cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርት⛪

ይህ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓት እና ደንብ የተከተለ ሃማኖታዊ መልእክት እሚተላለፍበት ነው ሃይማኖት እንደ አባቶቻችን ቴክኖሎጂ እንደዘመናችን! ቴክኖሎጂ ተጠቅመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ ክ ሃብቶችን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ " የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን 🌺 @Oretodokes_temeherete 🌺

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
382
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
የቦታ ለውጥ
نمایش همه...
ጎፋ ገብርኤል ነው የቦታ ለውጥ ተደርጓል።
نمایش همه...
00:30
Video unavailableShow in Telegram
መስቀልን ከንግሥት ዕሌኒ ጋር ያክብሩ
نمایش همه...
4.54 MB
★ ኢትዮጵያ ሰላም እንዳታገኝ መርዝ እየረጨ ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ነው።★ ★ የ 8ኛ ክፍል ሥነ ጥበባት መጽሐፍ በአስቸኳይ ይወገድ!! ★ ትውልዱ በጥላቻና በቂም በቀል አዕምሮው እንዲበከል የሚያደርጉ መጻሕፍት ተሰብስበው ይቃጠሉ !! ★ ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው የማይበርድ እሳት የሚነሳው በተለይም በኦ*ሮ*ሚያ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎች በየጊዜው በአሰቃቂ ግድያ እየተጨፈጨፋ የሚሞቱት ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የተሰገሰጉ የዲያብሎስ ፈረስ የሆኑ ሠራተኞች ከበላይ አለቆቻቸው በሚታዘዙት መመሪያ መሠረት በትውልዱ አዕምሮ ውስጥ ክፋ የጥላቻ መርዝ በየትምህርት መጻሕፍቱ ስለሚረጩ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር በአስቸኳይ እንዲህ ዓይነት ትውልድ ገዳይ ሰዎችን ያንሳ አሊያ ትምህርት ሚኒስቴር ራሱ የሚመጥነው ሰው እስኪመጣ ይዘጋ። የሌላው ዓላም ትውልድ በዕውቀት ተራቆ በሚደንቅ ፍጥነት መጥቆ ሄዷል፣የሌላው ሃገር ወጣቶች በልዩ ልዩ አዳዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀት አዕምሯቸው በልጽጎ የሃገራቸውን ኢኮነሚ በብዙ እጥፍ አሳድገው ደስተኛ ሕይወት እየኖሩ ባሉበት በዚህ በሰለጠነ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከ200 ዓመት በፊት ስለ ነበረ ታሪክ በውሸት ትርክት መርዘው የዛሬው ትውልድ እንደ አዲስ በቂም በቀል እንዲያስብና እንዲገዳደል እያደረጉ ትውልዱን በድንቁርና ጨለማ እየነዱት ነው። እጅግ የሚያሳዝነው በኦ*ሮ*ሚያ ክልል ሥልጣን ላይ ያሉ ደናቁርት ባለ ሥልጣን ተብዬዎች የእነርሱን ዕድሜ በጨለምተኝነት ጨርሰው አዲሱ ትውልድም የእነርሱን ርካሽ አመለካከት ይዞ እንዲያድግ የወጣቱን አዕምሮ የሚያቆሽሽ የውሸት ትርክታቸውን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በመላው የኢትዮጵያ ልጆች ላይ በየመጻሕፍቱ እየጫኑባቸው ይገኛል። ስለዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ አጥብቀህ ተቃወም ልጆችህ የዕውቀት ብርሃን ይዘው እያደጉ ሳይሆን ጥላቻና ቂምበቀልን በውስጣቸው ይዘው እንዲያድጉ እየተደረገ ስለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነዚህን መጻሕፍት አጥብቆ ይቃወም መጻሕፍቱንም እየሰበሰባችሁ አቃጥሉ።ሃገር ከምትቃጠል ትውልድ ከሚበላሽ የጨለምተኞች ዕቅድ ይፍረስ። መ/ር ታሪኩ አበራ እባካችሁ ሼር በማድረግ ለሕዝብ አድርሱ።ሃገር እንታደግ !! በየጉሩፑም ለጥፋት ★ ይህንን ፔጅ ላይክና ፎሎው አድርጉ ጠቃሚ ትምህርትና መረጃ ታገኙበታላችሁ።★ የቴሌግራም ቻናሌ ቤተሰብም ይሁኑ። ኦርቶዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት https://t.me/TarikuAbera
نمایش همه...
Tariku Abera

ኦርቶዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት

★ ትምህርት ሚንስቴር ትውልድ እየገደለ ነው።★ ★ እናንተ ባርነት ናፋቂዎች ሉዓላዊቷን ሃገር አታዋርዱ!! ★የግዕዝ ቁጥር ከግሪክ ቁጥር የተወረሰ አይደለም!! ★ የእናንተ መደንቆር ሳያንስ ትውልዱን የዕውቀት ድሃ አታድርጉት!! ★ ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የተሰገሰጉ ጸረ ኦርቶዶክስ ሠራተኞች የተጣለባቸውን ሃገራዊ ኃላፊነት ወደ ጎን ጥለው በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ያላቸውን ርካሽ ጥላቻ ለማሳየት የተበላሸ የሐሰት ታሪክ ጽፈው በማሰራጨት ትውልድ እየገደሉ ነው። ይህ በደናቁርት የተዘጋጀ መጽሐፍ ባስቸኳይ ታርሞ እንደገና ይታተም የተሰራጨውም መጽሐፍ ከያለበት ይሰብሰብ።የግዕዝ ቁጥር ጥንታዊ የሆነ የኢትዮጵያውያን ቀመር መቁጠሪያ እንጂ ሃይማኖት አይደለም።ሃይማኖትና ቋንቋ ለዩ፤ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ግዕዝ ኢትዮጵያዊ ቋንቋ በመሆኑ ታሪክን በክብር ጠብቃ ለትውልድ እያስተላለፈች ያለች ታላቅ የሃገር ባላደራ ነች።በዚህ ልትከበር ይገባታል።★ የግዕዝ ፊደላትና የግዕዝ ቁጥሮች የኢትዮጵያ ብቸኛ መለያ የሆኑ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች ናቸው።ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ብራና ዳምጠው ፣ቀለም በጥብጠው፣ብዕር ቀርጸው ኢትዮጵያዊ የሆነ ፊደልና ቁጥር በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ቀርጸው ለሃገር አበርክተዋል።ይህንን ታላቅ ሃገራዊ ቅርስ ከግሪክ የተወረሰ ነው ብሎ ማስተማር እጅግ የሚያሳፍር የአስተሳሰብ ዝቅጠት ነው። ሌላው ዓለም በቅኝ ግዛት ሲያዝ የቀኝ ገዢዎቹን ቋንቋ፣ቁጥር ፣የቀን መቁጠሪያ፣ባህልና እምነት ሳይቀር ሳይወድ በግዱ እንዲቀበል ተደርጎ ስለ ተጫነበት ዛሬ ድረስ አብዛኛው የዓለማችን ክፍል በቀኝ ገዢዎቻቸው ፊደልና ቁጥር ይጠቀማሉ ኢትዮጵያ ግን ማንም ቀኝ ያልገዛት ሉዓላዊት ሃገር በመሆኗ የራሷ ቀን መቁጠሪያ ፣የራሷ ፊደልና ቁጥር ይዛ እስከዛሬ ለዘመናት በነጻነት አለች።አለመታደል ሆኖ ግን ባርነት ናፋቂዎች ዛሬ በየቦታው ተሰግስገው የእነርሱን የመንፈስ ባርነት ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ እየተንፈራገጡ ነውና አጥብቀን እንቃወማቸዋለን። ስለዚህም ትምህርት ሚኒስቴር በአስቸኳይ የአራተኛ ክፍል የሂሳብ መማሪያ መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን ሐሰተኛ ትርክት ያስወግድ።ትውልድ እንዳይበላሽም የተበተነው መጻሐፍ በሙሉ ይሰብሰብ ። ትምህርት ሚኒስቴር እንዲህ ዓይነት የውሸት ትርክቶችን እየጻፈ ትውልድ ሲበክል ይሄ የመጀመሪያው አይደለም ከዚህ በፊትም ሌላ የውሸት ታሪክ ፈጥሮ ሲያሳትም ተቃውመናል አሁንም ይሄ ብልሹ አሰራር በአስቸኳይ ይቁም። መ/ር ታሪኩ አበራ እባካችሁ ሼር በማድረግ ለሕዝብ አድርሱ ወላጆች ልጆቻችሁ እንዳይበከሉ ታላላቆች ታናናሾቻችሁ እንዳይባላሹ ይህንን ገጽ ቀዳችሁ ጣሉ።
نمایش همه...
★ ጨዋታ መስሏችሁ በጥንቆላ ወጥመድ እንዳትያዙ ተጠንቀቁ !! ★ ★ እባብና እንቁላል ለጥንቆላ የሚጠቀሙባቸው መገልጋያዎቻቸው ናቸው።★ ወገኖች በጣም አስተውሉ ሰይጣን እጅግ በረቀቀና ዘመናዊ በሚመስል መንገድ ጥንቆላን ለትውልዱ እያለማመድ ነው። በጥንት ግሪካውያንና የግብፅ ጣዖት አምላኪዎች ዘንድ የእባብና የእንቁላል ምስል ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው የጥበብ፣የዕውቀት፣የፍልስፍና መንፈስ መገኛ ብለው የሚያመልኩትን ባዕድ አምላክ የሚወክሉበት ምልክታቸው ነው። በሕንድ የዝሆንና የላም ምስል ፣በአውሮፓ የንሥር ምስል በከፍተኛ ደረጃ ክብር የሚሰጣቸው ከጥንት ባዕድ አምልኮ ጋር ተያያዥ የሆኑ ትውፊታዊ ውርሶቻቸው እንደሆነ ሁሉ የእባብና የእንቁላል ምስልም በግሪክና በግብፅ ጠንቋዮች ዘንድ ትልቅ ሥፍራ ያላቸው የሰዎችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንተነብያለን እያሉ በአጋንንት መንፈስ በመመራት የሚጠነቁሉበት መጠቀሚያቸው ነው። አሁን ጊዜው እየዘመነ ስለመጣ ይህንን የጥንቆላ አሰራር በሞባይል አፕልኬሽን ላይ በመጠቀም ሰዎች ወደ ጠንቋይና አስጠንቋይ ልምምድ ውስጥ በቀላሉ እንዲገቡ እየተጠቀሙበት ስለሆኑ ክርስቲያኖች ከዚህ የሰይጣን ወጥመድ ራሳችሁን አርቁ።ዛሬ እንደ ቀላል ነገር የምትገቡበት የጥንቆላ ወጥመድ ወደ ፊት አዕምሯችሁን በእነርሱ ቁጥጥር ሥር የሚያደርጉበት ሌሎችንም ተመሳሳይ ወጥመዶች እየለቀቁ ስለሚቆጣጠሯችሁ መውጫው ጭንቅ ነው የሚሆንባችሁ። የጥንቆላው ዘዴ ስለ እያንዳንዱ ሰው ባህሪና የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚተነብዩ በመምሰል የእነርሱ ሐሳብ ተገዥ ካደረጉ በኋላ ቀስበቀስ ከእግዚአብሔር አምልኮና እንደ ጌታ ፈቃድ ይሁን እያልን በጸሎት የምንኖረውን ክርስቲያናዊ ሕይወት ያስለቅቁንና በእነርሱ ሰይጣናዊ አሰራር ውስጥ በመክተት ዕድል ፈንታችንን፣የትዳራችንን ጉዳይ፣ስለ ትምህርታችን፣ስለ ንግዳችን፣ስለ ጤናችን ወዘተ እነርሱን እየጠየቅን እንድንኖር በማድረግ የእርኩስ መንፈስ እስረኞች ያደርጉናል። ስለዚህ ክርስቲያኖች ንቁ !ንቁ! ተጠንቀቁ ! ራቁ ! አዕምሮና ልባችሁን ከሰይጣን ወጥመድ ጠብቁ። "መንፈሳዊ፡ሰው፡ግን፡ዅሉን፡ይመረምራል፡ራሱ፡ግን፡በማንም፡አይመረመርም።" 1ቆሮ 7 ፥ 15 መ/ር ታሪኩ አበራ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ሕዝባችንን እንጠብቅ። ★ Orphic Egg ★ Symbol of life and creativity The Orphic Egg is an ancient Greek symbol. It is an egg with a serpent wrapped around it. This egg represents the cosmic egg from which Phanes, a diety, was birthed. Phanes was the diety of procreation and life. Orpheus was a famous singer from Greek myth. He sang the Cerubus to sleep so he could pass through Hades and rescue his wife. Phanes was created from the Orphic Egg. Phanes was a hermaphrodite, male/female, deity of light and goodness. He was one of the first gods born of the watery abyss of time. He in turn created the other gods. The egg and snake represent the cosmos circled by the creative spirit.
نمایش همه...
ዕንቋ በዳኅና ወበሰላም እም ዘመነ ማርቆስ ኀበ ዘመነ ሉቃስ አብጽአነ አብጻእክሙ (አብጻእክን) ዘመኑ ዘሰላም ዘፍቅር ወዘ ተዋሕዶ ይኲን ለነ ይኲን ለክሙ ( ለክን) እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ዘመኑ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት ይሁንልን ይሁንላችሁ እንኳን ከዘመን ዘመን አሽጋገረን አዲሱ ዓመት አሮጌው ማንነታችን የሚወገድበት ለመንፈሳዊ አገልግሎት እራሳችንን አሳልፈን የምንሰጥበት የተጣላን ፍጹም የምንታረቅበት ይቅርታ የምናደርግበት ይቅርታ የምንቀበልበት በእውነተኛ መዋደድ የምንዋደድበት እንዲሆን እራሳችንን እንመልከት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል ወዳጆቼ????? #እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን #ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ #እግብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና #እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን #በጐ_ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ #ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም #የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ አወርቅ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.