cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከሱና ገፆች📚⭐

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
178
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው? ~~~~~~~~~~~ የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:– (إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ) "ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባ: 60] መጠነኛ ማብራሪያ ① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል። ② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም። ③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል። ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም። ④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው። አንደኛ፡- ካፊር ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው። – ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣ – የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው። – በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ – በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290] ⑤ እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው። የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል። ⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል። በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል። ⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል። ⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል። https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ቻናሉን ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። መልእክቱን ለሌሎች በማሰራጨት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።

⚠️ ተጠንቀቅ ⚠️ አንተ ጾመህ ፣ ሰግደህ ፣ ቁርዓን አኽትመክ ፣ ዚክር አድርገህ ፣ ሰደቃ አውጥተህ ፣ የሰዎችን ሀጃ ፈፅመህ ደክመህ የሰበሰብከውን አጅር ሌላው ምንም ሳይሰራ ዘና ብሎ አጅርህን ይወስድብሃል። 👉 ሀሜት ⛔️ Copy https://t.me/fromsunahhpages/56
نمایش همه...
ከሱና ገፆች📚⭐

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ይላሉ:– "አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ከሰለፍ ዑለማዎች አንዱ እንዲሂ ይላል "የዱንያን አገር ተጠንቀቋት ከሀሩትና ማሩት የባሰች ድግምተኛ ናት ሀሩትና ማሩት በድግምታቸው ባልና ሚስትን ነበር የሚለያዩት ድንያ ግን በአላህና በባሪያው መካከል ነው የምትለያየው " ተስሊየቱ አህሉል መሳኢብ ( 1/248) @AbuReslan5851
نمایش همه...
👉 በረመዳን መሞት ብዙ ሰዎች በረመዳን ወይም በጁሙዓ ወይም የዐረፋ ቀን መሞት ለየት ያለ ምንዳ እንዳለው ያስባሉ ። ይህ ስሕተት ነው ። በረመዳንም ሆነ በጁሙዐ ወይም የዐረፋ ቀን ወይም በሙሐረም አስረኛ ቀን ወይም በማንኛውም ቀን የሞተ ሰው ለየት ያለ አጅር የለውም ። በዚህ ዙሪያ የመጡ ሐዲሶች ደዒፎች ናቸው ። ማንም በየትኛውም ቀን ወይም ወር ስለሞተ ምንም የተለየ ምንዳ አያገኝም ። ነገር ግን አንድ ሰው በመልካም ስራ ላይ ሆኖ ቢሞት ወይም መልካም ስራ ሰርቶ እንደጨረሰ ቢሞት ከአላህ ይከጀልለታል ። ለምሳሌ ሐጅ ስራ ላይ ፣ ፆም ላይ ፣ሶላት ላይ ፣ ቁርኣን በመቅራት ላይ ፣ ዚክር ላይ ወይም እነዚህንና ሌሎችም መልካም ስራዎችን እየሰራ ወይም ሰርቶ እንደጨረሰ ቢሞት ከአላህ ይከጀልለታል የሑስነል ኻቲማ ምልክት ነው ይባላል ። ከዚህ ውጪ በዚህን ቀን ወይም በዚህ ወር የሞተ የጀነት ነው የሚል ትክክለኛ መረጃ የለም ። ከሰልማነል ፋርስ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – " ረመዳን አጥሏችኃል መጀመሪያው እዝነት መካከለኛው ምህረት መጨረሻው ከእሳት ነጃ መውጣት " ብለዋል ተብሎ የሚወራው ሐዲስ ደዒፍ ነው ። እንዲሁም በረመዳን አንድ ሱና እንደ ፈርድ ፈርዱ ደግሞ እንደ ሰባ ፈርድ ነው የሚለውም ደዒፍ ነው ። እንደነዚህ አይነት ሐዲሶች ብዙ ዳአዕዋ ላይ እንዲሁም ኹጥባ ላይ ይሰማሉ ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ውድቅ ናቸው ። በሜምበር ላይ የተወራ ሁሉ ትክክል አይደለምና ማጣራት ግድ ይላል ። በመሆኑም በመልካም ስራ ላይ የሞተ ከአላህ ይከጀልለታል ነው የሚባለው እንጂ ከዚህ ውጪ ለማነም በጀነት መመስከር አይቻልም ። አላህ ባወቅነው ተጠቃሚ ያድርገን ። ማሳሰቢያ : ከዚህ ቻናል ላይ ሊኩን አጥፍቶ መልእክቱን ወደ ራስ ጉሩፕ ወይም ቻናል ሼር ማድረግ አይፈቀድም ። http://t.me/bahruteka
نمایش همه...
☪ ሁለት ዊትር በአንድ ለሊት ተራዊሕ የሚሰግዱ ሰዎች መልሰው ተሃጁድ ለመስገድ ቢፈልጉ ምን ማድረግ አለባቸው ? ተራዊሕ የሚሰግድ ሰው ኢማሙ እስከሚጨርስ ድረስ አብሮ መስገዱ የተወደደ ነው ። ሐዲሱ የመጣው ከኢማሙ ጋር እስከሚጨርስ አብሮ የቆመ ( የሰገደ ) በሚል ስለሆነ ይህ ማለት ደግሞ ዊትርን ጨምሮ ማለት ነው ። በሌላ ዘገባ ደግሞ የሌሊት ሶላት መጨረሻ ዊትር አድርጉ በሚል መጥቷል ። ስለዚህ አንድ ሰው ተራዊሕ እስከመጨረሻው ሰግዶ መልሶ ተሃጁድ ለመስገድ ቢፈልግ ማድረግ ያለበት ተራዊሕ ላይ ኢማሙ ዊትር አሰግዶ ጨርሶ ሲያሰላምት እሱ ተነስቶ አነድ ረካዓ ጨምሮ ሁለት ወይም አራት በማድረግ እንደ ኢማሙ አጨራረስ ማለትም ሶስት አንድ ላይ ከሰገደ አራት በማድረግ አንድ ረካዓ ከሰገደ ሁለት በማድረግ ሙሉ አድርጎ በማሰላመት ለተሃጁድ ክፍት አድርጎ ተሃጁድ ላይ የገራለትን ሰግዶ ዊትር በመስገድ መጨረስ ይችላል ። ይህ የሚሆነው በአንድ ለሊት ሁለት ዊትር ስለሌለ ነው ። አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ። http://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 ቀኑ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ፆም አንዳንድ ሀገሮች በክረምትና በጋ ቀንና ለሊታቸው ይለያያል ቀኑ 21 ሰኣት ሆኖ ለሊታቸው 3 ሰኣት የሆኑ አሉ አንዳንዶች ረዝመቱ ከዚህ ቢያንስም ግን ከለሊቱ በጣም ይለያያል ሌሎች ደግሞ 6 ወር ቀን 6 ወር ለሊት የሚሆኑባቸው አሉ እነዚህን ሀገሮች በተመለከተ የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ የሚከተለውን ፈትዋ ሰጥቷል ቀኑ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ላይ የሚኖሩ ሙስሊሞች ፈጅር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ፀሀይ እስከ ምትገባ መፆም አለባቸው አንድ ሰው ፆሙ ከብዶት ከአቅሙ በላይ ከሆነ አፍጥሮ በሌላ ጊዜ ቀዳእ ያወጣል ለሊቱ ረዝሞ ቀኑ ቢያጥርም ያው ነው በቀኑ ልክ መፆም ለ6 ወር ቀኑና ረሊቱ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ሙስሊምቹ በ24 ሰኣት እያሰቡ ሶላታቸውን ማለትም በ24 ሰኣት ውስጥ አምስት ጊዜ መስገድ ይኖርባቸዋል እያንዳንዱ ሶላት ጊዜውን ጠብቆ ለመስገድ ከተቻለ ቅርብ ሆነው ፀሀይ እየወጣ ከሚገባባቸው ሀገሮች በመውሰድ ወደ ሰኣት ቀይሮ መወሰን ፆሙንም በተመለከተ እንደዚሁ የፈጅር መውጫና የፀሀይ መግቢያ ጊዜውን በመወሰን መፆምና ማፍጠር አለባቸው የሚል ነው :: http://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🚩የእውነት የሚወድህ ማነው❓ 🎙ሸኽ ሙሀመድ ቢን ሀዲ አልመድኸሊ እንዲህ ይላሉ 🔶በሚያስተነትን ሰው ላይ ሁሉ የመንድሙን ምክር - ምክር ባቀረበለት ግዜ - ሊቀበል ይገባል። ስህተቱን ባሳየውና በገለፀለት፣ በማስረጃ ባብራራለት ግዜ ሊቀበል ይገባል። 👉🏼ሲመክሩት ሊኩራራ አይገባም። በወንጀል ላይ ኩራት ሊይዘው ከቶ አይገባም። 🌱ልክ ለዚህኛው (ለመካሪው) ወንድሙ ሲሳሳት አይቶ በዝምታ ማለፍ እንደማይፈቀድለት ሁሉ! 👉🏼የእውነት የሚወድህ የሚመክርህ ነው! ⁉ለምን? ✳በዲንም ሆነ በዱንያ ጉዳይ ለራሱ የወደደውን ላንተም ስለወደደልህ! ለራሱ የጠላውን ላንተም ስለጠላልህ (እውነተኛ ወዳጅህ ነው)። 📚ሸርሁል_ኢባነቲ_ሱጝራ/ ደርስ 03
نمایش همه...
🍁የተከታይ መብዛት የሀቅ መንገድ ላይ መሆንን አያሳይም 🎓ታላቁ ሸኽ ሙቅቢል ቢን ሀዲ አልዋዲዒ እንዲህ ይላሉ 👉🏼ብዛት የሀቅም ሆነ የስህተት መለኪያ አይደለችም። 💐የሀቅም ሆነ የስህተት መመዘኛው የአላህ ኪታብ እና የመልእክተኛው ﷺ ሱና ነው። (ጛረቱል አሽሪጣ 1/166) https://t.me/fromsunahhpages/56
نمایش همه...
ከሱና ገፆች📚⭐

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ይላሉ:– "አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

Ꙭ ነፃ መውጫ መንገዶች ❗ 🍁ሰህል ኢብኑ ዐብደላህ እንዲህ ይላል:- ✋🏼ነፃ መውጫ (ዘዴዎች) በሶስት ነገሮች ውስጥ ናቸው! 👉🏼ሀላል በመመገብ 👉🏼ግዴታ (ፈርድ) ተግባሮችን በመተግበርና 👉🏼በነብዩ ፈለግ በመመራት!! 📚ተፍሲሩል ቁርጡቢ (2/208) •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈• join👇 https://t.me/fromsunahhpages/56
نمایش همه...
ከሱና ገፆች📚⭐

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ይላሉ:– "አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

🔷 ኢማሙ ማሊክ - ረሒመሁላሁ - እንዲህ ይላሉ :- " ሱና የኑሕ መርከብ ናት በሷ የተሳፈረ ሰው ይድናል ወደ ኀላ የቀረ ግን ይሰምጣል " ⬅ ️يقول الإمام مالك بن أنس رحمه الله تعالى : " السنة سفينة نوح من ركبها نجا ومن تخلف عنها غرق " تاريخ دمشق لابن عساكر 9/14 ታሪኹ ዲመሽቅ ሊብኒ ዓሳኪር 9/14 መጀመሪያ ላይ ላለ መስመጥ መርከቧ ላይ የሚሳፈሩ ብዙ ናቸው መንገድ ላይ ሆነው እንቅልፍ የሚወስዳቸውና በእንቅልፍ ልባቸው የደረሱ መስሏቸው የሚወርዱም ጥቂት አይደሉም :: አንተ ሰለፍይ ሆይ መርከቧ ላይ ሆነህ ከመተኛት ተጠንቀቅ ምክንያቱም ፌርማታህ መለከል መውት የጥሪ መመሪያ ይዞ መጥቶ ወደ ሚቀጥለው የበርዘኽ ህይወት መርከብ የሚያሸጋግርበት ቦታ ነው :: ከዚህ በፊት ከወረድክ ከሚሰምጡት ትሆናለህ መርከቡ ጉዞ ይቀጥላል ንቁዎቹን ይዞ ወራጅ የሚሉትን እያወረደ ከወረድክ በኀላ አውቶቢስ እንዳመለጠው ሰው ብትሯሯጥና በፀፀት ፀጉርህን ብትነጭ ዋጋ የለውም አላህ ካዘነልህና በሚቀጥለው የሱና መርከብ ካልተሳፈርክ በስተቀር :: በጉዞህ ላይ እያለህ የሚያዘናጉህና ያለ ፌርማታህ እንድትወርድ የሚያደርጉህ ብዙ ናቸው ተጠንቀቅ !!!! 🚫 እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ተከታተል ፡፡ እነ እገሌም እዚህ መርከብ ላይ ነበሩ ወርደዋል እነ እገሌም ሊወርዱ ነው ካላመንክ ሲወርዱ ታያለህ የሚሉህ ትንቢተኞች አዘናግተው ለመውረድ እንዳያስወስኑህ አደራ መርከቧ ውስጥ ያለውን እንዳትንገዳገድ እንዳትወድቅና እንዳያንሸራተትህ ቀጥ ብለህ እንድትቆም የሚረዱህን የቁርኣን የሐዲስና የሰለፎች አስተምሮዎችን አጥብቀህ ያዝ አላህ ካለ ትዘልቃለህ :: @bahruteka https://t.me/fromsunahhpages/56
نمایش همه...
ከሱና ገፆች📚⭐

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ይላሉ:– "አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.