ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر603
مشترکین
-224 ساعت
-57 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
❤ ጊዜው (5ኛውና 6ኛው መቶ ክ/ዘመን) ወዲህ ወርቃማ ወዲያ ደግሞ ጨለማ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ዘመን ነበር በብርሃንነቱ በተለይ በምሥራቁ ዓለም ያበሩ አበው እነ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ፣ ያዕቆብ ዘእልበረዲን የመሰሉ አበው ተገኝተውበታል ሲያልፍ ደግሞ ዘይኑንና አንስጣስዮስን የመሰሉ ደጋግ ነገሥታት በዘመኑ መነሳታቸውን እናስባለን።
❤ በተቃራኒው ግን ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ለ2 የተከፈለችበት መለካውያን የነገሥታቱ ደጀን አላቸውና ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከሥሯ ነቅሎ ለማጥፋት ብዙ የሞከሩበት ዘመን ነውና ጨለማነቱ ይጐላብናል። በእርግጥም ከመርቅያን እስከ ዮስጢኖስ ዳግማዊ ዘመን ድረስ ለ100 ዓመታት መለካውያኑ የልዮን ልጆች ሁለት ባሕርይ ማለትን ሊያሰፉ ተዋሕዶንም ሊያጠፉ የከፈቱት ዘመቻ ሊሳካ ጫፍ የደረሰ ይመስል ነበር።
ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔ
ዓለም አርመኖቹን ስቦ በ490ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ።
በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን፤ በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስን አስነስቷል። ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ ንግሥት ታኦድራን ማርኳል። በእነዚህ ቅዱሳን ትጋት የለመለመችው ተዋሕዶ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ያለ አርበኛን ግን ያገኘችው በጭንቅ ቀን ነበር።
❤ ሰው መሆን ሰው በጠፋባቸው ቀናት ነውና በግብጽና በቁስጥንጥንያ በትምህርትና ምናኔ ላይ የነበረው ቅዱሱ ታጥቆ ለአገልግሎት የተሰለፈው በ530ዎቹ አካባቢ ነበር። ጊዜው ወዲህ አንበሳው ቅዱስ ሳዊሮስ ከሶርያ ወደ ግብጽ እንደተሰደደ ያረፈበት ነበር ወዲያ ደግሞ ሊቁ አባ ቴዎዶስዮስ የግብጹ ለግዞት የተዳረገበት ነበርና የተዋሕዶ ምዕመናን ያለ እረኛ ተቅበዘበዙ። የቤተ መንግስቱ ተጽዕኖ ደግሞ ሁለት ባሕርይ በማይሉት ላይ እሥራትና ግድያን ወደ ማወጅ ተሸጋግሯልና የምእመናን ቁጥር እጅጉን
መመንመኑ ቀጠለ።
❤ ይህ ዕረፍት የነሳው ቅዱስ ያዕቆብ በበኩሉ ነገሩን በዝምታ ሊያልፈው አልወደደምና አገልግሎቱን አሰፋ። ሌሊቱን በጸሎት ያድራል። ቀን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማስተማር ባይችል በየቦታው እየዞረ ያስተምር ነበር።
ከትምህርቱ ጣዕምና ከመልእክቱ ሥምረት የተነሳም ምእመናን እንደገና ተነቃቁ። እርሱም ከግብጽ እስከ ሶርያ አልፎም እስከ ቁስጥንጥንያ ድረስ ያለ ዕረፍት ሲሰብክ 40 ዘመናትን አሳለፈ። በተለይ አዲስ አማኞችን ያጠምቅ ዘንድ በእሥረኛው ቅዱስ ቴዎዳስዮስ ኤጲስ ቆዾስነትን ተቀብሏል። የሶርያ (አንጾኪያ) የፕትርክና መንበሩ ክፍት ሆኖ እርሱን ቢጠብቀውም እርሱ ግን የዚህ (የስልጣን) ፈላጊ አልነበረምና ሌሎች እንዲሾሙበት አድርጉዋል።
❤ ቅዱስ ያዕቆብ በስብከት አገልግሎት ምሥራቁን ዓለም ሲያበራ የተባበሩት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም ያሳለፈው ድካምና መከራ ግን ተወዳዳሪ አልነበረውም። በተለይ የወቅቱ የአንጾኪያ ኃያላን መኳንንትና ሹመኛ መናፍቃን ብዙ አሳደውታል። እርሱ ግን በጥበብና በፈሊጥ እዚያው ደጃቸው ላይ የነበሩ ምዕመናንን በእረኝነት ጠብቁአል። ለዚህ ሲባልም ራሱን እየቀያየረ የመሣፍንቱን አጥሮችና ቅጥሮች አልፏል። ለቤተ
ክርስቲያን ክብርም እንደ እብድ እንደ ሴትም መስሎ የወንጌልን ዘር ዘርቷል። ከብዙ ፈተናና አገልግሎት በሁዋላም በተወለደ በ78 ዓመቱ በ578 ዓ.ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል።
❤ ትልቁ መታሰቢያው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ምዕመኑ "ያዕቆባውያን" መባላቸው ሲሆን እኛ ደግሞ በአንገታችን ላይ እንድናስራት ባስተማረን ማዕተብ (ማኅተም) ዘወትር እናስበዋለን። ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብን በአንገት ላይ ስለ ማሰር ያስተማረ እርሱ ነውና::
❤ የምሥራቁን ኮከብ እል-በረዲ ያዕቆብን በየዓመቱ ሰኔ 28 ቀን በነገረ ቅዱሳን መደበኛ ጉባኤ ጐንደር እናከብራለን። ሶርያውያን ደግሞ July 31 ሐምሌ 24 ቀን) ያከብሩታል። ከቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱ ሁላችንንም ይማረን!። ምንጭ፦ ዝክረ ቅዱሳን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለቴዎዶስዮስ_ዘተወክፈ_ክበዶ። ለሕማም ወለተሰዶ። በቃለ ሃይማኖት እንዘ ይሜህር ውሉዶ። በእንተ ዘገብረ ለክርስቶስ ፈቃዶ። ዐስበ ሐዋርያት ሎቱ ምንተኒ ኢውሕዶ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 28።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ጸላእኩ ማኅበረ እኩያን። ወኢይነብር ምስለ ጽልሕዋን። ወአሐፅብ በንጹሕ እየውየ"። መዝ 25፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥7-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-7 እና የሐዋ 7፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥23-32።የ ሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሰኔ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን #ለእስክድርያ (ለግብጽ) አገር ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ለሆነው ሃያ ስምንት ዓመት ሙሉ በስደትና በመከራ ላሳለፈ ለታላቁ አባት #ለአባ_ቴዎዶስዮስ_ለዕረፍት_መታሰቢያ በዓልና #ለአባ_ያዕቆብ_እል-በረዲ_ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰብ፦ #ከቅዱስ_ባስልዮስና_ከቢፋሞን፣ #ከባሊዲስና #ከኮቶሎስ_ከአርዳሚስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አባ_ቴዎዶስዮስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ አገር ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ነው። በዚህም ቅዱስ በስሙ በግብጽ ምድር ውስጥ ምእመናን ቴዎዶስዮሳውያን ተብለው ተጠርተውበታል። ይህም የሆነው እንዲህ ነው ሊቀ ጵጵስና ከተሾመ በኋላ ክፉዎች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሥተው በንጉሥ ምክር ከመንበረ ሢመቱ አሳደዱት በእርሱ ፈንታም አስቀድሞ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዲያቆናት የነበረ ስሙ አቃቅያኖስ የሚባለውን አንድ ሰው ሾሙ እርሱም ለአባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ጵጵስና እንዲገባው ከፈረሙት ቁጥር ውስጥ ነበር።
✝️ ይህም አባት ወደ ግርማኖስ አገር ሒዶ ሦስት ወሮች ኖረ በዚያም ወራት በግብጽ አገር ንቡረ እድ አባ ሳዊሮስ ነበር እርሱም በአባቶቻችን ሐዋርያት እንዲሁም በአትናቴዎስና በዮሐንስ አፈወርቅ የደረሰባቸውን መከራ እያስታወሰ ያጽናናቸው ነበር። ከዚያም ተነሥቶ መሊግ ወደሚባል አገር ሔደ በዚያም ሁለት ዓመት ተቀመጠ።
✝️ የእስክንድርያ ከተማ ሰዎችም የጠባቂያቸው የቴዎዶስዮስ መመለስ ሺተው በእስክንድርያው መኰንን ላይ ተነሡበት መኰንኑም ወደ መንበረ ሢመቱ መለሰው አቃቅያኖስንም አባረሩት። ይህም ነገር በንጉሥ ዮስጣቲያኖስና አምላክን በምትወድ በንግሥት ታዖድራ ዘንድ ተሰማ ንግሥቲቱም አስቀድሞ የተሾመው በሹመት ወንበሩ ይቀመጥ ብላ ጻፈች።
✝️ ሃምሳ ስምንት ካህናትም ጉባኤ አደረጉ "አስቀድሞ የተሾመ አባ ቴዎዶስዮስ ነው" ሲሉም ጻፉ። ያን ጊዜም አቃቅያኖስ በሕዝብ ፊት ቁሞ "ክፋዎች ሰዎች ስለ አስገደዱኝ ይህን ሥራ ለመሥራት ሕግን ተላልፌአለሁ" አለ። ከዚህም በኋላ አቃቅዮስን ከውግዘቱ እንዲፈታው ነገር ግን ክህነትም ሆነ ሊቀ ዲቁና ለዘለዓለም እንዳይኖረው ሕዝቡ አባ ቴዎዶስዮስን ለመኑት። አቃቅያኖስ "አዎ እንዲሁ ይሁን" አለ ይህም አባት ከግዝቱ ፈታው።
✝️ ሃይማኖቱን ያጠፋ ንጉሡ ግን በከፋች ሃይማኖቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ጋራ የሚስማማ መስሎት በእስክንድርያ ወዳሉ መኳንንቶቹ እንዲህ ብሎ ጻፈ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎዶስዮስ በሃይማኖት ከእኛ ጋራ የሚስማማ ከሆነ ሹመት ይጨመርለታል። ለእስክንድር ከተማ ገዥ ይሆናል። ይህ ካልሆነ ከሹመቱ ይሻር።
✝️ ይህም አባት ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ ሰይጣን "በበረሀ ጌታችንን ብትሰግድልኝ የዓለም መንግሥታትንና ክብራቸውን ሁሉ እሰጥሃለሁ" አለው። ያን ጊዜም ይህ አባ ቴዎዶስዮስ ተነሥቶ ከእስክንድርያ ወጣ ወደ ላይኛው ግብጽም ሔደ በዚያም ሕዝቡን እያስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ጥቂት ቀኖች ኖረ። ንጉሥም አባ ቴዎዶስዮስ ከእስክንድርያ ከተማ እንደ ወጣ በሰማ ጊዜ እየሸነገለው ወደ እርሱ መልእክት ላከ እንዲህም አለው እኔ ከአንተ ጋራ ልነጋገር ከአንተም ልባረክ እንድትመክረኝም እሻለሁ"።
✝️ ከዚህም በኋላ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ሔደ የጳጳሳት አለቆችና ሕዝቡ ሁሉ ሠራዊቱም ተቀበሉት ከፍተኛ ወንበርም ላይ አስቀመጡት። እርስ በርሳቸውም ስለ ሃይማኖት ተከራከሩ ንጉሡም አብዝቶ ሲሸነግለውና ሲአባብለው ሰነበተ ቅዱስ አባት ቴዎዶስዮስ ከቅዱሳት መጻሕፍት በመጥቀስ ይረታው ነበር። ከእርሱም ጋራ ባልተስማማ ጊዜ ከመንበረ ሢመቱ ወደ ላይኛው ግብጽ አሳደደው። በእርሱም ፈንታ ጳውሎስ የሚባለውን ሰው ሾመው።
✝️ ጳውሎስም ወደ እስክንድርያ ከተማ በመጣ ጊዜ ሕዝቡ አልተቀበሉትም ዓመት ሙሉም ኖረ በእጁም ማንም ቊርባንን አልተቀበለም። ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ ለመናፍቁ ጳውሎስ እስከሚታዘዙ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ አዘዘ። ምእመናንም ከእስክንድርያ በመውጣት ወደ ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቆዝሞስና ድምያኖስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዱ ነበር ካህናቱም በዚያ እየቀደሱ ያቆርኳቸው ነበር የአገር ልጆችንም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቋቸው ነበር።
✝️ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲከፍቱላቸው አዘዘ አባ ቴዎዶስዮስም ሰምቶ ንጉሡ እንዳያስታቸው ፈራ ማጽናኛ ቃልን የተመላች መልእክትም ጽፎ በቀናች ሃይማኖት እያበረታቸው ወደ ምእመናን ላካት እንዲህም አላቸው "በዚያ ከሀዲ ጳውሎስ እንዳትታዘዙ ተጠበቁ"።
✝️ ይህም አባት ሃያ ስምንት ዓመት በስደት ኖረ። መላው የሹመቱ ዘመን ሠላሳ ሁለት ነበር። ይኸውም በእስክንድርያ አራት ዓመት በስደትም ሃያ ስምንት ዓመት ነው።
✝️ ይህም አባት ብዙ ድርሳናትን ደርሷል ምእመናንም በያዕቆብ ዘመን ያዕቆባውያን እንደ ተባሉ በስሙ ቴዎዶስዮሳውያን እየተባሉ ሲጠሩ ኖሩ። መልካም ጉዞውንም ፈጽሞ ሰኔ 28 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 25 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዲ (እል-በረዳይ) በተለይ በሃገራችን የተዘነጋ የሚመስለው የምሥራቅ ኮከብ_ ኮከበ ጽባሕ "ያዕቆብ" ለሚል ስም ትርጉምን የሰጡ አበው በ2 መንገድ ያትቱታል።
1.አኃዜ ሰኮና፦ነገሩ ከወልደ ይስሐቅ ወርብቃው ርዕሰ አበው ያዕቆብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አበው ግን ለትህትና ይተረጉሙታል።
2.አእቃጺ (አሰናካይ)፦ ነገሩ ስድብ (አሉታዊ) ይምሰል እንጂ በዚህ ስም የተጠሩ አበው ሁሉ ለአጋንንትና ለመናፍቃን ትልቅ መሰናክል ሆነውባቸው ኑረዋልና አባባሉ ምስጋና እንጂ ነቀፋን አይወክልም።
❤ የ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ምሥራቃዊ ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብም ለመለካዊ መናፍቃንና ለተዋሕዶ ተገዳዳሪዎች ትልቅ መሰናክል ሆኖባቸዋል የቀናችውን ቀርነ ሃይማኖትንም አጽንቷል። ብዙ ጊዜ "ዘ"-እልበረዲ መባሉን ይዘው በ"ዘ" ምክንያት እልበረዲን እንደ ሀገር የቆጠሯት አልጠፉም በረከታቸው ይድረሰንና ትጉሑ ዻዻስ አቡነ ጐርጐርዮስ ካልዕ ግን ለዚሁ መላምት "የለም!" ባይ ናቸው። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ' በተሰኝ ተወዳጅ መጽሐፋቸው "እል-በረዲ" ማለትን በዓረብኛ ከሠጋር በቅሎ ከሥሙር ሠረገላ ጋር አነጻጽረው አስቀምጠውታል። ለምን ቢባል እንደ ሠረገላ በተፋጠነ አገልግሎቱ ወዳጅንም ጠላትንም አስደምሟልና።
❤ ቅዱስ ያዕቆብ የተወለደው በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ (በ500 አካባቢ) ሲሆን ያረፈው ደግሞ በ578 ዓ/ም እንደሆነ ይታመናል። ነገሩን ልብ ስንለው ቅዱስ ማኅሌታይ ያሬድን ወዲህ በዘመን ወዲያ ደግሞ በአገልግሎት ይመስለዋል። እርግጥ ነው ለውለታው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ስትባል የእኛዋስ ምናለ "ያሬዳዊት" ብትባል የሚል ቁጭትን ያመጣል።
❤ አብርሃም የተባለው ደቀ መዝሙራቸውም ወደ ጉድጓዱ አብሯቸው በመግባት የአቡነ ክፍለ ሥላሴን እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሰንሰለት ካሠራቸው በኋላ ወጣ፣ ጻድቁም እንዳዘዙት ጉድጓዱን ዘጉትና ሰው እንዳያውቀው አንድ ትልቅ መደብ ሠሩለት። ነገር ግን በማግሥቱ "ወዳጄ ክፍለ ሥላሴ ሆይ! ለምን እንደዚህ አደረግህ? አንተ ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገብተህ ማነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚያቀርብ? ማንስ ዕጣን ያጥናል? ስለዚህ አሁን ና ከዚህ ተነሥተህ ውጣ" የሚል ራእይ ተመለከቱ ወዲያውም የተዘጋው ጉድጓድ በተአምር ተከፈተ ታስሮ የነበረው እጅና እግራቸውም ሰንሰለቱ በተአምር ተፈታ። እርሳቸውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በእጃቸው ሲያጨበጭቡ አስሯቸው የነበረው ልጃቸው ድምፅ ሰምቶ ሲመጣ አባታችንን ሲመለከት ደነገጠና "አባቴ ሆይ! ማን አወጣህ? ማንስ እጅህንና እግርህን ፈታህ" አላቸው። እርሳቸውም ለልጆቻቸው የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው።
❤ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ደብረ መድኀኒት ብለው በሰየሟት ገዳማቸው ባምብቆ አካባቢ የከብት በሽታ (ጉልሓይ) ተከስቶ ነበር ነገር ግን ያንን በሽታ ያመጣውን ክፉ ሰይጣን ጻድቁ በጸሎታቸው ኀይል እያስጮኹ አባረው ጣሉት፤ ድምፁንም ሰምተው የአካባቢው ሰዎች ጠላታቸው እንደወደቀ ዐውቀው ከብቶቻቸውም ጤነኞች ስለሆኑላቸው የአቡነ ክፍለ ሥላሴን አምላክ አመሰገኑ።
❤ ጻድቁ የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበር፤ አንድ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ የማያስችል ሕማም አጋጠማቸውና በእርሳቸው ፋንታ አንድ እግሩን የሚያመው ወዳጃቸውን ሔዶ ዕጣን እንዲያጥን ነገሩት። እርሱም ሔዶ ግድግዳውን ተጠግቶ በሰሜንና በደቡብ አጥኖ በምዕራንና በምሥራቅ ሳያጥን ተመልሶ ሊጠይቃቸው ሲመጣ አባታችንም "አንተ ወንድሜ ስለምን እንደዚህ ታደርጋለህ? ለምን እንደአባቶቻችን አድርገህ በምዕራብና በምሥራቅ አላጠንክም?" አሉት ይህንንም ሲሰማ ያ ካህን ደንግጦ በሠራው ስሕተት ንስሓ ገባና እግዚአብሔርን አመሰገነ።
በመጨረሻም የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ካህን "ወንድሜ ሆይ! እኔ ማክሰኞ ቀን በአባታችን በአብርሃም በዓል ዕለት እሞታለሁ" በማለት የሚያርፉበትን ቀን ነገሩት። በተናገሩትም መሠረት ከምንኵስናቸው በፊት 20 ዓመት ከምንኩስናቸው በኋላ 8 ዓመት ኖረው በ28 ዓመታቸው ሰኔ 28 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ዐረፉ። ጻድቁ ራሳቸው በተከሏትና በጸለዩባት በደብረ መድኀኒት ቅድስት ሥላሴ ባምብቆ ከተቀበሩ በኋላም ብዙ ተአምራት አድርገዋል። ዝክራቸውን ያደረገ በጸሎታቸው የተማጸነ በዚህ ዓለም ከመከራ ሥጋ፣ በሚመጣውም ዓለም ከመከራ ነፍስ እንደሚድን ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ቃልኪዳን ስለገባላቸው የባምብቆ ሕዝብና የዛውል ሕዝብ ሰኔ 28 ቀን በዓላቸውን በታላቅ ክብር ያከብራሉ። ከአቡነ ክፍለ ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን።
❤ አብርሃም የተባለው ደቀ መዝሙራቸውም ወደ ጉድጓዱ አብሯቸው በመግባት የአቡነ ክፍለ ሥላሴን እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሰንሰለት ካሠራቸው በኋላ ወጣ፣ ጻድቁም እንዳዘዙት ጉድጓዱን ዘጉትና ሰው እንዳያውቀው አንድ ትልቅ መደብ ሠሩለት። ነገር ግን በማግሥቱ "ወዳጄ ክፍለ ሥላሴ ሆይ! ለምን እንደዚህ አደረግህ? አንተ ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገብተህ ማነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚያቀርብ? ማንስ ዕጣን ያጥናል? ስለዚህ አሁን ና ከዚህ ተነሥተህ ውጣ" የሚል ራእይ ተመለከቱ ወዲያውም የተዘጋው ጉድጓድ በተአምር ተከፈተ ታስሮ የነበረው እጅና እግራቸውም ሰንሰለቱ በተአምር ተፈታ። እርሳቸውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በእጃቸው ሲያጨበጭቡ አስሯቸው የነበረው ልጃቸው ድምፅ ሰምቶ ሲመጣ አባታችንን ሲመለከት ደነገጠና "አባቴ ሆይ! ማን አወጣህ? ማንስ እጅህንና እግርህን ፈታህ" አላቸው። እርሳቸውም ለልጆቻቸው የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው።
❤ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ደብረ መድኀኒት ብለው በሰየሟት ገዳማቸው ባምብቆ አካባቢ የከብት በሽታ (ጉልሓይ) ተከስቶ ነበር ነገር ግን ያንን በሽታ ያመጣውን ክፉ ሰይጣን ጻድቁ በጸሎታቸው ኀይል እያስጮኹ አባረው ጣሉት፤ ድምፁንም ሰምተው የአካባቢው ሰዎች ጠላታቸው እንደወደቀ ዐውቀው ከብቶቻቸውም ጤነኞች ስለሆኑላቸው የአቡነ ክፍለ ሥላሴን አምላክ አመሰገኑ።
❤ ጻድቁ የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበር፤ አንድ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ የማያስችል ሕማም አጋጠማቸውና በእርሳቸው ፋንታ አንድ እግሩን የሚያመው ወዳጃቸውን ሔዶ ዕጣን እንዲያጥን ነገሩት። እርሱም ሔዶ ግድግዳውን ተጠግቶ በሰሜንና በደቡብ አጥኖ በምዕራንና በምሥራቅ ሳያጥን ተመልሶ ሊጠይቃቸው ሲመጣ አባታችንም "አንተ ወንድሜ ስለምን እንደዚህ ታደርጋለህ? ለምን እንደአባቶቻችን አድርገህ በምዕራብና በምሥራቅ አላጠንክም?" አሉት ይህንንም ሲሰማ ያ ካህን ደንግጦ በሠራው ስሕተት ንስሓ ገባና እግዚአብሔርን አመሰገነ።
❤ በመጨረሻም የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ካህን "ወንድሜ ሆይ! እኔ ማክሰኞ ቀን በአባታችን በአብርሃም በዓል ዕለት እሞታለሁ" በማለት የሚያርፉበትን ቀን ነገሩት። በተናገሩትም መሠረት ከምንኵስናቸው በፊት 20 ዓመት ከምንኩስናቸው በኋላ 8 ዓመት ኖረው በ28 ዓመታቸው ሰኔ 28 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ዐረፉ። ጻድቁ ራሳቸው በተከሏትና በጸለዩባት በደብረ መድኀኒት ቅድስት ሥላሴ ባምብቆ ከተቀበሩ በኋላም ብዙ ተአምራት አድርገዋል። ዝክራቸውን ያደረገ በጸሎታቸው የተማጸነ በዚህ ዓለም ከመከራ ሥጋ፣ በሚመጣውም ዓለም ከመከራ ነፍስ እንደሚድን ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ቃልኪዳን ስለገባላቸው የባምብቆ ሕዝብና የዛውል ሕዝብ ሰኔ 28 ቀን በዓላቸውን በታላቅ ክብር ያከብራሉ። ከአቡነ ክፍለ ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሰኔ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ የእግዚአብሔር ከተጠራባቸው በፍርሀት ይታዘዙ ለነበሩት፤ ዳግመኛም ለነቢዩ ዕዝራ ታቦተ ጽዮን ባዘነች ሴት አምሳል እንደታየችው እንዲሁ ለአባታችንም አንዲት ያዘነች ሴት በራእይ መጥታ ዕጣን በማይታጠንበትና መሥዋዕተ ቍርባን በሌለበት ቦታ እንደ ሽኮኮ በጉድጓድ ውስጥ እንዳስቀመጧት ለነገረቻቸው #አቡነ_ክፍለ_ሥላሴ_ዘዛውል_ወዘባንብቆ_ዕረፍታቸው_በዐል እግዚአብሔር አምላከ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ክፍለ_ሥላሴ_ዘዛውል_ወዘባንብቆ፦ ከአባታቸው ከተክለ ማርያም ወልደ ዘኪዎስ እና ከእናታቸው ከርግበ ዳዊት ዛውል በሚባለው ቦታ ተወለዱ። በመጀመሪያ የወጣላቸው ስም "መሓርየ እግዚ" የሚባል ነው። አእምሮአቸው ንጹሕና ብሩሕ የሆኑት አቡነ ክፍለ ሥላሴ በልጅነታቸውም በጎችንና ፍየሎችን እያገዱ (እየጠበቁ) ወላጆቻቸውን ያገለግሉ ነበር።
❤ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የተመረጡ ስለነበሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ይታወቁ ነበር ስመ ሥላሴን በከንቱ አያነሡም ነበር። ስመ እግዚአብሔርም ከተጠራባቸው በፍርሃት ይታዘዛሉ። እረኞችም ከብቶቻቸውን እንዲመልሱላቸው የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩባቸው ይታዘዟቸው ነበር። በዚኸም ነገር አቡነ ክፍለ ሥላሴ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእን መሰሉ።
❤ በትግራይና በጎንደር በእጅጉ የሚታወቀው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩበት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይልም ነበር። ከልጆችም ጋር ሲጫወቱ ልጆቹ "ስለ እግዚአብሔር ብለህ ይህን አድርግልን" ሲሉት ያደርግላቸዋል። በእረኝነት ሳሉ ምሳውንም ሆነ እራቱን ለምስኪኖች ይሰጣል። ለእግዚአብሔር ስም እጅግ ቀናተኛ ስለነበረ ስሙን በመፍራት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው "ይህን ክፉ ነገር በራስህ ላይ አድርግ" ባሉት ጊዜ እንኳን በራሱ ላይ አንዳች ክፉ ነገር ወይም አደጋ ለማድረስ ወደኋላ አይልም ነበር። ይህንንም ሊፈትኑት ብለው አንድ ቀን ስለታም ጦር አምጥተው "ስለ እግዚአብሔር ብለህ እስቲ ራስህን በዚህ ስለታም ጦር ትወጋ ዘንድ ና" ባሉት ጊዜ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ በሕሊናው እንደወሰነ እርሱም በቁርጥ ሕሊና ሆኖ ራሱን በጦሩ ሊወጋ ሲል ዘለው ያዙት።
❤ በሌላም ጊዜ እንዲሁ ሊፈትኑት በጭነት ምክንያት ጀርባው የቆሰለ አህያ አምጥተው ዐቢየ እግዚእ "ስለ እግዚአብሔር ብለህ የዚያችን አህያ ቁስሏን ላስ" አሉት። እርሱም ያን ጊዜ "ርኩስን ብስም ኃጢአት ይሆንብኛል፣ አይሆንም ካልኳቸው ደግሞ ስመ እግዚኣብሔርን ጠርተንበት እምቢ አለ ስለሚሉ የፈጣሪዬን ስም መዳፈር ይሆንብኛል" ብሎ በልቡ አሰበና ያን ጊዜ ይስም ዘንድ ተመለሰ። ባልንጀሮቹም በቁርጥ ሕሊናው እንደወሰነ ባወቁ ጊዜ ሊያደርገውም ሲሔድ ተመልክተው ቶሎ ብለው ሮጠው ከኋላው ያዙት። እርሱም "እኔስ የፈጣሪዬን ስም እፈራለሁ ስሙን ተደፋፍሬ በምድር በሕይወት ከምኖር ሞት ይሻለኛል" አላቸው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም እንዲሁ በፈሪሃ እግዚአብሔር ይታወቃሉ። ስመ ሥላሴን በከንቱ ፈጽመው ጠርተው አያውቁም፣ ስመ እግዚአብሔር ከተጠራባቸው ማንኛውንም ነገር ያደርጉ ነበር።
❤ ከዚኸም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ወደ አቡነ ሳሙኤል ገዳም ደብረ ዓባይ ሔደው በሚያስደንቅ ትሕትና ለአባቶች እየታዘዙ መዝሙረ ዳዊትን ተማሩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አጠኑ። ከዚያም የአባቶችን ቡራኬ በመቀበል ወደ ደብረ ቢዘን በመሔድ የአቡነ ፊሊጶስንና የአቡነ ዮሐንስን ልጆች በማገልገል የቅዱሳኑን አሠረ ፍኖታቸውን ተከትለው በተጋድሎ ኖሩ። ሌሊትና ቀን በእያንዳንዱ ሥርዓተ ጸሎት ላይ አንድ አንድ ሺህ እየሰገዱ ይጸልዩ ስለነበር የእንቅልፍና የዕረፍት ጊዜ አልነበራቸውም። በእንደዚህም ዓይነት ተጋድሎ ከቆዩ በኋላ ከአቡነ ፊሊጶስ 6ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ገብረ ማርያም እጅ ምንኵስናን ተቀበሉ።
❤ ከመነኰሱም በኋላ መነኰሳቱ እህል እንዲፈጩ ሲያዟቸው አባታችን ክፍለ ሥላሴ በመታዘዝ ወደ እህል መፍጫው ቤት ገቡ፣ ነገር ግን አባታችን እህል መፍጨት አይችሉም ነበር። እርሳቸውም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ ሁሉም ሊፈጭ ተዘጋጅቶ የነበረው እህል በተአምራት ተፈጭቶ ተገኘ። መነኰሳቱ ግን ይህን አላወቁም ነበር።
❤ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ከዚኽ በኋላ ወደ ሀገረ ደምብያ ሔደው ከጳጳሱ እጅ ሥልጣነ ክህነትን ተቀበሉ። ከዚያም ሲመለሱ መረብ ወንዝ ሲደርሱ አብሯቸው የነበረውን የሥጋ ወንድማቸውን "ኦ ወንድሜ እነሆ በሥጋ የወለደን አባታችን ዛሬ ዐረፈ" በማለት የአባታቸውን መሞት በመንፈስ ቅዱስ ዐውቀው ነገሩት ወደ ሀገራቸውም ከገቡ በኋላ የሀገራቸው የውል ሰዎች ያላወቁ መስሏቸው የአባታቸውን መሞት ለአቡነ ክፍለ ሥላሴ ነገሯቸው። አባታችንም "አባቴ እንደሞተ አስቀድሜ ዐውቄያለሁ፤ እግዚአብሔር ወደ ገነት እንዲያስገባው በጸሎት አግዙኝ እንጂ አታልቅሱ" አሏቸው። ሰዎቹም የተሰጣቸውን ጸጋ አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
❤ ጻድቁ ወደ ደብረ ቢዘን ተመልሰው ሔደው በክህነት እያገለገሉ ሳለ ወደ አቡነ እንድርያስ ሰፍኣ ደብረ ጽጌ ገዳም ለመሔድ አሰቡ፤ ነገር ግን ትልቅ ዋርካ ያለበትን ባምብቆ የተባለውን ተራራ በራእይ ከተመለከቱ በኋላ ወደዚያ እንዲሔዱ እምላካዊ መልእክት መጣላቸው። እርሳቸውም የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ በደስታ ተቀብለው ወደ ባምብቆ በመሔድ ቤተ ክርስቲያን አንጸው የቅድስት ሥላሴን ታቦት አስገብተው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፤ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈሩ።
❤ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በባምብቆ ሳሉ ታቦተ ጽዮን ለነቢዩ ዕዝራ ባዘነች ሴት አምሳል እንደታየችው እንዲሁ ለአባታችንም አንዲት ያዘነች ሴት በራእይ መጥታ ዕጣን በማይታጠንበትና መሥዋዕተ ቍርባን በሌለበት ቦታ እንደ ሽኮኮ በጉድጓድ ውስጥ እንዳስቀመጧት ነገረቻቸው። በዚያም በበረሓ ውስጥ ደብቀው ያስቀመጧት ዮልዮስ የተባለ አንድ አመጸኛ መኰንን ቤተ ክርስቲያንን ሊያቃጥል በፈለገ ጊዜ ነው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም ወደተነገራቸው ቦታ በመሔድ ካህናቱን በጉድጓድ ውስጥ ስላስቀመጡት ታቦት ሲጠይቋቸው እነርሱ ግን "የደበቅነው ታቦት የለንም" አሏቸው። አባታችንም "ወንድሞቼ ሆይ! እውነቱን ተናገሩ" በማለት በራእይ የተመለከቱትን ነገር ነገሯቸው። ካህናቱም ፈርተው "አዎን አባታችን ይቅር በሉን፣ ዮልዮስን ፈርተን ታቦቱን ዋሻ ውስጥ ደብቀነዋል" ብለው ቦታውን አሳዩአቸውና አውጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን መለሱት።
❤ ከዚህም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በገዳማቸው በጽኑ ተጋድሎ ላይ ሳሉ የጌታችን ጾም በደረሰ ጊዜ ልጆቻቸውን ጠሩና "ሰባት ክንድ የሚሆን ጉድጓድ ቆፍራችሁ እኔ እዚያ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ጉድጓዱን ሸፍኑት፣ ከላይ የዕንጨት ሰሌዳ አድርጋችሁ በድንጋይና በጠጠር አድርጋችሁ በመቃብር ምልክት ዝጉት" በማለት ነገሯቸው። ዳግመኛም "ሰዎች የት ናቸው? ብለው ቢጠይቋችሁ የት እንዳለ አናውቅም በሏቸው፤ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሲሆን ግን ከፍታችሁ አረጋግጡ" አሏቸው።
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤️
❤️ #ሰኔ ፳፯ (27) ቀን።
❤️ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ ለሆነው ሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስን_ላጠመቀው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ሐናንያ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰንደላት ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ቶማስ፣ ከእርሱም ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶች ለዕረፍታው መታሰቢያ በዓል፣ ጌታችን ስለ እርሱ ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው በቅዱስ ወንጌል ለተናገረለት #ለድኀው_ለቅዱስ_አልዓዛርም_ለመታሰቢያው በዓሉና #ለመድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከማማስና_ከሲላስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ሐናንያ፦ ይህንንም ቅዱስ ሐዋርያት በደማስቆ ከተማ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በውስጧም ሕይወት ሰጭ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ዳግመኛም በቤተ ገብርኤል ውስጥ ሰብኮ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት ብዙዎቹን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው እውነተኛውንም የሃይማኖት ብርሃን አበራላቸው።
❤️ ይህም ሐናንያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ይቅር ባይ ጌታችን በቸርነቱ ከክህደቱ በጠራውና ምርጥ ዕቃ በአደረገው ጊዜ ያጠመቀው እጁንም በራሱ ላይና በዐይኖቹ ላይ ጭኖ ያዳነው እርሱ ነው።
❤️ ጌታችንም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ በስብከቱም ብዙዎች አሕዛብ አመኑ ከአይሁድም ብዙዎቹን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸው።
❤️ ከዚህም በኋላ ዐመፀኛው መኰንን ሉክያኖስ ይዞ ታላላቅና አስጨናቂ ሥቃይን አሠቃየው ጎኖቹንም ሠንጥቆ በእሳት መብራቶች አቃጠለው ከዚህም በኋላ ከከተማው አውጥተው በደንጊያ እንዲወግሩት አዘዘ በዚያም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነፍሱን ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐናንያ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #ሰንደላት_ከሚባል_አገር_የሆነው_ሰማዕቱ #ቅዱስ_ቶማስ፦ ይህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ አንድ ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንኰንኑ ሔዶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይታመን ዘንድ አዘዘው።
❤️ ያን ጊዜም ተነሥቶ የገመድ አለንጋ ይዞ ብቻውን ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ። መኰንኑም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ጸሐፊውም ሊያደርገው ቃል ኪዳን ገባለት ቅዱስ ቶማስም ተቆጥቶ ያቺን አለንጋ አውጥቶ መኰንኑን ብዙ ግርፋት ገረፈው የመኰንኑን ሎሌዎችም ይዘው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በብረት መጋዝ ሠነጠቁ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ርዳታ ለመነ ወዲያውኑም መልአኩን ልኮ አዳነው።
❤️ ከዚህ በኋላ በእሥር ቤት አሠሩት የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ስለ ታመመው ልጁ ለመነው እርሱም ያንን የገመድ አለንጋ ሰጠውና "ይህን አለንጋ በልጅህ ላይ አኑር" አለው እንዲሁም አደረገ። ያን ጊዜም ልጁ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አቅርቦ "ለአማልክት ሠዋ" አለው ቅዱስ ቶማስም "በፊትህ ዕሠዋ ዘንድ ና እንሒድ" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ዕውነት መስሎት ደስ አለው ወደ ጣዖቶቹ ቤትም ወሰደው ያን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ጣዖታቱን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ። ወዲያውኑ ሁሉም ጣዖታት ተሰባበሩ ሰይጣኑም በመኰንኑ ላይ ተቀመጠ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ እስሚታመን ድረስ አነቀው።
❤️ አሕዛብም ይህንን ድንቅ ነገር አይተው እጅግ አደነቁ "ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" እያሉም ጮኹ በእርሱም አመኑ። ያላመኑ ግን በጨለማ ቤት ውስጥ አኖሩት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ከብዙ ሥቃይም የተነሣ ከአፉ ደም እየፈሰሰ ዐሥራ አምስት ቀን በዚያ ተቀመጠ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ ፈወሰው። አንዲት ሴት ዕውር ልጅ ነበራት ከዚያም ደም ወስዳ የልጅዋን ዐይን አስነካችው ወዲያውኑም አየ።
❤️ ቅዱስ ቶማስንም ከወህኒ ቤት አውጥተው ሴት አንበሳ ሰደዱበት ወደርሱም በደረሰች ጊዜ እግሮቹን ላሰች ሰገደችለትም። ዳግመኛም በብረት መንደልቶ አፋ ላይ ደበደቡት በዚያን ጊዜም በሥቃይ ውስጥ ከእርሱ ጋራ ከበንደላ አገር ቅዱስ በብኑዳ ከበልኪም አገር ቅዱስ ሙሴ ነበሩ። እርስ በርሳቸው አንዱ አንዱን ያጽናናው ነበር።
❤️ ከዚህም በኋላ ቅባትና የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በቅዱስ ቶማስ ራስ ላይ ደፉት ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። እንደገናም አባለ ዘሩን ቈርጠው በአውድማ ውስጥ አበራዩት ደግመውም ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ ላይ ሰቅለው አሠቃዩት።
❤️ ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመው ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ወደ እንዴናው ከተማ ሊወስደው ይዞት ተነሣ ጣው ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ የቅዱስ ቶማስን ራስ ቆረጡት በዚያም ምስክርነቱን ፈጸሙ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ከእርሱ ጋራ መከራ ተቀበለው የሞቱ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶችም እርሱ ሥቃይ በተቀበለበት ወራት የሰማዕትነት እክሊል ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 27 ሰንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ለከ_ሐናንያ_ኵኑን። በዝብጠተ ድንቡስ ክቡድ እንተ አፍአሁ ኀፂን። ዘእንበለ እድ መጺአ እምኀበ ሀሎ መካን። ይቀጥቀጥ ከመ ልሕኵት ርእስ ፀርየ ሰይጣን። ውስተ ክሣድከ ዘተአሥረ ዕብን"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 27።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦"ነዳይ ወቊሱል አነ። መድኃኔ ገጽየ እግዚአብሔር ተወክፈኒ። እሴብሕ ለስመ አምላኪየ በማኅሌት"። መዝ 68፥29-30። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥28-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥9-27 እና የሐዋ ሥራ 9፥10-20። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥19-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ሐናንያ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሰኔ ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ገብርኤል_ለበዓሉ_መታሰቢያ እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ ለተከበረችበትና #ለታላቁ_ነቢይና_መስፍን ለነቢያት አለቃ #ለቅዱስ_ሙሴ ደቀ መዝሙር ለነዌ ልጅ #ለቅዱስ_ኢያሱ_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ በዚች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ #የቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው። በውስጧም ከቤተ ክርስቲያንዋ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር።
❤ የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የነዌ_ልጅ_ነቢዩና_መስፍን_ቅዱስ_ኢያሱ፦ ይህም ከታናሽነቱ ጀምሮ ለሙሴ አንገቱን ዝቅ አድርጎ የሚታዘዝ ፍጹም ትሑት ሆነ ስለዚህም በሙሴ ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ አደረበት። ነቢዩ ሙሴም ከአረፈ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤልን ሕዝብ ተረከባቸው።
❤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው "ከሙሴ ጋራ እንደኖርሁ ከአንተም ጋራ እኖራለሁ ጽና በርታ ለባለሟሌ ሙሴ ያዘዝሁትን ሕጌን ጠብቅ ከእርሱም ፈቀቅ አትበል ሕጉንም ትጠብቀውና በሱም ትጸና ዘንድ በውስጡም የተጻፈውን ታደርገው ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንደበትህ ማንበብን አያቋርጥ"። ኢያሱም ሌቡ ጸና ሰላዮችንም ወደ ኢያሪኮ ላከ ሀገሪቱንም አይተው ሲመለሱ የኢያሪኮ ሰዎች አዩአቸው ሰላዮችም እንደሆኑ አውቀው ተከተሏቸው። እነርሱም ረዓብ በሚሏት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሸሸጉ እርሷም ሠወረቻቸው እነርሱም በሚመጡ ጊዜ ከቤተ ሰቦቿና ከዘመዶቿ ጋራ እንደሚያድኗት ቃል ገቡላት በደኅናም ሸኘቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገረ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ታቦት ሕግ ተሸክመው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ቆመው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እስከሚሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ እግዚአብሔር እንደ ግድግዳ አቁሞት ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ በግንብ የተከበበች ኢያሪኮን ሰባት ቀን ዞራት ከእርሱም ጋራ የልዑል ታቦተ ሕጉ ነበረች ቅጽሮቿንም አፈረሰ በውሷም የሚኖሩ አሕዛብን ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር ገደለ ሁሉንም አጠፋቸው። አሕዛብ ሁሉ የእስራኤልን ልጆች ፈሩአቸው ከመፍራታቸውም ጽናት የተነሣ የገባዖን ሰዎች ተንኰል አደረጉ ስንቃቸውን ሰንቀውና አዘጋጅተው መጡ አሮጌ አቁማዶቻቸውን ያረጁና የተቀደዱ የተጠቀሙም የወይን ረዋቶችን በትክሻቸው ተሸክሙ። ጫማቸውም ያረጀና የተተበተበ ነበር። ለስንቅም የያዙት እንጀራ የደረቀና የሻገተ ነበር።
❤ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ወደ ገልገላ መጥተው "እኛ ከሩቅ አገር መጥተናል አሁንም ለእኛ ማሉልን" አሏቸው። የእስራኤልም ልጆች ኤዎያውያንን "ከእናንተ ጋራ እንዴት መሐሊን እንማማላለን አሁንም በአቅራቢያችን ትኖሩ እንደሆነ ተጠንቀቁ" አሏቸው። ኢያሱንም "እኛ ከሩቅ አገር የመጣን ባሮችህ ነን" አሉት እርሱም "ከወዴት ናችሁ ከወዴትስ አገር መጣችሁ" አላቸው። እነርሱም "እኛ ባሮችህ በፈጣሪህ እግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ አገር መጣን በግብጻውያን ያደረገውን ሁሉ በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁሉቱ በአሞሬዎን ነገሥታትም ያደረገውን ሁሉ ሰምተን መጥተናል" አሉት።
❤ "የአገራችን ሰዎች ሁሉና አለቆቻችን ለመንገድ ስንቅ ያዙ ትቀበሏቸውም ዘንድ ሒዱ እኛ ባሮቻችን ነን አሁንም ለእኛ ማሉልን በሉአቸው" አሉን። "እነሆ ወደ እናንተ እንመጣ ዘንድ ከቤታችን በወጣንበት ቀን ይህ እንጀራችን ትኩስ ነበር አሁን ግን ሻግቷል ደርቋልም ይህም የወይን ረዋት አዲስ ሳለ መላንበት አሁን ግን ተራቁቷል አርጅቶም ተቀድዷል መንገዳችን እጅግ የራቀ ነውና ይህም ልብሳችን ይህም ጫማችን አርጅቷል" አሏቸው።
❤ መኳንንቱንም ስንቃቸውን ተቀብለው አዩ የእግዚአብሔርንም ቃል አልጠየቁም ኢያሱም ከነሱ ጋራ ሰላምን አደረገ ሊያድናቸውም ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ የሕዝቡም አለቆች ማሉላቸው። ከሦስት ቀን በኋላም እስራኤል ከቅርብ እንደሆኑ ሰሙ። ኢያሱም በቅርብ እንደሆኑ በሰማ ጊዜ "በሽንገላ ለምን ወደእኛ መጣችሁ አሁንም እግዚአብሔር ቤትና ለእኛ ባሮች ትሆናላችሁ" አላቸው።
❤ የአሞሬዎን ነገሥታትም የገባዖን ሰዎች ሔደው ለእስራኤልና ለኢያሱ እንደ ተገዙ በሰሙ ጊዜ እነዚህ አምስቱ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬሮሮን ንጉሥ፣ የኢያሪሞት ንጉሥ፣ የለኪሶን ንጉሥና የአዶላም ንጉሥ ተሰብስበው ዘመቱ መጥተውም ገባዖንን ከበቡአት ሊዋጉም ጀመሩ።
❤ የገባዖን ሰዎችን በገልገላ ውስጥ ወደ እስራኤል ሰፈር ወደ ኢያሱ ልከው "ባሮችህን ለመርዳት እጅህ አትስነፍ ከተራሮች ላይ የሚኖሩ የአሞሬዎን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ወደ እኛ መጥተህ ርዳን ፈጥነህ አድነንም" አሉ። ኢያሱም ከጌልገላ ወጣ ሰልፈኞችም የሆኑ ሕዝብ ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው "በእጅህ እጥላቸዋለሁና በፊታችሁም አንድ ስንኳ የሚቀር የለምና አትፍሯቸው" አለው ኢያሱም ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት በሌሊት ደረሰባቸው።
❤ እግዚአብሔርም ከእስራኤል ፊት የተነሣ አስደነገጣቸው ኢያሱም ብርቱ ጥፋትን አጠፋቸው ከእርሱም ወደ ቢቶሮን ቊልቊለት በሸሹትም እግዚአብሔር የበረድ ድንጋይ ከሰማ አውርዶ ጨረሳቸው። የእስራኤል ልጆች በጦራቸው ከገደሏቸው በደንጊያ በረዶ የሞቱ በዙ። ያንጊዜም እግዚአብሔር አሞሬዎንን በእስራኤል ልጆች እጅ አሳልፎ በሰጣቸው ጊዜ ኢያሱ ፀሐይ በገባዖን ጨረቃም በኤሎም ቈላ ትቁም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ ፀሐይና ጨረቃም ቆሙ። ጠላቶችንም ሁሉንም አጠፋቸው ከእነርሱም የቀረ የለም።
❤ ከዚህም በኋላ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስትን አካፈላቸው ያለ ዕውቀት በስሕተት ሰው የገደለ በውስጡ ይማጠን ዘንድ ሰባት መማጸኛ ከተሞችን እግዚአብሔር እንደ አዘዘው ሠራ።
❤ ዕድሜውም መቶ ሃያ በሆነው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሰበሰባቸው የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ በአምኮተ እግዚአብሔርም እንዲጸኑ ትእዛዞቹንም እንዳይተላለፋ አዘዛቸው። እንዲህም አላቸው "እርሱ ፈጣሪያችን ቀናተኛ ነውና ጣዖት ብታመልኩ ያጠፋችኋል ሕጉን ብትጠብቁ ግን የበረከት ልጆች ትሆናላችሁ። ከዚህም በኋላ ሰኔ 26 ቀን በሰላም ዐረፈ ያዕቆብ ከኤሞርልጆች በመቶ በጎች በገዛው ናብሎስ በሚባል ቦታም ተቀበረ ሠላሳ ቀኖችም ያህል ታላቅ ልቅሶ አለቀሱለት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩና በመስፍኑ ቅዱስ ኢያሱ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 26 ሰንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወቀተለ ነገሥተ ፅኑዓን። ለሴዎን ንጉሠ አሞሬዎን። ወለዓግ ንጉሠ ባሳን"። መዝ 134፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 4፥1-17፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥35-44። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥36-44። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የቅዱስ ኢያሱ የዕረፍት ለሁላችንም ይሁንልን።
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤️
❤️ #ሰኔ ፳፭ (25) ቀን።
❤️ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው #የጌታችን_ወንድም_ለተባለው ለፀራቢው ለዮሴፍ ልጅ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ይሁዳ_ለዕረፍት_በዐል፣ ለእስክድርያ አርባ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና #ለክረምት_መግቢያ_ቀን በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #ቅዱስ_ይሁዳ፦ ይህም ቅዱስ ቁጥሩ ከሰባ ሁለቱ እርድእት የሆና የፀራቢው የዮሴፍ ልጅ የጌታችን ወንድም የተባለ ነው። ይህም ሐዋርያ በብዙ አገሮች ሰበከ ወደ አንዲት ደሴትም ገብቶ በውስጧም ሰበከ ሰዎቿንም በጌታ አሳመናቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው።
❤️ ከዚህም ወደ ሮሃ አገር ሒዶ የሮሃ ንጉሥ አውጋንዮስን ከደዌው ፈወሰው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ከዚያም ደግሞ ሐራፒ ወደሚባል አገር ሒዶ በውስጧ ሰበከ ከሰዎቿ ብዙዎቹን አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው። የዚያችም አገር ገዥ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ችንካር ያለው ጫማ በእግሮቹ ውስጥ አድርጎ አንድ ምዕራፍ ያህል አስሮጠው ከዚህም በኋላ ሰቅሎ በፍላፃ ነደፈው ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ።
❤️ ከመከረውም አስቀድሞ ለምእመናን መልእክት ጽፎ ላከ እርሷም ከሐዋርያት መልእክቶች ሰባተኛ የሆነች ምሥጢርን የተመላች ናት በእርሷም ብዙዎች አረማውያንን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አስገባቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ይሁዳ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አባ_ጴጥሮስ፦ ይህም አባት ለእስክንድር ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አራተኛ የሆነ ነው። ከመሾሙ በፊት የማርቆስ መንበር ያለ ጳጳሳት ለብዙ ዘመናት ኖረ የእስላሞች ንጉሥና መኳንንቶቹ አልፈቀዱላቸውም ነበርና።
❤️ ከዚህም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ መኰንን በእስክንድርያ ከተማ ላይ ተሾመ ያንጊዜም የአገር ሽማግሌዎች ወደ ርሱ ተሰብስበው ሊቀ ጳጳሳት እንደ ሌላቸው ኀዘናቸውን ነገሩት። እርሱም ደብረ ማሕው ወደሚባለው ወደ ደብረ ዝጋግ ወጥተው እንዲጸልዩ ለራሳቸውም ሊቀ ጳጳሳት እንዲሾሙ አዘዛቸው። በዚህም ነገር ደስ ብሏቸው ቀሲስ አባ ጴጥሮስን ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በእርሱም ደስ አላቸው።
❤️ በዚያም ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ሞተ የአንጾኪያ አገርም ያለ ሊቀ ጳጳሳት ትኖር ነበር የአንጾኪያ ምእመናንም ለእስክንድርያ ከተማ አባ ጴጥሮስ እንደ ተሾመ በሰሙ ጊዜ እነርሱም የተማረ ደግ ሰው ለአንጾኪያ ሾሙ ስሙም ታውፋንዮስ ይባል ነበር። እርሱም ስለ ቀናች ሃይማኖት በመልእክቶቻቸው ይገናኙ ነበር። ከእርሱም እያንዳንዱ በባልንጀራው ምክር በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ይሰብክ ነበር ወደ አገራቸውም መግባት አልተቻላቸውም ነበርና አባ ጴጥሮስም በግብጽ ደቡብ በአንባንያ ገዳምና በዝጋግ ገዳም ይኖር ነበር አባ ታውፋንዮስም ከአንጾኪያ ከተማ ውጭ በአፍቆንያስ ገዳም ይኖር ነበር።
❤️ በዚያም ወራት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ሰባት መቶ ገዳማትና ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንም ያሉባቸው ሠላሳ ሁለት መንደሮች ነበሩ በግብጽ አውራጃ ሁሉና በላይኛው ገብጽ በአስቄጥስ ገዳማት የሚኖሩ መነኰሳት እንዲሁም ኖባና ኢትዮጵያ በዚህ በአባ ጴጥሮስ ሥልጣን ሥር ነበሩ። እኒህ ሁሉ ሃይማኖታቸው የቀና ነበር። በትእዛዙም ጸንተው ይኖሩ ነበር። እርሱም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ወደእርሳቸው መልእክቶችን መጻፍ አያቋርጥም ነበር።
❤️ የእስክንድርያን ገዳማት ሁሉና መንደሮችንም እየዞረ ያስተምራቸውና ይመክራቸው ያጽናናቸውም ነበር። ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስና ዐዋቂ የሆነ ደቀ መዝሙር የነበረው እርሱም ሊቀ ጵጵስናው ሥራ ሁሉ ይራዳው ነበር።
❤️ ይህም አባት ጴጥሮስ አንዳንድ ጊዜ ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ነበር የሰዎቿንም ሥራቸውን ተመልክቶ ያስተምራቸውና በሃይማኖት ያጸናቸው ነበር። በዐሥራ ሁለት ዓመት የሹመቱ ዘመን እንደ ሐዋርያት መንጋዎቹን እየጠበቀ እንዲህ በሹመቱ ኑሮ ሰኔ 25 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 25 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ለይሁዳ_ለእግዚአብሔር_ገብሩ። በቀኖተ ኀፂን ርሱን ዘተቀነዋ አእጋሩ። ሃይማኖተ ወንጌል ፍፁመ እንዘ ይሜህሩ። ውስተ መክፈልቶሙ ሶበ መክፈልቶ ደመሩ። ምስለ ሐዋርያት ደርገ ተጽሕፈ ተዝካሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_25።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ የዕለቱ ምስባክ፦"ወአንተ ገበርከ አድባረ ወምድረ ኵሎ። ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ። ወተዘከር ዘንተ ተግባረከ"። መዝ 73፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 6፥7-13፣ ይሁ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 14፥16-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 14፥18-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ይሁዳ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤️
❤️ #ሰኔ ፳፬ (24) ቀን።
❤️ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አስቀድሞ ገዳይ ቀማኛ፣ ዘማዊና ያላመኑ ለነበሩ በንስሐ ተመልሰው በአባ መቃርስ እጅ ከተጠመቁ ከመነኰሱ በኋላ በግብፅ በአስቆጥስ ገዳም ታላቅ ተጋድሎ አድርገው በሰማዕነት ለዐረፉ #ለአባ_ሙሴ_ጸሊም_ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ፣ ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለእናታች ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አባ_ሙሴ_ጸሊም፦ ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ፣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር። አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደ ሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል። እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበር ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ "ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ" ይል ነበር ደግሞም በልቡ "የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ" ይል ነበር።
❤️ ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው። ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው። አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም "እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ" አለው። አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው። እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲለህም አለው "ታግሠህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ።
❤️ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ። ሰይጣንም ቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብሉና በመጠጡ መዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽናንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር።
❤️ ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእርሱ ሩቅ ነበረና እንዲም እያደረገ በመጋደል በብዙ ዘመናት ኖረ። ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ።
❤️ ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ። እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበ ምኔት ሆነ።
❤️ ከዚህም በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም ሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ በአቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር አረጋውያኑንም "ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት" አላቸው እነርሱም "መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መካም አደረጉብህ" በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው "ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ"።
❤️ በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህም በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጒድጓዶችን ሁሉ ሞላ። አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም "እግዚአብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን" አላቸው።
❤️ በአንዲት ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋር ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ" አላቸው አባ ሙሴም "አባቴ ሆይ ምናልባት እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና" ብሎ መለሰ።
❤️ ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት "እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ" አላቸው እነርሱም "አባታችን አንተስ አትሸሽምን" አሉት እርሱም "በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለ ሚለው የእግዚአብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ" አላቸው። ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስለ አልፈለጉ ከእርሱ ጋር ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መላአክ አየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም በአየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕታትንም አክሊል ተቀበለ።
❤️ ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርስቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው የንስሐን ኃይሏን ተመልከቱ።
❤️ ሥጋው በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሙሴ ጸሊም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 24 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ዕብል_ለሙሴ_ጸሊም። እንተ ነበረ ዕጉሠ ውስጤ ገዳም። ሶበ ተዘከረ ኵሎ እከያቲሁ ዘቅድም እትቀተል ይቤ በመጥባሕተ በርበር ዮም። ዘእንበለ ደም ኢይነጽሕ ደም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_24።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ኃጢአትየ ነገርኩ ወአበሳየ ኢኀባዕኩ። ወእቤ አስተዋዲ ርእስየ ኀበ እግዚአብሔር በእንተ ኃጢአትየ። ወአንተ ኅድግ ጽልሑቶ ለልብየ"። መዝ 31፥5። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 10፥46-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 14፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥20-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ሙሴ ጸሊም የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ በአለፉም ጊዜ የደናግል ገዳማት ካሉበት ደረሱ ደናግሎም ወጥተው ተቀበሏቸው ቊጥራቸው ሰባት መቶ ነበር ከእነርሱ ጋራም እስከሚሰበሰቡ በቅዱሳን ፊት ይዘምሩ ነበር። ወደ ንጉሡ ከተማም በደረሱ ጊዜ ወደ ንጉሡ ከመግባታቸው በፊት በውኃ ያጥቧቸውና አዳዲስ ልብሶችን ያለብሷቸው ጀመሩ እንዲሁም ለሁሉ አደረጉ ቅዱስ አባ ኖብ ግን አልታጠበም ልብሱንም አልለወጠም።
❤ ወደ ንጉሡም በገቡ ጊዜ ከእነርሱ ቡራኬ ተቀበለ ቁስላቸውንም ሳመ እጅግም አከበራቸው ብዙ ገንዘብም ሰጣቸው እነርሱ ግን ለቤተ ክርስቲያን ከሚሆን ንዋየ ቅዱሳት በቀር ምንም ምን አልተቀበሉም ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶ ወደየአገራቸው በሰላም አሰናበታቸው። አባ ኖብም ወደ ቦታው ተመልሶ ዐረፈና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኖብ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 23 ስንክሳር
ዘንድ በጧት በነቃሁ ጊዜም ያንን የሞተ ልጅ አገኘሁ በነጋም ጊዜ አየሁት እነሆ የወለድሁት ልጄ አይደለም" አለች።
❤ ያቺ ሁለተኛዋ ሴትም "አይደለም ይህ ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው እንጂ ያንቺ ልጅ አይደለም ያንቺስ የሞተው ነው" አለች። በንጉሡም ፊት እንዲህ ተባባሉ። ንጉሡም "ሰይፍን አምጡ ደኅኛውንም ልጅ ከሁለት ቆርጣችሁ እኵሌታውን ለዚች እኵሌታውን ለዚያች ስጡ" አለ። ስለ ልጅዋ ማሕፀኗ ታውኳልና ልጅዋ ደኅና የሆነ ያቺ ሴት መልሳ ንጉሡን "ጌታዬ አይደለም መግደልስ አትግደሉት ደኅነኛውን ልጅ ለሷ ሰጧት" አለችው ያቺ ሴት ግን "አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእርሷም አይሁን" አለች። ንጉሡም መግደልስ አትግደሉት እሱን ለእሷ ስጧት ላለችው ለዚች ሴት ደኅነኛውን ሕፃን ስጧት እርስዋ እናቱ ናትና" አለ። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ የፈረደውን ይህን ፍርድ ሰምተው ቅን ፍርድን ይፈርድ ዘንድ የእግዚአብሔር ጥበቡ በሱ ላይ እንዳለ አይተዋልና በንጉሡ ፊት ፈሩ።
❤ ከዚህም በኋላ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዘመን በሆነ ጊዜ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሊያንፅ ጀመረ። በዐሥራ አንደኛውም ዘመነ መንግሥቱ ወሩ ባዕድ በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱንና ሥርዓቱን ሁሉ ፈጸመ በሰባት ዓመትም ውስጥ ሠራው የራሱንም ቤት በዐሥራ ሦስት ዓመት ሠርቶ ጨረሰ።
❤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔር ቤትና የራሱን ቤት በሃያ ዘመን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያመጣቴ ዘንድ ያን ጊዜ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆች የአባቶቻቸውንም ቤት አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም በሰበባቸው። የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን በሰባተኛው ወር በጥቅምት ተሰበሰቡ። የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ ካህናቱም ታቦትዋንና የምስክሩን ድንኳን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያለ ንዋየ ቅዱሳቱንም ሁሉ ተሸከመ። ንጉሡና እስራኤል ሁሉ በታቦትዋ ፊት ሥፍር ቊጥር የልላቸው በጎችና ላሞችን ይሠዉ ነበር። ካህናቱም ታቦቷን ከኪሩቤል ክንፎች በታች በቤቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስት ቅዱሳን ቦታዋ አገቧት። ኪሩቤል በታቦትዋ ቦታ ላይ ክንፋቸውን ጋርደዋልና ኪሩቤልም በስተላይ በኩል በቅድስተ ቅዱሳን ላይ ታቦትዋን ጋርደዋት ነበር። ከቅድስተ ቅዱሳንም ጋራ የተያያዙ ነበር። ቅዱሳን ኪሩቤል ከፍ ብለው ከቅድስተ ቅዱሳኑ አንጻር ላይ ሁነው ያያሉ በውጭ ግን አይታይም ነበር። ከግብጽ አገር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ጋራ ቃል ኪዳን ከገባባቸው ሙሴም በዚያ በኮሬብ ከአኖራቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ አልነበረም።
❤ ከዚህ በኋላ ካህናቱ ከቤተ መቅደስ በወጡ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ሁሉ ብርሃን መላው። የእግዚአብሔር ብርሃን በማደሪያው ቤተ መቅደስ መልቷልና ከብርሃኑ መገለጥ የተነሣ ካህናቱ ሥራቸውን መሥራትና ከፊቱ መቆም ተሳናቸው። ያን ጊዜ ሰሎሞን "እግዚአብሔር በደመና ውስጥ እኖራለሁ ብሏል"። "እኔም ለዘላለም የምትኖርበት ማደሪያ ቤተ መቅደስን በእውነት ሠራሁልህ" አለ።
❤ ንጉሡም በፊቱን መልሶ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መረቃቸው ወደ እግዚአብሔርም ረዥም ጸሎትን ጸለየ። ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ልመና ወደ እግዚአብሔር ለምኖ በጨረሰ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ከሰገደበት እጆቹንም ከዘረጋበት ከመሠዊያው ፊት ተነሣ። ቆሞም "የእስራኤልን ማኅበር እንደተናገረው ሁሉ ለወገኖቹ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጣቸው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን" ብሎ በታላቅ ቃል መረቃቸው።
❤ ከዚህ በኋላ ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕትን ሠዉ። ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት የሠዋቸው ሃያ ሁለት ሽህ ላሞችና አንድ መቶ ሃያ ሽህ በጎች ናቸው ንጉሡ ሰሎሞንና እስራኤል ልጆች ሁሉ ያንጊዜ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለቤተ መቅደስ ቅዳሴ ቤት አደረጉ።
❤ ቀድሞ በገባዖን እንደታየው ዳግመኛ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ታየው "በፊቴ የለመንኸኝ ልመናህንና ጸሎትህን ሰማሁ። እንደ ልመናህም ሁሉ አደረግሁልህ ስሜ በዚያ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖር ዘንድ የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ አከበርሁት ልቡናዬም ዓይኖቼን በመኑ ሁሉ በዚያ ጸንተው ይኖራሉ" አለው።
❤ ሰሎሞንም አርባ ዘመን ነገሠ ከመንገሡም በፊት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ መላ ዕድሜውም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነበር በሰላም ዐረፈ። ይህም ጥበብ የተሰጠው ንጉሥ ሰሎሞን ጥቅም ያላቸው ብዙዎች መጻሕፍትን ደርሶአል። እሊህም ትንቢትና ትምህርት ያለባቸው ምሳሌዎችንና መኃልዮች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አባ_ኖብ፦ ይህም ቅዱስ መነኰስ በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ የሚጋደል ጽሙድ ነበር። ዲዮቅልጥያኖስም ብዙዎች ሰማዕታትን ሊአሠቃይና ደማቸውን ሊያፈስስ በጀመረ ጊዜ በአንዲት ቀን ሰማንያ ሰማዕታትን አቅርቦ ደማቸውን አፈፈሰሰ።
❤ በዚያን ጊዜ አባ ኖብን አስታወሱት የእንዴናው ገዥ ወደሆነው ወደ አርያኖስ አቀረቡት። እርሱም "ለአማልክት ዕጠን ሠዋ ይህንንም የምንኵስና ልብስ ከላይህ አውጥተህ ጣል" አለው። አባ ኖብም "ይህ ሥራ ከቶ ከእኔ ዘንድ አይደረግም የክብር ባለቤት ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስንም አልተውም የረከሱ ጣዖታትንም አላመልክም" አለ። መኰንኑም በየራሱ በሆነ ሥቃይ እጅግ አሠቃየው ያም አባ ኖብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ኃይል ታግሦ ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አምስቱ አህጉር ሰደደው በዚያም በጒድጒድ ውስጥ ጣሉት በውስጡም ጌታችን ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ አጥፍቶ ደግ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን እስከሾመው ድረስ ሰባት ዓመት ኖረ።
❤ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን ሁሉ ፈትተው ወደርሱ እንዲአበርቧቸው ከእርሳቸው እንዲባረክ ወደ አገሮች ሁሉ ደብዳቤዎችን ላከ። ለመልእተኞችም እንዲህ አላቸው "ሁሉንም ወደእኔ ማድረስ ካልተቻላችሁ እጆቻቸውን በራሴ ላይ ጭነው ይባርኩኝ ዘንድ ክብር ያላቸውን ታላላቆችንና መምህራኑን አምጡአቸው"። ከእነርሱም ውስጥ የታወቁ አህናህ ከተባለ አገር አባ ዘካርያስ ከፍዩም መክሲሞስ ከአገረ ድኂን አጋብዮስ ከአገረ በላኦስ አባ ኖብ ናቸው የንጉሥ መልእክተኞችም በየአገሮች ሁሉ እየዞሩ የታሠሩ ቅዱሳንን ከእሥር ያወጡአቸው ነበር እነርሱም ደስ ይላቸው ነበር የተመሰገነ እግዚአብሔርንም ያመሰግኑት ነበር ይዘምሩለትም ነበር።
❤ የንጉሥ መልእክተኛም አባ ኖብን ከአምስቱ አገሮች ፈልጎ የአገሩ አንጻር ወደ ሆነች ወደ አገር በሰላ ወሰደው። በዚያም የብረት ልብስ ለብሶ ተቀምጦ ነበር የንጉሡ መልእክተኛም አገኘውና ከእርሱ ጋራ ወሰደው ወደ እንዴናውም እስከ ደረሱ በመርከብ ተሳፈሩ ክርስቲያኖችም ተሰበሰቡ ከውጣቸውም አራት ኤጲስቆጶሳት ነበሩ አባ ኖብንም ያለ ውዴታው ቅስና ሾሙትና የቊርባን ቅዳሴን ቀደሰ። በቅዳሴውም ፍጻሜ "ቅዱሳት ለቅዱሳን" ብሎ ጮኸ ይህም ማለት ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ሥጋው ከደሙ ይቀበል ማለት ነው በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ ንስሐ የገቡትን ኃጢአታቸውን ይቅ ሲላቸው አየው ሥጋውንና ደሙንም ከአስቀበላቸው በኋላ ወደ ንጉሡ ለመሔድ ተዘጋጁ ቊጥራቸውም ሰባ ሁለት ነበር ሠላሳ ሰባት ሠረገላም አዘጋጅተውላቸው እየአንዳንዳቸው በሠረገላው ተቀምጡ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሰኔ ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን #ለንጉሥ_ለቅዱስ_ዳዊት_ልጅ ለጥበበኛው ንጉሥ #ለቅዱስ_ሰሎሞን_ለዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን በዓል፣ በክብር ባለቤት #በኢየሱስ_ክርስቶስ ለታመነ #ለአባ_ኖብ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለወራዊ በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ሰማዕታት #ከመርቆሬዎስ_ከቶማስና_ፊልጶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የልበ_አምላክ_የቅዱስ_ዳዊት_ልጅ_ንጉሥ_ሰሎሞን፦ የዚህ የሰሎሞንም እናት ስም ቤርሳቤህ ነው ዳዊትም ሕግ ተላልፎ ከእርሷ ጋራ ስለ መበደሉ ባሏንም ስለ ማስገደሉ ጌታ በገሠጸው ጊዜ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ጌታም ንጹሕ ስለሆነ ንስሓው ይቅር አለው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሷን አገባትና ሰሎሞንን ወለደው ንጉሥ ዳዊትም ከእርሱ በኋላ ልጅዋ ሰሎሞን እንዲነግሥና በዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ ቃል ገባለት።
❤ እንዲህም ሆነ ሰሎሞን ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አዶንያስ እነግሣለሁ ብሎ ተነሣ ምክሩም ሁሉ ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ አብያታር ጋር ሆነ። እርሱም አዶንያስን ተከትለው ሰደዱት። አዶንያስም በሮጌል ምድር ምንጭ አጠገብ ባለ በኤልቲ ዘዘኤልቲ ላይ ፍየሎችን በጎችንና ላሞችን አርዶ የንጉሥ አሽከሮች የሆኑ የይሁዳ አርበኞችን ሁሉና የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ ጠራ።
❤ ከዚህም በኋላ አዶንያስ ይህን እንዳደረገ ለቤርሳቤህ በነገሩዋት ጊዜ ወደ ንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ገብታ ለንጉሡ ሰገደች ንጉሥ ዳዊትም "ምን ሆነሽ" አላት። "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል ብለህ ለእኔ ለባርያህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም አንተ ማልክልኝ እነሆ ዛሬ አዶንያስ ነገሠ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አንተ ግን አላወቅህም" አለችው። ከንጉሥም ጋራ ገና ስትነጋገር ነቢዩ ናታን መጣ ለንጉሡም "ናታን መጣ" ብለው ነገሩት። ወደ ንጉሡም ገባ በምድር ላይም በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ነቢዩ ናታንም "ከእኔ ቀጥሎ አዶንያስ ይንገሥ በዙፋኔም ላይ ይቀመጥ ያልክ አንተ ነህን ዛሬ ወርዶ በጎችንና ብዙ ፍየሎችን አርዶ የሠራዊቱ አለቆችንና የንጉሥ አሽከሮችን ሁሉ ካህኑ አብያታርንም ጠርቷልና በፊቱም ይበላሉ ይጠጣሉ አንዶንያስ ሽህ ዓመት ያንግሥህ ይሉታል" አለው።
❤ ዳዊትም መልሶ "ቤርሳቤህን ጥርዋት" አለና ጠሩዋት ገብታም በንጉሡ ፊት ቆመች። "በእግዚአብሔር ፊት እንደማልኩልሽ አሁንም በዚች ቀን እንደዚሁ እንዳደርግ ሰውነቴን ከመከራዬ ሁሉ ያዳናት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕያው ነው" ብሎ ማለ። በቤርሳቤህም አንገቷን ደፍታ በግምባርዋ በመሬት ወድቃ ለንጉሡ ሰገደች "ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ኑር" አለች።
❤ ንጉሥ ዳዊትም "የዮዳሄ ልጅ ብንያስና ካህኑ ሳዶቅን ነቢዩ ናታንንም ግራዝማቹንና ቀኝ አዝማቹን ጥሩልኝ" አለ። ንጉሡም ከእናንተ ጋራ የጌታችሁ አሽከሮችን ይዛችሁ ልጄ ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን አውርዱት"። በዚያም ነቢዩ ናታንና ካህኑ ሳዶቅ "ቀብታችሁ በእስራኤል ላይ አንግሡት" አላቸው። ቀንደ መለከት ንፉ "ሰሎሞን ሺህ ዓመት ያንግሥህ በሉ። ተከትላችሁም ውጡ ገብቶም በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ እርሱም ስለ እኔ ፈንታ ይንገሥ በሁሉቱ ነገድና በዐሥሩ ነገድ ይነግሥ ዘንድ እኔ አዝዣለሁ"።
❤ ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳን ቀርነ ቅብዑን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው ቀንደ መለከትንም ነፉ ሕዝቡም ሁሉ ተከትለውት ወጡ ከበሮም መቱ ታላቅ ደስታም አደረጉ ከድምፃቸውም የተነሣ ምድሪቱ ተናወጸች።
❤ ሰሎሞንም በመንግሥት ዙፋኑ ተቀመጠ። የንጉሡም አሽከሮች ጌታቸው ንጉሡ ዳዊትን ሊአመሰግኑ ገቡ። "እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያደርገው ዙፋኑንም ከዙፋንህ ይልቅ የበለጠ ያድርገው" አሉት። ንጉሡም በዐልጋው ሁኖ ሰገደ። እንዲህም አለ "ዐይኖቼ ሲያዩ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ልጅን ለኔ ለባሪያው ዛሬ የሰጠ የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን" አለ።
❤ ዳዊትም የሚሞትበት ወራት በደረሰ ጊዜ ልጁ ሰሎሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው። "እኔ ሰው ሁሉ በሚሔድበት በሞት ጎዳና እሔዳለሁ አንተ ግን ጽና ብልህ ሰውም ሁን። በሕጉ ጸንተህ ትኖር ዘንድ የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ትእዛዝን ጠብቅ እኔ እንዳዘዝሁህ እንዴት እንደምታደርግ ታውቅ ዘንድ በመሴ ሕግ የተጻፈውን ትእዛዙንና ሕጉን ፍርዱንም ጠብቅ ልጆችህ ሕጌን ቢጠብቁ በፊቴም በፍጹም ልቡናቸው በፍጹም ሰውነታቸው በዕውነት ጸንተው ቢኖሩ ከእስራኤል ዙፋን ላይ ሰው አይጠፋብህም ብሎ እግዚአብሔር ለእኔ የነገረኝ ቃሉን ያጸና ዘንድ ጠብቅ" ብሎ አዘዘው። ዳግመኛም ከኢዮአብና በሳሚ ወልደ ጌራ ላይ በቀል እንዲአደርግ አዘዘው እነርሱ እጅግ የከፋና ብዙ ክፋት የሠሩ ነበሩና።
❤ ከዳዊት ዕረፍትም በኋላ ሰሎሞን ከዚያ መሥዋዕትን ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ወደ ገባዖን ሔደ ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና ሰሎሞንም በገባዖን በዚያው መሠዊያ ውስጥ ሽህ መሥዋዕትን ሠዋ።
❤ እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት በሕልም ተገለጠለት "ለአንተ እሰጥህ ዘንድ በልብህ ያሰበውን ልመናን ለምን" አለው። ሰሎሞንም "በቅንነትና በእውነት በንጹሕ ልቡናም ከአንተ ጋራ በፊትህ ጸንቶ እንደኖረ ከአባቴ ከዳዊት ጋራ ታላቅ ቸርነትን አድርገሃል በዚችም ቀን ልጁን በዙፋኑ ላይ ታስቀምጠው ዘንድ ይህን ታላቁን ቸርነት አጽንተህለታል" አለው። "አሁንም አቤቱ አንተ ፈጣሪዬ ስለ አባቴ ስለ ዳዊት ፈንታ እኔን ባሪያህን አነገሥኸኝ እኔም መግቢያዬንና መውጫዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ። እኔ ባሪያህ ግን የማይቈጠር ብዙ ሕዝብ በሆነ በመረጥከው ወገንህ መፍረድ የሚችል የለምና ሰምቶ ለወገኖችህ በእውነት ፍርድን ይፈርድ ዘንድ ከክፉ ነገርም ለይቶ በጎውን ነገር ያውቅ ዘንድ ለባሪያህ ዕውቀትን ስጠው"። ሰሎሞን ይህንን ነገር ለምኖታልና ይህ ነገር እግዚአብሔርን በፊቱ ደስ አሰኘው።
❤ እግዚአብሔርም "ይህንን ነገር ከእኔ ለምነሃልና ለአንተም ብዙ ዘመንንና ባለጸግነትን አለመንህምና ጠላቶችህንም አጥፋልኝ ብለህ አልለመንህምና ነገር ግን ፍርድ መስማትን ታውቅ ዘንድ ለምነሃልና እነሆ እንዳልህ አደረግሁልህ። እነሆ ከአንተ አስቀድሞ እንዳልነበረ ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ እንዳይነሣ አድርጌ ብልህና አስዋይ ልቡናን ሰጠሁህ። ሰው በመንግሥቱ እንዳንተ እንዳልሆነ አድርጌ ያልለመንኽኝን ባለጠግነትንና ክብርንም በዘመንህ ሁሉ እሰጥሃለሁ" አለው። ሰሎሞንም ከእንቅልፋ በነቃ ጊዜ እውነተኛ ሕልም እንደ ሆነ ዐወቀ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በጽዮንም በእግዚአብሔር ታቦት ሕግ አንጻር ባለ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የሰላም መሥዋዕትን አቀበረ ለሰዎቹና ለሱም ታላቅ ግብዣ አደረገ።
❤ በዚያን ጊዜም ሁለት አመንዝራ ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥተው በፊቱ ቆሙ አንዲቱም ሴት "ጌታዬ ስማኝ እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን በአንድ ቦታም ወለድን እኔ በወለድሁ በሦስተኛው ቀን ይህች ሴት ወለደች በአንድነትም እንኖራለን በዚያም ቤት ከሁለታችን በቀር ከኛ ጋራ ማንም አልነበረም። በላዩ ላይ ተጭናዋለችና የዚያች ሴት ልጅ በሌሊት ሞተ። በሌሊት እኩሌታም ተነሥታ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወስዳ በብብቷ አስተኛችው። የሞተውን ልጅዋንም በአጠገቤ አስተኛችው። ልጄን አጠባ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሰኔ ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አራዊትና እንስሳት እንደሰው በድምፅ ያነጋግሯቸውና ይታዘዙላቸው ለነበረው፤ ይጠብቋቸው የነበሩትን በጐችና ፍየሎችን በነብርና በተኩላ ያስጠብቁ ለነበሩት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ተጠምቀ_መድኅን_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ተጠምቀ_መድኀን፦ በጐጃም ከሚታወቁ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥ እንዱና ዋነኛው ናቸው። እርሳቸውም እንደነ አቡነ አብራንዮስ ላሉ ቅዱሳን ገዳማቸውን እንዲመሠርቱ ያደረጉ ታላቅ አባት ናቸው" አቡነ አብራንዮስ በነፋስ ሠረገላ እየሔዱ ሲታዩ እንዲሁም ሌሎች ተኣምራትን ሲያደርጉ ይኽንንም ድንቅ ሥራቸውን ሰዎች ቢያውቁባቸው ውዳሴ ከንቱን ንቀው ወደ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ዘንድ ሔደው በዚያ በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ አቡነ ተጠምቀ መድኀን "በአንተ ምክንያት ብዙ ነፍሳት ይድናሉ ክፍልህ በዚያ ነው" በማለት ዛሬ ላይ ኤርትራ ውስጥ ወደሚገኘው ደብረ ጥሉል ልከዋቸዋል። እርሳቸውም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየመሯቸው መጥተው አስደናቂውን እንዳ ኣቦና ደብረ ጥሉል ገዳምን መሥርተዋል።
❤ አቡነ ተጠምቀ መድኅን በጻድቁ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የነበሩ ሲሆን የታላቁ የጉሐንቻ አንድነት ገዳም መሥራች ናቸው። በ17ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት አቡነ ተጠምቀ መድኅን በርካታ ገዳማትን መሥርተዋል። ከእነዚኸም ውስጥ፡- አውሽካን ኢየሱስ ገዳም፣ ካጋና ኤዎስጣቴዎስ ገዳም፣ ወገዳ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እና ሌሎችንም በርካታ ገዳማትን ጻድቁ እንዳቋቋሙ ከጎሐንቻ ቅድስት ማርያም ገዳም የተገኘ ጽሑፍ ይገልጻል። እነዚኸም ገዳማት አሁን ላይ የት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም፣ ምናልባትም በእነ ግራኝ አህመድ የጠፉ ይሆናሉ።
❤ ሌላኛዋ በአቡነ ተጠምቀ መድኅን የተመሠረተችው ሐረጽ ማርያም ገዳም ናት። ይኸችም ገዳም የምትገኘው በአዊ ዞን ሀገረ ስብከት መተከል ውስጥ በጓንጓ ወረዳ ውስጥ ነው። ሌላው የጻድቁ ገዳም ቻግኒ የሚገኘው የስጋዲ ቅዱስ ሚካኤል አቡነ ተጠምቀ መድኅን አንድነት ገዳም ነው። ይኸም የጻድቁ ገዳም በርካታ መነኰሳት የሚገኙበት ታላቅ የአንድነት ገዳም ሲሆን በተለያዩ የልማት ሥራዎች ይታወቃል። አቡነ ተጠምቀ መድኀን አባታቸው ወልደ ክርስቶስ እናታቸው ወለተ ማርያም የተባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ጻድቁ የተወለዱት ታኅሣሥ 2 ቀን ነው። በጥምቀት ሀብተ ውልድና የተቀበሉት ደግሞ ጌታችን በተጠመቀበት ዕለት ጥር 11 ቀን ስለሆነ "ተጠምቀ መድኅን" ተብለው መጠራታቸውም ከዚህ ከክርስትና ቀናቸው በመነሣት ነው።
❤ አቡነ ተጠምቀ መድኅን አስተዳደጋቸው እንደማንኛውም የገጠር ልጅ እረኛ ሆነው ያደጉት። እርሳቸው ግን ከልጅነታቸው ጀምረው መንፈሳዊ ትምህርት ለመማር ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሣ ያግዷቸው (ይጠብቋቸው) የነበሩትን በጐችና ፍየሎችን በነብርና በተኩላ አስጠብቀውና አደራ ሰጥተው ወደ አባቶች ዘንድ በመሔድ ከመነኰሳት እግር ሥር ተቀምጠው ዳዊት ደግመው ወንጌል ተምረው ማታ ይመለሳሉ። ተምረው ጨርሰው ሲመለሱም በጐቹና ፍየሎች ከነብርና ከተኩላ ከአራዊት ጋር ሲቦርቁ ያገኟቸዋል።
❤ አባታቸውም ሳያውቁባቸው ከእረኝነታቸው እንደተመለሱ ሆነው ማታ ወደቤታቸው ይመለሳሉ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ባሕታዊ አባታቸውን ወልደ ክርስቶስን አግኝቶ "ልጅህን ስጠኝ ላስተምረው" ሲላቸው አባታቸውም "በጎቹንና ፍየሎቹን ማን ይጠብቃቸዋል?" በማለት እምቢ አሉ። አባታቸውም ተጠምቀ መድኅንን ዳዊት አንግበው ስላዩዋቸው ይኸንን ሁኔታ ለማረጋገጥ ልጃቸው እያገዱ በእረኝነት ከሚውሉበት ቦታ ቢሔዱ በሚያስገርም ሁኔታ በጎቹና ፍየሎቹ ከነብርና ከተኩላ ጋር ሲጫወቱ ሲቦርቁ ተመለከቱ። ሲመሽም አውራዎቹ እንስሶቹን ሲሸኟቸው አዩ" ማታም ልጃቸውን ተጠምቀ መድኅንን "ልጄ የት ዋልህ?" ብለው ሲጠቋቸው "ከብት ሳግድ ዋልሁ" ሲሉ አባታቸውም "ልጄ ሆይ! ነገሩን ተረድቼዋለሁ፣ ከዛሬ ጀምሮ እረኛ አትሆንም፣ ከባሕታውያን ዘንድ ሔደህ ተማር" ብለው ወደ ገዳም ላኳቸው።
❤ ከዚህም በኋላ አቡነ ተጠምቀ መድኅን መንፈሳዊ ትምህርት እየተማሩ የአባቶችን መንገድ እየተከተሉ በተጋድሎ መኖር ጀመሩ። ገና ከሕፃንነታቸው ጀምረው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት እርሳቸው ግን ሲጾሙ ውለው በቀን እንድ ጊዜ ብቻ ይቀምሱ ነበር። ተጋድሏቸውንም ለማጽናት ወደ ታላቋ መርጡል ማርያም በመሔድ በ23 ዓመታቸው አባ ዝክረ ማርያም በሚባለ አባት እጅ መነኰሱ። ከመነኰሱም በኋላ ከሚለብሱት የፍየል ቆዳ ሥር ሰውነታቸውን በሰንሰለት አሥረው ከመኖራቸውም በላይ ቅዳሜና እሑድ ከሚቀምሱት ዳቤ በቀር እህል አይቀምሱም ነበር። ስግደታቸውም በቀን አንድ ሺህ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል።
❤ ጻድቁ ከተሰጣቸው ጸጋ የተነሣ አራዊትና እንስሳት እንደሰው በድምፅ ያነጋግሯቸውና ይታዘዙላቸው ነበር። እንደ ረድእ ሆኖ የሚታዘዛቸው ጸዋሬ መስቀል የሚባል አንድ አህያ ነበራቸው፤ እርሱም መልእክት በማድረስና በመቀበል አባታችንን ያገለግላቸው ነበር፣ አምጣ ያሉትን ያመጣል፣ ውሰድ ያሉትን ይወስዳል። እርሳቸውም ከጐጃም እስከ ሱዳን ጠረፍ ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካታ ከሃዲያንን አስተምረው በማጥመቅ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጌታችን ቃልኪዳን ተቀብለው በጻድቁ ዮሐንስ ዘመን በ1670 ዓም በክብር ዐርፈዋል።
❤ አቡነ ተጠምቀ መድኀን ያረፉት ሰኔ 23 ሲሆን በዓለ ዕረፍታቸው ዐፅማቸው በክብር ተቀምጦ ባለበት በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም ውስጥ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ያረፉትም ለአገልግሎት ወደ ጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም በሔዱበት ወቅት ስለነበር ዛሬም የከበረ ዐፅማቸውም በዚያው ይገኛል። ከአቡነ ተጠምቀ መድኅን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ።
.....ወር በገባ በ22 ......
የከበረና የገነነ የመነኮሳት ሁሉ አባት ፤ ኮከበ ገዳም ማኅቶተ ገድል ፨ በገዳም ለሚኖሩም ሁሉ ተገድሎው እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው የ አባ_አንጦንስ ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደር ።
" ነገር ግን አስቀድማችሁ
የእግዚአብሔርን_መንግሥት_ጽድቁንም_ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤
ለቀኑ_ክፋቱ_ይበቃዋል። ማቴ 6 ፥ 33 - 34/
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤️
❤️ #ሰኔ_፳፪ 22 ቀን።
❤️ እንኳን #ለመነኰሳት_መጀመሪያቸው_ለሆነ ለከበረ #አባ_እንጦንስ_ረድእ ለነበረው ለየዋህ #ለቅዱስ_ጳውሎስ ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከከበሩ_ቅዱሳን_ከቆዝሞስና #ከድምያኖስ_ከእናታቸውና_ከወንድሞቻቸው ከበዐላቸው መታሰቢያና ቤተ ክርስቲያናቸውም ከከበረችበት ተአምራታቸውም ከተገለጠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የአባ_እንጦስ_ረድእ_የዋህ_ቅዱስ_ጳውሎስ፦ ይህም ጳውሎስ በረኸኛና እጅግ የዋህ ነበር ደም ግቧቷ ውብ ሥራዋ ግን ክፉ የሆነ ሚስት አገባ ከእርሱም ልጆችን ወለደች። በአንዲትም ቀን ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ከሎሌው ጋራ ስታመነዝር አገኛት በአያቸውም ጊዜ ሣቀ ያንን ሎሌውንም እንዲህ አለው "ከልጆቿ ከቤቷና ከንብረቷ ጋራ ውሰዳት እኔ ምንም አላዝንም እግዚአብሔርም ወደ ፈቀደልኝ እሔዳለሁ" አለው።
❤️ ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አባ እንጦንስ ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ የአባ እንጦንስንም ሥራ ተከተለ። በደዌያትና በሰይጣናት ላይ ጸጋና ኃይል እስከተሰጠው ድረስ በጾምና በጸሎት ተጋደለ።
❤️ በአንዲት ዕለትም ጋኔን የያዘውን ሰው ያድነው ዘንድ ወደ አባ እንጦንስ አመጡ። አባ እንጦንስም ይፈውሰው ዘንድ ረድኡ ጳውሊን አዘዘው ጳውሊም ጋኔናሙን ሰው ወስዶ "አባቴ እንጦንስ ውጣ ይልሃል" አለው ሰይጣኑ ግን መውጣትን እምቢ አለ። እርሱንም እንጦንስንም ተሳደበ። ጳውሊም "ካልወጣህስ ለእንጦስ እነግረዋለሁ እንደሚቀጣህም ታያለህ" አለ። ይህንንም ብሎ በቀትር ጊዜ ወጥቶ ፀሐይ በአጋለው ደንጊያ ላይ ቁሞ "ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው እስኪድን ድረስ ከዚህ አለት እንዳልወርድ እንዳልበላና እንዳልጠጣ ሕያው እግዚአብሔር" አለ። በዚያንም ጊዜ ጋኔኑ ጮኸ በታላቅ ዘንዶ አምሳልም ከሰውዬው ላይ ወጥቶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ገባ።
❤️ ይህም የዋህ ጳውሊ የሰዎችን ሥራ ሁሉ እያየ ስለ ኃጥአን ያለቅስ ነበር ስለ እነርሱም ይማልድ ነበር። በመልካም እርጅናም ሰኔ 22 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ የዋህ በቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 22 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ዕብል_ለጳውሎስ_ሊሉይ። እምነ ብእሲት ዘማ ሠናይተ ላህይ። ቀዊሞ ወዓለ እንበለ ናህይ። በመልዕልተ ኰኵሕ እንተ አርሰኖ ፀሐይ። እስከ እምጋኔን ሐይወ ብእሲ ድውይ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_22።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወኢትቅናእ ላዕለ ዘይዴሎ በሕይወቱ። ወላዕለ ሰብእ ዘይገብር ዐመፃ። ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቊጥዓ"። መዝ 36፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥6-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥39-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
