Harari Education Bureau
ይሄ ቴሌግራም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚያስተላልፋቸው ትምህርታዊ መልዕክቶችና የተለያዩ መረጃዎች ለትምህርቱ ማህብረሰብና ለተማሪዎች በቀላሉ ተደረሽ እንዲሆን ለማስቻል ነው ፡፡
نمایش بیشتر2 015
مشترکین
+124 ساعت
-17 روز
+1330 روز
- مشترکین
- پوشش پست
- ER - نسبت تعامل
در حال بارگیری داده...
معدل نمو المشتركين
در حال بارگیری داده...
ለሁሉም 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የ2015ዓ.ም የተመሪ ውጤት ሮስተር አንድ ኮፒ እስከ 28/1/2016 ድረስ ለት/ቢሮ ሙያ ፍቃድ ዳይሬክቶሬት እንድታሰገቡ እናሳውቃለን።
ጽህፈት ቤቱ ለትምህርት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ።
መስከረም 19/2016(ሀክትቢ)የኤረር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ።
የኤረር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ ትምህርት ቤት አመራሮች በእቅድ ዝግጅት እና ሪፖርት እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራር ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ጽህፈት ቤቱ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ምክትል ርእሰ መምህራን እና ዩኒት ሊደሮች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቀጥል መሆኑን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ትምህርት ጽህፈት ቤቱ ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ነው።
ዳይሬክተሩ ሽልማት ተበረከተላቸው ።
መስከረም 18/2016(ሀክትቢ)የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሁሴን በክልሉ ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሽልማት ተበረከተላቸው ።
የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመምህራን እና የትምህርት አመራሮች እየሰጠ በሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የቢሮው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሁሴን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና የግዜ አጠቃቀም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ በክልሉ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርእሰ መምህራን እና ሱፐር ቫይዘሮች ያዘጋጁት መሆኑም ተመላክቷል።
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
=======®======
ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ የደስታ፣ የሰላም እና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
መልካም በዓል!
#ቀን14/1/16ዓም ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳይሬክቶሬት የ2016 የስራ ዘመን እቅድን ወደታች በማውረድ በስሩ ከሚገኙ ፈጻሚዎች ጋር ተፈራረመ ፡፡