cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ahlu Al Qur'an

ኡማውን በዲኑ እውቀት ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው የአቅማቸንን ያህል ለማገዝ ጥረት የምናደርግበት ቻናል ነው!!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
535
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
نمایش همه...
Ustaz abubeker ahmed/ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ሙሉ ቪዲዮ: የነጃሺ መስጅድ እና አወልያ ህንጻ በሙስሊሞች ሊግ ጸሃፊ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ / Harun Media

https://youtube.com/watch?v=YaYO2d6BM5Y&feature=share

نمایش همه...
ወንድማማችነትን ለማጠንከር ክፍል 3 በኡስታዝ / ዓብዱራህማን ሱልጧን

አሰላሙዓለይኩምወረህመቱሏህ ወበረካቱህ ቢስሚላህ !! በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ ተሳትፈዋል :: ከላላ ሮቢት መንደር ከ 100 በላይ ደረሳ ለ 18 አመት ያህል እያቀሩ ይገኛሉ :: ሸህ ሙሀመድ አህመድ ሙህዮ ይባላሉ ርጋታቸውና ስክነታቸው ወረዕ የተላበሱ ታላቅ ዓሊም መሆናቸውን ይናገራል :: ሸኽየው ብዙ ደረሳዎችን ለሸኽነት መርቀው በየቦታው ዒልም እያወረሱ ይገኛል :: ከነዚህ መሀከል ሸይኽ ሙራድ ተማም መተሀራ ሸይኽ አህመድ ቁንቢ በአርሲ እያቀሩ ይገኛሉ :: ምንኛ መታደል ነው !!:: እኒህና ወደፊትም የማስተዋውቃችሁ ታላላቅ ዓሊሞች የሚመሩት የዑለማእ ጉባኤ ነው የተዋቀረው ::
نمایش همه...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዑማ ሆቴል ባካሄደው አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባዔዉን አጠናቋል። በግንቦት 19 ቀን 2015 የአቋም መግለጫ እኛ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በግንቦት 19 ቀን 2015 በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ የምክክር ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት፥የዑለማ ምክር ቤት እና የክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አባላት በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙ ጉዳዮች ላይ ባደረግነው ምክክር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል። 1.በሸገር ከተማ እየተደረገ ካለው የመስጂድ ፈረሳ ሂደትን አስመልክቶ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በአንዋርና ኑር መስጊዶች ዙሪያ የመስጂድ ፈረሳውን በሚቃወሙ ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ንጹኃን ሙስሊሞች አላህ በሸሂድነት(ሰማዕትነት) እንዲቀበላቸው፥ ለቤተሰባቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን አላህ እንዲሰጣቸው እንማጸነዋለን።በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን በቶሎ መሻርን አላህ እንዲለግሳቸው እንማጸነዋለን። 2.በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአንዋርና ኑር መስጊድ የተፈጠረው ክስተት እንዴት እንደተፈጠረና የደረሰውን ሞትና ጉዳት መንስኤዎች የሚያጣራ ከመንግስትና የእስልምና ጉዳይ ም/ቤት በጋራ ያሉበት ገለልተኛ አጣሪ ቡድን በአስቸኳይ እንዲቋቋም እንጠይቃለን። 3.በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት ምትክ ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ እናሳስባለን። 4.በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገራችን ክልሎች ለእምነት ቦታዎች ተገቢውን ክብርና ጥበቃ እንዲደረግ፥ እንዲሁም ለመስጂዶች ካርታ በመከልከልና ሆነ ብሎ ቢሮክራሲውን በማንዛዛት ሕዝቡን ላማረሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲፈታቸው እናሳስባለን። 5.በሕገ መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸው የእምነት ነጻነትን በመጻረር በሀገራችን አንዳንድ አከባቢዎች በተለይም በጉራጌ ዞን በጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎችን ለይቶ ከትምህርት የማባረር ሂደት በአስቸኳይ እልባት እንዲሰጠበት። መሰል ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም በኢስላም ጠልነት ምክንያት በሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በዘላቂነት የሚያስቀርና ለሃይማኖታዊ መብቶቻችንን የሚጥሱ አካላትን የሚቀጣ ሕግን መንግስት እንዲያወጣ እንጠይቃለን። 6.ሕዝበ ሙስሊሙ ከመሪ ተቋሙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ጎን በመቆም ሃይማኖታዊ መብቶችን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያደርግ ጥሪ እናደርጋለን። 7.የሃይማኖታችንን ክብር ብሎም የአላህ ቤት የሆነውን መስጂድ መድፈርና ማዋረድ እጅግ ዉስጥን የሚያደማ ብሎም ስሜታዊ የሚያደርግ መሆኑን የመንግስት የጸጥታ አካላት በመገንዘብ ወደ ሕብረተሰቡ ከመተኮስ እንዲቆጠቡ እናሳስባለን። 8.ሕዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎቹን ለማስከበር ከመሪ ተቋሙ መጅሊስ ጎን በመቆም በሚያደርገው ህጋዊ ትግል ለራሳቸው የፖለቲካ ፍላጎት ሕዝበ ሙስሊሙን መረማመጃና መጠቀሚያ ሊያደርጉ ከሚችሉ አካላት የማባባስና ግጭትን የማስፋፋት ቅስቀሳና ሴራ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ እናደርጋለን። 9.የሕዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄዎች የምናስከብረው በአንድነትና በመደማመጥ በመቆም ሕዝበ ሙስሊሙ በየእርከኑ ካሉ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤቶች ጎን በመቆም አንድነቱን በማጠናከር ለመብቱ ትግል ስኬት በአንድነት እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን። 10.መንግስት ኢስላም ጠል የሆኑ እና በመንግስት መዋቅር ዉስጥ በተለያዩ እርከኖች ያሉትን አካላት በመገምገም እና በማጥራት ሕዝብንና መንግስትን ሆነ ብለው ለማጋጨትና ሀገራችንን ወደ ለየለት ቀውስ ለመውሰድ እየሰሩ ያሉ አካላትን ፈትሾ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ መዋቅሩን እንዲያጠራ ጥሪ እናደርጋለን። 11.በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ ሕዝበ ሙስሊሙ በንቃትና በስፋት በመሳተፍ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ የሕዝበ ሙስሊሙ ችግሮችን፥ጥያቄዎችንና አጀንዳዎችን በማንሳት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን በፍትሃዊነትና በእኩልነት የምታስተናግድ ሀገር ለመግንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ጥረት እንድናደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ግንቦት 19 ቀን 2015 ፥አዲስ አበባ
نمایش همه...
https://www.facebook.com/1449316828720530/posts/3374120899573437/?sfnsn=mo&mibextid=6aamW6 የኢትዩዺያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ም/ቤት ኦፊሺያል የፌስ ቡክ ገፅ ነዉ ላይክ በማድረግ ይጎብኙ ።
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

https://www.facebook.com/1449316828720530/posts/3374120899573437/?sfnsn=mo&mibextid=6aamW6 የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ም/ቤት ኦፊሺያል የፌስ ቡክ ገፅ ነዉ ላይክ በማድረግ ይጎብኙ ።
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ በወበረካቱሁ ይኽ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። ለምክር ቤቱ የተሻለ ጉዞ የእርሰዎ ከኛ ጋር  መሆን ዋስትናችን ነው። https://t.me/AmharaMejlis
نمایش همه...
18:20
Video unavailableShow in Telegram