ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر607
مشترکین
-124 ساعت
-47 روز
-1230 روز
آرشیو پست ها
🌼 መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
🌼 ከዚህ በኋላ ንጉሡ "መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!" ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን ጽረ ገጽ የተወሰደ።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አድኅነኒ አግዚኦ ወተሠሃለኒ። እስመ በርዕቱ ቆመ እገርየ። በማኅበረ እባርከከ እግዚኦ። መዝ 25፥16-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥15-25።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥3-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥17-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም (የብዙኀን ማርያም) በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፳፩ (21) ቀን።
🌼እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል #በግሸን_በመስቀለኛው_ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ #ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ሃይማኖታዊ_ውሳኔ ለመወሰን፤ #በኒቅያ_ጉባኤ_አርዮስን_ለማውገዝ ከሩቅ #ለተሰባሰቡበት_ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ፦ ሃሌ ሉያ "ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት እንተ ኀሠሥዋ ወዖድዋ #ነቢያት ወይቤሎ #ለኖህ_አመ_አይህ ግበር ታቦተ በዘትድኅን እትአመን ባቲ እስመ #አርአያ_መስቀል_ይእቲ_አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ። ትርጉም፦ ያች መድኃኒት ማን ናት #ነቢያት_የፈለጓት የዞርዋት በጥፋት ጊዜ #ለኖህ አለው የምትድንበት ታቦት ሥራ በእርሷ አርአያ መስቀል ናትና እክሊል ተቀዳጅታ ትመላለሳለች።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_ዓራራይ (እግ. ነግ) #እዝል_ዜማ፦ "ሠለስቱ ምዕት ወሠርቱ ወሰመንቱ ኤጲስ ቆጶሳት ርቱዓነ ሃይማኖት እለ መሀሩ በስሙ በዕፀ መስቀሉ በውስተ ማኅበሮሙ ለቅዱሳን"። ትርጉም፦ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ኤጲስ ቆጶሳት ሃይማኖታቸው የቀና በስሙ በዕፀ መስቀሉ በቅዱሳን ማኅበር ያስተምሩ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
🌼 #ብዙኃን_ማርያም፦ በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል "ብዙኃን ማርያም" በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ለጉባኤ ኒቅያ ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤
✝ ✝ ✝
🌼 #ጉባዔ_ኒቅያ፦ በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መ*ና*ፍ*ቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ "አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!" የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
🌼 በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
🌼 ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
🌼 ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
✝ ✝ ✝
🌼 #ዕፀ_መስቀል፦ በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
🌼 ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
🌼 ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስከረም ፳፩በዚችም ቀን ቅዱስ ቆጵርያኖስና፤ ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት አረፉ። ቅዱስ ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሃዲና ሥራየኛ ነበር። በሥራዩም የሚበልጠው ካለ ሊማር ከሌለ ግን በእነርሱ ላይ ሊመካባቸው ወደ አንጾኪያ አገር ሔደ። በዚያም አንድ ጎልማሳ ነበረ። ላይዋ የሚያምር አንዲትን ድንግል ብላቴና ወደ ቤተ ክርስቲያን በምትሄድ ግዜ እያያት በእርሷ ፍቅር ልቡ እንደ እሳት ተቃጠለ በገንዘብ፣ በማስፈራራት፣ በስራይ ስራም ሊያገኛት አልተቻለውም። ጎልማሳውም ለቆጵርያኖስ ነገረው እርሱም ዮስቴናን እንዲያመጡለት አጋንንትን ላካቸው ከጸሎቷ የተነሳ ወደእርሱ ሊያመጧት አልቻሉም። ቆጵርያኖስም አጋንንቱን ድንግል ዮስቴናን ካላመጣችሁልኝ ክርስቲያን እሆናለው አላቸው። በዚሕም ጊዜ አንዱ ሰይጣን ዮስቴናን ተመስሎ ለቆጵርያኖስ ታየው። ቆጵርያኖስም እውነት መስሎት በደስታ የሴቶች እመቤት ዮስቴና መምጣትሽ መልካም ሆነ አለ። ስሟን በጠራ ጊዜም በእርሷ አምሳል የተመሰለው ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ። በዚሕ ጊዜ በልቡ ስሟን በጠሩበት ቦታ እንደጢስ የሚበተኑ ከሆነ በፊቷ ሊቆሙ እንዴት ይቻላቸዋል ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠለ። ከዚሕም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቆ የምንኩስና ልብስን ለበሰ። ዲቁና ዳግመኛም ቅስና ተሾመ። ቅድስት ዮስቴናንም ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት። በኋላም ከሀዲው ንጉስ ዳኬዎስ ስለእነርሱ ሰማ፤ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖቶቹ እንዲሰግዱ አዘዛቸው ትዕዛዙን ባልሰሙ ጊዜ ብዙ ሥቃይን አሠቃያቸው። በኋላም የቅዱስ ቆጵርያኖስን የቅድስት ዮስቴናን እራሳቸውን አስቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። በረከታቸው ይደርብን! አሜን
🌼"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፲፱ (19) ቀን።
🌼 እንኳ #ለኢትዮጵያ_ንጉሥ_ለናዖድ_ልጅ ለከበረችና ለተባረከች #ለቅድስት_ሮማነ_ወርቅ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ #ለከበረ_ለመስቀል_ለበዓሉ መታሰቢያ፣ ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት ለሆነ #ለአርማንያ_ሊቀ_ጳጳሳት #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ከዐዘቅት_ለወጣበት ለመታሰቢያ ቀን በዓልና በሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ዘመነ ለሆነ #ለከበረ_ለገዳማዊ_ቂርቆስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #በዚችም_ቀን_ደግሞ_የከበረ_መስቀል_የበዓሉ መታሰቢያ ነው በተገኘ ጊዜ ሦስት ቀኖች ያህል በፍጹም ደስታ በዓልን አድርገውለት ነበርና እኛም እንዲሁ በታላቅ ደስታ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ድኅነታችን በእርሱ ተደርጎልናልና።
🌼 በመስቀሉ ለአዳነን ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን ሁላችንን የሐዋርያት የሆነች የከበረች የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለእኛ የተቀበለውን መከራውን የምናስበውን በባለሟልነትና በፍቅሩ ወደእርሱ ያቅርበን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌼 #በዚችም_ቀን_የኢትዮጵያ_ንጉሥ_የናዖድ_ልጅ የከበረችና #የተባረከች_ሮማነ_ወርቅ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። እርሷም መጾምና መጸለይን የምትወድ ድኆችንና ችግረኞችን የምትጎበኝ ነበረች እግዚአብሔር በቅድስት ሮማነ ወርቅ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የአርማንያ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት_አቡነ_ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት (ጉድጉድ) መውጣቱ፦ ይህም በንጉሥ ድርጣድስ ዘመን በአርማንያ አገር ራሱን ባሪያ አድርጎ ይኖር ነበር። ይህም ንጉሥ ከሀዲ ነበርና ዕጣን ሊዐሳርግ ወደ ጣዖቱ ቤት ሲገባ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጠርቶ ለአማልክት ዕጣን እንዲአሳርግ አዘዘው። ቅዱሱ ግን የንጉሡን ትእዛዝ አልሰማም ስለዚህም እጅግ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ከዚህም በኃላ ጥልቅ ከሆነ ጉድጓድ ውስጥ ጣለው በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ።
🌼 በንጉሡ አዳራሽ አቅራቢያም አንዲት አሮጊት ነበረች እርሷም "እንጀራ እየጋገርሽ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በውስጡ ከአለበት ጉድጓድ ሁል ጊዜ ጣይለት" የሚላትን ራእይ አየች። ይችም አሮጊት እንዲህ እያደረገች እንጀራንም እየጣለችለት እስከ ዐሥራ አምስት ዓመት ፍጻሜ ኖረች።
🌼 በዚያም ወራት ይህ ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሎችንና ቅድስት አርሴማን ገድሎ ሥጋቸውም በተራራ ላይ ተጣለ። ሰይጣንም በንጉሥ ድርጣድስ ላይ ተጫነ እግዚአብሔርም የተፈጥሮ መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች ብዙዎቹን ሰይጣን ተጫነባቸው በቤተ መንግሥት ውስጥ ታላቅ ኀዘንና ጭንቀት ሆነ።
🌼 የንጉሡ እኅት ግን በሌሊት ራእይ "ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ ውስጥ ካላወጣችሁት አለዚያ አትድኑም" እንደሚላት ሰውን አየች ለወገኖቿም ነገረቻቸውና እንርሱም ሒደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን ከጎድጓድ አወጡት በዚያን ጊዜም ቅዱሳት ደናግልን ሥጋቸውን ገንዞ በመልካም ቦታ አኖራቸው ከዚያም በኋላ ንጉሡንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም ረወሳቸው። ዜናውም ሁሉ በዕረፍቱ ታኅሣሥ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል።
🌼 ገዳማዊው ቅዱስ ቂርቆስ፦ ይህም ቅዱስ ሰው ከከሀዲው ንጉሥ ከመርቅያን በሸሸ ጊዜ በከፍተኛ ተራራ ላይ በብቸኛነት ተቀመጠ በውስጡም አራዊት የኖሩበታል ምግቡንም ከእግዚአብሔር ለመነ አጋዘንም በየሦስት ቀን ወደርሱ እንድትመጣ ወተቷንም እንዲጠጣ አዘዘለት በእንዲህ ያለ ሥራም ዐሥር ዓመታት ኖረ።
🌼 የተረገመ ሰይጣን ግን በተጋድሎው በቀና ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ፈተና ሊፈትነው ጀመረ ያስፈራው ዘንድ በጥቁር ባሪያ አምሳል የሚመጣበት ጊዜ አለ ደግሞም በብዙ ሠራዊትና በፈረሰኞች አምሳል ሁነው ይዘው ያሥሩታል በጅራፍም ገርፈው በእግሮቹ ይጎትቱታል ሰይጣናት እንደሆኑ በአወቀ ጊዜ በመስቀል ምልክት በላያቸው ሲአማትብ ያን ጊዜ ሸሹ።
🌼 በአንዲትም ዕለት በሌሊት ሲሰግድ በታላቅ ከይሱ አምሳል በአንገቱ ላይ ተንጠለጠለና በፊቱ ውስጥ ሊተነፍስበት ፈለገ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ርዳታን ለመነ መልአኩን ልኮ አዳነው።
🌼 የዕረፍቱም ጊዜ ሲቀርብ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ሒዶ ሥራውን ሁሉ ነገረው ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመለሰ ሊቀ ጳጳሳቱም መገነዣውን እንዲያዘጋጁ ሦስት ኤጲስቆጶሳትን ወደርሱ ላከ ወደ በዓቱም በሔዱ ጊዜ ታሞ አገኙት ነፍሱም ከሥጋው በምትወጣ ጊዜ ለመነገር የማይቻል ታላቅ ክብርን ተመለከቱ በበዓቱም ውስጥ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በገዳማዊው ቅዱስ ቂርቆስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 19 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌼 "#ሰላም_ለቂርቆስ_ለነቢረ_ገዳም ዘአፍቀራ ይሰቲ ሐሊበ ቶራ። ድኅረ አመከሮ ሰይጣን በዘዚአሁ መከራ። አዕይንቲሆሙ ለኤጲስቆጶሳት ነጸራ። በጊዜ ዕረፍቱ ዘኮነ ነከራ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_19።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተመየጥከኒ ወአሕየውከኒ። ወእምቀላየ ምድር አውፃእከኒ። ወአብዛኅኮ ለጽድቅከ"። መዝ 70፥20፥21። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ጴጥ 5፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 10፥9-24። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥9-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት ሮማነ ወርቅ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
በነገው ዕለት ማለትም በ19/01/2017 ዓ.ም አጠር ያለ ጠቅላላ ጉባኤ ስለሚኖር ሁላችንም ከ08:00 ሰዓት እንድንገናኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን ለወንድም ለእቶቻችንም መልዕክቱን እናጋራ።
መልካም ቀን
🌼 ይህ የአቡነ አኖሬዎስ ገዳም ደሴ ዙሪያ በጽጋጋ የሚገኝ ሲሆን ከደሴ ወደ መካነ ሰላም በሚወስደው መንገድ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ የተመሠረተው በ1317 ዓ.ም በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ አቡነ አኖሬዎስ በጽጋጋ ገዳማቸው እያሉ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር ተታሎ የአባቱን ሚስት በማግባቱ ጻድቁ እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ንጉሡን ስለገሠጹት ታስረው ወደ ወለቃ ተጋዙ፡፡ ንጉሡ ሲሞት ሠይፈ አርዕድ ነግሦ የተጋዙት በሙሉ እንዲመለሱ ስላወጀ አቡነ አኖሬዎስም ወደ በዓታቸው ጽጋጋ ተመለሱ፡፡ አቡነ አኖሪዎስ በነገሥታቱ ፊት ቆመው የወንጌልን ሕግ በመመስከራቸው እየታሰሩ ምድረ ጸወን ወደምትባል አገር (ይህውም ደቡብ ወሎ ቦረና የምትገኝ ናት) እንዲሁም ዝዋይ ደሴ ገማስቄ ግድሞ (ባሌ አካባቢ) ወደ ተባለው አገር ተጋዙ፡፡ ለብዙ ዓመታት ገዳም መሥርተው ቆይተው ወደ ጥንት በዓታቸው ተመልሰው ጽጋጋ መጥተው በገዳማቸው ብዙ ተጋድለው በ1471ዓ.ም በዚሁ በጽጋጋ ገዳማቸው ነው ያረፉት፡፡
🌼 በኋላም ወደ አሩሲ በመሄድ ኢስላሞችን አስተምረዋል፡፡ ብዙ ተአምራት ያደረጉላቸው ሲሆን መንደራቸውንም ያማረ መንደር ብለው ሰይመውላቸዋል፡፡ የአሩሲ ኢስላሞች እጅግ ያከብሯቸውና ይወዷቸው ነበር። ከአክብሮታቸውም የተነሣ አቡነ አኖሬዎስን "ኑር ሁሴን" እያሉ ይጠሯቸው ነበር፡፡ ጻድቁ በአሩሲ ቆመው የጸለዩበት ቦታ ዛሬም ድረስ ተከብሮ ይኖራል፣ ሶፍ ዑመር ዋሻ ተብሎ የሚጠራው ታሪካዊ ዋሻ የአቡነ አኖርዮስ በዓት መሆኑ በታሪክ የሚታወቅ ሐቅ ነው፣ ይህም በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ጻድቁ በኢቲሳ 21 ዓመት ቆመው ሲጸልዩ ብርሃን ተተክሎ ይታይ ነበር፡፡ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ መስከረም 18 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ከአቡነ አኖርዮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!።
✝ ✝ ✝
🌼
"#ሰላም_ዕብል_ለዘረከብከ_ሞገስ። ምስለ ፈጣሪ ትትናገር ሱባዔያተ ሠላሰ። ኤዎስጣቴዎስ ዘሦጥከ ዲበ በድነ ሕፃን ነፍሰ። ጊዜ ዐደውከ ማዕበላተ ዘአልቦ አርማሰ። #በዘባነ_ባሕር እንዘ ትሰፍሕ ልብሰ"።
✝ ✝ ✝
🌼 "#ሰላም_ለከ_ለዘነሣእከ_ኃይሎ። ለመንፈስ ቅዱስ ምሕራመ አጋንንት በአሰስሎ። ዘበእንቲአከ ቃል ለተክለ ሃይማኖት ይቤሎ። አመ ተኀብአ አምኔከ ወአመ ሥውረ ሁሎ። ተረፈ ጣዖታት ያጠፍእ #አኖሬዎስ_ኵሎ"። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_18።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፲፰ (18) ቀን።
🌼 እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ወደ አርማንያ አገር ሲሆዱ ኢያሪኮ ባሕር በአጽፍቸው እንጀልባ አድርገው ለተሻገኑ #ለከፍሌ_ባሕር #ለአቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ለዕረፍት_በዓል፣ አሁን ሶፍ ዑመር ዋሻ እየተባለ የሚጠራው የጸሎት በዓታቸው ለነበረ #ለጽጋግ_መምህር_ለአቡነ_አኖሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #ከፋሌ_ባህር_አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ክርስቶስ ሞዓ የእናቱ ስም ስነ ሕይወት ይባላል ሁለቱም ደጋጎች እግዙአብሔርን የሚፈሩና በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ነበሩ ።
🌼 ከዘህም በኋላ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ይህን ቅዱስ ወለዱት ስሙን የጌታ ጥብቅ ብለው ሰየሙት። በአደገም ጊዜ የዳዊትን መዝሙርና የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን አስተማሩት።
🌼 ከዚህም በኋላ የእናቱ ወንድም አባ ዘካርያስ ወደአለበት የመነኰሳት ገዳም ወሰዱት። አባ ዘካርያስም የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዳደረችበት አውቆ የምንኵስናን ሥርዓት አስተምሮ የመላእክትን አስኬማ አለበሰው። ከገድሉ ጽናት የተነሣ በገዳም ያሉ አረጋውያን እስኪያደንቁ ድረስ በጾም በጸሎት የተጠመደ ሆነ እርሱ በጥበብና በዕውቀት የጸና ነውና። ከጥቂት ጊዜ በኋላም ዲቁና ተሾመ የዲያቆናት አለቃ እንደሆነ እስጢፋኖስም ለቤተ ክርስቲያን አገለገለ ።
🌼 ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን ሚካኤልና ከገብርኤል ጋር ተገለጠለትና ሰላምታ ሰጠው በንፍሐትም መንፈስ ቅዱስን አሳደበረት እንዲህም አለው "ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ እኔ ከእናትህ ማሕፀን መረጥኩህ ያለ ፍርሀትና ድንጋፄ ወንጌልን ለብዙዎች ሕዝቦች ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን ያልሰማ እኔን አልሰማም" ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ ።
🌼 ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስም ወደ ጳጳስ ሒዶ ቅስና ተሾመ የወንጌልንም ሃይማኖት ይሰብክ ዘንድ ጀመረ ብዙ ሰዎች ወደ ርሱ እስቲሰበሰቡ ድረስ በእርሱም እጅ መንኵሰው ደቀ መዛሙርትን ሆኑት ከእርሳቸውም ታላቁ አባ አብሳዲ ነው። ብዙዎችንም የከፋች ሥራቸውን አስትቶ ከክህደታቸው መለሳቸው ትምህርቱም በሀገሩ ሁሉ ደረሰ በመላ ዘመኑም የሰንበታትና የበዓላት አከባበር የጸና ሁኖ ተሠራ ከሐዋርያትም ሕግና ሥርዓት ወደቀኝም ሆነ ወደ ግራ ሁሉም ፈቀቅ አላሉም ።
🌼 ወደ ኢየሩሳሌምም ሁለት ጊዜ ሔደ እግዚአብሔርም በእጆቹ የዕውራንን ዐይኖች በማብራት፣ አንካሶችንና ጎባጦችን በማቅናት፣ አጋንንትን በማስወጣት ቁጥር የሌላቸው ተአምራትን አደረገ ።
🌼 ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለመሔድ በአሰበ ጊዜ ልጆቹን ሰብስቦ የመነኰሳትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ከመናፍቃንም ጋር እንዳይቀላቀሉ አማፀናቸው። ልጁ አብሳዲንም በእነርሱ ላይ ሾመውና ወደ ኢየሩሳሌም ሰንበትን እያከበረና የክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ሔደ። ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚንም ደርሶ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለ የሃይማኖትንም ነገር ተነጋገሩ ዳግመኛም ከከበሩ ቦታዎች በመሳለም በረከትን ተቀበለ በዮርዳኖስም ተጠመቀ ።
🌼 ከዚያም ወደ አርማንያ ሔደ ወደ ኢያሪኮ ባሕርም ሲደርስ በመርከባቸው ያሳፍሩት ዘንድ መርከበኞችን ለመናቸው በከለከሉትም ጊዜ ዓጽፉን በባሕሩ ላይ ዘረጋ በቅድስት ሥላሴ ስም በላዩ ባረከ ራሱንም በመስቀል ምልክት አማተበ እንደ መርከብም ሁኖለት በላዩ ተጫነ ሁለት መላእክትም ቀዛፊዎች ጌታችንም እንደ ሊቀ ሐመር ሆኑለት። ከባሕሩም ግርማ የተነሣ እንዳይፈሩ ልጆቹን አጽናናቸው። ግን እንዲህ አላቸው "ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ ለኔ ግን ከእናንተ አንዱ አንደ ሚጠፋ ይመስለኛል" ይህን ሲናገር ልቡ የቂም የበቀል ማከማቻ ስለሆነ ወዲያውኑ አንዱ ከእነርሱ መካከል ሠጠመ ።
🌼 በእግዚአብሔርም ፈቃድ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አርማንያ ከተማ ደርሶ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ተገናኘ ሰገደለትም ከእርሱም ቡራኬን ተቀበለ ሊቀ ጳጳሱም በአየው ጊዜ ታላቅ ደስታን ደስ አለው በፍቅርም ተቀበለው። አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ሁሉም በትምህርቱ አንድ እስከሆኑ ድረስ የአርማንያን ሰዎች ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው የሠሩትን ሥርዓት እያስተማራቸው ኖረ ።
🌼 ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳንን ሰጠው ። በዐረፈም ጊዜ ጳጳሳትና ካህናት በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገለጡ።
✝ ✝ ✝
🌼 #አቡነ_አኖሬዎስ_ትልቁ፦ አባታቸው ዘርዐ ሃይማኖት ወይም ዘርዐ አብርሃም እናታቸው ደግሞ ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ አቡነ አኖሬዎስ ታላቁ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ዜና ማርቆስና አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር እነዚህ ሁሉም የወንድማማቾች ልጆች ናቸው፡፡
🌼 እነኚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናትም የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው፡፡ ማለትም የአኖሬዎስ ታላቁ እናት ክርስቶስ ዘመዳ፣ የሕፃን ሞዐ እናት ትቤ ጽዮን፣ የንጉሡ የዐፄ ይኩኖ አምላክና የማርያም ዘመዳ እናት እምነ ጽዮን እኅትማማቾች ናቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ እኅትማማቾች (እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ) መድኃኒነ እግዚእ የሚባል አንድ ወንድም አላቸው፡፡ እርሱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት የቅድስት እግዚእ ኀረያ አባት ነው፡፡ ማርያም ዘመዳም አቡነ ዜና ማርቆስንና ማርያም ክብራን ወልዳለች፡፡ ማርያም ክብራም ትንሹን አኖሬዎስን ወልዳለች፡፡ ታላቁ አቡነ አኖሬዎስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ ወደ ትግራይ በመሄድ ፀዓዳ ዓንባ ከተባለ ቦታ ገዳም መሥርተዋል፡፡
🌼 ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት "ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ" ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል፣ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያን መርጠው ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው ለሐዋርያዊ ተልእኮ ተሠማሩ፡፡
🌼 እነዚህ ዐሥራ ሁለቱን ንቡራነ ዕድ ለስብከተ ወንጌል በመላዋ አገሪቱ ሲሠማሩ ለአቡነ አኖሬዎስ እንደ ግብጦን የተባለ ቦታ ደረሳቸው፡፡ ይህም ቦታ ከግንደ በረት እስከ ባሌ ያለውን አገር ያካትታል፡፡ እርሳቸውም ሰባት ታቦታት ይዘው በመሄድ አብያተ ክርስቲያናት ተክለው ክርስትናን አስፋፍተዋል፡፡ በአካባቢው ስብከተ ወንጌልን ካስፋፉ በኋላ ባርጋባን የተባለ የአካባቢው ሰው ተአምራታቸውንና ትምህርታቸውን ተመልክቶ በጽጋጋ ገዳም እንዲመሠርቱ ስለነገራቸው አቡነ አኖሬዎስ በጽጋጋ ገዳም መሥርተዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባታዊ መልእክት
“አስመ ነገረ መስቀሉሰ ዕበድ ውእቱ በኀበ ኅጉላን ወበኀቤነሰ ለእለ ድኅነ ኃይለ አግዚአብሔር ውአቱ፤
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው፤ ሰኛ ለምንድን ግን የአግዚአብሔር ኃይል ነው"
1ቆሮ.1÷8
በመስቀሉ ኃይል ከፍዳ ኃጢአት ያዳነን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት በዓለ ቅዱስ መስቀል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ጌታችን በዚህ ዓለም በተገለጸበት ዘመን የግሪካውያን ፍልስፍና ሰፊ ስፍራ አግኝቶ በመካከለኛው ምሥራቅ በሰሜን አፍሪካና በአውሮፓ የተስፋፋበት ዘመን ነበር፣ የግሪካውያን ባህልና ፍልስፍና የተመሠረተው በግዙፉ ቁስ ላይ እንደመሆኑ በግዙፉ መሳሪያ ላይ የሚተማመን ነበረ፤ ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ሥር ሰዶ በነበረበት ጊዜ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈሳዊ ኃይል በዚህ ዓለም ተገለጠ።
ጌታችን በሰው መካከል ተገኝቶ አጋንንትን ወደ ጥልቁ ሲያስምጥ፣ ልዩ ልዩ በሽታና ደዌ ያላቸውን ሲያድን፤ ሙታንን ሲያነሣ፤ ብዙ ተአምራትንና አስደናቂ ነገሮችን ሲያሳይ በመንፈሳዊ ኃይል እንጂ በቁሳዊ ኃይል አልነበረም፤ በመሆኑም በወቅቱ በዓለም ውስጥ ቁሳዊ ኃይልና መንፈሳዊ ኃይል ተብለው የሚታወቁ እነዚህ ሁለት ኃይላት እርስ በርስ ይጋጩ ነበር።
ዓለም በቁሳዊ ኃይል ተማምኖ በጉልበት የሚያደቀውን በመሳሪያ የሚቀጠቅጠውን ሲሻ፤ መንፈሳዊው ኃይል ደግሞ ከቍሳዊ ኃይል በላይ የሆነውን መለኮታዊ ኃይል በመጠቀም የሰውን ሁለንተና ሕይወት ለማዳን ይሰራ ነበር፤ እነዚህ ኃይሎች ከሥር መሠረቱ አነሣሣቸው፣ አመጣጣቸውና የኋላ ጀርባቸው የተለያየ በመሆኑ የሚጣጣሙ አልነበሩም፣ በዚህ ዓለም ጥበብ ወይም ፍልስፍና የሚተማመኑቱ ግሪካውያን የመስቀሉን ቃል ሲሰሙ እንደ ሞኝነትም እንደ ድክመትም አድርገው ይመለከቱ ነበር።
ወልደ እግዚአብሔር በሥጋ በዚህ ዓለም ተገለጠ፤ በለበሰው ሥጋም በኛ ፈንታ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ ሞተ፤ በሞቱም እኛን ከረቂቁ ፍዳ ኃጢአት አዳነን የሚለውን የመስቀሉ ቃል ወይም አስተምህሮ ቁሳውያን እንደሞኝነትም እንደ ደካማነትም በመመልከታቸው ለጊዜውም ቢሆን የመስቀሉ ቃል ጠጥሮአቸዋል፡፡
ይህም በመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመስቀሉ ቃል ሞኝነት መስሎ ለሚታያቸው የመጨረሻ ዕድላቸው መጥፋት ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ የመስቀሉ ቃል ሰውን ለማዳን የተደረገ የእግዚብሔር ኃይል እንደሆነ አምነው ለሚቀበሉና ለሚኖሩበት የመጨረሻ ዕድላቸው መዳን ነው በማለት የሁለቱም ዕድል አነጻጽሮ ይገልጻል የቍሳውያን ግንዛቤ በቍሳዊው ዓለም የተገደበ ስለሆነ ስለ መንፈሳዊው ዓለም የሚያውቁት ባለመኖሩና ለማወቅም ተነሳሽነቱ በማነሱ፣ በሌላም በኩል መንፈሳውያን ደግሞ ከቍሳዊው ዓለም ባለፈ መንፈሳዊው ዓለም መኖሩና ዘላቂና ወሳኝ ኃይልም ያለው መንፈሳዊው ዘንድ ነው ስለሆነም ሰው በቊሳዊ ኃይል ሳይሆን በመንፈሳዊ ኃይል ዘላቂ ድኅነትን ያገኛል ብለው በማስተማራቸው ልዩነቱ ተፈጥሮአል።
ከዚህ አንጻር የችግሩ ዋና ማጠንጠኛ የመንፈሳዊው ኃይል መኖርና አለመኖር ማወቅ ወይም ማመንና አለማመን ነበረ፤ ይህ እሳቤ ዛሬም ሳይቀር የዓለምን እሳቤ እንደሰነጠቀ ነው፤ ይሁን እንጂ በንጹህ ኅሊና በቅን ስብእና እንደዚሁም በጥልቅ አእምሮ ለሚያስተውለው ሰው፤ ሓቁ ብዙም የራቀና የረቀቀ አይደለም፤ ምክንያቱም ዓለም እየተመራ ያለው በሚታየው ግዙፍና ደካማ ቊስ ሳይሆን በማይታየውና በረቂቁ መንፈሳዊ ኃይል እንደሆነ ሥነ ፍጥረት ይመሰክራልና ነው።
በዓለማችን ለሚከናወኑት ቊሳዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሙሉ መልስ ያለው መንፈሳዊው ኃይል እንጂ ቍሳዊው ኃይል አይደለም፤ እንዳልሆነም ኅሊናችን ይመስክርልናል፡፡
ዛሬ በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ በዓል የምናከብረው የቅዱስ መስቀል በዓልም ከዚህ በላይ የጠቀስነው የሁለቱ አካላት ግጭት የፈጠረው ክሥተት ነው፣ መንፈሳዊው ሰው ከመስቀሉ በቀር ከፍዳ ኃጢአት እድንበታለሁ የምለው ሌላ ትምክህት የለኝም ብሎ የመስቀሉን ዘላቂ አዳኝነትን ከፍ አድርጎ ሲዘምር፣ ቍሳዊው ኃይል አልተመቸውም፤ ዝም ብሎ ማየትም ምርጫው አልነበረም፣ ስለሆነም ባለው ዓቅም ሁሉ ተንቀሳቅሶ መስቀሉን ከገጸ ምድር በማስወገድ በእሱ ላይ የተመሠረተውን አስተምህሮና እምነት እንዳይነሣም እንዳይወሳም በማሰብ መስቀሉን ቀበረ።
ቍሳውያን መስቀሉን ቢቀብሩትም የመስቀሉን ቃል ሊቀብሩ አልቻሉም፤ ምክንያቱም የመስቀሉ ቃል ቊሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊ፣ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ፤ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ፤ ስብአዊ ሳይሆን መለኮታዊ፤ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነውና፤ ይህም በመሆኑ ቍሳዊ የሆነው ዕፀ መስቀል ቢቀበርም እሱ የተሸከመው ቃለ ድኅነት በረቂቁ የሰው አእምሮ ተቀርጾና ተዘግቦ ስለሚኖር ተቀብሮ ሊቀር አልቻለም።
በሂደትም ያልተቀበረው የመስቀሉ ቃለ ድኅነት በንግሥት ዕሌኒ አእምሮ ውስጥ የእምነት ኃይል አቀጣጥሎ የተቀበረውን ዕፀ መስቀል በዛሬው ዕለት ከጥልቅ ጉድጓድ አውጥቶአል፣ በዚህም አሸናፊነቱን አረጋግጦእል
ዛሬ የምናክብረው በዓልም ይኸው ኃይለ እግዚአብሔር ለማሰብና በሱ ያለንን እምነት ለማስጠበቅና ቃለ ድኅነቱን ለማሥረጽ ነው፣ መስቀል ኃያልና አሸናፊ ቢሆንም ረቂቁንም ሆነ ግዙፉን ጠላት የሚያሽንፈው በሐቅና በሰላም፤ ኀሊናን በመርታትና በማሳመን እንጂ እንደ ቍሳዊ ኃይል አይደለምና እነሆ ዕፀ መስቀሉ በዛሬው ዕለት በኃይለ እግዚአብሔር በታጀበ ጢሰ-ዕጣን ከተቀበረበት ጉድጓድ በሰላም ሊወጣ ችሏል፡፡
የመስቀሉ ቃል ዛሬም ተቃራኒ ኃይል አላጣም፤ ዛሬም ለመስቀሉ ቃል ጀርባቸውን የሚሰጡ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ከዚህም የተነሣ ስጋቱ ጭንቀቱ ግጭቱ አለመተማመኑ በዓለማችን ከምን ጊዜውም በላይ ተንሰራፍቶእል
ሀገራችንም ከዚህ የተለየች ልትሆን አልቻለችም፤ በዓለ መስቀሉን ከማንኛውም ክፍለ ዓለም በተለየ ሥነ ሥርዓት ብናከብርም የመስቀሉ ሰላም ግን በሀገራችንና በሕዝባችን እየተነበበ አይደለም። ይህንን ለማስገንዘብ የሚተላለፈው መልእክትም እየተደመጠ አይመስልም! የመስቀሉ ቃል ማለት ስዎች በነፍሳቸውም ሆነ በሥጋቸው የተሟላ ደጎንነት ያግኙ ማለት ነው።
የመስቀሉ ቃል ማለት የሰዎች ሃይማኖታዊ ነጻነት ይከበር፤ በሕይወት የመኖር ሰብአዊ መብታቸውም ይጠበቅ ማለት ነው፤ የመስቀሉ ቃል ማለት ስዎች በዚች ምድር በእኩልነት በአንድነት በመተጋገዝ በመረዳዳት በፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በሰላም በፍቅር በስምምነት በመተባበር ይኑሩ ማለት ነው።
የመስቀሉ ቃል ማለት የሰው ሕይወት በዚህ ዓለም የተገደበ አይደለም ዘላለማዊ በሆነው መንፈሳዊ ዓለምም ሕይወት በቀዋሚነት ይቀጥላልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ለእርሱም ታዘዙና ተገዙ ማለት ነው፤ የመስቀሉ ቃል ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በፈሰሰው ደም የመዳን ዕድል ተከፍቶላችኋልና በደሙ ታጥባችሁ ወደ እግዚብሔር መንግሥት ግቡ ማለት ነው።
ይህንን የመስቀል ቃል ዓለም ብትቀበለው ኖሮ በየጊዜው እያንዣበባት ያለው ስጋት ሁሉ ቦታ አይኖረውም ነበር፤ አሁንም በመስቀሉ ስም ለዓለም ሕዝብም ሆነ ለሀገራችን ዜጎች ሁሉ የምናስተላልፈው ዓቢይ መልእክት የመስቀሉ ቃል ሁላችንንም በእኩልነትና በፍቅር የሚያስተናግድ ነውና እሱን እንቀበል፤ የዓለም ስጋቶች በሙሉ ሊቀረፉ የሚችሉ በመስቀሉ ቃል ብቻ ነውና የሚል ነው፡፡
†
🕊
† መስቀል †
❝ መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው ።
መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው ፤ የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው፡፡
መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደ እርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው።
መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው ።
መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው ፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው፡፡
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው፡፡
መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው ❞
[ ውዳሴ መስቀል ]
#እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !!!
❗#መስከረም_16_የደመራ_በዓል❗
❗#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 #ደመራ ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ያወቀችበት ዕለት ነው፡፡
🔷👉 ደመራ ማለት፤ ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡
🔷👉 ጥንተ ታሪኩም፤ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በጌታ መካነ መቃብር ጎልጎታ ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት የኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገው እነርሱም ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠዋትና ማታ በጎልጎታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡
🔵👉 ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተአምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ መፈወስ ጀመሩ፤ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ሳባቸው፡፡
🔶👉 ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየተጣለበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆየ፡፡
🔷👉 በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጕዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትዕምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ /በዚህ ምልክት ድል ታደርጋለህ/›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡
🔴👉 የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡
🔷👉 በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው እርሱም ሦስት ተራሮችን ጠቆማትና ከሦስት ተራሮች የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ግን በእግዚብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡
🔴👉 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ /አስደምረሽ/ ዕጣን አፍስሺበትና በእሳት አያይዥው የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጭሽ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
❗በዚህችም ቀን የጌታችን መካነ መቃብር ላይም ቤተክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ይታሰባል።❗
❗#መስቀል_ መስከረም 17❗
🔷👉 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
🌼 ጦብያም "አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ ከዚህም በኋላ አሽከር ሊፈልግ ሔደ ቅዱስ ሩፋኤልንም አሽከር በሚሆን ሰው አምሳል አገኘው እርሱም ከጦብያ ጋር መጣ "ስሙንም አዛሪያ ነኝ" አለ ጦቢትም ላካቸው። ሲሔዱም በመሸ ጊዜ ወደ ጤግሮስ ወንዝ ደረሱ ጦብያም ገላውን ይታጠብ ዘንድ ወረደ። ታላቅ ዓሣም ሊውጠው ተወረወረ ሩፋኤልም ጦብያን "ዓሣውን ያዘው አትፍራው እረደውና ጉበቱን፣ ልቡንና፣ ሐሞቱን ያዝ" አለው እርሱም እንዳዘዘው አደረገ።
🌼 ጦብያም ሩፋኤልን "አንተ ወንድሜ አዛርያ ይህ የዓሣ ሐሞት ጉበቱና ልቡ ምን ይደረጋል" አለው። አዛርያ የተባለ መልአክም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ጋኔን ያደረበት ሰው ወንድ ወይም ሴት ጉበቱንና ልቡን ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ያጤሱለት እንደሆነ ጋኔን ይሸሻል ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩ ሰውን ቢኩሉት ይድናል"። ሁለተኛም የራጉኤልን ልጅ ሣራን ያገባት ዘንድ ተናገረው እግዚአብሔርም ይጠብቀዋልና እንዳይፈራ አጽናናው። ወደራጉኤል ቤትም በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው።
🌼 ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሣራን ወደዳት። እርሷንም ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው አባቷም ለሰባት ባሎች አጋብቷት ሰባቱም እንደሞቱ ነገረው ጦብያም "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ። ወደ ጫጉላ ቤትም በአገቧቸው ጊዜ ሩፋኤል የነገረውን ቃል አስታወሰ የዓሣውንም ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋር አጤሰ ያን ጊዜ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን ሸሸ መልአክ ሩፋኤልም ይዞ ለዘላለሙ አሠረው።
🌼 ጦቢያም ሚስቱን ሣራን ይዞ ደስ ብሎት ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ አባትና እናቱም በደስታ ተቀበሉት የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሁኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ ዐይኑን አሸ ወዲያውኑ ድኖ ልጁን አየ። ከዚህም በኋላ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ራሱን ገለጠላቸው ብዙ ነገርንም ነግሮአቸው ወደ ሰማይ ዐረገ።
🌼 ከዚህም በኋላ ከወገኖቹ ጋር ተድላ ደስታን አደረገ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መከራ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "እርሱ በኃጢአታችን ይገርፈናል ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል" ሁለተኛም "መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው። እነርሱ ክብርህን በአዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና" አለ።
🌼 ዳግመኛም ስለ ኢየሩሳሌም መታነፅ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ኢየሩሳሌም ሰንፔር መረግድ በሚባል በከበረ ዕንቁ ትሠራለች ድልድልዋ፣ ቅጽርዋ፣ አደባባይዋ፣ ደጆቿም በከበረ ዕንቊ በጠራም ወርቅ ይሠራሉ አደባባይዋም ቢረሌ፣ አትራኮስ፣ ሶፎር በሚባል ዕንቁ ይሠራልና በመንገድዋ ሁሉ ሁሉም እግዚአብሔርን አስቀድሞ የነበረ ወደፊትም የሚኖር እያሉ ያመሰግኑታል ደግሞም ከዓለማት ሁሉ ጽዮንን ከፍ ከፍ ያደረጋት እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ"።
🌼 ሁለተኛም የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢት ተናገረ ሁለተኛም ደግሞ ዮናስ ከነነዌ እንዲወጣ ልጁን ጦብያን አዘዘው። ዳግመኛም ልጁን እንዲህ አለው "ልጄ ሆይ ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት" ይህን ተናግሮ በዐልጋው ላይ ሳለ በመቶ ኀምሳ ስምንት ዘመኑ ዐረፈ በክብርም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጦቢት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 16 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌼 "#ሰላም_ለጦቢት_መፍቀሬ_ምጽዋት ዘተብህለ። እስመ ይገብር ምጽዋተ ወብዙኅ ሣህለ። እንዘ ምስለ ሕዝቡ ይሄሉ ሀገረ ነነዌ ማዕከለ። እምከመ ረከበ በእሴ ቅቱለ። እንበ ይቅብሮ አይጥዕም እክለ"። #ሊቁ_አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 16።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር"። መዝ 86፥2-3 ወይም መዝ 50፥18-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥13-17 ወይም ዮሐ 9፥1-12።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦"እቤ አዐቅብ አፋየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ። ወአንበርኩ ዐቃቤ ለአፉየ። ሶበ ይትቃወሙኒ ኀጥአን ቅድሜየ"። መዝ 38፥1-2 ወይም መዝ 50፥18-19። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥10-18፣ ያዕ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥13-21። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 9፥1-12 ወይም 10፥22-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የደመራ በዓል ለሁላችንንም ይሁንልን።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፲፮ (16) ቀን።
🌼 እንኳን #ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ መቃብር ላይ #ቤተክርስቲያን_ለታነፀችበትና_ለተቀደሰችበት በዓል፣ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ ለተሠሩበትና ለከበሩበት በዓል (ለደመራ በዓል)ና በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር ለተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ ለሆነ ለገባኤል ልጅ ለቅዱስ ጦቢት ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ከወርቅላ፣ ከስምዖን፣ ከመርቄኖስ፣ ከሐሊ፣ ከሮቂኖስ፣ ከሉክያኖስ፣ ከአርዝማኖስ፣ ከጴጥሮስ፣ ከሐና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_አንገርጋሪ፦ ሃሌ ሉያ "ዝኒ ኮነ በፈቃደ እግዚአብሔር ዝንቱ ኵሉ ኮነ ወአንቲኒ ታቦት እምኀበ መጻእኪ ወኀበኒ ተሐውሪ መድኃኒተ ኩኒ ታቦት ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ"። ትርጉም፦ የንጉሥ የሕጉ ታቦት መድኃኒትን ሁኚ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ሆነ፤ አንቺ ታቦት ከወዴት መጣሽ ወዴትስ ትሄጃለሽ።
✝ ✝ ✝
🌼 በዚች ቀን #ከጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መቃብር ላይ #ቤተ_ክርስቲያን_የታነፀችበትና_የተቀደሰችበት ነው። ደግሞ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ።
🌼 ይህም እንዲህ ነው ልጇ ቈስጠንጢኖስ በነገሠ በሃያ ዓመት ቅዱሳን የሆኑ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶችን በኒቅያ ከተማ ከሰበሰበ በኋላ ቅድስት እናቱ ዕሌኒ እንዲህ አለችው "ልጄ ሆይ እኔ ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም በመሔድ የክብር ንጉሥ የሆነ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል ፈልጌ አወጣ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስዕለትን ተስያለሁ"።
🌼 ቈስጠንጢኖስም ሰምቶ በዚህ ነገር ደስ አለው ከብዙ ሠራዊትም ጋር ብዙ ገንዘብ ሰጥቶ ላካት የከበሩ የግምጃ ልብሶችንም ሰጣት እርሷም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ ከከበሩ ቦታዎች ተባረከች። ከዚህም በኋላ ስለ ከበረና አዳኝ ስለ ሆነ ዕፀ መስቀል መረመረች በታላቅ ድካምና ችግር አገኘችውና ታላቅ ክብርን አከበረችው በታላቅ ምስጋናም አመሰገነችው።
🌼 ከዚህም በኋላ በጎልጎታ በቤተ ልሔምም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዋሻ ደግሞ በጽርሐ ጽዮን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ በተቀበረበት በጌቴሴማኒ በደብረ ዘይትም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ የቤተ መቅደስ መሠዊያ እንዲሠሩ አዘዘች። ዳግመኛም በዕንቁ በወርቅና በብር እንዲአስጌጧቸው አዘዘች።
🌼 በኢየሩሳሌምም ስሙ መቃርስ የሚባል ኤጲስቆጶስ አለ። እርሱም ንግሥት ዕሌኒን እንዲህ ብሎ መከራት "ይህን እንዲህ አትሥሪ ከጥቂት ዘመናት በኋላ በዚህ አገር ሊነግሡ አሕዛብ ይመጣሉ። ሁሉን ይማርካሉ ቦታዎችንም ያፈርሳሉ ወርቁን፣ ብሩን፣ ዕንቁውን ይወስዳሉና ነገር ግን ጠንካራ የሆነ የማይናወጽና የማይፈርስ ጥሩ ሕንፃ ልታሠሪ ይገባል ከዚህ የሚተርፈውንም ለድኆችና ለችግረኞች ስጪአቸው" አላት። እርሷም የአባ መቃርስን ምክሩን ተቀብላ መኳንንቱ ሁሉ ለአባ መቃርስ በመታዘዝ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲአንፁ አዘዘቻቸው።
🌼 ከዚህም በኋላ ንግሥት ዕሌኒ ወደ ልጅዋ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በተመለሰች ጊዜ በኢየሩሳሌም ያደረገችውን ሁሉ ነገረችው ሰምቶ እጅግ ደስ አለው እንደገና ሌላ ብዙ ገንዘብና ሕንፃውን ተቆጣጥረው የሚያሠሩ ሹሞችን ላከ ለሚገነቡና ለሕንፃው ሥራ ለሚአገለግሉ ሁሉ ደመወዛቸውን ሳያጓድሉ ሁል ጊዜ ወደ ማታ እንዲሰጧቸው ንጉሡ አዘዘ። ስለ ደመወዛቸው እንዳይጮኹና እንዳያዝኑ እግዚአብሔርም ስለ ጩኸታቸው በእርሱ ላይ እንዳይቆጣ ይፈራልና።
🌼 ጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ በ፴ ዓመቱ የከበሩ ቦታዎች ሕንፃቸው በተፈጸመ ጊዜ ንዋየ ቅዱሳትን ዋጋቸው ብዙ ድንቅ የሆነ የከበሩ የግምጃ ልብሶችንም ላከ። ደግሞም ወደ ቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳቶቹን በመያዝ እንዲዘጋጅ እንዲሁም ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳትና ወደ እስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስ ኤጲስቆጶሳቶቹን በመያዝ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ኢየሩሳሌም ተሰብስበው በከበሩ ቦታዎች ውስጥ የተሠሩትን ወይም የታነፁትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያከብሩ።
🌼 ንጉሡም እንዳዘዘ ሁሉም ተሰበሰቡ እስከ መስከረም ወር ዐሥራ ስድስት ቀን ኑረው በዚች ቀን ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት መሠዊያቸውንም አከበሩአቸው የቁርባን ቅዳሴንም ቀድሰው ለምእመናን ሥጋውንና ደሙን አቀበሉ በዚችም ቀን ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታን ሆነ።
🌼 የከበረ መስቀልንም በመሸከም በነዚያ በከበሩ ቦታዎች ዞሩ በውስጣቸውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ አመሰገኑትም መስቀሉንም አከበሩት ወደ ሀገሮቻቸውም በሰላም በፍቅር ተመልሰው ገቡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በስቀሉ ኃይልም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌼 #ቅዱስ_ጦቢት፦ ይህም ጻድቅ በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር የተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ የገባኤል ልጅ ነው፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው ከወገኖቹም ጋር ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉ ዐሥራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች የሚሰጥ ነው።
🌼 በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሁሉም ክደው በዓልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሠው ነበር። ወገኖቹም ወደ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር የአሕዛብን መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና።
🌼 በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት ወዲያውኑ እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረው ፀሐይ ሲገባም ቆፍሮ ቀበረው በዚያች ሌሊትም እንደ ኃጢአተኛ ሁኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ። በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስለ አላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ኩሳቸውን ከዐይኖቹ ላይ ጣሉበት ዓይኖቹም ተቃጠሉ ከእሳቸውም ጢስ ወጣ ታወሩም ባለመድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም።
🌼 በዚያንም ጊዜ ጦቢት ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ለመነ "አቤቱ በቸርነትህ አስበኝ ወደ ችግረኛነቴም ተመልከት ለመማረክና ለመዘረፍ በአደረግኸን በእኔና በአባቶቼ ኃጢአት ተበቅለህ አታጥፋኝ። አሁንም በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን ነገር አድርግ ከመኖር ሞት ይሻለኛልና በሞት እሰናበት ዘንድ አፈርም እሆን ዘንድ ነፍሴን የሚቀበል መልአክን እዘዝ"።
🌼 በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ ሣራን በጭኗ ያደረ ክፉ አስማንድዮስ የሚባል ጋኔን ለሰባት ባሎች አጋብተዋት ወደርሷ ሲገቡ ሁሉንም ስለገደላቸው ስለዚህ የአባቷ አገልጋዮች ያሽሟጥጧት ነበርና ከሽሙጣቸው ያድናት ዘንድ እያለቀሰች ወደ እግዚአብሔር ትለምን ነበር ጸሎቷና የጦቢት ጸሎትም በልዑል እግዚአብሔር በጌትነቱ ልዕልና ፊት ተሰማ።
🌼 ጦቢትም በገባኤል ዘንድ አደራ ያስጠበቀውን የብሩን ነገር አሰበ ልጁ ጦብያንም ጠርቶ "ሳልሞት በገባኤል ዘንድ አደራ ያስጠበቅሁትን ብር ትቀበል ዘንድ ከአንተ ጋራ የሚሔድ በደመወዝ የሚቀጠር አሽከር ፈልግ" አለው።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፲፭ (15) ቀን።
🌼 እንኳን #ለዲያቆናት_አለቃ_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለሥጋው_ፍልሰት ለመታሰብያ በዓል፣ ጠራው ከሚባል አገር ለሆኑ እግራቸው በውኃው ሳይርስ በእግራቸው በባሕር ላይ ሲራመዱ ለነበሩት ለከበረ #ለጻድቁ_ለአባ_ጴጥሮስ በዓለ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዲያቆናት_አለቃ_ቀዳሜ_ሰማዕት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ_የሥጋው_ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው ከዐረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፉኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ "እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ" አለ።
🌼 ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ። "በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ" እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።
🌼 ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።
🌼 በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።
🌼 ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።
🌼 ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ "የቅዱስ እስጡፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ" ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።
🌼 እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም ለተመሰገነና ለተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ እስጢፋኖስ ሥጋው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌼 #አቡነ_ጴጥሮስ_ዘሃገረ_ጠራው፦ ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ክልቡ በቆራጥነት ተነሣ በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ። ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ። ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ማመስገን ነው። በዚህም ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና የሆነ መላእክትን መሰላቸው።
🌼 አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ተገባው እግሮቹም አይርሱም ሥጋ እንደ ሌለው መንፈስ እስከ ሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ ወደርሱ ሔደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 15 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌼 "#ሰላም_እብል_ለጴጥሮስ_ብሕትወ። ኮከበ ጠራው። ወውስተ ዓለም ኅሩም እምበሊዐ ኅብስት ወጼው። እስከ አስተርአየ በአምሳለ ምትሐት ሕስው። ተሴስዮ ሣዕር አብደረ በበድው"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_15።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወጾሩ ዘርዖሙ። ወሶበ የአትዉ ወጽኡ እንዘ ይትፌሥሑ። ወፆሩ ከላስቲሆሙ። መዝ 125፥6 ወይም መዝ 64፥4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥39-45 ወይም ሉቃ 10፥30-38።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ብፁዕ ዘኀረይኮ ወዘተወከፍኮ። ወዘአኅደርኮ ውስተ አዕፃዲከ። ጸገብነ እግዚኦ እምበረከተ ቤትከ"። መዝ 64፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው 2ኛ ቆሮ 3፥12-16፣ 2ኛ ጴጥ 2፥15-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 7፥55-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥30-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
መስከረም ፲፬በዚህች ዕለት ቅዱስ አባ አጋቶን ዘዓምድ አረፈ። እኚህ አባት ዘዓምድ ይባላሉ። ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው። ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር። በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ። በዚህ ጊዜ ደግሞ ይገባሃል ብለው ቅስናን ሾሟቸው። እኚህ አባት አብዝተው ምንኩስናን ይፈልጉ ነበርና አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከአባቶች ተቀበሉ። በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ። እድሜአቸውም 50 በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ። አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ። ወደ ዓለም ሳይገቡ ከዓለምም በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ። ለ50 ዓመታትም ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም። ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ። የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል። የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል። ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል። ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላ በተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐረፉ። በረከታቸው ይደርብን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
✝️ ✝️ ✝️
🌼 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ብፁዓን እለ ተኀድገሎሙ ኃጢአቶሙ። ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኵሎ ጌጋዮሙ። ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ"። መዝ 31፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ቆሮ 7፥12-18፣ ያዕ 5፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 19፥17-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 11፥5-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 መስከረም ፲፫ (13) ቀን።
🌼 እንኳን #ለታላቁና_ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ባስልዮስ አንድ ጎልማሳ አገርልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት እርሷንም ከመውደዱ የተነሣ እርሷን ለማግባት ብሎ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔዶ እግዚአብሔር ክዶ በሰይጣን አምኖ በእጁ ፈርሞ ለሰይጣን ሰጠው ይህንን የጽሕፈት ደብዳቤ በእግዚአብሔር ኃይልና በጸሎቱ #ቅዱስ_ባስልዮስ በመደምሰስ ድንቅ ተአምር ላደረገበት ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከከበረ ከባሕታዊ #ከአባ_ይስሐቅ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
🌼 #የቂሣርያ_ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ባስልዮስ ያደረገው ተአምር፦ ይህም እንዲህ ነው አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ልቡ እርሷን ወዶ እንደ እሳት እስከ ነደደ ድረስ እርሷንም ከመውደዱ ብዛት የተነሣ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው።
🌼 ይህም አገልጋይ ይህን ነገር ተቀብሎ ያ መሠርይ እንዳዘዘው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ከሰይጣናት አንዱ መጥቶ ወደ አለቃቸው ወስዶ አደረሰው ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ንጉሥህ ክርስቶስን ትክደዋለህን? ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላ ወደእርሱ አትመለስምን?" ይህም ጐስቋላ ባሪያ "አዎን ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው። መስሐቲ ዲያብሎስም "ይህን ልታደርግ በእጅህ ደብዳቤ ጻፍልኝ" አለው። እርሱም በከበረ ደሙ የዋጀውን የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ በደብዳቤ ውስጥ የክህደቱን ቃል ጻፈለት።
🌼 በዚያንም ጊዜ ሰይጣን በጌታው ልጅ ልብ ውስጥ የፍትወት እሳትን አነደደ ይህንንም ባሪያ እጅግ ወደደችው ከእርሱም መታገሥ አልተቻላትም። ወደ አባቷ በመጮህ በግልጥ "ከዕገሌ ባሪያህ ጋር ካላጋባኸኝ አለዚያ ራሴን እገድላለሁ" ትለዋለች እንጂ መታገሥ አልተቻላትም። አባትና እናቷም ፈጽሞ አዘኑ በምንም በምን ሊያስታግሥዋት አልቻሉም። የዚያም አገልጋይ ፍቅሩ በየዕለቱ በልቧ ይጨመር ነበር እንጂ። ስለዚህም ራሷን እንዳትገድል አባቷ ፈራ ለዚያ ባሪያ ሰጠው። እርሱም የጌታውን ልጅ ተቀብሎ ወደቤቱ አስገባት። ከርሷ ጋር ያለውን ፍላጎቱንም ፈጸመ። ከእርሱም ጋር ረጅም ጊዜ ከኖረች በኋላ አባትና እናቷም ይቅር ብሎ ኀዘናቸውን ከላያቸው ያርቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኀዘንንና ልቅሶን አብዝተው ነበር።
🌼 ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ጩኸታቸውን ሰማ ልመናቸውንም ተቀብሎ ይህ የወደደችው አገልጋይ ጐልማሳ ክርስቲያን እንዳልሆነ አስገነዘባት ከእርሷ ጋር በነበረበት በዚህ በረጅም ዘመን አንዲት ቀን እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ ሥጋውንና ደሙንም ሲቀበል ወይም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት ራሱን ሲአማትብ እርሷ አላየችውም።
🌼 ስለእምነቱም ጠየቀችው ግን አልገለጠላትም እርሷም እንዲህ አለችው "አንተ ክርስቲያን ከሆንክ ና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድና በፊቴ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበል"። እንዲህም በአስገደደችው ጊዜ ስለርሷ ያደረገውን ሁሉ ወደ ሥራየኛ እንደሔደም በሰይጣንም አምኖ እምነቱንም በክርታስ ጽፎ ያንን ክርታስ ለሰይጣን እንደ ሰጠው ነገራት።
🌼 ይህንንም ነገር ከእርሱ በሰማች ጊዜ ደነገጠች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች ራሷንም በማወዛወዝ እጅግ ተጸጽታ አዘነች። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሣች የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ወደሆነው ወደ ሀገርዋ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደች ከእግሩ በታችም ወድቃ ሰገደችለት በላይዋ የደረሰውን ሁሉ አስረዳችው ለሰው ልጆች ጠላት ከሆነ ከሠይጣን እጅ ፈጽሞ ያድናት ዘንድ ብዙ በማልቀስ ለመነችው። ቅዱስ ባስልዮስም ባሏ የሆነውን ባርያ ወደርሱ ልኮ አስመጣውና ጠየቀው እርሱም የሠራውን ሁሉ አስረዳው ቅዱስ ባስልዮስም "ተመልሰህ ክርስቲያን ልትሆን ከሰይጣንም እጅ ልትድን ትወዳለህን?" አለው ያም ባርያ "ጌታዬ ይሆንልኛልን?" አለ ይህ ቅዱስ አባትም "የፈጣሪህን ስም እየጠራህ ልብህን አጽና" አለው።
🌼 ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ በአንድ ቦታ ዘጋበት በመስቀል ምልከትም አማተበበት እንዲጸልይም አዘዘው ራሱ ቅዱስ ባስልዮስም ስለርሱ ጸለየ። ከሦስት ቀኖች በኋላም ጎበኘው እንዲህም አለው "በእሊህ በሦስት ቀኖች የደረሰብህ ምንድን ነው" እርሱም በላዩ በመጮህ ሠይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲአሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው ቅዱስ ባስልዮስም "ከእሳቸው ቁጣ የተነሣ አትፍራ እግዚአብሔር ይረዳሃልና አጽንቶም ይጠብቅሃል" አለው።
🌼 ከዚህም በኋላ ጥቂት እንጀራና ውኃ ሰጥቶ ወደ ቦታው መለሰው ቅዱስ ባስልዮስም ስለዚያ አገልጋይ ሒዶ ይጸልይ ጀመረ። ዳግመኛም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጐበኘውና በእርሱ ላይ ምን እንደ ደረሰበት ጠየቀው ያ አገልጋይም "ጩኸታቸውን እሰማለሁ ግን አላያቸውም" ብሎ መለሰለት። እንጀራና ውኃም ሰጠውና መከረው ወደ ቦታውም መለሰውና ስለርሱ ሊጸልይ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደ። እስከ አርባ ቀኖች ፍጻሜ ድረስ እንዲህ አደረገ። በአርባውም ቀን ፍጻሜ ከእርሱ ስለ ሆነው ጠየቀው ያ አገልጋይም እንዲህ አለው "ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ" አለው።
🌼 ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው የገዳማቱን መነኰሳትና ካህናቱንም ጠርቶ ስለዚያ ሰው ያቺን ሌሊት መላዋን እንዲጸልዩባት አዘዛቸ። በነጋ ጊዜም ያንን አገልጋይ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲአመጡት የዚያችንም አገር ሕዝብ ሁሉንም ሰብስቦ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንሥተው "አቤቱ ክርስቶስ ማረን ይቅር በለን" እያሉ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲማልዱ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ።
🌼 እንዲህም እያሉ ሲማልዱ ያ ሰው ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የከበረ አባት ባስልዮስም ባረካቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀብሎ ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በፍቅር አሰናበታቸው። እነርሱም ስለ ኃጢአታቸው ስርየትና ስለ ድኅነታቸው ፈጽሞ ደስ እያላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ባስልዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 13 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
🌼 "#በዛቲ_ዕለት_እግዚአብሔር_ገብረ። በእደ #ባስልዮስ_መንክረ። በአፍቅሮ ወለት አሐቲ ኀበ መሠርይ ዘሖረ። እንዘ ይከሥት በቅድመ መጽሐፈ ክህደቱ ስውረ። እምእደ ሰይጣን አንገፈ ወፄወወ ገብረ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_13።
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 እንኳን #ለዚህ_ዓመት_ሁለተኛ_ሳምንት #ዘመነ_ፍሬ_ለሚታሰቡበት_ዕለተ_እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "#እኩት_አንተ_ወስቡሕ_ስምከ ወዐቢይ ኃይልከ ዘተአርፍ በአርያም ወትሴባሕ በትሑታን ዘአንተ #ሠራእከ_ሰንበተ_ለዕረፍት ወወሀብከ ሲሳየ ዘበጽድቅ ለኵሉ እግዚኦ #ባርክ_ፍሬሃ_ለምድር መሓሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ለነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርኅብት እንተ ጸግበት ተአኵተከ። ትርጉም፦ #አንተ_ምስጉን_ነህ፤ #ስምህም_የተመሰገነ_ነው፤ ኃይልህም ታላቅ ነው፤ በአርያም የምትኖር በትሑታን የምትመሰገን አንተ ነህ፤ #ሰንበትን_ለዕረፍት_የሠራህ ለሁሉም በእውነት ምግብን የምትሰጠው አቤቱ #የምድርን_ፍሬ_ባርክ፤ ጻድቅና መሓሪ አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ ማነው! #ክረምትን_በጸጋህ_ታፈራርቃለህ፤ የዳነች ነፍስ የተራበች በልታም የጠገበች ነፍስ ታመሰግንሃለች። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
🌼 #ዘመነ_ፍሬ
🌼 #ከመስከረም 9 (ዘጠኝ) ጀምሮ እስከ #መስከረም_15 ድረስ "ዘመነ ፍሬ" በመባል ይታወቃል፤ይህም ሰምና ወርቅ ምሥጢር ያለው ሥያሜ ነው።
🌼 #ሰም:— ገበሬው በግንቦትና በሰኔ የዘራውን እህል ፍሬ የሚያይበት እግዚአብሔርን የሚያመሰግንበት፤ ምድርም በጠጣችው ዝናም ለተዘራባት ዘር በፍሬዋ መልስ የምትሰጥበት ወቅት ነው። "ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ" እንዲል ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤ መዝ 66÷7።
🌼 #ወርቅ:— ከሰኔ 26 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ያለውን ወቅት መዋዕለ ዘርእ ብለን እየተማርን ነበር፣ በወቅቱም ጌታ በዘርእ ያስተማረውን ትምህርት "ዘርእሰ ዘውእቱ ቃለ እግዚአብሔር" (ዘሩም የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ ማቴ 13÷19) በማለት የተረጎመውን ስንማር ቆይተናል።
🌼 በዚህ ወቅት ደግሞ ያኔ የተማርነው የእግዚአብሔር ቃል በእኛ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ምን ያህል ፍሬ ሰጠ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የምንገመገምበት ነው።
🌼 ምድሪቱ በሥርዓተ ተፈጥሮ መሠረት ገበሬውን አላሳፈረችውም የተዘራባትን አብዝታ አስረክባለች ፣ ምድር የተባለ የእኛ ልቡና የተዘራበትን የሕይወት ቃል የት አደረሰው? በመንገድ፣ በጭንጫ ፣ በእሾኻማና በመልካም መሬት እየተመሰለ ተምረን ነበር፤ የእኛ ልቡና የትኛውን መሬት ይወክላል? እነዚህን ጥያቄዎች እንመልስ ዘንድ አባቶቻችን ሊቃውንት ይህን ሥያሜ አስቀምጠውልናል።
🌼 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ምድር ለእመ ሰትየት ዝናመ ዘይወርድ ላዕሌሃ ትወልድ ሣዕረ" (ምድር የሚወርድላትን ዝናም ስትጠጣ ሣርን ትወልዳለች) (ዕብ 6 ÷7 )በማለት እንደነገረን መሬት በዚህ ወቅት በልምላሜ፤ በአበባና በፍሬ አጊጣ ተውባ የምትታይበት ወቅት ነው፣ ♠የተዘራባትን ባታበቅል ግን "ዘቅርብት ለመርገም ወደኃሪታ ለአንድዶ" (ለመረገም የቀረበች ናት፤ መጨረሻዋም መንደድ መቃጠል ነው።) በማለት ጠንከር አድርጎ አስተምሮናል።
🌼 ሰውም የተዘራበትን ቃለ ሕይወት ካልሠራበትና ካልተጠቀመበት እንዲሁ ይሆናል፣ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "ግበሩኬ ፍሬ ዘይደልወክሙ ለንስሐ" ካለ በኋላ "ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል" ማቴ 3÷8-10 በማለት በዛፍ አንፃር የእኛን ሕይወት አስተምሮናል፤ ጌታም ይህንኑ ቃል በቃል የተናገረው ሲሆን አምኖ ተጠምቆ ፤ተምሮ ክርስቲያናዊ ሥራ የማይሠራ ፣ በሠራው ክፋትና ተንኰል የማይፀፀት ሁሉ ከግንዱ የተለየ ቅርንጫፍ እንደሚሆን አስረግጦ ነግሮናል ዮሐ 15÷6።
🌼 በዚህም መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ "ወኲሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ ከመ በትዕግሥትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንርከብ ተስፋነ "( መጻሕፍትን በማመን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን እናገኝ ዘንድ የተጻፈው ሁሉ እኛ እንድንገሠጽበት ተጻፈ።") ሮሜ 15÷4 በማለት እንዳስተማረን የተማርነውን፤ የሰማነውን ያየነውን፤ያነበብነውንና የተረዳነውን የሕይወት ቃል ተግባራዊ እንድናደርግ የምንነሳሳበት ወቅት መሆኑን ልብ ይሏል!!!
🌼 ይህንን ቃል ስናስብና ስንረዳ ከእንስሳዊ ጠባይ ወጥተን ሰው ወደ መሆን እንሸጋገራለን፤ የፍቅርንና የአብሮነትን ትርጒም ወደ መረዳት እንመጣለን። እግዚአብሔርም የሰውነትን ፍሬ ሊለቅም ሲመጣ ከመረገም እንድናለን ማቴ 21÷18።
አምላካችን እግዚአብሔር ሁላችንም ለልምላሜ ንስሐ ለፍሬ ቊርባን እንድንበቃ ይርዳን!!! አሜን። ምንጭ፦ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘመካኒሳ ሚካኤል።
✝ ✝ ✝
🌼 #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "ምድርኒ ወሀበት (ትሁብ) ፍሬሃ። ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ። ወይባርከነ እግዚአብሔር። መዝ 66፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ ፱፥1-ፍ.ም፣ ያዕ ፭፥1-10፣ የሐዋ ሥራ 19፥21። የሚነበበው ወንጌል ማር 4፥24-39። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል ወራዊ በዓልና የኤፌሶን ጉባኤ የተሰበሰቡ የ200 ኤጲስቆጶሳት በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
