fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

رفتن به کانال در Telegram
2 406
مشترکین
+124 ساعت
+407 روز
+33730 روز
آرشیو پست ها
<<አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን>> ____________________________ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል አዘጋጅነት ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማካሄድ ቀኑ ተከብሮ ውሏል። ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ

🇪🇹16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአል🇪🇹 በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በከተማችን እየተከበረ ያለውን 16ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ክብረ በአል በሚከበርበት ስፍራ ላይ በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የተሰራ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያን እንዲህ ባለ ሁኔታ አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል።

🇪🇹በወቅታዊ የሀገር ጉዳይ ላይ የተደረገ ውይይት🇪🇹 ================================== ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሞያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ዘመቻ ለህብረብሔራዊ አንድነት የትና እንዴት እንዝመት? በሚል ሃሳብ ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ። ✍️በውይይት መድረኩም የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የተገኙ ሲሆን እየተመዘገበ ያለውን አኩሪ እና አንጸባራቂ ድል በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት በማስተላለፍ በቀጣይም ይህንን ድል አስጠብቆ ለመቀጠል በተለይም ሰራተኛው በልማትና መልካም አስተዳደር ግንባር በቁርጠኝነት ተሰልፎ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። ህዳር 24/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ ኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ሪብራንዲንግ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 =============================== ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሞያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተቋማት ሰራተኞች በሪብራንዲንግ ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፤ በመድረኩም ከፐብሊክ ሰርቪስ በመጡ ባለሞያ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቂ ግንዛቤ የጨበጡበት ሆኗል። ✍️ ከመድረኩ ጎን ለጎን በህልውና ዘመቻው በጀግንነት ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊታችን የደም ልገሳ ማድረግ ተችሏል። ህዳር 21/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

🇪🇹ደማችንን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን🇪🇹 ✍️በነገው እለት ህዳር 21/2014 ዓ.ም ከሰዓት ከሚኖረን የሪብራንዲንግ የገለጻ መድረክ ጎን ለጎን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የደም ልገሳ ስለምናደርግ ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ ተሳታፊ አንዲሆን ጥሪ እናደርጋለን።

🇪🇹 የአልባሳት ድጋፍ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን🇪🇹 ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የቴክኒክና ሞያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በስሩ የሚገኙ ተቋማትን በመማስተባበር የተለያዩ አልባሳትን በማሰባሰብ በጦርነት ለተፈናቀሉ እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖቻቸን ድጋፍ አድርጓል፤ ✍️ይህንንም ድጋፍ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በግንባር ቀደምነት አጠቃላይ ሰራተኛውን እና ሰልጣኝ ተማሪዎችን በማስተባበር ማሰባሰብ ችሏል፤ ✍️ለዚህም ድጋፍ መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ የኮሌጁ ሰራተኞችና ሰልጣኝ ተማሪዎች የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል። ህዳር 17/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ

🇪🇹ስንቅ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት🇪🇹 ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር የቴክኒክና ሞያ እና የኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተቋማት ሰራተኞች በአንድት ለጀግናው የሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ስንቅ ማዘጋጀት ተችሏል፤ ✍️በዚህም ስንቅ የማዘጋጀት ተግባር ላይ የቢሮው ሀላፊን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፤ ✍️በተጨማሪም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በቦታው በመገኘት ሰራተኞችን አበረታተዋል። ህዳር 15/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ

#NOMORE #HaaGahu #በቃ #OnEthiopia #DireDawa #Ethio-Italy #Polytechnic #College 🇪🇹#Management

"ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቴክኖሎጂ ሽግግር" ----‑------------------------------------------------------ ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አበይት ተልዕኮዎችን በትግበራ ምዕራፍ ውጤታማ በሆነ መልኩ መፈጸም እንዲያስችል የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፤ ከእነዚህም ጥናቶች የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበርን የተሻለና ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ለኮሌጁ የስራ አመራር ቀርቦ በቀጣይ ለሚደረገው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ጠቃሚ የሆኑ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል። ✍️በተጨማሪም የተመረጡ የቴክኖሎጂ ናሙናዎችን ለመስራት የቀረበ ፕሮፖዛል ላይም መወያየት ተችሏል፤ በተለይም ተረፈ ምርትን ወደ ምርትነት ለመቀየር የሚሰሩ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንዲሰሩና ኮሌጁም መሰል እንቅስቃሴዎችን ከግብአት ማሟላት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የኮሌጁ ዲን አስታውቀዋል።