cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

(Hamid Al_ashariy

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ @Sodrudin

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
738
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አንድ ሙስሊም "በፊቅህ በኩል ሐነፍይ ነኝ! ወይም ማሊኪ ነኝ! ወይም ሻፍዒ ነኝ! አልያም ሐንበሊ ነኝ!" ሲል እስልምናን ከፋፈልክ ወይም አዲስ ነገር አመጣህ እንደማይባለው ሁሉ በዓቂዳም በኩል አሽዓሪ ነኝ ወይም ማቱሪዲ ነኝ ብሎ ቢናገር አዲስ ነገር አመጣ አይባልም። በፊቅህ አራቱን መዝሃብ የምንከተለው የአራቱም ኢማሞች የመረዳትና የማስተማር ስልት ከትክክለኛው የነብዩﷺ አስተምህሮ ምንጭ የተቀዳ መሆኑ ስለተረጋገጠ እንጂ አራቱም በስያሜ ደረጃ በረሱል ጊዜ ኖረው አይደለም።ሐነፊ፣ማሊኪ፣ሻፊዒ፣ሐንበሊ ይሉት ስያሜ ነብዩም ሱሐቦችም አያውቁትም። በሌላ አነጋገር ስያሜው ቢድዓ ነው😊 በረሱል ጊዜ "አሽዓርይና ማቱሪዲይ የሚባል ነገር አልነበረም?" በማለት ሊሞግት የተነሳ ሰው አራቱ የፊቅህ መዝሃቦች የሚባሉትም በረሱል ጊዜ እንዳልነበሩ ካላወቀ ክርክሩ ሁሉ ውኃ ቅዳ ውኋመልስ ብቻ ይሆናል።ፋይዳ ቢስ ነገር! አስተምህሮው አንድ ሆኖ የመምህሩ የመረዳትና የማስተማር ስልት ሲለያይ የተለያዬ ስያሜ ሊፈጠር ይችላል።ስለዚህ ዋናው ጉዳይ መሠረቱ እንጂ ስያሜው አይደለም።ስያሜ የሚጎዳው መሠረቱን ሲለቅ ብቻ ነው።ለምሳሌ እንደ ቀደሪያ፣ሐሸዊያ፣ሙርጂአ፣ሙሸቢሃ፣ ሙጀሲማና የመሳሰሉት። እነዚህ ቢድኖች ምንም እንኳ በቃል"በኢስላም ጥላ ስር ነን"በሚል ቢሞግቱም አስተምህሯቸው ሲፈተሽ ግን ከኢስላም ጋር የሚጻረር ሆኖ በመገኘቱ ኢስላምም ታላላቅ ዑለሞችም አውግዘዋቸዋል። ውግዘቱ በዋናነት መሰረታቸው ላይ ያነጣጠረ ነበር!! ስለሆነም ከአራቱ ኢማሞች አንዱን መርጠን ስንከተል በፊቅህ በኩል ጠንካራ መሰረት ላይ መሆናችንን እንደሚያመለክተው ሁሉ በዓቂዳም አሽዓሪ ማቱሪዲ ነን ስንል የዓቂዳ መሠረታችን ከትክክለኛው የረሱል ﷺ አስተምህሮ ምንጭ የተቀዳ ነው ማለታችን ነው።ለዚያም ነው በወርቃማው የኢስላም ታሪክ ስማቸው የገነኑ ታላላቅ ዑለሞች ስለራሳቸው ሲጽፉ ስማቸውን ከጠቀሱ በኋላ በፊቅህ አንዱን በዓቂዳ ደግሞ አንዱን መርጠው የሚያስቀምጡት።ለምሳሌ ኢማም አልገዛሊን ብንወስድ በፊቅህ ሻፊዒ፣በዓቂዳ አሽዓሪ ነኝ ይላሉ። በሃገራችን የነበሩ ታላላቅ ቀደምት መሻይኾቻችንም በዚህ መንገድ የተጓዙ ነበሩ።አሏህ ያስረዳን! ኢስነይን🌴 ✦✦✦ http://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
ያኔ ገና ይህ እስልምና ምድርን ሳይሞላ ከ መካ ሳይወጣ ብሎም ከ 1 ጎሳ እንኳን ሳይሻገር በፊት፤ የመካ ቁረይሾች በኑ ሃሽም ላይ አድማ ያደረጉ ጊዜ ከነሱ ጋር ላይገበያዩ ምንም አይነት social ትስስር ላያደርጉ በወሰኑ ጊዜ እና በኒ ሃሽሞች ሳር እስከመብላት የተራቡበትን ታሪክ አስታወሳቹት? ያኔ በ ጃሂሊያ አስተሳሰባቸው እስላምን ባልተቀበለ በ ጣዖታት አምልኮ በጠቆረ ልባቸው እነ ዙሀይር ምን እንዳሉ ትዝ አላቹ? " የመካ ሰዎች ሆይ በኑ ሃሽም እያለቁ እኛ እንበላለን ? እንለብሳለን? ወላሂ እቺ ስምምነት ሳትቀደድ አንቀመጥም" ነበር ያሉት። ያ አላህ ታዲያ ዛሬ ወንድሞቻችን ሲገደሉ ሲራቡ እያየን የ ዙሀይር ጃሂሊያ ከኛ ስልጣኔ እንዴት በለጠ? እንዴት No ማለት አቃተን? ይህ ዲን አስተሳስሮን አልነበር ምን ከፋፈለን? ወንድሞቻችን እየተራቡ አንበላም ማለት ባንችል እንዴት ቀልድ እና ያልረባ የመንደር ወሬያችንን አላቆምንም? ህመማቸው ለምን አልተሰማንም? ለምን ልባችን አልደማም? ለ ተበዳይ አላህ አለው ለ ቀልባችን መድረቅ ግን እንፍራ💔 #freee_plastine
نمایش همه...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ኢስተዋ! ✦✦✦ ኢስተዋ" ይህ ቃል ቁርአን ላይ በተለያዩ አንቀጾች ውስጥ ሰፍሮ እናገኘዋለን። ለምሳሌ አል‐ቀሶስ 18 አል‐ፈትህ 29 ሁድ 44 ጧሃ 5 ✦✦✦ ወደ ማብራሪያው ከመግባታችን በፊት ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ በቋንቋችን አንድ አጠር ያለ ምሳሌ እንጥቀስ ለምሳሌ 1 አህመድ ዳቦውን በላው። 2 እሳቱ ልብሱን በላው ። 3 ጎርፉ ልጁን በላው። ከሶስቱም አረፍተ ነገር ላይ የገባው "በላው"የሚለው ቃል ሶስቱም ላይ የተለያዬ ፍች ይዞ መጥቷል።ቃሉ አንድ ነው ነገር ግን ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት የተለያዬ ነው።በመሆኑም መጀመሪያው ላይ "ተመገበው" ሁለተኛው ላይ "አቃጠለው" ሦስተኛው ላይ ደግሞ "ወሰደው" የሚል ፍች ይኖረዋል።በተቃራኒው ወይም ሶስቱም ተመሳሳይ ፍች አላቸው ብሎ ለመከራከር የሚሞክር አንድ ሰው ቋንቋውን በሚያውቁ ሰዎች ዘንድ አላዋቂ ተደርጎ ከመቆጠር ውጭ ሌላ አማራጭ አያገኝም። ኢስተዋም ልክ እንዲሁ ነው። . አልቀሶስ 18 ላይ ያለው "ኢስተዋ" የነብዩ ሙሳ አካላዊ ጥንካሬያቸው መሟላቱን ሲገልፅ።ኢስተዋ እዚህ አንቀፅ ላይ "ተሟላ" የሚል ፍች ይኖረዋል። .አልፈትህ 29 ላይ ያለው ደግሞ አዝመራው በአገዳዎቹ ላይ መቆሙን ያብራራል። .ሁድ 44 ላይ የነብዩ ኑሕ መርከብ ጆዳ ተራራ ላይ መደላደሏን ይናገራል። ✦✦✦ ከላይ የተገለጹ አንቀፆች የሚያስረዱን"ኢስተዋ" በየ አረፍተ ነገሩ የተለያዬ አውዳዊ ፍች ያለው መሆኑን ነው።ያ ማለት ልክ አንደ "በላው" ሁሉ ኢስተዋም ከአንድ በላይ ፍቺ ካላቸው ቃላት ይመደባል ማለት ነው።በቁርአንም እንዲህ ያሉት ቃላት ሙተሻቢህ ተብለው ይጠራሉ። ታላላቅ የሰለፍና የኸለፍ ዑለሞች አጠቃላይ ሙተሻቢህ አንቀፆችን በተመለከተ በምን መልኩ መተርጎም እንዳለባቸው ግልፅ መስመር አስቀምጠዋል።
نمایش همه...
4
አይ ወንድሜ! "የሶሒሕ አል‐ቡኻሪ እውቁ ተንታኝ ታላቁ ኢብኑ ሐጀር አል‐ዓስቀላኒይ [ከቁርአን ቀጥሎ እንደ ታላቅ መረጃ ተደርጎ የሚወሰደውን ሶሒሕ አልቡኻሪ የተሰኘውን የሐዲስ ኪታብ ወደ 16 ቅጽ የሚደርስ ትንታኔ ወይም ሸርሕ ያዘጋጁ እጅግ ግሩም ሙሐዲስ ናቸው]፣የርሳቸው ደረሳ አል ሐፊዝ አሰኻዊይ። በተጨማሪም አል ኢማሙ ሱዩጢይ ፣አልሐፊዝ ኢብኑ ዲሕያ፣አል ሐፊዙል ዒራቂይ፣የኢማሙ ነወውይ ሸይኽ አቡ ሻማህ እና እጅግ በርካታ ስለ ቢድዓ ምንነት አብጠርጥረው የሚያውቁ የሐዲስ ሊቃውንት ናቸው " መውሊድ ማክብር ይቻላል"ያሉት እያልኩህ አንተ በየቲክቶኩና ፌስቡኩ የሚለቀቀው ድስኩር ካስደነገጠህ አላገኘኸኝም Man! ሐበሻም ላይ እንዲሁ አሏህን በመፍራትና በዒልማቸው የሚታወቁት ጀማሉዲን አልአንይ፣ዳንዮች፣ሾንክይ፣ጫሎች፣አብሬትይ፣ቃጥባሮች፣ አልከስይ፣የቱን ጠርቼ የቱን ልተው?እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ክንደ ብርቱ ዓሊሞችና የአሏህ ወልዮች ፊቅሁን፣ተፍሲሩን፣ሐዲሱን፣ነሕውን ሶርፉን፣በለጛውን ሳይቀር እንደ ውሃ የጠጡ ታላላቅ መሻይኾቻችን መውሊድን ያከብሩት ነበር ለዛውም ስንት ወጭ አውጥተው እያልኩህ።የዚህ ሁሉ ታላላቅ አጂላእ ተግባር ትተህ የፌስቡክና የቲክቶክ መንደርተኛ መውሊድን ተቃወመ በሚል ግርርር የሚልብህና ከላይ የዘረዘርኩልህ ታላላቆች ሁሉ የተሳሳቱ የቲክቶኩ ደንበኛህ ግን ትክክል ከመሰለህ ባባዬ ወራጅ አለ! ምርጫው ያንተ ነው። እኛ ግን ወዳጄ ታላላቅ መሻይኾቻችንን እንሰማለን። ምክንያቱም ዲኑ የመጣው እንዲህ ሳይዛነፍ በጥንቃቄና በተቅዋ መሆኑን በሚገባ እናውቃለንና! ✦✦✦✦ http://t.me/hamid_al_ashariy http://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
3
Photo unavailableShow in Telegram
🥰 5
ሰይዱና አደም [ዓለይሂሰላም] ወደዚህች አለም የመጡት ጁሙዓ ቀን ሲሆን ከጀነት እንዲወጡ የተደረጉትም ጁሙዓ ቀን ነበር።ደስታም ኃዘንም በአንድ ቀን ዋለ።ሙስሊሞች ዘንድ ጁሙዓ አክብሮት የተሰጠው ግን የተፈጠሩበት ቀን መሆኑን በማሰብ እንጂ እንኳንም ከጀነት ወጡ በሚል ደስታውን ለመግለጽ አይደለም የረሱላችንም በተመሳሳይ! http://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
6
ያኔ ሐበሻዊያን አባቶች ነብዩﷺ ፊት ተገበሩት፤ እነሆ ልጆቻቸውም ተከተሉ!! ✦✦✦ የአሏህ ነብይ ሆይ!ﷺ እንደያኔው ሁሉ ዛሬም ሃበሻ ምድር ላይ ሙስሊሞች የሚሰበሰቡት ለርስዎ ነው። ✦✦✦ ስማኝ ወዳጄ! ሃበሻዊያን ሙስሊሞች እንዲህ አይነቱን ክስተት ዛሬ አይደለም የጀመሩት።ያኔ መልእክተኛው መዲና ላይ በነበሩት ወቅት በተመሳሳይ ተግብረውት ረሱሉሏህ እውቅና የሰጡበት ጉዳይ ነው። ለዚህ ደግሞ የኢማም አሕመድ ሙስነዳቸው እንዲሁም ታላቁን የነቢዩን ኻዲም አነስ ኢብኑ ማሊክን ጠቅሰው የዘገቡት የኢብኑ ሒባን ሶሒሕ ዘገባ ምስክር ነው።ምን ይሄ ብቻ! ታላቁ የሐዲስ ልሂቅ ኢማሙ ነሳኢይ "ሱነኑል ኩብራ"በተሰኘ ኪታባቸው ላይ በአቢ ሰለማ በኩል የተላለፈው የእናታችን አዒሻ የምስክርነት ቃል ከበቂ በላይ ማስረጃ ይሆናል። እናታችን አዒሻ رضي الله عنها እንዲህ አሉ "دخل الحبشة يلعبون فقال لي ياحميراء أتحبين أن تنظري إليهم ؟فقلت نعم ،فقام بالباب وجئته فوضعت ذقني على عاتقه فأسندت وجهي إلى خده ، قالت ومن قولهم يومئذ "أبا القاسم طيبا" "ሐበሾች እየተጫወቱ ገቡ፣ነብዩም "ሑመይራእ ሆይ ልታያቸው ትፈልጊያለሽን" አሉኝ።አዎን አልኳቸው።ከዚያም እሳቸው በሩ ላይ ቆሙ፤እኔም አገጬን አንገታቸው ላይ ፊቴን ወደ ጉንጫቸው አስደግፌ መመልከት ጀመርኩ።ያኔ ታዲያ [ሐበሾቹ] "አበል ቃሲሚጦይይባ" "ደጉ የቃሲም አባት" እያሉ ነበር [የሚያዜሙት]" ✦✦✦ አዎ ወዳጄ! ያኔ ከ1400 አመታት በፊት መዲናዊያን[አንሷሮች] ልባቸውን በኃሴት ሞልተውና እጃቸውን በአክብሮት ከፍ አድርገው ድቤ እየደቡ"ጦለዐልበድሩ ዓለይና" እነሆ ጨረቃው መጣልን "ብለው እንደተቀኙት አይነት ሃበሻዊያንም ረሱሉﷺ ፊትለፊት ቆመው ከወዲያ ወዲህ በፍቅር ተወዛውዘዋል፣ስማቸውንም በአክብሮት ጠርተዋል። መልእክተኛውም ይሁን ብለዋል! ✦✦✦ ይሄው ዛሬም ያኔ ሃበሻዊያን ሙስሊም አባቶች እንዳደረጉት ሁሉ"ልጅ የአባቱን ይወርሳል"ነውና በልጆቻቸው ቀጥሏል። ይሄን መሰል ተግባር እኛ ሃበሻዊያን ሙስሊሞች ከመልእክተኛው የማረጋገጫ ማህተም ያገኘንበት ልዩ መገለጫችን ነው።በመሆኑም ኢንሻአሏህ እስከየውመል ቂያማ ይቀጥላል! ✦✦✦
نمایش همه...
🥰 5 1
የመውሊዱን አቀባበል የመን ላይ ተመልከቱ! ✦✦✦ አቀባበሉ እንዲህ ከሆነ እለቱስ? እንዲህ ያለው ትእይንት የሰይድ ጫሊን ሐድራ ያስተውሰኛል። የዘቡራ ልጅ እንዲህ ብለዋል። "እጅግ ኑሮኑሮ መውሊዱ ቢቀርብ፣ ዓለሙን ኑር ሞላው ተሸርቅ እስተጘርብ፣" ታዲያ "ኑር" ማለት ይሄም አይደል?! ✦✦✦ አዎ ወዳጆቼ ይሄ ትእይንት የራሳቸው የረሱላችንﷺየዱዓ ውጤት ነው። ቡኻሪ በሶሒሕ ዘገባቸው እንዳሰፈሩት የኛ ነብይ ክቡር እጃቸውን ዘርግተው ሦስት ጊዜ እየደጋገሙ ዱዓ አደረጉ። "አሏህ ሆይ በሻምና በየመናችን ላይ በረከትን አድርግ ...... "አሏህ ሆይ በሻምና በየመናችን ላይ በረከትን አድርግ ...... "አሏህ ሆይ በሻምና በየመናችን ላይ በረከትን አድርግ ...... አሉ የኛ ረሱል። ያውና! አሏህ የወዳጁን ዱዓ የመቀበሉ ምልክት።የመኖች ከልጅ እስከ አዋቂ ለረሱላችንﷺመውሊድ አሏህን ማመስገኛ ብሎም የኛ ነብይ ሆይ እንኳንም መጡልን የሚል ፍቅራቸውን መግለጫ እንዲህ ደምቀዋል።መልእክተኛው "ወዳጆቼ ናፈቁኝ ያሉት" ያለ ምክንያት አይደለም።በውዱ ተይዞ በሩቁ የሚንሰፈሰፈው እልፍ አእላፍ ነውና።ውዴታ እስከጀነት።ኢንሻአሏህ! ✦✦✦
نمایش همه...
ሚስት የባሏን የገንዘብ መጠን ለማወቅ መሞከሯ አግባብ አይደለም። ገንዘቡ ትንሽ ከሆነ የባል ቦታ እሷ ዘንድ ይወርዳል።ብዙ ከሆነ ደግሞ የጌጥና አልባሳት ፍላጎቷን ጨምራ ትጠይቃለች።" ሶይዱል-ኻጢር ኢማም አብኑል-ጀውዚይ
نمایش همه...
👍 4🥰 1
2.56 KB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.