cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Sŧ🌠r ⚫D🌟ñćə

ሀዘን😧 ድብርት😯 ጭንቀት😵 ውስጣችን አይደለም አንኛ ምንፈልገው Jest ፈታ👉 join በማለት ይቀላቀሉን 👉የተለያዩ የ dance ውድሮች እናወዳድራለን 👉tutorial የ dance videos ይለቀቃሉ 👉Normal dance video አሉን for any comment & cross contact the admin 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @danceruuuu @stardancegroup

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
180
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✔️ለ20 ደቂቃ ከሃሳብ ተላቆ በደንብ መመሰጥ ለ2 ሰአት ከመተኛት እኩል ነው። @thiolophy @menge_degnaw @tobiyan *
نمایش همه...
نمایش همه...
@thiolophy @menge_degnaw @tobiyan ስለ ማሰላሰል ሳስብ ይሄን እረዳለው
نمایش همه...
نمایش همه...
نمایش همه...
نمایش همه...
የማያጠግብ እንጀራ (ሜሪ ፈለቀ) ጥፍጥፍ ነኝ!! ይሄ የሚወዷትን ጎራዳ ሲያቆላጵሷት 'ጥፍጥፍ' የሚሏት ዓይነት አይደለም:: እልም ያልኩ ጥፍጥፍ ነኝ:: ሰዎች ከፊት ገፅታ ላይ መርጠው 'ከንፈሯ ሲያምር' 'ዓይኗ ሲያምር' ሲሉ ያልተገለጠላቸው የውበት ቀመር መኖሩ ፍንትው ይልልኛል:: እኔን ቢያዩ እላለሁ:: ዓይን ያለ አፍንጫ በፍፁም ብቻውን አያምርም:: ከንፈርም እንደዛው.... ጎላ ጎላ ያሉ ዓይንና ከንፈር ከሰራልኝ ወዲያ የረሳው በሚመስል ዓይነት አፍንጫዬን ዘለለው:: ዘለለው ነው እኮ የምላችሁ:: መናፈጫ የለ .... መነፅር መደገፊያ የለ .. በምንም ዓይነት concealer የማይቀና .. እሱማ ጥርሴንም እንደ ድሃ የእንጨት አጥር እዚያና እዚህ ዘርዝሮ ነበር የተከለልኝ:: ቤተሰቦቼ ምስጋና ይግባቸውና ማስተካከል የሚቻለውን እንኳን እናብጅላት ብለው ነው መሰለኝ በልጅነቴ አሰብስበው አሳስረውልኝ ድርድር ጥርስ ባለቤት ለመሆን በቃሁ:: ይኸው በ30 ዓመቴ የጠበሰኝ የመጀመሪያ ወንድ "የኔ ውብ" እያለ ሲጠራኝ ሳቅና ለቅሶ ይሳከርብኝ ይዟል:: ሆ .. የመጣበት ቀን ጭራሽ "የኔ ቆንጆ " ይለኝና ከአጥንትና ከቆዳ በተሰራ ቂጤ ከተቀምጥኩበት ወንበር ተስፈንጥሬ ተነስቼ ሌላ ሴት ፍለጋ አማትራለሁ:: (አሁን ፈጣሪ ግን እንደው ካልጠፋ አፈር .. ቂጥ? እኮ ይሄ ለመቅረፅ ልፋት የሌለውን መቀመጫ ይነሳኛል? ) ሲመስለኝ የሆነ የጥፍጥፍ ማሳያ ፈልጎ የሰራኝ ይመስለኛል:: አባቴ መጽሐፍ ቅዱስ የሆነ ቦታ ላይ መልዓክት ከሰው ልጆች ጋር ባልገው ድቅል ዝርያ እንደፈጠሩ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ:: ይሄን ነገር ስሰማ ብዙ ጥያቄዎች ይመጡብኛል? ሰዎቹ መቼም አማላይ ሴቶች ናቸው .. የመልዓክ ሴት አለው እንዴ? ኸረ ቀድሞ ነገር ወንድስ ቢሆን መልዓክት አክሱም አላቸው እንዴ? ማነው ቀድሞ የወሰወሰው? የት ተገናኝተው ተሸፋፈዱ? የት ነውስ የተጣመዱና ያላቡት? ብቻ የሆነ ሆኖ የመልዓክና የሰው ዝርያ ተፈጠረ:: ውቦች ... ቁመተ ለግላጋ .., አፍንጫ ሰልካካ ... እና ሲመስለኝ አንዲት የውቦች ንግስት .. የሆነች የመላዕክት ዝርያ ያላት የድቅሎቹ የልጅ ልጅ ልጅ ልጅ ልጅ .... የሆነ ቀን መስታወቷ ፊት ተሰድራ ... " አምላኬ ሆይ ቤተሰቦቼ ሁሉ ከኔ የሰለከኩ ናቸው:: ለምን መካከለኛ ሰልካካ አድርገህ ፈጠርከኝ? ምን በደልኩህ? ከኔ በላይ ጥፍጥፍ በዓለም ላይ አልሰራህም::" እያለች ከቤተ መንግስቷ ፍጣሪ ዙፋን ስር እንደወንዝ የተንፎለፎለ እንባ አነባች:: ያው የመላዕክት ዝርያ እንጥፍጣፊም አይደለች? አዘነላት!!! ጥፍጥፍ ምን እንደሚመስል ማሳያ እኔ ተጠፈጠፍኩ:: ... እሷ ተፅናናች:: እኔን ምን ያፅናናኝ? በዚህ ላይ ወላጆቼ ሙድ ሲይዙ ምን ብለው ሰየሙኝ "ውብ ዓለም" ቡፍፍፍፍ ... ከፍተኛ ልግጫ መሆኑ የገባኝ ቀን "ስሜን ቀይሩልኝ:: አልፈልግም" ብዬ እሪሪሪ አልኩ:: "ውብ ዓለም አንቺነትሽን እንጂ መልክሽን አይደለም የሚገልፀው:: ውብ የሆነ ዓለም አንቺ ውስጥ አለ ማለት ነው::" ብሎ አባቴ ተፈላሰፈልኝ:: እስከአሁንም ድረስ ግን ሰዎች ልክ ጨብጫቸው ስሜን ስነግራቸው ሳቃቸውን እንዳላይባቸው ከከንፈራቸው ጋር ግብ ግብ ይገጥማሉ:: "ላግባሽ?" አላለኝም ታዲያ ይኸው የአንድ ኢትዮጵያዊ አማካይ የመኖር እድሜ ገሚሱን ካገባደድኩ በኃላ የጠበስኩት ሰው:: ከኔ መለስ ያለ ጥፍጥፍ ነው:: እኔና እሱ ተጋብተን ከኔ የባሰች ሰልካካ ሴት ባየች ቁጥር ቁርንድድ ፀጉሯ በብስጭት የሚቆም ጥፍጥፍ እንውለድ? በፍፁም!!! "ለምን ልታገባኝ ፈለግክ?" "ስለምወድሽ ነዋ!!" "እኮ እንዴት ወደድከኝ?" "የሚወደድ ማንነት ስላለሽ" ህምምምም ....ዓመት ሆነን:: አንድም ቀን እውነት ሳይመስለኝ:: ግን ልለየው አልፈልግም:: ውሸቱን ነው ብዬ እያሰብኩም ደጋግሞ እንዲዋሸኝ እፈልጋለሁ:: የኔ ቆንጆ ... የኔ ውብ... በውስጤ ድገምልኝ ውሸትህን እለዋለሁ:: እንደሴት የተኖረ ዘመን አልነበረኝም:: ከልጅነቴ ጀምሮ የማሰቢያዬ የሆነኛው ክፍል እንደሴት በማጎጥጎጫ እድሜዬ የሚያሽኮረምሙኝ እንደማልሆን ገብቶኝ ነበር መሰለኝ ጨዋታዬና ውሎዬ ከወንዶች ጋር ነበር:: ኳስ ስራገጥና ካራቴ ስማር ጡንቻ ያወጡት ባቶቼና ክንዶቼ ተደምረው "አንተ" እንጂ "አንቺ" የሚለኝ አልነበረም:: ሴትነት እጣ ፋንታዬ አለመሆኑ ገብቶኝ መሰለኝ ሌሎች ነገሮች ላይ አተኮርኩ:: መማር : ዝም ብሎ መማር ... ህክምና አጥንቼ ዶክተር ሆንኩ:: ጥሩ የሚባል ስራ ኖረኝ:: የሆነኛው እድሜዬ ላይ ግን ሴት መሆን አማረኝ:: እርግፍ አድርጌ በኳስና በካራቴ የቀየርኩት ሴትነት ናፈቀኝ... መሽኮርመም .. ቁርንድድ ፀጉሬ ላይ የህንዷን ፀጉር ሰክቶ መቆላት.. ጥፍር ማስተከል.... ቅንድብ መግጠም... ጥፍጥፍነቴ በነዚህ ሁሉ አይሞላም ነበር:: ... ድጋሚ ሴትነትን እርግፍ አድርጌ ትቼው ህክምናን ብቻ ህይወት አድርጌ ስኖር .... የኔ ቆንጆ እያለ የሚዋሸኝን ጣለልኝ:: "ማግባት አልፈልግም:: ... መለየትም አልፈልግም:: ይሄ ከተስማማህ አብረኸኝ ሁን:: ካለበለዚያ ነፃ ነህ::" አልኩት:: 🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️ (ወደ ቀደመው አጫጭር ፅሁፋችን መለስ ስንል)
نمایش همه...
┈┈┈◦◎●◉ትኩሳት◎●◉◦┈┈┈ ➛ ስብሃት ለትምህርት ወደ ፈረንሳይ በተላከበት ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር በፓሪስ ያሳለፈውን ጊዜ የሚተርክ። ➛ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ከኢትዮጵያ ባህልና ስርአት ወጣ ያለ ልቦለድ ነው። ➛ ከስብሃት ገብረ እግዚአብሔር ክፍል 1 #ማስታወሻ! ➛ቤት እንቀመጥ! ➛እጅ አንስጥ እጅ እንንሳ! °°✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው°° ✦✦ ✦✦ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎አዘጋጅ፦ ◎ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●
نمایش همه...
Tikusat 1.pdf8.70 MB
┈┈┈◦◎●◉ትኩሳት◎●◉◦┈┈┈ ➛ ስብሃት ለትምህርት ወደ ፈረንሳይ በተላከበት ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር በፓሪስ ያሳለፈውን ጊዜ የሚተርክ። ➛ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ከኢትዮጵያ ባህልና ስርአት ወጣ ያለ ልቦለድ ነው። ➛ ከስብሃት ገብረ እግዚአብሔር #ማስታወሻ! ➛ቤት እንቀመጥ! ➛እጅ አንስጥ እጅ እንንሳ! °°✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው°° ✦✦ ✦✦ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎አዘጋጅ፦ ● ◎ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●
نمایش همه...
┈┈┈◦◎●◉አደፍርስ◎●◉◦┈┈┈ ➛ ዳኛቸው ወርቁ በዛብህ አደፍርስ ፲፱፻፷፪ ዓ.ም በተሰኘ ልብ ወለድ ድርሰቱ ባነሳቸው ጭብጦች እና የተራቀቀ የአጻጻፍ ስልቱ የአማርኛን ዘመናዊ ልብ ወለድ ወደ ድንቅ ከፍ ካለ እርከን ያወጣ፥ እምቧ በሉ ሰዎችበሚለው የግጥም መድብሉ ➛ ፲፱፻፷፯ ዓ.ም.ውስጥ በተካተቱ ግጥሞቹ ስለሀገሩ ልማትና ዕድገት ተቆርቋሪነቱን የገለጠ ዕውቅ የሥነ ጽሑፍ ምሁር፥ ሐያሲና ተርጓሚ የነበረ ሲሆን በልሳነ እንግልጣር (እንግሊዝኛ) በመጻፍም «The Thirteenth Sun» የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ በዓለም አቀፉ መድረክ ካስተዋወቁ በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጸሓፍት አንዱ ነበር። ➛ ከዳኛቸው ወርቁ በዛብህ #ማስታወሻ! ➛ቤት እንቀመጥ! ➛እጅ አንስጥ እጅ እንንሳ! °°✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው°° ✦✦ ✦✦ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎አዘጋጅ፦ ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎● ◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●◎●
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.