cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የእኛ መዝሙር ጥናት

ስምሽ ጉልበት አለው ጨካኙን ያራራል ስለእማምላክ ብሎ ደሀም ጠግቦ ያድራል...💚💛💖

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
1 201
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#ከንቱ_ነኝ ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ #አዝ እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ በመጨረሻውም በሞት ተወሰድኩኝ (2) #አዝ ከጣይቱ በታች አዲስ ነገር የለም ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ (2) #አዝ ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ አፈር ተጭኗቸው በመቃብር አሉ እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው (2) #አዝ ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩት አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረት ነኝ (2) #አዝ ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር (2) ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ @mazemur @mazemur @mazemur
نمایش همه...
ዝማሬ_ዳዊት_ከንቱ_ነኝ_የከንቱ_ከንቱ_ነኝ_16k.m4a7.19 KB
#እሮብ... በማቴዎስና በማርቆስ መሠረት በዚህ ዕለት ሶስት ነገሮች ተደርገዋል ። እነርሱም :- 1. የካህናት አለቆችን ጸሐፊዎች የሕዝብ ሽማግሌዎች ላይ ተማክረዋል ። 2. ጌታ በለምጻሙ ስምኦን ቤት ተገኝቶ አንዲት ሴት ሽቶ ቀብተዋለች 3. ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ለመስጠት ወደ ካህናት ሄዶ ሲማከር ሠላሳ ብር መዝነዉለታል ። በአይሁድ ዘንድ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሸንጎ ነበር ። ይህም ሸንጎ ሲንሃድሪየም ይባላል ። አብዛኞቹ ሰድቃዉያን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ጻፎችና ፈሪሳዉያን ነበሩ ። እነሱም ቀያፋ በሚባለዉ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰብስበዉ እየሱስ ክርስቶስን በተንኮል አስይዘዉ እንዴት እንደሚገድሉት ተማከሩ ።ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ይሁዳ ይህን ባወቀ ጊዜ የገንዘብ ፍቅር ስለሚያጠቃዉ እና ከረጢት ይዞ በዉስጡ ከሚገባዉ እየሰረቀ የሚወስድ ሌባ ስለነበር ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄዶ ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁኝ በማለት ጌታን በገንዘብ ለመለወጥ ተዋዋለ ።ይሁዳ ይህን ያደረገዉ ጌታ በለምጻሙ ስምኦን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋዉ ዉድ በሆነ በአልባስጥሮስ ሽቶ ከቀባችሁ በኋላ ነበር ። ያን ጊዜ ገንዘቡን ለእራሱ ሊወስድ አስቦ በድሆች በማሳበብ ይህ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር ብሎ ነበር ። ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄዶ በሠላሳ ብር አሳልፎ ለመስጠት ተዋዋለ ። ይህ ታሪክ በሶስቱ ወንጌላት ዉስጥ በሚከተሉት ጥቅሶች ተመዝግቧል ። 1. ማቴ.26፥3-16 2. ማር .14፥1-11 3. ሉቃ.22፥1-6 በዚሁ ዕለት በቤተክርስቲያን በየሰዓቱ የሚሰበከዉ ምስባክ :- - በአንድ ሰዓት ( መዝ . 83፥5-6 ) - በሶስት ሰዓት ( መዝ . 41፥5-7 ) - በስድስት ሰዓት ( መዝ. 41፥5-6 ) - በዘጠኝ ሰዓት ( መዝ . 83፥2-3 ) - በአስራ አንድ ሰዓት ( መዝ . 6፥2-3 ) ምክረ አይሁድ እሮብ የእንባ ቀን ጌታዬ አባቴ አይሁድ አንተን ሊሰቅሉ ተማክረዉ ጨረሱ ! ማርያም እንተ እፍረተ መጣች ሽቶ ይዛ በእራስህ ላይ አርከፍክፋ ይቅርታ ልታገኝ የኔ ጌታ ! አነባች በብዙ ይቅርታህ ደረሳት ቸር ነህና የኔ ጌታ ! የምህረት የፈዉስ ቀን አድርግልን ! አሜን ፫ ዉለታህን የማይረሳ ልብና ህሊና ስጠን !!! አሜን ፫
نمایش همه...
(ሕማማት ማክሰኞ ሰሞነ ህማማት) 📖 የማቴዎስ ወንጌል 21: 23÷32. 23፤ ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና። በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት። 24፤ ኢየሱስም መልሶ። እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤ 25፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ። ከሰማይ ብንል። እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤ 26፤ ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ። 27፤ ለኢየሱስም መልሰው። አናውቅም አሉት። እርሱም ደግሞ። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው። 28፤ ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ። ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ አለው። 29፤ እርሱም መልሶ። አልወድም አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ። 30፤ ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ። እሺ ጌታዬ አለ፤ ነገር ግን አልሄደም። 31፤ ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው? ፊተኛው አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል። 32፤ ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፥ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም። 🔴የሰሞነ ሕማማት ማስታወሻ:- ይህ ቀን (ማክሰኞ) የጥያቄ እና መልስ ቀን ይባላል ምክንያቱም በዚህ ቀን ጌታችን ከካህናት አለቆች: ከፈሪሳውያንም: ከሰዱቃውያንን: እንዲሁም ከሄሮድስ ወገን የተላያዩ መንፈሳዊ (ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት) እና ፖለቲካዊ (ከመንግስት ጋር ጋር ለማጋጨት) ጥያቄዎች ቀርበውለታል ግን እንዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ጌታችን እንደ አመጣጡ መልስ ሠጥቷል:: ከጌታችንም መልስ የተነሣ ምንም እንኳን ሶስት አመት ከሶስት ወር እየተከተሉ ጥያቄ ቢያቀርቡም በዛሬው እለት ግን የመጨረሻ የጥያቄ ቀን ነበር:: "ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" ማቴ 22:46 እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ሰዎች እኛን ክፉ ለማናገር ወይም ለመፈታተን ለሚያቀርቡልን ጥያቄው ሁሉ መልሳችንን በመንፈሳዊ እና በጥበብ መሆን አለበት:: መፅሔት ቅዱስ ስለ ንግግር እንዲህ ይላል:: "ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።" የማቴዎስ 12:37 "ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።" ቆላስይስ 4:5÷6
نمایش همه...
💦💦💦💦ሰኞ....💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦.. በሆሳህና ማግስት ሰኞ በድጋሜ ከቢታኒያ ወደ እየሩሳሌም ገብቷል። እሁድ የሆሳህና ዕለት ጊዜዉ መሽቶ ስለነበር በማግስቱ ሰኞ ከቢታኒያ ወደ እየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል ። እነሱም:- 1.ቅጠል ብቻ ሆና ፍሬ ያላገኘባት ዕፀ በለስ ረግሟታል ። 2. ወደ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለዉጡትን አስወጥቷል ። ማቴ 21፥19 ማር 11፥12-19 ለቃ 19 ፥ 45-46 በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን የሚሰበከዉ ምስባክ :- 1.በአንድ ሰዓት መዝ.72 ፥ 18-19 2 . በሶስት ሰዓት መዝ. 122 ፥ 1-2 3. በስድስት ሰዓት መዝ. 122 ፥ 4-5 4 . በዘጠኝ ሰዓት መዝ. 65 ፥ 5-6 5. በአስራ አንድ ሰዓት መዝ. 13 ፥2-3 ክርስቲያን ሆይ ? በቤተክርስቲያናችን ይህ ሰኞ የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነዉ ። ዛሬ ቢሆን ጌታችን ወደ እኛ ሕይወት ቢመጣ የሚገኘዉ ምንድን ነዉ ? ፍሬ ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ ሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል ። (ማቴ 3፥8) ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገዉን የመንፈስ ፍሬ ይዘን ልንገኝ ይገባናል ።(ገላ. 5፥ 22) እንዲህ ከሆነ ይባርከናል እንጅ አይረግመንም ። ክርስትናዊ ሕይወት ፈተና ፈርተዉ የሚሸሹበት ሳይሆን በፈተና ዉስጥ አልፈዉ ለክብር የሚበቁበት ሕይወት ነዉ፤ ዕያ 1፥ 12 ክርስቲያን ማለት ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ የሚያደርግ ነዉ፤ ክርስቲያን ማለት ሰዉ በጠፋበት ዘመን ሰዉ ሆኖ የሚገኝ ነዉ ኢሳ 6 ፥8 ፈጣሪ ሆይ የእናታችን የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ፍሬ የሚገኝብንና የፍሬ ሰወች አድርገን አሜን አሜን አሜን በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡- በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ #ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ #እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው #ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ #ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው #ትስቡጣ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው #አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
نمایش همه...
#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸ_ሥርዓቶች 1, #ስግደት :- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። 2, #ጸሎት :- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው። በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። 3, #ጾም :- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል። 4, #አለመሳሳም :- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 5. #አክፍሎት :- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው። 6, #ጉልባን :- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው። 7, #ጥብጠባ :- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው። 8, #ቄጠማ :- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
نمایش همه...
Ethiopian_orthodox_tewahedo_mezmur_by_Dn._Mindaye.m4a4.40 MB
ጽርሐ አርያም ጽርሐ አርያም/4/ ክብርሽ ገናና ነው ለዘለአለም አዝ በመላእክት ዓለም በሶስቱ ከተማ በኤረር በኢዮር እንዲሁም በራማ ውዳሴ ቀረበ ለሰማይ ንግስት የአምላክን እናት በክብር አየናት አዝ በበረሀ ያሉ አለምን የናቁ ውዳሴሽን ደግመው ስምሽን የሰነቁ አንቺን ስንጠራ ጠላት ገለል ይላል ማርያም በግርማሽ ከሳሻችን ያፍራል አዝ ከእግሮቿ በታች ጨረቃን ተጫምታ የክብርን አክሊል በራሶቿ ደፍታ በቅዱሳን ሁሉ ትመሰገናለች አለም የዳነባት ድንግል ማርያም ነች አዝ ብርሃንን ለብሳ በንጽህና አጊጣ ፍጥረትን ስትባርክ በክብር ተገልጣ ነፍሳት ተቀደሱ በእምነት ከበዋት ከበሮን አንስተን እንዘምርላት @mazemur @mazemur @mazemur
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.