cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

👳መዲነቱ_ዳ҉ ና҉ {☆نور محيبو}

(#መዲነቱ_ዳና(#ⒹⓐⓃⓐ) ✧--------------☆---------------☆ #በዚህ_ቻናል ✧----------- 👉 #የሀበሻ_መሻኢኾች_ታሪክ 👉 #ቂሶዎች 👉 #ስለረሱል_ሙሀባ 👉 #የአሪፎች_ሀድራ 👉 #መንዙማ 👉 #ምንም_የሚቀር_ነገር የለምም #ሀሳብ_አስተያየት_ካለወት_በዚ_ያድርሱን ➊👉 @Nurahussen ➋👉 @somed34

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
406
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#መዲነቱ_ዳና አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ ወድና የተከበራቹ የመዲነቱ ዳና ቤትሰቦች እነሆ ዛሬ ከስንት ጊዜ በሆላ ተገናኝተናል አልሀምዱሊላህ ስለሁሉም ነገር ውዶችየ ይቺ ጊዜ ለሁላችንም የፊትና የችግር የሀዘን የመሰደድ የመነፋፈቅ ከቂየ ከመንደራችን ከሀገራችን ከተወለድንበት ቦታ በሀገር ጠል በጨካኝ አረመኔ በእናት ጡት ነካሾች ጁንታ ምክኒያት ብዙ ስቃይን እና ሀዘንን እያሳለፍን መሆኑ ይታወቃል ግን ውዶችየ በማልችለው አስቤው በማላቀው ማሰብ ሁሉ በሚያቅተኝ #እናቴን_እማይየን 😭😪❤️በጦርነቱ ምክኒያት አጣሆት እናም ውዶች ስሜቴን ከዚ በላይ መግለፅ አቅቶኛል ብቻ ለእማምየ በአላህ እለምናቹሀለሁ ከልባቹ ዱአ አድርጉላት በፈጠራቹ እናንተም እህት ወንድሞቸ ቤትሰባችሁን ላጣቹ ሁሉ አላህ ሶብሩን ይስጠን እነሱንም አላህ ጀነትን ይወፍቃቸው አላህ ያሻውን የወደደውን ነውና የፈፀመው ስለሁሉም ነገር #አልሀምዱላህ
نمایش همه...
#መዲነቱ_ዳና ☞ ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤ ሀብታም ብትሆን ዶላር ያሳበጠው ይሉሀል። ☞ ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤ ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል ። ☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ። ☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ። ☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ ☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ። ☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ። ☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። በቃ ምን ልበላቹ ሰዎች ከማውራት አይቆጠቡም ነገር ግን አንተ ራስህ እንደገባህ እንጂ ሰዎች እንደተረዱህ አትኑር። ምክንያቱም ከአንተ በላይ ስላንተ የሚያውቅ የለምና። @arifochu @arifochu
نمایش همه...
👍 19
#ኸሚስ_ሙባረክ 🙏💚 ` ዱቤው ሲመታነው ጀስዴ ሚፋካው ቀልቤ የሚሽረው 💚💚💚👏👏👏 ~ዞበል በራ በሩ. ገደምዩ እንደት ነው እንደ ኑር ሊገባ በሀድራው ጦሪቃ የተሽሞነሞነው ባንቱ ቃዬ መስሎኝ በመንዙማው እሳት ኢልም የሚጋገረው !!
نمایش همه...
#መዲነቱ_ዳና وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا! "ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ። በል!" """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" እነሆ አንድን ሙእሚን ወደ ከፍታው ማማ የሚያዘልቀው ዒልም ነው፤ለመልእክተኛውም "ጨምርልኝ" እንዲሉ ጀሊሉ በትእዛዛዊ ቃል ወሕዩን ያወረደላቸው ዒልምን ነው።[ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም] አዎ! ጨምርልኝ ከሚያሰኙ ነገሮች ሁሉ እንደዒልም ያለ ምን አለ? ✦✦✦ ዒልም ኑር ነው፣ዒልም የጥፋት ባህር ውስጥ እንዳትሰምጥ ድልድይ ሆኖ ወደ ሰላሙ ሰፈር ያሻግርሃል፣ዒልም ከሌለ ዓመል የለም፣ዓመል ከሌለ፣ኢኽላስ የለም፣ኢኽላስ ከሌለ ተቅዋ የለም። ✦✦✦✦ የታላቅነት ምንጩ ዒልም ነው፣ወደ ወልይነት ጎራ ማስፈንጠሪያው ዒልም ነው፣ኢማሙ ዓልይ[አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና] ገንዘብን አንተ ትጠብቀዋለህ፣ ዒልም ግን አንተን ይጠብቅሃል፣ዒልም በተጠቀምከው ቁጥር ይጨምራል ገንዘብ ግን ይቀንሳል።ብለው እንዳሉት ዒልም ከስጦታዎች ሁሉ ታላቁ ስጦታ ነው። ✦✦✦ በመሆኑም በዘመናችን ተገኝተው ዘመናችንን ካደመቁ አያሌ የዒልም ጀንበሮች መካከል ከቀዳሚው [ሶድሩል ዑለማኢ ወል ዓሚሊን] ሐበሻዊው ሸይኹነል ዓብደሪይ[ራሐማቱሏሂ ዓለይህ] ሦር በአደብ ተኮትኩተው ያደጉት አለም አቀፉ ዳዒ ዶክተር ሸይኽ ጧሪቅ አል‐ሊሐም[ሐፊዞሁሏህ] አዲስ አበባ ከሚገኘው መርከዝ ሸይኽ ዓብዲላህ በመገኘት በአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ተሰራጭተው ዒልሙን ሲያስፋፉ የነበሩ ትንታግ የዒልም ወጣቶችን ጋብዘው እጅግ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢውን ዒልም፣የመላው ሙስሊሞች ዓቂዳ የሆነውን የዐቂደቱል አሻዒራ ወል ማቱሪዲያን ዒልም ሰብስቦ የያዘውን፣ በተለያዩ ነቅልይና ዓቅልይ ማስረጃዎች የተሞላውንና ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ታላላቅ መሻይኾች "ወሳኝ ኪታብ" በሚል ፊርማቸውን ያሳረፉበት "ነፋኢሱል ሙሐደራት"የተሰኘውን የዓቂዳ ኪታብ በማስተማር ላይ ይገኛሉ ።አልሐምዱሊላህ። ✦✦✦ እኔም በአሏህ ችሮታ በመላኢካ አጀባ በሚከበበው በዚህ የዒልም ማእድ ኪታቤን ይዤ ዙሪያውን ተኮልኩሎ ዒልም ከሚቀስመው የዒልም ወታደር መሀል ወሳኙን ዒልም መቅሰሙን ተያይዤዋለሁ።ለምን ቢሉ "ኢነመል ዒልሙ ቢታዓሉም"ዒልም የሚገኘው ከመሻይኾች አንደበት ሰነዱን ጠብቆ ሲወርድ ነውና! ✦✦✦ ወዳጄ! በዚህ የመሻይኾቻችን ክብር በሚጣስበት አስቸጋሪና አሳዛኝ ወቅት አሏህ ዘንድ ምንዳ የሚያስገኝልህና ዲኑንም ከመንጋው ወረረሽኝ የምትታደገው በዒልምና በዒልም ነው። አሏሁ ተዓላ ኢኽላሱን ይስጠን። ✦✦✦ @arifochu @arifochu
نمایش همه...
#መዲነቱ_ዳና •┅┈┈┈┈┈•❀ ┊ ┊ ┊ ★ ┊ ┊ ☆ ┊ ★ ☆ «ምን ብታይ ድካሜ አይሎ እንደሰው ችየ ባልፀና አያስችለኝም ሲነኩ ያመኛል ገና ለገና» ❤️ፊዳከ ነፍሲ... ያ ሐቢቢ ያረሱለሏህ!❤️ ☆ ┊ ★ ┊ ┊ ☆ ┊ ┊ ┊ ★ ••┅┈┈┈┈┈•❀ @arifochu @arifochu
نمایش همه...
#መዲነቱ_ዳና ✍ #ኑር_ሙሂቡ በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅህ በቂ ነው። @arifochu @arifochu
نمایش همه...
👍 4
#መዲነቱ_ዳና ✍ #ኑር_ሙሂቡ 🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏 "1. ብዙዎቻችን በህይወታችን በጣም አስፈላጊ የምንለዉን ነገር ማግኘት ሳንችል እንቀራለን፡ግን አሳዛኙ ነገር አስፈላጊ ነዉ ያልነዉን ነገር በትክክል ሳናጣጥመዉ እያሳደድን እንኖራለን፡፡ 2. ብዙዎቻችን ጠቃሚ የሆነዉን ነገር ትተን ጠቃሚ ይሆናል ብለን ባሰብነዉ ነገር ላይ እንዳክራለን፡፡ሳምንቱን ሙሉ ፈግተን ህልም ያልነዉን ነገር ስንጨብጠዉ የምንወዳቸዉን ሰዎችና ማንነቶች ወይ ሞተዉ አለበለዚያ ጥለዉን ሄደዉ እንደርሳለን፡፡ ሠአታችንን በራስ ወዳድነት‹ህልም› ዉስጥ ቀብረን ስናበቃ ያ ህልማችን ካጣናቸዉ ሰዎች ጋር ሲነፃፀር ተራ እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ 3. ብዙዉ የህይወታችን ጊዜ ትርጉም አልባ ይሆንብናል፤ሌላ ቀን ደግሞ ህይወት ትርጉም ሰጥታን እንዉላለን፡፡አምላካችንን ስናማርርና ‹ምነዉ በገደልከኝ!› እያልን እንከርምና ትንሽ ፀሃይ ሲወጣልን ደግሞ ለአምላክ የምናሸበሽብ መላእክት እንደሆንን አይነት ይሰማናል፡፡ 4. ማንም ለማንም የማይጨነቅበት ሰአት ላይ ደርሰናል፡፡ሁላችንም ስለራሳችን በማሰብ ዘመናችንን እንጨርሳለን፡፡ምን እበላ ይሆን ምን እሰራ ይሆን እያልን ከራስ ያልዘለለ ማንነት ዉስጥ ተጠልለን እንሞታለን፡፡ 5. አለምን የምናየዉ በነበረበት ሁኔታ ሳይሆን በራሳችን ሁኔታ ነዉ፡፡ ስራ ያጣ ሰዉ አለምን የሚያየዉ ስራ ለሚፈልግ ሰዉ ቦታ የሌላት የዘመድ አዝማድ ጥርቃሚ የተሞላባት የመስሪያ ቤቶች ጋጋታ ሊሆን ይችላል፡፡ ፍቅር የያዘዉ ሰዉ አለምን የሚያየዉ ፍቅር እንዴት ታላላቅ መሪዎችን እንደማረከና አገሩ በሙሉ በጥንዶች እንደተሞላ እንዲሁም ምን ያህል እድለኛ እንደሆነ ነዉ፡፡ ከራሳችን ስሜት በላይ ሆነን አለምን የምናይ ሰዎች እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ ", 🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌 @arifochu @arifochu
نمایش همه...
#መዲነቱ_ዳና 🗣 #ኤርዶጋን "የእኔን ፊርማ የሚጠብቅ ወረቀት እያለ ሳልፈርም የተኛሁበት ጊዜን አላስታውስም።ምናልባት አንድ ሰከንድ የማይፈጀው የኔ ፊርማ በመዘግየቱ የሰውዬውን ጥቅም ለረጅም ጊዜያት ሊያዘገይበት ይችላል።" @arifochu @arifochu
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.