cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ግጥም ከብሩኬ አንደበት

መንፈሶን በግጥም ያድሱ🆎 ግጥም የውስጥን ገላጭ ነውና🅾 ፈጥነው ይ🀄️ላ🀄️ሉን😍 👇👇👇👇👇👇 @getem_besamuel Comment👉 @Lanchisel #ሂወት_ወደፊት_ተጓዥ_ናት መመለስ_አይኖርም

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
233
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

• ችዬ ላላስቀርሽ #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ክረመቱ እየባሰ ውርጩ እየከበደ ያዘለው ደመና ዶፍ እያወረደ እደጅ አያስወጣ ብርዱ መከራነው ይሄኔን እያየሽ ልሂድ የምትይኝ ምን ብበድልሽ ነው? ላንቺም አይመችሽ መንገዱ ጭቃ ነው ለኔም አይመቸኝ ከሌለሽኝ አንቺ ቅዝቅዝ ይልብኛል ጎጆዬ ኦና ነው ትንፋሽሽ ካልሞቀው ገላዬ ባዳ ነው ልንገርሽ ሂወቴ ..... ከጎኔ መሆንሽ ለኔ መኖሪያ ነው ድምፅሽን ካልሰማው አይንሽን ካላየው የለመደሽ ውስጤ ፍፁም ወዳቂ ነው የምልሽ የለኝም የምለው ይሄው ነው ከሰማሺኝ መቼም ካዘነልኝ ልብሽ በጋው እስኪመጣ አይቁረጥ አንጀትሽ ግዴለም የኔ አለም ክረምቱ እስኪወጣ ካጠገቤ ሁኚ እንደው ልማፀንሽ ክረምቱ በቃኝ ሲል አኔው ነኝ ምሸኝሽ የምቴጂው መንገድ ብዬ ጨርቅ ያልግልሽ እንባ እያነቀኝ ሁነኛው ወዳጅሽ ቆርጠሻል መሰለኝ ችዬም አልመልስሽ ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• ካልሰሩ ላይኖር! #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ትግል ነው አለሙ መነሳት መሰበር ማፈግፈግ ምንድነው ለፍቶ ነው መከበር ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል አንድ ቀን የሰው ፊት ማየት ይቸግራል አትሰስት ጉልበትን ድካም ከፍ ያረጋል ካልጠነከሩማ ሂወት በቀላሉ መቼ ይበገራል!! ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• ይግለፅሽ ብዕሬ #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ምን ብዬ ልጀምር እንደምን ልግለፅሽ ቃል አጣው እናቴ ላንቺ የሚሆንሽ ለአብራክሽ ክፋይ ሞተሽ የምትኖሪ በሰሀን ለሠጠሽ በቁና ሰፋሪ ያንቺ ልፋትማ ሽልማት አይበቃው የንግስቶች ካባ ፍቅርሽን ላውራ ብል ይቀድመኛል እንባ እማዬ እማአለም አያውቅሽ ኩነኔ አንቺው ነሽ ያለሺኝ ከእግዜር በታች ለኔ ሰዎች ፍቅር ብለው ደርሰው ቢሯሯጡ ከእናት በላይ ፍቅር ከወዴት ሊያመጡ ዘመን የማይሽረው የማይኖረው አቻ የእናት ፍቅር ብቻ !!! አዎ እናት አለም ለስቃይሽ ዋጋ ክፍያ እንደሌለው የወለድሽው ልጅሽ ዬሄን አዋቂ ነው እንዳይርበኝ ርቦሽ እንዳይጠማኝ ጠምቶሽ ይደግልኝ ስትይ ደምሽ ጠብ ብሏል ውለታሽን ዛሬ ያጠባሽው ጨቅላ አድጎ ይመሰክራል ዘውድ ነሽ እናቴ ሁሌም የምወድሽ ከስኬቴ በላይ ዘውትር የማኖርሽ መስዋት ከፍለሻል ተመን የማይኖረው እድሜ ልኬን ብኖር ከፍዬ ማልችለው ፍቅርሽ ቀለቤ ነው ባንቺነት ነው ክብሬ ያንቺን ገደልማ ባይገልፀውም ቃሌ ልፃፍ በጥቂቱ ትንሽ ጀማምሬ ቢያቅተውም አፌ ይግለፅሽ ብዕሬ ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• ከቻልሽ ምላሹን #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) መንገድ አየሽ አሉ ከወደ ልቤ ጋር ወስዶ የሚያመጣሽ እውነቱን ሳታውቂው እንዲው ደጅ ጠናሽ ልቤ ፀባይ የለው ቢያንኳኩም አይከፍትም ጎራ ያለ እንግዳ ብዙ አይጫወትም እንዳይመስልሽ እቴ የሚያዛልቅ ማዶ መከረኛው ሆዴ ካንጀቱ ሰው ወዶ አልመለስ ብለሽ ብትከርሚ ተይ ስልሽ ፈትኚው ግዴለም ልቤም ከተኛልሽ ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
🌙🌙 ኢድ ሙባረክ 🌙🌙 ለሙላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንዲሁም የቻናላችን ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉ የሰላም፣ የደሰታ ፣የፍቅር የመከባበር እንዲሁም የመረዳዳት እንዲሆንላችሁ ተመኘን። #EID_MUBARAK
نمایش همه...
• በቃን #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) በልተነስ አንበሳው ቤትህን ደፈሩት የታገስክ እንደሆን ከፍራት ቆጠሩት በቃኝ በል አታንባ ተጭኖብህ ዝግባ በደጃፍ ከመሞት ታግለህ ካፈር ግባ ነፍጥህን ከፍ አርገው እንዲታይ ከሩቁ ስምህ ለጠፋቸው ጀግና መሆንህን አይተውት ይወቁ ነገር የከፋ ለት ግማሽ ስጋህ ጎሎ ውሎ አይሰጥለት ከመጣብህ ምሎ መመለስ አይኖርም መቀመጥ ዝምብሎ ሸኘው በመጣበት ይበቃኛል እስኪል ነገም እንደትናንት ከድንበርህ ገብቶ ገድያለው ከሚል ታግል ጎበዜዋ ያታግላል በደል አሳደህ አስገባው ጨምረው ከገደል ግፍ እየበዛበት ፍርድ የታጣ ለታ እምቢኝ ያለ እንደሆን ከታጠቀ አይፈታ ስበርና ውጣ ጠላት ካጠመደው ልክ ልኩን ስጠው ክብር ላልወደደው ታሪክህ ታላቅ ነው ያሚያወሳው ሀገር ቆርጠህ ከተነሳህ ክንድህ አይበገር እምቢ በል ያገር ሰው ትግሉን አሳምረው እምቢ ያለ ሰው ነው ተከብሮ ሚኖረው ጀምርው ዳርዳሩን ዝለቅ ወደ መሃል ከቶ ከዚ በላይ ምን ይመጣብሃል ሴረኛው ተኩላ ጨርሶ ሊበላህ ጥላ እጥልቶብሃል መክት በአንድነት ክብርህ በውሾች ተረግጦ እንዳይጣል ታገል ለነፃነት ትግል ነፃ ያወጣል ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• ሂወት ውል የሌላት #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ሂወት ትሰጣለች ደግሞም ትነፍጋለች አንዱን ስታነሳ አንዱን ትጥላለች ኩራዟን ለኩሳ እድል እያዜመች ሲያሻት ከብርሃን ስትፈልግ ከጭሱ ታከፋፍላለች ሂወት እንደዚ ነች ከቶ ማትገመት ውሏ ያልታወቀ ድንገቴነቷ ሰው እያሳቀቀ ጥቁር ስታለብስ ነብስ እየማቀቀ ያደለች እንደሆን በሠጠችው ፀጋ ውስጥም እየሳቀ ግፋ በለው ስትል ተስፋ እየሰጠች ሆድ የምታባብል ትንሽ እያሳየች ልብ የምታማልል ከዚያኛው ቀምታ ለዚኛው መስጠትን ደርሶ ማደላደል ሁሉን የታካነች ሂወት እንደዚ ነች ሂወት እንዳሻት ነች አዎ በትክክል ቃሉን እመንበት በሰጠችህ ዛባያ ሳታቆም ዙርበት ከቶ አታፈግፍግ ጀርባህን ግረፊኝ ብለህ አታሳያት ጀግነህ ቁምና ከፊት ተጋፈጣት ክፉውን ካልወጣህ ደግን ላታገኘው ጠንክር ወንድም አለም አይዞኝ እህት አለም በርችልኝ እናቴ በል ግፋው አባቴ ግርፋቷን ፈርቶ ከሩቅ ለሚሸሻት ገፍታ ብትጥለው ወድቆ ለቀረላት ቦታ እንኳ የሌላት…………… ሂወት እንደዚ ናት ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• አወይ መሸታ ቤት #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ደስ ያለው የደስታ እያለ ሲጋብዝ ያዘንው ብቻውን ጠጥቶ ሲተክዝ ሞቅ ያለው ሲጨፍር ተነስቶ በሆታ የበቃው ሲወጣ ባሳር በጉተታ ሌላው ሲበሻሸቅ ቃል እየሸጎጠ ለቤቱ አዝማሪ ግጥም እየሰጠ ሆድ ያባው በብቅል ጉዱን ሲዘረግፍ ዝም ያለው ለወሬ ጆሮን ሲያሰፈስፍ እከሌ እንዲ ሆነ ሀገር እንዲ ሆነች ዜናው እንዲህ አወራ ሲባል በመሸታው ጨዋታው ሲደራ ያየው የሰማውን ለጠጪው ሲነግር ሁሉም ከየአፉ ያለውን ሲገብር ልክ ነው አይደለም ሲጧጧፍ ክርክር ከየፓለቲካ አያሌው ሲቃመስ ደግፍ አትደግፍ ጎራው ሲወቃቀስ ሃሜቱ እንደጉድ እንደ ውሃ ሲፈስ ቂም የተያያዘ ነገር ሲመዛመዝ ቅስሙን የተነካ ለዱላ ሲጋበዝ አሳላፊ ሲባል መጠጡ ሲቀዳ ገሚስ አይኑን ሲጥል ሲከጅል ኮረዳ ተቀበል ሲባባል በጭብጨባ ሲያመሽ እጅ ይዞ ተነሱ ትከሻ ሲፈተሽ ለጉድ መንበሻበሽ ለጉድ መረባበሽ የሞላበት ቅኔ ከየዘርፉ ያዘለ አወይ መሸታ ቤት ምን ያማይወራ የማይታይ አለ ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• እረፍት ያጡ ነብሶች #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ገዳይ ሲሞላለት ካራ ተሸክሞ በበልፅግ ባይ አቻው ነፃነት ቢሰጠው እግር እጁን ስሞ ሸፍጥ ሲያቀጣጥል ባልታጠቀ ምስኪን ታጥቆ ሲያውደለድል መስዋት ሲያረገን ሲያስመታን ቸነፈር ታርደን ስንበሰብስ አማን ካጣው መንደር ሰምተው እንዳልሰሙ ሳያሻቸው ማዘን አወይ ባለተራ ባለጊዜ መሆን ቀባሪ እያሳጡን ዘውትር ቢበድሉን በዝሆን ጆሮዋቸው ዝንብ እያስመሰሉን ድረሱልን ብንል ቆመው አስገደሉን አወቸው መከራ ያልተገራው ጨቅላ ሲመዘን ከስሩ ደም ያበለፅጋል ሆኑዋል መፈክሩ #እግዚአብሄር_ይፈርዳል! ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
• የአባይ ዳር ፍቅር #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ከአባይ ፏፏቴ እግድም ዳር ቤቷ ታጫውት የለም ወይ ያቺ ልጅ ካንጀቷ ስቃ ስታስቀኝ ሳቋን ብውድላት የታደማት አይኔ ቀልቤ ሸፈተላት ፍቅሯን ስታወጋኝ በአባይ ዳር ጨዋታ ውስጤን ስታሞቀው በከንፈር ሰላምታ የወንዙ መግነጢስ እያስተሳሰረን በሰመመን መንፈስ ስሎ ሲሰውረን በመውደድ ወላፈን ሀሴት ስንፈጥም ቃል ስንገባባ ልባችን ሲገጥም ኧረግ አባይ ፈካ ፍቅር ስናጣጥም ሳንተያይ ውሎ መሽቶ እዳይነጋ ፎጣዬን ለብሼ ስበር ወራጁጋ ቆማ አገኛታለው ጥለቷን ጣል አርጋ ከእቅፌ ገብታ በራ ስትሸጎጥ ራስ ይላል ናፍቆቴ ያቃጠለኝ ረመጥ ያቺ ልጅ ላንድ ቀን ያልመጣች እንደሆን ጭንቀት በሆዴ ላይ ብሶት ያሳርፋል ልቤም አይችልልኝ አባይም ያኮርፋል ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.