fa
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

نمایش بیشتر
636
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-47 روز
-1230 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤              ❤ #ሐምሌ ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ላሳለፈ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ታዴዎስ ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ታዴዎስ፦ ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለት ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልአኩ በሚአምር ጎልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ "ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከእንተ ጋራ እኖራለሁና" አለው። ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ❤ ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና "ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን" አሉት። እርሱም "ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ" አላቸው። እነርሱም " እንዳልክ ይሁን" አሉት። ❤ ያሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ "ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኀፍረት ነው ያሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና" አለ። ይህንኔም ብሎ ተነሥቶ እርፋን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበርና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችኖም አረሰ። ❤ የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ "እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን" አላቸው እነርሱም "እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም" አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው "ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱባት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን"። "ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት። እኛም ወዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውጧ ለመኖር እንሻለን" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው "አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ" አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት። ❤ ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን" ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ "ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም" አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። "ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው" አሉት እርሱም "ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻቸችሁ ታይዋቸዋላችሁ" አላቸው። ❤ ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ "እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ" አሉ። እኩሌቶቹም "ልገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማ መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም" አሉ። ❤ እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም በአያት ጊዜ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላክልን" አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ሰዎችም አዩዋት ያቺ ሴትም በከተማው መኳንንቶ "አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች" ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ሰደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለትውን ሴት አወረዳት። ❤ ከዚህም በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። ❤ በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ እውሮች አየ፣ ሀንካሶችም በትክክል ሔዱ፣ ዲዳዋች ተናገሩ፣ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ፣ አጋንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን ስኪያምኑ ሙታን ተነሱ። ❤ ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልቡ አድሮ በሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ላይ አነሳሳው ወደእርሱም ሰገደለትና እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ" አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን "ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻው በሌላው ላይ አታድርግ፣ ደግሞም ገንዘብህ ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለዓለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ" አለው። ይህንንም በሰማ ጊዜ ቊጣን ተመልቶ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ይገድለው ዘንድ አነቀው የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሳ አይኖቹ ተመዘው በወጡ ነበር። ❤ አባት ቅዱስ ጴጥሮስም "የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ" አለው። ያን ጊዜም ተወው። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም "ጌታችን እንደአንተ ላለው ሀብታም ባለፀጋ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ገመል በመርፎ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" ብሎ በእውነት ተናገረ አለው። ጎልማሳ "ባለፀጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል" አለ። ❤ በዚያ ጊዜም በዚያ ጎዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያው ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያው እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣል" አለው።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤                ❤ #ሐምሌ ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን ሰማዕት ለሆነች ሰውነቷን ለእግዚአብሔር ለሰጠች #ለቅድስት_ድንግልና_ለመስጋድልት_ለቅፍሮንያ_ለዕረፍቷ_መታሰቢያ_በዓልና #ለቅዱሳን_መስተጋድላን #ብዮክና_ብንያሚን_ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሮሜ_ሊቀ_ጳጳሳት_ከክልዮስና #ከበርተሎሜዎስ #ከጻድቁ_ከገብረ_መድኅንም_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች #ቅድስት_ድንግልና_መስተጋድል_ቅፍሮንያ፦ እርሷም በደናግል ገዳም ቊጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች። የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው። ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት። በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት። ❤ ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር። ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች። በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ። እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ። እመ ምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች። ❤ በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኖች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም። ቅድስት ቅፍሮንያን "በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት" አለቻቸው። እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው። ❤ ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት። ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦርያናም "አንተ ከሀዲ ይችን ታናሽ ብላቴና እንዳጎስቈልሃት እግዚአብሔር ያጎሳቊልህ ዘንድ አለው" ብላ ጮኸች። ❤ መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህችን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲአሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ። ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች። ❤ ከዚህ በኋላ ደግሞ ምላሷንና ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ሕማም አስነሣት። መኰንኑም እርሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች። ❤ አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ቅፍሮንያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳን_መስተጋድላን_ብዮክና_ብንያሚን፦ እሊህም ቅዱሳን በግብጽ ደቡብ በቴዎዳ አውራጃ ቱና በሚባል አገር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ነበሩ። እነርሱም ወንድማማች ነበሩ። አባታቸውም የቤተ ክርስቲያን ሹም የሆነ ደግና የዋህ ሰው ነበር እሊህም ሁለቱ ልጆች በእግዚአብሔር ጸጋና በቅድስና ፍጹማን ነበሩ። ❤ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ተአምራትን ያደርግ ነበር በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር እነርሱም ከቤተ ክርስቲያኑ የጉድጓድ ውኃ ቀድተው በሽተኞችን ያጥቧቸዋል ወዲያውም ከበሽታቸው ይድኑ ነበር። ❤ አባታቸውም የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ በዚያን ሰዓት ቀሲስ ብንያሚን ቊርባን ያሳርግ ዘንድ የቅዳሴ ልብስ ለብሶ በቤተ መቅደስ ነበረ መልክተኞችም መጥተው አባቱ ለመሞት እንደ ተቃረበ እርሱንም እንደሚፈልገው ነገሩት። ብንያሚንም "የቊርባኑን ሥርዓት ሳልፈጽም ልብሰ ተክህኖውን አላወልቅም ከመሞቱ በፊት እንደየው እግዚአብሔር ከፈቀደ ይቆየኛል ካልሆነም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ። አባቱም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ላከ አባ ብንያሚን ግን የቊርባኑን ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ አባቱ ሔደ ሙቶም አገኘው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅዱሳትም እጅግ አዘነ እነርሱ በእርሱ ዘንድ እየኖሩ ዕቃዎችን ያኖረበትን ቦታ አላመለከታቸው ነበርና። ❤ ወንድሙ ብዮክም አባታቸው ስለ አስቀመጠው ንዋየ ቅዱሳት ወደ አስቆጥስ ገዳም ወደ ቅዱሳን አረጋውያን ሒዶ እንዲጠይቅ መከረው። አባ ብያሚንም በሔደ ጊዜ የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት አባ ዳንኤልን አገኘው አባ ዳንኤልም ስርሱ የመጣበትን ሥራ ሁሉ ነገረው ነገር ግን ወደ አንድ ጻድቅ ሰው እንዲሔድ አዘዘው እርሱ ንዋየ ቅዱሳቱ ያለበትን እንደሚያስረዳው ነገረው። በሔደም ጊዜ እንደ አመለከተው ያንን ጻድቅ ሰው አገኘው። እርሱም ገልጾ አስረዳው በተመለሰም ጊዜ እንዳስረዳው አገኘው። ❤ ከዚህም በኋላ በመልካም ገድል ሁሉ ከወንድሙ ጋራ ተጠምዶ ኖረ። ለሕሙማን ነፍሳቸው ሳትወጣ ያቀብሏቸው ዘንድ ከቅዱስ ቊርባን ከፍለው በሣጥን የሚኖር ሥርዓት ነበራቸው ሰይጣንም ከይሲን አነሣሣውና ሣጥኑን ቀድዶ ከዚያ ከቅዱስ ቊርባኑ በላ። ❤ ብዮክና ብንያሚንም ይህን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዘኑ ከይሲውንም ገደሉት ከዚህም በኋላ የተቀደሰውን ቊርባን ስለ በላ ከይሲውን ይበሉት ዘንድ ተማከሩ ፈቃዱም ከሆነ እንዲያስረዳቸው እግዚአብሔርን ለመኑት የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጸላቸውና ያን ከይሲ ይበሉት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም በሉት። ከበሉትም በኋላ ዐረፉ። ❤ እግዚአብሔርም ሥራቸውንና ገድላቸውን ለአንዲት ድንግል ሴት ገለጸ እርሷም የእሊህን ቅዱሳን ገድል ለሕዝብ ተናገረች። እርሱም የአማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 1 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለቅፍሮንያ_አስናኒሃ_ዘሰበሩ። ወመለያልያቲሃ ዘመተሩ። ወዘንተ ኲሎ እንዘ ይገብሩ። ኢክህሉ በጽንዖሙ ለዲዮቅልጥያኖስ ማኅበሩ። ከመ ይምጥዋ ለክርስቶስ እምፍቅሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 1።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ለስሒት መኑ ይሌብዋ። እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ። ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ። መዝ 18፥12። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 5፥1-18፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 9፥36-ፍ.ም። የሚበበው ወንጌል ዮሐ 20፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

ክረምቱን በአብነት 🎤ከአቀባይ መምህር ተቀድቶ በትውልድ አእምሮ ላይ የተቀመጠ እውነት መጥፋት አይችልም። 🎤የአብነት ትምህርት  ጠንክረው ከተማሩት ተኖ የሚጠፋ፦"የድምጫ ትምህርት የገቦ አዝርዕት"አይደለም።ልጆቻችንን ጠንክረን ብናስተምራቸው ቢያንስ ቢያንስ ለመካሪ አያስቸግሩም። 🎤ሴት ልጆቻችሁንም ወደ አብነት ትምህርት ላኳቸው። "አርፈሽ ተቀመጭ አንቺ አትቀድሺ"?የምትሉ ወላጆች ትክክል አይደላችሁም። የቅዳሴም የማኅሌቱም ዋነኛዋ ሴት አይደለችም እንዴ? ሴቶች በዕውቀት በእምነት ሲጸኑ ያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በብዙ የአገልጋይ ፍሬ ትሞላለች። እግዚአብሔርም በነቢዩ አድሮ "ሴቶች ልጆቼ ቍርባኔን ያመጡልኛል።"ሶፎ.፫፥፲እንዳለ። 🎤ሴቶችም ወንዶችም ልጆቻችን፦ፊደል ቆጥረው፣ውዳሴ ማርያም አጥንተው፣ ዳዊት ደግመው፣የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ አውቀው፣ትምህርተ ሃይማኖት ተምረው፣ሥነ ምግባርን ተላብሰው፣ከመቅደሱ ሥር ዕጣን አሽተው፣ጸበል ጠጥተው፣እምነት ተቀቦተው..ቢያድጉ ጉዳቱ ምንድን ላይ ነው? 🎤እንኳን ከእግዚአብሔር ለተቀበልነው ለአብነት ለሌላውስ ተምህርትስ ቢሆን ይጠቅማል ብለን ገንዘብ ውጥተን ጊዜ በጅተን ደክመን የለም ወይ? 🎤መርጌቶች፣ካህናት፣ዲያቆናት፣ሰባክያን፣የከፍተኛ የአብነት ደቀ መዛሙርት የክረምት ሥራችን በአብነት ትምህርት በኩል ትውልድ መተካት ላይ መሆን አለበት። አጥቢያዎች፣መንደሮች ሁሉ በየአቅራቢያው ትምህርት ሊሰጥባቸው ይገባል። ወላጆች፣ሰበካ ጉባኤያት፣ወጣቶች፣ማኅበራት፣ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ማኅበረ ካህናት፣ሰንበቴዎች..ዐይናችሁን ወደ አብነት መልሱ። እየተደራጃችሁ መምህር መቅጠር ካለባችሁ ቅጠሩ፣መደጎም ካለባችሁ ደጉሙ። በተለይም ሰበካ ጉባኤው የትምህርት ኬላዎን አበጅቶ በበቂ ሁኔታ መምህራንን መመደብ እና መከታተል አለበት። 🎤መምህር የማይመድብ ሰበካ ጉባኤ ካለ ምእመናን አጥብቃችሁ ጠይቁት። የሰበካ ጉባኤ ዋነኛ ሥራው ይሄ ነው።ሕንጻ ግንባታዎ፣ልማቶች ከዚህ ባሻገር ናቸው።በምድር ላይ ሁሉም ከሰው በታች ነው። ሰው ግን ከሁሉም አመክንዮ በላይ ነው። 🎤ዘመኑን መዋጀት፣ቀድሞ መገኘት ማለት ትውልድ ላይ መሥራት ነው። ኋለቀር ማለት የነገውን ትውልድ መርሳት ነው። ስለዚህ በተተኪ ትውልድ ላይ እንሥራ ማለት መጻኢ ዘመኑን እንዋጅ ማለት ነው። 🎤የሰንበት ተማሪዎችም ከነጠላ  ዘፈናዊ ዝማሬ ወጥተን ወደ መሠረታዊ የአብነት ትምህርት እና ትምህርተ ሃይማኖት ብናተኩር ጥሩ ነው።ሀምሳ ዝማሬ ከመላስ አንድ ውዳሴ  ማርያም አጥንቶ መቅመስ ይሻላል። 🎤በተለይም በጦርነት ቀጠና ያሉ ሕጻናት ሦስት ዓመት ሙሉ ያለ ትምህርት በመባጀታቸው በነገው ማኅበረ ሰብእ መካከል ትልቅ ክፍተት ነው። ስለዚህ የማያነብ፣የማይጽፍ፣የማይረዳ፣የማይጸልይ ትውልድ እንዳይኖር ጥልቅ እሳቤ ቅን ህሊና፣ትጋት ያለው ተግባር ይጠይቃል። 🎤የማያነብ፣የማይጽፍ፣የማያሰላ ትውልድ ያለበትን ክፍተት አስበችሁታል? በዲጅታል ዓለም፣በ5G ትውልድ፣በAI ዘመን፣በበርችዋል ሥርዓት መካከል ፊደል ሳይቆጥሩ ሂሳብ ሳያሰሉ ተቀምጠው እንዴት ነው ራሳቸውን መምራት እና ዘመኑን መዋጀት የሚችሉት? 🎤ቢያንስ በየገጠሩ ሁሉ ሰላም መጥቶ የትምህርት ዕድሉ እስኪገኝ ድረስ በአብነት ትምህርት ቤት ከየኔታዎቻች ተምረው ማንበብ፣ መጻፍን፣ቁጥር ማስላት መለማመድ አለባቸው። 🎤በሥሁት ትርክት የተጠለፉት ግን ከትናንት እስከ ዛሬ የሀገር እና የቤተ ክርስቲያን መልካም እና ርቱዕ የሆኑ ሀብተ-ትምህርቶችን አይፈልጓቸውም። አለዚያም በጣሊያን ወለድ ድረታ የደብተራ ዕውቀት እያሉ ያጣጥሏቸዋል።ደብተራ የትምህርት ሚንስተር ሁኖ የሠራት፣ የጠበቃት፣ ያቆያትን ሀገር መሆኗን ስለዘነጉት "ድንቡልቡል መሀይምነታቸው"ሊገልጹብን ይሞክራሉ። 🎤በዚህ መንገድ "ዘመናዊ ፊት ኋላ ቀር ልቦች"በማያባራ ትርክትና ትችት እየነዘነዙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ያናንቋቸዋል ያጠፏቸዋል። 🎤እውነተኛውን መንገድ ከሚያመክኑባቸው ነገሮች አንዱ ትውልዱን ያለ ዕረፍት በሰላም እጦች፣በድረታ ትርክት፣በሥሁት ሥርዓት፣ በመነዝነዝ ማሰላቸት ማፍዘዝ እና ራስ ጠል አድርጎ ከርቱዕ ሀገር በቀል እሳቤው ጋራ ማጣላት ነው። 🎤ከመሠረቱ፣ከጥንቱ፣ከአብነቱ እየለዩ የትውልዱን ህሊናቸውን ብኩን ተግባሩን ትኑን ብኑን ማድረግ ተገቢ አይደለም አልነበረም።በጭፍን ግልበጣ የተዋስነው ያደረሰብንን የማያውቅ የለም ማለት ይቻላል። "ጥንቱን የተውሶ ያውም ጠፋ ተጨርሶ"እንዲሉ። 🎤የባከነ ህሊና እና የተነነ ተግባር ሀገር የለውም፣ሃይማኖት የለውም፣ሥርዓት የለውም፣ሞራል የለውም፣ሰብአዊነት የለውም፣ኪዳን የለውም፣ባህል የለውም፣ ወግ መዕረግ የለውም፣መረጋጋት የለውም፣ዕውቀት የለውም፣ተተኪ ትውልድ የለውም..። 🎤በድርት ስሁት ሀሳባቸው እና ዕቅዳቸው ወደ ጥንተ መሠረታችን እንዳናይ፣ከትምህርት ከመሠረት እንድንፋታ የሚፈልጉ በለ ጊዜዎች በሚያመጡት የመከራ ዜና ጧት መነዝነዝ፣ማታም መነዝነዝ፣ነገም መነዝነዝ፣በቃ ነገር እየፈለጉ መነዝነዝ ዕረፍት ማሳጣት ማባከን ማዋከብ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። 🎤ስለሆነም በችግር ዘመን ያልሠራነውን ትውልድ በሰላም ዘመን ትክክለኛ ሰው ሁኖ አናገኘውም። 🎤መፍትሄው ከጥፋት በላይ የሆነ፣መሠረተ-ዕውቀት ያለው፣ ራስ በቅ የሆነ፣ሁሉን መመዘን የሚችል፣ በራሱ የማያፍር፣አዲስ ተቸኪ ትውልድ በአብነት ትምህርት በሀገር በቀል ዕውቀት መቅረጽ ነው። 🎤ከመሠረቱ የተፋታ ትውልድ ግን ጽኑዕ ሃይማኖት፣ የተረጋጋ ሀሳብ፣ሀገር በቀል ዕቀት፣መልካም ሰብእና፣ትሁት እና ጠቢብ ሰውነት..አይኖረውም። 🎤ሀገር በቀል ዕውቀት የሌለው ሰው ልቡን የተበላ ሰው ነው።ማሰቢያ ልቡን የተበላ ትውልድ ደግሞ መዳረሻው ጉጻጉጽ ነው።መስተሀልይ ህሊናውን ከአብነት አፋትቶ አንተ እለቅ እኔ ላጥልቅ፣አንተ ጥፋ እኔ ላናፋ የሚል ሰው መዳረሻው ወና ነው። 🎤ተተኪውን ትውልድ ከመሠረቱ እያነጹ መተካት እና ማውጣት ካልተቻለ፦ዛሬ በትቂቱም ቢሆን ጽኑዕ ሃይማኖት፣ መልካም ሰብእና፣ቋሚ ጠቃሚ ሀሳብ፣ቅን ህሊና ያላቸው ሰዎችም ከንዝነዛው ብዛት የተነሣ መሰላቸት መፋዘዝ መደንዘዝ ያገኛቸዋልና መንገድ የሚያሳይ ጠፍቶ ጨርሶ መናድ መውደም ሊመጣ ይችላል። 🎤በሥሁት እሳቤ ከሚፈልቀው ንዝናዜ ብዛት የተነሳ አብነት የሚሆነውን አባት እና የህሊና ዕረፍት ያጣ ምእመን ደግሞ ከአስጨኛቂ ጫጫታዎች ሁሉ ለመራቅ ሲል የሚያደርገው የስደት ሽሽት፣የማስመሰል ኑሮ፣የህሊና መታወክ፣ሀገርንም ቤተ ክርስቲያንንም ይጎዳታል። 🎤የአንዱ ዳፋ ሌላውንም ያዳፋልና የአንዱ ንዝነዛ ወደ ሁሉም ምእመናን ይጋባና አዚም በሚመስል መልኩ ብዙዎቻች ንዝነዛው ሰልችቶን ከርቱዓዊ መንገዱ እንዳንወጣ ወሳኙ ጠጋኙ አብነት ትምህርት ነው። 🎤ሚልዮን ብራናዎች፣የተራቀቁ ቅኔዎች፣የለዘቡ ዜማዎች፣የተቀደሱ ባህሎች፣ተሻገሪ ቀመሮች፣ምሥክር የሚሆኑን ውቅሮች፣የርቱዓዊነት መገለጫዎች፣ትናንታዊ ታሪኮች፣ሀገር በቀል ፍልስፍናዎች፣ጣዕም ያላቸው የአባቶች ጫወታዎች፣...የአብነት ፍሬዎች ናቸው። 🎤አብነት ትምህርታችን የትናንት ማያ፣  የነገ ማስያ፣ የዛሬም መዋያ ነው።በራሳችን ዐይን ወደ ኋላ ማየት እና ለነገም መተንበይ የሚቻለው በአብነት መረዳት ውስጥ ተሁኖ ነው። 🎤ስለሆነም ሁሉም ሕጻናት እና ጊዜ ያለን ወጣቶች በሙሉ ክረምቱን በአብነት ማሳለፍ መቻል አለብን። ያልሰማ እንዳይኖር በየአካባቢያችን እንቀስቅስ።         🎤(ክረምቱን በአብነት)🎤

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church.: ❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ_፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሰማይ_ጭፍራ ለተባለ #ለቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ ክርስቲያን_መርዩጥ በተባለ አገር #ለከበረችበት_ለቅዳሴ_ቤቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤት፦ ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበሸ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጒድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋራ አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ለንሡም የቊስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ ከዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አላት። ከእንቅልፍም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ስሟም መርዩጥ ተባለች። ❤ እግዚአብሔር ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቊጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ሰኔ 15 ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ15 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ እንተ ተሐንፀት በመርዩጥ። በትእዛዝ ንጉሥ ሥሉጥ። #ሚናስ ዘአንቃሕከ በድነ ሐራውያ እምጸጥ። አስተዋጺኦሙ ዕደው ዘበበ፪ቱ ቂራጥ። መባአ ለከ ዘነሥኡ በሤጥ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_15።                            ❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለሐዋርያት_ሰኔ_ጾም_ሁለተኛ_ሳምንት #ስለ_ዕርገቱና_ስለ_ጰራቅሊጦስ ለሚነገርበት ዕለተ ሰንበት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ሃሌ ሉያ በ፫ "#ዐረገ_እግዚአብሔር_በቃለ ቀርን #በይባቤ_ዐርገ ወበቃለ ቀርን ወነበረ በየማነ አቡሁ (ዐርገ) አዝ፣ #ዐርገ_በስብሐት_ውስተ_ሰማያት ተኰነኑ ሎቱ መላእክት (ዐርገ) አዝ፣ ተኰነኑ ሎቱ መላእክት ኵሉ ኃይል ወኵሉ ፍጥረት (ዐርገ) አዝ፣ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ ለንጉሥነ። ትርጉም፦ እግዚአብሔር በመለከት #ድምፅ_ዐረገ በዕልልታና #በመለከት_ድምፅ ዐረገ፤ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ፤ በክብር በምስጋና በጌትነት #ወደ_ሰማያት_ዐረገ፤ መላእክት ተገዙለት ኃይል ሁሉ ፍጥረት ሁሉ ተገዙለት፤ ለአምላካችንም ዘምሩ፤ አመስግኑ ለንጉሣችን ዘምሩ አመስግኑ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "ኢትግድፈኒ እምቅድመ ገጽከ። ወመንፈስከ ቅዱሰ ኢታውፅእ እምላዕሌየ። ዕሥየኒ ፍሥሓ ወአድኅኖትከ። መዝ 50፥11_12። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 14፥1-27፣ 1ኛ ዮሐ 4፥1-9፣ የሐዋ ሥራ 10፥11-44። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥17-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ። መልካም ዕለተ ሰንበትና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤             ❤ #ሰኔ ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን #ለቅዱሳን_አባ_አክራና_ለዮሐንስ፣ #ለአብጥልማና_ለፊልጶስ_ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱሳን_አባ አክራ_ዮሐንስ_አብጥለሰማና ፊልጶስ፦ ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ። መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አደረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ሰኔ 14 ቀን ቆረጡአቸው። ❤ ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጠ። ❤ እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዱሳን የፊልጶስን፣ የአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገንዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቊጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት በአባ አክራና ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ14 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለአብጥልማ_ወፊልጶስ_አብያጽ። ዮሐንስ ወአክራ ዘደቡብ ግብጽ። አመ ቆሙ ለስምዕ በዐውደ መኰንን ስሑጽ። እግዚአብሔር ባልሖሙ እምዘ ይሰርር ሐፅ። ወአድኃኖሙ ካዕበ እምእሳት ብቊፅ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የሰኔ_14።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥7-15፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 27፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

ሰኔ ሚካኤል በደብረ አባይ
+9
ሰኔ ሚካኤል በደብረ አባይ

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን በጦርነት ድል አድራጊው ከቤተ መንግሥት ወገን ለሆነ #በንጽሕናው_የመላእክት_አርያ_ላለው #ለከበረ_ሰማዕት_ለቅዱስ_ገላውዴዎስ ለተጋድሎው ፍጻሜ #ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም በእስክንድርያ ከተማ ከሠራችበት #ከአርባ_ሰማዕታት #ከቅዳሴ_ቤተ_ክርስቲያንና #ከእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት #ከቅዱስ_ክርዳኑ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ገላውዴዎስ፦ ይህ ቅዱስ ምድራዊ መንግሥትንና የዚህን ዓለም ክብር የናቀ ነበረ መልካም ገድልንም ተጋደለ። የማይጠፋ ሰማያዊ መንግሥትንና የማያልቅ ክብርንም ወረሰ። ❤ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብጥልዎስ ነው እርሱም ለሮሜ ንጉሥ ለኑማርያኖስ ወንድሙ ነው መልኩም እንደ እስራኤል ያዕቆብ ልጅ እንደ ዮሴፍ ውብ ነበር። እርሱም በጦርነት ላይ የበረታ ነበር። የአንጾኪያ ተወላጆችም ይመኩበት ነበር። ስለ ደም ግባቱና ጽናቱ በሁሉ ዘንድ የተወደደ ነበር። እርሱንም ከመውደዳቸው ብዛት የተነሣ ጠላቶችን ድል እንዳረጋቸው እነርሱም ድል ሁነው በውርደት በብዙ ድንጋጤ ከፊቱ እንደሸሹ አድርገው ሥዕሉን ሥለው በከተማው መግብያ በር ላይ ያኖሩት ነበር። ❤ ቅዱስ ገላውዴዎስ የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር። የሮሜ ንጉሥም ዜናውን ሰምቶ ሊያየው ወደደ ልጁ ገላውዴዎስንም ይልክለት ዘንድ ወደ አባቱ ላከ እርሱም ላከለት። በደረሰም ጊዜ በደስታ ሊቀበለው ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋራ ወጣ በአየውም ጊዜ ደስ ተሰኘበት የሮሜ ከተማ ሰዎች ሁሉም ደስ አላቸው። ከእነዚያ ወራቶችም በኋላ ከቊዝ አገር ሰዎችና ከአርማንያ ታላቅ ጸብ ተነሣ ይህም ቅዱስ ገላውዴዎስ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታምኖ ወደ እነርሱ ወጣ ድልም አደረጋቸው ንጉሣቸውንም ያዘው ጣዖታቶቻቸውንም ሰበራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ዲዮስቆሮስም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክዶ አምልኮ ጣዖትን በአጸና ጊዜ እጅግ አዘነ ፊቅጦር የሚባል የኅርማኖስ ልጅ ወዳጅ ነበረው ሁልጊዜም የመጻሕፍትን ቃል ይሰሙ ነበር ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ያነቡ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ ተስማሙ። በዚያ ጊዜም ሰይጣን በሽማግሌ አምሳል ታያቸው ያዘነላቸውም መስሎ እንዲህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ መልካምች ጐልማሶች ናችሁ የነገሥታት ልጆችም ናችሁ። ስለ እናንተ እፈራለሁ አዝንላችኋለሁም እኔም ከንጉሡ ጋር ትስማሙ ዘንድ ለአማልክትም ታጥኑ ዘንድ እመክራችኋለሁ ሲአዝዛችሁም ትእዛዙን አትተላለፉ እናንተም ክርስቶስን በቤታችሁ አምልኩት ይህ ንጉሥ ኃይለኛ ርኅራኄም የሌለው ጫካኝ ነውና" አላቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገራቸው ሰይጣን እንደሆነ አስገነዘባቸው "ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሐሰት አባት ሆይ ከእኛ ራቅ አንተ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ሕግ ትቃረናለህና" አሉት። ያን ጊዜም መልኩን ለውጦ እንደ ጥቁር ባሪያ ሆነ እንዲህም አላቸው "እነሆ ከንጉሥ አጣልቼ ደማችሁን እንዲአፈስስ አደርገዋለሁ" ሰይጣኑም ይህንን ብሎ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ሔዶ "ፊቅጦርና ገላውዴዎስን ካልገደልካቸው በአንተ ላይ ይነሣሉ አንተንም ገድለው መንግሥትህን ይወስዳሉ እነርሱም የመንግሥት ልጆች ናቸውና" አለው። ❤ ስለዚህም ንጉሡ ወደ ቅዱስ ገላውዴዎስ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ለጣዖታቱም እንዲሠዋ ለመነው የአባቱንም ሹመት ይሾመው ዘንድ ቃል ገባለት ሰምቶም አልታዘዘለትም። ንጉሡም ክፉ ቃልን ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን በድፍረት ይናገረው ነበር ያለ መፍራትም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ሰደበ። ኅርማኖስም ቅዱስ ገላውዴዎስን ወደ ግብጽ እንዲልከውና በዚያ እንዲገድሉት ንጉሡን መከረው እርሱ እንደ ልጄ እንደ ፊቅጦር ዐመፀኛ ነውና። ❤ ንጉሡም ወደ እንዴናው ገዥ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ገላውዴዎስ ትእዛዛችንን አልተቀበለም ቃላችንንም አልሰማም አንተም ወደ ትዕዛዛችን ይመለስ እንደሆነ በብዙ ድካም ሸንግለው ይህ ካልሆነ ራሱን በሰይፍ ቁረጥ"። ቅዱስ ገላውዴዎስ ወደ እስክንድርያ ይወስዱት ዘንድ ንጉሡ እንደ አዘዘ በአወቀ ጊዜ የእኅቱ ባል የሆነ ሲድራማኮስን ጠርቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን በማመን እንዲጸና ወገኖቹንም እንዲያጸናቸው አደራ አለውና በሰላምታ ተሰናበተው። ❤ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም በደረሰ ጊዜ አርያኖስ አይቶ ደነገጠ ተነሥቶም እጁን ሳመው እንዲህም ብሎ ለመነው "ጌታዬ ገላውዴዎስ ሆይ ይህን ሥራ አትሥራ የንጉሥንም ትዕዛዝ አትተላለፍ። ቅዱስ ገላውዴዎስም እንዲህ ሲል መለሰለት "ንጉሥ ያዘዘህን ልትፈጽም እንጂ በነገርህ ልታስተኝ አልተላክሁም" አለው። መኰንኑም እስከሚቆጣ ድረስ እንዲህ እርስበርሳቸው ይነጋገሩ ነበር በመኰንኑም እጅ ጦር ነበር ቅዱስ ገላውዴዎስ ወጋው ነፍሱንም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ሰኔ 11 ቀን ሰጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ምዕመናንም መጥተው የቅዱስ ገላውዴዎስን ሥጋ ወሰዱ በመልካም አገናነዝም ገነዙት ከቅዱስ ፊቅጦር ሥጋ ጋርም በሣጥን ውስጥ አኖሩት። የስደቱም ዘመን እስኪሚፈጸም ጠበቁት። ❤ ከዚህም በኋላም የቅዱስ ፊቅጦር እናት ቅድስት ሶፍያ ወደ እንዴናው አገር መጣች የቅዱሳን ገላውዴዎስንና የፊቅጦርን ሥጋቸውንም ወስዳ ወደ አንጾኪያ አደረሰች። የቅዱስ ገላውዴዎስ ሥጋ አስዩጥ በሚባል አገር ይኖራል የሚልም አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መስተጋድል በቅዱስ ገላውዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሀሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 11 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መድኃኒነ። በእስክንድርያ ዘኮነ። ኀቤከ እግዚኦ አንቃዕዶና አዕይንተነ። ከመ ተሀበነ እምቅኔ ኃጢአት ግዕዛነ። ንጸንሐከ ንሕነ እምዘመን ዘመነ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_11።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት። እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት። እምግብር ዘየሐውር በጽልመት"። መዝ 90፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 5፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 5፥7-12 እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ አቡነ መዝሙረ ድንግልና የቅዱስ ገላውዴዎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። በሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ነገረ ማርያምን ወደ ግእዝ ቋንቋና አራቱ ወንጌልን ወደ ተለያየ ቋንቋ ለተረጎሙት #ለአቡነ_መዝሙረ_ድንግል ለዕረፍታቸው በዐልና #በግብጽ_ቤተ_ክርስቲያ_ጨምር_ቅድስና ለተሰጣቸው #ለአብረ_ገብረ_ኢየሱስ_ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል፦ የተባሉት ጻድቅ አገራቸው ጎጃም ነው፤ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው። ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል። ❤ ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር። በጣም ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው። ከአቡነ መዝሙረ ድንግል እግዚአብሔር አምላክዐ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ፦ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በአገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌል ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብጽ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብጽ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ። ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ። አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብጻውያን ይቀኑባቸው ነበር። ❤ ስልሳ ስድስተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ። በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ አቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው "ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባው ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ" በላቸው ብሎ ነገራቸው። አቡነ ገብረ ኢየሱስም "ከመካከላችሁ ስሙ ገአርጊ የሚባል ጻድቅ አለና እርሱን ሹሙት" ብለው መልአኩ የነገራቸውን መልእክት ነግረዋቸው አባ ገአርጊን ስልሳ ሰባተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል። ❤ አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል። የጻድቁ አባታችን ገዳላቸው በጣና ይገኛል። ሰኔ11 ቀን ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል። ከአቡነ ገብረ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።

ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም
ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም ኮርስ ያልተማራችሁ እና ከቀዳማይ ኮርስ 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁ ሁሉ ያለን ጊዜ አጭር ስለሆነ ሙሉ ኮርሱን በመከታተልና በመጨረስ ለአገልግሎት ብቁ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏 🔴 ማሳሰቢያ :- 👉 ኮርሱ የሚጀመረው በቀን 09/10/2017 ዓ. ም 👉 ኮርሱ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ 👉 ቀዳማይን ያልጨረሰ ሁሉ ሙሉውን የመማር ግዴታ አለበት ( 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁን ጨምሮ ) 👉 ያልተማራችሁ ትምህርቱ ላይ እንድትገኙ እና ላልሰሙ ወንድም እህቶቻችሁን እንድትጋብዙ ስንል በአምላከ ቅድስት አርሴማ ስም እናሳስባለን 🙏                                አዘጋጅ: ት/ት ክፍል

ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም
ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለፆመ ሐዋርያት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክፍላችን ትምህርት ክፍል ከግንኙነት ክፍል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ ላይ ከዚህ በፊት ምንም ኮርስ ያልተማራችሁ እና ከቀዳማይ ኮርስ 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁ ሁሉ ያለን ጊዜ አጭር ስለሆነ ሙሉ ኮርሱን በመከታተልና በመጨረስ ለአገልግሎት ብቁ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏 🔴 ማሳሰቢያ :- 👉 ኮርሱ የሚጀመረው በቀን 09/10/2017 ዓ. ም 👉 ኮርሱ የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ 👉 ቀዳማይን ያልጨረሰ ሁሉ ሙሉውን የመማር ግዴታ አለበት ( 1ም 2ም 3ም ትምህርት የቀራችሁን ጨምሮ ) 👉 ያልተማራችሁ ትምህርቱ ላይ እንድትገኙ እና ላልሰሙ ወንድም እህቶቻችሁን እንድትጋብዙ ስንል በአምላከ ቅድስት አርሴማ ስም እናሳስባለን 🙏                                አዘጋጅ: ጉባኤ ደማስቆ : ት/ት ክፍል