cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Grace playlist

ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ። መዝሙር 18:3 ሰላም። እንኳን ደህና መጡ። በዚህ channel መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው የተመረጡ ዝማሬዎችን ከነግጥማቸው ታገኛላችሁ። በእነዚህ ዝማሬዎች ጌታን አብረን እናመልካለን። Join my little sister: 👉 @witnessgfx Request a song here 👉 @graceDMbot

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
466
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
መማር_ድንቅ_ዝማሬ_በይደነቅአብ_ጥላሁን_SEP_16_MARSIL_TV_WORLDWIDE.m4a8.78 MB
💙 5
በቆየ ባደረ በደል እንገበገባለሁ አትፈርድም ወይ ወርደህ ወይ እኔ ፈርዳለሁ ይቅርታስ ከማን ዘንድ ነው ምህረትስ የማን ማን ነው የተበደለው በእኔ አለመማር ይቅርታስ ከማን ዘንድ ነው ምህረትስ የማን ማንን ነው የበደልኩት በእኔ አለመማር /2x በዝምታ መቀጣት ቁስልን በማብሰልሰል ወይ በአቤቱታዬ ውረድ ፍረድልኝ ስልህ መች ደረስኩኝ ዛሬ ነኝ ትናንትና ላይ ራሴን እየወጋሁ ከወጉኝ ቦታ ላይ ቂም ጎተተኝ ድኜ ነገን እንዳላይ /2 በዝምታ መቀጣት ቁስልን በማብሰልሰል ወይ በአቤቱታዬ ውረድ ፍረድልኝ ስልህ እለምናለሁ ፍርድ ያልተገማደለ ማመርህ ባያድን ፍድርህ በገደለ እለምናለሁ ፍርድ ያልተገማደለ ማመርህ ባይመጣ ፍርድህ በገደለ “ሰው በበደል ጊዜ ይቅር ማለት የማይችለው ለራሱ ካለው ልክ የሌለው ፍቅር የተነሳ ነው። በጣም ራሱን የሚወድ ሰው ይቅርታን መስጠትም መቀበልም ይከብደዋል።” መማር … ምንድነው መማር ከይቅርታ ደክሜአለው ማለቴ በዝቶ እኮ ነው የኔ መገፋቴ ሰባ ጊዜ ሰባት አይሆንልኝም የወጋኝን ጦር አይነቅልልኝም ሰባ ጊዜ ሰባት ሺህ ቁስልን አይሽርም ሺህ ሞት የሞተ ሰባ ጊዜ ችሎ አይምርም እላለሁ እኮ መማር መማር ምንድነው? መማር … ምንድነው መማር በላይ ያለኸው አንተ ለገፊ ማዘንህ ይቅር በሉ የምትለን የተገፋነውን እኮ ማን ነው አሁን ጠበቃችን ለኛ ለካ ይህ አይደለም ይቅርታ ቢገባን የተገፋን ገፍቶ ያውቃል አንድ ቀን ምንጠራው ፍርድ ቢመጣ እኛንም አይለቀን እኛ ካልተማማርን ምሕረቱ አይወርድም ያልማረን ንሰሐ እሱኮ አይወድም እውነት ነው እኮ መማር ግድ ነው ጌታ በመስቀል ላይ ስም እየተሰጠው እየተተፋበት ምንድነው የወጣው ባሳዳጁ ላይ ሳይሆን ለአሳዳጁ ጮኸ እኛስ ምን እንማር? እስኪያድር ምን አቆየን እየወጉን ሳለ ነው መማር ባሳዳጁ ላይ ሳይሆን ለአሳዳጁ ጮኸ እኛስ ምን እንማር? እስኪሽር ምን አቆየን እየቆሰልን ሳለ ነው መማር ይቅር አላልኩም ግን ባክህ ይቅር በለኝ አምሳ እጅ አልተውኩም ሺህ እጅ ተውልኝ ይቅር አልልም ግን ባክህ ይቅር በለኝ አምሳ እጅ አልተውም ሺህ እጅ ተውልኝ በድሎ ከማያውቅ ታላቁ ተበዳይ ይቅርታን ብንማር እያስታመምን ሳይሆን እየወጉን ሳለ ነው መማር በድሎ ከማያውቅ ታላቁ ተበዳይ ምሕረትን ብንማር ስለሻረልን ሳይሆን እየወጉን ሳለ ነው መማር መማር እንዲህ ነው መማር መማር //Watch on YouTube// 🎤 ይደነቅአብ ጥላሁን | Yidenekab Tilahun 🎧 መማር | Memar @grace_playlist
نمایش همه...
አንተ በዙፋንህ ላይ ነህ ጌታ ልገዛልህ ልዑል ልስገድልህ ባይ'ገባኝን እንኳ እንደ ህጉ እኔ ግን እገባለሁኝ በፊቱ ንጉስ ይረዳዋል ጥያቄዬን ይመልስልኛል የመሻቴን 3X ብዬ በእምነት እኔ ባደረኩት ጠራኸን ፍቅርህን እጅግ ወደድኩት የወርቅ በትር ተዘርግቶ አስገባኝ ወደ ፊትህ ጎትቶ ምን ትፈልጊያለሽ ተባለልኝ እኔም እንደ ሰዎች ወግ ደረሰኝ 3X ገባሁኝ የልቤን አጫወትኩህ ወደድከኝ ወደድኩህ ተጠጋሁህ 3X ዛሬም በዙፋንህ ላይ ነህ 3X ጌታ ልገዛልህ ልዑል ልስገድልህ ጌታ ልገዛልህ ልዑል ልስገድልህ ታሪኬን የለዋወጥከው ኑሮዬን እንዲህ ያስዋብከው ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህ እና ይብዛልህ አሁንም ምስጋና 6X ያልተገባኝ ሆኜ ሳለሁኝ በአንተ ሞገስ አገኘሁኝ ከፊትህ አልጣልኸኝም እና ምሕረትህ በእኔ ላይ ጸና ከፊትህ አልጣልኸኝም እና ምሕረትህ በእኔ ላይ ጸና ታሪኬን የለዋወጥከው ኑሮዬን እንዲህ ያስዋብከው ኤልሻዳይ ለዘላለም ነህ እና ይብዛልህ አሁንም ምስጋና 6X የህግ መምህር በወሰንከው ስፍራ በምድረበዳ ሸለቆ ተራራ ለበረከት ወደኸኝ ስትጠራ አገኘሁኝ መንገድ ለሕይወቴ ለጥቅሜ ነው ለደህንነቴ ደስ አለኝ በአንተ መጠራቴ የሰው መንገድ ከራሱ አይደለም አካሄድ በምኞቱ አይቀናም ሁሉን አንተ ታዘጋጃለህ ለድሃው በቅን ትፈርዳለህ በመረጥከው መንገድ አስተምረህ በመልካም ታሳድረዋለህ ዘሩ ደግሞ ምድርን ይወርሳል እግሩን ከወጥመድ ሁሉ ያመልጣል። //Watch on Youtube// 🎤 Wendimayehu W/G and Mihret W/G 🎧 ታሪኬን የለዋወጥከው | Tariken Yelwawetkew 📝 ወንድማየሁ & የልቤደሳለኝ @grace_playlist
نمایش همه...
نمایش همه...
ታሪኬን_የለዋወጥከው_Tariken_Yelewawetkew_mihret_and_Wendmayehu_New_.m4a8.01 MB
💙 3
ጽድቅን እንዲያወራ ምላሴ እንድትረካ እንድታርፍ ነፍሴ የዋጀኸኝ አምላኬ መድኅኔ ከዚህች ዓለም አመፃ ኩነኔ እንዳይረክስ በከንቱ ከንፈሬ እንዳልጥለው ውድ እንቁውን ክብሬ ዘመኔን በእጆችህ ያዝክና አራመድኸኝ በህይወት ጎዳና ተመስገን /3 ልበልህ ደግሜ ከኃጢአት በሽታ ተፈውሼ በአንተ ታክሜ እንድረዳው ማዳንህን እንዳውቀው ልቦናዬን ወደ አንተ የመለስከው እንዳያልፈኝ የህይወቴ መና ህሊናዬን ለቃልህ አቀናህ በረከሰው ዓለም የቀደስኸኝ በጽድቅ መንገድ ላይ የመራኸኝ ከብዙዎች እኔ ተለይቼ ዘምራለሁ መቅደስህ ገብቼ ተመስገን… አልመኝም ከእንግዲህ ወደ ውጪ ረክቻለሁ ጌታ አንተን መርጬ የዓለምን ከንቱነት ኮተቷ ንቄዋለሁ ከነማንነቷ ወስኛለሁ ልኖር አስከብሬህ ላፈራልህ ጣፋጭ መልካም ፍሬ ደስ እንዲልህ ሁሌ በኔ ጌታ እገዛለሁ ፈቅጄ በደስታ ተመስገን… ላመግንህ ዕድል ስላገኘሁ በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ ከፍ ላደርግህ መቅደስህ ልግባና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ምስጋና ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን ውዴ ተመስገን ተመስገን አንተ ተመስገን ተመስገን ዘላለም ተመስገን አሃሃሃ በእውነት እንደዳነ በህይወት እንዳለ ሰው አሃሃሃ እስኪ በጎነትህን አሃሃሃ እኔም ልዘምረው /2 አሃሃሃ ለሰው ሁሉ ልንገር አሃሃሃ ማዳንህን ላውራ አሃሃሃ ሆኜ በብርሃን አሃሃሃ ቆሜ በተራራ /2 ተመስገን… //Watch on YouTube// 🎧 Temesgen | ተመስገን 🎤 Azeb Hailu | አዜብ ኃይሉ @grace_playlist
نمایش همه...
نمایش همه...
Temesgen_by_Azeb_Hailu_with_Kingdom_Sound_ተመስገን_አዜብ_ሀይሉ_Live.m4a9.59 MB
💙 7
نمایش همه...
አመልክሃለው_Yezeru_Misale_Saron_Shelemew_and_Daniel_Tadesse_Dada.m4a8.72 MB
አመልክሃለሁ ጅማሬ የለህም አመልክሃለሁ አልፋና ኦሜጋ አመልክሃለሁ ዘመናትህ ብዙ አመልክሃለሁ የለህም መለኪያ አመልክሃለው ቅዱስ ቅዱስ ያለህና ምትኖር ኃያል አምላክ ይገባሃል ክብር በዙፋንህ ለዘላለም ነግሰህ ትኖራለህ አምረህና ደምቀህ ውበትህ እጅግ ያማረ ነው ማንም አይመስልህም ኃይልህ የላቀ ነው ዙፋንህ የፀና ሀይልህ የዘላለም የሚወዳደርህ የሚመስልህ ማነው ሰማይን ምድርን በክብርህ ሞልተሃል እግዚአብሔር ክብር ይገባሃል //Watch on YouTube// 🎧 Amelkhalehu | አመልክሃለሁ 🎙 yezerumisale | የዘሩ ምሳሌ @grace_playlist
نمایش همه...
Merry Christmas Everyone. "አምላክ ስጋ ሆነ ለኛ ማለደ ከአብ አስታረቀን ስርየት ወረደ" ✨ መልካም በዓል! ✨ @grace_playlist
نمایش همه...
ነፍሴ ሆይ አስቢ ያደረገልሽን እግዚአብሔር ከጥፋት ከልሎ እዚህ ያደረሰሽን ሆኖሽ ቅጥር ከደዌሽ በሙሉ የፈወሰሽ በጭንቅ ሰዓት የደረሰልሽ ጎልማሳነትሽን እንደ ነስር ጉልበት የሚያድሰው ምኞትሽን ከበጎ ነገር የሚያረካ እግዚአብሔር ነው ህይወትሽን ያዳነ ከጥፋት መንገድ ከፊት ለፊትሽ ቀድሞ የሚሄድ የውስጥ ሰውነቴ ቅዱስ ስሙን በቀንም በማታ አክብሩት እርሱን እግዚአብሔር መሐሪ ይቅር ባይ ነውና ነፍሴ ሆይ እያሰብሽ አቅርቢ ምስጋና ኦ ነፍሴ እባክሽ ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ኦ ነፍሴ እባክሽ ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ለቁጣው የዘገየ ፍቅሩም የበዛ አምላክ ነውና ለሚፈሩት ሁሉ የምህረት አምላክ ነው የእንደገና ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ መጠን ከአንቺ አስወገደው `ሚያስጨንቅሽን እንደ ሚራራ አባት ለውድ ልጆቹ ዘወትር የያዘሽ በሰፊው እጆቹ ነፍሴ ሆይ አስቢ ታላቅ ውለታውን ሁልጊዜ አፍልቂ ለርሱ ሚገባውን ኦ ነፍሴ እባክሽ ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው ኦ ነፍሴ እባክሽ ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ ርህራሄው እጅግ ብዙ ነው በበረሀው ምድር ምንም በሌለበት ለጥምሽ እርካታ ለድካምሽ እረፍት ከጠላት ፍላጻ ከቀስተኛም ትኩረት ከለላ የሆነልሽ ካንቺ ፍቅር ይዞት በለመለመው መስክ ዘውትር እየመራሽ በጠላትሽም ፊት በዘይት የቀባሽ እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ምህረቱን ያበዛልሽ እግዚአብሔር ነው እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ቸርነቱን ያበዛልሽ እግዚአብሔር ነው ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ 🎤 ዳዊት ጌታቸው | Dawit Getachew 🎧 ነፍሴ ሆይ | Oh My Soul //Watch on Youtube// @Grace_playlist
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.