ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر608
مشترکین
-124 ساعت
-37 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
💥💥💥💥💥በዓለ ደብረ ቁስቋም
እንኳን አደረሰን💥💥💥💥💥
🖊️ ዲያቆን ዘካርያስ ነገደ
ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡
ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)
የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡
ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡
እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም)
ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡
ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ኅዳር ፭/5/በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው:: ይህም ቅዱስ በጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ብቻውን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት:: በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ። ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗም ብዛት የተነሣ ተኛች። ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚያ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበትም ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት እግዚአብሔርንም አመሰገነች ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት በታላቅ ክብርም በአማረ ቦታ አኖረቻት። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
ኅዳር ፬ /4/በዚችም ቀን የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ በግብጽና በሶርያ እስላሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ቶማስ ከመምህራኖቻቸው ውስጥ አንድ እስላም በተከራከረው ጊዜ ቅዱስ ቶማስ በረታበት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ አምላክ እንደሆነ በማስረዳት አይሎ ረታው። ያም እስላም በአፈረ ጊዜ ወደ መኰንናቸው ሒዶ ይህ ክርስቲያናዊ ቶማስ ሃይማኖታችንን ረገመ ብሎ ወነጀለው። መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ በውኑ ሃይማኖታችንን ትረግማለህን አለው፤ ቅዱሱም መርገምስ ከአፌ አልወጣም ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ከእርሱም ሕግ በኋላ ሌላ ሕግ እንደማይመጣ አጽንቼ አስረዳሁት እንጂ ብሎ መለሰለት። መኰንኑም የእኛስ ሕግ ከእግዚአብሔር ነውን ወይስ አይደለም አለው፤ ቅዱሱም ከእግዚአብሔር አይደለም አለው። በዚያንም ጊዜ መኰንኑ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና ቅድስት ራሱን ቆረጡት። በመንግሥተ ሰማያትም የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
ኅዳር ፫ /3/በዚች ቀን ከቆሮንቶስ አገር ቅዱስ አባት ኪርያቆስ አረፈ። የዚህም አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና የከበሩ ናቸው የቤተክርስቲያንን ትምህርትና የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩት ከዚህም በኋላ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ጴጥሮስ አቀረቡት እርሱም በላዩ ጸልዮ አናጒንስጢስነት ሾመው። ከዚህም በኋላ ዘወትር መጻሕፍትን የሚያነብ የቃላቸውንም ትርጓሜ የሚመረምር የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓቷንና ሕጓን የሚያጸና ሆነ በትምህርቱና በእውቀቱም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ መጻሕፍትንም በሚያነብለት ጊዜ ኤጲስቆጶሱ በእርሱ ደስ ይለው ነበርና። ዕድሜውም ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነ ጊዜ ሚስትን ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ጠየቁት እርሱ ግን ይህን አልወደደም ግን ከገዳማት ወዳንዱ ይሔድ ዘንድ እንዲአሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው የከበረች የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ከአባ ቄርሎስ ጋር ተገናኝቶ ስለ ምንኲስና ኀሳቡን ሁሉ ነገረው። እርሱም በጎ ሥራን ወደሃል አለው ታላቅ አባትም እንደሚሆንና በእርሱም የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገረለት ። ከዚህም በኋላ የመነኰሳት አባት ወደ ሆነ በፍልስጥዔም ወደ ሚኖር ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላከው እርሱም በደስታ ተቀብሎ የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት በታላቅ ድካም በቀንና በሌሊት በገድል ተጸምዶ በትዕግሥት በትሕትና በቅንነት ኖረ። እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት ወደርሱ የሚመጡትን በሽተኞች ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ:: ከዚህም በኋላ በመልካም ሽምግልና እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
ኅዳር ፪/2/በዚች ቀን ከአባ ጢሞቴዎስ በኋላ የተሾመ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ጴጥሮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈለት እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን። ይህ አባ ጴጥሮስም እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት ። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት። ከዚህም በኋላ ሌላ መልእክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳት መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት ። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ ። ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀድያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሹመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት ። ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ኅዳር ፪ (2) ቀን።
🌹 እንኳን #ከአባ_ጢሞቴዎስ በኋላ ለተሾመ አረማውያን ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራ ላደረሱበት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ሃያ_ሰባተኛው_ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ_በዓል መታሰቢያና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ ለሆነ ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ሱንትዩ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ ነቢዪት ከሆነች #ከሴቴንዋ_ከቅድስት_አንስጣስያና #ከአባ_ሊባኖስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #የእስክንድር_ሊቀ_ጳጳስ_ቅዱስ_አባት #አባ_ጴጥሮስ ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልክትን ጻፈለት "እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን"። ዳግመኛም በዚች መልክት ውስጥ እንዲህ ብሎ ገለጠ "የተዋሕዶ ጥቅም እንዳይሻር ከተዋሕዶ በኋላ የአካላዊ ቃልን መለኮትን ከትስብእቱ ሊለዩት አይገባም"።
🌹 ይህ አባ ጴጥሮስ እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት።
🌹 ከዚህም በኋላ ሌላ መልክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳን መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ።
🌹 ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀዲያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሢመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት።
🌹 ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌹 በዚችም ቀን ዳግመኛ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ_የሆነ_የእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት #አባ_ሱንትዩ_ዐረፈ፦ ይህም አባት መንጋዎቹን እያስተማረ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ አምስት ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 2 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹 "#ሰላም_እብል_ለብፁዕ_ሱንትዩ። #ወለጴጥሮስ ዓዲ ሱታፌ ዕበዩ። ኪያሆሙ ሕዝብ በከመ ሠምሩ ወኀርዩ። ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ ቤተ ክርስቲያኑ ይርዐዩ። እንተ አጥረያ በደሙ ወማዩ"። #ሊቁ_አርከ ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር2።
✝️ ✝️ ✝️
🌹 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ። ወኢይፈርህ እምነገር እኩይ። ጥቡዕ ልቡ ለተወክሎ በእግዚአብሔር"። መዝ111፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 4፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 20፥18-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹 "በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #የተባረከ_የኅዳር_ወር_ቀኑ_ዐሥር_ሰዓት ሲሆን ከዚህም ይጎድላል።
🌹 #ኅዳር ፩ (1) ቀን።
🌹 እንኳን #አፍራቅያ_አገር_ለሆኑ_ለቅዱሳን_ሰማዕታት #ለመክሲሞስ_ለማንፍዮስ_ለፊቅጦርና_ለፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኪዎስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያው በዓልና #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ነአኵቶ ለመታሰቢያው በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌹 #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ከመክሲሞስ_ከማንፍዮስ፣ #ከፊቅጦርና_ከፊልጶስ፦ እነዚህ ቅዱስ በገሀዲ ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት ያረፉ ናቸው። በዚህም ከሀዲ ንጉሥ ዘመን ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው የነቁ ከእርሱ በሸሹ ጊዜ ነው። እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲአሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ "እኛ በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጦ የምናምን ክርስቲያኖች ነን ለእርሱም እንሰግዳለን እናመልከዋለንም" ብለው ጮኹ።
🌹 ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፋአቸው አዘዘ አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም ታላቅ ግርፋትን ገረፏቸው በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች ደበደቧቸው።
🌹 ከዚህም በኋላ በበርኖስ እላቂ ጨርቅ ከመጸጸና ከጨው ነክረው ቊስላቸውን አሹአቸው የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰሙ ጊዜ ሥቃዩንም ፈርተው ከበጎ ምክራቸው ባልተመለሱ ጊዜ ቁጣን በማብዛት ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ከዚያ የነበሩ ብዙ ሕዝብም ትዕግሥታቸውን በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አጠቃቅነውም እንዲቈርጧቸው አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ኅዳር 1 ቀን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 1 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹"#ሰላም_ለመክሲሞስ_ወለአኃዊሁ_በጽድቅ። እለ አበዩ ሰጊደ ለስብኮ ወርቅ። ሐራ ዳኬዎስ ዓላዊ ኰናኔ ሰብዓቱ ደቂቅ። በዘአርሐስዎ በብሂእ ወበፄው ድቁቅ። ቊስላቲሆሙ መዝመዙ በሠቅ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ)
#የኅዳር_1።
ጥቅምት ፴ /30/በዚችም ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እራስ የታየበት ነው። ሔሮድስ ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው። እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት። አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ። የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል። ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት። ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት። በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች። ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጸድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር /ዝክረ ቅዱሳን/
+5
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🌹ስንክሳር ጥቅምት 29 🌹
🙏✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞🙏
" እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ "
🙏" አባ ሳሙኤል ዘወገግ "🙏
ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን (ምዕራፈ ቅዱሳን) እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::
በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም:
✍*ሳሙኤል ዘዋሊ
✍*ሳሙኤል ዘወገግ (የዛሬው)
✍*ሳሙኤል ዘጣሬጣ
✍*ሳሙኤል ዘቆየጻ
✍*ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና
✍*ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው::
ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም::
የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል::
የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ12ቱ ኅሩያን (ምርጦች) አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር::
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን 12ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ2ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::
ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል::
ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ155 ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ::
በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው (የአባ አንበስ ዘሐዘሎ) ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው::
በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል::
ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር::
በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ 10: ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት 27 ነው::
🌿" አባ ጸቃውዐ ድንግል "🌿
እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው::
የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው::
በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ::
40 ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል::
አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት::
ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::
🌿"ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት "🌿
ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ::
አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር::
ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው::
የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል::
አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🌹✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞🌹
🌹🌹🌹
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን።
🌹 እንኳን በከሀዲው በመክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም የተወለደበት #ከልደቱ_ከበዓለ ወልድ ወራዊ በዓል መታሰቢያ፣ #ከድሜጥሮስ_ወዳጅ_ከሰማዕቱ_ስቅጣር ዐረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ድሜጥሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከተሰሎቄ አገር ነው የከበረች የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ በቀናች ሃይማኖት ጸና ሕዝብንም የሚያስተምር ሆነ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በመስበክ ብዙዎቹን ከስህተት መለሳቸው። ስዚህም በከሀዲው ንጉሥ ዘንድ መነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ እንዲያወጡት አዘዘ በንጉሡም ዘንድ አንድ ሥጋው የደነደነ የጸና አጥንቱ የሠፋ ሰው ነበር ለሰዎችም ሁሉ እርሱ ሁሉንም የሚያሸንፍ እርሱን የሚያሸንፈው የሌለ ይመስላቸው ነበር ንጉሡም ይወደዋል ይመካበታል እንዲህም ይል ነበር "ይህን አካሉ ግዙፋ የሆነ ሰው የሚያሸንፍ ብዙ ገንዘብ እሰጠዋለሁ"።
🌹 በዚያን ጊዜ ስሙ በስጥዮስ የሚባል አንድ ክርስቲያናዊ ሰው ተነሥቶ ወደ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሆደ እንዲጸልይለትና በስጋውም ሁሉ አሸናፊ በሆነ በመስቀል ምልክት እንዲያማትብበት ለመነው እርሱም በላዩ ጸለየለት በሥጋው ሁሉ ላይ በመስቀል አማተበበት ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ገብቶ ከዚያ ሥጋው ግዙፋ ከሆነው ጋር ያታግለው ዘንድ ለመነው ንጉሡም ፈቀደለት በታገሉም ጊዜ ሥጋው የደነደነውን ያ ክርስቲያናዊ ሰው አሸንፊ ጣለው ንጉሡም አዘነ አደነቀም ሥጋው የደነደነውም በመሸነፉ አፈረ ተመክቶበት ነበርና። ንጉሡም ስለዚህ ነገር ወታደሮቹን ጠየቀ እነርሱም ቅዱስ ድሜጥሮስ በላዩ እንደጸለየለትና በሥጋው ላይ በመስቀል ምልክት እንዳማተበበት ነገሩት።
🌹 ንጉሡም ይህ በሰማ ጊዜ በቅዱስ ድሜጥሮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ለአማልክትም እጣን እስከማያሳርግ ድረስ እንዲገርፉት አዘዘ ንጉሡም እዳዘዘ እንዲሁ አደረጉበት የንጉሡንም ትዕዛዝ ባልሰማ ጊዜ እስከሚሞት በጦሮቹ እንዲወጉት ሁለተኛ አዘዘ።
🌹 ለቅዱስ ድሜጥሮስም ይህ ፍርድ ነገሩት ሃይማኖቱን ትቶ ለአማልክት የሚሰግድ መስሏቸው ነበርና ቅዱስ ድሜጥሮስም "እኔ ከእውነተኛ አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት እሰግድ ዘንድ እጣን ማሳረግም አድቅድም የወደዳችሁትን አድርጉ" አላቸው። በዚያን ጊዜ ንጽሕት ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ እስከሚሰጥ በጦር ወጉት ሥጋውንም በጣሉት ጊዜ ምዕመናን ወደእርሳቸው ወሰዱት የስደቱም ወራት እስከሚያልፍ በሳጥን አድርገው በቤታቸው ውስጥ ሰውረው አኖሩት።
🌹 የስደቱም ወራት ከአለፈ በኋላ እግዚአብሔር ገለጠውና ከዛ አወጡት ያማረች ቤተ ክርስቲያንንም በተሰሎንቄ አገር ሰሩለት ሥጋውም በውጧ አኖሩ ድንቅ የሆነ ታላቅ ተአምርን እያደረገ እስከ ዛሬ አለ ሽታው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከእርሱ ይፈሳልና በእምነት የሚቀቡትን በሽተኞች ሁሉንም ያድናችዋል። ይልቁንም በዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ጥቅምት 29 ከሌሎቹ ዕለታት ተለይቶ በብዙ ይፈሳል ከአውራጃ ሁሉ ብዙዎች ሰዎችም ይመጣሉ ከዚህም ቅባት ወስደው በማሰሮቻቸው ያደርጋሉ ይች ምልክትም እስከ ዓለም ፍጻሜ በመኖ እንደምትገኝ ደጋጎች ካህናት ምስክሮች ሆኑ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በሰማዕቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 29 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹 "#ሰላም_ለከ_ድሜጥሮስ_ሰማዕት። ርጉዘ ገቦ በኵናት። እስእለከ ኅፅረኒ በጽጌ ቅድሳት። ኢያማዕርር ጒርዔየ ጸቃውዐ ዘማ ኅስርት። ፈዳዬ መጥባሕት ስሑል ወመሪር ሞት"። #አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_29።
✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ 109፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8።
✝ ✝ ✝
🌹
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወታቀንተኒ ኃይለ በጸብእ። ወአዕቀጽኮሙ ለኵሎሙ እለ ቆሙ ላዕሌየ በመትሕቴየ"። መዝ 17፥39-40። የሚነበቡት መልክዕታት 2ኛ ቆሮ 7፥1-10፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-12 እና የሐዋ ሥራ 9፥20-23። የሚበበው ወንጌል 8፥1-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ታዴዎስ የተአምራት በዓልና መልካም የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
ጥቅምት ፳፰/28/በዚች ቀን ቅዱስ መርትያኖስና መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ። እኒህም ለቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ ::አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በአርማንያ በሥውር እሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት ካደረገ ቡኃላ እኒህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ::አርዮሳዊውንም ንጉሥ ረገሙት :: ንጉሡም እንደረገሙት በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደ እርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም ገደሏቸው:: በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቍስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያማረች ቤተክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን በዓልን አደረገላቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
ጥቅምት ፳፯ /27/በዚች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ። ይህ አባት በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ የወገኖቼን ኃጢአታቸውን፤ የከፋች ሥራቸውንም እያየ ዘወትር ያለቅስ ነበር። ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጐዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል። የንጉሡም መልክተኛ አባ መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ከወደደው ክርስቶስም የመንግስተ ሰማያትን ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
ጥቅምት ፳፮/26/
በዚች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞች ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።
ይህ ቅዱስ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ተሾመ።
በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ:: በውስጧም ሃይማኖትን አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።
የዚያች አገር ገዢም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💥በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
⚡️⚡️⚡️ ስደተኞች ክፍል ፮ ⚡️⚡️
አቅራቢ :- አቤል ለታ
አብርሃም ሙላቱ
ረድኤት ብርሃኑ
ሳሙኤል ገዛኸኝ
🔴 አዘጋጅ :-ኪነ-ጥበብ ክፍል
+1
ጥቅምት ፳፭/25/በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው። በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው። አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው። ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በዚያንም ጊዜ እጅግ ለመስማት የሚዘገንን መከራ እና ስቃይ በህፃኑ ላይ አደረሰበት የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው። ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚለይበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ወርዶ ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት በደረቱም ላይ አድርጎ ወደ አየር አወጣው። የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር
