cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Fuad shemsu || ፋአድ ሸምሱ

ይህ የኔፋአድሸምሱ(alburda)የግልገፄ ነው የተለያዪ የኔንም ሆነየሌሎች ኢስላማዊ የጥበብ ስራዎች ከደጋጎች የተገኙ ዲናዊምክሮች እንዲሁም የህይወት ተሞክሮዎች አጋራለው አርሂብ ኹዝቢየዲ ዘይኔ ያነቢ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
605
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

_ኑር_ሁሰይን_ፉዓድ_ሸምሱ_New_Ethiopan_Menzuma_2021_Al_Faruk_Multimedia_Production480P.mp316.12 MB
🇪🇹 𝕓𝕚𝕝𝕒𝕝 𝕗𝕒𝕣𝕚𝕤: ይህ የኔ የቢላል ፋሪስ ይፋዊ የዩቲብ ቻናል ነው አዳዲስ የመንዙማ ስራዎቼን በዚህ የዩቲብ ገፅ ያገኛሉ Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/channel/UC9p62AAcytXdRqnBZCZDLsw
نمایش همه...
ሰይዱል ዓሪፊን ኑርሁሴን ባሌ ክፍል ሁለት (ቅድመ ታሪክ 02 ) ሼኽ ኢብራሂም በመማርና ማስተማር ሲዘዋወሩ ቆይተው በኋላ ወደ ባግዳድ በመጓዝ በሰይዱና ዐብዱልቃዲር አል ጀይላኒ የትምህርት ማዕከል በመግባት የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን ከተሰዉፍ ጋር ተምረው ብልህና ዕውቀት የሰረጻቸው ትጉህ መሆናቸውን አስመስክረዋል። የኋላ ኋላ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ጥበባዊ መንገድ እንጂ በጦርና ተጽዕኖ የማትቀና መሆኑን አጥብቀው የተረዱት የቃዲሪያ ጦሪቃ ቀንባቢ ዐብዱልቃዲር አል ጀይላኒ በትምህርት ማዕከላቸው ተምረው የተመረቁትን 405 ምሩቃን ዳዒዎች '' ወደ ሐበሻ ሂዱና በጥበብ ወደ ኢስላም ተጣሩ '' በማለት ተልዕኮ አስይዘው፣ ቡድኑንም ታላቁ ሸይኽ አባዲር ይመሩት ዘንድ መርጠው መርቀው ላኳቸው። ከነዚህ 405 ጠቢባን መካከል ደግሞ የሰይዲ ኑርሁሴን ወላጅ አባት ሸይኽ ኢብራሂም ዓብዱላህ ይገኙ ነበር። ይህ የዳዒዎች ቡድንም በታላቁ አባዲር እየተመራ እንደ ኤሮፓውያኑ የጊዜ ቀመር በ 1216 ዓ\ል ወደ ምስራቃዊቷ ፈርጥ ሃረር ገባ። ዳዕዋውም በይፋ በሐረር ተጀመረ ጠቢባኑም በመላዋ ኢትዮጵያ ተበተኑ። ሰይድ አባድር የጠቢባኑ መሪም ሃረር ላይ ቀርተው ታላቅ ታሪክ ሰርተው እዛው ሐረር አረፉ። ሸይኽ ኢብራሂም ዐብዱላህም የአላህ ውሳኔ ዐሩሲ ባሌ አናጂና ውስጥ ጉልቻ አስጎለታቸው። ሼኽ ኢብራሂም የመጡበትን አላማ ለማሳካት በሃገረ ሐበሻ ላይ ታች ሲሉ ቆይተው በስተመጨረሻ ዐሩሲ ባሌ ላይ ተቀመጡ። እዚያም በቃዲሪያዊ መደድ ኸልቁን በተሰዉፍ ጥበብ ሲጣሩ ኖረዋል። በዚህም ምንም እንኳን ዓረባዊ ቢሆኑም ከማህበረሰቡ ጋር ተላምደው የኦሮሚኛ ቋንቋንም ተምረው ከዛው ከባሌ የተገኘች ማኪዳ የተባለች እመቤት በሃገሩ ወግ መሰረት አግብተው ኖረዋል። ከዚህ የተባረከ ትዳርም ሙሐመድ ፣ ሱለይማን እና ኑርሁሴን የተባሉ ደጋግ ልጆች ተወልደዋል። ከ3ቱ ልጆችም በሰፊው የአባታቸውን የዳዕዋ እርምጃ የተራመዱት ሸይኹ ሰቀለይን ኑርሁሴን ናቸው። ሸኽ ኢብራሂም መልካ የሚል ቅጽል ስም እንደነበራቸውና መልካ ከሚባል ወንዝ ጋር ተጎራብተው የኖሩ የነበረ በመሆኑ የተሰጣቸው ስያሜ መሆኑን ፣ ሲጠሩም ሸህ ኢብራሂም መልካ ተብለው መሆኑን የሚጠቁሙ ሰነዶች መኖራቸው ተረጋግጧል። ውድ አንባቢያን አሁን እያወራን ይለነው የቅርብ ግዜ ታሪክ ወይም የዛሬ 100 እና 200 አመት ገደማ የተከሰተ ክስተት አይደለም። ይልቁንም አሁን ካለንበት ዘመን ከ750 ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ተመልሰን ታላላቅ ዐለም አቀፍ ለሂቃን በነበሩበት ልዩ ዘመን የተከሰተውን ነው። ያ ዘመን በኤሮፓውያንና በኛ አቆጣጠር የ አስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በሂጅራ አቆጣጠር ደግሞ የሰባተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ነበር። #ይቀጥላል ................ S U A L I H A S T A T K E
نمایش همه...
ሰይዱል ዓሪፊን ኑርሁሴን ባሌ ክፍል አንድ (ቅድመ ታሪክ 01 ) ስለ ሊቀ ጠበብቱ የምሁራን አባት ጠቢቡ የተሰዉፍ አክሊል ሰይዲ ኑርሁሴን ግለ ማንነት ከማውራታችን በፊት ስለ መሰረታቸው ማውራት ተገቢ ነው፡፡ የሰይድ ኑርሁሴን አያት ሼኽ ዐብዱላህ ይባላሉ። እሳቸው የአቡበክር ልጅ ናቸው። የዘር ሃረግ ሰንሰለታቸውም ዐብዱላህ አቡበክር ዑመር የሕያ ኢድሪስ ዒሳ ዳዉድ ዓባስ አቡበክር ይልና ቆጠራው ከአቡበክር አባት ዓቂል ቢን ዐቡጧሊብ ቢን አብዱልሙጠሊብ ጋር ተሰናስሎ ይመዘዛል። በዚህም ሙጦሊብይ ናቸው ማለት ነው። ይህ የአሽራፍ ዘር ነው። ትልቁ አያታቸው ዓቂል የሰይዱና ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ወንድም ናቸው፡፡ ሰይድ ኑርሁሴን ደሞ የነብያችን አያት ዐበዱል ሙጦሊብ 13ኛ ዝርያ ናቸው። ለዚያ ነው የአናጂናው ጸሃይ ቁረሽይ ያውም የሰይዱል ኸልቅ ነብዩ ሙሐመድ ቤተሰብ ናቸው የምንለው፡፡ እኒህ ዐብዱላህ የተባሉ ሰው ዐረባውያንና ሶማሌያውያን በጋራ በሚኖሩበት ስፍራ ይኖሩ የነበሩ በሃገሩ የታወቁ ዳዒ ገሳጭ የነበሩ የታወቁ ሊቅ ናቸው። በዚያ አካባቢ እስልምናን በማስፋፋትና ሙስሊሞቹን በኢስላማዊ አዳብ በማደርጀት ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ይነገራል። የርሳቸው አባትና አያትም እንደሳቸው ሁሉ ዳዕዋው ላይ የተሰማሩ እንደነበሩ ፣ ስራውን የወረሱትም ከወላጅ አባታቸው እንደሆነ ይነገራል። በኋላ ላይ እሳቸውም ስራቸውን ለልጃቸው ማወረሳቸውን ወይም ልጃቸውም የአባታቸውን መንገድ ለማስቀጠል መታተራቸውን ወደፊት እንገነዘባለን። በባህሪያቸውም ከዓለማዊ ክጃሎት የነጡ ዓላማና ግባቸው ኢስላምን ማስፋፋት የሆነ እየተንቀሳቀሱ የሚያስተምሩ ነበሩ። እኒህ ዐብዱላህ የተባሉ ሰው ካበረከቷቸው የሳቸውን ስራ የወረሱ ልጆች መካከል አንደኛው ደግሞ የሰይድ ኑር ሁሴን አባት ሼኽ ኢብራሂም ዐብዱላህ ናቸው። ሼኽ ኢብራሂም በአባታቸው መስመር ተጉዘው ፣ ዙህድን መርጠው ፣ ዐለማዊነትን እንቢ ብለው እድሜያቸውን በመማርና በማስተማር ያሳለፉ ለብዙዎች መቅናት ምክንያት የሆኑ ሰው ናቸው። የነበሩበት ዘመንም ታላቁ ሱፊይ የባግዳዱ ቁጥብ ሰይድ ዐብዱልቃድር አል ጀይላኒ ዒራቅ ባግዳድ ላይ የነገሱበት፣ ዝናቸውም የተንሰራፋበት ነበርና እዚያ ድረስ በመሄድ የጀይላኒ ደረሳ ሆነው ዕውቀት ሲቀስሙ ቆይተዋል። በማስተማርም በተለይ በየመንና በአሁኗ ሳዑዲ መሃል ጂዛን በምትባል ቦታ በልዩ ስሟ ''አሲር'' ውስጥ ከፍተኛ ዕውቅናን ያተረፉ ናቸው። እንዲህ ነው። የብዙዎቹ ዓለም አቀፍ ልሒቃንና ወልዮች የህይወት ታሪክ ሲመረመር ከጀርባቸው ብርቱ ሊቅ አባት መኖሩን ማስተዋል የተለመደ ነው። በርግጥ አንዳንዴ ከደግ አብራክ እርጉም ፤ ከመርዛማ ሰው አብራክ መልካም መወለዱ የማይስተባበል ሐቅ ነው። የሆነው ሆኖ ከዐቂል ቢን አቢጧሊብ ጀምሮ ጥሩውን ጥሩ፣ ደጉን ደግ፣ ሸጋውን ሸጋ እየወለደው በዐብዱላህ አርጎ ሸህ ኢብራሂም ጋር እስኪደርስ በርካታ ታሪክ መመዝገቡ አይሳትም። ነገር ግን ከሁሉም የዚህ ዘር ማንዘር ውጤቶች በላይ የጎላ ታሪክ ያስመዘገቡት ፣ ከኋላ መጥተው የፊተኞቹን ሁላ ያስረሱት የሐበሻ ሁለንተናዊ ቁጥብ አቢዮ ሰይድ ኑርሁሴን ናቸው። #ይቀጥላል ................ ኢንሻ አሏህ በተከታታይ ስለ አቢዮ ኑራ ሁሴይን ታሪክ ለመዳሰስ ክንሞክራለን S U A L I H A S T A T K E
نمایش همه...
ሰይዱል ዓሪፊን ኑርሁሴን ባሌ ክፍል ሶስት (ቅድመ ታሪክ ማጠቃለያ) ውድ አንባቢያን ባለፉት ክፍሎች ላይ ስለ ሰይዲ ኑርሁሴን ወላጆች የተወሰነ ብለናል። አሁን ደሞ ወደ ዋናው የታሪካችን ይዘት እንገባና ስለ ሰይዱል ዐሪፊን እናወራለን። ከዚህ ቀደም እናዳስቀመጥነው እያወራን ያለነው ከ700 አመታት በፊት ስለነበሩ ታላቅ ሰው ነው። ታድያ ስለሳቸው ታሪክ እድሜ ጠገብ ከሆነ የጽሁፍ መረጃ ይልቅ እድሜ ጠገብ አፈ ታሪክ መብዛቱ ገንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል። ይህ ማለት ግን ፍጹም አልተጻፈም ማለት አደለም። በኢትዮጵያ ኢስላማዊ ታሪክ ላይ ዳዴ እያሉ ያሉ ጸሃፊያን ሁሉ ስለሳቸው አትተዋል። የበዙ የውጪ አሳሽ የታሪክ ተመራማሪዎችም ከ50 አመታት ወዲህ በሰፊው ከትበዋል። የሀበሻን ልሂቃን ታሪክ በመመዝገብ የታተሩት ኢትዮጵያውያን ልሂቃንም ቀላል የማይባል ታማኝ መረጃ አኑረዋል። ዋናው ነገር በጽሁፍ ከሰፈሩትና በበዙ ሰዎች በአንድ አይነት ቃል የተተረኩትን አፈ ታሪኮች በመሰብሰብ ቀጣዮቹን ክፍሎች የቀደሙትን ክፍሎች እንዳስቀመጥነው እንደምንሄድበት ይሰመርበት። ሰይዱናቁጥቡል ሐበሻ ኑርሁሴን ኢብራሂም አል ዐሩሲይ አል ባልይ አል አናጂንይ እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ 1291 እንደ ሂጅሪያ አቆጣጠር ደግሞ በ 690 ባሌ አናጂና ውስጥ ተወልደዋል። ይህ የተወለዱበት ትክክለኛ ዘመን መቼት መሆኑን ጸሃፍቱም አፈታሪኩም በአንድነት አጽድቆታል። በርካታ የተለያዩ ጥናቶች ላይ ተመርኩዘው የተጻፉ ባለ መረጃ ጽሁፎችና የታሪክ ማህደሮች ሰይዱል ዐሪፊን ከ 400 ዓመታት በላይ በህይወት የቆዩ እድሜ ጠገብ አባት መሆናቸውን በጉልህ ያመለክታሉ። እንደውም ወጣቱ የተባ ብዕረኛ ከድር ታጁ ዘመነ ታሪክ በተሰኘ መጽሃፉ መረጃዎች ተሟልተውልኛል በሚል መንፈስ ሰይዱል ዐሪፊን ከ 1291 እስከ 1765 በህይወት የኖሩ የ 474 ዓመታት ባለጸጋ መሆናቸውን ጽፏል። በዚህ አካሄድም እርሳቸው ከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ኖረዋል ማለት ይሆናል። ይህም ለመቀበል የማያዳግት እውነት ሆኖ ይገኛል.። በስያሜያቸው ላይ ልሂቃን ሁለት አይነት አስተያየት ሰጥተዋል። ይኸውም ከፊሉ ስማቸው ኑር ሁሴን ነው ሲሉ የተቀሩት ደግሞ ስማቸው ሁሴን ነው ይላሉ። ሰይዱል ዐሪፊን ኑርሁሴን በሚል ስም መታወቃቸው አሻሚ ጉዳይ አይደለም። ሆኖም ስማቸው ሁሴን ነው የሚሉቱ ልሂቃን ኑር የሚለው ስይሜ ሁሴን ከሚለው ስያሜ የተጨመረው በብዛት ብርሃን የማብራት ከራማ ስላሳዩና በርካቶችን ከኩፍር ጨለማ በጥበብ ወደ ብርሃናዊው እስልምና የመመርያ ሰበብ ስለሆኑ '' ብርሃናማው ሁሴን'' የሚለውን ለማንጸባረቅ ነው የሚል አመክንዮ ያቀርባሉ። ታድያ ሁለቱም እሳቤዎች ለመቀበል የሚያዳግቱ ሆነው አናገኛቸውም። በመሆኑ ሁሴንም ሆነ ኑር ሁሴን የስያሜው ጉዳይ የሚያጣላ አይሆንም። ግን የበዙ የሳቸው ተከታዮች ''ኑር ሁሴን'' ከሚለው ይልቅ ''ኑራ ሁሴን'' ፣ ''ድሬ ሼኽ ሁሴን '' የሚለውን ስያሜ መጠቀማቸው ምናልባትም ስማቸው ሁሴን ሞገሳዊ ቅጥያ ስማቸው ደግሞ ኑር ወይም ኑራ ነው የሚሉት የተሻለ መረጃ ያለው ሆኖ ይስተዋላል። #ይቀጥላል ................ S U A L I H A S T A T K E
نمایش همه...
(Awrad,katbare).amr4.73 MB