cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

✞ገድለ ቅዱሳን✞

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝

نمایش بیشتر
Advertising posts
16 142مشترکین
+224 ساعت
+97 روز
-8030 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید هابه اشتراک گذاشته شدهديناميک بازديد ها
01
Media files
7300Loading...
02
Media files
6981Loading...
03
✞✝✞ ሚያዝያ 18 ✞✝✞ ✞✝✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✝✞ *+" ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ "+* =>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: +ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: +እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: +እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: +በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: ❖ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ ነው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን (3ኛው መቶ ክ/ዘ) ግብፅና ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡ ❖ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው (ከአክስቱ) ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡ በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡ ❖በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡ ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ ቀብሮታል፡፡ =>አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡ =>ሚያዝያ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት 2.አባ ዼጥሮስ ሰማዕት 3.ሰማዕታተ ጠርሴስ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
6661Loading...
04
Media files
1 3220Loading...
05
Media files
10Loading...
06
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት "ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "*+ =>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6) *የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: *ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ በስተእርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: *ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: *የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: *ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ:: *እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: *ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ:: *ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም:: *ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና:: *ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና:: *ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው:: *"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው:: *በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6) *ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያትበኋላ በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት:: *ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች:: =>" አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ/ የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች" 1.ነቢይ 2.ሐዋርያ 3.ሰማዕት 4.ጻድቅ 5.ካሕን 6.ባሕታዊ/ገዳማዊ 7.መጥምቀ መለኮት 8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ) 9.ድንግል 10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ) 11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ) 12.መምሕር ወመገሥጽ 13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ) ❖ጌታችን መድኃኔ ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: ❖ሚያዝያ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ጸዐተ ነፍሱ) 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ (ከ318ቱ ሊቃውንት) 3.ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት 5.አቡነ አቢብ ጻድቅ ወርኃዊ በዓላት 1 ቅዱስ ሚናስ 2 .ቅዱስ ማርቂርቆስ ለእሙ ኢየሉጣ 3 ቅድስት ዕንባ መሪና 4 ቅድስት ክርስጢና 5 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ++"+ ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም. . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው :: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ:: +"+ (ማቴ. 11:7-15) ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖
1 4688Loading...
07
Media files
1 4613Loading...
08
Media files
10Loading...
09
††† እንኳን ለአባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ††† ††† "ዻዻስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም *ዲቁና: *ቅስና: *ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው:: ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር "ሸክም" : "ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም:: ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው:: አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኩዋ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት (ዽዽስና) ሐዋርያዊ አገልግሎት: ከባድም ኃላፊነት ነው:: አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው:: ††† እነዚህም:- *የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: *የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: *የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና *የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው:: እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443 (451) ዓ/ም {ጉባኤ ኬልቄዶን} ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው:: የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች:: በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ መክሲሞስ ነው:: አባ መክሲሞስ የእስክንድርያ (ግብጽ) 15ኛ ፓትርያርክ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ለ15 ዓመታት አገልግሏል:: ቅዱሱ ከልጅነቱ ጀምሮ ምስጢረ ሃይማኖትን የተማረ ሲሆን መናኝ ሰው እንደ ነበርም ይነገርለታል:: በደቀ መዝሙርነትም ለአባ ያሮክላ (13ኛው ሊቀ ዻዻሳት) እና ለአባ ዲዮናስዮስ (14ኛው ሊቀ ዻዻሳት) በትህትና አገልግሏል:: ዲቁናና ቅስና ሹመት ያገኘውም በዚህ ጊዜ ነው:: ፓትርያርክ ሆኖ ከተመረጠ በሁዋላም ምዕመናንን በአፍም : በመጣፍም ብሎ አስተምሯል:: በዚህም መንጋውን ከተኩላ የመጠበቅ ተግባርን ከውኗል:: በተለይ ደግሞ ዓለማቀፍ መናፍቃን የሆኑትን ማኒንና ሳምሳጢን ተዋግቷል:: ትግሉም ተሳክቶ መናፍቃኑ ተወግዘዋል:: ቅዱሱ አባት አባ መክሲሞስ (ማክሲሙስ) ከዚህም የሚበልጥ ብዙ በጐ ሥራ ሠርቶ በበጐ ዕረፍት በዚህች ቀን ዐርፏል:: ††† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ብሎ ለመንጋው የሚራራ እረኛን ይስጠን:: ከቅዱሱ በረከትንም ይክፈለን:: ††† ሚያዝያ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. 20:28) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝✝✝
1 4685Loading...
10
Media files
2 3138Loading...
11
Media files
2 1115Loading...
12
†††  እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ ††† ††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል:: በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል:: ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ 1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::" 2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር:: አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን:: ††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር) 2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ: ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ:: ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" ††† (ይሁዳ. 1:1) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
2 2838Loading...
13
††† እንኳን ለብጹዐን ጻድቃን: ቅዱስ ዞሲማስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ብጹዐን ጻድቃን ††† ††† በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ:: በሃይማኖት ትምሕርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች:- 1.ገነት (በምሥራቅ) 2.ብሔረ ሕያዋን (በሰሜን) 3.ብሔረ ብጹዐን (ብሔረ - አዛፍ - እረፍት) {በደቡብ} 4.የእኛዋ ምድር (ከመሐል) እና 5.ሲዖል (በምዕራብ) ናቸው:: ††† ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን:- *ኃጢአትን የማይሠሩ:: *ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ:: *ሐዘን የሌለባቸው:: *በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው (2 ወንድና አንድ ሴት) ሁለቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው:: ††† ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል:: ††† በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ:: ††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን:: +*" አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ "*+ =>አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ : እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ : ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው አመስግነዋል፡፡ +የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ +በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋል፡፡ +አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ +አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል፡፡ +አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ +ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡ +ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ +አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ +በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ +ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ +ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታህሳስ 9 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ (ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ) =>አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ሃገራችንን ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ሚያዝያ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 3.ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ (ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት) 4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት (ገና በ10 ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ) 5.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) ††† "ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ::" ††† (1ዼጥ. 1:13-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1 92415Loading...
14
Media files
2 6725Loading...
15
Media files
1 8492Loading...
16
=>አምላካችን እግዚአብሔር ለሰማይ ለምድሩ በቅድስናቸው ከከበዱ ወዳጆቹ በረከትን ያድለን::=>ሚያዝያ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን አዳምና ሔዋን (የዕረፍታቸው መታሠቢያ) 2.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት (ልደቱ) 3.አባታችን ቅዱስ ኖኅ (ልደቱ) 4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (የጌታችንን ጐኑን የዳሰሰበት) 5.ቅድስት ማርያም ግብፃዊት (ከኃጢአት ሕይወት ተመልሳ በፍፁም ቅድስናዋ የተመሠከረላት እናት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም 2.እናታችን ሐይከል 3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 4.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 5.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 6.ቅድስት ሰሎሜ 7.አባ አርከ ሥሉስ 8.አባ ጽጌ ድንግል 9.ቅድስት አርሴማ ድንግል =>+"+ እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅን አደረጉ:: የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ:: የአንበሶችን አፍ ዘጉ:: የእሳትን ኃይል አጠፉ:: ከሰይፍ ስለት አመለጡ:: ከድካማቸው በረቱ:: በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ:: የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ:: +"+ (ዕብ. 11:32-35 <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
1 8373Loading...
17
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ): † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ሚያዝያ 6 † =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት እነዚህን ታላላቅ ቅዱሳን ታስባለች:- † ቅድስት ማርያም ግብፃዊት † † በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ። በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት። ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም። የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም። ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሄር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች። በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት። ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ። ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት። ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር። እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች። በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ። ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን  ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት። ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው። በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ። ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት። አመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት። በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ።ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ። ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ። ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል። ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ † በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ሳምንት ለሀዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጉኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም  ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሳትህን አመንኩ አለ። ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት። በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኀኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ ፣በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች ። " አባታችን አዳም " =>አባታችን አዳም የመጀመሪያው ፍጥረት (በኩረ ፍጥረት) ነው:: አባታችን አዳም:- *በኩረ ነቢያት *በኩረ ካኅናት *በኩረ ነገሥትም ነው:: *በርሱ ስሕተት ዓለም ወደ መከራ ቢገባም ወልድን ከዙፋኑ የሳበው የአዳም ንስሃና ፍቅር ነው:: +አባታችን ለ100 ዓመታት የንስሃ ለቅሶን አልቅሷል:: ስለዚህ አባታችን አዳም ቅዱስ ነው:: ከሌሎቹ ቅዱሳን ቢበልጥ እንጂ አያንስም:: +ለአባታችን አዳም የተናገርነው ሁሉ ለእናታችን ሔዋንም ገንዘቧ ነው:: ዛሬ የሁለቱም የዕረፍታቸው መታሠቢያ ነው:: =>አባታችን ቅዱስ ኖሕም ከላሜሕ የተወለደው በዚሁ ቀን ነው::
2 1826Loading...
18
Media files
2 58012Loading...
19
Media files
1 6275Loading...
20
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † † ሚያዝያ ፬† † ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት) † =>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ አራት በዚች ቀን የከበሩ ፊቅጦርና ዳኬዎስ ኤርሞ ሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ሴቶችና ወንዶች ደናግሎች በሰማዕትነት ሞቱ። እሊህም ቅዱሳን በታላቁ ቈስጠንጢኖስና በልጁ ዘመነ መንግስት የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰው ጣዖታትንም ሰብረው አቃጥለው በቦታቸውም አብያተ ክርስቲያናትን ሠርተው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሌሎችም በብዙዎች ቅዱሳን ስም ታቦቱን ሰይመው ነበር። ከሀዲ ዮልያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቆመ የጣዖቱንም ካህናቶች አከበራቸው ብዙዎች ክርስቲያኖችንም አስገደለ። የእሊህ ቅዱሳን ዜናቸው አስቀድሞ በጣዖታት ቤቶች ላይ ያደረጉት ጣዖታትን እንደሰበሩ ሁሉ ተሰማ።ይዘውም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው ብዙ ቀንም ሲሰቅሏቸውና ሲገርፉአቸው ቆዳቸውንም በሾተል ሲነጥቁ ኑረው በኃላም ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ቆረጡ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። =>ሚያዝያ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት= 1.እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ 2.ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ (ጻድቃን ነገሥት) 3.ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው) 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) =>+"+ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: +"+ (ዘፍ. 1:26-31) †ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
1 8097Loading...
21
Media files
1 9765Loading...
22
Media files
1 7205Loading...
23
✝✝✝ እንኩዋን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ጻድቁ ቅዱስ መርቄ "*+ =>ቅዱስ መርቄ በሁለት ዓለም የተሳካለት ደግ ሰው ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው:- +ቅዱሱ በዓለም የሚኖር ታዋቂ ነጋዴ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደ አስቸጋሪ ከሚታዩ የሥራ ዘርፎች አንዱ የንግድ ሥራ ቢሆንም እርሱ ግን "ቅዱሱ ነጋዴ" ለመባል በቅቷል:: +ለዚህም ምክንያቱ 2 ነገሮች ናቸው:- 1.በንግድ ሕይወቱ ማንንም ሳያጭበረብር ከመኖሩ ባለፈ ፍጹም ጸሎትን ጾምንና ምጽዋትን ያዘወትር ነበር:: 2.ለንግድ በተዘዋወረባቸው ሃገራት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ያለማቁዋረጥ የሚሰብክ በመሆኑ በርካቶችን አሳምኖ ሐዋርያዊ ክብርን አግኝቷል:: +ቅዱስ መርቄ በሕይወቱ ይሕንን ከፈጸመ በሁዋላ አንድ አረማዊ ጉዋደኛ ነበረውና : ሐብት ንብረቱን ሰብስቦ "ጌታችን ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለ ለርሱ ስጥልኝ" ብሎ ላከው:: +አረማዊው ጉዋደኛውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ግርማ አግኝቶ ንብረቱን ከእጁ ተቀብሎታል:: +አረማዊውም በዚህ ምክንያት ከ75 ቤተሰቦቹ ጋር አምኖ ተጠምቁዋል:: ቅዱስ መርቄ በርሃ ውስጥ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዳዊት ከሰማይ ወርዶ ዘምሮለታል:: መላዕክት በምስጋና ገንዘውት አንበሶች ቀብረውታል:: =>አምላክ ከቅዱሱ በረከትን ያድለን:: =>ሚያዝያ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም 3.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ 4.እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ =>ወርኀዊ በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5.አቡነ ዜና ማርቆስ 6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል =>+"+ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:14-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
1 8936Loading...
24
Media files
2 1697Loading...
25
Media files
2 0392Loading...
26
†† እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ††† ††† ክርስቶፎሮስ ትርጉሙ "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ መሆኑ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ይጠሩ ነበር:: ከነዚህ አንዱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ሃገሩ በላዕተ ሰብእ (ሰውን የሚበሉ) ውስጥ ነበር:: ይህች ሃገር አሁን የት እንዳለች በውል ባይታወቅም የቅዱስ ማትያስ ሃገረ ስብከት በመሆኗ አውሮፓና እስያ ድንበር አካባቢ እንደሆነች ይገመታል:: የአካባቢው ሰዎች ከሰው ሥጋ ውጪ እህልን አይቀምሱም ነበር:: ቅዱስ ማትያስ በነርሱ ያደረውን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ አሳምኗቸዋል:: ከሃገሩ ሰዎችም አንዳንዱ ገጻተ ከለባት (የውሻ መልክ ያላቸው) ነበሩ:: ክርስቶፎሮስም ከነርሱ አንዱ ነበር:: በክርስቶስ አምኖ ከተጠመቀ በሁዋላ በስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ : ስለ ሃይማኖትም ብዙ ጸዋትወ መከራ ተቀብሎ በዚህች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: ††† ከሰማዕቱ በረከት አምላኩ ያድለን:: ††† ሚያዝያ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ክርስቶፎሮስ (ሐዋርያና ሰማዕት) 2.አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ 3.ቅዱስ መላልኤል (የያሬድ አባት - ከአዳም 5ኛ ትውልድ) 4.እግዚአብሔር ፀሐይን : ጨረቃን : ከዋክብትን ፈጠረ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት 2.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 4.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 5.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 7.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ ††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" ††† (1ቆሮ. 10:14-18) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
2 48710Loading...
27
Media files
2 8276Loading...
✞✝✞ ሚያዝያ 18 ✞✝✞ ✞✝✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✝✞ *+" ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ "+* =>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: +ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: +እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: +እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: +በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: ❖ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ ነው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን (3ኛው መቶ ክ/ዘ) ግብፅና ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡ ❖ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው (ከአክስቱ) ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡ በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡ ❖በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡ ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ ቀብሮታል፡፡ =>አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡ =>ሚያዝያ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት 2.አባ ዼጥሮስ ሰማዕት 3.ሰማዕታተ ጠርሴስ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...