cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

AA Airport Customs branch office /አ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ

ራዕይ፡- "በ2022 በአገራችን ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ተገንብቶ ማየት"

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 272
مشترکین
+224 ساعت
+77 روز
+1430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የዕቃ አስተላላፊዎች ግዴታ ➡️የኢትዮጵያ ማሪታይም ኮሚሽኑ የዕቃ አስተላላፊነት ፍቃድ የሚሰጣቸውን እና ፍቃድ የታገደባቸውን ወይም የተሰረዘባቸውን ዕቃ አስተላላፊዎች ዝርዝር መረጃ በየጊዜው ለኮሚሽኑ ማሳወቅ አለበት፤ ➡️ የዕቃ አስተላላፊው በጉምሩክ ትራንዚት አፈጻጸም ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ የሚያመጣ አደጋ ወይም ያልተጠበቀ ሁኔታ ሲከሰት ወዲያውኑ በአቅራቢያው ለሚገኘው የጉምሩክ ጣቢያ ወይም አግባብ ላለው ሌላ የመንግስት አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- ደንብ ቁጥር 518/2014
نمایش همه...
👍 3
የጉምሩክ አስተላላፊ ግዴታዎች ➡️ የወከለው ደንበኛ የሰጠውን የውክልና ሥልጣን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ ለኮሚሽኑ ወዲያውኑ የማቅረብ፤ ➡️ደንበኛው በሰነዶች ላይ ማንኛውም ስህተት ወይም ግድፈት በመፈጸም ህግን አለማክበሩን ካወቀ ሕግ በሚያዘው መሠረት እንዲፈጽም ደንበኛውን የማማከር እና ስህተቱ እንዲታረም የማድረግ፤ ➡️ የጉምሩክ ሥራን አስመልክቶ ለደበኛው የሚሰጠው መረጃ ትክክለኛነት ላይ የማረጋገጥ፤ ➡️ በጉምሩክ በኩል የሚጠየቀውን ቀረጥና ታክስ እና ሌሎች ክፍያዎችን ወዲያውኑ ለጉምሩክ የሚከፈል ቀረጥና ታክስ እንዳይሰበሰብ የሚያደርግ ስህተት የፈጸመ እንደሆነ ለቀረጥና ታክስ ክፍያው ከደንበኛው ጋር በአንድነት እና በተናጠል በፍትሐብሔር ተጠያቂ የመሆን፤ ➡️ የጉምሩክ ትራንዚት ዕቃዎች በኮሚሽኑ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ተከብረውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ጉምሩክ መዳረሻ ጣቢያ እንዲደርሱ የማድረግ፤ ➡️በማንኛውም የጉምሩክ ጣቢያ ላይ የሚሰራን የጉምሩክ ሹም ወይም ፖሊስ ከማስፈራራት፣ በሀሰት ከመክሰስ፣ ለሕገወጥ ተግባር ከመደለል፣ ውለታዎችን ከመስራት ወይም በጥቅም ትስስር ከመስራት ወይም ጥቅም ከመስጠት ወይም ለመስጠት ከመሞከር የመታቀብ፤ ➡️ ሚስጥራዊ የሆኑ የጉምሩክ መረጃዎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በህገወጥ መንገድ ለማግኘት ወይም ለማስተላለፍ ከመሞከር የመታቀብ፤ ➡️የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ስላስፈጸመባቸው ጉዳዮች፣ ስላከናወናቸው የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ስላደረጋቸው የደብዳቤ ልውውጦች እና በአጠቃላይ ከጉምሩክ አስተላላፊነት ሥራ ጋር የተዛመዱ የተሟሉ ሰነዶችን የያዝ፤ ➡️ ከላይ የተመለከቱትን ሰነዶች በማናቸውም ጊዜ በኮሚሽኑ የጉምሩክ ሹም ሲፈለጉ የማስመርመር እና እንደ አስፈላጊነቱ የጉምሩክ ሹም ቅጂዎችን እንዲወስድ የመፍቀድ ➡️ከሥራው ጋር የተዛመዱ ሰነዶችን ለጉምሩክ ሥራ አፈጻጻም እስከ አምስት ዓመታት ድረስ ይዞ የማቆየት ➡️በገቢ ዕቃዎች ከመግቢያ በር እስከ ዕቃው መዳረሻ ድረስ እና ለወጪ ዕቃ ከመነሻው ጣቢያ እስከ መውጫ በር ድረስ ባለው ክልል ብቻ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- ደንብ ቁጥር 518/2014
نمایش همه...
👍 6
የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣን የመውጫ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት አፈጻጸም 1. የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣን የሚመለከተው የመውጫ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት እንደ አግባቡ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡- ➡️የመውጫ ዲክላራሲዮን ለኮሚሽኑ ማቅረብን፤ ➡️የማጓጓዣውን ጭነት በጉምሩክ ማሸጊያ እንዲታሸግ ማድረግን፣ ➡️ጉዞው የተወሰነ የጉምሩክ መስመርን እንዲከተል ማድረግን፣ ➡️ያልተፈቀደ የመውጫ መዘግየትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎች መውሰድን፡፡ 2. የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣ ወደ ጉምሩክ ክልል ከገባበት የጉምሩክ ጣቢያ ውጪ በሆነ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ ተመልሶ እንዲወጣ ይፈቀድለታል፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- አዋጅ 859/2006
نمایش همه...
👍 2
መለዋወጫዎችና መሣሪያዎች በጊዜያዊነት እንዲገቡ ስለመፍቀድ ➡️ ለጭነት መጫኛ፣ ማራገፊያ፣ አያያዝ ወይም አጠባበቅ የሚያስፈልግ ልዩ መሣሪያ ከንግድ አገልግሎት ማጓጓዣው ተነጥሎ አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችል ቢሆንም ባይሆንም ከንግድ አገልግሎት ማጓጓዣው ጋር ተመልሶ የሚወጣ እስከሆነ ድረስ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ከንግድ አገልግሎት ማጓጓዣው ጋር በጊዜያዊነት ወደ ጉምሩክ ክልል እንዲገባ ይፈቀዳል፡፡ ሆኖም አስመጪው የተቀየረውን አካል ከአገር ማስወጣት ወይም ለኮሚሽኑ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ ➡️ በጊዜያዊነት ወደ ጉምሩክ ክልል አስቀድሞ የገባ የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣን በመጠገን ወይም በማደስ ሂደት በማጓጓዣው ላይ የተገጠሙ አካላትና በማጓጓዣው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ መሣሪያዎችን ለመተካት የሚያገለግሉ መለዋወጫዎችና መሣሪያዎች ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው በጊዜያዊነት ወደ ጉምሩክ ክልል እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- አዋጅ 859/2006
نمایش همه...
👍 1
የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣን በጊዜያዊነት እንዲገባ ስለመፍቀድ 1. ማንኛውም ጭነት የያዘ ወይም ያልያዘ የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣ፡- ➡️በጉምሩክ ክልል ውስጥ ለአገር ውስጥ ማጓጓዣ አገልግሎት የማይውል ከሆነ፣ ➡️በአጠቃቀም ምክንያት ከሚደርስበት መደበኛ እርጅና፣ ከቅባቶችና ነዳጅ መደበኛ ፍጆታና ከአስፈላጊ ጥገናዎች በስተቀር ምንም ለውጥ ሳይደረግበት ተመልሶ ከአገር እንዲወጣ ለማድረግ ታስቦ ከሆነ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት በጊዜያዊነት ወደ ጉምሩክ ክልል እንዲገባ ይፈቀዳል፡፡ 2. የውጭ አገር የንግድ ማጓጓዣ ወደ አገር ውስጥ በጊዜያዊነት ሊገባ የሚችለው ማጓጓዣው በተመዘገበበት አገርና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት ወይም የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሲፈቅድ ብቻ ይሆናል፡፡ 3. ኮሚሽኑ የማጓጓዙ ሥራ ሂደት የሚጠይቃቸውን ሁኔታዎች በማገናዘብ የንግድ አገልግሎት ማጓጓዣው ተመልሶ የሚወጣበትን የጊዜ ገደብ ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ 4. ኮሚሽኑ በሚመለከተው ሰው ጥያቄና ተቀባይነት ባለው ምክንያት ላይ ተመሥርቶ በተራ ቁጥር 3 መሠረት የተወሰነውን የጊዜ ገደብ ሊያራዝም ይችላል፡፡ 5. በተራ ቁጥር 2 መሰረት ወደ አገር ውስጥ የገባ የውጭ አገር የንግድ ማጓጓዣ በአገር ውስጥ ጭነትና በወጪ ዕቃ ትራንስፖርት አገልግሎት መሰማራት አይችልም፡፡ 6. ከላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የትራንስፖርት ሚኒስቴር አገር ውስጥ የገባ የውጪ አገር የንግድ ማጓጓዣ ህጋዊ የወጪ ዕቃ ጭኖ ከአገር እንዲወጣ ሊፈቀድ ይችላል፡፡ 7. በጊዚያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገባ የውጭ አገር የንግድ ማጓጓዣ በተወሰነለት ጊዜ ተመልሶ ከአገር ያልወጣ እንደሆነ ወይም በአገር ውስጥ ጭነትና በወጪ ዕቃ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሰማርቶ የተገኝ እንደሆነ ብር 50 ሺሂ ቅጣት ከፍሎ ማጓጓዣው ከአገር እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 13 /2016 ዓ.ም ምንጭ፡- አዋጅ 859/2006 እና የተሻሻለው 1160/2011
نمایش همه...
👍 3
ከአጋር አካላት ጋር የዉይይት መድረክ ተካሄደ፤ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ራሄል ጌታቸዉ እና ከሌሎች የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የዉይይት መድረክ ተካሄደ፡ የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮንን መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት አንጋፋ ከሆነዉ ከኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ጋር በጋራ የሚደረጉ የትዉዉቅ እና የዉይይት መድረኮች የተሳለጠ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ለማከናወን ወሳኝ መሆኑን እና በሁለቱ ተቋማት መካከል ጠንካራ ግንኙት የሚፈጥር መሆኑን የገለፁ ሲሆን በመጨረሻም በተቋማቱ መካከል የሚደረግ የግንኙነት መድረክ ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑን በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 12/2016 ዓ.ም
نمایش همه...
ከመንገደኛው ተለይቶ ስለሚጓጓዝ ሻንጣ  ከመንገደኛው ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚደርስ ወይም የሚጓጓዝ የመንገደኛ ሻንጣ ከመንገደኛ ጋር አብሮ ለሚጓጓዝ ሻንጣ ተፈጻሚ በሚሆነው ወይም በሌላ ቀለል ባለ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይስተናገዳል፡፡  ማንኛውም ውክልና የተሰጠው ሰው ከመንገደኛው ተለይቶ የተጓጓዘን ሻንጣ መንገደኛውን ወክሎ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት እንዲፈጸምበት ለማድረግ ይችላል፡፡  በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ዕቃው በካርጎ ወይም በየብስ ማጓጓዣ የመጣ እንደሆነ የመንገደኛው ዕቃ የሚስተናገደው በጭነት ማጓጓዣ ወደ አገር ውስጥ የመጣ ዕቃ በሚስተናገድበት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ይሆናል፡፡  ከላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የመንገደኛው ዕቃ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በጭነት ማጓጓዣ ወደ አገር ውስጥ የገባ እንደሆነ ዕቃው እንደ መንገደኛ ዕቃ ተቆጥሮ የመንገደኛ እቃ በሚስተናገድበት ስነ-ሥርዓት መሰረት ይስተናገዳል፡፡  ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎች በሚኖሩበት አገር በተፈጠረ አስገዳጅ ሁኔታ ነው፡፡ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 8/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- አዋጅ 859/2006 እና የተሻሻለው 1160/2011
نمایش همه...
👍 7
ቅ/ጽቤቱ የእቅድ አፈጻጸም የዉይይት መድረክ አካሄደ! ====== የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቀን 07/10/2016 ዓ.ም የቅ/ት/ቤቱ አመራሮች በተገኙበት የግንቦት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ዉይይት አካሄደ፡፡ ቅ/ጽ/ቤቱ በግንቦት ወር 1,678,899,227.29 አቅዶ 1,802,015,697.97 ወይም የዕቅዱን 107.33 % የሰበሰበ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን የወቅቱ ክንውን ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ብር 1,350,828,484.49 ጋር ሲነፃፀር በብር 451,187,213.48 ወይም 33.4 በመቶ የጨመረ ገቢ መሰብሰቡን ያሳያል፡፡ ቅ/ጽ/ቤቱ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የበቃው ቁርጠኛ የሆኑ አመራሮችና ሰራተኞ ከቅ/ጽ/ቤቱ ደንበኞች ጋር ተቀናጅተው በመስራታቸው መሆኑን አቶ ተፈሪ መኮመንን በመግለጽ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህን አመርቂ ስኬት በሰኔ ወርም የሚደገም መሆኑን በቁርጠኝነት በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ ------//--------- የደንበኞች ትምህርት ቡድን ሰኔ 07 ቀን 2016ዓ/ም አዲስ አበባ
نمایش همه...
3👍 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.