cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከዝህም ከዝያም

Fair and truthfull news ... stay with us This is ETHIO NEWS official Telegram channel. For more updates please visit

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
216
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ደሞዝ ና ደሞዝተኛ በሮበርት ሙጋቤ አገላለፅ ፡፡ """""""""""''"''''''''''''''''"""" ደሞዝ የመጣ ቀን ዶሮ ትበላለህ። በማግስቱ ደሞዝ ሲያንስብህ የዶሮ ውጤት (እንቁላል) ትበላለህ። በቀጣዩ ቀን ደሞዝህ የበለጠ ሲሳሳ ደግሞ የዶሮ ምግቦችን(በቆሎ እና ገብስ) ትመገባለህ። በቀጣይ ቀናት ደሞዝህ ሲሟጠጥ ደግሞ አንተ እራስህ ዶሮ ትሆንና የምትበላውን ነገር ፍለጋ ወዲያ ወዲህ በመባዘን ጊዜህን ታሳልፋለህ፡፡ .......................................................... ... መልካም ምሽት @ethionews_1
نمایش همه...
🚺✅ #የፍቅር_ዓይነቶች (types of Love) ✅🚹 ✳✅ #ሮማንቲክ_ላቭ /Romantic Love/ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ሄሮድስ ነው። ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ያፈቀራት ስትደንስ አይቷትና ዳንሷም ስለማረከው ብቻ ነው። ይህ ዓይነቱ ፍቅር “ሄሮድሳዊ ፍቅር” ይባላል። ይሄኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርጽ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው። ሌሎች መሰረታዊ ነገሮችን ለምሳሌ ሃይማኖት ፣ባሕርይ ፣ አስተሳሰብ ወዘተ ተረፈዎችን ከቁም ነገር አይቆጥሩትም። ሮማንቲክ አፍቃሪዎች ብዙን ጊዜ ቀናተኛ ናቸው። ያፈቀሩት ሰው ከማንኛውም ሰው ጋ እንዲያዩት አይፈልጉም። ✳✅ #ፓሽኔት_ላቭ passionate Love ስሜታዊ ፍቅር! ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር ነው። ስሜታዊ ፍቅር passionate Love በጣም አስቸጋሪ የፍቅር አይነት ነው። ሕሊናን ረፍት ከመንሳቱ በላይ ሕይወትን የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ አለው። ለምሳሌ ትምርትና ስራ መጥላት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ይገኙበታል። ስሜታዊ ፍቅር የሚቆየው ስሜቱ እስኪሳካ ሩካቤ ሥጋ እስኪፈፅም ድረስ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ግን መጀመሪያ ከወደደው ውድ ይልቅ በኋላ የሚጠላው ጥል ይበልጣል! ይህን የመሰለው ፍቅር በመፅሐፍ ቅዱስ የአምኖን ፍቅር /አምኖናዊ ፍቅር/ ይባላል። ✳✅ #ሎጂካል_ላቭ Logical Love ይህ ፍቅር ጣራና መሰረቱ “መመሳሰል” የሚለው ቃል ነው። እነዚህ ፍቅረኛሞች የሚመሩት በሎጂክ ነው። ለምሳሌ እሷ ድግሪ ካላት የምትመርጠው ድግሪ ያለውን ሰው ነው። ወንዱም እንደዚሁ። ✳✅ #ፍሬንድ_ሺፕ /Casual friendship/ ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም። ሁለቱ ፍቅረኛሞች ምስጢር ይለዋወጣሉ፣ የሚያስደስታቸውም ጥምረታቸው ብቻ ነው። ✳✅ #ፉሊሽ_ላቭ foolish Love “የጅል ፍቅር” አንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው። ለምሳሌ ምንነቱን ሳታውቅ ፎቶውን ብቻ አይታ ከነፍኩ በረርኩ የምትል ሴት አጋጥሟችሁ አያውቅም? ፎቶውን ብቻ አይታ ወደደችው! በቃ! ቆረጠች። በእቴጌ ጣይቱ ጥናት መሰረት ብዙዎች በዚህ ፍቅር ከተያዙ ቆይተዋል ይባላል። እድሜና ጤና ለፌስ ቡክ ይሁንና የእቴጌ ጣይቱ ጥናት ፍንትው ብሎ ያሳየናል። ይህ አይነቱ ፍቅር በምሁራን አገላለፅ “የጅል ፍቅር” foolish Love ይባላል። ✳✅ #ፖሰሲቭ_ላቭ /possessive Love/ ይህ ዓይነቱ ደግሞ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ነው። ወንድ ስለሆንክ ለራስህ አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ጥናቱ እንደሚያሳየው ብዙውን ጊዜ ይህ አይነት ፍቅር የሚይዛቸው ሴቶች ናቸው። እንደዚህ ዓይነቶቹ የእገሌ ባል መባልን ይፈልጋሉ። ✳✅ #አንሰልፊሽ_ላቭ unselfish Love ይህ እሷ ከምትጎዳ እኔው ልቸገር ዓይነት ፍቅር ነው። ፍቅር ግን መዋደድ እንጂ ውለታ መዋዋል አይደለም። ✳✅ #ጌም_ፕሌይንግ ላቭ Game playing Love ይህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ዓላማቸው አንድ ብቻ ነው። የሩካቤ ሥጋ ጥማቸውን ማርካት ብቻ። ይህ ብዙውን ጊዜ በወንዶች የሚበረታ የፍቅር ዓይነት ነው። ✳✅ #ኢምፒቲ_ላቭ Empty Love ባዶ ፍቅር! ይህ ዓይነቱ ፍቅር በአጋጣሚ ተገናይተው ወደድኩሽ ፣ ከነፍኩልሽ ፣ አበድኩልህ ፣ ክንፍንፍ አልኩልህ የሚያሰኘው ነው። ✳✅ #ሰልፊሽ_ላቭ selfish Love ራስ ወዳድ ፍቅር! እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርን “ሀ” ብለው የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ነው። ለዚህኛው ፍቅር መሰረቱ ገንዘብ ነው። “ገንዘብ ያልቃል ፍቅር ግን ይዘልቃል!” ገንዘቡ እስካለ ድረስ ሆዴ! አንጀቴ! ሞትኩልህ! አበድኩልሽ! ይባባላሉ። ገንዘቡ የጠፋ ዕለትስ? ያኔማ ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ ዓይናቸውንም አያሹም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን የኢዮብ ሚስት ናት። ኢዮብ ሐብት ንብረቱ ሲያልቅ የሚስቱ ፍቅርም አለቀ፤ ኧረ እንዲያው ለመሆኑ ፍቅር በአንድ ጊዜ የሚለቅ የጥፍር ቀለም ነው እንዴ? ይህ ዓይነቱ ፍቅር ገንዘቡ ሲጠፋ ፍቅሩም ድርግም የሚል “የኢዮባዊ ሚስት ፍቅር” ይባላል። ✳✅ #ኮምፓኒየን_ላቭ companion Love ይህ እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጪ ወጣ ያለባቸው ሰዎች የሚጀምሩት ውጥን ነው። ከእድሜያቸው ጋር ግብግብ ስለሚይዙ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ያገባሉ። ምክንያቱም ፊታቸው ያለው የልጅ አምሮት ፣ ልጅ ማሳደግ አብሮ መኖር …… ነው። እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ ትዳራዊ ፍቅር companion Love ይባላል። ✳✅ #ፍቅር_እስከ_መቃብር “ኮንሲዮሜት ላቭ” consummate Love ይህ ዘለቄታ ያለው የአባ ወራ እና የእማ.ወራዎቻችን ፍቅር ነው። ይህ ክቡር አዲስ አለማየው እንደደረሱት “ፍቅር እስከ መቃብር” እንደ በዛብህና ሰብለ ወንጌል ያለ ፍቅር ነው።.ይህ የሽማግሌው የአቶ ዘካርያስ እና የወ/ሮ.ልቤነሽ “ፍቅር እስከ መቃብር” ነው! ይህ “እውነተኛ ፍቅር ነው!!nፍቅርን ፍቅር ነው የሚያሰኙት 3 ነገሮች ሲሟሉ ነው።nስሜት /passion/ ቅርበት /intimacy/ ቁርጠኝነት Commitment.“መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” እንዲሉ መግባባት ያስፈልጋል። ሁለቱnፍቅረኛሞች በስሜትና በአስተሳሰብ መግባባት አለባቸው። በአስተሳሰብ መቀራረብ ያስፈልጋል በችግርና በኀዘን ለመረዳዳት ቁርጠኝነትም ያስፈልጋል። ራስን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ማንም ራሱን ፈልጎ ማግኘት አለበት! እኛ የቱ ጋ ነው ያለነው? ከተመቻችሁ forward እና ሸር አድርጉ ሼርርርር @ethionews_1
نمایش همه...
✅ አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ ✅ ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ! ✅ ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ! ✅ አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ! ✅ ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ! ✴ ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ! ✴ ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ! ✴ ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ! ✴ ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ! ✴ ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ! 🌀 ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ! 🌀 እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ! 🌀 አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ! 🌀 ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ! 🌀 ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ! 🌀 ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! ሼርርርር @ethionews_1
نمایش همه...
#አንተ_ማለት ✳ "ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ ። እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ። ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል። አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ። ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ። ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል። ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ። ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል። ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም። Never Give Up በቀላሉ ተስፉ አትቁረጥ ። ተመልከት ሰይጣን ተስፉ የለውም ግን ተስፉ አይቆርጥም ። ሰው ግን ተስፉ አለው ግን ተስፉ ይቆርጣል። ✅ አምፖል ሽቦው ከረገፈ አያበራም ጠርሙስ ይሆናል ። የሰውም የብርሃን ሽቦው ተስፉ ነው ። ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ ። 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ። ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል። ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው ። ✅ የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ። ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል ። የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው ። ✅ በረዶ ፀሀይ ላይ ብታረገው ይቀልጣል የተቦካ ሲሚንቶ* ፀሀይ ላይ ብታረግ ግን ይጠነክራል። እንደ ፀሀይ የከረሩ ችግሮች በህይወትህ ሲያጋጥሙህ እንደ በረዶ አትቅለጥ እንደ ሲሚንቶው ጠንክርባቸው። እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው ።መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ። ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ። ሸርርር @ethionews_1
نمایش همه...
🚺 ሕይወት የሁለት ነገሮች ድምር ውጤት ናት። 🚺🚹 🌀 ማግኘት አለ 👉 ማጣት አለ 🌀 መወለድ አለ 👉 መሞት አለ 🟢 ደስታ አለ 👉 ሀዘን አለ 🟢 እንባ አለ 👉 ሳቅ አለ። 🚻 ሁለቱም የህይወት አካሎች ናቸው። አንዳንዴ ህይወት እንደ ሸማኔ መወርወሪያ የሁለቱንም ጫፍ እያስነካች ትመልሰናለች። አንድ ቀን 24 ሰዓት አለው። 12ቱ ሰዓት ብርሃን 12ቱ ሰዓት ጨለማ ነው። አይ እኔ ጨለማ አልወድምና ለሊቱ ይቅርብኝ ብንል ቀናችን ጎዶሎ ነው ሚሆነው ። አንድ አመትም ክረምትና በጋ አለው። አይ ጭቃ አልወድምና ክረምቱ ይቅርብኝ ብንል አመታችንም ጎዶሎ ነው ሚሆንብን ። ስለዚህ ህይወትም ያለ ችግር ደስታውን ብቻ እንኑረው ብንል ጎዶሎ ህይወት ነው ምንኖረው። አንዳንዴ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ችግር ውስጥ የሚከተን ሕይወታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው ። ከለሊት በኋላ ንጋት እንጂ ሌላ ሌሊት አይመጣም ። ከመከራ ቡሃላም ደስታ እንጂ ሌላ መከራ አይመጣምና ታገስ። ወዳጄ አንድ ኮኮብ ዙሪያው በጨለመ ቁጥር እሱ ይበልጥ ይበራል። ህይወትህ የጨለመብህ ይበልጥ እንድታበራ ነውና ተደሰት። እህቴ በተለያየ ሀገር በተለያየ ስራ ውስጥ እራስሽን ለመለወጥ በተለያየ አይነት ችግር ውስጥ ተወጥረሽ ይሆናል። ግን የረገበ የክራር ክር ሙዚቃ ማውጣት አይችልም። አንድ ክራር ሙዚቃ ከማውጣቱ በፊት መጀመሪያ ክሩ በደንብ መወጠር አለበት። ህይወት አንቺንም የወጠረችሽ ሚያምር ማንነትሽን ለማውጣት ነው። ወንድሜ እራስህን ለመለወጥ ስትሞክር ብዙ ነገሮች ቅጥል አርገውህ እርር ብለህ ይሆናል። ግን አስታውስ አንድ መዓዛው የሚያምር እጣን ይሸተን ዘንድ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ገብቶ መቃጠል አለበት። አንተንም ሕይወት ያቃጠለችህ ሚያምር ማንነትህ እንዲወጣ ነውና ተደሰት።
نمایش همه...
✅🌀 #ለማትፈፅመው_ነገር_ቃል_አትግባ!!! 🌀✅ #በአንድ ወቅት አንድ ንጉስ ብርዳማ በሆነ ምሽት ወደ ቤተ መንግስት ሲገባ ድንገት አንድ ቀልቡን የሚስብ ነገር ይመለከታል። አንድ ሰው ለራሱ በብርድ ተቆራፍዶ ነገር ግን ከጎኑ ላለው ውሻ ልብስ አልብሶት ይመለከታል በዚህ ጊዜ በጣም በመገረም ወደ ሰውየው ተጠግቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው። #በዚ ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት ከሰው በተሻለ ብርድን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ችሎታ ላለው ለዚ ውሻ ልብስህን አልብሰህ አንተ ግን በብርድ ተቆራፍደሀል??? እና ይህን ለምን አደረክ ሲል ጠየቀው??? #ሰውየውም፦ ጌታዬ እኔ እንደርሶ ያሉ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁኝ ከውሻው በተሻለ ስለህመሜ፡ችግሬ፡ቁስሌ ባጠቃላይ ስሜቴ የመናገር ተፈጥሯዊ ችሎታ አለኝ ነገር ግን ይህ ውሻ ሲያመውም ሆነ ሲበርደው አፍ አውጥቶ ስሜቱን እንኳን መግለፅ አይችልም ለዚህ ነው ያለችኝን ልብስ ያለበስኩት አላው። #ንጉሱም፦የሰብአዊነትን ጥግ በተግባር በማየቱ በጣም እየተደነቀ ከጠባቂዎቹ አንዱን ወታደር ጠርቶ ለሰውየው ብርድ ሊቋቋም የሚችል ወፍራም ልብስ እንዲያመጣለት ትዛዝ አስተላልፎ እየተደነቀ ወደ ቤተ መንግስቱ ገባ። #ሰውየውም፦በንጉሱ ንግግር በጣም ተደሰቱ የሚመጣላቸውንም ብርድ የሚከላከል ልብስ በጉጉት መጠበቅ ጀመሩ። ነገር ግን ትዛዙ የተሰጠው ወታደር የንጉሱን ትዛዝ ረስቶት ልብሱን ሳያመጣላቸው ቀረ። #በንጋታው ንጉሱ ያሀን ሩህሩህ ሰው ለማየት ወደ ደጃፍ ሲወጡ ያሀ ቅን ሰው ትናንት ትተውት ከሄዱበት ቦታ ክልትው ብሎ ሞቶ አገኙት። ንጉሱም ካጠገቡ አንድ ብጣሽ ወረቀትላይ የተፃፈ መልእክት አገኙ ፁሁፉም እንዲህ ይል ነበር፦ንጉስ ሆይ እኔ ለብዙ አመታት ብርዳማ ለሊቶችን መቋቋም እችል ነበር። ነገር ግን እርሶ ለማያሳኩት(ለማይፈፅሙት) ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ ቃል መግባትዎ የኔን ብርድ የመቋቋም ሀይሌን ነጠቀኝ ስለዚህ ንጉስ ሆይ እኔስ አንድ ግለሰብ ነኝ ነገር ግን እርሶ የሚመሩት ህዝብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገቡለትን ቃል የማትፈፅሙለት ከሆነ በእርሶ ላይ ያለውን እምነት ሊሸረሽለው ይችላልና በተቻሎት መጠን ቃሎትን አይጠፉ ይላልፁሁፉ። ✅ #እስኪ ስንቶቻችን ነን፦ ለማንፈፅመው ነገር ለጓደኞቻችን ፍቅረኛችን ለሚስታችን ፡ለልጆቻችን ለቤተሰባችን ባጠቃላይ ለወዳጆቻችን ቃል ገብተን በባዶ ተስፋ ልባቸውን የሰበርነው??? ✅ #ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦ ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን አንተ ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት ይችላሉና ለማታሳካው ወይም ለማትፈፅመው ነገር ቃል አትግባ። ከተመቻችው ሼርርርር @ethionews_1
نمایش همه...
"ኢትዮጵያውያን በዓለም ልዩ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በጦር ሜዳ ውሏቸው ጤነኛ መሆናቸው እስኪያጠራጥር ድረስ እንደ እብድ መድፉን መትረየሱን ታንኩንና የአውሮፕላን ቦምቦችን ከመጤፍ ሳይቆጥሩ እየፎከሩና እየሸለሉ የጠላትን ጉሮሮ አንቀው ይወድቃሉ..." አዶልፍ ፓርለሳክ 'የሃበሻ ጀብዱ' በሚል ከጻፈው የተወሰደ ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነዉ ለታላቁ የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት የመታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! እትዮጵያ ትቅደም!!✊✊✊ @ethionews_1
نمایش همه...
✴✅ ልብ ብለው ያንብቡት ✅✴ 🌀 ከዕለታት አንድ ቀን ሰው ፣እባብ ፣ይጥ እና ዝንጀሮ ተያይዘው መንገድ ይሄዳሉ። ካሰቡበትም ሳይደርሱ ይመሽባቸዋል ከዚያም ወደ አንድ ሰውዬ ቤት ይሄዱና ተራ በተራ እንዲያሳድራቸው ይጠይቁታል። በመጀመሪያ ሰውየው ሄዶ እንዲህ አለው እባካችሁ እዚህ ቤት የመሸበት የማታ እንግዳ ማደሪያ ፈልጌ ነበር ሲል ባለቤቱ ብቅ ብሎ ውይ ምን ችግር አለ ደሞ ለሰው ብሎ አቅፎ ስሞ አስገባውና ማደሪያ ሰጠው። በመቀጠልም ዝንጀሮ ወደ ሰውየው ቤት ሄዶ ሰውየው እንዲያሳድረው ጠየቀ ሰውየውም ዝንጀሮውን እህሉን እንዳይነካበት በማስጠንቀቅ ማደሪያ ቦታ ሰጠው። ከዚያም አይጥም በተራዋ ሄደች ለሷም እንደ አቅሟ ትንሽዬ ቦታ እበሩ አጠገብ ተሰጣትና ከዛ ቦታ እንዳትንቀሳቀስ ማስጠንቀቂያ ተነገራት። በመጨረሻም የፈረደበት እባብ እንደሌሎቹ እሱም ባቅሙ ማደሪያ ሲጠይቅ ሰውየው በቁጣ አንተ ክፉ ደሞ አንተን እቤቴ ላሳድር ብሎ ሰደበው እባብ ግን አይ "ብከፋ ብከፋ ከሰው አልከፋ" በማለት ማደር ስላልተፈቀደለት በሃዘን እዛው ውጪ በሩ ላይ እየበረደው አደረ። በነጋታው ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነስተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። እንዲሁ በአንጻሩ አንድ ቀን ይሄ እነዚህን ሁሉ የተቀበለና ሁሉንም እንደ ስሜቱ ያስተናገደ ሰው ሃብቱ ሁሉ ጠፍቶበት ደህይቶ የሚበላው አጥቶ ተቸግሮ መንገድ ላይ ሲሄድ ያን ጊዜ የተቀበላትን አይጥ አገኛት እና እንዲህ አላት "አይጥ እንደምን አለሽ? አስታወሺኝ?" እሷም በመመለስ "አዎ አስታወስኩህ ሰው እንደምን አለህ ምነው በሰላም ነው?" አለችው። እርሱም የደረሰበትን ሁሉ ከነገራት በኋላ በነገሩ በጣም በማዘኗ መርዳት ስለፈለገች "ቆይ እዚህ ጋር ጠብቀኝ ብላ ሄዳ ከሰው ቤት ሰርቃ ወርቅ ሰብስባ አምጥታ ያሄንን ሸጠህ ሰው ሁን።" ብላ ሰጠችውና ተሰናብታው ሄደች። አይጥ ብድሯን በምትችለው መንገድ ከፍላ እንደ ሄደች ያን ግዜ በቤቱ የተቀበለውን ሰው አገኘው እሱም ያንን ሰው "አስታወስከኝ?"ብሎ ጠየቀው። ያ ውለታ የተዋለለት ሰው ግን ውለታ የዋለለትን ሰው አላስታወሰውም ከብዙ ንግግር በሃላ አስታወሰው እሱም የደረሰበትን ችግር ሁሉ ነገረው እሱም "በል ምንም የለኝም ልረዳህም አልችልም ነገር ግን እሱን የያዝከውን ወርቅ የምትሸጥበት ቦታ ልውሰድህ" ይለውና ወርቁን ተቀብሎ ይይዝለትና አብረው ይሄዳሉ። ብዙ ከተጓዙ በኋላ ያን ምስኪን ሰው ወደ ገደል ገፍትሮ ከቶ ወርቁን ይዞበት ይሮጣል። ያ ምስኪን ሰው ተገለባብጦ ገደል ወስጥ ይወደቃል በድንገትም ያን ግዜ ውለታ የዋለለትን ዝንጀሮ ያገኘዋል ሰው ያደረገውን ከሰማ በሃላ በጣም በማዘን ዝንጀሮ ምንም ሊረዳው ስላልቻለ እንደ ምንም ብሎ ከጉድጓድ ውስጥ ያወጣውና በሃዘን ይሸኘዋል ያው ዝንጀሮም በሚችለው መጠን ብድሩን መለሰ። ከብዙ መንገድ በኋላ ያሰው እባብን ያገኘውና እንዲህ ይለዋል "እባብ እንምን አለህ? አስታወስከኝ? " ሲለው እባብ በፍጥነት "አዎ አስታወስኩህ አንተ ያን ጊዜ ክፉ ብለኸኝ ውጪ ያሳደርከኝ ሰው ነህ አይደል ብሎ ጠየቀው። ሰውየውም አዎ ብሎ መለሰለትና ሰው ያደረገውን እና ሌሎቹ የከፈሉትን ውለታውን ሲነግረው እባብም በማዘን "ያን ግዜ ብከፋ ብከፋ ከሰው አልከፋም አላልኩህም አለውና በል እኔ ምንም የለኝም ግን በአንድ ነገር እረዳሃለሁ እዛ ማዶ ጋራ ያለ አንድ ሃብታም ሰው አንድ የሚወዳትን ልጁን ነገ ይድራል እኔ ላንተ መርዜን እሰጥህና ሄጄ እሷን እነድፋታለሁ ከዚያም አንተ መርዙን ይዘህ መጥተህ እሷን ታድናታለህ አባቷም ደስ ይለዋል" ይለውና፤ በነጋታው መርዙን ሰጥቶት ይሄድና ልጅቷን ይነድፋታል ከዚያም አባቷ ልጄ ልትሞትብኝ ነው ብሎ ሲጨነቅ ልጁን ያድንለታል ከዚያም አባትየው በደስታ የሃብቱን እኩሌታ በእባብ ምክንያት ይሰጠዋል ስለዚህ የተናቀውና የተጠላው እባብ ታላቁን ቁም ነገር ላልተዋለለት ውለታ መለሰ። የተከበረው የሰው ልጅ ግን የተዋለለትን ውለታ በክፋት ለውጦ እራሱን አዋረደ። ማስተዋልን ይስጠን! ፈጣሪን እንፍራ። ሼርርርር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ @ethionews_1
نمایش همه...
🟣🌀 #ወርቃማ_አባባሎች 🌀🟣 🟢 ከልምዶች ሁሉ ጎጂ 👉👉 ጭንቀት 🟢 የሚያኮራ ስራ 👉👉 ሰወችን መርዳት 🟢 አስቀያሚ ባህሪ 👉👉 ራስ ወዳድነት 🟢 መጥፎ ልማድ 👉👉 መስረቅ 🟢 ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት 👉👉 ወጣትነት 💠 ትልቅ መሳሪያ 👉 ብርታት 💠 መጥፎ ፀባይ 👉 ይሉኝታ 💠 ቆንጆ ጌጥ 👉 ፈገግታ 💠 አደገኛ ስብከት👉 አሉባልታ 💠 ትልቅ ስጦታ 👉 ምክር 🟣 የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ 👉 ኑሮ 🟣 አደገኛ መሳርያ 👉 ምላስ 🟣 ራስን የመጉዳት ዘዴ 👉 ማልቀስ 🟣 በሀይል የተሞላ ቃል 👉 እችላለሁ 🟣 ታላቅ ተስፋ 👉 እኖራለሁ 🔶 ️ዉድ ሀብት 👉 እምነት 🔶 ️ሀይለኛ የመገናኛ መሳርያ 👉 ፀሎት 🔶 ️ልንፈታዉ የሚገባን ችግር 👉 ፍርሀት 🔶 ️ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን 👉 የአእምሮ እረፍት 🔶 ️መጥፎ የዉድቀት በሽታ 👉 ከስህተት ይቅርታን አለመጠየቅ 🔶 ️የህይወት ሀይለኛ ጉልበት 👉 አእምሮ 🔶 ️ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ 👉 መስጠት 🟢 #ወዳጀ_ሆይ 🟢 🚹 ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ 🚺 ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት 🚹 ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት 🚺🚺 ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል 🚹🚹 @ethionews_1 ሼርርርር
نمایش همه...
✅🌀 ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮሀል፡፡ በዛው ልክ በውሀ የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም ሲንከባለልም በእርጋታ ነው የሰው ልጅም እንደዛ ነው፡፡ ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው #ከመጮህ እና #ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር የለም፡፡ 👉 በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ። 👉 በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው፡፡ አንዱ ፌርማታ ላይ #ይወርዳል ከዚያ በኋላ አታገኘውም፡፡ አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል፡፡ 👉 ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ባለጌም የመከሩት ዕለት ይብሰዋል" እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም ፣መልስ ለሁሉም አይመለስም፤ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም፡፡ ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ለይ፡፡ ዕንቁላሎችህንም የምታስታቅፋቸውን ዶሮዎች ምረጥ፡፡ ❇✴ የሶቅራጠስ አባባሎች ✴❇ ✅ ያልተፈተነ ሕይወት መኖር እርባና ቢስ ነው ። ✅ ልታስፈፅም የማትችለውን ትዕዛዝ አትዘዝ ። ✅ ራሱን በቅድሚያ ማንቀሳቀስ የቻለን ፣ ዓለምን እንዲያንቀሳቅስ ፍቀድለት ። ✅ እውነተኛ ጥበብ አለማወቅን ማወቅ ነው ። ✅ ብቸኛው ጥሩ ነገር ማወቅ ሲሆን ፣ ብቸኛው መጥፎ ነገር ደሞ መሀይምነት ነው ። ✅ ሐሰተኛ ቃላት በራሳቸው ብቻ ኃጢያት ሳይሆኑ ነፍስንም በሀጢያት ይመርዛሉ። ✅ በቅንነት ስህተትህን የሚገልፁልህን እንጂ ቃልህንና ተግባርህን በሙሉ የሚያወድሱት ታማኝ አይምሰሉህ ። ✅ አንዳንዶች ለመኖር ሲበሉ ሌሎች ደሞ ለመብላት የሚኖሩ አሉ ። ✅ አላዋቂ መሆኔን በማወቄ ብልህ ነኝ። ✅ መልካም ሰውን በህይወትህ እያለም ሆነ ከሞተ በኋላ የሚጎዳው ነገር የለም። ✅ ባለው ያልረካ የሚመኘውንም ቢያገኝም አይረካ ። ✅ ለራስህ ማሰብ ስትጀምር ራስህን ታገኘዋለህ። ✅ እውነተኛ ጥበብን የምናገኘው ስለሕይወት ፣ ስለአለምና ስለራሳችን ብዙም እንደማናውቅ ስንገነዘብ ነው። ✅ በዚች ምድር ሁሉም ነገር ያልፋልና ስታገኝም ከልክ በላይ አትፈንጥዝ ፣ ስታጣም አብዝተህ አትከፋ! ። ✅ ወደ ክብር የሚወስደው አቋራጩ መንገድ የምትመኘውን ለመሆን መጣር ነው!። ሼርርርር @ethionews_1
نمایش همه...