር አገልግሎት የተበላሸ የብስር ምጣኔ 3.5 በመቶ ሲሆን ይህም በብሔራዊ ባንክ አሰራር መሰረት ጤናማ መሆኑን ገልፀዋል። በካፒታል እድገት ካፒታሉ ከነበረበት 293.3 ሚሊዮን ብር ወደ 532.7 ሚሊዮን ብር ያደገ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ 826 ሚሊዮን ብር እንዲደርስ አስችሏል ብለዋል። በሀብት መጠን እድገት 890.2 ሚሊዮን ብር ወይም 116 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን ይህም ጠቅላለሰ የባንኩ ሀብት 1.3 ቢሊዮን ብር እንዲደርስ አስችሏል ነዉ ያሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ መስፈርት ለማሟላት በመጪዎቹ 5 ዓመታት የባንኩን ካፒታል 5 ቢሊዮን ብር ለማድረስ በትኩረት ይሰራል ነዉ ያሉት። በቢቂላ ቱፋና ደብሪቱ በዛብህ ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ገፃችንን ይከታተላሉ https://www.facebook.com/profile.php?id=61552994691808
نمایش همه...
Shashemene Fana FM 103.4

Shashemene Fana FM 103.4. 102 likes · 95 talking about this. In Speed Of Life

የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም የfacebook በዚህ ሊንክ በመቀላቀል ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ https://www.facebook.com/profile.php?id=61552994691808
نمایش همه...
Shashemene Fana FM 103.4

Shashemene Fana FM 103.4. 5 likes · 3 talking about this. In Speed Of Life

በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ እስማርት ሲቲዎችን ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ተናገሩ ። ከተሞችን ፅዱና ምቹ በማድረጉ ረገድ እያንዳንዱ ዜጋ ሀላፊነት በተሰማው መልኩ አካባቢውና ከተማውን ፅዱ በሆነ መልኩ እንዲጠብቅ ማስቻል ይገባል ብለዋል ። በፕላን የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር ህገ ወጥነትን ለማስወገድንና ከተሞችን በስራት ለመምራት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል ። ከተሞችን በራሳቸው ገቢ ኢኮኖሚያቸውን እንዲያስተዳድሩ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል  ። ከተሞችን በካዳስተር ስርዓት ውስጥ ማስገባትና ተግባራዊ ማድረግ ሌብነትን ከመከላከል ባሻገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ። የ2016 በጀት አመት የሴክተር ጉባኤና የንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል ። የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምሬ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በ2015 በጀት አመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ በዘርፋ ውጤት መምጣቱን አንስተዋል ። የመሬት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ የገለፁት ሀላፊው ባለፋው በጀት አመት ከእቅዳችን አንፃር ከተዘጋጀው መሬት ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነውን መሬት ለዜጎች መቅረቡን ገልፀዋል ። በከተሞች  ከ 30 ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች በተለያዩ የስራ መስኮች የስራ እድል የተፈጠረ ቢሆንም በቀጣይም በበለጠ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል ። በቀጣይ ከተሞች ከዚህ በበለጠ ፈጣን የተሳለጠና የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ። ባለፈው አመት በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የግብዓቶች የዋጋ ጭማሪ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ተግዳሮት የፈጠረ ቢሆንም ዘርፈ ብዙ ተግባራቶች መከወኑን አንስተዋል ። የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያለፋ ተግባራትንና ቀጣይ መሰራት በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ከሁሉም አካባቢዎች ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየመከረ ይገኛል ። እየቀረበ ባለው ሪፖርት ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ። በብርሃኑ በጋሻውና ተመስገን ቡልቡሎ
نمایش همه...
የሲዳማ ክልል በጀት አመት 13.1 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገለጠ የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን :-  የታክስ ህግ ተገዢነት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል ። መድረኩ ግብር ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል  እየተካሄደ ነው ። የባለስለጣኑ ሀላፊ አቶ ሀይሉ ጉዱራ ግብርን ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት ቢገኝም አሟጦ ከመሰብሰብ አንፃር  በበለጠ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል ። ክልሉ በዚህ በጀት አመት 13.13 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የክልሉን አጠቃላይ ወጪ 60 በመቶ በላይ ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ስለመሆኑ አመላክተዋል ። ደረሰኝ መስጠትና መቀበል አለመቻል ክፍተቶች፣ ከግንዛቤ ጋር የሚታዩ ችግሮች ፣ የኮንትሮባንድ ህገ ወጥ ተግባራቶችና መሰል ችግሮች በዘርፋ ከታዩ ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀው ሁሉም አካል በቅንጅትና በሀገር ወዳድነት መንፈስ በመስራት ክፍተቶቹን መፍታት ይገባል ብለዋል ። መንግስት መሰረተ ልማቶቹን ለመገንባትና የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት ህዝቡ በአግባቡ ግብሩን መክፈል እንደሚገባው አስታውቀዋል ችግሩን ለመፍታትም ግንዛቤን መፍጠር ፣ የንቅናቄ መድረኮችን መፍጠር ፣ ለአመት የሚቆይ የንቅናቄ መድረኮችን በማካሄድም ግንዛቤ የሚፈጠር ይሆናል ። ዛሬ እውቅና የሚያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅናን ከማግኘት ባሻገር አምባሳደር በመሆን ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ። ግብራቸውን በወቅቱ በማሳወቅና በታማኝነት ግብራቸውን ለሚከፍሉ   ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብርም ይካሄዳል ። በመድረክ ላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮችና በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የዘርፋ አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝቷል ። ብርሃኑ በጋሻው
نمایش همه...
መስከረም 12 /2016 የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ የማሳላ በዓል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ በደመቀ መልኩ በመከበር ላይ ይገኛል ። በዓሉም ትላንት የጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም በርካታ ህዝብ በተገኘበት በከምባታ ሁለገብ ስቴዲየም በተለያዩ ክዋኔዎች ታጅቦ እየተከበረ ነው ። የማሳላ በዓል አብሮነት የሚደረጅበት ፣ በናፍቆት የሚጠበቅና በከፍተኛ ዝግጅት ደምቆ የሚያልፍ በመሆኑ በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል ። ከወራት በፊት አስቀድመው  የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማህበረሰቡ ያከናውናል።  በተለይም ለባህላዊ ምግቦች ግባዕቶችን በማዘጋጀት በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ ጥረት ይደረጋል ። እናቶች የቅመማቅመሞችና ለአታካና ባህላዊ ምግብ ዝግጅት የሚሆን ቆጮ ማሰናዳት እንዲሁም ለበዓል የሚሆን ቂቤን በስፋት የማጠራቀሙ ተግባር ለወራት የሚከወን ነው ። የበሬ የመግዛትና በጋራ አርዶ በዓልን ከጎረቤት ጋር ለማሳለፍም አባቶች ቀደም ብለው ለበሬ ግዢው ገንዘብ በማጠራቀምና በማስቀመጥ ለበዓል የሚሆን ሰንጋ የሚሸምቱበት ልዩ ጊዜያቸው ነው ። ከአብሮነቱ ባሻገርም ለበዓል የሚሆኑ ግብዓቶችን የማስቀመጥ ባህላዊ ስለታቸው ቀድሞ የነበረን የቁጠባ ባህል መጎልበቱን የምንመለከትበት እውቀት ነው ። የብሔሩ ተወላጆች በማሳላ በዓል በግጭት ውስጥ ሆኖ አዲስ አመትን መቀላቀል የለባቸውም ተብሎ ስለሚታሰብ የሀገር ሽማግሌዎች የተጣሉትን በማስታረቅ ቆይታ የሚያደርጉበት ወቅት ይሆናል ። ከችቦ ዝግጅት ጀምሮ የደመራ ማብራት ስነ ስርዓትና ሌሎች ባህላዊ ክዋኔዎች በአብሮነት የሚከወኑ እሴቶች ናቸው። ዛሬ በአደባባይ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ የማሳላ በዓል እየተከበረ ይገኛል ። ማለዳ 12 ሰዓት ላይ በርካታ ሰው የተሳተፈበት የማሳላ ታላቁ ሩጫ ተካሂዷል ። በዚህ የማሳላ ሳምንት ተብሎ በተሰየመው የበዓል አከባበር በተለያዩ አካባቢዎችም መሰል ዝግጅቶች እየተከናወኑ የሚቀጥሉ ይሆናል ። የመስከረም ወር በከምባታ በደስታና በፍቅር የሚታለፍበት ሆኖ ያልፋል ። ከተለያዩ አካባቢዎች ለበዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው የመጡ የብሔሩ ተወላጆችም ከሰሞኑን በበዓል ድባብ ውስጥ ሆነው ከቤተሰቦቻቸው ከጎረቤቶቻቸውና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ደስ የሚል ጊዜን የሚያሳልፋ ይሆናል ። በትላንትናው እለት የባህል የታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም የተካሄደ  ሲሆን የብሔሩ  እሴቶች ላይ የሚያተኩር ጥናታዊ ፅሁፍፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ። በባህል ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም  የፖናል ውይይት ከማድረግ ጎን ለጎን የመፃሀፍ ምርቃት ፣ ባህላዊ የሙዚቃ ስራ ማስመረቅ ፣ የተለያዩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ማህበራትና ግለሰቦች  እውቅና የመስጠት ስነ ስርዓትና ተከናውኗል ። በመድረኩ ላይ ከፌደራል ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፣ የከምባታ ተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ሙሁራኖችና የብሔሩ ተወላጆች ታድመዋል ። ምሽቱንም የአተካና ባህላዊ ምግብ የተመለከተ ስነ ስርዓት  በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎችና ዜማዎች እንዲሁም በፈረስ ጉግስ ትርዒት ታጅቦ ተከናውኗል ። በብርሃኑ በጋሻውና በጥላሁን ይልማ
نمایش همه...