cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኑ አብረን እንዘምር🙏🙏🙏🙏

በስመኣብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አሜን። ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በ ቻናላችን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ስርዓት የጠበቁ መዝሙሮች የሚለቀቅበት እንዲሁም መንፈሳዊ እውቀቶችን የምናገኝበት ነው ። ሃሳብዎን ከስር ባለው link ያጋሩን። 🙏 🙏 @selam_lek🙏🙏🙏 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 004
مشترکین
+224 ساعت
+587 روز
+25930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አግኝቼሻለሁ በጎልጎታ አለሽ በፊቴ ከእግረ መስቀሉ ስታነቢ ድንግል እናቴ አይረሳኝም ያንን ዕለት አስታውሳለሁ ልጅሽ ተሰቅሎ አንቺ አልቅሰሽ እኔ እፅናናለሁ በኤፍራታ በምድረ ይሁዳ ታቅፈሽው ታላቁን እንግዳ በአውግስጦስ ቄሳር ትዕዛዝ ህዝቡ ሲቆጠር በጀርባሽ ላይ ስየዋለሁ የአምላኬን ፍቅር ከሁሉም የበለጠ ከትቦት ህሊናዬ የቀራንዮ ትዝታ አይጠፋም ከአይምሮዬ(2) አዝ....... ሰብዓ ሰገል ከምስራቅ የመጡ በአስተብርኮት እጅመንሻ ሰጡ በክህነቱ ለመንግስቱ ለሞቱ የሚሆን በልቦናሽ አንዱ ደስታ አንዱ ነበር ሀዘን ከሁሉም የበለጠ ከትቦት ህሊናዬ              የቀራንዮ ትዝታ አይጠፋም ከአይምሮዬ(2) አዝ............. ከሄሮድስም አስከፊ ጭከና ልታተርፊው ተሰደሻልና በበረኃ ወንበዴዎች ይገድሉታል ብለሽ ስታለቅሺ አይቻለሁ በእንባ ታጥቦ ገፅሽ ከሁሉም የበለጠ ከትቦት ህሊናዬ              የቀራንዮ ትዝታ አይጠፋም ከአይምሮዬ(2) አዝ.............. ፀሀፍትና ፈሪሳዉያኑ በዘመኑ እርሱን ሲፈትኑ ያለበደል በመስቀል ላይ በሰቀሉት ጊዜ አገኘሁሽ ተሰጠሽኝ ሳለሽ በትካዜ ከሁሉም የበለጠ ከትቦት ህሊናዬ              የቀራንዮ ትዝታ አይጠፋም ከአይምሮዬ(2) አዝ......
نمایش همه...
ታላቅ የቤተክርስቲያን ምርቃት🌷                            እና               የበዓለ ንግሥ ጥሪ!!!🌷 🌸🌷✨✨🌷✨✨🌷✨✨🌷🌸                           እንኳን ደስ አላችሁ!! ✥🌷✥🌷✥🌷✥✥🌷✥🌷✥✥🌷✥ የቃሊቲ ስርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል                    ማርያም ቤ/ክርስቲያን አዲስ የተሰራው ህንፃ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ! #ግንቦት_20     ታቦተ ህጉ  ከቀድሞ መቃኖ ወደ አዲሱ ህንፃ ቤተክርስቲያን  በብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት ተባርኮ  ይገባል!! #ግንቦት_21 በእመቤታችን ዓመታዊ በዓል ቀን ታቦተ ህጉ ወጥቶ ቅዳሴ ቤቱ ይከብራል!! ✥🌸✥🌸✥🌸✥🌸✥🌸✥🌸✥🌸 ሁላችንም በእነዚህ ታላቅ የበረከት ቀናት እንድትገኙ በእመቤታችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!! 🌷✥🌷✥🌷✥🌷🌷✥🌷✥🌷✥ አድራሻ :- ቃሊቲ ቶታል (መናኸሪያ ) በስተግራ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ (ማርያም ሰፈር)
نمایش همه...
✞ #ኪዳነ_ምህረት_እመቤት ✞ ኪዳነ ምህረት እመቤት/2/ ነይልን /2/ ካለንበት ከሰማያት በላይ ካለው ከማደሪሽ/2/ ዝማሬ ከሞላው ከዘላለም ቤትሽ የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ/2/ የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሰረገላሽ/2/ #አዝ ከፀጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ/2/ ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ ሰዓሊለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ/2/ ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ/2/ #አዝ ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሰማያት ዕንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት የፅዮን ዝማሬ ተሞላ ነፍሳችን/2/ ነዪ/3/ እንበል እነደ አባቶቻችን/2/ #አዝ ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ/2/ የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሸ ትውልድ ይህን አምኖ ብፅዕት ይልሻል እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል/2/ #አዝ የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሽ ዝም አትይም ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም ከአይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሻለሽ/2/ ከሐዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ/2/ @nu_abren_enzemr
نمایش همه...
✞ ለእመቤቴ_ችግሩን_የነገረ ለእመቤቴ ችግሩን የነገረ /2/ በቃና ገሊላ ውኃው ተቀየረ ለእመቤቴ በእናትነት ፍቅሯ ለእመቤቴ ተስፋዬ ሲከስል ለእመቤቴ በርታ ቁም ስትለኝ ለእመቤቴ ባንቺ አፍሬ አላውቅም ለእመቤቴ ማረው ይቅር በለው ለእመቤቴ ብላ እየማለደች ለእመቤቴ ዘመኔን በምህረት ለእመቤቴ ትባርከዋለች /አዝ ===== ለእመቤቴ ከሞላው ማድጋ ለእመቤቴ ምህረት እየቀዳች ለእመቤቴ ከአዳኙ ልጇ ለእመቤቴ ና ተማር እያለች ለእመቤቴ ከመኃሪው ጌታ ለእመቤቴ ከቅፉ እንዳልወጣ ለእመቤቴ ትለምነዋለች ለእመቤቴ ከቀኙ ተቀምጣ /አዝ ===== ለእመቤቴ እመቤቴ ስላት ለእመቤቴ አፌማ ተከፍቶ ለእመቤቴ ልቤ በሀሴት ቃል ለእመቤቴ ተትረፍርፎ ሞልቶ ለእመቤቴ ፍቅሯን በልቤ ላይ ለእመቤቴ ጣዕሟን በአንደበቴ ለእመቤቴ እንዳኖረው እርዳኝ ለእመቤቴ ክርስቶስ አባቴ /አዝ ===== ለእመቤቴ የዶኪማስ ተስፋ ለእመቤቴ ጭንቀቱን ያስወገድሽ ለእመቤቴ ከልጅሽ ፊት ቆመሽ ለእመቤቴ ጎዶሎውን ያስሞላሽ ለእመቤቴ እኔም ላመስግንሽ ለእመቤቴ ውዳሴሽን ላብዛ ለእመቤቴ ወልዳ ለሰጠችኝ ለእመቤቴ የህይወትን ቤዛ @nu_abren_enzemr
نمایش همه...
እንወድሻለን ኪዳነምሕረት✝ ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሡ የክብራችን ጌጥ ሽልማት እንወድሻለን ኪዳነምሕረት በጨለማው ላለ ብርሀንን አየ ለእርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ አንቺ ነበርሽ ተስፋው ለአዳም መዳኛ አዝ__ ያን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም ዓለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን ደምሽን ተዋህዶ መድኃኔዓለም ዋጀን አዝ__ አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት ዓለም ያልተረዳው ያለወቀው እውነት ያወቀ የተረዳ የመድኃኑን ምስጢር አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር አዝ__ አውቃለው እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር ላመስግንሽ እኔም ሳልቀንስ ሳልጨምር ሚባርክሽ ቡሩክ ነው እና እናቴ ኪዳነምሕረት ንገሽ እመቤቴ በዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ @nu_abren_enzemr
نمایش همه...
#አልረሳውም_ያንን_ዕለት አልረሳውም ያንን ዕለት አልዘነጋው ያን ደግነት እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/ ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/ ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት #አዝ ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/ አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን #አዝ እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/ በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ #አዝ ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/ ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ @nu_abren_enzemr @nu_abren_enzemr
نمایش همه...
ሁላችሁም ከላይ ያለውን link 👆እየነካችሁ tap tap በማድረግ ብቻ ብር ይሰብሰቡ ⚠️ 5ቀን ስለቀረው ቶሎ ጀምሩት
نمایش همه...