cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

😘 £őņķå ❤ ßĥã 😍

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
1 033
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሚያዝያ ፳፩ (21) ቀን። ❤ የዕለቱ ስንክሳር። + + + ❤ በዚች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው። እርስዋ ወደ ተወዳጅ ልጅዋ ስለ ሰው ልጆች ትማልዳለችና ስሟን ለምንጠራ ለእኛ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ስለዚህም በየወሩ ሁሉ መታሰቢያዋን ልናደርግ ይገባል። ልመናዋ በረከቷ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን የከበረ አባት ቡሩታዎስ ዐረፈ። ይህም አባት የአቴና አገር የሆነ ከምሁራን ጥበበኞች አንዱ ነው እርሱም ደግሞ ደራስያን ከሆኑ ከአረጋውያን መምህራን ጋራ የተቆጠረ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስንም ተገኝቶት ስለ ቀናች ሃይማኖት ተከራከረው። የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች ተረድቶ አመነ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እጅ ተጠምቆ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተማረ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ በአቴና አገር ቅስና ሾመው። በታላቂቱ አገር በአቴና የመምህራን አለቃ ከሆነ ዘመደ ላሕም አብሮባ ከተባለ ከከበረ ዲዮናስዮስ ጋራ ተገናኘ። እርሱም የክብር ባለቤት ስለሆነ ጌታ ኢየሱስ ሃይማኖት ብዙ ገለጠለት ከውስጡ ሥውር የሆነበትንም ተረጐመለት እጅግም ዐዋቂ ሆነ። ❤ ይህም አባት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም በዐረፈችበት ቀን ደርሶ በሐዋርያት መካከልም ቆመ በደረሰው ማኅሌትና ዝማሬ ጣዕም ባለው በመሰንቆ በዜማ ድምጽም አጽናናቸው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን መልሶ ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታ ክርስቶስ እምነት አስገባቸው። በተሰጠችውም ጸጋ ነግዶ ታላቅ ትርፍ አስገኘ። ❤ ሐዋርያትም ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በፈለጉ ጊዜ ጌቶቼ ይቅርታ አድርጉልኝ እኔ ለዚች ለከበረች ሹመት አልበቃሁምና የቅስናንም አገልግሎት ልፈጽም አልቻልኩምና ተውኝ ብሎ ማለዳቸው። በዕውቀቱና በሥራው ሰማያዊ ሀብትን ተቀብሎ ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔር ሚያዝያ21 ቀን ሔደ። የአባ ቡሩታዎስ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። + + + ❤ በዚች ዕለት የከበሩ አካርክስ የቅሪይስና የይወራስ መታሰቢቸው ነው በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን በጎ ስም አጠራር ያለው የከበረ አባት የሐዋርያት አምሳል ሃይማኖትን የሚሰብክ የአባ ዕንባቆም መታሰቢያው ነው። ❤ ይህንንም ቅዱስ በአባ ጴጥሮስ ዘመን ይኸውም የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀውና ያስተማረው ነው እስከ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ድረስ እግዚአብሔር ከሩቅ አገር ጠራው ከዚያም የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ከዚህም በኋላ በአባታችን ተክለ ሃይማኖት ወንበር ለመሾም እስከተገባው ደረስ በበጎ ገድል ሁሉ ሊጋደል ጀመረ ከዐሥራ አንዱ መምህራንም ውስጥ ተቈጠረ። ብዙ መከራ ስደትና ድካምን ከተቀበለ በኋላ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ። የአባ ዕንባቆም በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ21 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለብሩታዎስ ዘዘመረ ማዕከለ ሐዋርያት ዘኤፍራታ። በጺሖ ለማርያም ጊዜ ዕረፍታ። ወአመ ፈቀዱ ይሢምዎ ዘኢጲስቆጶስ መዐረገ ፆታ። ኢይክል ይቤ ሢመታተ መንታ። እስመ ኢያብጻሕኩ ለቅስና ሠናየ መልእክታ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሚያዝያ 21። ❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም። ❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
نمایش همه...
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤ ❤ እንኳን ለሰሞነ ሕማማት አራተኛ ለሕጽበተ እግር፣ ለጸሎተ ሐሙስ፣ ለምስጢር ቀን፣ ለሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፣ ለነጻነት ሐሙስና ለአረንጓዴው ሐሙስ በሰላም አደረሰን። ❤ ዕለተ ሐሙስ + + + ❤ የዕለቱ ዜማ፦ ''ሐዋርያቲሁ ከበበ፤ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤ ኮኖሙ አበ ወእመ፤ ወመሀሮሙ ጥበበ"። ትርጉም፦ ሐዋርያቱን ሾመ፤ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤ አባትና እናት ኾናቸው፤ ጥበብንም አስተማራቸው። + + + ❤ ሃሌ ሉያ "ሐፀበ እግረ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ አነኒ ሐፀብኩ እግሪክሙ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ"። ቅዱስ ያሬድ። ❤ ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ 1 ሕጽበተ እግር ይባላል። ❤ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት ጳሳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ ዮሐ 13፤4-15 2 የጸሎት ሐሙስ ይባላል፡፡ ❤ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ ማቴ 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1 3.የምስጢር ቀንም ይባላል፡፡ ❤ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢር አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡ 4.የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ ❤ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ሉቃ 22፤18-20 ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡ 5.የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡ ❤ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አይደላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ ዮሐ.15፤15 ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ ማቴ 26፤17-19 6.አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡ ❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ፡፡ + + + ❤ የዕለቱ ሕጽበተ እግር ምስባክ፦ "ትነዝኀኒ በአዛብ ወእነጽሕ። ተሐፅበኒ ወእምበረድ እጸዓዱ(ወእጻዓዱ)። ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወኃሤተ። "። መዝ50፥7-8። የሚነበበው ወንጌል13፥1-20። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወሠራዕከ ማእደ በቅድሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ። ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ"። መዝ22፥5 ወይም መዝ40፥9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ26፥20-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ነው። መልካም የጸሎተ ሐሙስ በዓልና የሰሞነ ሕማማት ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን። ❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም። ❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

††† እንኩዋን ለታላቁ "ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† +*" ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ "*+ =>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል:: +ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:- ¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር:: +ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ 12ቱን ሐዋርያት መረጠ:: +እሊህም:- 1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን 2.እንድርያስ (ወንድሙ) 3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ 4.ዮሐንስ (ወንድሙ) 5.ፊልዾስ 6.በርተሎሜዎስ 7.ቶማስ 8.ማቴዎስ 9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ 10.ታዴዎስ (ልብድዮስ) 11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና 12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1) +እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር:: +ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28) +ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23) +የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19): እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: (ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው:: +ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጌዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ:: +ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ:: +ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41) +ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12 ተካፈሏት:: +ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ:: +በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ:: +ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን:: ✞ ቅዱስ ያዕቆብ ✞ =>በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱሱ ሐዋርያ አባቱ ዘብዴዎስ: እናቱ ማርያም ባውፍልያ: ትንሽ ወንድሙ ደግሞ ዮሐንስ ወንጌላዊ ይባላል:: +ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን አሳ አጥማጅነቱን ትቶ: ከጌታችን እግር ተምሮ በዓለም ወንጌልን አስፋፍቷል:: (ማር. 1:19) ከሌሎቹ ሐዋርያት በተለየም የእንስሳትን ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበር:: +በመጽሐፍ ቅዱስ በሔሮድስ መገደሉ (ሰማዕትነቱ) የተነገረለት ከ12ቱ ብቸኛው ነው:: ሰማዕት የሆነውም በ44 ዓ/ም : ማለትም ከጌታ ዕርገት 10 ዓመታት በሁዋላ : ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሳይበተኑ ነው:: (ሐዋ. 12:1) =>እግዚአብሔር ከቅዱስ ያዕቆብና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን:: =>ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ከ12ቱ ሐዋርያት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ 3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ ዘመደራ 5.አባ ዸላሞን ፈላሢ 6.አባ ለትጹን የዋህ =>+"+ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው:: የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው:: አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ዼጥሮስን ደግሞ ያዘው:: የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ:: +"+ (ሐዋ. 12:1) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
እናት አለኝ የምታብስ እምባ: ✟ድንግል የዚያን ጊዜ✟ ድንግል 'የዛን ጊዜ /2/ ሐዘንሽ በረታ 'በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅሽ ሲንገገላታ/2/ የግፍ ግፍ ደርሶበት የዛን ጊዜ ተጠማሁ ሲለሽ ለውሻ ያጠጣሽ በወርቅ ጫማሽ/2/ አዝ________________ ሴቶች ሲያባርሩት የዚያን ጊዜ ራርቶ ሆድሽ ለፍጡር በማዘን ወኃ ያጠጣሽ/2/ አዝ________________ ተጠማሁ እያለ የዚያን ጊዜ ሲናገር ልጅሽ ታዲያ እንደምንቻለው ወላድ እጀትሽ/2/ አዝ________________ እንደዚያ ስታለቅሽ የዚያን ጊዜ ሐዘን ሲውጥሽ እነማን ነበሩ ያስተዛዘኑሽ /2/ አዝ________________ ስታለቅሽ በማየት የዚያን ግዜ ራርቶ ልጅሽ ዮሐንስን አጽናኝ እንደልጅ ሠጠሸ /2/
نمایش همه...
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት "*+ =>ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን የተቀበለው በሃገረ ፋርስ (በአሁኗ ኢራን አካባቢ) ነው:: ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት (መሐመዳውያን) መነሳት (7ኛው መቶ ክ/ዘ) ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል:: +ብዙዎቹ የዚያው (የፋርስ) ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ ነበር:: +ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ ቆዾስነትን (እረኝነትን) ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ" አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን (እረኛው) እና 150 የሚያህሉ ልጆቹ (መንጋው) ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል:: +በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ ተወስኖባቸው 151ዱም ተሰውተዋል:: =>አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው ይክፈለን:: =>ሚያዝያ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት (አርማንያዊ) 2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (የስምዖን ማሕበር) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 4.አቡነ ስነ ኢየሱስ 5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም =>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.