cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

👑👑@Official_gamine

https://t.me/joinchat/AAAAAFPb57mP2KJTzjrIMw @Alegaminexobot

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
264مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Watch "አስቸኳይና አሳዛኝ መልእክት! ለሁሉም አድርሱ" on YouTube https://youtu.be/PU2uHN_a6Is
نمایش همه...
አስቸኳይና አሳዛኝ መልእክት! ለሁሉም አድርሱ

አስቸኳይና አሳዛኝ መልእክት! በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማቅንብር:- e-BZAugust 23, 2020 - Washington DC

نمایش همه...
[ንቁ] ሰለሞን ቴክ ቶክ ለኢትዮጵያ ህዝብ እያስተላለፈ ያለው ግልፅ የኢሉሚናቲ ዕቅዶች | GMO, Micro Chips, Vaccination

ስለተመለከታችሁን እናመሰግናለን ቪዲዮውን ሼር በማድረግ እናንተ ያገኛችሁትን እውቀት ለሌሎች አሳውቁ። ይህንን የአክሱም ቲዩብ ዝግጅት ዳውንሎድ አድርጎ ድጋሚ በሌላ ቻናል ላይ መጫን በጥብቅ የተከለከለ ነው። © Axum TubeLike, Comment a...

😂😍😁😊😘 @offical_gamine
نمایش همه...
ፈ ተ ና ዬ🌺 ❣ :¨·...............:¨·.❣ ♥️ ክፍል 6 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ በፍቅር እኔ እና አንቺ ተዘጋጅቶ የቀረበ🥀 ልኡሌንና እናቱን ትቻቸው ስሮጥ ለሚያየኝ ሰው እብድ እመስል ነበር ልኡልም ተከትሎ እጄን ያዘኝ እንባዬ ይጎርፋል እሱም በጣም ደንግጦ ይቅርታ አጥፍቻለውኮ ግን እባክሽ ይቅርታ አርጊልኝ አለ እኔም እንባዬን እየጠራረኩ እኔ ይቅር ብልህ ባንተ ምክንያት የተመሰቃቀለው ህይወቴ ይቅር የሚለኝ ይመስልሃል አልኩት እባክሽ እክስሻለው ደግሞ እመኚኝ የጠፋሁብሽ ላንቺ ስል ነው ብዙ ማስተካከል የነበረብኝ ነገር ነበር አለ አይደል እኔም ሁሉንም አውቄዋለሁ ዳግም ግን አትምጣብኝ የኔ ልብ ስትፈልግ የምትወጣበት ስትፈልግ ደግሞ የምትገባበት መሸታ ቤት አይደለም እንዳትከተለኝ ብዬ በጩኸት ከተናገርኩ ቡሃላ በድጋሜ ትቼው ሄድኩ ከዛ ቀን ቡሃላ ደግሞ ፍቅር በድጋሚ ያገረሽብኝ ጀመር ስለልኡል ማሰብ ለማቆም የግድ ሌላ ወንድ መተዋወቅ ነበረብኝ እናም ስራ ቦታ አብሮኝ ካለ አንድ ወንድ ጋር ፍቅር ጀመርኩ በእውነቱ ቆንጆና እረጋ ያለ ባህሪ አለኝ ለዛም ይመስለኛል ወንድ ልጅ ለመማረክ ግዜ አይወስድብኝም እናም ከአዲሱ ፍቅረኛዬ ሱራፌል ጋር ጥሩ ግዜን ማሳለፍ ጀመርኩ በርግጥ ሱሬን አላፈቀርኩትም እሱ ግን በጣም ይሳሳልኝ ጀመር ሁሌም ለኔ አዲስ ነገሮችን ያዘጋጃል ሁሌም ይሸኘኛል ልኡል ደግሞ እኔን መከታተል ስራው አርጎታል ... ከናቲ ጋርም እደመጀመርያው አንገናኝም ምክንያቱም እሱ የሚሰራው ከአዲስ አበባ ውጪ በመሆኑ ነው... አንድ ቀን ልደቴ ነበር እናም ሱሬ ሰርፕራይዝ አርጎኝ በጣም ደስተኛ ነበርኩ ሱሬ ከብዙ ነገሩ ውስጥ ለኔ ያለው ክብር የእውነት ይገዛኛል እናም ዛሬ ለመጀመርያ ግዜ ሱሬን ከንፈሩን ሳምኩት ይሄኔ ሉሌ ባይኑ በብረቱ ተመለከተኝ ተመልክቶም ዝም አላለም ከሱሬ ጋር የቆምንበት ቦታ ጋር ከጓደኞቹ ጋር መጣ ከዛ ጓደኞቹ ሱሬን እናናግርህ አሉት ልቤ በፍርሃት ራደ ምንድን ነው ብዬ ዞር ስል ለኔ ሲል የተወውንና እናቱን ያስደሰተበትን ሲጋራ ለኩሶ ሲምገው አየሁት የምሬን ፈራሁት ከዛም ሱሬን እጁን ይዤ ታክሲ የሚይዝበት ቦታጋ ወሰድኩት ግራ እንደተጋባ ያስታውቃል ይሄኔ ልኡል ሰምተሃላ ድጋሚ ካጠገቧ ባይህ እገልሃለው አለው እኔም እልህና ንዴት መላ ሰውነቴን ተቆጣጥሮት ሱሬ እስኪሄድ ዝም ካልኩ ቡሃላ... ቆይ ምንድን ነህ ህይወቴን ለመመሰቃቀል የተፈጠርከው ምን አረኩህ ብዬ ጮህኩ ይሄኔ እንደ ህፃን እምባው እየረገፈ አንቺስ እንደመልአክ ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ካስተካከልሽኝ በኋላ እንደ ሴጣን መልሰሽ የከዳሽኝ አለ እኔም ንዴቴ ሳይበርድ በኔ አታሳብ ሲጀመር የልጅ አባት መሆንህን አትርሳ ደግሞ ልንገርህ አላፈቅርህም አርፈህ ልጅህን አሳድግ አትድረስብኝ አልኩት ይሄኔ የምን ልጅ ነው የምታወሪው እኔ አፈቅርሻለው ካንቺ ውጪ ሴት ልጅ በፍቅር ቀርቤ አላውቅም ሙሉ በሙሉ ማጨስና አጉል ሱስ የተውኩት አንቺን ሳገኝ ላንቺ ነበር አለ ውሸታም ጭራሽ ከዛች ሴት መውለድህን ካድክ አልኩት የቷ አለ ለማስታወስ በሚመስል መልኩ ፊቱን ጭፍግግ አርጎ ይበልጥ አናደደኝ........ ✎ ክፍል ሰባት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ •●◉Join us share •• @offical_gamine ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
نمایش همه...
​​ፈ ተ ና ዬ🌺 ❣ :¨·...............:¨·.❣ ♥️ ክፍል 7 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ለማለቅ አንድ ክፍል ቀረው🥀 እኔና ሉሌ እረጅም ሰአት ተጨቃጨቅን ከዛ የዛን ቀን ስለመሸብኝ ትቼው ሄድኩ በሁለተኛው ቀን ስራ ልገባ ታክሲ ስጠብቅ ልኡል መጣ ይሄኔ ከልኡል አርግዣለው ስላለችኝ ልጅ ነገርኩት በመጀመርያ አላመነኝም ነበር ከዛ ግን የተፈጠረውን በሙሉ ነገርኩት የእውነቱን ተናዶ ፊቱ ተለዋወጠ ቀይ ፊቱ ሚጥሚጣ መሰለ እገላታለው አለኝና በቆምኩበት ትቶኝ ሄደ ... ግራ ስለገባኝ ምንም አልመለስኩለትም ... ቀጥታ ወደስራዬ ሄድኩ ... ቀኑን ሙሉ ስለልኡል ሳስብ ዋልኩ ለምን እንደዛ ሆነ ምናልባት ልጅቷ ዋሽታኝ ይሆን? ግን ለምን ብላ ደግሞም አብረው አይቻቸዋለው ... ብቻ ከራሴ ጋር ስሟገት ዋልኩ በጭንቀት እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ በርግጥ ከበፊቱ አሁን ደና ነኝ ማለትም ማምሸትና ባመሸሁበት ማደር ትቻለው እድሜ ለሱሬ ከኔ ምንም ምላሽ ሳይጠብቅ ከልቡ ይወደኛል ይንከባከበኛል ... ያ ደግሞ እኔን ከመጥፎ ጎዳና መልሶኛል እማዬም እፎይ ብላ በኔ ደስተኛ ሁናለች ስለዚህ ምንም ሆነ ምን ዳግም ልኡልን አልቀርብም ሲቀጥል ደግሞ ምንምኳ መጠጥ ጭንቀቴን ቢያስረሳኝም አልጠጣም ... ይህ በንዲህ እንዳለ ማታ ላይ ከስራ ስወጣ ብቻዬን ነበርኩ ሱሬ ስራ አመሻለው ስላለኝ ብቻዬን ወደቤት መሄድ ጀመርኩ ይሄኔ ልኡል ሁሌም እንደሚያረገው ውጪ ይጠብቀኝ ነበር ዛሬ ግን ለየት የሚያረገው ሉሌ ከልጁ እናት ጋር ነው ሳያቸው ሊነግሩኝ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ ገባኝ ከዛም ወደኔ ሲመጡ ቆሜ ጠበኳቸው ልጅቷ ታለቅሳለች ለምን እንደምታለቅስ ባይገባኝም ዝም ብዬ መከታተል ጀመርኩ በይ ንገሪያታ አላት ለመስማት ብዙም አልጓጓው ይሄኔ አንዱ የልኡል ጓደኛ መጣ ሁላችንንም ሰላም ካለን ቡሃላ ቅድስቴ እሷ ህይወት ትባላለች የልጄ እናት ነች አለኝ ... ከት ብዬ ሳኩና የተሻለ ድራማ የላቹም አልኩት ... 3ቱም በየተራ እኔን ለማሳመን ማውራት ጀመሩ ማንንም አልሰማም በቃ የኔና ያንተ ግንኙነት አብቅቷል ብዬ ትቻቸው ሄድኩ.. ይሄኔ ልጅቷ ሮጥ ብላ ያዘችኝና እባክሽ ይቅርታ አርጊልኝ እናም ልኡል ያፈቅርሻል ፍቅራቹን ቀጥሉ አለች በጣም ስለተናደድኩ በጥፊ መታኋትና ያኔ ምን ብለሽኝ ነበር አንቺ ምን አይነት ሰው ነሽ ሁለተኛ ብትደርሺብኝ እገልሻለሁ ብያት ጥያት ሄድኩ........ ✎ ክፍል ስምንት ወይም የመጨረሻው ክፍል ይለቀቅ ካላቹሁ ❤VOTE ያርጉ👇 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ •●◉Join us share ••●◉ @offical_gamine ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
نمایش همه...
​​​​​​ ┈┈••◉◈◈◈◉●••┈ ፈ ተ ና ዬ💔 :¨·.◈............◈:¨·. ♥️ ክፍል 3 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 በፍቅር እኔ እና አንቺ ተዘጋጅቶ የቀረበ። እንደዛ በፍቅር ክንፍ ያልኩለት ወንድ በከዋክብት ፊት የገባውን ቃል እረስቶ በጠራራ ፀሀይ ከሌላ ሴት ሲወዳጅ ማየት ለኔ ሞት ነበር ያስመኘኝ ... መንገድ ላይ እናቷ እንደጠፋችባት ህፃን እንባዬ መንታ መንታ እየወረደ እጓዛለው ይሄን ሁኔታዬን የተመለከተ ወጣት ወደኔ ተጠግቶ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ ቀና ብዬ ሳላየው እንኳ ትቼው መንገዴን ቀጠልኩ ይሄኔ ክንዴን ያዝ አደረገኝ ንዴት መላ አካላቴን ሲወረኝ ይሰማኛል መንጭቄው ልሄድ ስል ተረጋጊ የኔ ቆንጆ አለ የድምፁ እርጋታ የእውነትም ያረጋጋል እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆም አልኩ ... ቀና ብዬ ስመለከተው ፈገግታን ለገሰኝ ቆንጆ አይባልም ግን ወንዳወንድ ነው አብሬው ብሆን የልኡልን ክህደት የምረሳ መሰለኝ ልጁም በድጋሚ አይዞሽ እሺ ተረጋጊ አለኝ እኔም እሺታን ለመግለጅ አይኖቹን እያየው እራሴን ነቀነኩ ጀምበር እያዘቀዘቀች ነው ከመርካቶ ወደ አብነት በእግራችን መራመድ ጀመርን ዝምታችንን ለማፍረስ ይሁን ባላውቅም ናትናኤል እባላለሁ ናቲ ብለሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ አለኝ እኔም ሀዘኔን ለመርሳት እየጣርኩ ቅድስት እባላለሁ አለኝ እሱም እሺ ኪዲ በጣም ታምሪያለሽ ይህን ታውቂ ነበር አለኝ ...እእእ አልኩ እንደመሽኮርመም እያረገኝ ..እ... አይ አታውቂም ነበር ማለት ነው ዛሬ ልንገርሽ በተለይ አይኖችሽ ውብ ናቸው አልቅሰሽባቸው እንኳ ውበታቸውን መሸሸግ አልቻሉም አለኝ ... ይሄኔ ሉሌ ትዝ አለኝ በድጋሚ ተረበሽኩ እናም ስለተፈጠረው ሁሉ አጫወትኩት... ናቲ ጥሩ ልጅ ይመስላል ልኡል ምናልባትም አኔ ባሰብኩት መንገድ ላይሆን ይችላል አብሯት የቆመው የሚለውን እንዳስብ መከረኝ ... እየውልሽ ኪዲ ቆንጆ አንቺ ገና ህፃን ነሽ ስለዚህ በቀላሉ መሸነፍና እጅ መስጠት የለብሽም በዛ ላይ እናትሽ አንቺን ያልሆነ ቦታ ልታይሽ እንደማትፈልግ አትርሺ ... ነገ ይህን ፍቅረኛሽን አጊኝተሽ ለምን እንዲ እንዳረገ ጠይቂው ወይምኮ ይህች ልጅ እህቱ ልትሆን ትችላለች አለኝ ከተል አርጎም አሁን ወደቤትሽ ግቢ አጉል ሰአት ለሴት ልጅ ጥሩ አይደለም አለኝ... በጣም ገርሞኝ አየሁት ከዛም ወደቤቴ ገባሁ ለሊቱን ሙሉ ስለ ልኡል ሳስብ ነጋ አምላኬ እንደናቲ አፍ ባረገልኝና ምናለ እፎይ ባልኩ ምናለ ፍቅሬን ለሌላ ባላጋራብኝ ስል ተመኘው ልክ ሲነጋ ስራ ፍለጋ በሚል ሰበብ ወጣሁ ከዛም ቀጥታ የልኡል ሰፈር ሄድኩ ሉሌ ስራ ገብቶ እንደሆን ለማረጋገጥ ብዙም ሰአት አልፈጀምኝም ነበር ሄጄ እሱ ሲደብረው ተቀምጦ ሲጋራውን እያጨሰ በጭሱ የሚመሰጥበት ቦታ ተቀመጥኩ... ድንገት ባይምሮዬ የጎሳዬ ዘፈን ይመላለስ ጀመር..."ሸጋ ልጅ ባ^ሳቤ ድንገት ልቤ ገብታ ትመላለሳለች ቀን ማታ ቀን ማታ(2)" ይሄኔ ከሩቅ ትላንት ከልኡል ጋር ያየኋትን ሴት ተመለከትኩ ጊዜ ሳላጠፋ እየሮጥኩ ወሷ ሄድኩ ልጅቷ ነብሰ ጡር ናት ሆዷን አይቼ እርጉዝ ነሽ ምነው ጥላ ሳትይዢ በዚ ፀሀይ አልኳት የምፀት የሚመስል ፈገግታ በትንሹ ፈገግ ብላ ፀሀይ የታል አለች እኔም የማወራው አጥቼ በመዘባረቄ እንደ ማፈር ብዬ እባክሽ ስለ ልኡል ልጠይቅሽ ብዬ ነው አልኳት እሷም በቅፅበት ፊቷልውጥውጥ ብሎ እንደ መቆጣት አረጋትና መልሳ አይኗ እምባ አቀረረ ... እኔም ግራ ገብቶኝ ሁኔታዋን እከታተል ጀመር ከዛም አየት አርጋኝ አንቺንም አስረገዘሽ አለች ቃሉ ድንገት ሆኖብኝ አንደበቴ ተሳሰረ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ........ ✎ ክፍል አራት ከ110 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share @offical_gamine ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
نمایش همه...
​​ፈ ተ ና ዬ💔 ❣ :¨·...............:¨·.❣ ♥️ ክፍል 5 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ውጪ እንኳን ላድር አምሽቼ የማላውቅ ልጅ ዛሬ ሊያውም ከማላፈቅረው ወንድ ጋር ተኝቻለሁ ግም ምን ልበል ልናደድ ወይስ ደስ ልሰኝ ምንም አላውቅም ቀስ ብዬ የለበስኩትን ልብስ አየሁት እናም እንደለበስኩት ነው እኔ ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም ያም ማለት ድንግል ነኝ ግን ምንም አይነት ደም አይታየኝም ግራ ገባኝ ወንድ ልጅ ነው አብሬው እስከመተኛት ደርሼ ምንም አላረግንም ማለት አይታሰብም ... ነቅቶ የተፈጠረውን እስኪነግረኝ ጓጓው ... እኔ በጭንቀት ተጣጥፌ ወንበር ላይ ተቀምጬ እንዳቀረቀርኩ ነቃ በስስት ተመለከተኝ አይኖቼ እምባ አቀረሩ አንድ ጥያቄ እንዳለኝ ያወቀ ይመስል ለመናገር ጉሮሮውን ጠራረገ ከዛም ትላልቅ አይኖቹን በሁለት እጆቹ ያሻቸው ጀመር ሲነቃ ደፍርሰው ከነበረው በላይ ደፈረሱ ደና አደርሽልኝ ቆንጆ አለ ይሄኔ ያላባት ያሳደገችኝ እናቴ ሳልነግራት አድሬ ምን ያህል እንደምትጨነቅ እና ሉሌ ከሌላ ወንድ ጋር መማገጤን ሲያውቅ ምን ሊለኝ እንደሚችል አስቤ እራሴን ጠላሁት የማረባ ሴት መሆኔ ታወቀኝ ... ዝምታዬ ያስፈራው ናቲ ከተኛበት አልጋ ወርዶ ከተቀመጥኩበት ወንበር ላይ አንስቶ አልጋው ላይ በጀርባዬ አስተኛኝ የልብ ምቴ ጨመረ ግን ካንደበቴ ቃል አሎጣም ... ክንዱን አንተርሶኝ ከጎኔ ተኛ ... ደንግጠሻል? አለኝ አይ አልደነገጥኩም አልኩት እሺ ማታ ምን እንደተፈጠረ ታስታውሻለሽ ሲል ጠየቀኝ አ...ይ አልኩ እሺ እነግርሻለሁ ሲል ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ካንገቴ ቀና አልኩ ከዛም እ...እኔ ማወቅ የምፈልገው አንድ ነገር ነው እናም ወሲብ ፈፅመናል? ብዬ ጠየኩት ከት ብሎ ሳቀ ይበልጥ ግራ ገባኝ ... ዝም ብዬ ተመለከትኩት ልክ ስቆ ሲጨርስ ... በፍፁም አለኝ ኮራ ብሎ አላመንኩትም ... ብፈልግ እንኳ ሰክረሽ አላደርግም አለኝ ይሄኔ በልቤ ፈጣሪን አመሰገንኩ... ከዛ ቀን ቡሃላ እኔም ዱርዬ የምባል አይነት ሴት ሆንኩ መጠጥ እጠጣለው ሺሻ ቤት ቤቴ አርጌዋለው ታድያ እናቴም በኔ ማዘኗን ቀጥላለች ናቲ በርግጥም ብዙ ግዜ መክሮኛል ከሱ ጋር ስሆን መጠጥ እንኳ ብዙ አይፈቅድልኝም ሺሻም ፈፅሞ አላጨስም ግን ከሱጋ የምሆነው ውስን ጊዜአቶችን ነው ምክንያቱም እሱ ስራ አለው... በዚ መልኩ ወራት አለፉ እናም ከዛ በላይ ክብሬን ማስጠበቅ አልቻልኩም ከናቲ ጋር አንሶላ ተጋፈፍን ... ይሄኔ ከዚ ቡሃላ ፍቅር የለም ብዬ አመንኩ እናም ስራ ፈልጌ ተቀጠርኩ ግን እቤት የምገባው ከምሽቱ 4፡00 ቡሃላ ነው ማንም ሰው ሲመክረኝ ያናደኛል ናቲ ፍቅረኛዬ ይሁን ወንድማዊ ጓደኛዬ ምኑንም አላውቀው ግን አብረን ማደር አዘወተርን ... ፍቅረኛ እይዛለው 3ወር ሳይሞላ እጣላዋለሁ ሌላ ፍቅረኛ እይዛለው ከዛም ከሱጋም እፋታለው ህይወቴ በዚ መልኩ እየቀጠለ ልክ ባመቴ ልኡል ደወለ ስልኩን ሳየው የደነገጥኩት መደንገጥ አሁን ድረስ ትዝ ይለኛል ግን አላነሳሁለትም የሚገርመው ግን ስራ ቦታዬን አፈላልጎ መጣ ሳየው የማደርገው ጠፋኝ ፍቅር እንዳዲስ አገረሸብኝ ግን ህይወቴ የተበላሸው በሱ ስለነበር ዳግም መጎዳት አልፈለኩም ግን ሊተወኝ አልቻለም ደጋግሞ ይቅርታ ጠየቀኝ... አንድ ቀን ከስራ ስወጣ ልኡል ከእናቱ ጋር እየጠበቀኝ አገኘሁት ደንግጬ ቆምኩ እናቱም የኔ ቆንጆ ደሞ ስታምር ብለው ይስሙኝ ጀመር ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ ልጄን ከአጉል ሱስ አወጣሽልኝ የጠፋውን ልጄን መለስሽልኝ እደጊልኝ አሉኝ አይናቸው የደስታ እምባ አቅርሮ... እኔ በሱ ምክንያት ህይወቴ ተመሰቃቅሎ እናቴ በኔ ሀሌም ታዝናለች ልኡሌ ደግሞ በኔ ተለውጧል ግን እንዴት ቢያፈቅረኝ ኖሮ ሌላ ሴት እንዳለው አይደብቀኝም ነበር ይሄን ያህል ግዜም አይጠፋም ነበር... ወደኋላ ተመልሼ ሳስብ እንባዬ ይምዘብ ጀመር ከዛም እናትና ልጅ በቆሙበት ትቻቸው ሮጥኩ..... ✎ ክፍል ስድስት ከ100Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share @offical_gamine ፍቅር እኔ እና አንቺ❣ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
نمایش همه...
​​ፈ ተ ና ዬ🌺 ❣ :¨·...............:¨·.❣ ♥️ ክፍል 4 ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ከደቂቃዎች ቡሃላ እራሴን አንዲት ጠበብ ያለች ቤት ውስጥ ልብሴ በውሃ በስብሶ አገኘሁት ወድያው ያቺን እርጉዝ ሴት አየሁ ይሄኔ ነቃሽ ብላ ወደኔ ተጠጋች ፈራኋት ምን ልትለኝ ይሆን ስል አሰብኩ.... አይዞሽ አለችኝ ይሄኔ ነበር ቅድም ያለችው ትዝ ያለኝ መናገር ተሳነኝ እንባዬ እየወረደ አንደበቴን አሰረው ቆይ ልኡል ምንሽ ነው አለችኝ ከዛም ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ልብሴን እየጨመኩ ምኔም አልኳት እኔ እንደዛ ያልኳት ምክንያት አለኝ... አባቴ እናቴን በፍቅር አማሎ እንድታፈቅረው ካደረጋት ቡሃላ እናቴ በሱ ሙሉ ለሙሉ ተማምና ነበር እኔን ያርገዘችለት ሆኖም የኋላኋላ ሌላ ልጅና የሞቀ ትዳር እንዳለው ሰማች እናም እናቴ ሁሌም እራሷን ከሱ ሸሽጋ የሱን ትዳር ላለመበጥበጥ አባቴን ሳላውቀው አደኩ ... ለዛም ነው ልኡሌ ምኔም አይደለም ያልኩት ለዛም ነው እያፈቀርኩት ዋሸኝ ያላልኩት ልጅቷም ከብዙ ዝምታ ቡሃላ በቃ መሸብሽ ሂጂ እራስሽን ስትስቺ ደንግጬ ነው እቤቴ ያስገባሁሽ አለችኝ እኔም ደና እደሪ እንኳ ሳልል ወጥቼ ሄድኩ ... ወጥቼ መንገድ ላይ ስሄድ እቃ የጠፋብኝ እመስል ነበር በቀኝና በግራ እንዲሁም ወደኋላዬ እየዞርኩ ትላንት ተስፋ የሰጠኝን ናቲን ማግኘት ፈልጌአለው ልክ ትላንት እጄን የያዘኝ ቦታ ስደርስ ቆምኩ ኪዲዬ የሚል ድምፅ ስሰማ በቀጥታ ዞርኩ ናቲ ለመሆኑ ምንም አልተጠራጠርኩም እሱን ሳይ እምባዬ ያለገደብ ይወርድ ጀመር እሩጬ ተጠመጠምኩበት እሱም አቀፎ አባበለኝና ያረጋጋኝ ጀመር ... ከቆጨይታ ቡሃላ ምን ትፈልጊያለሽ አለኝ እንባዬን እየጠራረኩ እራሴን መርሳት እፈልጋለሁ አልኩት ኮስተር ብሎ አልገባኝም አለኝ በቃ መጠጣት እፈልጋለው ከቻልክ ቀውጢ ቤት ውሰደኝ አልኩት እሱ ግን አመነታ የኔ ቆንጆ ይሄ አይጠቅምሽም ገናኮ 18 እንኳ አልሞላሽም ተረጋጊ እንጂ አለኝ ይሄኔ ከከዳኝ ልኡል በላይ እሱ አበሳጨኝ ሁለተኛ እንዳትከተለኝ ሌላ ፍላጎቴን የሚያሟላ አላጣም ብዬ ትቼው ስሄድ እሩጦ ያዘኝና ... እሺ እንዳልሽ አለኝ ይሄኔ ደስ ብሎኝ ፈገግ አልኩ... እኔ በሀሳቤ ልኡልንና ያረገዘችውን ሴት እያሰብኩ ፒያሳ አካባቢ የሚገኝ ባር ውስጥ ተቀመጥን ቤቱ ውስጥ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ተከፍቷል ሰው እየተነሳ ይወዛወዛል እኔም ከልኡሌ ጋር ያሳለፍኩትን እያሰብኩ በትዝታ እዋኛለሁ ናቲም በሀሳብ ተውጧል በመሀላችን እረጅም ሰአት ዝምታ ሰፈነ ... ይሄኔ ሳላስበው ታውቂያለሽ እኔ የማፈቅራት ልጅ ነበረች ያየሁሽ ቀን ለፍቅር ስታለቅሺ እሷን ነበር የመሰልሽኝ በጣም ታፈቅረኝ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ድንገት ቤተሰቦቿ ለማታውቀው ሰው ድረው እንግሊዝ ሀገር ላኳት አለ የሆነ የሀዘን ድባብ ፊቱ ላይ ይታያል አሳዘነኝ... ቆይቶ ትዝ የሚለኝ ሁለታችንም ስሜታችንን ለመርሳት ስንጨፍር ነበር ከዛ የሆነውን አላስታውስም ስነቃ እንደ አንድ ሰው ተጣብቀን ተኝተናል በድንጋጤ አላበኝ...... ✎ ክፍል አምስት ከ120 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ •●◉Join us share ••●◉ @offical_gamine ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
نمایش همه...
ክፍል ሶስት ነገ ይቀጥላል