cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

📚⏱ ማራኪ ስነ-ፅሑፍ ⏱📚

💦 መብረር ካልቻልክ ሩጥ፣ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፣ መራመድ ባትችል ተንፏቀቅ እንጂ ወደ ፊት መራመድህን አታቁም!👏 መለወጥ ማደግ ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ ቻናል ትክክለኛ ምርጫ ነው! ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን! 🙏 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡👉 https://t.me/maraki_eth 𝙜 𝙧 𝙤 𝙪 𝙥👉 https://t.me/maraki_1 ለአስተያየት👉 https://t.me/Abresh_D7

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
356
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❇️ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው አስሩ ነገሮች! ••●◉ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራትና ስሜታቸውን በመቆጣጠር ይታወቃሉ። በአዕምሯዊ ብስለትና በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች አያደርጉም፡፡ ➊. #ፍርሃት_የለባቸውም መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች #ምክንያታዊ አስተሳሰብን ስለሚያጎለብቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ወደፊት ሊገጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች አስቀድመው ስጋት ውስጥ ለሚጥል ጭንቀት አይዳረጉም ፡፡ ➋. #በሌሎች_ሰዎች_ስኬታማነት_አይቀኑም አዕምሯቸው ሚዛናዊነትን ያጎለበተ ሰዎች ስኬትን ከተቀዳጁ ከሌሎች ሰዎች ትምህርትን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆኑ ይነገራል ፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች በሌሎች ሰዎች ድክመትና ስኬትማነት ላይ ማተኮር የራስን እቅድ ያሳጣል ይላሉ ፡፡ ➌. #ባለፈ_ነገር_አይፀፀቱም ስላለፈው ጉዳይ መጨነቅና በፀፀት ጊዜን ማሳለፍ ለወደፊቱም እቅድን እንዳይነድፉ መሰናክል ይሆናል ፤ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ካለፈው ችግራቸው ወይም ውድቀታቸው ትምህርት በመውሰድ አሁን ያለውን የተሻለ በማድረግ ለነገ ስኬታማነታቸው በጥረት ይሰራሉ ፡፡ ➍. #ራሳቸውን_አሳልፈው_አይሰጡም ፤ አይሸነፉም ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አካላቸው እንኳ ቢደክም በአስተሳሰብና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይዘው ለስኬት ይበቃሉ ፡፡ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡ ➎. #ለውጥን_አይፈሩም እነዚህ ሰዎች ነገሮችን አመዛዝነው የሚተነብዩ በመሆናቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ለሚመጣው ውጤት ዝግጁ ናቸው ፡፡ ➏. #ከአቅማቸው_በላይ_በሆነ_ጉዳይ_ጊዜያቸውን_አያባክኑም በአዕምሯዊ ብስለታቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ሁሉም ነገር እነሱ ባቀዱት ልክ እንደማይሆንና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ስለሚያስቡ አይጨነቁም ፡፡ ከአቅማቸው በላይ ሆነው ለጭንቀት የሚዳርጉ ነገሮችን በአግባቡ በማስተናገድም ካልተገባ ውጥረት ራሳቸውን ያድናሉ ፡፡ በዚህም ሰኬታማነታቸውን ያጎለብታሉ ፡፡ ➐. #ተመሳሳይ_ስህተት_አይሰሩም ብዙ ጊዜ ስህተት በድጋሚ ሊከሰት የሚችለው ያለፈውን ካለማገናዘብና እንዳይደገም ካለመዘጋጀት እንደሆነ የስነ ልቦና ምሁራን ናገራሉ ፡፡ ጥሩ የአዕምሮ ብስለት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለሚሰሩት ስህተት ኃላፊነትን በመውሰድ በቀጣይ እንዳይደገም መፍትሔ አስቀምጠው ይሰራሉ ፡፡ ➑. #በመጀመሪያው_ውድቀታቸው_አይሸነፉም አዕምሯዊ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች በመጀመሪያው ውድቀታቸው መሸነፍን አያውጁም ፤ ከውድቀታቸው ትምህርትን በመውሰድ የተሻለ ውጤትን ለማምጣትም በትጋት ይሰራሉ ፡፡ ➒. #ቅፅበታዊ_ውጤትን_አይጠብቁም አስተሳሰባቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት ስራ ወዲያውኑ ውጤት እንደሚያስገኝላቸው በማሰብ አይጓጉም ፡፡ ከዚህ ይልቅ ሁሉ ስራ የራሱ ጊዜ እንዳለውና የስኬቱም ምንጭ የተቀመጠለት ጊዜ ፣ የሚደረግለት ተግባራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በእቅዳቸው አስቀምጠው ጉዞ ወደ ፊት ይላሉ ፡፡ ይህ ደግሞ ምክንያታዊ ወይም እውናዊ የስኬት ምንጭ በአንድ ሌሊት እንደማይመጣ መረዳትን ያሳያል ነው ያሉት ባለሙያዎቹ ፡፡ ➓. #ዓለም_ሁሉንም_ነገር_እንድታበረክትላቸው_አይፈልጉም ዓለማችን ብዙ ተቃርኖዎች ስኬትና ውድቀት ፣ ሀብትና ድህነት ፣ ሀዘንና ደስታ ወዘተ የተጣመሩባት እንደመሆኗ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ ከዓለም እንዲያገኙ አይፈልጉም ፡፡ ከዚህ ይልቅ በዓለም ላይ ደስታም ሆነ ሀዘን ፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት የሚያጋጥመው በራስ ጥረትና ጥንቃቄ ልክ ነው ብለው ያሉ። . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💦 የሚያቆመን ሀሳባችን ነው! የምንጎዳው የምንሰበረው የምንፈራው የምናጣው መጥፎ የሚባሉት ስሜቶች በአጠቃላይ የሚፈጠሩት በሀሳባችን ነው ፤ ገና በተግባር ያላየናቸው በእውኑ አለም ያላወቅናቸው ነገሮች በሙሉ ቀድመው በሀሳችን ይፈጠሩ እና ከመንገዳችን ያስቆሙናል መሰናክል ይሆኑብናል መሄድ ከምንፈልግበት መጓዝ ካሰብነው ቦታ ያርቁናል ስለዚህ እናስተውል እየተረበሽኩ ያለውት በምንድን ነው እውነት በተፈጠሩ ነገሮች ነው? ለምንድነው የቆምኩት ? ገብቼ አይቼው ነው ወይንስ በሀሳብ የሳልኩት መጥፎ ስዕል እየረበሸኝ ነው? ብለን እንነሳ ከመቆማችን በፊት ለምንድነው የቆምኩት ብለን እንመርምር! . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💥 ጓደኛህ የዕድሜ ልክ እንቅፋትህ ወይም አሸናፊነትን የሚያቅድልህ ቅፅበታዊ መሪህ ነው! . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
❇️ ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ #አሥር_የሕይወት_መርሆች! ❶. #እራስህን_ከሌላ_ሰው_ጋር_አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። ❷. #አትኩሮትህ_በሌለህ_ነገር_ላይ_ሳይሆን_ባለህ_ነገር_ላይ_ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። ❸. #እራስህን_ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡ ❹. #ሁሉን_ለማስደሰት_አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር። ❺. #የውሸት_ደስታን_አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡ ❻. #ማንን_እንደምታገኝ_አታውቅምና_ለሁሉም_ሰው_ቅን_ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡ ❼. #መለወጥ_የማትቻለውን_ነገሮችን_ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው። ❽. #የራስህ_እውነተኛ_ወዳጅ_ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡ ❾. #መልካም_አስብ_መልካም_ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል። ❿. #ለምን_እንደምትኖር_እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡ . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💦 መስጠት! የፈጣሪ የሒሳብ ቀመር ደስ የሚለው አንተ ስታካፍል እሱ አየደመረ እያባዛ መስጠቱ ነው። የተሰጠህን ስጦታ ለራስህ ብቻ ባስቀረኸው ቁጥር እንዳይጨምር እያረከው መሆኑን ሁሌም አስታውስ። ወዳጄ የምትሰጠው ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ ለምትወዳቸው ጊዜህን ስጣቸው! ለተጨነቁ ጆሮህን ስጥና አድምጣቸው! ግራ ለገባቸው ሀሳብህን አካፍላቸው! ያኔ ባለህ ገንዘብ፣ ዕውቀትና ጥበብ ላይ ብዙ እጥፍ ሲጨመርልህ ታይና በግርምት እጅህን አፍህ ላይ ትጭናለህ። . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💥 ስኬት ሀብት ብቻ ማለት አይደለም ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ ካለህ ስኬታማ ነህ! . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
❇️ ለአዕምሮ ጤና 10 ነጥቦች! መልካም ምክር ለክፉ ጊዜ ስንቅ ነው፡፡ ማንበብ ከጀመሩ ሳይጨርሱ አያቋርጡት፡፡ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉት የበለጠ ሰዎች እንዲወድዎት ያደርጋል፡፡ ❶. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው፡፡ በቫይረስ መጠቃት የለበትም፡፡ ሁልጊዜ ሊፀዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ- በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡ ❷. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል፡፡ ያስወግዷቸው፡፡ ❸. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡ ❹. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡ ❺. ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ ያገለግላል፡፡ ❻. አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡ ❼. ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡ ❽. ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡ ❾. የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡ የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡ ❿. ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለፀጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡ . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💦 ውሎ! የምትውልበት ቦታ የምታሳየውን ባህርይ የሚኖርህን አስተሳሰብ እና የምታመጣውን ውጤት የደስታህን መጠን ይወስናል። እውነተኛ ሰው ለመሆን እውነት የሚወራበት ቦታ ዋል! ስኬታማ ለመሆን ስኬታማ ሰዎች ጋር ወይም እንዳንተ የእውነት ስኬታማ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ጋር ዋል! መንፈሳዊ ለመሆን እና ሃጥያትን ለመተው ሃጥያት ከሚሰራበት ቦታ እራቅ የጽድቅ ቦታ ሂይ! ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ጎበዙን ተማሪ የልብ ጓደኛህ አድርገው። ሀብታም ለመሆን ከሀብታሞች ጋር ዋል! "ውሎህን ብትቀይር ህይወት ይቀየራል!" . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
💥 ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸንፍ! . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...

❇️ ማንበብ! ስለ ማንበብን ጥቅም ትንሽ ልበላችሁ፦ ❶. ሰውነትህ እስፖርት ሲሰራ ጡንችህ እንድሚያድግ ስታነብም አስተሳሰብህ ያድጋል እይታህም ይሰፋል ማስተዋልህም ይጨምራል። ❷. ቻይኖች "3 ቀን ሳታነብ ከዋልክ አፍህ ይሸታል" ይላሉ። ምን ማለትህ ነው ደሞ? ልትል ትችላለህ እውነታቸውን ነው ሰው ካላነበበ የሚናገረው አይኖረውም ስለዚ የድሮ አስተሳስቡን ይዞ ነው ሚናገረው። ❸. ማንበብ አእምሮአችን በተሻለ ፍጥነት እንዲሰራ እንዲያስብ ያደርጋል። ❹. ማንበብ ራስህን ፈጣሪህን እንድታውቅ ይረዳሃል ❺. ማንበብ ብልህ አስተዋይ ያደርግሃል ❻. የምታነብ ከሆነ የምትናገረው አታጣም . . የማንበብ ጥቅም ብዙ ነው። ጥቅሙን ብናቅም ግን አናነብም። ብናነብም ያነበብነውም አንኖረውም። ማወቅ ብቻ ደሞ አይለውጠንም ያወቅነውንም መኖር አለብን ያኔ ለውጣችን ይጀምራል። ከላይ የተጠቀሱት የማንበብ ጥቅም ግን የሚወሰነው የምናነበው ምን ያህል ጥሩ መጽሃፍ ነው በሚለው ላይ ነው። እንጂ ያገኘነውን ስላነበብን እንለወጣለን ማለት አይደለም። . #በፍቅር እንራመድ በይቅርታ እንሻገር . . #በቅንነት ያጋሩ | #ቤተሰብ ይሁኑ!!! . 🎸.. https://t.me/maraki_eth .. 🎸 ▰▰▰▰▰ 🍃 🌸 🍃 ▰▰▰▰▰
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.