ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر606
مشترکین
-224 ساعت
-57 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል ማርያም ከተወለደች በኋላ #በሰማንያ_ቀን_ከርግ_ገላግልቶች_ጋር_ወደ #መቅደስ_ለተወሰደችበት_ቀን_መታሰቢያ_በዓልና ለታላቁና ለክቡር ለሆነ ለሠራዊት አለቃ #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ቴዎድሮስ_ለዕረፍት_በዐለ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከታአኪጦስ፣ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት #ከቅዱስ_ጢሞቴዎስ_ከሙሴ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሕፃኑ_ከቅዱስ_ቂርቆስ ከእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጋር በሰማዕትነት ከአረፉ #ከአራት_መቶ_አራት_ሰማዕታት_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሠራዊት_አለቃ_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ። አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።
❤ ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።
❤ ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ "ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ" አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ ይበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና"። ንጉሡም "እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ" አለው።
❤ በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም "የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና" አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በእግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም"። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ "ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ" አላቸው። እነርሱም "ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን" አሉት እርሱም "ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ" አላቸው። "ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ" አሉት።
❤ ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ "ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው ጌታዬ አምላኬ ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን"።
❤ ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በመስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ "እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ" እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።
❤ አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።
❤ በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው። ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል እግዚአብሔርም ይበቀልላታል" አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።
❤ ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው "አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል"።
❤ በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት። በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው "ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ" እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ "መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ
❤ ቅዱስ በጥላንም ጥበብ ያደርግ ነበር። ያለ ዋጋም ሰዎችን ያድናቸው ነበር። ነገር ግን ክብር ይግባውና በክርስቶስ እንዲያምኑ ይሻ ነበር። ስለዚህም ጥበበኞች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሡ ወደ ንጉሥም ሒደው ከቄሱ ጋራና ከአዳነውም ዕውር ጋራ በጌታችንም ከአመኑ ከብዙዎች ጋራ ከሰሱት። ወደ ንጉሡም በቀረቡ ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ "ለአማልክት ሠዉ" አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። የሰማዕታት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ በጥላንንም የጸና ሥቃይን አሠቃየው። ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ በእጁም ብዙ ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ። በሰማዕነትም ዐረፉ። ንጉሡም አይቶ በበጥላን ላይ ተቆጣ። ለአንበሳም አስጣለው አንበሳውም እግሩን ላሰው እንጂ ክፉ አላደረገበትም። ሁለተኛም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚህም ምስክርነቱን ሐምሌ 19 ቀን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ በጥላንና ከእርሱ ጋራ በሰማዕትነት በዐረፉ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ስማቸው_ሱርስ_ኅርማን #ያኑፋ_ስንጣንያ_የሚባሉ_የእስና_አገር_ሰዎች የሆኑ፦ የሰማዕትነታቸው ምክንያትም እንዲህ ነው መኰንኑ አርያኖስ ወደ እስና ከተማ ሦስት ጊዜ ደረሰ። በመጀመሪያ የተባረከች መስተጋድልት የሆነች ዳላዢን ገደላት። ስማቸውን አስቀድመን የጠራናቸው አራቱን ልጆቿንም ገደላቸው። የሰማዕነታቸውም ፍጻሜ ግንቦት ሰባት ቀን ሆነ። ሁለተኛም ስማቸው አውሳፍዮስ ታማን ኅርማን ባኮስ የሚባል አራቱን መኳንንት ገደላቸው። የሰማዕታቸውም ፍጻሜ ሰኔ ሰባት ቀን ሆነ። ሦስተኛም ጊዜ በቤቷ ውስጥ በዐልጋዋ ላይ ተኝታ የነበረችውን አሮጊት የአርያኖስ ወታደሮች ስለ እነዚህ ቅዱሳን ከጠየቷት በኋላ ገደሏት።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከክርስቲያን ወገን ያገኙትን ሁሉ እንዲገድሉ የተክል ማጠጫ በተባለች በከተማዋ ምዕራብም መግደልን እንዳያቋርጡ አዘዘ ወደ ከበረ አባት ወደ ባሕታዊ ይስሐቅም እስኪደርሱ ድረስ በመንገድ ብዙ ሕዝብን አገኙ። ያን ጊዜም ጠባቂያቸው እንዲህ እያለ ያጽናናቸውና ያረጋጋቸው ነበር "ወደ ሰማያዊት መንግሥት እንድትገቡ ጸንታችሁ ታገሡ"። እንዲህም ሲወስዷቸው መኰንኑ ደረሰ በአዩትም ጊዜ ሁሉም በአንድ ቃል "እኛ ክርስቲያን ነን" እያሉ በግልጽ ጮኹ መኰንኑም ሁሉንም እንደበግ ያርዷቸው ዘንድ አዘዘ። ጭፍሮች ግን በላያቸው በሰይፎች አጋና ተጫወቱ። በዚችም በሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ ቀን የእስናን ከተማ ሰዎች ከታናሾቻቸው እስከ ታላቆቻቸው ሴቶችንና ወንዶችን ጨረሷቸው። የመላእክት ሠራዊትም ነፍሶቻቸውን ይቀበሉ የብርሃን አክሊሎችንም ያቀዳጁአቸው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከዚያ ወደ እስዋን ከተማ ሔደ ሁለተኛም ወደ እስና ከተማ ተመለሶ ሦስት ገበሬዎችን የእርሻ ዕቃቸውን ተሸክመው አገኘ። በመኰንኑም በአዩት ጊዜ "እኛ ክርስቲያን ነን" ብለው በግልጥ ጮኹ መኰንኑም ሰምቶ ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ በእርሻ መሣሪያቸውም ገደሏቸው የእነዚህም ስማቸው ሱሩፋስ፣ አንጣኪዮስ፣ ስሐድራ ይባላል የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ መስከረም ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
❤ ይህንንም ቅዱስ አባት ኤጲስቆጶስ ይስሐቅን መኰንኑ አሥሮ ለጣዖት እንዲሠዋ አስገደደው። እምቢ ባለውም ጊዜ ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ የሰማዕትነቱም ፍጻሜ ታኅሣሥ ዐሥራ አራት ቀን ነው ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት። የስደቱ ወራትም ከአለፈ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በስሙ አከበሩዋት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአገረ እስና ሰማዕትነት ሁሉ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 19 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ሰማዕት_በጥላን። ዘሀገረ ትእማዳን። በእንተ ኢየሱስ ዘሞትከ በሰይፈ ኀፂን። ምስለ ዕውር ዘፈወስኮ ወምስለ መምህርከ ካህን። እንዘ ክዋኔከ ከመ ኤር ወስን"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ19።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወአፅዐንከ ሰብአ ዲበ አርእስቲነ። አኅለፍከነ ማእከለ እሳት ወማይ። ወአውጻእከነ ውስተ ዕረፍት"። መዝ65፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥1-12።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ይትኀፈሩ ኵሎሙ እለ ይሰግዱ ለግልፎ። ወእለ ይትሜክሑ በአማልክቲሆሙ። ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ መላእቲሁ"። መዝ 96፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥33-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 23፥10-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 11፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም እና ፌስቡክ ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያሉት ሊንኮች ይጫኑት።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለመጋቢ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ገብርኤል_ሕፃኑን_ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ ወደ ፈላ ውሃ ውስጥ በጣሏቸው ጊዜ ከእግዚአብሔር ተልኮ የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ አድርጎ ላደነበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዐል፣ ትዕማዳን ከምትባል ከተማ ብልህ ለሆነ ለሰማዕቱ #ለቅዱስ_በጥላን_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት_ለዕረፍቱ በዐልና #ለቅዱሳን_ሰማዕታት_ስማቸው_ሱርስ፣ #ኅርማን_ያኑፋ_ስንጣንያ የሚባሉ የእስና አገር ሰዎች ለሆኑ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍቻው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_አቃራቦን_ከመቃርስና_ከስካ አገር ሰው ከሆነ #ከሙሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ኢየሉጣን_ቅዱስ_ገብርኤል_እንዳዳናቸው፦ ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ አገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም "መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ" አለችው።
❤ ሕፃኑም ቅዱስ ቂርቆስ ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና "አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ" አለው። ሕፃኑም መልሶ "አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና" አለው። እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑም በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም "ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ" አለችው። "ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት" አለችው ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ ሐምሌ 19 ቀን በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጎትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል፣ በቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ ትዕማዳን ከምትባል ከተማ ብልህ የሆነ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_በጥላን፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ አረማዊ ነበረ ስሙም አውጢኪዮስ ነበር እናቱ ግን አማኝ ነበረች ስሟም ኤልያና ነበር። በአደረገ ጊዜም አባቱ ጥበብን ሁሉ አስተማረው እጅግም አዋቂ ሆነ።
❤ በበጥላን ቤት አቅራቢያም አንድ ቄስ ይኖር ነበር። በጥላንም በፊቱ ሲያልፍ መልኩንና ዕውቀቱን ብልህነቱንና አስተዋይነቱንም ይመለከት ነበር ከሀዲ ስለ መሆኑም ስለርሱ ያዝን ነበር። ቄሱም በጥላን መንገድ መርቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ያስገባው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው። ስለ በጥላንም ልመናውን በአዘወተረ ጊዜ በጥላን በእርሱ እጅ ያምን ዘንድ እንዳለው ጌታችን በራእይ ገለጠለት ቄሱም ደስ አለው ሁልጊዜም በፊቱ ሲያልፍ በጥላንን ያነጋግረውና ሰላምታ የሚሰጠው ነበር። ስለዚህም በመካከላቸው ፍቅር ጸና።
❤ ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ቤት ይገባና ስለ ሃይማኖት ይነጋገር ነበር። ቄሱም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ምን ያህል ክብር እንዳላት ለሚያምኑበትም ሁሉ ዕውቀትና ማስተዋል እንደሚሰጣቸው ድንቆችና ታላላቅ ተአምራቶች እንደሚደረግላቸው ታላቅ ፈውስም እንደሚያደርጉ ገለጠለት። በጥላንም ክብር ይግባውና በክርስቶስ የሚያምኑ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ይህን በሰማ ጊዜም እጅግ ደስ ብሎት በዚያ ቄስ ትምህርት በጌታ አመነ ቄሱም ሁል ጊዜ የሃይማኖት ትምህርት ያስተምረው ጀመር።
❤ በአንዲትም ዕለት ቅዱስ በጥላን በከተማው አደባባዮች ሲያልፍ እባብ የነደፈውን አንድ ሰው ሲጨነቅ አየው እባቡም በርሱ ዘንድ ቆሞ ነበር በልቡም "የመምህሬን ቃል ልፈትን ክብር ይግባውና በክርስቶስ ከአመንክ በስሙ ታምራት ታደርጋለህ ብሎኛልና" አለ። እባቡ ወደ ነከሰውም ሰው ቀርቦ ኃይሉን ይገልጽለት ዘንድ እባቡንም ይገድለው ዘንድ ሰውዬውን ያድነው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ረጅም ጸሎትን ጸለየ ያን ጊዜም ሰውዬው ያለ ምንም ጉዳት ድኖ በጤና ተነሣ ከይሲውም ወደቀ ወዲያውም ሞተ። የበጥላንም ሃይማኖት ተጨመረለት።
❤ ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ሁል ጊዜም ወደ ቄሱ እየመጣ ይማር ነበር። በአንዲት ቀንም ያድነው ዘንድ አንድ ዕውር መጣ። የቅዱስ በጥላም አባትም ባየው ጊዜ ዕውሩን ከውጭ መልሶ ሰደደው በጥላንም አባቱን "ማነው የፈለገኝ?" ብሎ ጠየቀው አባቱም "ልታድነው የማትችል አንድ ዕውር ነው" አለው። እርሱም አባቱን "የእግዚአብሔርን ክብር ታይ ዘንድ አለህ" አለው ይህንንም ብሎ ዕውሩን ጠራውና "ዐይኖችህ ቢገለጡ ያዳነህን ታመልከዋለህን?" አለው ዕውሩም "አዎን አምናለሁ" አለ ቅዱስ በጥላን በዕውሩ ላይ ረጅም ጸሎትን ጸለየ እጆቹንም በዕውሩ ዐይኖች ላይ አኑሮ "እንድታይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመን" አለው ወዲያውኑም ዐይኖቹ ተገለጡ። አባቱም ይህን ድንቅ ሥራ በአየ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ከዕውሩ ጋር አመነ ቅዱስ በጥላንም ወደ ቄሱ ወሰደጃቸውና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ከዚህም በኋላ ባሮቻቸውን ነፃ አወጡ ገንዘባቸውንም ለድኆችና ለችግረኞች አከፋፈሉ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወኢነበርኩ ውስተ ዐውደ ከንቱ። ወኢቦእኩ ምስለ ዐማፅያን። ጸላዕኩ ማኅበረ እኩያን "። መዝ25፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥1-13፣ ያዕ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 15፥13-20። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥ 1-ፍ14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ለነበረው ለጌታችን ወንድም ለሚባለው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ_ለዕረፍት በዓል፣ ከቁልዝም ከተማ ለሆነ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_አትናቴዎስ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዱራናና_ከጦቢያ፣ #ከኤስድሮስ_ማኅበር_ከዘጠኝ_ሽህ ጭፍሮችና #ከመኰንኑ_ከእንድራኒቆስና ከሠራዊቱ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ያዕቆብ፦ ይህም የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው። እርሱም ከልጆቹ ሁሉ የሚያንስ ነበር። እርሱም ንጹሕ ድንግል ነበር ከጌታችን ጋራ አደገ ስለዚህም ክብር ይግባውና የጌታችን ወንድም ተባለ። ከጌታችን ዕርገትም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም አገር ላይ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተምሮ ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው። እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ።
❤ በአንዲት ዕለትም በጎዳና ሲጓዝ አንድ ሽማግለሸ አገኘ። ቅዱስ ያዕቆብም "ሽማግሌ ሆይ በቤትህ ታሳድረኛለህን?" አለው። አረጋዊውም "እሺ እንዳልክ ይሁን" አለ በአንድነትም ሲጓዙ ጋኔን ያደረበት ሰው አገኘው በአየውም ጊዜ "የክርስቶስ ሐዋርያ ሆይ እኔ ካንተ ጋር ምን አለኝ ልታጠፋኝ መጣህን" ብሎ ጮኸ። ሐዋርያውም "በናዝሬቱ ኢየሱስ ስም ተዘጋ ከሰውዬውም ውጣ" አለው። ወዲያውም ያ ጋኔን ከሰውዬው ላይ ወጣ።
❤ ያ ሽማግሌም ይህን ድንቅ ተአምር አይቶ ደነገጠ ከሐዋርያው እግር በታችም ወድቆ እንዲህ አለው "ወደ ቤቴ ልትገባ አይገባኝም ነገር ግን እድን ዘንድ ቤተ ሰቦቼም ሁሉ ይድኑ ዘንድ ምን ላድርግ" አለ ያን ጊዜም ሐዋርያው "አቤቱ ጌታዬ ሆይ መንገዴን አሳምረህልኛልና አመሰግንሃለሁ" ብሎ ጌታችንን አመሰገነው። ወደ ሽማግሌዎች ተመልሶ የድኅነትን ነገር ነገረው ከብር ይግባውና ስለጌታችን ሰው መሆን ስለ መከራው ስለ ሞቱና ስለ መነሣቱ አስተማረው።
❤ ከዚህም በኋላ ያ ሽማግሌ ሐዋርያውን ወደ ቤቱ አስገባው ቤተ ሰቦቹም ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ ቅዱስ ያዕቆብም አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው።
❤ የከተማው ሰዎችም በሰሙ ጊዜ በሽተኞችን ሁሉ ወደርሱ አመጡ ሁሉንም አዳናቸው ለእነርሱም ሃይማኖትን አስተምሮ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው። ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመላቸው ያንን ሽማግሌም ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው ክብር ይግባውና የጌታችንንም ወንጌል ሰጣቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ያስተምር ዘንድ ወደ ሌሎች አገሮች ወጥቶ ሔደ። አንዲትም መካን ሴት ነበረች እግዚአብሔር ልጅን ይሰጣት ዘንድ ስርሷ እንዲጸልይላት ቅዱስ ያዕቆብን ለመነችው። እርሱም ጸለየላትና ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው ልጅዋንም ተሸክማ ወደ ሐዋርያው መጥታ ሰላምታ አቀረበችለት ከልጅዋም ጋር ከእርሱ ተባረከች።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ብዙዎች አይሁድ ወደርሱ ተሰበሰቡ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስም የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ጠየቁት እነርሱ እርሱ ጌታች የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ እርሱም ወንድሙ እንደሆነ እንዲነግራቸው አስበው ነበርና። ቅዱስ ያዕቆብም በሦስተኛ ደርብ ላይ ወጥቶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ከአብ ጋራም ትክክል እንደሆነ ይገልጽላቸው ጀመረ።
❤ ይህንንም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ ከደርቡ ላይ አውርደው የጸና ግርፍትን ገረፉት ከእነርሱም ውሰጥ የልብስ ማጠብያ የእንጨት ገበታ የያዘ አንድ ሰው መጣ በዚያ እንጨትም ቅዱስ ያዕቆብን ራሱ ላይ መታው ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
❤ ስለርሱ ወይን እንዳልጠጣ ደም ከለው ወገን እንዳልበላ በራሱም ላይ ምላጭ እንዳልወጣ በውሽባ ቤት እንዳልታጠበ ሁለት ልብስን እንዳለበሰ ሁል ጊዜም እንደሚቆምና እንደሚሰግድ ተጽፏል። ከመቆም ብዙ የነሳ እግሮቹ አብጠው ነበር። ከዚህም በኋላ ዐረፈና በቤተ መቅደሱ ጎን ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አትናቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከነገሥታት ወገን ነበረ በሃይማኖቱም የጸና ነበረ። እኒህ ከሐዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ የጣዖታትን አምልኮ በዓወጁ ጊዜ ይህን አትናቴዎስን ለግብጽ አገር ገዥ አድርገው ሾሙት አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲአፈርስ አዘዙት።እርሱ ግን ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ሒዶ በረከትን ተቀበለ እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ነገረው በእርሱም ደስ አለው። ንጉሡም በሰማ ጊዜ ይዞ ይመረምረው ዘንድ ሌላ መኰንን ላከ።
❤ መኰንኑም በደረሰ ጊዜ ተገናኘውና "የአማልክትን ፍቅር ለምን ተውክ" አለው። አትናቴዎስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ከታናሽነቴ ጀምሬ ክብር ይግባውና የክርስቶስ ነኝ የቀናች ሃይማኖቴንም አልተውም"።
መኰንኑም "የንጉሥን ትዕዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ቅጣት እንዲአገኘውና በጽኑ ሥቃይ እንዲሠቃይ አታውቅምን" አለው። ቅዱስ አትናቴዎስም እንዲህ አለው "አንተ ሰነፍ በአንተ ላይና በንጉሥህ ላይ ቸር ሕይወት ሰጭ እግዚአብሔርን በሚጠላ በአባትህ ሠይጣን ላይ የሚመጣው የዘላለም ሥቃይን እስከምታይ ጥቂት ታገሥ" አለው።
❤ መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ቅዱስ አትናቴዎስም ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋራ እንዲያሳርፍ ከቤተ ክርስቲያንም መከራን እንዲያርቅ የሮምንና የአኲስምን የክርስቲያን መንግሥት እንዲአጸና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጸሎቱም በፈጸመ ጊዜ በክር ብሎ ሰገደ ጭፍሮችም ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ቀበሩት። ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋ ይሁን እኛንም በቅዱስ አትናቴዎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 18 ስንክሳር
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለያዕቆብ_በኀበ_ማርያም_ዘተሐፅነ። ዕጓለ ማውታ እምእሙ እስመ ውእቱ ኮነ። ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ። ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 18።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4 ወይም መዝ 25፥4 ። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥52-ፍ.ም ወይም ማር 6፥1-14።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን #ለየዋሁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ዮናስ_ከዓሣ_ዐንበሪ_ሆድ ውስጥ ለወጣበት ቀን መታሰቢያ በዓልና #ለቅድስት_አውፎምያ_ሰማዕትነት_ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ኤስድሮስና #ከሰማዕቱ_ቤዱል፣ #ከዘካርያስና_ከአውልያን_ከዐይነ_ፀሐይ ከመታሰቢያቸው #ከቅዱስ_ሰማዕት_ከዮስጦስም_ዐፅሙ_ከተገኘበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_አውፎምያ፦ ይቺም ቅድስት በርሴፎስ የሚባል ከዲዮቅልጥያኖስ መኳንንቶች አንዱ አሠቃያት። የታሠሩ ሰማዕታት በሚያልፉ ጊዜ በአንገታቸው የሚከብዱ ሰንሰለቶች ነበሩ። እንደ ውሾችም ይጎትቷቸው ነበር። ግፋቸውንም ባየች ጊዜ ይቺ ቅድስት አለቀሰች ልቡናዋም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ፍቅር ተቃጠለ ዲዮቅልጥያኖስንና የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች። ያንንም መኰንን እንዲህ ብላ ዘለፈችው። "ርኅራኄ የሌለህ ልብህ እንደ ደንጊያ የሆነ ለእኒህ ቅዱሳን ሰዎች አትራራምን ፈጣሪያቸውስ እንዲያጠፋህ አትፈራንምን"።
❤ መኰንኑም ሰምቶ ወደርሱ ያቀርቡአት ዘንድ አዘዘ። ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት እርሷም ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ አመነች። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ በግርፋትና በስቅላት ታላቅ ሥቃይን አሠቃያት።
❤ ከዚህ በኋላ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩዋት ነገር ግን ከሥቃዩ የተነሣ ምንም ጉዳት አልደረሰባትም። በዚያን ጊዜሜ በእሳቱ መካከል ቆማ ጸለየች ፊቷንና መላ ሥጋዋንም በመስቀል ምልክት አማተባ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አውፎምያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 17 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለአውፎምያ_ኅሪት። ክበደ ሰናስል ነጺራ በክሣደ ሰማዕት። ወሶበ ነደ ልባ በአምላካዊ ቅንዓት። መቅሠፍት ኢያፍርሃ ወኢያደንገፃ ስቅለት። ወለኪፎታ ኢክህለ እሳት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_17።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወአይቴ እጎይይ እምቅድመ ገጽከ። እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ። ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላይ ህየኒ ሀሎከ"። መዝ 138፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-12፣ 1ኛ ጴጥ 2፥1-11 እና የሐዋ ሥራ 26፥1-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥38-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ ጻድቁ ከበዓታቸው ጣና ዘጌ ተነስተው አቡነ ሐራ ድንግልን እየሄዱ ይጎበኟቸው እንደነበር በአቡነ ሐራ ድንግል ገድል ላይ ተጽፏል። አቡነ በትረ ማርያም ከበዓታቸው ወጥተው ወደ ሌላ ቦታ የሚሔዱት ለምነው ለነዳያን የሚሰጡትን ለመሰብሰብ ሲፈልጉና ገዳማትን ተሳልመው የቅዱሳንንም በረከት ለመቀበል ሲፈልጉ ብቻ ነበር። ቅዱሳንን ጎብኝተው ወደ ገዳማቸው ዘጌ የሚመለሱትም ለነዳያን የሚሰጡትን ከሰበሰቡ በኋላ ነው። ለነዳያን የሚሰጡትን ገንዘብ የሚሰበስቡትም እንደባርያ እየተሸጡ ለፈረስ ሳር በማጨድና የመንገደኞችን ዕቃ በመሸከም የሚከፈላቸውን ገንዘብ በማጠራቀም ነበር። "ላጡ ለድኆች የሚሆን ምግብ ለማግኘት ሲሉ ለፈረስና ለበቅሎ ሣር ያጭዱ ዘንድ ባሪያ ሆነው የተሸጡበት ጊዜ አለ። ከባለጸጋ ቤት ቁራሽ እንጀራን ተቀብለው ለድኆች ይሰጡ ዘንድ በባለጸጋው ደጅ ከድኆች ጋር ተቀምጠው የሚለምኑበት ጊዜም ነበር። በመንገድ የሚያልፉ ሰዎችን ዕቃቸውን ይሸከሙ ዘንድ በመንገድ የሚቆሙበት ጊዜም ነበር" በማለት ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል የአቡነ በትረ ማርያምን የትሩፋት ሥራ ይነግረናል።
❤ አቡነ በትረ ማርያም ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን በማድረግ ይታወቃሉ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባታችን ከመነኰሳት ልጆቻቸው ጋር በገዳማቸው ሳሉ በህርመት የሚኖሩ መሆናቸውን የሰማ አንድ መነኵሴ ከሩቅ መጣና እንደገዳሙ ሥርዐት በእንግዳ ቤት ተቀመጠ። መነኰሳቱም የጸሎተ ማዕድ አድርሰው እንደመነኰሳቱ መቁነኑን ለእንግዳው ሰው አደሉት። መነኵሴው ግን መቁነኑን ሳይበላው ደብቆ ይዞ በአኩፋዳው ውስጥ ከተተው። በልቡም "እነዚህ መነኰሳት የሚመገቡት ይኸንን ነው" ብዬ "ለሀገሬ ሰዎች ማሳየት አለብኝ" ብሎ አሰበ። ወዲያም በአኩፋዳው የደበቀውን መቁነን ሰውሮ ይዞ ለመሔድ ሲነሣ ቡራኬ ሊቀበልና ሊሰናበት ከአቡነ በትረ ማርያም ፊት ቆመ። አባታችንም ሰውዬው ደብቆ የያዘውን መቁነን በመንፈስ ቅዱስ ዐወቁበትና "…ይኸ እንግዳ እኛ የሰጠነው እንደሆነ ክብራችንን ከገዳሙ ውጭ አውጥቶ ሊገልጽ አይገባም፣ ይኽንን ይበላሉ እያለ ሊገልጽብን ነው" አሉ። ዳግመኛም የየራሱ የሆነው ይባረክለት የገዳሙ መቁነን የሆነው ግን ከይሲ ይሁን" በማለት እንደተናገሩ ወዲያው ከአኩፋዳው ውስጥ ሰባት ክንድ የሚሆን እባብ ራሱን ከአኩፋዳው ውስጥ ብቅ አደረገ። በዚኸም ጊዜ እንግዳው ሰውዬ እጅግ ደንግጦ ከአባታችን እግር ሥር ወድቆ "በድያለሁ፣ ኀጢአት ሠርቻለሁ፣ ይቅር በሉኝ" እያለ የሠራውን ሁሉ እየተናዘዘ ይቅርታ ያደርጉለት ዘንድ ለመናቸው። አቡነ በትረ ማርያምም "እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ዳግመኛ እንዳትበድል" አሉትና ወደመጣበት መለሱት።
❤ አቡነ በትረ ማርያም መልካሙን ተጋድሏቸውን ፈጽመው ሩጫቸውን ጨርሰው የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ ተገለጠላቸውና "ወዳጄ በትረ ማርያም ሆይ! በዚኽች ዕለት ከኀዘን ወደ ደስታ፣ ከሕመም ወደ ሕይወት ልወስድህ ነፍስህንም አሳርፋት ዘንድ መጣሁ፤ ቦታህን እንደ ኢየሩሳሌም አደረግሁልህ፤ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሠራ፣ ዕጣን የሰጠውን መብዓ ያቀረበውን፣ ሥጋህ የተቀበረበትን ዐፅምህ ያረፈበትን ገዳመ ዘጌን የተሳለመውን፣ ወንዱ በ40 ቀን ሴቷ በ80 ቀን ጥምቀተ ክርስትና የተቀበለውን፣ በቦታህ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን የተቀበለውን፣ በስምህ ገድልህን የጻፈውን፣ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ልብ ያላሰበውን እንደ አንተ ላሉት አባቴ ያዘጋጀውን አወርሰዋለሁ። በገዳመ ዘጌ ላይ መብረቅና ነጎድጓድ፣ በምድር የሚሳቡ በመርዛቸው ሰውን የሚጎዱ እባቦች፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩ አራዊቶች ሁሉ በዘጌ የሚኖረውንና በአንተ ያመነውን አይጣሉ (አይጉዱ)፣ በገዳሙ የሚኖሩ መነኰሳትና ምእመናን እንደ መላእክት ኃጢአት የሌለባቸው ይሁኑ፣ ደምህ ከፈሰሰበት ከገዳመ ዘጌ መቃብርህ ላይ አፈር ቆንጥሮ የተቀባ ከሕማሙ ይፈወስ፣ መቃብርህን እጅ የነሣ የእኔን መቃብር እጅ እንደነሣ ይሁንልህ" በማለት አስደናቂ የምሕረት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ዐሥራ ኹለት የክብር አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ጌታችን በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ።
❤ አባታችንም ከዚህ በኋላ መነኰሳት ልጆቻቸውን ሰብስበው የዕረፍታቸው ጊዜ መድረሱን ነግረዋቸው በመጨረሻው ዘመን ወደ ገዳሙ ክፉ ሰዎች ይመጣሉና ከእነርሱ ጋር አትጨመሩ… እያሉ ከመከሯቸውና ካስተማሯቸው በኋላ ረዳታቸውን አቡነ በርተሎሜዎስን በእርሳቸው ቦታ ከሾሙላቸው በኋላ በዕለተ ዐርብ ከቀኑ በሦስት ሰዓት በ89 ዓመታቸው ሐምሌ 17 ቀን በክብር ዐርፈው በዚያው በመሐል ዘጌ ተቀበሩ። ቅድስት ነፍሳቸውን ቅዱሳን መላእክት በምስጋና በማኅሌት ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አስገቧት። ጻድቁ ከዘጌ ጊዮርጊስ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ በተቀበሩበት ቦታ ላይ ሌላ ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት ሲሆን ከመካነ መቃብራቸው ላይ እየተወሰደ ለምእመናን የሚሰጠው እምነት በዘመናችንም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል። ከአባታችን ከአቡነ በትረ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከት ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ ገጽ 320-327።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_የረገጡት_የጸለዩበት_መሬትና_ድንጋይ_ሁሉ_እምነት_ሆኖ_ብዙ_ድውያንን_ይፈውስ ለነበሩት፤ #በትራቸውም_በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ #የወይን_ዘለላ_ፍሬ እያፈራ ይለቀም ለነበሩ ለታላቁ አባት #አቡነ_በትረ_ማርያም_ዘዘጌ ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_አቡነ_በትረ_ማርያም_ዘዘጌ፦ በጣና ሐይቅ ደሴት ውስጥ ካሉት 37 ደሴቶች ውስጥ በአጠቃላይ 30 ያህል ጥንታዊ ገዳማት ይገኛሉ። ከእነዚኽም ውስጥ ሰባቱ በዘጌ ባሕረገብ መሬት ላይ የሚገኙ ናቸው። ከእነርሱም ውስጥ ዋነኛውና ቀደምቱ የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ነው። ይኽንንም ገዳም በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በ1264 ዓ.ም የመሠረቱት አቡነ በትረ ማርያም ናቸው።
አቡነ በትረ ማርያምና ስድስቱ ወንድሞቻቸው ሰባቱ ከዋክብት ተብለው ይጠራሉ። እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት ቅዱሳን እየራሳቸው ከገደሟቸው ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ አቡነ በትረ ማርያም (መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስን) ፣አቡነ ኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስን)፣ አቡነ ያሳይ (ማንዳባ መድኀኔዓለምን)፣ አቡነ ዘካርያስ (ደብረ ገሊላን)፣ አቡነ አፍቅረነ እግዚእ (ጒጒቤንና ጣና ቂርቆስን)፣ አቡነ ታዴዎስ (ደብረ ማርያምን) እና አቡነ ዘዮሐንስ (ክብራን ገብርኤልን) ገዳማትን ገድመዋል።
❤ የጻድቁን ገድል በአጭሩ ከገዳሙ ታሪክ ጋር አንድላይ ገዳመ ዘጌ ያሳተመው መጽሔት እንደሚገልጠው አቡነ በትረ ማርያም የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ሙገር ነው። አባታቸው ቅዱስ ተክለ ማርያም እናታቸው ቅድስት ኢላርያ ይባላሉ። ወላጆቻቸውም በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን እንደ ቅዱስ ኢያቄምና እንደ ቅድስት ሐና ልጅ ስላልነበራቸው የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ዘወትር በጾም በጸሎት ይለምኑት ነበር። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተኝተው ሳለ ቅድስት ኢላርያ ራእይ ተመለከተች። ቅዱስ ተክለ ማርያምም ተመሳሳይ ራእይ ተመልክቶ ኹለቱም ስላዩት ራእይ ተነጋግረው "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አሉ።
❤ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ምዕመናንን ስቦ በወንጌል ጎዳና የሚመራ የተመረጠ ልጅ እንደሚወልዱ ነገራቸው። መልአኩም በነገራቸው መሠረት አቡነ በትረ ማርያም ነሐሴ 16 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 21 ቀን ተወለዱ። የተወለዱትም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለክርስቲያኑም ለእስላሙም በምትገለጥበት ዓመታዊ በዓል ላይ ስለሆነ አንድም ይረዳናል ምርኩዛችን ይሆናል ብለው ወላጆቻቸው ስማቸውን በትረ ማርያም አሏቸው።
❤ አቡነ በትረ ማርያም ሰባት ዓመት በሆናቸው ጊዜ ወላጆቻቸው ሃይማኖትን እንዲማሩ ወደ ደብረ ኤዎስጣቴዎስ አባታችንም ገዳም ላኳቸው። ትምህርታቸውን እየተማሩ ገዳማውያን አባቶችን ዕንጨት በመስበር በመቅዳትና ውኃ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ እየተራዱ ብሉይንና ሐዲስን ተምረው አጠናቀቁ። በኋላም አስኬማ መላእክትን ከአቡነ ዜና ማርቆስ ተቀብለው ከጳጳሱም ዘንድ ሔደው ሥልጣነ ክህነትንና ቁምስናን ከተቀበሉ በኋላ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የከበረች ወንጌልን ሰበኩ።
❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ከሥዕለ ማርያም ፊት ቆመው ሲጸልዩ ክብርት እመቤታችን ተገልጣላቸው ሕሙማንን የሚፈውሱበት ጽዋ ሰጠቻቸው። በአንድ ወቅት የረኀብ ዘመን ሆኖ ሳለ አቡነ በትረ ማርያም ግን ለመንፈሳዊ ወንድማቸው የረኀቡን ዘመን ማሳለፊያ እንዲሆነው ብለው ጌታችን በተሸጠበት ዋጋ በሠላሳ ብር ተሸጠው በጉልበታቸው ሠርተው በማገልገል ለወንድማቸው የረኀብ ዘመን ማሳለፊያ ሆነዋል። በተሸጡበትም ቦታ በጉልበታቸው እያገለገሉ ሳለ የመኰንኑ ልጅ በጽኑ ሕመም ታማ ለሞት ስትደርስ አባታችን እመቤታችን በሰጠቻቸው ጽዋ ውኃ አድርገው ጸልየው አጥምቀው አድነዋታል።
❤ ከዚኸም በኋላ አቡነ በትረ ማርያም ከሸዋ ወደ ዳሞት (ጎጃም) አውራጃ ተሻግረው በጣዖት ያመልኩ የነበሩ ሰዎችን አስተምረው አጥምቀው በወንጌል ሕግ እንዲኖሩ በማድረግ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመዋል። በጎጃም ካስተማሩ በኋላ ወደ ቤጌምድር ሔደው በዚያም በተጋድሎ እየኖሩ የከበረች ወንጌልን ሰበኩ። አባታችን የረገጡትና የጸለዩበት መሬትና ድንጋይ ሁሉ እምነት ሆኖ ብዙ ድውያንን ይፈውስ ነበር። በትራቸውም በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ የወይን ዘለላ ፍሬ እያፈራ ይለቀም ነበር። በዚያም አካባቢ ጠበል አፍልቀው ብዙ ሕሙማንን እየፈወሱ ዜና ተአምራቸው በየቦታው ሲናገር ውዳሴ ከንቱን ሸሽተው ክብራቸው እንዳይታወቅ ወደ ምድረ ደንቢያ ሔዱ።
❤ አቡነ በትረ ማርያም በምድረ ደንቢያም ለስድስት ዓመት ምንም እህል ሳይቀምሱ በተጋድሎ እየኖሩ ወንጌልን እየሰበኩ ብዙ ሕሙማንን ፈወሱ። ከዚኸም በኋላ ከስድስት ወንድሞቻቸው ጋር ተገናኝተው በእግዚአብሔር ተእዛዝ ወደ ጣና መጡ። ሰባቱም ከዋክብት አንድ ላይ የጣናን ባሕር በእግራቸው ጫማ እየጠቀጠቁ ተሻግረው ዳጋ ደሴት ደረሱ። ከእነዚህ ሰባት ከዋክብት በፊት "አትማረኝ" እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባት ቀድመው ወደ ደሴቱ እንደገቡ ታሪካቸው ያስረዳል። አቡነ በትረ ማርያምም በዳጋ ደሴት ምንም ሳይቀምሱ የዐቢይ ጾምን ከጸሙ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ዕጣ ክፍላቸው የሆነችውን ዛሬ ላይ ቤተ መቅደሳቸው የታነጸበትን ደሴት አሳያቸውና "የእስራኤልን ልጆች በሙሴ በትር የኤርትራን ባሕር እንዳሻገርኳቸው አንተንም በያዝካት በትር አሻግርሃለሁ" ካላቸው በኋላ በበትራቸው ባሕሩን ተሻግረው ዘጌ ምድር ደረሱ። በዚያም በአት አበጅተው በጸሎት ተወስነው በተጋድሎ ጸንተው ሲኖሩ ከእግራቸው ሥር ሕሙማንን የሚፈውስ ሙት የሚያስነሣ ዐይነ ሥዉራንን የሚያበራ፣ አጋንንትን የሚያወጣ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት የሚያደርግ ፈዋሽ ጠበል ፈለቀ። ከየቦታው የሚመጡ ሕሙማንም በዚኽ ጠበል በአባታችን እጅ እየተጠመቁ የተፈወሱት በርካቶች ናቸው።
❤ አቡነ በትረ ማርያም በዘጌ ምድር እየተዘዋወሩ ሲያገለግሉ አሁን አዝዋ ማርያም ከምትባለው ቦታ የሥዕል ቤት አድርገው ሲጸልዩ ከንጉሥ ዓምደ ጽዮን የተላኩ መልእክተኞች መጥተው "አባታችን ወዴት ናቸው?" ብለው ሲጠይቁ በቦታው የነበሩ መነኰሳት "እዛ ናቸው" በማለት ስላመለከቱ ቦታዋ በዚያው አዝዋ ተባለች። አባታችን ከዘጌ አናት ተራራ ላይ አራራት ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ሆነው በአራቱም ማዕዘን እየባረኩ የታቦተ ማርያምንና የታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ይዘው "ለኖኅ የሰጠኸውን ቃልኪዳን አትርሳብኝ" በማለት እየባረኩ ይጸልዩ ነበር። ከዚኽም በኋላ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ላይ ሆኖ ተገለጠላቸውና እየመራቸው ጣና ባሕርን ተሻግረው መሐል ዘጌ አደረሳቸው።
❤ ከዚያም "እዚሁ ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን ሥራ" ብሎ በፈረሱ ድንጋዩን ረግጦ እንደሰም አቅልጦ እንደጭቃ ረግጦ የፈረሱን ኮቴ ምስል አስቀመጠላቸው። አቡነ በትረ ማርያም የመሐል ዘጌን ቤተ ክርስቲያን ሲያንጹ ሳንቃዎቹ (መዝጊያዎቹ) በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በነፋስ ተጭነው የመጡ ናቸው። ጻድቁም የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው የጸሎት ልብሳቸውን እርሱም 25 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ከብረት ሰንሰለት የተሠራው ቀሚሳቸውን ለብሰው ወደ ጣና ሐይቅ እየገቡ ጸሎት እያደረጉ ለ23 ዓመታት በእንዲህ ዓይቱ ጽኑ ተጋድሎ ኖረዋል።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
📣በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በትላንትናው ዕለት የሰንበት ትምህርት ቤታችን፲፪ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአስተማሪና አዝናኝ ደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ ከቁጥር ሳያጎድል ያድርሰን አሜን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን #ለቅዱስ_አባት_ወንጌሉ_ዘወርቅ ለተባለ ልክ እንደ ገብረ ክርስቶስ በእናት አባቱ ቤት እንደ ነዳይ ሆኖ ለተጋደለ #ለአባ_ዮሐንስ_ለዕረፍት_በዐል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ወንጌሉ_ዘወርቅ_የተባለው_ቅዱስ_አባት_አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ነበር አባቱም አጥራብዮስ የሚባል ባለጠጋ ነው። የእናቱም ስም ብዱራ ይባላል። እንዲማርም ለመምህር ሰጡት ቅዱሳት መጻሕፍትንም ተማረ።
❤ ከዚህም በኋላ ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራለት ዘንድ አባቱን ለመነው አባቱም እንደፈለገው አሠራለት ሁል ጊዜም ያነበው ነበር። በሚያነብ ጊዜም አባቱና እናቱ ደስ ይላቸው ነበር።
❤ በዚያም ወራት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ መነኵሴ ወደ እነርሱ መጣ በእነርሱም ዘንድ አደረ ከቅዱስ ዮሐንስም ጋራ ተነጋግሮ የምንኵስናን ሥራ አመሰገለት ይህን ዓለም እስከ ናቀና እንደ እርሱ መነኰስ ይሆን ዘንድ እስከ ወደደ ድረስ ልቡን ማረከው። ያን ጊዜም ያ መነኰስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ሁለተኛም ተመልሶ እንደ ልማዱ በእነርሱ ዘንድ አደረ። ቅዱስ ዮሐንስም መነኵሴው ወደ ገዳም ይወስደው ዘንድ ፈለገ መነኵሴውም "አባትህን እፈራዋለሁ ልወስድህ አይቻለኝም" አለው። ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሱ ጋራ እንዲወስደውና ነፍሱን እንዲያድን አማለው።
❤ ከዚህም በኋላ በስውር ወሰደው በመርከብም ተጭነው ያ መነኰስ ወደሚኖርበት ገዳም ደረሱ የገዳሙም አበ ምኔት የወጣቱን ዮሐንስን መልኩን አይቶ አደነቀ። ቅዱስ ዮሐንስም የምንኵስናን ልብስ ያለብሰው ዘንድ አበ ምኔቱን ለመነው አበ ምኔቱም "ልጄ ሆይ የምንኵስና ሕግ እጅግ ጭንቅ ናት እኮ" አለው። አብዝቶም በለመነውና ግድ ባለው ጊዜ ራሱን ላጭቶ አመነኰሰው።
❤ ከዚህም በኋላ ከጾም ከትጋትና ከኀዘን የተነሣ ሥጋው ደርቆ አጥንቶቹ እስከ ሚታዩ ድረስ በብዙ ተጋድሎ ተጸመደ። አም ምኔቱም "ልጄ ሆይ ለሰውነትህ እዘን ድካምህንም ቀንስ መነኰሳቱም ሁሉ እንደሚሠሩት ሥራ" እያለ ያጽናናውና ይመክረው ነበር።
❤ በዚህ ተጋድሎም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ "ከእነርሱ በረከትን ትቀበል ዘንድ ከመሞትህ በፊት ወደ አባትህና እናትህ ሒድ" የሚል ራእይ አየ። ይህንንም ራእይ በሦስት ሌሊቶች ውስጥ አየ ለአበ ምኔቱም እንዴት እንዳየ ነገረው አበ ምኔቱም "ይህ ራእይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ ልትሔድ ይገባሃል" አለው።
❤ ከገዳሙም በወጣ ጊዜ አንድ ምስኪን ሰው ጨርቅ ለብሶ አገኘ። የእርሱንም ልብስ ሰጥቶት ጨርቁን ወሰደ። ወደ አባቱ ቤትም በደረሰ ጊዜ በትንሽ ጎጆ ውስጥ በአባቱ ደጅ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደለ ባሮች ከአባቱ ማዕድ የሚጥሉለትን ፍርፋሪ እየተመገበ ሰባት ዓመት ኖረ። እናቱም በአንጻሩ ስታልፍ የሚከረፋ ሽታው ያስጨንቃት ነበር።
❤ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ "ከሰባት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ትወጣለህ" ብሎ ነገረው። ያን ጊዜም ወደ እናቱ ልኮ ልምናውን ልትሰማ ወደ እርሱ መጣች ልጅዋም እንደሆነ ፈጥኖ አልነገራትም ነገር ግን በዚያች በታናሽ ማደሪያ ውስጥ በላዩ ባለ ጨርቅ እንድትቀብረው የለበሰውንም ጨርቅ እንዳትለውጥ አማላት። ከዚህም በኋላ ያንን የወርቅ ወንጌል ሰጣት። እንዲህም አላት "ይህን መጽሐፍ አንብቡ እኔንም አስቡኝ"።
❤ አባቱም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል አሳየችው ለልጁ ያሠራለት ወንጌል እንደሆነ አወቀ። አባቱና እናቱም ወደ እርሱ ሔደው ስለ ልጃቸው ጠየቁት እርሱም "ከዚህ ጨርቅና ከዚህ ትንሽ ማደሪያዬ ውስጥ በቀር በሌላ እንዳትቀብሩኝ ማሉልኝ" አላቸው። በአማላቸውም ጊዜ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ ገራቸው ያን ጊዜም ጮኹ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ የሮሜ ከተማ ሽማግሎዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበሰቡ ሰባቱ ቀንም ሲፈጸም ቅዱስ ዮሐንስ ሐምሌ 16 ቀን ዐረፈ።
❤ እናቱም መሐላዋን ረስታ አስቀድማ ለሠርጉ ያዘጋጀቻቸውን ያማሩ ልብሶች አውጥታ ገነዘች። በዚያችም ጊዜ ታመመች አባቱ ግን መሐላውን አስታውሶ እነዚያን ያማሩ ልብሶች አስወገደ በጨርቆቹም ገነዙት በዚያ በትንሹ ማድሪያም ውስጥ ቀበሩት ከሥጋውም በሽተኞች የሚፈወሱበት ታላቅ ድኅነት ተገኘ።
❤ ከዚህም በኋላ በስሙ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 16 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለዮሐንስ_ዘወንጌል_ወርቅ_ንዋዩ። ዘአግበረ ሎቱ አቡሁ እምነ ዕበዩ። ወበተጋድሎ ማሰነ ወተወለጠ ራእዩ። እስከ ሰእኑ ጠይቆተ ገጹ ኪያሁ ዘአርእዩ። ወእስከ ሰአልዎ ያውሕድ እምብዙኅ ሥቃዩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 16።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ከመ ነኪር ኮንክዎሙ ለአኃውየ። ወነግድ ለደቂቀ አቡየ ወእምየ። እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዐኒ"። መዝ 68፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 4፥8-15፣ ያዕ 2፥1-10 እና የሐዋ ሥራ 14፥21-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማር 8፥34-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !
ከግ/ደ/ዓ/ቅ/አ/ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የ2016 ዓ/ም የእንኳን አደረሳችሁ የጽ/ቤት መልዕክት
ለአገልግሎት እግዚአብሔር የመረጣችሁ ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ ቤት አባላት በቅድሚያ እንኳን ለ፲፪ የሰንበት ት/ቤታችን የምስረታ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልን በነበረን የዓመታት ቆይታ ሁሉ ምስጋናና ክብር ለአምላካችን ይሁን። በዛሬው ዕለት "ቸር አገልጋይ" በሚል መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሪቃል የምታከብሩ እናንት የፍኖተ ብርሃን አገልጋዮች፤ አገልጋይነት ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ንፁህ መስዋት ነውና ለዚህ ክብር የታጫችሁ ሁሉ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን። ቀጥሎም ቃሉን የሚሰሙ ብፁአን ናቸው እንዲል መፅሃፉ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምታችሁ በሕይወት ለመኖር የተጠራችሁ እናንተ ምስጉን ናችሁ። ሁሉም ዓባል በእያንዳንዱ አገልግሎት ውስጥ የሰ/ት / ቤቱን ዓላማና ዕቅድ ለማሳካት መትጋት እንዳለበት ለማስታወስ እየወደድን ፤ ለትልቅነት የሚሰሩ ሰውን ይገድላሉ ፤ ትልቅ ስራን የሚሰሩ ግን ይሰደባሉ ፤ ይታሰራሉ አልፎም ተርፎም ሞቶ አልቀረም እንጂ ልክ እንደ ክርስቶስ ይገደላሉና በውስጥም ሆነ በውጭ በአገልግሎታችሁ ላይ በሚገጥማችሁ እንቅፋትና ተግዳሮት አንድም ለበጎ ሲቀጥልም ለዋጋ እንደሆነ ማሰብ አንዱ የአገልጋይነት ፀባይ ነው። ውድ የፍኖተ ብርሃን ልጆች "ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ " እንዳለን አምላካችን፤ ክፉ ዓመል መልካሙን ፀባይ ያበላሸዋልና መንፈሳዊነታችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻም ሳይሆን በሄድንበትና ባረፍንበት ቦታ ሁሉ ይሆን ዘንድ የሁል ጊዜ መልዕክታችን ነው።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን፤ መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሆንልን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ምልጃና ፀሎት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን ። አሜን
14/11/2016ዓ.ም
ሰላምታ ሰጥተዋቸው ወደ ፊልጶስ ሀገር ሔዱ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት በቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 15 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ሕሊናክሙ_ቅዱሰ። ዘኢያኅዘነ መንፈሰ። #ጴጥሮስ_ወጳውሎስ ወእደ እግርክሙ ጌሠ። ጽንዐ ኃይልክሙ ሰቀለ ንጉሠ። ወዕበይክሙ አሰገደ አፍራሰ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_15።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወኢያስጠሚኒ ዐውሎ ማይ። ወኢየኀጠኒ ቀላይ። ወኢያብቅዉ አፉሆሙ ዐዘቃተ ላዕልየ"። መዝ 68፥15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥6-15።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "መኑ ይትዔረዮ ለእግዚአብሔር በደመናት። ወመኑ ይመስሎ ለእግዚአብሔር እምደቂቀ አማልክት። እግዚአብሔር ስቡሕ በምክረ ቅዱሳን"። መዝ 88፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 1፥18-26፣ ያዕ 5፥12-17 እና የሐዋ ሥራ 9፥22-30። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 4፥17-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን ለአባቶቻችን #ለቅዱሳን_ሐዋርያት #ለጴጥሮስና_ጳውሎስ_በንጉሥ_ጰራግሞስ_ላይ ተአምራትን ላአደረጉበትና #ዐሥር_ሺህ_ሁለት_መቶ ምዕመናንን በአንድ ጊዜ ላሳመኑበት ለመታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአርባ_አምስት_ሰማዕታት ጋር #ከአባ_ሐርዮንና ተአምራትን ከሚያደርግ ከመስተጋድል #ከመነኰስ_ከፍሬምናጦስ ከመታሰቢያቸው፣ በምስር ስንክሳር እንደ ተጻፈው #ከሕፃኑ_ከቅዱስ_ቂርቆስ_ከሰማዕትነት_ከመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን አባቶቻችን #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ጴጥሮስና_ጳውሎስ በንጉሥ ጰራግሞስ ላይ ተአምር አደረጉ። አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት በኋላ ደመና ነጥቆ ወሰዳቸውና በቤተ መንግሥት አወረዳቸው ንጉሥ ጰራግሞስም በአያቸው ጊዜ ደንግጦ "እናንተ ምንድን ናችሁ" አላቸው። እርሱም "መንግሥታትን ሁሉ የሚያጠፋ የሚሰሙትን ማዳን የሚችል የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሮች ነን" አሉት። ንጉሡም "ነገራቸው ትክክል መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ያደረገላቸውን ድንቆችና ተአምራትን ነገሩት። "የቀኝ ዐይኗን ወፍ ያወጣት አንድ ልጅ አለችኝ እርሷን ካዳናችኋት በአምላካችሁ አምላለሁ" አላቸው "ልጅህን ወደእኛ አምጣ" አሉትና ልጁን ወደ እነርሱ አመጣት። ሐዋርያትም ወደ እግዚአብሔር ጸልየው እጆቻቸውን በአይኗ አኖሩ። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዳነች። ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ አይተው ከሐዋርያት እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በጌታችን እንዳዘዛቸው ወደ አገረ ፊሊጶስ ሔዱ። ሰይጣንም በእንዶር ንጉሥ ተመስሎ አጋንንት በጭፍራ አምሳል አስከትሎ ወደ ንጉሥ ጰራግሞስ መጣ "በሥራያቸው አገርን ሳያጠፉ እኒህን ሁለቱን ሥራየኞች ፈጥነህ የማታጠፋቸው ለምንድነው" አለው።
❤ ንጉሥ ጰራግሞስ ልቡ ወደ ክህደት ተመለሰ። ሐዋርያትም ያመጧቸው ዘንድ ዐሥር ሺህ ጭፍሮችንና ሁለት መቶ ፈረሰኞችን ላከ ጭፍሮችም ሔደው ከተማዋን ከበቧት የከተማው ሰዎች ደንግጠው ለሐዋርያት ነገሩዋቸው። ሐዋርያትም ከከተማው ወጥተው በጭፍሮቹ ፊት ቁመው ርዳታን ይልክላቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለዩ።
❤ ያንጊዜም የጭፍሮቹ ፈረሶች ወደ ሐዋርያት ተመለሱ እግሮቻቸውንም አስተካክለው ተንበርክከው ሰገዱ እንደሚያለቅስም በቃጪን ድምጽ ጮኩ። ከፈረሶችም አንዱ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ እንደ ሰው ተናገረ "እናንት ሰነፎች የጰራግሞስ ጭፍሮች ክብር ይግባውና የክርስቶስን ጭፍሮች ጴጥሮስንና ጳውሎስን ለምን ትፈልጓቸዋላቸሁ ሥራየኞችስ ለምን ትሏቸዋላችሁ እነርሱ ግን ሥራይንና የሰይጣንን ሥራ ሁሉ ሊያጠፉ መጥተዋል። ክብር ይግባውና ከንጉሣቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው አታዩአቸውምን ለክብር ንጉሥ ለክርስቶስ ጭፍሮቹ ትሆኑ ዘንድ ስሞቻችሁም በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍ ዘንድ ስለ እናንተ ይለምናሉ። እኛ እንኳ እንስሳ ስንሆን ለአምላካችው እንሰግዳለ"ን ፈረሱም ይህንን ተናግሮ ዝም አለ።
❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ተሰማ "ሐዋርያቶቼ ሆይ ሐዲሶች አትክልቶችን ቸለል አትበሏቸው"። ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ዐይኖቻቸውን ቀና አድርገው በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ሲዐርግ ጌታችንን አዩት እነዚያም ዐሥር ሺህ ሁለት መቶ ጭፍሮች ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ለሐዋርያትም ተገዙላቸው።
❤ ሐዋርያትም የምድራዊ ንጉሥ ጭፍራ መሆንን እንዲተዉ ፈረሶቹንና የጦር መሣሪያውንም እንዲመልሱለት ክብር ይግባውና በክርስቶስ በግልጥ እንዲአምኑ አዘዟቸው። እነዚያ ጭፍሮቹም ወደ ንጉሣቸው ጰራግሞስ ሔደው በፊቱ ቆሙ "ታመጧቸው ዘንድ የላክኋችሁ እነዚያ ሁለት ባለ ሥራዮት ወዴት አሉ" አላቸው። "የልጅህን ዐይኗን በማዳን በጎ በሠሩልህ ፈንታ ለምን በክፋት ትፈልጋቸዋለህ" አሉት። ከዚህም ጥሩራቸውንና ትጥቃቸውን ፈትተው "ገንዘብህን ውሰድ እኛ ግን ከአንተ የተሻለ ንጉሥ አግኝተናል ይኸውም የቅዱሳን ጴጥሮስና የጳውሎስ አምላክ ነው" ብለው ከፊቱ ጣሉለት። በሰማ ጊዜም ደነገጠ ተቆጥቶም እስከሚገድላቸው ድረስ በወህኒ ቤት ይጨምሯቸው ዘንደ አዘዘ።
❤ ከዚህ በኋላም ራሱ ይይዛቸው ዘንድ ተዘጋጀ የጦር መሣሪያውንም አዘጋጀ ወደ ፊልጶስ አገር ሔደው እስከ መሠረቷ ያጠፏት ዘንድ ሃያ ሺህ አራት መቶ እግረኞች ጭፍሮችን አዘዛቸው። ቅድስ ጴጥሮስም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ አለው። "ወንድሜ ሆይ አገርን እንዳያጠፋ ሳይወጣ ወደ ጰራግሞስ ተነሥ እንሒድ" አለው ከዚህም በኋላ ጸሎትን ጸለዩ ወጥተውም በደመና ተጫኑ በቤተ መንግሥት መካከልም አወረዳቸውና በጰራግሞስ ፊት ቆሙ እንዲህም አሉት "እነሆ እኛ በፊትህ ነን ስለ እኛ አገርን አታጥፋ"። ያን ጊዜም ጭፍሮች እንዲመለሱ አዘዘ።
❤ ሐዋርያትንም እንዲህ አላቸው "አገሩን ሁሉ በሥራይ የምታጠፉ ሥራየኞች አናንተ ናችሁን" እነርሱም "ይህ ሥራ ለእኛ አይገባም" አሉት። ሁለተኛም "ኃጢአታችሁ ነው ወደዚህ ያመጣችሁ" አላቸው። ችንካር ያላቸው ሁለት የራስ ቁሮችን ከብረት እንዲሠሩ አቃቂርንም እንዲመሉአቸው በእሳትም አግለው በሐዋርያት ራስ ላይ እንዲደፉአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ያን ጊዜም ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ ጸለየ "አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ የጌትነትህን ኃይል በጰራግሞስ ላይ ግለጽ"። ያን ጊዜም ጰራግሞስ ከወገኖቹ ሁሉ ጋር በነፋስ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ። በዚያን ጊዜም "ጌቶቼ ሆይ ይቅር በሉኝ ከዚህ ፆዕርም አድኑኝ" እያለ ጮኸ "የእንዶር ንጉሥ አስቶኛልና የተረገመ ይሁን በእናንተም ላይ ክፉ የሚናገር ሁሉ የተረገመ ይሁን" አለ። ቅዱስ ጴጥሮስም "የታሠሩትን ጭፍሮች ይፈቷቸው ዘንድ እስከምታዝ ከዚህ ስቅላት አትወርድም" አለው እርሱም ወደ ልጁ ወደ ሎይ ተጣርቶ ትፈታቸው ዘንድ አዘዛት እርሷም አንዳዘዛት ፈታቻችው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም ዳግምኛ አለው "አሁንም ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም በምድር ላይም እንደእኔ ያለ ርኩስ የለም ብለህ ካልጻፍህ አትወርድም ይህችንም በከተማው መካከል ያነቧት ዘንድ ታዝዛለህ"። ንጉሡም ወረቀትንና ቀለምን ታቀብለው ዘንድ ወደ ልጁ ተጣራ እርሷ ብቻዋን ከስቅላት ቀርታ ነበርና ባመጣችለትም ጊዜ ቊልቊል ተሰቅሎ እያለ ጻፈ በከተማውም መካከል ያነቧት ዘንድ ላካት።
❤ ያን ገዜም ጰራግሞስንና ወገኖቹን አወረዷቸው ወደ ሐዋርያትም መጥተው ከእግራቸው በታች ሰገዱላቸው ንጉሡም "ጌቶቼ ይቅር በሉኝ እኔ በአምላካችሁ አምናለሁ" አለ ሕዝቡም ሁሉ ሕያው በሆነ አምላካችሁ እናምናለን እያሉ ከሐዋርያት እግር በታች ወድቀዉ ሰገዱ።
❤ እነርሱም ሃይማኖትን አስተምረው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው ጭፍሮችንም አጠመቋቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን አንድ ሆኑ። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ከአዋቂዎቻቸውም ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾሙላቸው። ነገረ ምሥጢርንም እያስገነዘቡአቸው በእነርሱ ዘንድ ኖሩ። ሃይማኖታቸውንም ይጸና ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰጧቸው። እንዲህም አሏቸው "በሃይማኖታችሁ ጽኑ እኛ ካስተማርናችሁ ትምህርት አትናወጹ ወደ እናንተም እንመለሳለን"። ከዚህም በኋላ
