cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ገምሀልያ❤️

ካየሁት 👀 አስገራሚ ከሠማሁት 👂 መሣጭ ካነበብኩት 📖 አስተማሪ ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ እነሆ ፅሁፎቻችሁን በ @Gemhalya1 አካፍሉን። ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @Gemhalya1 ይጠቀሙ።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
206
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ከሮበርት_ሙጋቤ ንግግሮች ውስጥ 👇 ➊.ደሞዝ የመጣ ቀን ዶሮ ትበላለህ። : ➋.በማግስቱ ደሞዝ ሲያንስብህ የዶሮ ውጤት (እንቁላል) ትበላለህ። : ➌.በቀጣዩ ቀን ደሞዝህ የበለጠ ሲሳሳ ደግሞ የዶሮ ምግቦችን (በቆሎ እና ገብስ) ትመገባለህ። : ➍.በተከታዩ ቀን ደሞዝህ ሲሟጠጥ ደግሞ አንተ እራስህ ዶሮ ትሆንና የምትበላውን ነገር ፍለጋ ወዲያ ወዲህ በመባዘን ጊዜህን ታሳልፋለህ። : #ሮበርት_ሙጋቤ! ♡ ㅤ   ⎙ㅤ  ⌲   🔔                     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ unmute
نمایش همه...
ተረኛው ጨባጭ! “አንድ ሰው ሕጻን ሆኖ ሲወለድ እጁን (መዳፉን) ጨብጦ ነው፤ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት ደግሞ እጁን (መዳፉን) ዘርግቶ ነው” ይላል ካልታወቀ ምንጭ የተቀዳ አባባል፡፡ ለአንድ ሕጻን አንድን ነገር በእጁ አስይዛችሁት ካወቃችሁ ልጁ የያዘውን ነገር በቀላሉ እንደማይለቅ ትደርሱበታላችሁ፡፡ አንድ ሕጻን ልጅ እጁን ጨብጦ መወለዱ ሁሉን ለመያዝ፣ ሁሉን በእጁ ለማስገባትና ሁሉን ነገር በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የመሞከሩ ምልክት ነው፡፡ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት እጁን ዘርግቶ መሞቱ ደግሞ ሁሉን አይቶት፣ ሞክሮት፣ ጨብጦና “የእኔ ነው” ብሎ በመጨረሻ ምንም ነገር የእርሱ እንዳልሆነና አንድ ቀን ሁሉም ነገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ እንደሚሆን የመገንዘቡ ምልክት ነው፡፡   እውነታው ይህ ነው፡- ተወልደን በልጅነት ባሳለፍንበት ወቅትና ሸምግለን ከዚህ አለም ወደመሰናበት በምንደርስበት ወቅት መካከል ባሉን እንደ ጥላ በሚያልፉት አመታቶቻችን መያዝና መቆጣጠር በምንችለውና በማንችለው መካከል መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ነገ ሁሉንም ነገር ትተነው እንደምናልፍ በመገንዘብ ሁሉን ነገር የእኛ ለማድረግ ጦር ስንማዘዝ ዘመናችንን እንዳናባክነው እናስተውል፡፡ እጅህ በገባው ነገር ደስተኛ ሁን፣ ለመልካም ነገር ተጠቀምበት፡፡ እጅህ ለማስገባት ያልቻልከውን ነገር ለማስገባት ሞክር፣ ነገር ግን ሁሉን ካልያዝኩ በማለት ስትሟገት በጦርነትና በፍርድ ቤት ዘመንህን አታስበላ፡፡ የአለምን ምድር ሁሉ ጨብጠን የእኛ እናደርጋለን ብለው የነበሩ ምእራባውያን ቅኝ ገዢዎች የጨበጡትን ሁሉ ቀስ በቀስ እየለቀቁ እንደሄዱ አትዘንጋ፡፡ እንዲያውም የእነሱንም ቀስ በቀስ የሚያስለቅቃቸው ሁኔታ እየተጋረጠባቸው ነው፡፡ ለጊዜው ነው እንጂ ምንም ነገር በቋሚነት የአንተ አይደለም፡፡ የእኔ ነው ብለህ የምታስበው ሁሉ ለጊዜው በአደራ የተሰጠህ ነው፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበትን ቤትና መሬት ትናንት የእኔ ነው ብሎ የሚኖርበት ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአንተ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ይህንን ስፍራ ሌላው ተረኛው ጨባጭ ይረከበዋል፡፡ ቁም ነገሩ በዘመንህ የጨበጥከውን ነገር የመልቀቂያህ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ለመልካም ዓላማ የመጠቀምህ ጉዳይ መሆኑን ላስታውስህ፡፡ ✍ዶ/ር እዮብ ማሞ @Gemhalya
نمایش همه...
ቅር ቢለው አይደል ግርር ቢለው አይደል ከሕይወት ተኳርፎ፣ ብሎ "የት ይኬዳል"? እንጂማ ማን ደፍሮ ሞት ጋር ይሰደዳል። 🖤
نمایش همه...
#አሞኛል ! ... አባቴ ተሰቅሎ፣ ወንድሜ ተቃጥሎ። እህቴ ታግታ፣ እናቴ ተቀልታ። አያቴ ተሰ'ዶ ህፃን ልጄ ታርዶ...  አሞኛል!                 ወገን ሞቶብኛል!                 ሰው ተገ'ሎብኛል (በአርቲስት ሜሮን ጌትነት)
نمایش همه...
"የኔልሰን ማንዴላ .. ☞ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው ። ስሙም ፒተር ይባላል ። አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና ወፍ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" አላቸው ፣ ብልሁ ማንዴላም " አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ .... ►"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ብር በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ ጥበብ ቢኖር በቅድሚያ የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ጠየቀው ፣ ►ማንዴላም "ገንዘቡን አወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት ። ►ፕሮፌሰሩም በግልምጫ " አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ አወስድ ነበር" አለው፣ ►ማንዴላ ፈገግ እያለ" ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው ። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል ። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ፣ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ " ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ፃፍልኝ"😁
نمایش همه...
🙂
نمایش همه...
ለወጣቶች የተዘጋጁ የህይወት ክህሎቶችን እና የስራ እድሎችን ለማግኘት አዋቂን ይቀላቀላሉ! @awaqiethiopia ነፃ የስልጠና እና የተለያዩ እድሎችን እንዲሁም አዝናኝ እና አነቃቂ ቪድዮዎችን በየጊዜው ለማግኘት አዋቂን ይቀላቀሉ. https://t.me/awaqiethiopia Promotion Details Contestant name: #የ mõm Contestant ID: #421512035
نمایش همه...
ጓደኛ ማለት...! 1. እንደፈለክ በነፃነት የምትሰድበው 2. በጣም ጨንቆህ ስታማክረው እሱ የሚቀልድብህ 3. በጣም አስከፍቶህ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ በድጋሜ የሚሰድብህ ?? እንደዚህ አይነት ጓደኛ ካለህ.. እድለኛ ነህ💜
نمایش همه...
በተሳፋሪዎች የተሞላ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ:: ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታየሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን። ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ... መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም ለመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ነበር፡፡ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 30) 12፤ ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ። 13፤ ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ ረምሃይም ኢትዮጵያዊ ቀለም ፤ የሐበሻ ጦማር
نمایش همه...