cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Rimaz islamic channel

እስልምናን ለወፈቀን አላህ ምስጋና ያገባው አልሀምዱሊላህ . . . 🙏🙏🙏🙏 ለአስተያየትዎ @Rimz_bot

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
185
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#EID_MUBARAK #🄴🄸🄳_🄼🅄🄱🄰🅁🄰🄺 ╔────── ¤ ¤ ──────╗ @JUBI_PIC ╚────── ¤ ¤ ──────╝
نمایش همه...
ቢላል ኢብን ረባህ ታሪክ
نمایش همه...
Bilal.mp340.49 MB
ሰብስክራይብ
2.46 KB
Yes
🅽🅾
በዚህ channel የተለያዩ profile picture ለሙስሊሞች ብቻ በልዩ ሁኔታ እናቀርባለን። ለረመዷን ፕሮፋይል ፒክቸሬን ምን ላይ ላርግ ብላቹ ከመጨናነቅ ይልቅ ከስር👇 የሚለውን ብቻ በመጫን የተለያዩ profile picture ማግኘት ትችላላችሁ። 👇ይቀላቀላሉ👇
نمایش همه...
˙·٠•●♥ Join ♥●•٠·˙
📖እውነተኛ ፍቅር😍 🌹ክፍል 1⃣ በቅድመ ኢስላም በጃህሊያ ዘመን ወደ ኢስላም ጥሪ ከመጀመሩ በፊት አስራአምስት አመት ገደማ አንድ ውብና ተክለ ሰውነቱ ያማረ ወጣት ካዕባ አጠገብ ከሚገኘው በኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረዐ) ቤት አጠገብ አለፈ፡፡ ወጣቱ ሲያዩት ፊቱ እንደ በድር ጨረቃ የፈካ ፤ መልከመልካም ፣ የዐይኖቹ ጥቁረት የበረታ ፣ የሽፋሽፍቶቹ ፀጉር ረዥም ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ፣ አንገቱ መለሎ፣ አይኖቹ በተፈጥሮ የተኳሉ ፣ ቅንድቡ ቀጭን እና ረዥም ከሩቅ ሲያዩት እጅግ ሲበዛ ቆንጆ ሲቀርቡት ተወዳጅ ጥርሱ ነጭ አፍንጫው ቀጥ ያለ ነበር፡፡ በወቅቱ የከድጃ ቤትና የዳረል አሰድ ቢን አብድልዑዛ ፣ ቤት ከካዕባው ጥቂት እርምጃ ነበር የሚርቀው፡፡ አንድ የአይሁድ መነኩሴ በከድጃ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ሳለ መልከመልካሙን ወጣት አየው ፣ ከድጃንም ወጣቱ ተጠርቶ እንዲመጣ አዘዛት ፣ ወጣቱም በከድጃ አገልጋይ ተጠርቶ መጣ፡፡ አይሁዳዊው መነኩሴ ወጣቱን በትህትና ልብሱን ከትከሻው አካባቢ ገልጦ እንዲያሳየው ጠየቀው ፣ ወጣቱም እንደተጠየቀው አደረገ ፣ አይሁዳዊው ትከሻው አካባቢ ባየው አስደናቂ ነገር ተደሰተ አቅፎም ሳመው፡፡ ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ከድጃ ለአይሁዱ "ይህንን ድርጊትህን ቁረይሾች ቢያዩህ አንተን ከመቅጣት ትዕግስት የላቸውም " አለች፡፡ በርግጥ የአይሁዱ ድርጊት ለምን እንደሆነ ከድጃን (ረዐ) የገባት ነገር የለም ፣ ወጣቱን ስታየው ፊቱ የፈካና የሚያምር አንደበተ ርቱዕ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ አይሁዱ ለከድጃ እንዲህ አላት፡፡ "በተውራትና በኢንጂል ኪታቦች ላይ ሰፍሮ እንዳየሁት የአንድ ብርቱ ሰው መምጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እዚሁ በመካ ነው ፣ እናትና አባቱ በልጅነቱ ይሞታሉ ፣ አጎቱ ያሳድጉታል ወደ መዲናም ይሰደዳል ፣ የሻምን ስልጣን በእጁ ያደርጋል ፣ በመካ ያሉትን ጣኦታት በሙሉ ሰባብሮ በማስወገድ ካዕባን ንፁህ ያደርገዋል፡፡" ከድጃ አይሁዱ የተረከላትን በጥሞና አዳመጠች ፣ በንግግሩም ተማረከች ልቧ ጓጓ ወጣቱንም ለማወቅ ፈለገች፡፡ በሌላ ጊዜ አጎቷ ወረቃን ስለዚው ጉዳይ ጠየቀችው ፤ ወረቃም ወደ ሻምና ሶሪያ በመሄድ የኢንጅልን መፅሀፍ ስላጠናና ስለመረመረ ይመጣል ተብሎ የተተነበየው ታላቅ ሰው ከቁረይሾች እንደሚያገባ በገንዘብ እንደምትረዳውና ከጎኑ እንደምትሆን አረጋገጠላት፡፡ . የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ እሷ ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ ሀብትና ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡ ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡ አላህ በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡ ከድጃ ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ ይህን ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡ አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው ስሙ አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ የተከበረችው ከድጃ ስትቀር . . ይቀጥላል ኢንሻ አላህ🌹 @ISLAMICINF0 🌹━━━━━━━━━━━━🌹
نمایش همه...
━━━━አርጦግሮል━━━━ 3(የመጨረሻ ) ⊙━━━━━━━━━━━━━━━━⊙ ሱልጣኑም ከቤዛንታይኖች ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ምዕራብ አናዶልያ (Anatolia) የተወሰነ መሬት በመቁረጥ ጎሳዎቹ የሚሰፍሩበትን ቦታ ሸለመው። የካይ ጎሳም እዛ ሰፈረ። ሱልጧኑ ይህን ቦታ የሰጣቸው በዚ በኩል ያለው የሰልጁቆች ድንበር ከቤዛንታይኖች ጥቃት እንዲጠበቅለት በማሰብ ነበር ተብሏልም። ከዚ ድል በኋላም የተቀሩት የቱርክ ጎሳዎች አርጦግሮልን የራሳቸው መሪ አድርገው በላያቸው ላይ ሾሙት። ሱልጧኑ ለአርጦግሮል ከቤዛንታይኖች ድንበር ባሻገር በመቆጣጠር ወደ ሰልጁቅ empire እንዲጨምራቸው ፈቀደለት። ብዙም ሳይቆይ ግን አርጦግሮል ሁሉንም በጀግንነቱ አስደነቃቸው። ከተወሰነ ግዜ በኋላ ሱልጧኑ ለአርጦግሮል የሶጎት ከተማን ፈቀደለት። የዚ ቦታ ስፋት ከ1000 እስከ 2000 ኪ/ሜ square ይገመታል። ነገር ግን ይቺ ትንሽዬ ቦታ ወደፊት በልጁ ዑስማን የምትመሰረተው የዑስማኒያ ስርወ መንግሥት መሰረተ ድንጋይ ነበረች። እ.ኢ.አ በ1258 በሂጅራ አቆጣጠር ደግሞ በ656 ልጁ ዑስማን ቢን አርጦግሮል በሶጎት ከተማ ተወለደ። ይህ አመት የሞንጎሎች መሪ የሆነው ሆላኮ ኻን ባግዳድን የተቆጣጠረበትና ያንኮታኮተበት አመት ነበር። ነገር ግን ሞንጎሎችም ሆኑ የአውሮፓው አለም ይህ የተወለደው ህፃን በዚች ህዝብ ላይ በድጋሚ ነብስ እንደሚዘራ፣ ፡ሀይማኖቷንም እንደሚያድስና አለምን ለ600 አመት የሚመራ ጠንካራ empire እንደሚመሰርት አላወቁም ነበር። አርጦግሮልም እጅግ ከረዘመ የትግልና የድል ኑሮ በኋላ አጥንቱ ሰውነቱን መሸከም አልቻለም። ቀኑም ደረሰ። አርጦግሮል በ1281 ይቺን ምድር በመሰናበት ወደ ማይቀረው አለም ተጓዘ። በዚህም ጊዜ እድሜው ከ90 አመት ያልፍ ነበር። ከአርጦግሮል ህልፈት በኋላ የሱ ተተኪ የሆነው ታናሽ ልጁ ዑስማን ነበር። ዑስማን ጋዚ ልክ እንደ አባቱ አርጦግሮል ትክክለኛ ሙስሊም፣ ጀግናና ደፋር ሰው ነበር። እንዲሁም የአባቱን አርጦግሮል ህልም በማሳካት ከብዙ ትላልቅ ድሎች በኋላ ለ600 አመታት አለምን የገዛውን፣ ሶስት አህጉራትን (ኤዥያ፣ አፍሪካና አውሮፓ) ተሻግሮ የዘለቀውንና ከ20 ሚሊዮን ኪ/ሜ square በላይ ስፋት የነበረውን የOttoman Empire አቋቋመ። የአርጦግሮል መቃብር በሶጎት ከተማ ውስጥ ይገኛል። በአሁን ስዓት ያለው የሱ መቃብር የተገነባው በሱልጣን አብዱልሃሚድ ሁለተኛው ጊዜ የነበረ ሲሆን የTurkmenistan መንግሥትም ለአርጦግሮል ክብር ስትል በ1998 በዋና ከተማዋ Ashgabat ውስጥ በሱ ስም መስጂድ አስገንብታለታለች። ⊙━━━━━━ ተፈፀመ ━━━━━━━⊙ Join & share ━━━━━━━━━━
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.