cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

Professional Sport Club Website -http://saintgeorgefc.com/blog/ Facebook - https://www.facebook.com/Saint-George-SA-177342563049631 YouTube -https://www.youtube.com/channel/UC1M4f0IYEbdcwjMz-QQrepg 💛❤አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ 💛❤

نمایش بیشتر
Advertising posts
7 001مشترکین
+824 ساعت
+177 روز
+15730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"ሁልጊዜም ዳኞች ለምን ጫና እንደሚያደርጉብኝ አይገባኝም … በድርጊቱ ያስከፋሁትን ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ "                                ሞሰስ ኦዶ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ሰነ-ስርዓት ኮሚቴ በክለባችን የፊት መስመር አጥቂ ሞሰስ ኦዶ ላይ  ያስተላለፈውን ቅጣት በተመለከተ ከተጫዋቹ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል፡፡ "የኢትዮጰያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር  በጣም አሪፍ ፣ ፉክክር የሚስተዋልበትና ሁሉም ቡድን በተለይ ከጊዮርጊስ ጋር ሲሆን ራሱን በደምብ አዘጋጅቶ የሚመጣበት ቢሆንም ዳኞች ግን በተደጋጋሚ ክለባችን ላይ ጫና ሲያደርጉ ይስተዋላል ፤ በተለይም በኔ ላይ ያላቸው እይታ  በትኩረት ሊታይ ይገባዋል ፡" ብሏል። ሞሠስ አያይዞም " ከወላይታ ዲቻ ጋር በነበረን ጨዋታ ለክለቤ ውጤታማነት ከመጣር ውጪ የተለየ ያደረኩት ነገር አለ ብዪ  አላምንም ሆኖም ግን ተፈጠረ በተባለው ድርጊት ያስከፋሁትን ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ ፡፡ " ብሏል የዲሲፕሊን ኮሚቴው ሞሰስ አዶን በዲሲፒሊን ጥሰት 3 ጨዋታ እና 28ሺ ብር ቅጣት ማስተላለፉን አስታውቋል ፡፡
نمایش همه...
👉 ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር 21ኛ ጨዋታ 👉የጨዋታው ውጤት ⚽️ቅዱስ ጊዮርጊስ (20) 1 - 2 ድሬደዋ ከተማ (20)⚽️ ⚽️ሀብታሙ
نمایش همه...
👉 ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር 21ኛ ጨዋታ 👉የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት ⚽️ቅዱስ ጊዮርጊስ (20) 0 - 1 ድሬደዋ ከተማ (20)⚽️ 💛❤️ድል -ለተስፋ ቡድናችን 💛❤️
نمایش همه...
#የጨዋታ ቀን 👉 ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር 21ኛ ጨዋታ 👉በሰበታ ከተማ ዛሬ ሐሙስ በ4:00 ሰዓት ላይ ጨዋታው የሚያደርግ ይሆናል ። ⚽️ቅዱስ ጊዮርጊስ (20) ከ ድሬደዋ ከተማ (20)⚽️ 💛❤️ድል -ለተስፋ ቡድናችን 💛❤️
نمایش همه...
ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀዋሳ ከተማ የሚያደርጋቸው ተከታታይ አምስት ጨዋታዎች ።
نمایش همه...
ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀሪ ጨዋታዎች  በሰበታ ከተማ እንዲከናወኑ መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ቡድናችን ዛሬ  ከፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታ የነበረው ቢሆንም ተጋጣሚው ቡድን በሜዳው ስላልተገኘ  ቡድናችን ሶስት ነጥብና ሶስት ንፁህ ጎል ማግኘት ችሏል።
نمایش همه...
ይርበተበታሉ እንደያዛት ምጥ›› ይጨበጨባል፡፡፡ፉጨት ይሰማል እንደገና ሌላም ግጥም የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ እኛም ሀገር አለ ገብረመድህን ሀይሌ...... ግጥሙ ለአሁኖቹ ብቻ ሳይሆን ታሪክ ለሰሩት ለነመንግስቱም እየተዳረሰ ነው፡፡ ምሽቱን ሲጨፈር አደረ፡፡ አልጋ ያላገኘ ድንኳን ጥሎ አደረ፡፡ለብቻው የተኛ አልነበረም አንድ አልጋ ላይ ተጠጋግተው ሶስትና አራት ሰው መተኛት ነበረበት፡፡ ፍቅር ካለ ..ምቾት ዛሬ አይስራም፡፡ፍቅር ካለ ታሲክም ባስ ይሆናል ይሉ የለ? እንደዚያ ነው፡፡ በነጋታው ሌላ ቀን ነው....ሁለቱ ቡድኖች መጋቢት 27 ቀን በኬንያ 0ለ0 ስለተለያዩ ጊዮርጊስ በጥንቃቄ ካልተጫወተ አደገኛ ነገር ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩ አልቀረም፡፡የጊዮርጊስ እድል በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው፡፡ብሪዌሪ ጎል አስቆጥሮ አቻ ከሆኑ ጊዮርጊስ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ተጫዋቹ በዝና ብቻ የሚውቁትን የጅማ ከተማ ህዝብ ማሳፈር የለበትም፡፡ የከተማው ወጣትና ነዋሪ ተጨዋቾቹ ባረፉበት ሆቴል ተኮለኩሉ ‹‹ዳኛቸው የቱ ነው?...ሙሉጌታ የቱ ነው?...ገበረመድንስ?.....እያለ በስምና በዝና የሚያውቃቸውን አላስገባም አላስወጣም አለ፡፡...... በነጋታው የድል ስታዲየም በሚል ስያሜ በሚጠራው ስታዲየም በነቂስ ወጥቶ ስታዲየሙን አጨናነቀው፡፡በስታዲየሙ ቢጫና ቀይ ባንድራ በዙሪያው ይውለበለባል፡፡ቡድኑም ያንን ግርማ ሞገስ የሚያጎናጽፈው ቢጫና ቀይ ማሊያ ለብሶ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን ወደ ሜዳው ዘልቆ የገባው የጊዮርጊስ ቡድን አረንጓዴ ማሊያ ለብሶ ብቅ አለ ፡፡ክለቡ ፈልጎ አልነበረም ይሄ ያደረገው፡፡የእንግዳው ቡድን ቢጫ ማሊያ ለብሶ ‹‹አርማዬ ይሄ ነው›› ብሎ በመገኘቱ ነው፡፡ወቅቱ ደግሞ የካፍ ህግ ለእንግዳው ቡድን ቅድሚያ የሚሰጥበት በመሆኑ ጊዮርጊስ ማሊያ ለመቀየር ተገደደ፡፡ነገር ግን ጊዮርጊስ ሁለተኛ ማሊያ አልነበረውም፡፡ምን ይሻላል?፡፡ የእርሻ ሰብል ቡድን ከጅማ ምርጥ ጋር ለመጫወት ወደ ከተማው ብቅ ብለው ነበር፡፡ በ8 ሰዐት ተጫወቱ ፡፡እርሻ የሚታወቁበትን አረንጓዴ ማሊያ ለጊዮርጊስ ሰጡና ያንን ለብሰው ወደ ሜዳ ብቅ አሉ፡፡ ደጋፊው ግራ ተጋባ ፡፡ጊዮርጊስን በዚህ አይነት ማሊያ አይተውት አያውቁም፡፡፡.የጅማ ድል ስታዲየም ከአቅሙ በላይ ይዟል፡፡ሀዝቡ ቆሞ ነው የሚያየው፡፡ ወደ ሜዳ የገባው የጊዮርጊስ ቡድን አሰላለፍ ተሰፋዬ ዘለቀ ሰይፉ(ኮማንደር) ሰለሞን ሀይሌ ዳኛቸው ደምሴ ታረቀኝ ቢሻው ሰለሞን ዮሀንስ ህሩይ እቁበእዝጊ አዲስ ብስራት ሰለሞን መኮንን ሙሉጌታ ከበደ ገበረመድን ሀይሌ እንደተጀመረ በህዝቡ ጩኸት እየታገዙ ጊዮርጊሶች በፍጥነት ያጠቃሉ፡፡ግብ ግን የለም፡፡በዝና ብቻ የሚያውቃቸው የጅማ ደጋፊ አሸናፊነታቸውን ማየት አለባቸው፡፡12ተኛ ደቂቃ ሆነ ፡፡ሰለሞን ሀይሌ እገፋ ሄዶ ለገብረመድን ሰጠው፡፡ ገብረመድን ለህሩይ አቀበለ፡፡ ህሩይ አታለለና ለገብረመድን፡፡ገብረመድህን እንደገና ለህሩይ....... ህሩይ እይታለለ ሄደ፡፡ አሾልኮ ለሙሉጌታ ሰጠው፡፡ ሙሉጌታ በጥግ በኩል ገባ፡፡ በረኛው ባጠበበት በአስደናቂ ሁኔታ አሰቆጠረ፡፡ ደጋፊው በጭፈራ ስታዲየሙን ቀውጢ አደረገው፡፡ብረት እንደጋለ መቀጥቀጥ እንደሚባለው ሁካታው እንደቀጠለ ማጠዳፍ ተጀመረ፡፡ ከአስር ደቂቃ በኋላ ገበረመድን እያታለለ ሲገባ በመጠለፉ ሪጎሬ ተገኘ፡፡ዳኛቸው ደነሰ፤ ጨፈራና በረኛውን ሸውዶ አስቆጠረ፡፡ ማታ ነው ድሌ የሚለው ዘፈን ቀረ፡፡ማታ እስኪሆን የሚያስጠብቅ ነገር አልነበረም ፡፡በጧት ድሉ ተገኝቷል፡፡ እረፍት ሊወጡ አንድ ደቂቃ ሲቀር ብሪወሪ አገባ፡፡ከእረፍት መለስ ተጨማሪ ግብ ለስማቆጠር መሯሯጥ ተጀመረ፡፡ ሆኖም ግን የቡድኑ ቴምፖ እተቀዛቀዘ መጣ፡፡ ብሪዎሪ ማንሰራራት ጀመረ፡፡ጊዮርጊስ በእጁ የያዘውን እድል ላለማጣት መከላከል ጀመረ ፡፡አሰልጣኙ ታደሰ ወልዳረጋይ ከሜዳቸው ወጥተው እንዲያጠቁ ትእዛዝ ሰጠ፡፡በእርግጥም ማጥቃት ጀመሩ፡፡ ግን ግብ የለም፡፡ጊዮርጊስ እንደመጀመሪያው ባለመሆኑ ደጋፊው ስጋት ውስጥ ወደቀ፡፡ ብሪዎሪ እያጠቃ መጣ ፡፡ነገሩ አስፈሪ ነው፡፡ብሪዎሪ አንድ ግብ አስቆጥሮ አቻ ከሆነ ነገሩ አከተመ ፡፡ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋል፡፡ ይሄ ደግሞ መሆን የለበትም ፡፡የጅማ ህዝብ ለክለቡ የነበረውን ታላቅ አድናቆት መኮሰስ የለበትም፡፡ የባከነ ሰዓት ላይ በግብ ክልላቸው ቅጣት ምት ተገኘ፡፡አደገኛ ነው ፡፡ቅድም ያገባው የብሪወሪ ተጫዋች ለመምታት ተዘጋጀ፡፡ ሁኔታው የሚያስፈራ ነው፡፡በዚህ ሰኣት ከተቆጠረ አከተመ፡፡ ቅጣት ምቱ ከመመታቱ በፊት የጊዮርጊስ ደጋፊ ሜዳ ገብቶ አጥር ቢሰራ ደስ ባለው ነበር፡፡ነገር ግን መቺው ወደ ውጭ ሰደዳት ፡፡የብሪወሪ የማለፍ እድል እንደዚህች ኳስ ተነነና የማለቂያ ፊሽካ ተነፋ፡፡እንደገና ጭፈራ ፡፡ጅማ ደመቀች፡፡ሲነጋ ግን ዝናብ ነበር፡፡ . በነጋታው በጭፈራ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ተጫዋቾቹን መሀል አድርገው አውቶብሶቹ በጡሩንባ እያስገመገሙ ጅማን ቻው ብለው ነጎዱ፡፡ማርሽ ተቀያየረ፡፡ከተማው ጫፍ ኬላው ጋር ደረሱ፡፡፡የእንጨት መቀርቀሪያ ተወድሮ አውቶብሶቹ እንዲቆሙ ምልክት ሰጠ፡፡ጡሩምባው ማርሽ ባንድ በሚመስል ሁኔታ የሚያምቧርቁት አውቶብሶቹ ‹‹ዝነኛው የጊዮርጊስ ባለድሎች ነው የያዝነው ገለል በሉ ››እያሉ እንዲያሳልፏቸ ምልከት ሰጡ፡፡ ነገር ግን ኬላውን ወጥረው የያዙት ፈታሾች ‹‹አውቶብሱን አቁሙ እንናተም ውረዱ›› አሉ፡፡ፍተሻ ተደረገ፡፡ ብዙ ቡና ጭነው ነበር፡፡ ተጫዋቾቹ በቋጠሮ የያዙትን ማራገፍ ነበረባቸው፡፡ነጋዴዎች አይደሉም፡፡ኮንትሮባንድም ሰርተው አያውቁም ፡፡ወደዚህ ከተማ እየተመላለሱ ቡና አይነግዱም፡፡ በእንግድነት ስለመጡ የጅማን ምርት ተቋድሰው ለመሄድ ነበር፡፡ደግሞም አስተዳዳሪው ስላስደሰታችሁን የምትፈልጉትን ያህል ይዛችሁ ሂዱ ብለው ፈቅደውላቸው ስለነበር ነው የያዙት፡፡ነገር ግን ፈታሾቹ ምህረት አልነበራቸውም ፡፡አንዲት ፍሬ እንዲያልፍ እድል አልሰጧቸውም፡፡አንድ የተበሳጨ ደጋፊ ፈታሾቹን ‹‹እነዚህ የብሪወሪ ደጋፊ ናቸው እንዴ ?››ብሎ እስከመናገር አድርሶት ነበር ፡፡ፈታሾቹ ስራቸው ነው ፡፡ነገር ግን ‹‹ትንሽ ለቤተሰብ የምንወስደው ልቀቁልን›› ቢሉም አልተሳካም፡፡ ልመናውን ባለመቀበላቸው ቅር አሰኛቸው፡፡ ብዙ ኪሎ ለተወሰደባው ተጫዋቾች ደጋፊው ኪሳራ እንዳይገጥማቸው እዛው ካሳ እስከመክፈል ደርሷል፡፡ኬላውን በድል ባይሻገሩም አስፈላጊውን ነጥብ ከብሪወሪ ወስደው ወደ ቀጣዩ ዙር መሻገር ችለዋል፡ ምንጊዜም ጊዮርጊስ ✌️
نمایش همه...