cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አድስ መረጃ

👉 እንኳን ወደ (አድስ መረጃ) channel በሰላም መጣችሁ።ለወዳጅ ጓደኛ link ሼር ያድርጉ 🇪🇹 ነፃነት ለህዝባችን ብልጽግና ለሀገራችን 🇪🇹 ⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰ ☕ አድስ ☕ መረጃ ☕ ☕ ☕ ⏰⏰⏰⏰⏰⏰⏰

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
248
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

«የፌደራል መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” ባልደራስ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ማዕከላዊ መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” ሲል አስታወቀ። ፓርቲው የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን ባለበት ጸንቶ እንዲቆይ ያስተላለፈውን ውሳኔንም ነቅፏል። ባልደራስ ይህን ያለው፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ አራት አመራሮቹ ከተፈቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ዛሬ ሐሙስ ጥር 5፤ 2014 በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዋነኛ ትኩረት የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው። ፓርቲው “መንግስት ‘ምዕራፍ አንድ’ ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ፤ ትልቅ አደጋ ያዘለ ነው” ሲል ስጋቱን ገልጿል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል” ያለው ባልደራስ፤ መንግስት “ዘመቻውን ያቆመበትን ምክንያት በተመለከተ በቂ ምላሽ አልሰጠም” ሲል ተችቷል። የፌደራል መንግስቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ “ንቀት እያሳየ ነው” ሲልም ነቅፏል፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ከእስር የተፈቱት አቶ እስክንድር ነጋ፤ መንግስት “እከሌ ወሰን ጋር ሄጄ አቆማለሁ ማለት አይችልም” ሲሉ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩትን የፓርቲያቸውን አቋም አሳውቀዋል። “ብልጽግና ይህን ሊወስን ይችላል። መንግስት ግን እንደመንግስት አማራጭ የለውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የገቡትን ቃለ መሃላ ማስጠበቅ አለባቸው” ሲሉ አቶ እስክንድር አሳስበዋል። @ethiozena24 @ethiozena24
نمایش همه...
የከረዩ አባገዳ በአሸባሪው ሸኔ ተገደሉ‼️ የከረዩ አባገዳ ከድር ሀዋስ ቦሩ በአሸባሪው ሸኔ መገደላቸውን የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡ በከረዩ አባገዳ ላይ በአሸባሪው ሸኔ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡ ሸኔ በየጊዜው በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ግድያ አሸባሪው ቡድኑ ህዝባዊ ዓላማ እንደሌለው ማረጋገጫ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል፡፡
نمایش همه...
በደብረ ብርሃን በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ጅምላ ጨራሽ ቦምብና ድምፅ አልባ መሳሪያን ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ❗️ በሰሜኑ የኢትዮጲያ ክፍል ባለው ውጊያ የተነሳ ከደሴ ኮምቦልቻ ፣ ወልድያ ፣ አላማጣ፣ ሰቆጣ እና ከሌሎችም አከባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የተጠለሉ ተፈናቃዮች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ ማለፉን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ልማት ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አካሉ ወንድሙ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ። ተፈናቃዮቹ በአስር የመጠለያ ጣቢያዎች እና በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ሃላፊው አንስተዋል ።በአሁን ሰዓት የደብረ ብርሃን ከተማ በኮማንድ ፖስት ዕዝ እየተመራች ትገኛለች ያሉት አቶ አካሉ ከ500 በላይ በጎ ፍቃደኞች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን እንዲለዩ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል ። በዚህ ሂደትም በተሰራው ስራ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ጅምላ ጨራሽ ቦምቦችን ጨምሮ ድምፅ አልባ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል።ከእዚህ ባለፈ በከተማዋ ሰርገው የገቡ ከ15 የማያንሱ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ ማጣራት እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው አቶ አካሉ ወንድሙ በተጨማሪነት ለጣቢያችን ተናግረዋል። በናትናኤል ሀብታሙ @ZHagerEthiopia @ZHagerEthiopiaBOT
نمایش همه...
የWho Scored የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ 11 ይህን ይመስላል።
نمایش همه...
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ በባህር ስር የሚጓዝ ፈጣን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቁ! የአዲሱ ሚሳኤል የውጊያ ጊዜ 5 ደቂቃ መሆኑን ያሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ፍጥነቱም ከድምጽ በ9 እጥፍ የሚበልጥ እንደሆነም ገልፀዋል። ሚሳኤሉ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አስታውቀዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አክለውም፤ ሞስኮ ምዕራባውያን ወደ ዩክሬን የኒኩሌር አረር ተሸካሚ ሚሳዔሎችን ለማስገባት የሚደርጉትን ሂደቶችን በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል። ምዕራባውያን የኬይቭን ወታደራዊ አቅም እና መሰረተ ልማት ማስፋፋታቸውን ከቀጠሉ ግን ሩሲያ ምለሽ ለመልጠት እንደምትገደድም ነው ፕሬዝዳንቱ ያስታወቁት። @kknewses
نمایش همه...
ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ ተላለፈ!! የትምህርት ማህበረሰቡ ለህልውና ዘመቻው ደጀን እንዲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ዝግ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡
نمایش همه...
በኢትዮጲያ አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ ኦሚክሮን እንዳይከሰት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጥንቃቄ ያድርግ ተባለ። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮቪድ-19 ዝርያ 'ኦሚክሮን' አሳሳቢ መሆኑን ማስታወቁን ተከትሎ በኢትዮጵያም እንዳይከሰት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥንቃቄዎች ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ የአዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከደቡብ አፍሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በቦትስዋና፣ በቤልጂየም፣ በሆንግ ኮንግ እና በእስራኤል መገኘቱ ኢንስቲትዩቱ ለብስራት ሬድዮ የላከዉ መረጃ ያሳያል። ኢንስቲትዩት አዲሱ የኮቪድ-19 የኦሚክሮን በኢትዮጲያ እንዳይከሰት እና የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ እያንዳንዱ ግለሰብ ፤ ቤተሰብ ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፤ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ከዚህ በፊት ህብረተሰቡ ያደርገው ከነበረው በበለጠና በተጠናከረ ሁኔታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ማስክን ሁልጊዜና በአግባቡ ማድረግ ፤ የእጅ ንፅህናን መጠበቅ ፣የኮቪድ-19 ክትባቶችን መከተብ፣ አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ እንደሚገባ አሳስቧል ፡፡ በትግስት ላቀዉ @ZHagerEthiopia @ZHagerEthiopiaBOT
نمایش همه...
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ዋናዋናዎቹ! -"የሽግግር መንግሥት ወይም ሌላ ሕገ ወጥ ቅርጽ ያለው መንግሥት እንመሠርታለን ብለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ አካላት ላይ የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ማዘዙን ገልጿል። -በማንኛውም ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ የመከላከያ ሠራዊትን ፣ የፌዴራል ፖሊስን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችንና የመደበኛ ፖሊስን ዩኒፎርሞች፣ የጸጥታ አካላት አባል ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለብሶ መገኘትም ተከልክሏል። -ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ተከልክሏል።
نمایش همه...
ለቀጣይ 3 ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው - የአ/አ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉ ይታወሳል፡፡ አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ " ይህ ያለንበት ወቅት አገርን ከተጋረጠባት የህልዉና አደጋ የማዳን በመሆኑ ውሳኔውን ለቀጣይ ሶስት ወራት ባለበት እንዲጸና ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል። በመሆኑም ከሕዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል። @kknewses
نمایش همه...
#ተጨማሪ‼️ መንግስት ባለፉት 2 ቀናት በተካሄደ ኦፕሬሽን ከፍተኛ የህወሓት ከፍተኛ የጦር አመራሮችን መደምሰሱን ከዚ ቀደም በሰበር ዜና ማሳወቃችን ይታወሳል! የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫ ተደመሰሱ ካላቸው ውስጥ በፌዴራል መንግስት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ይገኙበታል። በመግለጫው ላይ ተደመሱ የተባሉት ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ስም አልተገለፀም። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ይህን ነው ያሉት ፦ እነዚህ አመራሮች በፌዴራል መንግስት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈጉ የነበሩ ከሃዲ ጄነራሎች እና ኮሎኔሎች ናቸው። በተጨማሪ በከሚሴ ግንባር በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ልዩ ኦፕሬሽኖች የጠላትም ግንባር ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከሃዲ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። በዛሬው ዕለት በባቲ ግንባር በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ቀደም ሲል ከነበሩት ጥቃቶች ተርፎ ለዳግም ማጥቃት ተዘጋጅቶ የነበረው የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ኃላ እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት እግር በእግር የወገን ኃይል እየተከተለ እያፀዳው ይገኛል። በሌሎች ግንባሮችም የወገን ጦር በሰነዘረው ከፍተኛ ማጥቃት ጠላት በከፍተኛ ደረጃ እየተመታ ይገኛል። በዚሁ አጋጣሚ የወገንን ክንድ መቋቋም አቅቶት በተናጠል እና በቡድን እየሸሸ የሚገኘውን የጠላት ኃይል ዘረፋ እንዳይፈፅም እና ንብረት እንዳያወድም ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መንግስት ጥብቅ ጥሪ ያቀርባል። እንዳሁም እየሸሸ ያለው ጠላት እጁን እንዲሠጥ የማይሰጥ ከሆነ ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ መንግስት ያስገነዝባል"
نمایش همه...