fa
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

نمایش بیشتر
603
مشترکین
-324 ساعت
-87 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
ብዙዎቻችን ከትንሣኤ በኋላ ሩጫውን ጨርሶ ወደ መልበሻ ክፍሉ እንደሚገባ አትሌት ማልያችንን በፍጥነት አወላልቀን ወደ ቀደመ አኗኗራችን እንመለሳለን:: ከስምንት ሳምንታት የትራክ ላይ ሩጫ ማልያ ወደመቀ
ብዙዎቻችን ከትንሣኤ በኋላ ሩጫውን ጨርሶ ወደ መልበሻ ክፍሉ እንደሚገባ አትሌት ማልያችንን በፍጥነት አወላልቀን ወደ ቀደመ አኗኗራችን እንመለሳለን:: ከስምንት ሳምንታት የትራክ ላይ ሩጫ ማልያ ወደመቀየር ለመሄድ እርምጃችን ከአትሌቱም ይፈጥናል:: 8ኡ ሳምንታት ጥቂት ቀናት እንኳ ሊያስተምሩን አንፈቅድም:: የቤተክርስቲያን ቅጥሮች ባዶ ይሆናሉ:: የምሕረት አውዶች የምዕመናን ድርቅ ይገጥማቸዋል:: ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ ማክሰኞ ምሽት የት ነን? አርብ ያለቀስንለትን ክርስቶስ እንደ ወረት እንረሳው ይሆን? ወይንስ ዳግም ወደ ምሕረቱ አደባባይ እናቀና ይሆን?

#ቀዳሚት ሥዑር #ገብረ ሰላም(ለምለም ቅዳሜ)    +እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ሁሉ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለ አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ ምድር አርፎባታል ማቴ 27-61 "ሥዑር" የተባለችበት ምክንያት በዓመት አንድ ጊዜ ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው። የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና ሌሎችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሀነ ትንሳኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሳኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረውታል የቻልን ይህን መነሻ በማድረግ ከዐርብ ጀምረን በማክፈል(በመጾም) እህል ውኃ ሳንቀመስ ለሁለት ቀናት እናድራለን (እናከፍላለን)።     #ገብረ ሰላም(ለምለም ቅዳሜ) ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ "ገብረ ሰላመ መስቀሉ (በመስቀሉ ሰላምን አደረገ መሠረተ)" እያሉ በቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጤማ ያድላሉ #ቄጤማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምድር በተጠለቀለቀች ጊዜ ኖኅ ወደ መርከብ ይዟቸው ከገቡት እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን ልኮ ነበር እርሷም ቄጤማ በአፏ ይዛ በመመለስ የምሥራች ምልክት የውኃውን መድረቅ እንደነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ ኦ.ዘፍ 9-1-21 "በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ" ስንል ቅድስት ቤተክርስቲያን ለልጆቿ ቄጤማ ታድለናለች የምሥራች ተምሳሌት የሆነው ቄጤማም ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን።

ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞ
+1
ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ። “ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤ ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለዐበይት በዓል ለአንዱ ለሰሞነ ሕማማት አምስተኛ ቀን #ለስቅለት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                              ❤ #ዕለተ_ዓርብ። ❤ የስቅለት ቀን ስቅለት ማለት መስቀል፣ መሰቀል፣ አሰቃቀል ማለት ነው፡፡ መስቀል በቁሙ መስቀያ፣ መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማር 8፥34 "ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀል ሞቱ ወይትልወኒ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" ይላል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ. 1፤17 ላይ "ወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር መስቀሎ ለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም" ይላል፡፡ ❤ ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከሰድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ ፀሐይ ጨለመ፣ እነሆም የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳን ብዙዎች ተነሱ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ፡፡ ማቴ. 27፤51 ❤ ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቀለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱ የሚመለከቱ ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል፡፡ የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ፡፡ ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምፅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው፡፡ ሉቃ. 23፤31 በዕለተ ዓርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን።                              ✝ ✝ ✝  ❤ #የጠዋት_የ12_ሰዓት_ምስባክ፦ "እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ። ወሐሰት ርዕሰ ዐመፃ። እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ"። መዝ26፥12 ወይም መዝ34፥11። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 27፥1-14፣ ማር 15፥1-5፣ ሉቃ 22፥66-71 እና ዮሐ18፥28-40 ናቸው።                             ✝ ✝ ✝  ❤ #የሦስት_ሰዓት_ምስባክ፦ "ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን። ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን"። መዝ 21፥16። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 27፥15-16፣ ማር15፥6-15፣ ሉቃ 23፥13-25 እና ዮሐ 19፥1-12 ናቸው።                             ✝ ✝ ✝  ❤ #የስድስት_ሰዓት_ምስባክ፦ "ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ። ወኈለቁ ኲሎ አዕፅምትየ። ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ"። መዝ 21፥16። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 27፥27-45፣ ማር 15፥16-33፣ ሉቃ 23፥27-44 እና ዮሐ 19፥13-27 ናቸው።                              ✝ ✝ ✝  ❤ #የዘጠኝ_ሰዓት_ምስባክ፦ "ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልየ። ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ። ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልየ"። መዝ 68፥21። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 27፥46-50፣ ማር 15፥34-37፣ሉቃ 23፥45-46 እና ዮሐ 19-28-30 ናቸው። ❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበ ሰላም። ❤ መልካም የስቅለት በዓልና የስግደት ቀን ለሁላችንም ይሁንልን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

​​​​​​አክፍሎት በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡ ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡ ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

#ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝ
+2
#ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#​​ሰሙነ_ሕማማት💔 ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ #ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። #ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። የትምህርት ቀን ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ረቡዕ ምክረ አይሁድ ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። የእንባ ቀን ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። #ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። #ዓርብ የስቅለት ዓርብ ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። መልካሙ ዓርብ ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። #ቅዳሜ ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾምና የስግደት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።🙏🙏🙏 √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

🌿🌿🌿🌿ሆሳዕና በአርያም🌿🌿🌿🌿 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዛሬው ዕለት የሆሳዕና በዓል በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ለስቅለቱ እና
+2
🌿🌿🌿🌿ሆሳዕና በአርያም🌿🌿🌿🌿 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዛሬው ዕለት የሆሳዕና በዓል በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ለስቅለቱ እና ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን አሜን!!

ህፃን ዳግም ነጋሽ ✝️🌿ሆሳዕና በአርያም🌿✝️ ያን ጊዜ ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና "በፊታችሁ ወደ አለ ሀገር ሂዱ አህያዋን ከውርንጭላዋ ጋር ፈትታችሁ አምጡልኝ" አላቸው።(ሉቃ ፲፰፥28) ኪነ- ጥበብ ክፍል

✝️🌿ሆሳዕና በአርያም🌿✝️ "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው!" 'መዝ 117:25 #በዓለ_ሆሣዕና_ምሥጢሩ #ሆሳዕና መድኃኒት ማለት ነው። ሆሣዕና ማለት “አሁን አድን” ማለት ነው።በዳዊት መዝሙር ቃሉ ተጠቅሶ እንደሚገኘው"ኦ እግዞኦ አድህንሶ”... "አቤቱ አሁን አድን" (መዝ 117፥25) በአርያም:የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰማይ ያመለክታል። የመጀመሪያው ከሮማውያን ቅኝ አገዛዝ አድነን የሚል የሥጋ ጩኸት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ አድን ማለታቸው ነበር፡፡ ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ በመቅደሱ ዙሪያ ያሉት ለዋጮችንና ሻጮችን ያስወጣበት ቤተ መቅደሱ የጸሎት ቤት መሆኑን ያወጀበትና ክብሩን የገለጸበት በዓል ነው፡፡ከ፪ኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ሆሳዕና የጸበርተ ዕሁድ ከሚሉት ይልቅ 'የይፍቱኝ ዕለት" እያሉ የሚጠሩት ብዙዎች ናቸው:: በዚህ ዕለት የእስራኤል ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ሆሣዕና በማለት እየጮኹ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አጀቡት ትንቢቱም ይፈፀም ዘንድ ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል” ተብሎ እንደተፃፈ (ዘፍ49÷ዘካ 11 9÷9,ኢሳ 40:20) ጌታችን በሕዝበ እስራኤል የተለመደውን ሥርዓተ ነቢያትን በመጠቀም (ቀደምት ነቢያት ዘመነ መዓት መምጣቱን ለማሰታወስ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው በከተማ ሲዘዋወሩ ዘመነ ሣህል (ዘመነ ምሕረት) መምጣቱን ለማሳየት ደግሞ በአህያ ላይ ተቀምጠው ይታዩ ነበር። ይህ ምሥጢርም በቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በማቴዎስ ፳፩፥፩-፲ 6፤ በማርቆስ ፲፩፥፩-፲፤ በሉቃስ ፲ ፱፥፳፰-፵ እና በዮሐንስ ፲፪፥፲፪-፲፭ በተጻፈው ኃይለ ቃል መሠረት መመልከት ይገባል፡፡ ያን ጊዜ ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና "በፊታችሁ ወደ አለ ሀገር ሂዱ አህያዋን ከውርንጭላዋ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ" አላቸው።(ሉቃ ፲፰፥28) ሰው ሁሉ ከማዕሠረ ኃጢአት ለመፈታተ እንደ ደረሰ ለማጠየቅ ።የሐዋርያት አገልግሎት የታሰሩትን በወንጌል ቃል መፍታት ነው።ሌቦች አጋንንት ያሠሯቸው ብዙ የኃጢአት እስረኞች አሉ ጌታ የታሰሩትን እንደ እሱ እንዲፈቱ ደቀ መዛሙርቱን አዟቸዋል። አህያ የተናቀች ናት። ራሳቸውን ዝቅ ባደረጉ መንፈሳቸው ወደ ተሰበረ አምላክ እንደሚመለከት ያስተምራል (ኢሳ53፥23) ማቴ 11÷29) አንተም የማትቆረቁር ሕገ ወንጌል ሰጠህን ሲሉ ልብሳቸውን ጎዝጉዘው ተቀብለውታል። "እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐት በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንስቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ” (መዝ፷፥፪) ባለ አእምሮ ነን የሚሉት ልብ ሲታወር አንደበታቸው በሰይጣን ምክር ሲዘጋ የሕፃናት አንደበት ምስጋናን ያዘንብ ነበር፡፡ ቤተ ፋጌ ማለት ደግሞ "የበለስ ቤት” ማለት ነው፡፡በእኛ አባቶች ደግሞ "የተመሳቀለ ጎዳና" ተብሎ ተተርጉሟል። ጌታችን ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አዕሩግና ሕፃናት ልብሳቸውን እንዲሁም የዘንባባ ዝንጣፊ በማንጠፍ "ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" እያሉ ክብሩንና መድኃኒትነቱን ገልጠዋል። (ሉቃ19÷38, መዝ ፰፥፪) ከሆሳዕና በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

🕊 ✞ ሚያዝያ ፲፰ [18] ✞ [  ✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ] 🕊  ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ   🕊 ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬]  ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ ነው። በዚያ የመከራ ዘመን [፫ኛው መቶ ክ/ዘ] ግብፅና ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡ ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው [ከአክስቱ] ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡ በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡ በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡ ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ ቀብሮታል፡፡ አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡ 🕊 [  † ሚያዝያ ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት ፪. አባ ዼጥሮስ ሰማዕት ፫. ሰማዕታተ ጠርሴስ [    †  ወርሐዊ በዓላት    ] ፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ ፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን] ፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ ፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ " በድካም : አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " [፪ቆሮ.፲፩፥፳፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

✨ኒቆዲሞስ ✨ኒቆዲሞስ ማለት :- በቤተክርስቲያን ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል። ✨ትርጓሜው የአይሁድ መምህር ወይም ደሞ የጌታችን ደቀ መዝሙር የሌሊቱ ተማሪ ማለት ነው። ✨ኒቆዲሞስ_
✨ኒቆዲሞስ ✨ኒቆዲሞስ ማለት :- በቤተክርስቲያን ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል። ✨ትርጓሜው የአይሁድ መምህር ወይም ደሞ የጌታችን ደቀ መዝሙር የሌሊቱ ተማሪ ማለት ነው። ✨ኒቆዲሞስ_ፈሪሳዊ ነው።ዮሐ 3:1 ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው።ዮሐ 3: 1 ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው።ዮሐ 3:10 ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው።የሐ 7:51 ✨ኒቆዲሞስ በኢየሩስ አሌም በሀብት በእውቀት ዝና በስልጣን የታወቀ ነው።ኒቆዲሞስ ስለ ሶስት ነገር ሌሊት ሌሊት እየሄደ ከጌታ እግር ስር ይማር ነበር። 1 አይሁድ ፈርቶ:-በዛን ሰአት በአይሁድ ህግ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሀብት ንብረቱ ስለ ሚቀማ ከነሱ ለመሸሽ ሌሊትን መረጠ። 2,ውዳሴ ከንቱን ሽቶ:-በወቅቱ የነበረ እውቅ ሊቅ ነበርና እንዴት ከመምህር ስር ይማራል እንዳይሉት። 3 ልቡናው እንዲሰበሰብ:-ከቀን ይልቅ ሌሊት የአይምሮ እረፍ ስላላት እሱን ሽቶ ነው። ✨ኒቆዲሞስ ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ ስለ ምስጢረ ጥምቀትና ዳግመኛ ልጅነት የፅድቅ ስራ በሰፊው ተምሯል።ዮሐ ም 3፡ 1-12 √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሚያዝያ ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ሚካኤል_እግዚአብሔር_ወደ_ነቢዩ_ቅዱ_ኤርምያስ ለላከበት (ንጉሥ ሴዴቅያስ ጠባብና ረግረግ ከሆነ ጒድጓድ በጣለው ጊዜ #ኢትዮጵያዊው_ቅዱስ_አቤሜሌክ ከጒድጓድ ውስጥ ላወጣው) ወራዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ለአባ_እለእስክድሮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከአገረ ጠመው ኤጲስቆጶስ ከከበረ #ከአባ_እንጦንስና_ከአውሳንዮስ ከመታሰቢያቸው፣ #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ ከተገለጠላቸው #ከቅዱሳን_ጋይዮስና_ኤስድረስ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ዕለት #የመላክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤልን_እግዚአብሔር_ወደ_ነቢዩ_ቅዱስ_ኤርምያስ ላከው ጠባብና ረግረግ ከሆነ እሥር ቤት ሴዴቅያስ ንጉሥ በአሠረው ጊዜ የንጉሡ ባለሟልና የጭፍራ አለቃ የሆነው አቤሜሌክ አወጣው። ያንጊዜም የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ መራራ ምርኮንም እንዳይቀምስ ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ መረቀው እንዲሁም ሆነ። ስሳ ስድስት ዓመትም ተኝቶ ኖረ ከእርሱ ጋራ ወይንና በለስ ነበር አልተለወጠም የእስራኤል ልጆች ምርኮ እስቲመለሱ በለሱንም ከደብዳቤ ጋራ ወደ ኤርምያስ ባቢሎን አገር ላከው። ❤ ስለዚህ የዚህን የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን። የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነቱ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ አባ እለእስክድሮስ፦ ይህም ቅዱስም አስቀድሞ በቀጰዶቅያ አገር ኤጲስቆጶስነት ተሹሞ ነበር። እርሱም የከበሩ ቦታዎችን ተሳልሞ በረከት ተቀብሎ ወደ አገሩ ሊመለስ አስቦ ኢየሩሳሌም መጣ። ❤ በኢየሩሳሌምም ስሙ በርኪሶስ የሚባል መቶ ዐሥር ዓመት የሆነው ጻድቅ ሰው ነበር ሹመቱንም ሊተው ይወድ ነበር ወገኖቹ ግን አልለቀቁትም። ቅዱስ እለእስክድሮስም ሥራውን ፈጽሞ ወደ አገሩ ቀጰዶቅያ ሊመለስ በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል እንሆ ከሰማይ አሰማ። "ወደ እገሌ በር ውጡ አስቀድሞ የሚገባውን ይዛችሁ በላያችሁ ኤጲስቆጶስነት ሹመት"። ያን ጊዜም ሲወጡ አባ እለእስክድሮስን አገኙትና ያዙት። እርሱም "እኔ የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ነኝ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ በእነርሱ ላይ የሾመኝን መንጋዎቼን ልተው አይቻለኝም" አላቸው። እነርሱም ከሰማይ ስለሰሙት ስለዚያ ቃል ስለርሱም እንደአመለከታቸው ነገሩት። ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆነ በተረዳ ጊዜ ለበዓሉም የተሰበሰቡ አባቶች መከሩት ቃላቸውንም ተቀበለ ወደ አገሩ ቀጰዶቅያም እንዲህ ብሎ መልክት ጽፎ ላካት "ይቅርታ አድርጉልኝ በእኔ ላይ አትዘኑ በእናንተ ላይም ኤጲስቆጶስ በእኔ ፈንታ ሹሙ እናንተም የተፈታችሁ ናችሁ" ያቺን መልእክትም ከእርሱ ጋራ አብረው ከመጡ ከቀጰዶቅያ ሰዎች ጋራ ላከ። ❤ ከዚህም በኋላ እየተራዳው አምስት ዓመት ያህል ከአባ በርኪሶስ ጋራ ኖረ። ከዚህም በኋላ ሽማግሌው አባ በርኪሶስ ዐረፈ። አባ እለእስክድሮስም መንጋውን ተረክቦ እንደ ሐዋርያትን በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው። ❤ ከሀዲ መክስምያኖስም በነገሠ ጊዜ ይህን አባት ይዞ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃየው። ከዚያም በላዩ የሚያደርግበትን እስከሚያስብ ድረስ አሠረው። ጌታችንም ይህን ከሀዲ ፈጥኖ አጠፋው ወገኖቹም ይህን አባት እለእስክድሮስን ከእሥር ቤት አወጡት። ❤ ገርድያኖስም በነገሠ ጊዜ ጸጥታና ሰላም ሆነ ከክርስቲያን ወገኖች ላይም ጥቂት ወራት መከራው ጸጥ አለ። ገርድያኖስም በሞተ ጊዜ በርሱ ፈንታ አማኒ የሆነ ፊልጶስ ነገሠ። እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ስለሚያምን በክብር ባለቤት በጌታ ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ምዕመናን ፈታቸው እጅግም አከበራቸው ይህም አባት በጸጥታ ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዳኬዎስ ተነሣ ፊልጶስንም ገድሎ መንግሥቱን ወሰደ ክርስቲያኖችንም እጅግ አሠቃያቸው ይህንንም አባት ያዘው ብዙዎችንም ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጽኑ ሥቃይም አሠቃያቸው። ይልቁንም ይህን አባት አብዝቶ አሠቃየው ጽኑ ግርፋትንም ገርፎ ስለት በአላቸው በትሮች የጐኑ አጥንቶች እስመታው። ከዚህም በኋላ እስከ እሥር ቤት ጐትተው በዚያ እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። እግዚአብሔር ለመረጣቸው ያዘጋጀውን መንግሥተ ሰማይ እስከ ወረሰ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሰጠ ድረስ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ በዚያ ወድቆ ኖረ። ከአባ እለእስክድሮስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ12 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለከ_ዘተረሰይከ_በክብር። መልአከ ኪዳኑ ወምክሩ ለእግዚአብሔር። #ሚካኤል_ረዳኢ ለእለ ውስተ የብስ ወባሕር። ለረድኤትከ ዘየዓፅቦ ነገር። አልቦ በሰማይ ወአልቦ በምድር። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሚያዝያ_12።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታምእሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥30-36።                              ✝ ✝ ✝ ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወአድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውፅአ እሞቅሕ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ"። መዝ 141፥7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 4፥9-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥13-17 እና የሐዋ ሥራ 24፥14-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-20 የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ  ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨