fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪወች ጀመዓ ቻናል

የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪወች ጀመዓ ቻናል

رفتن به کانال در Telegram

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አቅሷ መስጂድ ጀመአ 🕌

نمایش بیشتر
208
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
+130 روز
آرشیو پست ها
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ እንቁ የብርቅዬዉ ጀመዐችን ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን አላሁ ሱወ ለዚህ ክብር አበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!      🎁Congratulations🎉              ሙሀረም 12 1448 ዓ.ሂ

Update! ከመጅሊስ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ ኡስታዝ አዩብ ደርባቸው፣ ኡስታዝ ሸሃቡዲን ሸኑራን ጨምሮ 5 ልዑካን አባላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ከጀማዓው ተወካዮች እንዲሁም ከአ
Update! ከመጅሊስ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ ኡስታዝ አዩብ ደርባቸው፣ ኡስታዝ ሸሃቡዲን ሸኑራን ጨምሮ 5 ልዑካን አባላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ከጀማዓው ተወካዮች እንዲሁም ከአጠቃላይ ተማሪዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ በነገው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውይይት እንደሚደረግ፤ ይህንንም ጉዳይ በኃላፊነት እንደሚይዙት በመናገር ተማሪዎች እንዲበተኑ ሆኗል። አሁንም የመጅሊስ አመራሮች ለተማሪዎች የገባችሁትን ቃል አክብሩ! ተማሪው እናንተን አምኖ ጥያቄየን ታሳካላችሁ ብሎ አማና ሰጥቷችኃል። ይህን አማና መብላት አላህ ፊት፤ ተማሪው ፊት፤ ህዝብ ፊት እንዲሁም ታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋችኃልና አማናችሁ ተወጡ! @aaumsu

ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ አሁን ምሽት 2:40 ሰዓት ድረስ፣ ተማሪዎቻችን በብርዱና በጨለማው ውስጥ ቁጭ ብለው ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ። መብትንና ክብርን ለማስከበር የሚደረግ ጉዞ
ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ አሁን ምሽት 2:40 ሰዓት ድረስ፣ ተማሪዎቻችን በብርዱና በጨለማው ውስጥ ቁጭ ብለው ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ። መብትንና ክብርን ለማስከበር የሚደረግ ጉዞ መራራና ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ የእነዚህ ወጣቶች ጽናት ግን የፍትሃዊነታቸው ትልቁ ማረጋገጫ ነው። 📌 ለተማሪዎቻችን፦ በዚህ ብርድ በበዛበት ምሽት እያሳያችሁት ያለው ተስፋ አለመቁረጥና ቁርጠኝነት ታሪክ የማይረሳው ታላቅ የጽናት መዝገብ ነው። ቅስናችሁ አይሰበር፣ ሞራላችሁ አይውረድ። በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት የምታሳዩት ትዕግስት (ሰብር) እና አንድነት ለነገው ድላችሁ መሰረት ነው። አላህ እውነተኞችንና መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁትን መቼም ቢሆን አይጥልም። 📌 ለሚዲያ አካላት፦ እነዚህ ወጣቶች የነገዋ ሀገር ተስፋዎች እንጂ የሁከት አራማጆች አይደሉም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ህጋዊና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ይዘው መልስ ፍለጋ በብርድ ላይ ተቀምጠዋል። ለነዚህ ተማሪዎች ድምጽ በመሆን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን። 📌 ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፦ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ላነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምላሽ መስጠት የሀላፊነት ሁሉ መጀመሪያ ነው። ጉዳዩን በቸልተኝነት መመልከት ወይንም ማዘግየት መፍትሄ አይሆንም። አሁንም ጥያቄያችን ግልጽ ነው! ከምላሹ መሸሽ አይቻልም! 📌 ለመጅሊስ፦ የናንተ የመጀመሪያ ኃላፊነት የሙስሊሙን መብት ማስጠበቅ ነው። ሰላማዊው ጥያቄያችን በፍትሐዊ መንገድ ይመለስ ዘንድ ስሩ። ሴት ልጅ ብርድ ላይ አትደር፤ ተማሪዎች እንቅልፍ አጥተው ሜዳ ላይ አይደሩ። ስለፍትሕ ቁሙ! ታሪክ እየተፃፈ ነው!! 📌 ለሙስሊም ማህበረሰብ፦ እነዚህን በብርድና በጨለማ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን በዱዓና በሞራል ከጎናቸው ቁሙ። ©️ @EHEMSU

እዚያ ያለውን ተማሪ ማስነሳት ሲያቅታቸው ተማሪዎች ወደግቢው እንዳይገቡ እየከለከሉ ይገኛሉ። አሁንም መፍትሄው የተማሪን ድምጽ ማፈን ሳይሆን ለተጠየቀው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ነው። ጥያቄ አለን! መልስም እንፈልጋለን! Video: አሁን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ©️aaumsu @EHEMSU

ፌደራል ፖሊሶች ተማሪውን እንዲበተን ለማድረግ እየሞከሩ ቢሆንም ተማሪው አሁንም በእምቢታው ቀጥሏል። ©️aaumsu @EHEMSU
+2
ፌደራል ፖሊሶች ተማሪውን እንዲበተን ለማድረግ እየሞከሩ ቢሆንም ተማሪው አሁንም በእምቢታው ቀጥሏል። ©️aaumsu @EHEMSU

ወረቀት ያሳጥራል waraqata ni gabaabsa

በለተሞ መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ! ~ 1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው። 2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል። 3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም። 4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!" 5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትን ጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ። 6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ። በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው። ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor ◈ እንደ ለተሞዎች አትሁን! በብዙ ቦታዎች የሚስተዋለው ለተሞዎች የሱና ሰዎችን እንደሚያኮርፉ ነገር ግን ከተለያየ የቢድዓ ሰዎች ጋር "ጥሩ" መስተጋብር እንዳላቸው ይታወቃል። ➮ አህባሾች እንኳን ሲገናኙ ሰላምታ ይለዋወጣሉ አንተ ግን ለሰላምታህ እንኳን መልስ ላይሰጡህ ይችላሉ በዚህ መሰረት አድርህ እንደ ለተሞዎች አትሁን! አንተ እንደ እሱ ከሆንክ በምን ትሻላለህ?! ሙስሊምን ሰላምታ የሰጠህን አታኩርፍህ የሚስሊም መገለጫ ያየህበትን ሁሉ ኢስላማዊ ሰላምታ ስጥ! መኮራረፍ አይገባም! ይህም ሲባል ለክርክር ቦታ ከመክፈት ተጠንቀቅ! 🖊 አቡ ተይሚያ https://t.me/Menhaje_Selef/ ለበለጠ ይህችን ቻናል ተቀላቀሉ👇👇👇 https://t.me/yedaewachannel https://t.me/yedaewachannel

በመጨረሻም ሙስጠፋ -አላህ ይምራውና- አሁን ሀገር አቋርጦ ተጉዞ እየተማርኩባቸው ነው የሚላቸው ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ ስለ ሸይኽ ረቢዕ ምን እንዳሉ አውስቸ ፅሁፌን አጠናቃለሁ። ▫️ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ:- ↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ عبدالعزيز الراجحي –حفظه الله-: ما نصّه: بعض الناس يتهم من تمسك بالمنهج السلفي بأنّه جامي، ويحذر من الشيخ ربيع والشيخ النجمي والشيخ زيد بن محمد هادي المدخلي وغيرهم من أهل العلم؟ "ከፊል ሰዎች የሰለፊያን መንሃጅ አጥብቆ የያዘን አካል ጃሚይ ነው ይላሉ። ከሸይኽ ረቢዕ፣ ከሸይኽ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ከሸይኽ ዘይድ አልመድኸሊይና ከሌሎችም የዒልም ባለቤቶች  ያስጠነቅቃሉ። ተብለው ተጠየቁ። فأجاب بقوله: ((الألقاب لا تغيّر، النبز بالألقاب لا يصلح، المهم ثقل الشخص، المشايخ نعرف أن معتقدهم سليم، ومن أهل السنة والجماعة، الشيخ ربيع والشيخ أحمد والشيخ زيد لا غبار عليهم)). ሸይኹም -ሓፊዘሁላህ- እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ስያሜ ለውጥ አያመጣም። በቅፅል ስም መሰየምም አይገባም። ዋናው የሰወየው ማንነት ነው። የተወሰቱ መሻኢኾች ዓቂዳቸው እንከን የሌለበት መሆኑን እናውቃለን። ከአህሉሱናዎችም ናቸው። ሸይኽ ረቢዕ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ዘይድ ምንም አይነት አቧራ (እንከን)  የለባቸውም።" ↩️ وسئل –أيضاً-: ما رأيكم في كتب وأشرطة الشيخ ربيع بن هادي المدخلي –حفظه الله، هل تنصحون بقراءة كتبه واستماع أشرطته؟ በሌላም ጊዜ "ስለ ሸይኽ ረቢዕ ኪታቦች እና ካሴቶች ምን ይላሉ? ኪታቦችን በማንበብና ካሴቶችን በማዳመጥ ይመክሩናልን?" ተብለው ተጠየቁ። فقال: ((نعم، لا بأس بها، كتبه وأشرطته ما رأينا فيها ما ينتقد، ما انتقدت فيها شيئاً، أشرطته جيّدة، وكتبه جيدة ومفيدة)) [من شريط لدى تسجيلات منهاج السنّة بالرياض].   እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ "አዎ! ችግር የለባቸውም። ኪታቦቹም ካሴቶቹም ውስጥ የሚተቹ ነገሮችን አላየንም። ካሴቶቹ ምርጥ ናቸው። ኪታቦቹም ምርጥና ጠቃሚዎች ናቸው።" የሸይኹ ንግግር ይህን ይመስላል። የሌሎችም የሱንና ዑለማኦች በተመሳሳይ "ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ የሱንና ዓሊም ናቸው።" ይሉናል። መነሻና መድረሻ የሌላቸው የኸዋሪጅ ስራ አስፈፃሚ እና የተክፊር አቀንቃኝ የሆኑት እነ ሙስጠፋ ደግሞ "የሱንና ሰው አይደሉም። ሙርጂእ ናቸው።" ይላሉ። ማንን መስማትና መቀበል እንዳለብህ እራስህ ታቃለህ። ይህን ስል ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ እኛ ሸይኽ ረቢዕም ይሁኑ ማንም ዓሊም አያጠፋም አይሳሳትም ማለታችን አይደለም። ነገር ግን የሱንና ዓሊም የሱንና ዓሊም ነው። ስህተቱ እንደ ስህተት እውቀታዊ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንጅ ማንም የመንደር ጎረምሳ እገሌ ሙርጅእ ነው እያለ ሊላገግ አንፈቅድለትም። እናም ማንሳት የፈለኩት ሸይኽ ረቢዕን ከሱንና ውጭ ናቸው የሚለው የነ ሙስጠፋ አቋም የሓዳዲያና የተክፊሮች ቅዠት እንጅ ሁሉም የሰለፊያ ዑለማኦች ሸይኽ ረቢዕ የሱንና ሰው መሆናቸውን ያረጋገጡት እወነታ መሆኑን ነው። የነ ሙስጠፋ ቁማር ግን እንዲህ ነው ከገባህና ከሰማሃኝ። የሆነን አቋም ሲዪዙ በሆኑ ዓሊሞች ለመጠለል ይሞክራሉ የፈለጉትን ይሰቅላሉ የፈለጉትን ያወርዳሉ። ትላንት የሕየል ሓጁሪን በጭፍን ተከትለው ሃገር ሲያምሱ እያለ ሲሉ የነበረው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ የሕያን ጠብ እርግፍ አድርገው ትተው ላመጡት የተክፊር ጉዞ በመዲና ዑለማኦች እራሳቸውን ይወሽቃሉ። የመዲና ዑለማኦች ያሉበትና የነእርሱ ጉዞ ግን ሰማይና ምድር ነው። እስኪ መልሱልን ሸይኽ ረቢዕን ኢብኑ ባዝ ናቸው ሙርጂእ ያሉት? ወይስ ሸይኽ ፈውዛን? ወይስ ራጂሒይ እስኪ ንገሩን። አላህ ሁላችንንም ለሚወደው መንገድ ይምራን። رحم الله الشيخ المجاهد ربيع السنة وأسكنه فسيح جناته، ሐምሌ 6/2017 የቴሌግራም ቻናል = t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

▫️. ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ ኢብኑ ዑሠይሚን -ረሒመሁላህ- ↩️ قد سئل الشيخ العلامة محمد بن صالح بن عثيمين –رحمه الله- عن الشيخ ربيع كما في (شريط الأسئلة السويدية) فقال :” أما بالنسبة للشيخ ربيع فأنا لا أعلم عنه إلا خيراً والرجل صاحب سنة وصاحب حديث”. ኢብኑ ዑሰይሚን ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ሸይኽ ረቢዕን በተመለከተ ከእርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም። ሰውየው የሱንና እና የሓዲሦ ባለቤት ናቸው።" ↩️ وجاء في الشريط الأول الذي هو بعنوان (كشف اللثام عن مخالفات أحمد سلام ) -عبر الهاتف من هولندا-: سؤال: ما هي نصيحتكم لمن يمنع أشرطة الشيخ ربيع بن هادي بدعوى أنها تثير الفتنة وفيها مدح لولاة الأمور في المملكة وأن مدحه ـ أي مدح الشيخ ربيع للحكام ـ نفاق؟ الجواب : "رأيُنا أن هذا غلطٌ وخطأٌ عظيم، والشيخ ربيع من علماء السنة، ومن أهل الخير، وعقيدته سليمة، ومنهجه قويم. لكن لما كان يتكلم على بعض الرموز عند بعض الناس من المتأخرين وصموه بهذه العيوب." በሌላም ቦታ የሸይኽ ረቢዕን ካሴቶች ከማዳመጥ ስለሚከለክሉ ሰዎች ተጠይቀው እንዲህ ይላሉ:- "ይህ ታላቅ ስህተት ነው። ሸይኽ ረቢዕ ከሱና ዑለማኦች ውስጥ ናቸው። ከኸይር ባለቤቶችም። ዓቂዳቸውም እንከን የለሽ መንሃጃቸውም የተስተካከለ ነው። ..." ↩️ وسئل ما نصّه: يقال أن منهج الشيخ ربيع يخالف منهج أهل السنة والجماعة؟ فأجاب بقوله: "ما أعلم أنه مخالف، والشيخ ربيع أثنى عليه أهل العلم المعاصرين، أنا ما أعرف عنه إلا خيراً" [شريط ثناء أئمة الدعوة على الشيخ ربيع]. "የሸይኽ ረቢዕ መንሃጅ የአህለሱንና ወልጀማዓዎችን ይቃረናል ይባላል?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም "እኔ መቃረናቸውን አላቅም። ሸይኽ ረቢዕ ማለት የዘመናችን ዑለማኦች አወድሰዋቸዋል። እኔ ከርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም።" ▫️.ሸይኽ ፈውዛን -ሐፊዘሁላሁ ተዓላ- ↩️ قد أثني عليه الشيخ العلامة صالح بن فوزان الفوزان –حفظه الله- في تقديمه لكتاب “منهج الأنبياء في الدعوة إلى الله فيه الحكمة والعقل” و في تقديمه لكتاب “جماعة واحدة لا جماعات” في الرد على عبدالرحمن عبدالخالق، ሸይኽ ፈውዛን ለሸይኽ ረቢዕ ብዙ መፅሃፎች መግቢያ ሲፅፉ በርካታ ውዳሴዎችን ተችረዋቸዋል። አንዴ ደግሞ ተጠይቀው በዚህ መልኩ መልስ ሰጥተዋል። ↩️ وسئل فضيلته في شريط ” الأسئلة السويدية ” (5 ربيع الآخر 1417 هـ) فقال بعد ما ذكر الشيخ ربيعاً مع مجموعة من أهل العلم: "كذلك من العلماء البارزين الذين لهم قدم في الدعوة، فضيلة الشيخ عبدالمحسن العباد، فضيلة الشيخ ربيع هادي ...،" ▫️. ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ -ረሒመሁላህ-: ↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي –رحمه الله-: في شريط ” الأسئلة الحضرمية”: ما رأيك فيمن يقول عن الشيخ ربيع أنه متهّور؟ فأجاب –رحمه الله- : "الشيخ ربيع له خبرة بمعرفة الواقع لأنه عاش مع الإخوان المفلسين زمناً طويلاً -والحمد لله- هو أحسن من يعالجون الأمور وينكر على المبتدعة ابتداعهم فأسال الله أن يحفظه. ሸይኽ ሙቅቢልም በዚህ መልኩ አወድሰዋቸዋል። የሸይኽ ረቢዕን ኪታቦችና ካሴቶች እንድንጠቀምባቸውም በዚህ መልኩ ይመክራሉ። ↩️ وقال الشيخ –رحمه الله- في جواب له على سؤال: "وأنا أنصح الأخوة بالاستفادة من كتب أخينا الشيخ ربيع بن هادي –حفظه الله تعالى- فهو إن شاء الله [بصير] بالحزبيين، ويخرج الحزبية بالمناقيش .... ،" ↩️ وقال في كتاب “تحفة القريب والمجيب” السؤال (75): "وأنصح بقراءة كتاب أخينا في الله ربيع بن هادي “جماعة واحدة لا جماعات وصراط واحد لا عشرات” فهو كاف واف". በሌላም ቦታ ሰዎች ከታላላቅ ዑለማኦች ጋር ግንኙት እንዲኖራቸውና ከቻሉም ወደእነርሱ በአካል እንዲጓዙ ሲመክሩ ሸይኽ ረቢዕን ለምሳሌ ያወሳሉ። ↩️ وقال في السؤال (123): "الذي ننصح به، أن يراسلوا أهل العلم، وان استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، مثل الشيخ الألباني، والشيخ ابن باز، والشيخ عبدالمحسن العباد، والشيخ ربيع بن هادي، والشيخ ابن عثيمين، فإن استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، وإن لم يستطيعوا أن يرحلوا إليهم فبواسطة الهاتف والمراسلات". በሌላም ጊዜ ወደ እነርሱ ሊመለሱባቸው ስለሚገቡ ዑለማኦች ተጠይቀው ሲመልሱ "ሸይኽ ረቢዕ የጥመት አንጃዎችን በማወቅ ረገድ ከአላህ ተዓምራቶች አንዱ ነው" ሲሉ ያወዱሷቸዋል። ↩️ وفي السؤال (135) لما سئل عن العلماء الذين يرجع إليهم قال: "والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، فهو آية من آيات الله في معرفة الحزبيين، لكن لا كآيات إيران الدجالين" ↩️ وفي السؤال (140) سئل: مَن مِن علماء السعودية تنصحون بالأخذ عنهم وحبذا لو ذكرت لنا بعض الأسماء؟ فقال: "أمّا الذين أنصح بالأخذ عنهم والذين أعرفهم فهم الشيخ: عبدالعزيز بن باز حفظه الله، والشيخ محمد بن صالح بن عثيمين حفظه الله، والشيخ ربيع بن هادي حفظه الله،..." ሸይኽ ረቢዕ ታላቅ የሱንና ዓሊም ለመሆናቸው የተወሱት ታላላቅ አኢማዎች ውዳሴ ከበቂም በላይ ነው። እነዚህን ለምሳሌ አወሳሁ እንጅ ከነዚህም ውጭ እነ ሸይኸ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አል'መድኸሊይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲላህ አስሰቢል፣ ሸይኽ ሷሊሕ አስሱሓይሚይ፣ ሸይኽ ዑበይድ አልጃቢሪይ፣ ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒ እና ሌሎችም በዓለም የሚገኙ ታላላቅ ዑለማኦች በጣም በተዋቡ ገለፃዎች ሸይኽ ረቢዕን አወድሰዋቸውል።

~ ሙስጠፋ ዓብደላህ እና ዑለማኦች    የሙስጠፋ ዓብደላህ ማንነት ዛሬም ያልገባቹህ ካላቹህ እዚህ ጋ ሸይኽ ረቢዕ ላይ ሐያእ በጎደለው አንደበቱ እንዴት እንደሚላገግ ተመልከቱ። የእርሱን የተክፊር አካሄድ አጥብቀው ስለኮነኑና የሓዳዲያዎችን ፀያፍ ገፅታ በሚገባ ስላብራሩ ብቻ አስፀያፊ በሆነው የኢርጃእ ቢድዓ ይወርፋቸዋል። ሙርጂኣዎች አህለሱናዎች አለመሆናው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ሙስጠፋ እከተላቸዋለሁ እያለ የሚሞግታቸው የመዲና ዑለማኦችም ይሁኑ በዓለም ያሉ የሱና ዑለማኦች ግን ሸይኽ ረቢዕ -ረሒመሁሏህ- ታላቅ የሱንና ዓሊም፣ የሰለፊያ ረዳት እና የቢድዓ ሰዎችን አንገት ያስደፉ ታላቅ ሙጃሂድ መሆናቸውን ባንድ ድምፅ ይመሰክራሉ። ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱ ዑለማኦች እጅግ በጣም በርካታ ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ የተወሰኑትን እናውሳ። ◾️ ለምሳሌ :- ▫️. ሸይኽ ኢብኑ ባዝ -ረሒመሁሏህ-: ↩️ قال الإمام العلامة سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز -رحمه الله تعالى- "الشيخ ربيع من خيرة أهل السنّة والجماعة، ومعروف أنّه من أهل السنّة، ومعروف كتاباته ومقالاته" [شريط بعنوان ثناء العلماء على الشيخ ربيع-تسجيلات منهاج السنة]. "ሸይኽ ረቢዕ ከምርጥ አህለሱንና ወልጀማዓዎች ናቸው። ከአህለሱንና መሆናቸው የታወቀ ነው። እንደዚሁም ኪታቦቹና ንግግሮቹም ታዋቂ ናቸው።" ↩️ وقد سئل ـ رحمه الله تعالى ـ عن الشيخ ربيع بن هادي والشيخ محمد أمان فقال: "بخصوص صاحبي الفضيلة الشيخ محمد أمان الجامي والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، كلاهما من أهل السنة، ومعروفان لدي بالعلم والفضل والعقيدة الصالحة،" [شريط الأسئلة السويدية]. ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አማን እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:- "ሁለቱም የተከበሩ የሱንና ሰዎች ናቸው። ሁለቱም እኔ ዘንድ በዒልም፣ የተከበሩ በመሆናቸውና በትክክለኛ ዓቂዳቸው የታወቁ ናቸው።" ↩️ وقال-رحمه الله-: "وإخواننا المشايخ المعروفون في المدينة ليس عندنا فيهم شك، هم أهل العقيدة الطيبة ومن أهل السنة والجماعة مثل الشيخ محمد أمان بن علي، ومثل الشيخ ربيع بن هادي ... ،" [شريط توضيح البيان]. "መዲና ውስጥ ያሉ የታወቁ መሻኢኾችና ወንድሞቻችን እነርሱን በተመለከተ እኛ ዘንድ ምንም አይነት ጥርጥር የለም። እነርሱ የምርጥ ዓቂዳ ባለቤቶች ናቸው። ከሱንና ሰዎችም ናቸው። ምሳሌ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ፣..." ↩️ وقال الشيخ العلامة ربيع بن هادي المدخلي في كتابه “إزهاق أباطيل عبداللطيف باشميل” (ص:104): "لقد زرت سماحة الشيخ ابن باز –حفظه الله- فنصحني بالرد على كل مخالف للحق والسنة. ونِعْمَة النصيحة، فما أعظمها، وأوجبها على من يستطيع القيام بها." ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝን አንዴ ዘየርኳቸውና በማንኛውም ሐቅን የተፃረረ አካል ላይ መልስ እንድሰጥ መከሩኝ። ያማረች ምክር!! ምን የገዘፈች አደረጋት!! በእርሷ ለሚቆምባት አካል ምን የወጀበች አደረጋት!" ↩️ قال الشيخ خالد بن ضحوي الظفيري: "وقد سمعت بأذني الشيخ ابن باز –رحمه الله- يقول مخاطباً الشيخ ربيعاً: "يا شيخ ربيع رد على كل من يخطئ، لو أخطأ ابن باز رد عليه، لو أخطأ ابن إبراهيم رد عليه…" وأثنى عليه ثناءً عاطراً، والله على ما أقول شهيد. [الثناء البديع من العلماء على الشيخ ربيع] ሸይኽ ኻሊድ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንዲህ ብለው ሲያናግሩ በጆሮየ ሰምቻለሁ:- "ሸይኽ ረቢዕ ሆይ! በማንኛውም የተሳሳተ አካል ላይ ረድ አድርግ (መልስ ስጥ)። ኢብኑ ባዝም ቢሳሳት መልስበት። ኢብኑ ኢብራሂምም ከተሳሳቱ መልስባቸው።" ↩️ ويقول الشيخ خالد أيضا : "بل قد أذن له سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز بالتدريس في مسجده وذلك قبل وفاته بأشهر، مما يدل على أنه توفي وهو عنه راض." [المصدر السابق] እንዲህም ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ከመሞታቸው ከወራት በፊት ሸይኽ ረቢዕ በመስጅዳቸው እንዲያስተምሩ ፈቅደውላቸዋል። ይህም ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንደወደዷቸው መሞታቸውን ነው የሚያመላክተን።" ¤ ከዚህም ውጭ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱባቸው ንግግሮች በጣም በርካታ ናቸው። የሸይኽ ኢብኑ ባዝን ንግግር ደጋግሜ ያወሳሁት እነ ሙስጠፋ እንከተላቸውዋለን እያሉ በሚሞግቱት ቀጣፊዎች መሆናቸውን ለማሳየት ያክል ነው። ▫️. ሸይኹል አልባኒይ -ረሒመሁላህ-:- ↩️ قال الشيخ العلامة المحدث محمد ناصر الدين الألباني –رحمه الله- في شريط (الموازنات بدعة العصر للألباني) بعد كلامٍ له في هذه البدعة العصرية: "وباختصار أقول: إن حامل راية الجرح والتعديل اليوم في العصر الحاضر وبحق هو أخونا الدكتور ربيع، والذين يردون عليه لا يردون عليه بعلم أبداً، والعلم معه،"   "ባጭሩ በዘመናች የጀርሕ እና ተዕዲል ባንዴራ ተሸካሚ በእርግጥም ወንድማችን ዶ/ር ረቢዕ ናቸው። በእርሱ ላይ መልስ የሚሰጡ ሰዎች መቸም በእውቀት ላይ አይመልሱም። እውቀት ከእርሱ ጋር ነው።" ↩️ ويقول أيضا عن الشيخ ربيع والشيخ مقبل رحمهم الله تعالى: "... فهؤلاء الذين ينتقدون الشيخين ـ كما ذكرنا ـإما جاهل فيُعلّم، وإما  صاحب هوى فيُستعاذ بالله من شره، ونطلب من الله -عز وجل- إما أن يهديه وإما أن يقصم ظهره." شريط ( لقاء أبي الحسن المأربي مع الألباني )  ሸይኹ በሌላ ጊዜ ስለ ሸይኽ ሙቅቢል እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ሲሊ ተናግረዋል:- "ሁለቱን ሸይኾች የሚተች አካል ወይ መሃይም ነው ሊማር ይገባዋል። ወይ ስሜቱን ተከታይ ነው።...."

እናቴ አላህ ላንች ስል ያኑረኝ እንጅ እንደኔ ወንጀል እና ክፋት የተሻለ ካደረገልኝ ቢወስደኝ ይሻለኛል። ያረቢ...... አላህ የተሻለ ነገር ይስጠኝ። በለተሞ መንጋ እና በተክፊር መንጋ እንደት ሰው እራሱን አላስፈላጊ ቦታ ላይ ይጥላል።

በእኛ ላይ ግደታ የሚሆነው ነገር እውነትን ብቻ መናገር ነወ።የሚቆጣም ይቆጣ፤የወደደም ይውደድ፤ውደታን የምንፈልገው ከአላሁ ሱብሀነሁ ወተዐላ ብቻ ነው።

📚 የኪታቡ ስም ፡ በሰለፊያዊ መንሓጅ የተመዩዕ ወንጀል اسم الكتاب : جناية التميّع علی المنهج السلفي  المؤلف : العلامة الشيخ عبيد بن عبد الله الجابري ፀሀፊ ፡ 🖊 ታላቁ ሸይኽ ዑበይድ ብን ዐብዲላህ አል-ጃቢሪይ ረሂመሁሏህ https://t.me/Menhaje_Selef/

ተርጓሚውን አዳምጥ። ሸይኽ ረሻድ አልሑበይሺ አሜሪካ ከገቡ ቆይተዋል። ብዙ ጊዜ ይመላለሳሉ። የአህለሱና ደዕዋ ወደ "ዋይት ሀውስ" ይገባል ጠብቅ።

وقفات مع سورة الأنفال.mp31.02 MB

ومن تأمل في مسلك طائفة من دعاة الصحوة وجد أنهم يألفون أهل البدع وينصرونهم ويعنفون على من يرد عليهم بدعتهم ويتسامحون مع دعوتهم ويتحالفون معهم في العمل الدعوي ويلزمون الصمت في كثير من انحرافاتهم ويهونون من إجماع السلف في هذا الباب ويتأولون كلامهم ويحرفونه عن مراده ولا يلتزمون هذا الأصل في منهجهم وخطابهم ويحاولون الالتفات عليه بتقعيدات وشبه وأمثلة فاسدة وهذا خلاف منهج علمائنا الكبار الذين عرف عنهم التحذير من مجالسة أهل البدع والأخذ عنهم وذلك لأنهم كانوا ينهلون من مشكاة النبوة وفقه السلف الصالح فمن كانت دعوته مقتفية لمنهج السلف حذر من اتباع الخلف ومن كانت دعوته مقتفية لمذهب الخلف زهد في آثار السلف ووالى أهل البدع. وقد سئل شيخنا ابن باز: الذي يثني على أهل البدع ويمدحهم هل يلحق بهم؟ فأجاب: (نعم ما فيه شك من أثنى عليهم ومدحهم وهو داع إليهم هو من دعاتهم نسأل الله العافية). وقال أيضا: (من أظهر المنكر أو البدعة يحذر منه ولا ينظر إلى حسناته حسناته بينه وبين ربه من أظهر المنكر أو البدعة يحذر منه وينصح حتى يهتدي هكذا جاءت السنة). وهذا المسلك المحدث أعني صحبة أهل البدع والتسامح معهم وتزكيتهم ومد الجسور معهم له أثر سيئ في انحراف الأتباع والصغار فكم من شاب كان على خير وسنة ثم دخلت عليه بدعة من طريق ثناء أستاذه على أحد المبتدعة بقوله الحق أو فصاحة لسانه أو اجنهاده في الدعوة أو ثقافته الواسعة فاشرأب عنق هذا الفتى للاستفادة منه فخالطه أو تتلمذ على كتبه فانحرف عن السنة كان أبو ذر الهروي راوي صحيح البخاري من أهل الحديث على الجادة وكان يسير يوما مع شيخه الدارقطني في بغداد فالتقوا بأبي بكر الباقلاني الأشعري فالتزمه الدارقطني وقبله وأثنى عليه في مناظرته للمعتزلة فتأثر التلميذ أبو ذر الهروي بموقف شيخه فعظمه وأخذ عنه علم الكلام المحدث وصار من رؤوس الأشعرية ودعاتها المتعصبين لها ثم أخذ عنه جل المغاربة مذهب الأشاعرة وكان له دور بارز في تحول بلاد المغرب من مذهب أهل الحديث إلى مذهب الأشاعرة قال ابن كثير: (والمغاربة إنما أخذوا الأشعرية عن أبي ذر الهروي). فهؤلاء الدعاة المتسامحون مع المبتدعة إنما هم مسوقة لمذهب المبتدعة بطريقة لا يفطن لها كثير من أهل الديانة وخطرهم عظيم على السنة ولهذا قال ابن عون: (من يجالس أهل البدع أشد علينا من أهل البدع). وقد وجد من مشاهير الدعاة من يقبل رؤوس الإباضية والأشاعرة والصوفية والإخوان ومن يعزي الشيعة ومن يتصالح مع وجوه الليبرالية من غير نكير واستهجان بين أهل السنة. وقد رأينا كيف انتشر مذهب الخوارج والليبرالية والمرجئة والصوفية عند شبابنا بعد نحو عقدين من الصحوة وكانت هذه النتيجة حتمية للابتعاد عن المدرسة السلفية والارتباط بمدرسة الإخوان الفكرية المنحرفة عن منهج أئمة السلف الصالح.