cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቀልድ እና ቁም ነገር

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
459
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሀይ
نمایش همه...
ውስጥህ ሲደሰት.... ደስታህን በኑሮህ ከሚገጥሙህ ሁኔታዎች ጋር አታገናኘው፤ ደስታ ማለት የችግር አለመኖር አይደለም፤ በችግር ውስጥ እያለፍክ መሳቅ ነው። ነገሮች ምርጥ ሲሆኑማ ሁሉም ይደሰታል እኮ፤ አንተ ግን በአምላክህ እና አጠገብህ ባሉ መልካም ነገሮች ሁሌም ደስተኛ ሁን። ውስጥህ ሲደሰት ውጪህ ላይ ይገለጣል፤ ከዛ አንተ ደስተኛ ስለሆንክ አለም አብራህ ትስቃለች፤ ከባድ የመሰለህ ነገር ተራ ሲሆን ታየዋለህ፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አንተ ጋር ማውራት ወይ አብሮህ መሆን የማይፈልግ የለም፤ ያንተ ስራ መገረም ብቻ ይሆናል። ወዳጄ መቼም የማይተው አምላክ እንዳለህ ማሰቡ ራሱ የደስታ ጥግ ነው።
نمایش همه...
መጠንከር አለብህ! ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ አንተ መክበድ አለብህ፤ ሰዎች ለምን አልተረዱኝም ብለህ አትዘን በተግባር ማን እንደሆንክ አሳያቸው! አለም ለጠንካሮች ታዳላለች፤ ሰዎችም ቢሆኑ ደካማ አይወዱም። ከሁሉ በላይ ግን ለራስህ ስትል ቆራጥ መሆን አለብህ ምክንያቱም በምንም ነገር ውስጥ ብታልፍ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ማንነት ስላለህ! ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
نمایش همه...
ጥቂት ውሳኔ ብዙውን ለውጥ ያመጣል! ህይወታችን ላይ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥረው ትልቁ ውሳኔ አይደለም! እያንዳንዷ በየደቂቃው የምንወስናትና የምናከናውናት ጥቃቅኗ ውሳኔያችንና ተግባራችን ነው እንጂ! መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
نمایش همه...
ባለህ ታመን ! ታላቁ መፅሀፉ "በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል " ይላል ሰው ቦታ ቢሰጠኝ እኮ እስተካከላለው ፣ ትዳር ስይዝ እሰበሰባለው ፣ የስራ እድገት ሳገኝ ጥሩ አድርጌ መስራት እጀምራለው ከሚለው ሀሳብ የሚያሶጣን ትልቅ ቃል ነው ! ትልቁን ነገር አዘጋጅቼላችዋለሁ ግን አሁን ባለቻችው ትንሿ ነገር ተለማመዱባት አለበዚያማ ይከብዳችዋል ማለቱ እኮ ነው ! የምኞታችንን ከሰጠን ኋላ አያያዝ አቅቶን ብናጣው አያምም ታድያ ከአሁኑ ባለን ጠበቅ አርጎ ታምኖ መዘጋጀት ነው እንጂ ! መልካም ጁምዐ ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
نمایش همه...
ወንድ ልጅ ባንቺ ምክኒያት እራሱን ካጠፋ የምር ያፈቅርሻል ማለት ነው አግቢው😜🙃 @kume_neger_be_sake
نمایش همه...
ፍቅርህን ከፍ አድርገው ! ቤቱን ማስተዳደር ያልቻለ ሰው ውጪ ወጥቶ ማንንም መምራት አይችልም ፤ ህይወት ሁሌ ወጥ አይደለች ብዙ ለውጦችን ታስተናግዳለች ለዚህም እኮ ነው ጣፋጭ የሆነችው ስለዚህ ሁሌም ቤትህ ውስጥ ለትዳርሽለቤተሰቦችህ ባጠቃላይ ደስ የሚል ልዩ ደስታን የምትፈጥሪ ጀግና ሁኚ ያኔ አንቺም ሳታስቢው ደስታው ፍቅሩ ሰላሙ ሁሉ ይጋባብሻል እና መቼም ቢሆን ከሁሉ አስቀድመህ ቤትህን አስብ የሁሉ መሰረት የሚጀምረው ከርሱ ነውና የምትፈልገውን የስኬት ጥግ ታገኝበታለህ! መልካም ቅዳሜ ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
نمایش همه...
ሰላማችንን እኛ እንስራው! አባቶቻችን ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ይበላል ይላሉ ፤ ምን ማለታቸው ነው ያስብላል አይደል? የሠው ልጅ ፍቅር እና ሰላም በሌለበት ቦታ 1 ቂጣ እንኳን በልቶ ለመጨረስ አቅም ያጣል የሀሳብ ብዛትና ጭንቀቱ በራሱ ሰውነታቸን ውስጥ ሞልቶ አቅም ያሳጣናል ፤ ለመስራት ፣ መልካም ለማሰብ ፣ መልካም ለማድረግ ሆነ የፈለግነውን ያህል ርቀት እንኳን ለመሄድ ይጎትተናል! ስለዚህ በተቻለን አቅም ያለንበትን አካባቢ ቤተሰባችን ውስጥ በጓደኝነት በሁሉም ቦታ ሰላም እንፍጠር ከእኛ መረጋጋት ይጋባባቸው እነሱ እንደኛ ላይስማሙ ይችላሉ እኛ ግን በፍቅር እንቀበላቸው የእኛ ሰላምና ደስታ በሁሉም ላይ እንዲጋባ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ያኔ መቼም ወደኋላ የማይመለስ ደስታና ስኬት እንላበሳለን! መልካም ጁምዐ ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
نمایش همه...
ሁሉም ለበጎ ነው! ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው። ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማስተዋል አለብህ! ደግሞ አትርሳ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ። ታላቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
نمایش همه...
ፈጣሪ ከአንተ ጋር ነው ! ነገሮች ተስፋ ሊያስቆርጡህ ወደ አንተ ሲመጡ ሶስት ነገሮችን አስብ ፈጣሪ - ከአንተ ጋር እንደነበረ - አሁንም ከአንተ ጋር እንዳለ እና - ወደፊትም ከአንተ ጋር እንደሚኖር ስለዚህ ወዳጄ ሁሉን ነገርህን በፈጣሪህ ላይ ጣልና የሚጠበቅብህን ስራ እርሱ ለሁሉም ምክንያት አለው ! የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
نمایش همه...