cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Idran 🙏🙏12

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
171
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በመንገድህ ሁሉ ሰዎች ሳይሆኑ እግዚአብሔር ካንተ ጋር መሆኑን ጠንቅቀህ መርምር ። ብቸኝነት ማለትም ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር መራቅ ነው ። መልካም አሳብ ለኅሊና ምቹ ዕረፍትን ይሰጣል ። ቆመው የማይጠብቁ ሁለት ነገሮች አሉ ፡- ጊዜና ዕድል ። ጊዜና ዕድል ሲገጥምህ ቶሎ ተጠቀመው ። ብዙ ሰው የሚቆጨው ጊዜና ዕድልን ሸኝቶ ነው ። በነጻ የመጣ ነገር ከሄደ በኋላ በዋጋም አይመለስም ። ከመንገድ ምልክቶች አንዱ “ቁም” የሚል ነው።መቆምም የመጓዝ አንዱ ክፍል ነው ። ቆም ብለህ ሥራህን ገምግም ። አባት ሳለ መማር ፣ እናት ሳለች መሥራት ፣ ንጉሥ ሳለ መሮጥ ተገቢ ነው ። መኪና በፍሬን ካልቆመ ነዳጅ ጨርሶ ወይም ተጋጭቶ ይቆማል ። ሁሉም መቆም ቢሆንም እንደገና የሚጓዘው በፍሬን ሲቆም ነው ። አንተም ለቃልህና ለምኞትህ ፍሬን ይኑርህ ። በመንገድ ሁሉ አይኬድም ፣ በሚያደርሰው መንገድ እንጂ ። ያየኸው ሁሉ አይመርህ ። ሁሉም ያንተ እንዲሆን አትፈልግ ። ሁሉንም ታጣለህና ። መቀበሪያ እንኳ ያጡ ነገሥታት ሁሉ የእኔ ይሁን ያሉ ናቸው ። የከበረ ቀብር የምታገኘው ያነሰ ምኞት ሲኖርህ ነው ። ስግብግብ ሰው በሥጋው ጨርሶ በነፍሱ ሲወቀስ ይኖራል ። የሹም ሌባ ያጸይፋል ። ሁሉም የእርሱ ሳለ የራሱን የሚሰርቅ ነውና ። በዝምታ የዋልህበት ቀን ኃይልህ ያልባከነበት ቀን ነው ። የእግዚአብሔርን ቃል የተናገርህበት ቀን ደግሞ ኃይልህ የሚታደስበት ቀን ነው ። ከመከራ ይልቅ ዕድልን ታገሠው ። ከቀን በኋላ ሌሊት እንደሚመጣ ከዕድል በኋላም ችግር ይመጣል ። ዕድል ማለት እግዚአብሔር የሰጠህ ጊዜ ማለት ነው ። እግዚአብሔር በሚበልጠው ሊሾምህ በሚያንሰው ይፈትንሃል ። 😁 ከእጅ ሌባ የአፍ ሌባ ይከፋልና አንደበትህን ተቆጣጠር ።
نمایش همه...
"የተራበውን ማብላት፥ የተጠማውንም ሰው ማጠጣት የሞተ ሰውን ከማስነሣት ይበልጣል፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
نمایش همه...
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን? እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው? #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
نمایش همه...
ዓመታትን በቸርነቱ የሚያቀዳጅ እግዚአብሔር ከዘመን ዘመን ስላሸጋገረን ይክበር፡፡ የተሻለም ጊዜን ያመጣልን ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን። መልካም አዲስ ዓመት!
نمایش همه...
🙏እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏 🌼መልካም አዲስ አመት🌼
نمایش همه...
🌼🌼🌼 ጊዜ ንጉስ ነው ! 🌼🌼 🌼🌼🌼 ይጥላል ያነሳል። 🌼🌼 🌼🌼😊 ይብዛም ይነስም በህይወታችን ውስጥ ያሳለፍናቸው ጥሩም ሆነ መጥፎም አጋጣሚዎች ይኖሩናል። ❤❤ 😀👊 ታዲያ እኛ የሰራናቸው ጥሩ ነገሮች ሁሉ ለራሳችን እንደሆነ እንወቅ ! 👍👍 ❤ ''ጥሩ ስራ የክፉ ጊዜ ስንቅ ነው'' ❤ ከመጥፎዎቹ ደግሞ በመማር ቢያንስ ያደረግነውን መጥፎ ነገር ባለመድገም የነገ ህይወታችንን እናስተካክል።👏👏 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼❤️❤️ እንግዲ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት ልንሸጋገር ነው። 🙈🙈 የምር ምንሸጋገረው ነገር አለ ብለው ያስባሉ ? 😳😳 የጊዜ ሽግግር የለም የቁጥር እንጂ ! 🙂🙂🙂 ሁሌም ቢሆን አስተሳሰባችን ከአጥር ውጪ ቢሆን ጥሩ ነው። 👏👏😏😏🌼🌼👍👍 👉 ካየን እንመልከት 👉 ከሰማን እናዳምጥ 👉 እናሰላስል 👉 እንተግብር 🌼🌼🌼🌼 መጪው ጊዜ መልካም መልካም ብቻ የምናይበት እና የምንሰማበት ይሁንልን አሜን ! 🌼🌼🌼
نمایش همه...
አስበው እስኪ....በየቀኑ የሚያስደስትህን ብቻ ስታደርግ፤ ከምትወዳቸው ጋር ሁሌም በደስታ ስትኖር፤ የጠየከው ሁሉ ተሳክቶ አይምሮህ ሰላም አግኝቶ የተረጋጋ ህይወት ስትኖር...እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ሰው ይሄን ህይወት ይፈልጋል። ፈጠሪ አንድ ቀን ሲጨምርልን የሚያስደስተንን ነገር ብቻ ወደ ህይወታችን እንድናመጣ እድል እየሰጠን ነው። ወዳጄ ያንተ ስራ ዛሬን ከትናንት የተሻለ ማድረግ ይሁን! ያኔ ያሰብከው ሁሉ በህይወትህ መገለጥ ይጀምራል።
نمایش همه...
በፈጣሪህ ተደገፍ! ህይወትህን የሚቀይረው ከሰው ጠብቀህ የምታገኘው ነገር አይደለም፤ ፀጋው፣ ስጦታው፣ ቸርነቱ ከማያልቀው ከፈጣሪህ ከምታገኘው በረከት ነው ህይወትህ የሚቀየረው። ወዳጄ በጭራሽ ከሰው እንዳጠብቅ፤ ሰው ማለት ሸንበቆ ነው የሆነ ቀን መቀንጠሱ አይቀርም! ከፈጣሪ ቀጥሎ ራስህን እመነው! እምነት የሞላው ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
نمایش همه...
ስሜት! ያለህበትን ሁኔታ ቀላልም ከባድም የሚያደርገው ስሜት ነው፤ አስበው እስኪ በጣም የሚያስደስት ሁኔታ ውስጥ ሆነህ የምታደርጋቸው ነገሮች እኮ ትርጉም ይሰጡሀል፤ ከባድ የሚባለውን ስራ ሳይደክምህ በሚገርም ሞራል ትሰራዋለህ። አየህ ብዙ ነገር ያሳኩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከላይ የነገርኩህ ስሜት ላይ ናቸው፤ ሁሌም የሚያበረታ ኃይል ከውስጥ ይገፋቸዋል። አንተም ውስጥ ያ ሀይል አለ! አሁን ራሱ ምንም አይነት ስሜት ውስጥ ብትሆን እስኪ ወደምትፈልገው ኑሮ፣ ሀብት፣ ደስታ እና የአይምሮ ሰላም እየተጓዝክ እንደሆነ አስብ...ስሜትህ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነኝ። አስደናቂ ሰኞ ተመኘንላችሁ🙏
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.