425
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
425
#እኔም_ጠላሻለሁ
፧
ለአንቺ አይነቷ ልዩ አፍቃሪ ቃላት ሁሉ ይታዘዛል፤
የማይወደድ ከአፍ ወጥቶ በአንቺ አንደበት ፍቅር ይገዛል፤
አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ የሚለው ቃል፤
ላፈቀረ መች ይበቃል፤
ጨመረችው ስላልበቃት ከጥላቻ ተበደረች፤
የፍቅር ቃል ሲያጥራት በጥላቻ ተናገረች፤
"አልወድህም ጠላሀለሁ" ትለኛለች ደግማ ደግማ፤
ጆሮዬ ደነቀው የሚስከፋውን ቃል በደስታ ሲሰማ፤
ትናገር እንዳሻት ትሁን እንደ ልቧ ልቧን የሰጠች ሴት፤
ጠላሀለሁ ትበል ለፍቅሯ መግለጫ ይሰጠኛል ሀሴት፤
በቃል አሞካሽቶ ልቡን ያልሰጠ ነው በፍቅር የሌለ፤
ዘልቆ ልብ አይመታም አፈቅርሀለሁ ቢል በምላስ የዋለ፤
ከልብ ያፈቀረ እጠላሀለሁ ሲል ፍቅሩን ይገልጣል፤
ውሸታም አፍቃሪ አፍቅርሀለሁ ሲል ህሊውን ያጣል፤
የፍቅር ከሆነ አልወድህም በይኝ በደስታ ይመታል፤
የልቤ አመል ይህ ነው ላመነው ይሞታል፤
አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ የሚለው ቃል፤
ላፈቀረ መች ይበቃል፤
እኔም ጠላሻለሁ።💕💕❤
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ቃል_የለኝም
፧
ቃል የለኝም ተናግሬ፣
ልገልፅ ስል ስለፍቅሬ፣
ብን ቃላት እልም ፊደል፣
ሆሄ ሙሉ ገባ ገደል፣
ምላስ ታስሯል ቋንቋ አያቅም፣
ስሜት ሞልቶ ጠፍቷል አቅም፣
መዝገበ ቃል ካሰፈረው...
የውስጤን ስሜት ስገልፅልሽ፣
አፈቅርሻለሁ ብቻ ነው ምልሽ?
ሁሉን ስትሆኝ እናት እህት፣
መልካም ጓደኛ ደግ ትሁት፣
ታማኝ አፍቃሪ ለሆንሽ ሰው፣
ቃል ከማን ነው የምዋሰው፣
ከጠፋ ቃል ዝምታዬ ስሜቶቼን ከገለጠ፣
ስለፍቅሬ ይገባሻል ካንደበቴ በበለጠ፣
ጭጭ ልበል ውስጤን አይተሽ ካነበብሽው፣
ዓለሜ ነሽ ይበቃኛል ዝምታዬን ካደመጥሽው።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#በድምፅ_ማዳመጥ_ከፈለጋችሁ
👇👇👇
@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
#እኔና_አንቺኮ
፧
እኔና አንቺኮ ብዙ ታሪክ አለን እናሳዝናለን፣
በልጅነት ዓለም ስቀን ተጫውተናል፣
በትምህርት ሰአት ወሬ እናዳናወራ
መምህሩ ባንድ ወንበር አስቀምጠውናል፣
ወንድ ከሴት ጋራ ሴትም ከወንድ ጋር ከተደባለቀ፣
ወሬ የለም ነበር ለቅሶም አያጣውም ብዙ የተጨነቀ፣
ለኔ ግን ደስታዬ ኩራቴ ነበረ መቀመጥ ከአንቺጋ፣
ተማሪው ቢስቅም ወላጅ በፃፈበት የአሽሙር መንጋጋ፣ እንባዬ እስከሚያመልጠኝ ከልኸኛው ልቤ እስከሚገነፍል፣
ካንቺጋ ከታየሁ እፎገር ነበረ በእያንዳንዱ ክፍል፣
እኔና አንቺ እኮ ብዙ ታሪክ አለን እንሳዝናለን፣
ሳይሽ እፈራለሁ ደሞም ስተክዢ ታሳዝኚኛለሽ፣
አንጀት ትበያለሽ ሆዴን ታባቢያለሽ፣
በልጅነት ዓለም፣
የውሸት ልብ የለም፣
ሀሴትን ነው እንጂ ሐሰትን አናውቅም፣
መታዘዝ ነው እንጂ ምስኪን አንንቅም፣
በዛ ንፁህ ልቤ እድፍ በሌለበት፣
ጌታ እንኳን በቃሉ"መንገስተ ሰማይን እንደህፃን ካልሆናችሁ አታዩዋትም" ብሎ የተናገረበት፣
በዛ ህፃን ልቤ እኔ አፈቅርሻለሁ፣
ጉድፍ በሌለበት አስታውስሻለሁ፣
ይህን ሁሉ ነገር አንዱንም ሳታውቂ ጊዜ ቢያራርቀን፣
ብቻዬን አግኝቶኝ ደቁሶ ጥሎኛል የማጣት ሰቀቀን፣
እኔና አንቺ እኮ ብዙ ታሪክ አለን እናሳዝናለን፣
ፎቶ ብርቅ በሆነው በኛ ኩሩ ዘመን ስልክ በሌለበት፣
ፎቶሽ ግን ነበረኝ አንድ በልቤ ላይ አንድ በመፅሄት፣
ሌቱ እስከሚነጋ በዓይኔ ሲንከራተት ቪዲዮሽ በህልሜ፣
የሞት ሞቴን ነበር እየተንገዳገድኩ ያለአንቺ መቆሜ፣
በናፈቅሺኝ ቁጥር ሁለቱን ፎቶዎች እየተመለከትኩ፣
ብዙ አመት ጠበኩሽ ትመጣለች ብዬ ለልቤ እየነገርኩ፣
አቅም እያነሰኝ ተስፋዬ እየጠፋ ቀን እየበረረ፣
ጊዜ ከልቤ ላይ ፍቆ ባይጠርግሽም አጥሩን አጠረ፣
ሌላ ከአጥር ማዶ ሲያንከራትት ቢውል፣
የውሸት ሆነበት የትርታው ደውል፣
የማስመሰል ህይወት ቀን እየጠበቀ ለራስ ይሰለቻል፣
ራሱን የሆነ ንፁህ ልብ ላ'ለው ግን መከራም ይመቻል፣
ግና ቢያዝንም ልቤ ቢሰበርም ቅሉ፣
የኔ ለኔ ይመጣል ይኔ ነበር ቃሉ፣
እኔና አንቺ እኮ ብዙ ታሪክ አለን እናሳዝናለን፣
በህይወት ቀለበት ጊዜ ሲሽከረከር ሚዛኑን ጠብቆ፣
ይኸው መጣሽልኝ እሰይ አገኘሁሽ ልብሽ ልቤን አውቆ፣
ጊዜው ደረሰና ያን ሁሉ ናፍቆቴን የአመታት ጉጉቴን፣
ይኸው አገኘሁሽ መቼም ላትዪኝ ሁለተኛ እናቴን፣
የፍቅር ጥማቴን በሳም አረካሽው፣
የልቤን ልብ ምት ከቦታው መለሽው፣
ላውራ ስለፍቅር ለምን? ስላየሁት፣
ልመስከር ባንቺ ስም ለምን? ስለኖርኩት፣
ከልብ የሆነ ነው ለልብ የሚመቸው ህሊና አይቆረቁር፣
አንቺ እስካለሺልኝ መች ይሰማኝና ወበቅ ወይደሞ ቁር፣
እኔ ውስጥ ስላለሽ እንለያያለን ብዬ አልጨነቅም፣
አንቺ ደሞ እኔ ነሽ ሰው ከራሱ አይርቅም፣
እኔና አንቺ እኮ ብዙ ታሪክ አለን እናስደስታለን
እናሳዝናለን፣
በህይወት መንገድ ላይ እስከመጨረሻ
ባንድ እንጓዛለን፣
ልጅነት በፃፈው በነጭ ወረቀት ላይ በማይጠፋ ቀለም፣
ካንቺ ፍቅር ውጪ በልቤ ላይ ነግሶ የደመቀ የለም።
ከቃል በላይ አፈቅርሻለሁ የኔ ህይወት❤
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ሌባና_ሌባ
፧
ምን ሊጠቅምሽ ነው? ልቤን ሰረቅሺው፣
እኔን ልበ ቢስ አደረግሽና ላንቺ ደረብሽው፣
ላይጠቅምሽ ነገር መንታ ልብ ሆነሽ፣
ስለምን ሲባል?
ልቤ በጠፋው በባዶነቴ ትጨነቂያለሽ፣
ልሞት ሳጣጥር ሀኪም ሆነሺኝ፣
ልቤን ስፈልግ ያንቺን ሰጠሺኝ፣
ሌባ ነሽ እኮ ለዛውም የልብ የሰው ሙሉ አካል፣
ልብ የሌለው ሰው እንዴት አስቦ በምን ይለካል፣
ሩህሩህ ሌባ የኔን ቀምተሽ ያንቺን ሰጠሽኝ፣
ልብ ለሌለኝ ልቤ ሆንሽና ሌባ አደረግሺኝ፣
ሌባና ሌባ አሪፍ ፍቅረኞች ለክፉ አንዘምትም፣
በፍቅር ዓለም ሌባና ፖሊስ አንጫወትም።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#አዎ_እጨነቃለሁ
፧
ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንዲህ ሆኜ አላውቅም፣
የጠፋሽብኝ ቀን እጨነቃለሁ ስል፣
"ለምን?" ለምን አትበይኝ
ከፍቅርሽ ሌላ የተለየ ጉዳይ ያለብኝ ይመስል፣
አዎ እጨነቃለሁ፥
እሳሳልሻለሁ፥
ባንቺ ፍቅር ምክንያት፥
ልቤ ሆኗል የእናት፥
ስጠፊ ለሰከንድ፥
እሳት ሆኜ ስነድ፥
ቦታዬ እንድረጋ፥
አትጥፊ ከኔጋ፥
ሆዴን አይጭነቀው፥
ልብሽ እያወቀው፥
የጠፋሽ እንደሆን፥
ፍቅሬ ሰውም አልሆን፣
ጠፍተሽ አትቀሪም እንደማትቆዪም
በልቤ አውቃለሁ፣
ፍቅርሽ አስሮኝ የለ ልቤን የእናት አርገሽ
ሁሌ እጨነቃለሁ፣
ስለማፈቅርሽ ነው።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ሁሉም_ያውቅሻል
፧
የኔ ፍቅር በየመስኩ በየአቅጣጫው፣
ስማችን ነው ጨዋታውን መቀወጫው፣
እንዴት? ካልሺኝ
በግጥሜ የኔን ታሪክ ሁሉም ያውቃል፣
ርዕሴ "ተጣለሁ" ሲል "ተጣላችሁ?" ይጠይቃል፣
የኔ ግጥም "ታረቅን" ሲል ታረቃችሁ? የሰዉ ቃል፣
የኔ ፍቅር
ሁሉም ያውቃል የማያውቀው ይጠይቃል፣
ስለሚያውቅሽ በግጥሜ በከተብኩት በስንኝ ቃል፣
መች አበቃ በዚ ብቻ በህሊና ቃል በሳሳላት፣
የኔ ፍቅር ልዩዋ ሴት በስዕልም ሀገሩ አያት፣
ታድላለች የውበት ጥግ ሞናሊዛን አስንቃለች፣
ፀሀይ በብርሀን ሸራዬ ላይ ተቀምጣለች፣
ከኔ በላይ በኔ ህይወት እሷ ጎልታ ትታያለች፣
በልቤ ላይ ትልቅ ቦታ መጠን አልባ ዘርግታለች፣
የኔ ፍቅር ትለያለች፣
የምታውቁ አትመስሉም ግን እቺ ልጅ ማነች?
የኔን ልዩ ከኔ ውጪ ማን ያውቃታል፣
ስዕሌ ላይ እንዳታዩ ግጥሜ ግን ደብቋታል፣
አታውቋትም በ'ውን ማንም ቢደሰኩር፣
ሰርግ ጠርቻችሁ ለልዩዋ ፍቅሬ ቀልበት እስካስር።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ሁሉም_ሰው_ይጣላ
፧
ህይወቴ የኔ አለም💕
በሚያዳልጥ መንገድ መውደቄ ቢያመኝም፣
ተመስገን ነው መልሴ ህመሜ አይከብደኝም፣
የወደኩበትን ምክንያቱን አላውቅም፣
ሊያድነኝ ቢሆንስ?
ከተተኮሰብኝ ከጥይት ጥርቅም፣
ፍቅርዬ የኔ አለም💗
እንኳንም ተጣላን እንኳን አለቀስን፣
በመራራቃችን ፍቅርን አነገስን፣
የይቅርታ ፍሬ ከወይን ይጣፍጣል፣
ለእውነተኛ ልቦች...
ተጣልቶ መታረቅ ፍቅርን ይሰጣል፣
የኔ ነብስ ነገር💝
መቶ ሺህ ሚሊዮን ከዛም የበለጠ
ቃላት ቢደረደር፣
የአንቺን ልዩ ፍቅር ላንቺ ያለኝን ስሜት
አይችል መገዳደር፣
የኔ እናት የኔ ዓለም💞
ካንቺ ዓለሜ ውጪ ለኔ ፍቅር የለም፣
ሁሉም ሰው ይጣላ ሁሉም ሰው ይኳረፍ፣
የእውነት ልብ ካለው በይቅርታ ይረፍ፣
ከኔና አንቺ ውጪ ያለም አይመስለኝም፣
ታርቆ የሚፋቀር ለምሳሌ አይገኝም፣
💘ታድለን የኔ ዓለም።💘
ገጣሚ
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ታድለሽ
፧
አዛኝ ልብ ሰቶሻል የሚራራ ለሰው፣
ከእናቶች ልብ ነው ላንቺ የተቀነሰው፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
በዚ ሰአት እኮ የዋህ ልቦች የሉም፣
ቆንጆዎች በሙሉ መልካሞች አይደሉም፣
ከምን ተመርጥሽ ነው ግን የተለየሽው፣
የዋህ ልብ ቁንጅናን የተከናነብሽው፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
ፈገግ በይ ሳቂልኝ እኔ ልድመቅ ባንቺ፣
ጥርስሽ ያበረያል ከንፈርሽን ስትከፍቺ፣
ሁሌም ተናገሪ ዝም ብዬ ልስማ፣
አንደበትሽ ማር ነው ለጆሮ ሚስማማ፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
ሁሉም ተሰቶሻል ምስኪን ነሽ አፍቃሪ፣
ውብ ፀሀይ የመሰልሽ ሁሌ አብረሽኝ ኑሪ፣
በአሁን ሰአት እኮ የዋህ ልቦች የሉም፣
ቆንጆዎች በሙሉ መልካሞች አይደሉም።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#አሜን_በይ_በሆድሽ
፧
ባይሸብት ፀጉሬ ዕድሜዬ ባይረዝም፣
እመርቅሻለሁ በዝምታዬ ዳግም እንዳልቅዝም፣
አሜን በይ በሆድሽ!
ከቶ ዝም የማይል ወሬ ማያልቅበት፣
ጆሮ የማይሰጥሽ የማይሰማሽ ቅፅበት፣
ያድልሽ ፍቅረኛ ያድልሽ ጓደኛ*
አሜን በይ በሆድሽ!
ፍቅሩን በአንደበቱ እየዘረዘረ
እንደሚሳሳልሽ እየተናገረ፣
ነገር ግን በተግባር ሽራፊውን ያህል
ፍቅርን ያልኖረ፣
ያድልሽ ፍቀረኛ ያድልሽ ጓደኛ*
አሜን በይ በሆድሽ!
"ደና ነሽ?" እያለ አብዝቶ ማይጠይቅ፣
"ደና ነኝ" ካልሺው መልስ ድብቅ ህመምሽን
ቅንጣቱን የማያውቅ፣
ያድልሽ ፍቅረኛ ያድልሽ ጓደኛ*
አሜን በይ በሆድሽ!
ወረት የምላበት
አንዴ የሚወድሽ አንዴ የሚጠላሽ፣
ትቶኝ ሄዷል ስትይ
የማይርቅ ከጥላሽ ግራ የሚያጋባሽ፣
ያድልሽ ጓደኛ ያድልሽ ፍቅረኛ*
አሜን በይ በሆድሽ!
ጥፋቱን በሙሉ ባንቺ የሚያሳብብ፣
ምንም የማይረዳሽ ራሱን የሚክብ፣
ያድልሽ ጓደኛ ያድልሽ ፍቅረኛ*
አሜን በይ በሆድሽ!
የአቅሜን ምርቃት እንዲ መርቂያለሁ፣
እኔ ባጎደልኩት
የቀድሞ ፍቅረኛሽ ይሙላበት ብያለሁ፣
አሜን በይ በሆድሽ!
ከአፍሽ እንዳይወጣ
"አሜን" የሚለው ቃል እኔ ስመርቅሽ፣
ስሜ እየመሰለኝ
"አሜን" ባልሽ ቁጥር "አቤት" እንዳልልሽ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ከኔ_የተሻለች
፧
እኔ ምፈልገው ሁሉ ነገር አለሽ፣
ከሌሎቹ እንስት አንቺ ትለያለሽ፣
ስቀርብሽ ቀርበሽኝ ስትዋሺኝ አመንኩሽ፣
ከራሴ አስበልጬ አንቺን አፈቀርኩሽ፣
ማፍቀሬ እውነት ነው መፈቀሬ እምነት፣
አምኖሽ ነበር ልቤ በሙሉ ቅንነት፣
"የኔ ጌታ" ስትይ ልቤ ይረጋጋል፣
"አስመሳይ ነሽ" ብሎ
አልጠረጠረሽም ፍቅር በግ ያደርጋል፣
ምን ባልችልም እንኳ ከልብሽ ላይ መንገስ፣
አላቆምሽ ሸንጎ በፍቅር ስም አልከስ፣
ደሞ ቸር ይመስል ታስተዛዝኛለሽ፣
በተስፋ ስጠብቅ ጥለሽ ትሄጃለሽ፣
"ከኔ የተሻለች ይገባሀል" ብለሽ ትተሺኝ ሄደሻል፣
ካንቺ የተሻለች ለኔ አንቺ ብቻ ነሽ ቅኔው ይገባሻል።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
