cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ጥበብ

አጭር ልበ ወለዶች😘😘፡ የፍቅር ጥቅሶች😍😍 የፍቅር ታሪኮች💏💏 ረጅም ልበ ወለዶች🙌 መፅሀፍትን በpdf📚📚📚📚📚📚 ማንኛውንም አስታየት ለመስጠት&"ጥያቄ ---------👇--------- @mexxx14

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
449
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሰዎች እንደተቀየርክባቸዉ ያወራሉ፤ በእነርሱ ምክንያት እንደተቀየርክ ግን አይገባቸዉም…ስለዚህ ሲወዱህ የሚወድ ሲጠሉህ የማይጨነቅ ብርቱና ቅን ልብ ይኑርህ ፤ በኑሮህ ሁሉ የምታዉቀዉን ሁሉ መናገር ላይጠበቅብህ ይችላል፤ የምትናገረዉን ሁሉ ግን ማወቅ አለብህና! ግለ ኑሮህን በአስተዉሎት ኑር። በዚህ ምድር ሰዉ መሆን ነዉ እንጂ፤ ሰዉ መምሰል ቀላል ነዉ፤ እንዲሉ በፍጹም ራስ ተማመን፣ ሁሌም ራስህንም ሁን፤ በዙሪያህ ላሉ ጩኸቶች ሁሉ ጆሮህን አትስጥ። ሀይቅ ዳር ተሰብስበዉ እንቁራሪቶች አብዝተዉ ስለጮሁ ሀይቁ የእንቁራሪቶች ነዉ ማለት አይደለም:: ለክብራቸዉ ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ ዓሳዎች በሀይቁ ዉስጥ አሉና። ©ሎሬት ፀጋዬ_ገብረመድህን
نمایش همه...
ለአንዲት የገጠር ሴት . . ስትፈጭ የኖረች ሴት መጁ በመጠኗ ወፍጮውም በልኳ ጓያ ትፈጫለች ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ!! . . አስባው አታውቅም ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች ከእለታት አንድ ቀን ከእናቷ ሆድ ወጣች ከእለታት አንድ ቀን ጡት አጎጠጎጠች ከእለታት አንድ ቀን ለባሏ ተሰጠች....!! . . ከዚያን ቀን ጀምራ ከዚያን ቀን ጀምሮ ድንግል ድንጋይ ወቅራ ትፈጫለች ሽሮ.............!! . . አታውቅም ማን እንደሚባሉ ጠቅላይ ሚንስተሩ ሹማምንት በእሷ ስም ምን እንደምሰሩ ፖለቲካ እና እራስን ማራቀቅ ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ..! . . ከቶ ማንም የለ አበባ የሚሰጣት ከቶ ማንም የለ ከተማ የሚያወጣት ከቶ ማንም የለ በዳንኪራ መላ ወገቧን የምያቅፋት ልፋቷም ዕረፍቷም ወደዚህ መጅ መሳብ ወደዚያ መጅ መግፋት። እንደ ዓባይ ፏፏቴ ሺህ ዓመት ብንጣለል ቢጎርፍም ዱቄቱ እንደ ሲኦል ወለል ጫፍ የለውም ቋቱ . . ከዘመናት በአንዱ መስታወት ፊት ቆማ በተወለወለው ራሷን ለማየት ከፀጉሯ ላይ ያለው ዱቄት ይሁን ሺበት ሲያቅታት መለየት ያኔ ይገባታል የተሰጣት ዕጣ ከማድቀቅ ቀጥሎ መድቀቅ እንዳመጣ . . የመጅ አገፋፉ አምሳለ ሲፈስ ከቋት ሦስት እንጅ ሲሳይ አይታፈስ ትቢያ የሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ ከባርኔጣ አይሰፋም የኑሮ ጣርያዋ ስትፈጭ የኖረች ሴት ይህ ነው መጠርያዋ። በዕውቀቱ ስዩም @Ethio12tbeb
نمایش همه...
#ተዓምረኛው_አባ . . . ለምድረ በዳይቱ አገራቸው ሽፍታ ላስቸገረው ሕዝባቸው ሊጸልዩ ሊሰግዱ ሊማልሉ ሊማልዱ አባ ተኝተው መሬት በ'ንባ በሳግ በምሬት “ጌታ ሆይ አገሬን ባክህ አጽናናት ከቀማኞች አድናት” በማለት አርባ ዓመት ሙሉ ኪራላይሶ ስማኝ ሲሉ እሱም ተልቡ በማድመጡ ቀማኞች ከሕዝቡ ወጠ እናም ከጊዜ በኋላ የመናኙ ያባ ገላ ተለውጦ እንደ ዘበት ግዙፍ ጫካ በቀለበት አባም ይህን ታምር ቢያዩ እንዲህ በለው ጸለዩ “ጌታ ሆይ እነሆ የጌ ብፅዕና ይኸውልህ ዛሬ ገና ቀማኞችን ከሕዝብህ አውጥቶ አስኮበለለ ከመሬታችን ተሽሎ ገላዬም ደን አበቀለ ከቀባሀቸው ጣድቃን መሀል እኔን 'ሚያክል ማን አለ?” በታብዮ ይህን ብለው ምልጃቸውን ሲዘጉ ከሕዝብ የሸሹ ሽፍቶች መጥተው እየተንጋጉ ጀርባቸው ላይ ባለው ደን ውስጥ ጥልቅ ብለው ተሸሽጉ!፡፡ #በዕውቀቱ_ስዩም ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @ethio12tbeb
نمایش همه...
እንደምነሽ እቱ✍ እቴ ሆይ እንዴት ነሽ እንደምን ሰነበትሽ አማን ሰላም ነው ወይ ከደጁ ከቀየሽ መንገድ አካሄድሽ እንዴት ነው ጎዳናሽ ምሽትና ለሊት ቀንና አዋዋልሽ እንዲያ እንደበፊቱ ገና ከመንጋቱ ፀሀይ ከመውጣቱ ማለዳ ተነስተሽ ነጠላን አንግበሽ ድርሳን መፃፍ ይዘሽ ደጀ ሳሌም ሄደሽ ፀሎት ታደርሻለሽ? ተዚያ ተመልሰሽ ስራሽን ከውነሽ ማድረግ ወዳለብሽ ወደዚያ ትሄጃለሽ? ጓጉተሽ ሲመሽ ደሞ ልብሽ ለመሄድ ቆሞ ቀሚሱን ጎትተሽ አጣፍተሽ ነጠላ ከነፍስ ስንቅ አለም ከጉባኤ ተድላ ከህይወት ምግብ ቤት ትቋደሻለሽወይ? ወይስ ደሞ እቴ ሆንሽ ምናምንቴ ፍለጋ ወተሻል ማንነትሽ ጠፍቶ የሴትነት ወግሽ ማተብሽ ተፈቶ? እኮ እንዴት ነሽ እቴ ገና ከመንጋቱ ፀሀይ ከመውጣቱ ያ ወዛሙ ፊትሽ በአመድ መንጣቱ የቅንድብሽ ጥቁረት የከንፈር ቅላቱ የልብስ ያለ የሚያሰኝ ያረግሽው እጥረቱ ራስሽ በሁማንሄር ተከምሮ መታየቱ እኮ ገና ከመንጋቱ አልሆንሽማ እቱ? እቴ ሆነሻል ወይ ስራ ፈት የስንቱን ልብ የሚያስት ሆነሻል ወይ ተላካፊወጪ ወራጅ አሰላፊ ገንዘብ ወዳድ ተሸናፊ እግዜር የተለያት የጂኒ ጓደኛ ሆነሻል ወይ እቴ በሱስ አደገኛ??? ጭንቀት ሊገለኝ ነው የቱ ተስማምቶሻል የላይኛውን ነው የታቹን መርጠሻል? ንገሪኝ እታለም እንደ ቀድሞ በይኝና ይረፍ ልቤ ባንቺ በደስታ ይኩራና ግን እንደታችኛው ከሆነ እንደኋላ ንገሪኝ ላልቅሽልሽ ህርምሽን እንዳልበላ በይ ንገሪኝ ከፊቱ ነሽ ከኋላ የጥንቱ ማተብሽ ጠበቀ ወይ ላላ? ሶሊ ነኝ(ቤቲ)✍✍ 7:03am 18/12/2013ዓ.ም ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @ethio12tbeb
نمایش همه...
መለያየት ማለት እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት ያለመተያየት መፋቀርም ማለት በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት ዘወትር ዘወትር ምናልባት ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን ብለሽ ንገሪያቸው ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት ✍️✍️ገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም @ethio12tbeb
نمایش همه...
በቻናላችን ለምትገኙ ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል-አድሐ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ለማለት እየወደድን በዐሉ የሰላም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆን በቻናላችን ስም እንመኛለን! መልካም በዓል 💫 ጥበብ channel @ethio12tbeb @ethio12tbeb @ethio12tbeb
نمایش همه...
መለያየት ማለት እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት ያለመተያየት መፋቀርም ማለት በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት ዘወትር ዘወትር ምናልባት ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን ብለሽ ንገሪያቸው ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት ✍️✍️ገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም
نمایش همه...
አምሳሉ ...... አበባው አየሩ ዛፉ ሳር ቅጣሉ በፍጥረት አለም ላይ የሚታየው ሁሉ ውብ የሆነው ነገር የሚያምረው በሙሉ ሐሩ ቀጭን ኩታው አልማዝና ሉሉ ቀሚሱና ሻሹ መስቀሉና ሀብሉ የወርቅ ጌጣጌጡ አርባን ስራው ሁሉ ሀብቱ ደግነቱ ደግ ደግ በሙሉ ምንም ነገር ሳይቀር ያንቺ ነው አምሳሉ። [ አፈወርቅ ዮሀንስ ] @ethio12tbeb
نمایش همه...
🌙 እንኳን ለኢድ አል አደሀ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🌙
نمایش همه...