cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

@Sami የፍቅር ጥቅሶች እና ዘፈኖች

@Sami የፍቅር ዘፈኖች ጥቅሶች እና አጫጭር የፍቅር ቪድዮዎች የምገኙበት በተጨማርም ፕራንኮች የምገኙበት ቻይናላችንን ይከታተሉን ችግር ካለ @Samiyecoffee ያናግሩ @Sami የፍቅር ጥቅሶች እና ዘፈኖች @Sami የፍቅር ጥቅሶች እና ዘፈኖች ተዝናኑበት

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
225
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
መልእክት _DagiFish.mp33.03 MB
❤️የእለቱ ምክር❤️ …ሰው ለምን አልወደደኝም ብለን ራሳችንን ማስከፋት የለብንም። የጠላን መልአክ ወይም አምላክ ሳይሆን ልክ እንደኛ አይነት ሰው ነው። ሰው እንዲወደን መለመን እና መታገል የራሳችንን ዋጋ አለማወቅ ይመስለኛል። ስህተታችን ራሳችንን ሳንወድ ሌላ ሰው እንዲወደን መመኘታችን ነው። አስመስለን ከመወደድ ይልቅ ራሳችንን ሆነን መጠላት የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ደሞም እውነት ነው።🙏❤️ 🌟ዝም ብለን የራሳችንን የተለመደ አለም እንኑር🌟ቢያስጠላንም የሰዎችን ህይወት copy አናድርግ። እኛው በመረጥነው መንገድ ከኛው ጋር እንጓዝ። ❤️ትክክለኛ ሰዎች ካሉ እውነተኛ ማንነታችንን ፈልገው ወደኛ ይመጣሉ።🙏 ካልመጡም ቀረንባቸው እንጂ ሚቀርብን ምንም ነገር የለም። 🙌በራሳችን አንደራደር 🙌ለመወደድ አንለምን 🙌ስላልተወደድን አይክፋን 🙌ሁሌም ራሳችንን እንውደድ ለወዳጅ ለጓደኛዎ 💌ሼር💌  ┄┉┉✽̶»̶̥✨🌹✿🌹✨»̶̥✽̶┉┉┄               #ያለው_ፍሰሀ ነኝ  ╔═══❖•✨🌺✨•❖═══╗ #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ            ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️ 🌹✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨🌹 🔱 @Yelib_kuankua 🔱                    ✣🍂የልብ❤️ቋንቋ🍂🌹✣
نمایش همه...
👉ከመሮጥህ በፊት የሚያሯሩጥህን ከማልቀስህ በፊት የሚያስለቅስህን ከመፈለግህ በፊት የምትፈልገውን ከመጨነቅህ በፊት ስለሚያስጨንቅህ ነገር ...... ቆም ብለህ አስብ። ...... ቆም ብለሽ አስቢ፡፡ 👉የሮጥክላቸው ጉዳዮች ሁሉ የማያስሮጡ ፣ ያለቀስክባቸው ነገሮች ሁሉ የማያስለቅሱ ፣ የፈለግካቸው ነገሮች ሁሉ ላያስፈልጉህ ፣ የተጨነክባቸውም ጉዳዮች ሁሉ ላያስጨንቁ ይችላሉ… ሁሉም ነገር ቀላል ሊሆን ይችላል ብቻ ከመድከምህ በፊት #ቆም_ብለህ_ትንሽ_አስብ_አስቢ 🌹▫️🍃SHARE🍃▫️🌹 ⚡️@Yelib_Kuankua⚡️               ✣🍂የልብ❤️ቋንቋ🍂✣
نمایش همه...
​የድሀ ፍቅር ክፍል5⃣ //በእውነተኛ ህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ/ ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ እየጠበቅን ነው ሜላት ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ አኮረፈች ሁሌም ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና ጉንጫን በእጆቼ ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ,. ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ ደንግጠን ዞር ስንል የሜላት አባት መኪና ነበር ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ,ሜላትም እሽ ብላ ቻው ብላኝ ወደ መኪናው ገባች አባቷ እኔን ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ., ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል ነበር ብዬ አሰብኩ ቀኑ አርብ ስለነበር ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን የለኝ ብቻ ጨነቀኝ እቤት ገብቼ ለእናቴ የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ አምላክ ያለው ይሆናል አለችኝ ,እሽ አልኳት በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ ሜላት የለችም ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም.,እሁድም አላገኝኃትም ይበልጥ ጨነቀኝ., ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ ሜላት ግን የለችም ተደውሎ ወደ ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት እንደመጣች ሳላውቅ መጥታ ተጠመጠመችብኝ ከንፈሬን አንገቴን አይኔን ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ አለችኝ ምን ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ለረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ መምህር ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን., የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት የተፈጠረውን እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም ጨንቆኝም ነበር ,መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ ሰአቱን መግፋት ብችል ገፍቼ አሳልፈው ነበር ግን አልቻልኩም ,የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ አይቀር ወጥቼ ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ አለችኝና ቁጭ አልን,. ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ ጋር ከታየች ችግር እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም እንዲጎዱህ ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም ብዬህ የገባሁት ከዚህ በኃላ ከ ትምህርት ቤት ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም ምናልባት ማታ ማታ ቤተክርስቲያን እንገናኛለን አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት ., ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ አውጥታ በዚህ ስልክ እንደዋወል አለችኝ እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ እንደምጎዳ በደንብ ገባኝ ከዝይች ቀን ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ መገናኝት አቆምን ሜላት ማጥናት ትታለች በቃ ከኔጋር ለምዳ ብቻዋን ማጥናት አልቻለችም., የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት ተወጥሪያለው ሜላት ግን ማጥናት ትታ እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ ላስጠናት እንደምችል ግራ ገብቶኛል ,ማታ ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም እንዳላጠናች ነገረችኝ አጥኚ ነገ ከትምህርት መልስ እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ ብላኝ ቻው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ..በድጋሚ ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር,........ ይቀጥላል....... @SAMIDAVIDEFA
نمایش همه...
​🍂🍃 የድሀ ፍቅር 🍃🍂 ክፍል4 //በእውነትኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ.// እኔና ሜላት ፈተና ስለደረሰ ሰናጠና አምሽተን ልሸኛት እንደወጣሁ ካፌ ሻይ ብና እንበል ብላኝ ገብተን ቁጭ እንዳልን ድንገት የሜላት አባት ከፊት ለፊታችን ድቅን አሉብን ... እኔ ሰለማላውቃቸው ዝም አልኩ ሜላት ተርበተበተች ማ..ማነዉ አልኳት ? በጣቶቿ አፏን ተመተመች ዝም በል ለማለት ነበር... ሜላት ከመቀመጫዋ ተነስታ አ...አባቢ አለች እየተርበተበተች ... አባቢ ስትል ቀልቤ ግፍፍ አለ .. ደግነቱ ዩኒፎርሜን ከላይ ያለውን አላወለቅሁትም ነበር። የየየክፍሌ ተማሪ ነው ስናጠና ቆይተን ሻይ ብና እንበል ብለን ነው አለች እየተርበተበተች... አባቷም ሰላምታ አይቀድምም ልጄ አሉ ... ይቅርታ አባቢ ብላ አቅፋ ሳመቻቸው .እኔም ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላም አልኳቸው. የሜላት አባት ሰላም ብለውን በጊዜ ግቢ ቻው ብለውን ሌላ ወንበር ወደ አለው ጏደኛቸው ሄዱ .,እኔና ሜላት ደንግጠናል ያዘዝነው መጥቶልን ቶሎ ቶሎ ጠጣን አባቷ ቀድመው ሂሳብ ከፍለውልን ስለነበር ቻው ብለናቸው ተያይዘን ወጣን.,. ሜላት ፊቷ ላይ የፍረሀት ስሜት ይነበባል ሜላቴ ምን ሆንሽ ምን እያሰብሽ ነው አልኳት። አባቢ... አለች አባትሽ ምን? ኡሁን እቤት ስገባ ጭቅጭቁ አይጣል ነው አለች በፍረሀት። አይቆጡሽም አስጠኒዬ ነው በያቸው ባይሆን ሁለተኛ አብረን እንዳያዬን እንጠነቀቃለን አልኳት እሽ አልችኝና ግንባሯን ለመጀመርያ ጊዜ ስሜ ተለየኃት., ሜላትን በታክሲ ሽኝቼ እኔ ወክ እያደርግሁ ወደ ቤት ተመለስኩ ግን የሜላትዬ ፍርሀት እኔን አሳሰበኝ አባቷ ይቆጡ ይሆን ብዙ ነገሮችን አሰብኩ .ምክንያቱም የሜላት ቤተሰቦች ሀብታም ስለሆኑ ልጃቸው ደግሞ ከእንደኔ አይነት መናጢ ድሀ ጋር የፍቅር ግንኝነት እንዳላት ቢያውቁ ከባድ ነው የሚሆነው... አምላኬ አደራህን ብዬ እቤቴ ገባሁ መንጋት አይቀር ነጋ... ጠዋት ትምህርት ቤት ቶሎ ሄድኩ በሩ ላይ ጠበቅኃት እሷም እንደምጨነቅ ስለገባት በጠዋት መጣችልኝ ደስ አለኝ ቶሎ ብዬ ምን ተፈጠረ አልኳት .,ሰላም በለኝ እንጂ ቅድሚያ አለችኝ አቅፌ ሳምኳት .ምንም አልተፈጠረም አባቢ ምንም አላልኝም አለችኝ በጣም ተደሰትኩ ለሚቀጥለው እንጠነቀቃለን አልኳትና ተያይዘን ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ ገባን,. እኔና ሜላቴ ፍቅራችንን በድብቅ አድርገን መዝናናትም ስንፊልግ ደበቅ ያለ ቦታ እየሄድን እንዝናናለን .አብዛኛውን ጊዜ ግን እኛ ቤት ነው የምናሳልፈው.አመቱ አልቆ ተፈትነን ውጤት መጣ ሁለታችንም አልፈናል ደስ የሚል ነገር ተመስገን አልተነጣጠልንም., ሁለት ወር ክረምትን ያው እንደተለመደው እኔ እናቴን በማገዝ አሳለፍኩ ከሜላትም ጋ አልፎ አልፎ እቤት እየመጣች ካልሆነም ማታ ማታ እነሱ ሰፈር ቤተክርስቲያን ውስጥ እንገናኛለን..በቃ ደስ በሚል መዋደድና መፈቃቀር አብረን ቀጠልን ., አዲሱ አመት ገብቶ ትምህርት ጀመርን 12ኛ ክፍልን በጣም መጠናት እንዳለበት ስለማምን ብዙ ጊዜያችንን በጥናት ነው የምናሳልፈው .ሜላትም ከኔ ጋር ታጠናለች በርትተን መማር እንዳለብን ሁለታችንም እናምናለንና .,ስለዚህ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል እናጠናለን. እኔ ስናጠና ስለ ትምህርት ወክ ስናደርግ ስለ ነገ ተስፋ ነው የማስበው ወደፊት ምን ማድርግ እንዳለብኝና ምን መሆን እንደምችል ብዙ ነገር ሜላትን እንደማገባት ነው የማምነው ,.ሁሌም ስለያት ወይ ግንባሯን ወይ አንገቷ ስር ስሜ እለያታለው.... አንድ ቀን ማታ ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ሜላት ፊቷን ሳይ አኩርፋለች ምነው ሜላትዬ ምን ሆነሽ ነው አልኳት.,ሳመኝ አለችኝ አይናይኔን እያየች ,.እ!! አልኳት ሳመኝኝኝኝ! አልቸኝ ግንባሯን ሳምኳት ,ኡፍ ብላ ተበሳጨች ,ትዝ ሲለኝ እእ....እ ....... ይቀጥላል.... @SAMIDAVIDEFA
نمایش همه...
​#የድሀ_ልጅ_ፍቅር ክፍል 6 በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ እኔና ሜላት በስልክ ስናወራ ቆይተን ነገ ቤተስብን አስፈቅደሽ እናጠናለን ብያት ስልኩ ተዘጋ። ስልኩን እንደዘጋሁት ሌላ ስልክ ተደወለልኝ የማላውቀው ስልክ ነበር ዝም አልኩት። ደግሞ ተደወለልኝ ግራ ገባኝ ከሜላት ውጪ ይሄንን ስልክ ማንም አያውቀውም... በሶስተኛው አነሳሁት በር ላይ ነኝ ውጣ የሚል ጎርናና ድምፅ.. ማን ልበል ስለው ውጣ! ብሎኝ ስልኩን ዘጋው። ደነገጥሁ! ለእናቴ ሳልነግር መጣሁ ብዬ ወደ ውጪ ወጣሁ አንድ ግብዳ ሰውዬ በር ላይ ቆሞ አገኘሁት። አቤት ማን ልበል? አልኩት.. ና! አለኝ ቆጣ ብሎ ተጠጋሁት ስልክህን! አለኝ.. አልሰጥም አልኩት ! አምጣ !! ብሎ ጮኸ ሰጠሁት 'ስማ ከዚህ በኃላ ከሜላት ጋ እንዳላይህ ካየሁህ ግን ከምድርገፀ ነው የማጠፋህ' አለኝ። ወዲያው ከፊት ለፊት የመኪና መብራት በረጅሙ በራ ወደኛ ተጠጋ። የመኪናው መብራት አይኔን እየወጋኝም ቢሆን የግዴን አየሁት... የሜላት ወንድም ነበር መኪናው ውስጥ የነበረው። አጠገቤ የነበረውም ግብዳ አስፈሪ ሰውዬ ካስጠነቀቀኝ በኃላ መኪናው ውስጥ ገብተው ሄዱ። ሜላት የሰጠችኝ ስልክ አዲስ ሴም ነበር ግን ከስልኳ ውስጥ ነበር ስልክ ቁጥሩን የወሰዱት በስልክ እንደምንገናኝና ትምህርት ቤትም አብረን እንደምንውል፣ ቤተክርስትያን እንደምንገናኝም፣ በደንብ ያውቃሉ። ምክንያቱም በቅርብ እርቀት ይከታታሉን ስለነበር። በጣም አዘንኩ ትንሽ በር ላይ ከቆምኩ በኃላ ወደ ቤት ገባሁ ለእናቴ ሁሉንም ነገር ነገርኳት። በቃ ይቺ አመት እስክትጠናቀቅ ድረስ አብራችሁ አትሁኑ አለችኝ ግን እንዴት አድርጌ... አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቤተክርስቲያን ደርሼ ስመጣ የስራ ማስታወቂያ ለማንበብ ጠጋ ብዬ ቆምኩ ድንገት አይኔ ተወርውሮ አንድ ስራ ላይ አረፈ እነ ሜላት ሰፈር ካሴት(cd)ፊልም ማከራየት የወር ደሞዝ 150 ብር ይላል ደስ አለኝ ወዲያው ሄጄ ተነጋገርኩ ስራ ስላልነበረኝ እዛ ተቀጠርኩ። ስልክ ቤት ሄጄ ለሜላት ነገርኳት ደስ አላት ፊልም ለመክራየት እየመጣች እንደምንገናኝ ተነጋገርን። እቤት ሄጄ ለእናቴ ሁሉንም ነገርኳት ግን ክፍያው በቂ አይደለም ጫማ ብጠርግ በቀን ከ150 ብር በላይ አገኛለው ብቻ ትንሽ ጊዜ ልየው ብዬ አሰብኩኝ። እናቴ ደስ ያለህን አድርግ አለችኝ። ስራ ጀመርኩ.. ከሜላትም ጋ መገናኝት ጀመርን ስናፍቃት መጥታ አይታኝ በአይን አውርተን እንለያያለን። እኔም ከቀጠረኝ ሰዉዬጋ ተነጋግሬ በር ላይ ጫማ መጥረግ ጀመርኩ። ታናሽ ወንድሜ ፊልም ማከራየት ጀመረ። እንደምንም ብለን ሁለት ወር ክረምት እየተገፋ ነው እኔም የአቅሜን እየሰራሁ ጫማ እየጠረግሁ ጎን ለጎን የሞባይል ካርድ ማስቲካ ሌሎች ትናንሽ ነገሮችን እየሸጥሁ ነው። እናቴ የሰው ቤት እንጅራ መጋገርና ልብስ ማጠብ ትታ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማስተካከል ትሰራለች። ባለቻት ሰአት ደግሞ ሽንኩርት ቃሪያ ድንች ትቸረችራለች ተመስገን አሁን ነገሮች እየተስተካከሉ ነው። ሁለት ወር ክረምት አለፈ የማትሪክ ውጤት ሊመጣ ነው ውጤቱ ምን እንደሚሆን አይታወቅም ብቻ አሪፍ ውጤት አምጥቼ እንደማልፍ እርግጠኛ ነኝ ከፈጣሪ ጋር !. ሜላቴም እንድታልፍ ፀሎቴ ነው! ብቻ መድረሱ አይቀር የማትሪክ ፈተና መጣ ሲባል እኔም ሜላትም ተያይዘን ውጤት ለመቀበል ሄድን። ውጤትም ተቀበልን ግን ............... ይቀጥላል........... @SAMIDAVIDEFA
نمایش همه...
​​የድሀ ፍቅር Part 3 በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ., እናቴ በክረምት ወራት ሰርታ ያጠራቀመችውን ብር ሰብስባ ዩኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ .ሜላት ቀድማ ዩኒፎርም አሰፍታ አመጣችልኝ ደነገጥሁ ለምን ገዛሽ ?እኔ እንድትረጂኝ አልፈልግም::አልኳት ተቆጥቼ .ሜላትም ፊቷን አዙራ ከቤት ወጣች .ስቆጣ ሰምታኝ የማታውቀው እናቴ ደነገጠች.እኔም ሜላትን ከመከተል ይልቅ ፈዝዤ ቀረሁ,.... ድንገት ታናሽ ወንድሜ ገፍትሮኝ ወደ ውጪ ሲሮጥ ብንን እንደማለት አልኩ .እንደዛው እንደቆምኩ ብዙም ሳልቆይ ታናሼ ምን እንዳላት ባላውቅም ሜላትን ይዟት መጣ .እስኪ ዞር በል እንግባበት,ብሎኝ ይዟት ገብቶ ያለችው መቀመጫ የኔ የበሰበሰች ፈራሽ ላይ ተቀመጭ አላት,. እኔ አሁንም ፈዝዣለው እማዬ ቡና አፍይ እስኪ አላት እናቴ እሽ ብላ ተፍ ተፍ ማለት ጀመረች.አቦ አትቁምብና ና ተቀመጥ!!አለኝ እሽ ብዬ ሜላት ስር ቁጭ አልኩ ለማየት ፈራኃት .እንዳቀረቀርኩ ይቅርታ አድርጊልኝ ሜላት አጥፍቻለው አልኳት ,!አይ ችግር የለውም !!አለችኝ ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ አየኃት .እውነትሽን ነው አልኳት አዎ አልችኝ,.እጆቿን ያዝ አድርጌ ሜላትዬ እውድሻለው አፈቅርሻለው ግን በገንዘብ እንድትረጂኝ ሳይሆን ንፁህ ፍቅርሽን ነው የምፈልገው አልኳት አይናይኗን እያየሁ. እየውልህ የኔ ውብ እኔ እየረዳሁህ አይደለም ማደርግ ስለፈለግሁ እንጂ ደግሞ ካንተና ከእናንተ ቤተሰብ የማገኘው ፍቅር ከሺ ሚልዮን ብር በላይ ደስታን ይሰጣል .አትበሳጭብኝ ይቅርታ እሽ አለችኝ .,ታናሽ ወንድሜ ጣልቃ በመግባት እድሜ ለኔ መለስኩልህ ፈዛዛ ይኸኔ እቤቷ ደርሳ ነበር አለኝ ተሳሳቅን ቡና ተፈላ ቤት ያፈራውን ቀማመስን በቃ ደስተኛ ሆነን አመሽን በጣም ማምሽት ሰለማይፈቀድ ሜላቴንም ወደ ቤቷ ሸኘኃት..... እኔም እሷን ሽኝቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ወደ ቤቴ ተመለስኩ..እናቴም ዩኒፎርም ስለተገዛላት ያለው ብር ለደብተርና እስክርቢቶ ይሆናል ተመስገን አለች.ዞር ብላ አንተ ከዚህ በኃላ እንደዚህ ጮኸህ ስትቆጣ መስማት አልፈልግም አለችኝ.እሽ አልኳት,. ቀናቶች ሄደው የትምህርት መሳሪያዎቼን አሟልቼ ትምህርቴን ጀመርኩ ሜላቴም እኩል ጅመርን አንድ ክፍል መሆን ፈልገን ነበር ግን አልተሳካም መምህሮቹ አልፈቅድ አሉ ይሁን ብለን በክፍል ተለያየን ግን እርፍት ሲሆን እኔ ቀድሜ ቀወጣሁ እነሱ ክፍል በር ላይ እጠብቃታለው እሷም ከቀደመች እንደዛው .ደስ የሚለው ሁላችንም ዩኒፎርም ስለምንለብስ የድሀ የሀብታም ልጅ ብሎ ነገር የለም .የሚበላ ስንፈልግ ሜላት ብር ሰጥታኝ እኔ እከፍላለው ., እኔና ሜላት ተለያይተን አናውቅም እኔም ከእሷ ውጪ እሷም ከእኔ ውጪ ትምህርት ቤት ውስጥ ጏደኛ የለንም.ተማሪዎች ሁሉ ይቀኑብናል .እሷ ቆንጆ ነገር ስለሆነች ሌሎች ይመኟታል እሷ ግን ከኔ ውጪ ማንንም አትፈልግም.,እኔም እንደዛው. ከትምህርት ቤት ውጪ እኔ እናቴን ለማገዝ ስራ ስለምሰራ ብዙም አንገናኝም ጥናት ካለብን ግን አብረን እናጠናለን ጥናት ስንጨርስ ወክ አድርገን እንለያያለን እናቴም አብሮነታችን በጣም አስደስቷታል ደስተኛ ነች እኔም እንደዛው .አንድ ቀን ፈተና ስለደረሰ ስናጠና ቆይተን ልሸኛት ወጥቼ ሻይ ቡና እንበል ብላኝ ካፌ ውስጥ ተቀምጠን ያላሰብነው ሰው ድንገት መጣብን.......................... ይቀጥላል ... @SAMIDAVIDEFA
نمایش همه...
​​"የድሀ ፍቅር" በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,:: ክፍል 1⃣ ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግሁት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ ነው አባቴን አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም እንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል,ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች , እናቴ ያገኝችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች , በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው ከትምህርት ቤት እምደተመለስክ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ,. በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ, እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሀብታሞች,የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለናል, የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን,ሁለት ወር ክረምትን ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው . ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዬ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈልግም እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ,....... ይቀጥላል✍🏻 @SAMIDAVIDEFA
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.