cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🤴Nahi👸Marsi

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
830
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አይለያቹ ምርጦቾ @chel1905 @couple_goal2
نمایش همه...
😘 አለሜ ነሽ 😘 ክፍል 9 መኪናው ሲገለበጥ ግማሾቻችን ደነዝዘን ግማሾቻችን ጮክን ሌሎቻችን ደሞ ለማምለጥ በመስኮት ሞከርን ግን አልሆነም መኪናው ተገልብጦ ሁላችንንም ጣር እና ስቃይ ላይ ሆንን በጣም ተስቃየን አንዱ ጓደኛችን በትንሽ ማቃሰት በኋላ ህይወቱ አለፈ ከዛም በተራ በተራ ቀስ በቀስ የጣር ድምፅ ጠፋ ካንደኛው ጓደኛዬ በስተቀር። ከዛም ከብዙ ስቃይ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች መጥተው ወደ ጣሬዛ እያርጉ በመኪና ይዘውን ሄዱ ኡፍፍፍፍፍፍ ስቃይ ውስጥ ሆኔ ከጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩትን እያስብኩ አዘንኩኝ በጣም እወዳቸው ነበር ልክ እንደ ነብሴ ከ ነብሴ እኩል ብወዳቸውም የራሴን ነብስ እንጂ የእነሱን ማትርፍ አልቻልኩም ለነገሩ የኔንም ነብስ ፈጣሪ በጥበብ ነው ያተርፍው የአንደኛው ጓደኛዬን ጭምር አጋጣሚ እኛ ሁለታችን ከ ጋቢናው እና ከኋላኛው ወንበሮች መሀል ያለው ወንበር ላይ ነበር የተቀመጥነው መሀለኛው ቦታ ብዙ አልተጎዳም አለ አዳም ባዘነ ድምፅ ዲና እየሰማች ሳታስበው ማልቀስ ጀመርች አልቻለችም አዳምም አብሯት አለቀሰ አዳም እንባውን ጠርጎ ወደ ወሬው ተመለስ እምምም እና ከዛ እኔ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ብቻ የሆነ ጊዜ ላይ ካለሁበት ድንዛዜ ስነቃ ሆስፒታል ነኝ ሳሚን አየውት ሳሚ ማለት መዝናናት የሚባል ነበር በጭራሽ የማይወድ እና ከራሱ ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ ሰው ነው በእዛ ምክንያት እኛ ለመዝናናት ስንሄድ እሱ አልመጣም ነበር የሚለን ሁሌም እንዲህ አይነት ነገሮች ላይ አይሳተፍም ሳሚን ሳየው ፈገግ አልኩኝ እሱም ፈጠን ብሎ እ አንዴት ነክ ብሎ ረጋ ባለ መልኩ ጠየቀኝ እኔም በፊቴ ደህንነቴን ገለፅኩለት ነርስ ጠርቶ እስኪመጣ እርፍት እንዳደርግ እና አንድ ጓደኛው ከሻይ ቤት ቡና ልታመጣ እንደሄደች እና እንደምትመጣ ነገረኝ ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ እሺ አልኩት ከዛም ሄደ እንደሄደ በእጇ 2 ሻይ ይዛ መጣች ሳያት በጣም ደነገጥኩኝ በጣም ልቤ ሲመታ ክፍሉን ያናወጠው መሰለኝ የፈጣሪ ያለ እንዴት መጣች ብዬ ገረረመኝ ሄዋን ነበርች ደስስስ አለኝ ስታየኝ ሞቅ ደመቅ ባለ ደምፅ እንዴዴዴዴ አዲዬ ፍቅር ነቃክ ብላ ጭምቅ አድርጋ አቅፋኝ ማውራት ጀመረች የድምጿ ጩሀት እና የተጫነችኝ ቁስሌን መቆጣጠር እስኪሳነኝ አቅፍኝ ስማኝ አዲዬ አስደነገጥከን እኮ የኔን ውድ እያለች ትጨምቀኝ ጀመር ቢያመኝም ህመሜን ዋጥ አደርኩት ምክንያቱም ስታቅፍኝ ካመመኝ ይልቅ ስላቀፈችኝ ብቻ ደስታዬ በጣምም ትልቅ ስለነበር ከዛም ሁለቱን አይኔን ግንባሬን ሁለት ጉንጮቼን እና አገጬን አንገቴን ያለ ፋታ እያፈራርቀች ሳመችኝ ደስታዬ ወደር አልነበርውም የቁስሌም ህመም በጣም አየለብኝ እእእእ ይቅርታ ግን ቁስሌን ስላት ኣ ይቅርታ በጣም ስለተደስትኩኝ አላስተዋልኩም የሆነ ነገር ልንገርክ አለችኝ እሺ አልኳት በጉጉት አፍ አፍፏን ማየት ጀመርኩኝ ቀኝ እጄን ብድግ አድርጋ ልቧ ላይ አደርገችው የልብ ምቷን እጆቼን አስጠግታ አስዳሰሰችኝ ልብዋ በጣም ይመታል እጄ ከ አካሏ ጋር ሲነካካ ትንፍሽ አጠራት ዲና አስቆመችው እና እሺ እና አንተስ አለችው አዳምም ቀጠለ የኔን ነገርማ ተይው እንደ ውሀ ፈስሼ እንደሻማ ቀለጬ ምንም አላልኩም ከዛ እሷ በድጋሚ አይኔን ትኩር ብላ አየችው አየዋት የሆነ ነገር በለኝ እንጂ አለችኝ ምን ልበልሽ አልኳት በፍቅር አይን አያየዋት አዲዬ አፍቅርካለው ካላንተ መኖር አልችልም እያልኩክ እኮ ነው አለች እንባ እየተናነቃት እየተናነቃት መጣና ማልቀስ ጀመርች በጣም ደነገጥኩ እና በድንጋጤ ብድግ ብዬ እንባዋን ጠርኩላት አቀፍኳት ለምን ታለቅሻለሽ አልኳት እንባዋን በእጄ እያበስኩ በጣም ደስስስ ብሎኝ አለችኝ እኔም በምኑ ስላት እንደማፍቅርክ ስነግርክ አይንክ ውስጥ አንደምታፈቅረኝ ስላየው አላስቻለኝም እውነተኛ ግን ያልጠበኩት መልስ ስለሆነ በድጋሚ ደነገጥኩኝ ምንም ቃል ካፌ ሊወጣልኝ አልቻለም በውጤ ግን ለካ ፍቅር እንዲ ነው? አልኩኝ ከዛም ህመሜ ተነሳብኝ አአ አ አአ ስል ድንግጥ ብላ ምነው ምን ሆንክ ስትለኝ አይ ምንም ትንሽ አመመኝ አልኳት እሺ እርፍት አድርግ በላኝ አመቻችታኝ ተኛው ግን እንቅልፍ አልወሰደኝም ከዛ ትንሽ ቆይቼ እእ ስል ከወንበሯ ብድግ ብላ ምነው አለችኝ አፍቅርሻለው ያላንቺ መኖር አልችልም እንዳትተይኝ ልልላት አሰብኩና ፈራው አይ ተይው ምንም አልኳት ልቤ ግን ያለ ማቋርጥ ይመታል ደስስስ እያለኝ መጣ ከዛ ስናወራ ሰው የሰማን ይመስልሻለል አልኳት እኔጃ ግን ለምን ጠየከኝ ስትለኝ አይ ምን አልባት ስላት ፊቷን አኮሰታትራ እ መልስልኛ ምን ልትለኝ ነው ሰው ከሰማስ ምን ይሁን እ ንገርኛ አለች እየጮከች ድምጿ እንኳን ጮሃበት እንዲሁም በጣም ጮክ ያለ ስለሆነ ሽምቅቅ ድንግጥ አልኩኝ ክትክት ብላ መሳቅ ጀመርች ግራ ገብቶኝ አፍጥጬ ዝም ብዬ አያት ጀመር ሳቋን ገታ አድርጋ አትደንግጥ የጮኩብክ ላስደነግጥክ ነው ደሞ ተሳክቶልኛል አይደል አለችኝ እኔም ቁስሌን በማይጎዳ መልኩ ስቄ በጣም ጓበዝ ነሽ አልኮት አይዞክ አትደንግጥብኝ የኔ ፍቅር ጓደኛክ ደሞ ነገ ነው የሚመጣው ቅድም ቡናውን ይዤ ወደክፍል ስመጣ አግኝቼው እንዳይመጣ እና እኔ ካንተ ጋር ብቻዬን መሆን ስለምፈለግ እንዳይመጣ ነግሬዋለው ሀኪሞቹም ካላመመክ አይመጡም ማለቴ ካልጠራናቸው ጠዋት ነው የሚመጡት አለችኝና በል አሁን ተኛ ብላ አደላድላ በድጋሜ አስተኛችኝ ግንባሬን ሳመችኝና ወንበሯ ላይ ልትቀመጥ ስትል እጇኝ ያዝ አረኳትና አጠገቤ ሁኚ አልኳት ት አላርም ቅጠሪና ዶክተሮች ሳይመጡ ትነሻለሽ አልኳት ፈገግ እያለች እሺ ብላኝ ለሊቱን ሙሉ ተቃቅፍን ተኛን ከሚያፍቅሩት ከሚወዱት ጋር መሆን እንዴት ደስስስ ይላል ። አላርሙ ጩኸ አልስማነውም ነበር ጠዋት ዶክተሩ ሊያየኝ ከ ነርሷቹ ጋር ሲመጣ አየን ሁሉም በስሱ ፍገግ ብለው ቁልቁል ሲያዩን ጀመር አይኔን ስገልጥ እና ሳያቸው ደነገጥኩኝ ሄዋንም ተነሳች ግን እሷ ምንም አልመስላትም ደና አደራቹ ብላ ዘብነን ብላ ጉንጮቼን ስማኝ እርቦኛል ቁርስ በልቼ እመጣለው ውዴ ብላኝ ወጣች ብሎ አዳም ንግግሩን ገታ። ዲና አዳምን ኮስተር ብላ እያየችው እንዴ ቀጥልልኛ አለችው ብዙ አስወራሽኝ የቀር ረው ለነገ ይሁንልሽ ነገስ ማን አለው አላት እሺ አለችው ዛሬ አላስጨነቀችውም ሄዋን ክፍል ተያይዘው ገቡ። ሄዋን ጣራ ላይ አይኗን ልክ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ስው ተክለዋለች አተኩሮም ሆነ ሳያተኩር ላያት አንድ በጣም ትንሽ ነገር ጠፍታት ወዴትም እንዳትሄድ ጠብቂያት የተባለች ትመስላለች አዳም እና ዲናን አላየቻቸውም በመጨርሻ ዲና እህም እህም ብላ ከተመስጦዋ አነቃቻት ሄዋንም ሁለቱንም እያፈራርቀች አየቻቸው ከዛም አዳም ላይ አይኖን ጥላ ቀርች አፈጠጠች አስተያየቷ የፍቅር ነው ልክ ከአደጋው በፊት እንደምታየው አስተያየት አዳም እንባው በአይኖቹ ሊወጡ ክፉኛ ታገሉት ታገሉት ከዛም አዳም ክፍሉን በፍጥነት ጥሎ ወጣ ሄዋንም በደከመ ድምፅ እናንተ ማናቹ አለቻቸው ዲና ምን እንደምትል ጠፍባት ተርበተበተች ከዛ... ✎ ክፍል 10 ከ 20 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905🌹 🌹 @couple_goal2 🌹 ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
نمایش همه...
❤️ 1
😘 አለሜ ነሽ 😘 ክፍል 8 ዲና ስልኳን አንስታ አንተ እድሜክ እርዥም ነው አሁን በልቤ ሳነሳክ ነበር አለችው አዳምም አዎ እድሜዬማ በጣም እረጅም ነው ዛሬ እድሜዬ ጨምሯል እልልልል በይ ዲናዬ ሄዋኔ ነቅታለች እናትዬ ነቅታልኛለች ፍቅሬ ነቅታለችችችች አላት ዲና አፏን ከፍታ ቀርች አዳምም ዲና ኧር ምነው ዝም አለሽ ሄሎ ዲና ሲላት የምርህን ነው አለችው እጅግ ፈገግ እያለ የምሬን እኮ ነው ነቃች ታውቂያለሽ ለአያሌ ቀናት የተሰማኝን ስሜት እንዴት እንደተሰቃየው አሁን ግን ያ ሁሉ አልፎ ሄዋኔ ስትነቃ የተሰማኝ ደስታ በቃላት አይገለፅም አለ ዲናም ቀጠል አድርጋ ቆይ እሺሺ መጣው ላያት በጣም ነው የምፍልገው አሁን አንተ የት ነክ ውስጥ ከሷ ጋር ነህ እንዴ የማገገሚያ ክፍል አስገብተዋት እዛው በር ላይ ሆኔ ነው የምደውልልሽ ግን አለ አዳም እረጅም የጭንቀት ትንፋሽ እያወጣ አሷ እኔን አታስታወሰኝም ለኔ በጣም ከባድ ነው ቢሆንም በመትረፏ ግን በጣም ደስስስ ብሎኛል ፈጣሪን አመሰግነዋለው አለ አዴም እና አሁን እንዴት ናት አለች ዲና ለመውጣት እየንጎዳጎደች አዘነ አሁን ጥሩ ስሜት ላይ አደለችም መስለኝ ፊቷ ላይ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሏት ያሳብቃል እና ደሞ ዳክተሩ ማንነትህን ከጠየቀችክ ላለመንገር ጣር ስላለኝ ስለእሱ እቅድ እንድናወጣ ነይ እባክሽ አላት ዲናም እሺሺ ስልኩን ዝጋው እየመጣው ነው አለችና ለባብሳ ወጣች የዲናና የአዳምን ቅርርብ ያየ ሰው ረዥም ጊዜያት በጓደኝነት የቆዩ ነው የሚመስሉት አዳም ይህ ቅርርባቸው ያሰጋዋል ምክንያቱም ያ ሰይጣን ጊዲዮን ጓደኛ እንደሆኑ ካወቀ ይገላታል ስለዚህ ያስጋዋል። ዲና ሀኪም ቤት ደረሰች ሄዌን ወደተኛችበት ሄዳ በሩ ላይ ቆመች ሄዋን በግሉኮስ ተኝታ አዳም ደሞ በፍቅር ወንበሩን ወደ አልጋው አስጠግቶ ተቀምጦ በሀሳብ ነጉዷል የደስታ የመከፋት የማዘን ስሜት ይንፀባረቅበታል ዲና በሩን እንደማንኳኳት ብላ ገባችና ራቅ ብሎ የተቀሙጠውን ወንበር አምጥታ ቁጭ አለች ክፍሉ በዝምታ ተዋጠ ዲናም አዳም አለችው ሄዌንን አተኩሮ ሲመለከታት የነበረው አዳም ወደ ዲና ዞር አለ ሄዋን ንገረኛ ምንድነው ዶክተሩ ያለህ በዝምታ ላብድ እኮ ነው አለችው እሱም ወደ መውጫው በር ሄዶ በአይኑ ተነሽ የሚል ምልክት ለዲና ስጣት ዲናም ወጣች ምንድነው አለችው ዲናዬ ሄዋን ምንም አታስታውስም እንዴት ልለምደው እችላለው አላት እጁን ጭንቅላቱ ላይ እያረገ ከምንም ቅድሚያ ያንተ መረጋጋት ይቀድማል ቢያንስ አንተ በብዙ ከሷ ትሻላለህ ቢያንስ ስላሳለፋችሁት ነገሮች ታውቃለህ ሁሉንም ታውቃለህ ጤነኛ ነህ ስለዚህ ተረጋጋ አዳም አለችው በረጅሙ እየተነፈሰ ልክ ነሽ መረጋጋት አለብኝ አለ ግን ዲናዬ በፈጠርሽ መላ ዘይጂ ሄዋኔን ማን ብዬ ልተዋወቃት አላት ዲናም እንዴ ለካ እሱም አለ ለምን ታዲያ ፍቅርኛሽ ነኝ በላታ አለችው በተዝናኖት በሞላው አነጋገር አዳም ጭንቅላቱን በቀስታ እያወዛወዘ አይ አይሆንም ዶክተሩ ምንም ስላለፈው ህይወቷ እንዳትነግራት በሽታዋ ይብስባታል ነው ያለኝ ስለዚህ ምን እናድርግ አለች አዳምም ቀጠል አድርጎ እንቺና እሷ እህትማማች እንደሆናቹ እና እኔ ደሞ የሁለታችውም ጓደኛ እንደሆንኩ እና ደሞ ሶስታችን አንድ ቤት ስንኖር እንደነበር አንቺ ደሞ ቤት መቀመጥ ስለማትወጂ ውጪ እንደምታድሪ እና አንዳንድ ቀን ነው የምትመጪው እንደዛ ብለን በ ብንነግራትስ አለ። ቀጠል አድጎ የሆነ ጊዜ ነው ከጓደኞቼ ለመዝናናት ወጣን ሹፊሩ ጠጥቶ ስለነበር መኪናውን በፍጥነት ነበር ሲያሽከርክር የነበረው መኪናው ፍጥነቱን ጨመረ ጨመረ በመጨረሻ መኪናው ተገለበጠ። ✎ ክፍል 9 ከ 20 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905🌹 🌹 @couple_goal2 🌹 ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
نمایش همه...
❤️ 1
Photo unavailableShow in Telegram
​​😔ስላንቺ ሳወራ አንደበቴ ሁሉ ይተሳሰራል💘 ቃላቶች ሁሉ የሉኝም💋 እስዋ እኮ………❣ እስዋ እኮ………❣ እስዋ እኮ………❣ እስዋ እኮ………❣ እያልኩ በቃ አንደበቴ ስላንቺ ያዜማል💗.... 🧡አንቺ ለኔ አፈቅርሻለሁ ከሚለውም ቃል በላይ ነሽ ። 💔ያንቺን ፍቅር ልቤ ውስጥ ለመያዝ የኔ ልብ ብቻውን በቂ አይደለም ያንቺን ፍቅር ለመያዝ 100000000000000 ልቦች ራሱ በቂ እስከማይመስሉኝ ድረስ አፈቅርሻለሁ! 💝 @couple_goal2
نمایش همه...
😘 አለሜ ነሽ 😘 ክፍል 7 የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወርቀቱ እንዲህ ይላል ሰላም ላንተ ይሁን ጠበቃ አዳም የጠበቃ እስማኤል ወዳጅ ነኝ ወዳጅ ብቻ አይደለሁም መከታዬ ነው ወንድሜም ጓደኛዬም ሁሉም ነገሬ ነው ለፍትህ ዘብ የቆመክ ለእውነት የምታድር ሰው መሆንህን አውቃለው እስማኤል ፍትህ ለተራበ የሚያጠግብ ለጎደለበት የሚሞላ ነው እስከኖረበት ጊዜ ለእውነት ኖሯል በመጨረሻም ግን ለአንድ አውሬ ሰው ተበገረ ይህ አውሬ የወዳጄ እስማኤልን ህይወት ቀጥፎብኛል አንተም እንደሱ ነህ ባንተ በኩል ፍትህ ያገኙት ስላንተ አውርተው አይጠግቡም እጅግ የጠበቀን ወዳጄን ህልም እንደምታስጨርስው እርግጠኛ ነኝ ትወጣዋለክ እንደምትወጣው አምናለው አንብቦ እንደጨርሰ ያን በተለያዩ ልኮች የተፃፈውን እና አርንጎዴ ክር የተያዘውን ደብተር ከፍተው ውስጡ በሉኮቹ ላይ የሰፈሩትን ተመለከተ ፅሁፎቹ እጅግ የተዋቡ ናቸው በሰማያዊ እና በጥቁር እስኪብርቶ የተፃፈ ነው የታሪኩ ርእስ መንገደኛው ሎሌ ይሰኛል መንገደኛው ሎሌ መሄድ የለመደው አንድ ቀን ተነስቶ መጓዝ የጀመርው በሄደበት ሁሉ ብዙ ይታዘባል ተመልካች ታዛቢ ሁሉንም ይሆናል ዛሬ ከቆመበት መንገዱን ጀምሮል ብሎ አጠር ባለ መልኩ መንገደኛው ሎሌን ገልፇታል መንገደኛ ስሙን ደሞ በሎሌ ቀይሮ የእዛን አውሬ ስራ አስፍሮታል። አዳም መፅሀፍን ማንበብ ቀጠለ መፅሀፉም እንዲህ ይላል። ይገርማችዋል ዛሬ መንገዱኛው ሎሌ እንደለመደው ጉዞውን ቀጥሏል እየሄደ በመንገዱ ያጋጠሙት ደሀ እናት እና ልጅ ን አየ እስከሚችለው ሊከተላቸው ወስኖ ሳይሆን እግር መንገዱን እያያቸው መጓዝ ጀመር እናትና ልጅ በፀጥታ ከተጓዙ በኋላ ልጅየው እናቷን ሽቅብ አንጋጣ እያየች እናቴ አለቻች እናት የስማቻት አትመስልም የእኔ እናት እናትዬ እማ እያለች ስትጎቶጉታት ሀሳቧን እና መንገዷን ገታ አድርጋ ወዬ የእኔ ልጅ አለች በጣም በደከመና ትንፋሽ በተቀላቀለበት መለኩ እማ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ እሽ እሺ ልጄ ጠይቂኝ ፍቅር እና መውደድ ልዩነት አላቸው እንዴ እንዴ እናትም ልጄ በጣም እንጂ በጣም ልዩነት አላቸው ልጅየው እንዴት አለቻት እናት ልጆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ልጄ አለቻት ልጅም እሺ እማ አለቻት ጥንድ ጥንድ የሆኑ አካላቶችሽን ንገሪኝ ብላ እናት ከመናገሯ ልጅት ጥንድ ጥንድ የሆኑት ለምሳሌ አይናችን ሁለት ነው አለች እናት እሺ ሌላስ አለቻት ሌላ ደሞ እጃችን እግራችን ሌላስ አለች እናት ልጅቱ ሌላ ጆሮአችን ሌላ ግን የለም አለቻት እናት ፈገግ ብላ ተሳስተሻል የእኔ ውድ ልጅ አለቻት ልጅም እኔ የምልሽ እማ ይህ አሁን ከጠየቅሽኝ ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው ያገናኘዋል እንጂ ልጄ እይውልሽ እንዳልሽው እጃችን እግራችን አይናችን እና ጆሮችን ብቻ ሳይሆን ከልባችን በቀር ሁሉም አጋዥ አለው ልጅየው ግራ ገባትና እንዴት እናቴ አለቻት ለምሳሌ ጣትሽ ስንት ነው 10 እሺ ጨንጓራችንንስ እኔጃ እማ እሱም ትንሹ እና ትልቁ አንጀት የሚባሉ አጋዦች አሉት ፀጉሯችንንም ብዙ አሉት ከንፍራችን ደሞ ከላይና ከታች አለ ጥርሳችንን ተመልከች ብዙ ናቸው ሊላም ብዙ ጥንድ ነገሮች አሉ ሁለም አጋዥ የላችውም ልባችን ግን ብቸኛ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደሞ ሊ ሌላኛው ልባችን ጋር ሌላ ሰው ጋረ ስለሆነ ነው አለች እናት ልጅቱ እየተገረመች ማን ጋር? ብላ ጠየቀቻት እናትም የወደፊት የህይወትሽ አጋር ጋር እሱ ጋር ነው ለዛም ነው ፍቅር ሲይዘን ሁሉም ነገራችንን የሚቆጣጠርን ፍቅር ሲይዘን ሁሉም አካላታችን ስራውን አቁሞ ልባችን የሚስራው ፍቅር ሲይዘን ልባችንን የሚስማን ፍቅር ሲይዝሽ በ ፍቅር ካፍቀሩት ጋር መኖር እድለኝነት ነው። አዳም ንባብን በእዚህ ገታ እና ወርቀቱን ከደነው። የማያልፍ ቀናት የለም አለፈ ዛሬ ሄዋን ከጥቄት ሰአታት በኋላ ትነቃለች አዳም ውስጡ ደስ አለው ቀጥሎ የሚፈጠረው ነገር መልካም እንደሚሆን አሰበ ስትነቃስ አለ በልቡ ስትነቃስ እንዴት ነው የምቀርባት ሁሉንም ነገር እኮ እረስታለች ድጋሚ እንድትወደኝ ላረግ ነው ስቀርባት ማነህ ብትለኝስ ልቡ ፈራ ውዴ እረሳሽኝ ወይ እስቲ መልሽለኝ ምነው ቢሆን ለእኔ ሁሉን ባርገልኝ ብዬ ለመንኩትኝ ሀሳቤን ቢስማኝ ብዬ በመጠበቅ ይህው ወራት ሞላኝ ለእሱ ብዙ ነገሩ ናት የሄዋን እጃች በትንሹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አላመነም ዶክተሩ ትነቃለች ቢለውም የሚንቀሳቀስ እጇን ሲያስ አዳም ደስስስ አለው ዶክተሩን ለመጣራት ከነፈ አጠገቡ ማንም አልነበርም ዲና በጠዋት ቤቷ ፍቅድ ጠይቃ ሄዳለች ዲና በመንገድ ላይ እና ቤቷም ከገባች በኋላ ሰለ አዳም ያለ ማቆርጥ ታስባለች ዲና ስልኳ ጠራ አዳም ነበር ሄሎ አለችው በተርጋጋ ድምፅ....... ❤️❤️❤️❤️ ✎ ክፍል 8 ከ 20 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905🌹 🌹 @couple_goal2 🌹 ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
نمایش همه...
❤️ 1
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 6 ✍አዘጋጅ➛ Hema . . . አዳም ድካም እየተስማው ሲመጣ ሌላኛው አግዳሚ ወንበር ላይ ሄዶ ጋደም አለ ግን ነገ ሄዋን ስለምትነቃ በጉጉት ሊሞት ነው ሄዋን ከነቃች በኋላ ለሚፈጠርው ነገር እራሱን አእምሮውን አዘጋጀ ሄዋን ነገ ከኮማ ስትነቃ ልክ እንደማታቀኝ ልታስመስል ነው ወይ ብሎ እራሱን ከጠየቀ በኋላ መልሶ ለእራሱ አይ አይ ሄዋኔ ወዳ አደለም የረሳችኝ እንደዚህ መሆኗስ ለእኔ ስትል አደል አለና እራሱን አፅናና እንዲ ከራሱ ጋር በሀሳብ ሲሞገት ሳያስበው እንቅልፍ አሽለበው። የሆነ የሚያስፍራ ኮቴ ሰማ በቀስታ የሚጓዝ ማን እንደሆነ ለማየት ቀና አለ ምንም አይነት ሰው አልታየውም መልሶ ተኛ አሁን የሚንሾካሾክ ድምፅ ሰማ ቀና ሲል ከእሱ ትይዩ የተኛችው ዲና የለችም የት እንደሄደች ግራ በመጋባት እና በፍርሀት ስሜት ወደ ሄዋን ክፍል እያመራ ሳለ ዲና በ2 ትልልቅ አቅም ባላቸው ስዎች ተይዛ በጥቁር ፕላስተር እጇ አፏ እና እግሯ ተይዟል በአስተማሚ ወንበር ላይ ጥብቅ አድርገው አስርዋታል ። አዳምን ስታየው በተቀመጠችበት ወንበር ላይ መወዛወዝ ጀመርች አዳም ከታስረችው ዲና ትይዩ ኮማ ውስጥ ያለችውን ሄዋንን አንድ ጭንብል ያርገ ሰው በህይወት እና በሞት መካከል እስትንፋሷ የሆነውን ማሽን አዳምን ፍገግ ብሎ በ ሰራውልክ አይነት አስተያየት እያየው ነቀለው አጭር ጩሀት ሰማ ዞር ሲል ዲናን ድምፅ በሌለው መሳሪያ አናቷን በታተኑት አዳም አይይይይይሆሆሆሆንንምምምምምምም ብሎ ጮከ ኧረ ድረሱልኝ ሰው የለም እንዴ እያለ ቢጮክም ምንም አይነት ሰው ሊደርስለት አልቻለም አዳምን የሆነ ባትሪ መሰል መብራት ነገር ስውነቱ ላይ ጭንብል ከለበሱት ውስጥ አበራበት አዳም አቅም አጠርው መንቀሳቀስም አልቻለም ከቆይታ በኋላ የአንድ ሰው ኮቴ ተሰማው ይህንን ኮቴ ያውቀዋል ሁለት እግር አንድ ከዘራ ባለ ከዘራው እና ባለ ብዙ ሀጢያቶች ባለቤት ይህ ሰው ሄዋን ለእዚህ ችግር እንድትጋለጥ ያረገው ሰው ነው ፈገግ እያለ ወደ አዳም ቀረበው አዳምም አይሆንምም ብሎ ከህልሙ ነቃ ዲና ደንግጣ በርግጋ ተነሳች ምንነው ችግር አለ አዳም አለችው እሱም የለም ተኚ ብሏት በጥድፊያ ሄዋን ጋር ሄዶ በመስታወቱ ያያት ጀመር። እውነት ቢሆንስ ቆይ ህልሜ ካንቺ ተለይቼ እንዴት እኖራለው ብሎ ተንስቀሰቀ። ይህ ሰው ጌዲዬን ይባላል በወንጀል የታወቀ ነገር ግን መፍትሄ ያልተገኘለት ሰው ለብዙ ህፃናት ደሀዎች እና ፍትህ ፍላጊዎች እልቂት ተጠያቂ እጁ እስከ ከፍተኛ የወንጀልም ሆነ የቢዝነስ ነክ ጉዳዎች ላይ የሚረዝም ከፈለገ ምንም ማድርግ የማያቅተው ህይወት ያለው ሰው የሚታዘዘው ነው። ታዲያ ለእሱ አለታዘዝ ያለ ስው በህይወቱ ፈርዶ ነው ባአስቃቂ እና በሚዘገንን መልኩ ያስቃየዋል በቁሙ በህይወት እንዳለ ያለ በለዚያ ፈፅሞ አይርካም አንድን ሰው ገደለ ማለት በጣም ጥሩ ስራ እንደስራ ነው የሚስማው ሰውን በቁሙ ማስቃየት በአለም ላይ ለእሱ ትልቅ ፌሽታ ነው ሁሉም ሰው የእዚህ ስው ስም ሲነሳ ይንቀጠቀጣል። አዳም በጥብቅና ሙያው ማንም የማይስተካከለው እልልልል የተባለለት ጠበቃ ነው ስራ የጀመርው ከአመት በፊት ቢሆንም ባጭር ጊዜ ባጭር የፍርድ ቀጠሮ ብዙ አልበገር ባይ እና ወንጀል ስርተው የሚሸሽጉ ስዎችን አጋፍጦ ለፍርድ ልኳል ወደ ሚገባቸው አስናብቶቸዋል ።ጠበቃ አዳም ማለት ለወንጀለኖች ስይጣን ፍትህ ለተነፈጉ ደሞ መላክ ነው። ጌዲዮን የአዳምን የጥብቅና ችሎታ እና ዝናውን ሰምቶ በቢዝነስ ይሁን በማንኛቸውም አይነት ጉዳዮችን አብሮት እንዲሆን በረብጣ ገንዘብ ድርድር ያቀርብለታል ጊዲዮን በዙሪያው ሌሎች የእራሱ ጠበቆች ቢኖሩትም የአዳምን ጥብቅና ግን አብዝቶ ፈልጎታል አዳም ግን የጊዲዮን ድርድር ሆነ ገንዘብ አላማለለውም ጠበቃ አዳም ለህሊናው የተገዛ ለፍትህ ጥብቅና የቆመ ለእውነት የሚኖር ሰው ነው ። ልክ እንደ አዳም በጊዲዮን አልመራ ያለ እና ጊዲዮን በቁሙ አስቃይቶ የገደለው እስማኤል የተባለ እሳት የላስ ጠበቃ ነበር እስማኤል የጊድዮንን ትእዛዝ አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ሊያስፈርድበት ሂደት ጀምሮ ነበር በጊዲዮን ሴራነት ሰውን ያለ ምክንያት በሀሰት በመፍርድ ተብሎ ተከሶ ለእርዥም አመት ታስሮ የታሰርበት እስር ቤት ውስጥ በጊዲዮን ትዛዝ መሰርት የታሳሪያን ሻውር ቤት ውስጥ ሞቶ ነበር የተገኘው ይህንን ጠበቃ መጀመሪያ የሚወዳቸውን ስዎች በመግደል ነበር አይምሮውን የገደለው ጌዲዮን ይህ ነው ቁመቱ እጅግ የረዘመ የአይኑ ብሌንን ትኩር ብሎ ለተመለከተው ልክ እንደ በርበሬ የቀላ መልኩም ወደ ጥቁር ያደላ ሰው ነው። ጋሞ ጎፋ እንደሆነና ይህንን ፀባዩን ከአባቱ እስከ ሰውነት አቆሙ እንደወርሰው ይወራል ብዙ ሴቶችን አስርግዞ አረገዝኩ ብለው ሲነግሩት የፀነሱትን ፇታ ካወቀ በኋላ ሴት ከሆነች ከእነ እናትየው ይገላታል የተረገዘው ወንድ ከሆነ ግን እስኪወለድ ጠብቆ እሱን ካልመስለ ይገለዋል ከመሰለ ግን አሳድጎ ገረዱ ያርገዋል ይህንን ታሪኩን መንጉደኛው ሎሌ በሚል ርእስ ያ እሳት የላስ ጠበቃው እስማኤል ፅፎታል እንዲፅፍ የረዳው ደሞ የጌዲዮን አሽከር ነበር፡፡ አዳም ጠረፔዛው ላይ ፒያሳ አራዳ ጋር 9ስአት ጠብቀኝ የሚል አጠር ያለ ፅሁፍ አገኘ አዳም የሰውየውን ማንነት ሳያውቅ የተባለበት ቦታደረሰ ምናልባት ፍትህ የተነፈገ ሰው ስለሱ ሰምቶ ሊያገኘው እንደፈለገ አልተጠራጠረም ፒያሳ ጋር እንደደረሰ የሆነ ኩትት ያለ ልብስ የለበሰ ሰው ላዳ ይዞ ና ግባ እኔ ነኝ የጠራውክ ብሎ ካስገባው በኋላ ጭር ያለ ቦታ ወሰደው ሲደርሱ የተቀመጥከበትን ወንበር ግለጠው እና እየው ብቻህን ሆነክ ክፈተው ተጠንቀቅ ማንም እንዳያይክ እዚህ ውስጥ ስለከተትኩህ ይቅር በለኝ ግን እንደምታስተካክለው አውቃለው አለውና ቤቱን ሳይነግርው ወደ ቤቱ አደርሰው አዳም ቤቴን እና መስሪያ ቤቴን እንዴት አወቀ ብሎ ለእራሱ ጠይቆ ለስውየው ሳይጠይቅ ወረደ ቤቱ በጥድፊያ እንደገባ ቦርሳውን ከፈተው ቦርሳ ውስጥ በብዙ የተለያዩ ልሙጥ እና ባለ መስመር ሉክ ለሁለት ታጥፈው በእስቴፕራል ሳይሆን በአርንጓዴ ክር የተሰፋ ደብተር አለ ሳያነበው እየገላለለጠ ማየት ጀመር የብዙ ስው ፎቶዎች እና ከፎቶዎች ስር ማብራሪያ ተፅፏል ደብተሩን ከደነው እና ቦርሳ ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ ስአት አገኘ በድጋሜ እጁን ሰደደው የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወረቀቱ እንዲህ ይላል.... ይቀጥላል... ✎ ክፍል 7 ይቀጥላል... ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905🌹 T.me/couple_goal2
نمایش همه...
❤️ 2
😘አለሜ ነሽ😘 ክፍል_5 ግጥሜን ገጥሜ ስጨርስ ጮክ ብዬ የማንብ ልምድ ነበርኝ አንብቤ ስጨርስ ዋው በጣምምምም አሪፍ ነው ብርቮ የሚል ድምፅ ከኋላዬ ከጭብጨባ ጋር ሰማው የስማውት ደምፅ በጣምምም ጮክ ያለ እና ጆሮ የሚበሳ ነበር ያቺ ሴት ሄዋን ነበርች ለካ ከምቀመጥበት ዛፍ ጀርባ ሄዋኔ ነበረች ዛፉ በጣም ሰፊ ግንድ ስላለው አላየዋትም ነበር ጎበዝ ነክ ብላ ሞቅ ባለ ድምፅ ግንባሬን እና ጉንጬን ሳመችኝ ዲና በመገርም እንዴ ሳታቅክ አለችው አዳምም ፍገግ ብሎ አዎ ሳታቀኝ ዲናም ፈገግ ብላ እና አንተ ምን አለካት እኔ እኔማ እኔማ ስስመኝ ዲና አታጓጓኛ በእናትክ ንገርኝ እሺ ይኸውልሽ ከሳመችኝ በኋላ ምንም ያልኳት ነገር የለም ፈዝዤ ነበር የሳመችውን ጉንጬን ይዤ የቀረውት እሷ ፊት ላይ ግን ስስመኝ በመፍዘዜ ምክንያት ሳቅ ይታይባታል ደግማ ጠጋ ብላ "ምነው ችግር አለ?" አለችኝ አይ ስላት እና "ፈዘካል እኮ እሺ በቃ ቻው እንገናኛለን በቀጣይ ለእኔም ግጥም ገጥመክ ይዘክ ና እሺ" ስትለኝ "እሺ መቼ አልኳት".... "ነገ ማታ 12 ስአት ላይ እዚህ አለችኝና አትፍዘዝ ስስምክ ስትፈዝ እኮ ሳቄም መጥቶ ድንጋጤም ያዘኝ" ብላ በድጋሚ ግንባሬን ግጥም አድርጋ ስማኝ ሄደች ከሄደች በሆላ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ዲና በወሬው መሀል ገባችና እንዴት ግን" አለች ምን እንዴት አለው ያኔ ጓደኛዬ የለከፋት ለት ገና ሳያት እኮ ነው ልቤን የስርቀችው ኡፍፍፍፍፍፍ በጣም ደስስስስ እሚል ስሜት ነበር የተሰማኝ የምር ከሳመችኝ በኋላ ያለውን ጊዜ ዝም ብዬ ስስቅ አሳለፍኩት ነገ በድጋሜ ተገናኝተን ግንባሬን እና ጉንጭኤን በደንብ እንድትስመኝ ምርጥ ግጥም ልገጥምላት ወስኩኝ ዲና አፉ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም እሱም በጣም በተመስጦ ነበር ሲነግራት የነበርው ጉሮሮውን ጠራርጎ ሊያወራ ሲል "ንገረኛ" አለችው እሱም ልነግሽ እኮ ነው ከዛ ማታ ለእሷ ግጥም ስፅፍ አመሸው ዲናም ፈጠን ብላ ምን የሚል እስቲ በልልኝ ስትል ኧረ ተረጋጊ አላትና ወደወሬው ተመለሰ ማታ ግጥም ገጥሜላት ግጥሙን12 ሰአት ደርሶ እስከማነብላት ቸኮልኩኝ በጣምም ጓጓውኝ ሰአተለ እንደምንም ደረሰልኝ እና 11:40 ላይ የግራሩ ዛፍ ስር ቁጭ ብዬ ጠበኳት 11:50 ሆነ ሰአቱ አልሄድ አለ በመከራ 12 ስአት ሞላልኝ አልመጣችም ባትመጭም ቅጠሪኝ አለ ገጣሚው ባትመጣም ስለ ቀጠርችኝ ደስስ ብሎኝ ነበር ከባትመጭም ቅጠሪኝ ግጥም ውስጥ የነፍስ ጥርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ በቆመ አውሎ ንፍስ ተመቶ እንደመውደቅ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ የሚያሳቅቅ ነበር እንደሌለ የገጠመው ግጥም ውል አለብኝ ትዝዝም አለኝ 12:15ሲል ሄዋኔ ጥቁር የቱታ ሱሪ ሌዘር ጃኬት አድርጋ እስኒከር ጫማ ተጫምታ ስትመጣ አየዋት ልቤ እሷ በቀረበችኝ ቁጥር እርምጃዋን ባፈጠነችው ቁጥር የእኔም የልብ ምት ይፈጥን ጀመር በስተመጨርሻ እኔ ካለሁበት ደረሰች እና ጉንጬን ስማኝ ቀልጠፍ ብል ተቀመጠች እንደተቀመጠች እጇን ወደፊቴ ዘርጋችው አፍጠጠች አፈጠጥኩባት እ ምን ታፈጥብኛለክ ልትለኝ ነው እንዴ በል ግጥሜን ስጠኝ እንደውም አንተ እራስክ አንብብልኝ አለችኝ ከዛ እኔም ድምፄን ለሰለስ አርጌ ግጥሙን ማንበብ ጀመርኩ ግጥሙ እንዲህ ይላል ዲና በጣምም ተመስጣ እሺ በልልኝ አለችው ከግራሩ ዛፍ ስር ከግራሩ ዛፍ ስር ልክ እንደለመድኩት እያነበብኩ ሳለ ግጥም የገጠምኩት በጩከት ውስጥ እና በመመስጥ ውስጥ አንድ ድምፅ ተስማኝ የሚመስጥ ድንገት ከየት መጣ ብዬ ደነገጥኩኝ አንድ ልጅ ነበርች ግጥሜን ስቀኝ ከተመጥኩበት ከግራሩ ዛፍስር ከጀመርዬ ሆና ቃላቶችን ሳስር ልጅት ብቃቴ እጅክ ተደምማ ጉንጭና ግንባሬን በአድናቆት ስማ ለኔም ግጠምኝ ብላ ብጠይቀኝ 12 ሰአት ላይ ልጅት ቀጠርችኝ ትእዛዝንን አክብሬ ይህው ግጥም ገጠምኩኝ የሚል ነበር እና ልክ ግጥሙን አንብቤ ሰጨርስ አመሰግናለው የኔ ውድ ብላ ሁለቱን ጉንጮቼን እና ግንባሬን ሳመችኝ ዲናም ወሬውን እኔ እምለው ሄዋን ግን እንደተርዳዋት በጣም ሰውን መሳም ትወዳለች አለች አዳምም ቀጠል አድርጓ ሄዋኔ መሳም ትወዳለች አዎ መሳም ትወዳለች አለ እና ዝም አለ ዲና እሺ ቀጥላ አለችው አዳምም ወሬውን ቀጠለ ከዛ በነጋታው ጠዋት ክላስ ልገባ ሰል ሄዋንን ከብዙ ወንዶች ጋር ቆማ ስትሳሳቅ አየዋት ቅናት ቢጤ ጫር አረገኝ ቆሜ የሚሆነውን ማየት ጀመርኩ ትንሽ ካወሩ በኋላ ሄዋኔ ሁሉንም እየዞረች ግንባራቸውን ሰማቸው ሄደች እራቅ ካለች በኋላም እጆን እያውለበለበች ተሰናብታቸው ወጣች ልከተላት ስለፈለኩኝ መከተል ጀመርኩኝ። አዳም ዲናን እንደደከማት እያስተዋለ ውይ በጣም ደከመሽ አይደል እንቅልፍሽ መጥቷል ታስታውቄያለሽ በቃ ተኚ ነገ እነግርሻለው አላት አይ ንገርኝ አለችና ድርቅ አለች ግን ደሞ እሱም ድርቅ ብሎ እንድትተኛ ነገራት እሺ ብላ ካመጣችው አነስተኛ ኩኪስ ውሀ እና ጋቢ ሰጠችው እሱም ወደ ሄዋን ሄዶ ሄዋንን በተመስጦ እና በፍቅር አይን ማየት ጀመር ይቀጥላል... ✎ ክፍል 6 ይቀጥላል... ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905🌹 T.me/couple_goal2
نمایش همه...
❤️ 1
አለሜ ነሽ ክፍል 4 . . . አዳም ዶክተሩ ጋር ከመሄዱ በፊት ሄዋን ስትነቃ አበባ መስሎ እሷ ፊት ለመቅርብ በማስብ እንዳልተጨፈጨፈ ደን የተጠቀጠቀውን ፂሙን ሊስተካከለው ፀጉሩንም በወጉ ለማድርግ በማስብ ሄዋንን አይቶ ባይጠግባትም ብዙ ደቂቃ አይቷት ወደ ፀጉር ቤት ከነፈ በደስታ በሳቂታ ፊት እየተራመደ ከሆስፒታሉ ትንሽ እራቅ ብሎ ወደሚገኘው ፀጉር ቤት ገባ እና ቁጭ አለ ወረፋው እስኪደርስ የእሱን እና የሄዋንን ፎቶዎች እያየ ውስጡ በሀሴት ሞላ ፀጉር ቤት የተከፈተው ሬዲዮ ላይ አንድ ታዋቂ ዘፋኝ ቃለ ምልልስ እየተደርገለት ነው ስልኩን በኪሱ ከቶ ቃለ ምልልሱን መስማት ጀመር ጠያቂው ለታዋቂው ዘፋኝ የሚጠላው ነገርን ጠየቀው ያው ሁሉም የሚለው ግን የሆነውን ውሽት እንደሚጠላ መለስለት በስተመጨሻ ማስተላለፍ የምትፍልገው ነገር ካለክ እና አንድ ዘፈን ለአድማጮቻችን ብታስማልን የማስተላልፈው ነገር እንኳን የለም ዘፈን ደሞ ከእኔ ሳይሆን ከሌላ ሰው ዘፈን ላንጎራጉር ታመሽ ታምሜያለው ስደኝም እንደዛው ስትሞች ግን አልሞትም እኔ ምን በወጣኝ ብሎ እንጉርጉሮውን ገታ። አዳም በጣምም ተናደደ ብሽቅ አለ በገነ... ምክንያቱ ግልፅ ነው የመጀመሪያው ሰው እንዴት የሚያስተላልፈው መልክት አይኖርም በሚለው ሲሆን ሌላው እና ዋነኛው ደሞ ለእሱ አይነት አፍቃሪ ልብ ለሚያፈቅራት ሴት ላበደው ለአዳም ታመሽ ታምሜያለው ስድኝም እንደዛው ስትሞች ግን አልሞትም እኔ ምን በወጣኝ የሚለውን ቃል መስማት ያማል አይምሮን አልፎ ውስጥ ድረስ ልብ ድረስ ገብቶ ያደማል። ፕሮግራም አቅራቢዋም ለመስናበቻ የሚሆን ዘፈን ብላ አሜን አሜን አሜንንንን ልበል እስቲ አሜንንን የሚለውን የኑዋይ ደበበን ዘፈን የፕሮግራሙ መዝጊያ አረገችው ቢያንስ ጋባዥዋ በጋበዘችው ዘፍን ንዴቱ ጠፋ ወደ ኋላ ከሄዋን ጋር ወዳሳለፈው የፍቅር ጊዜ ማስብ ጀመር ከ አመት በፊት ዩንቨርሲቲ እያሉ ልደቷን ስታከብር ይህንን ዘፈን በማራኪ ድምፁ በ ዩንቨርስቲ የሙዚቃ ባንድ አጋዥነት በምርጥ እና ጊቢውን ባነጋገረ እና ባስደመመ መልኩ ዘፍኖ ሰርፕራይዝ አርጓት ነበር ከዛም ልደቷን ግቢ አክብረው ወጣ ብለው ሲዝናኑ በድንገት ተንበርክኮ በደስታ የታገቢኛለሽ ጥያቄ አቅርቦላት እሷም ተንበርክካ ተያይዘው ተላቅስው ጥያቄውን የተቀበለችበትን ጊዜ ከዛ ደሞ እሷም በተራዋ አንነጋገርም ጨዋታው ይቅርብኝ ቁጭ በል ከጎኔ ያይን እራብ አለብኝ የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዘፈን ከዘፈኑ ጋር አብራ እየዘፈነች በፍቅር አይን እንዴት ታየው እንደነበር አስታወስ እና ፍገግም ሳቅ ሳቅ እያለ ከዋዠቀበት ሀሳብ ነቃ ያነቃው የፀጉር ቆራጩ ድምፅ ነበር አዳም ደነገጠ ብዙ ጊዜ ጠርቶት እንዳልስማው ተርዳ እንደማፈር ብሎ ቀና ሲል ና ወርፋክ ደርሷል ብሎ ፀጉር መታጠቢያ መቀመጫው ላይ እንዲቁመጥ ጋበዘው አዳምም ቀልጠፍ ብሎ ተቀመጠ ለ2 ወራት ውሀ ያልነካውን ፀጉሩን አጠበው ለእሱ ፊት የሚሆን ቁርጥ አስመርጦ ተቆርጦ ለ ፁጉር ቆራጩ ከምስጋና ጋር ክፍያውን እስከ ጉርሻው ሞላ አድርጎ ሰጠብ ፀጉር ቆራጩም ጎንበስ ቀና ብሎ አመስግኖ አዳምም በአቆራርጡ ቆራጩም በጉርሻው ተደስተው ተመሰጋግነው ተለያዩ አዳም በጣም ሽበላ ሆኖል ያው ከ አንገቱ በላይ ቢሆንም ። አንድ ነገር እንደሚቀርው አሰበ ልብስ እና ጫማ ልግዛ ወይስ ሄዋኔ የምትወዳቸውን ልብስ እና ጫማ ላድርግ ብሎ ከራሱ ጋር ትንሽ ግብግብ ከፈጠር በኋላ በስተመጨርሻ ሄዋኑ የእሱ ውድ የምትወዳቸውን ለማድርግ ወሰነ ይህን እያስበ ሆስቲታል ደርሰ ዶክተሩ ና ያሉበት ስአት ስለደርስ ወደ ዶክተሩ ቢሮ አመራ ሲደርስ አንኳኳ ኳኳኳኳኳኳኳኳ ዶክተር "ማነው? ይግብ" አለ "እኔ ነኝ" አለ አዳም ዳክተሩም "ኦኦኦኦኦኦ አዳም ና ግባ እባክህ ቁጭ በል አዳም በጣም አምሮብካል ደሞ ዛሬ አሉ አዳምም ያው ለእሷ ብዬ ነው አለ አዳም ልብ እንደ ከበሮ ለጉድ መምታት ጀመር አዳም ጉሮሮውን ጠራርጎ ለምን ነበር የፈለጉኝ ዶክተሩ ርዥምምምም ትንፋሽ ተንፍሰው ትንፍሻቸውን መልስው ከስበሰብ በኋላ ንግግራቸው እንዲ ሲሉ ጀመሩ እየውልክ አዳም አሁን በምነግርክ ነገር በጭራሽ እንዳታዝን እንደውም ጠንካራ ሁን የአዳም የልብ ምት በጣምም ፍጠነ ልብ በአፉ ሊወጣ ደርሰ እሺ ዶክተር ቀጥሉ እኛ ሄዋን ብለው አሁንም ረጅም ትንፋሽ ወስዱ አዳም ሊያብድ ምንም አለቀርውም እና ምን ዶክተር ንገሩኛ እእእእ ዶክተር ወሬያቸውን ቀጠሉ ሄዋንንንን አዳም ሰፍ ብሎ ሄዋን ምን ብሎ አፈጠጠባቸው ሄዋን በደርስባት የመኪና አደጋ ምክንያት ብለው አሁንም ዝም አሉ አዳም እራሱን መቆጣጠር አቃተው እኔ ላብድ ነው በሉ ይናገሩ ምንድነው መሄድ አችልም ሊሉኝ ነው ወይስ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሷል ስለዚህ አተርፍም የምታያት ዛሬ ማታ ብቻ ነው ልትሉኝ ነው አለ ዶክተር አይ እሱ አደለም እንደዛ አደለም ሄዋንንን የምታያት ነገ ነው መዳኒቷን አስተካክዬላት ነገ እንድነቃ አርጊዋለው ግን ሄዋን ጭንቅላቷ በሀይል ስለተመታ ብሎ ዶክተሩ ወሬውን ሳይጨርሱ ይህው ብያለው በቃ ትሞታለች ልትለኝ ነው አደል አለ በለሆሳስ ዶክተርም አይ አይ ሄዋን አልዛይመር ወይም የመርሳት በሽታ ይዞታል ሰለዚህ አንተንም ሆነ በዙሪያዋ ያሉትን ነገሮች አታስታውስም አለው አዳም ስቅስቅ ብሎ አለቀስ እናትዬ መከራሽ በዛ የኔ ህይወት አያለ ተንስቀስቀ ዶክተሩ ከተቀመጠበት እየተነሳ አዳም ላንተ ከባድ እንደሚሆን አውቃለው ግን ቆፍጠን ማለት አለብክ አለው አዳምም እንዴት እንዴትትትት አለ በመከራ ዶክተሩ አዳምን አረጋጋው ከረዳሃት ወደ ድሮ አቆሟ እንደምትመስል ነገረው እና ነገ ማታ ስትነቃ ቁጥብነት እና ስርአት ባለው መልኩ እንዲያናግራት አስጠነቀቀው አዳም ምድር የተደፍበት መሰለው ከዶክተሩ ቢሮ ውልቅ ብሎ ወጣ ቤተ ክርስቲያን ሄደ እና ሄዋንን ትውስታዋን እንዲመልስ የሚያደርግ ትግስት እንዲስጠው እና እሷንም እንዲያኖርለት ለመነው ተማፀነውም ፀሎቱን ሲጨርስ ወደ ሄዋን ሄደ አያት ከዛም ኮሊደሩ ጥግ ባለ አግዳሚ ወንበር ላይ ተኝቶ እንቅልፍ ጣለው የነቃው ዲና መጥታ ስትቀስቅስው ነው ማታ 2 ስአት ላይ በርግጎ ሲነሳ ዲና ፈገግ ብላ አይዞን አለችው ካጠገብ ተቀመጠች እና ዛሬ እዚህ ነው የማድርው ተረኛ ነሽ እንዴ አይ አይ እያየከኝ በልብስ ነኝ እኮ እና አላት እናማ በመጀመሪያ ዛሬ አምሮቦካል መቼም ለሄዋን ነው እንዲ መዋብክ ሁለተኛ ደሞ በጣም አዝነካል ከቅድሙ ምን ሆነክ ነው ሶስተኛ ደሞ ከሄዋን ጋር እንዴት እንደተዋወቃቹ ንገርኝ እሱም ቀጠለ በመጀመሪያ አመስግናለው ሁለተኛ የከፋኝ ደሞ ብሎ እንባውን አረገፍው ዲና ደነገጠች ምምምምም ምን ሆነክ ነው አለችው ሁለተኛው ደሞ እናትዬ የኔ ህይወት ቢደርስባት አደጋ ምክንያት ከአደጋው በኋላም ሆነ በፊት ያለውን ነገር አታስታውስም አለኝ ዶክተሩ ሶስተኛው ጥያቄሽ ምን ነበር አዎ ትዝ አለኝ ከሄዋኔ ጋር በደንብ የተዋወቅነው ዩንቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ያሉ ልጆች ከጊቢ ውጪ ድግስ ቢጤ አዘጋጅተው ነበር እና ጓደኛቼን እኔ እንደማልሄድ ነግሬያቸው ጊቢ ቀረው ግጥም መፃፍ በጣም እወድ ስለነበር ወደ ማታ 1 ስአት ላይ ከምወደው ዛፍ ስር ተቀምጬ . . . .ይቀጥላል ••●◉Join us share @chel1905 T.me/couple_goal2
نمایش همه...
❤️
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 3 . . . ጩኸቱን ሲጨርስ ረዥም ሳቅ ሳቀ። በረዥሙ ተንፍሶ ወደ ቀልቡ ተመለሰ ። ዲና አሁን ላይ ይህቺ ሴት ማን እንደሆነች ልትጠይቀው ወሰነች ። ጉሮሮዋን ከጠራረገች በኋላ" እእእእእ እስቲ ስለ ሄዋን ንገረኝ አዳም" አለችው " ምን ልንገርሽ" አላት "ማለቴ ያው እንዴት እንደተዋወቃችሁ... ፍቅር እንዴት እንደጀመራችሁ እና እንዴት እንደዚህ ልታፈቅራት እንደቻልክ" ዲና ይህንን ብላ ቁልቁል አዳምን አየችው ። ፊቱ በፈገግታ በርቷል ። ልክ እንደ ነፀብራቅ ፈክቷል ። ባለፈው ፈገግ ካለው ይልቅ ሲስቅ በጣም እንደሚያምር አወቀች ። " ኡፍፍፍፍ እሷን ያወቅኩበትን ቀን ላንዴም አልዘነጋውም ። ከ5 አመት በፊት የካምፓስ ተማሪ ነበርኩ ። 6 ጓደኞች ነበሩኝ ። ከእኔ ጋር 7 ማለት ነው ። የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርን ። ከእነሱ በጣም የተለየ ፀባይ ነበረኝ ። ማለቴ እነሱ ሴት ማተራመስ እና መላከፍ በጣም ይወዳሉ ። ወሬያቸው ሁሉ ሰለ ሴት ነው ። እኔ ደግሞ ሀሳቤ ሁሉ መፅሀፎቼ ላይ ነው ። ፀጥ ያለ ቦታ ይመቸኛል ። ግን ጓደኞቼ አብሬያቸው እንድሆን ሲጠይቁኝ እንቢ ማለት አልችልም ። ሄዋኔን ያየኋት የሁለተኛ አመት ትምህርት ለመጀመር ተማሪው ከቤቱ ወደግቢ የሚጎርፍበት ሰአት ላይ ነበር ። ጓደኞቼ እንደለመዱት ለመላከፍ ወደሚመቻቸው ቦታ ሄደው ተደላድለው ተቀምጠው ነበር ። ያኔ እኔም ነበርኩኝ ። አንድ መካከለኛ ቁመት ያላት በጣም ቀይ እና ፀጉሯ በጀርባዋ የወርደ ግን በቅጡ ያልተያዘ ፀጉር ያላት...የወንድ የሚመስል አለባበስ ለብሳ በአጠገባችን ልታልፍ ስትል አንዱ ጓደኛዬ "ኧረ ይቺ ልጅ ፍሬሽ ናት መስለኝ አይቼያት አላዉቅም ። እስቲ ላስደስታት" አለና ድምፁን ሰልከክ አርጎ "እሙዬ ሻንጣውን ላግዝሽ " አላት እሷም ፈገግ ብላ "አመሰግናለው ወንድሜ አጋዥ አያስፍልግም" አለችው ቀጠል አድርጎ "ወይም አንቺን ተሽክሜሽ ልግባ " አላት... ጥቂት ሄድ ካለች በኋላ ፊቷን ፍክት አድርጋ ፈገግ እያለች "አንዴ እስኪ ና " አለችው... ደስ እያለዉ ወደ እሷ ቀረበ ። ሌላኛው ጓደኛችን "ኧረ ንቀት እራስሽ አትመጪም እንዴ..ምንሼ ነው" አላት... እሷም ዝም ብላ ያኛውን ጎደኛችንን በአይኖቾ አታላ አጠገቧ አመጣችው ። ከዛም በጥፊ ጭንቅላቱን አዞረችበት ። ሁሉም ደነገጡ ። እኔ እራሴም ደነገጥኩ ። 'ትስማኛለህ ' አለች እየጮኸች... " አንተ ከንቱ.. የማትርባ አፍክህ በከፈትክ ቁጥር ባዶነትህን ነው የሚያሳየው ። ዳግም እንዲህ ብታደርግ አንላቀቅም ።" ብላው ሄደች... ስታወራ...ጩከቷ አለም ላይ ያለ ሰዉ ድምፅ አዋጥቶ ለእሷ የተሰጣት ይመስላል ። በጣም በጩከት ነው የምታወራው ። ልጅቷ ከሄደች በኋላ ጓደኛችን በድንጋጤ ደርቆ ጉንጩን እየሸፈነ መጣ ። ምን ብለሃት ነው ስንለው...' ለምንድነው ወንድሜ የምትይኝ ..ይልቅ ማታ አልጋ ይዘን ለምን አናወራም ' ነበር ያልኳት አለ ። ሁላችንም በጣም ሳቅንበት ። ይቺ ሴት ሄዋን ነበረች ። ሁሉም ሴት ሲለከፉ እያፈሩ እና እየተሽኮርመሙ ሲሄዱ እራስዋን ያላስበገርችው ሄዋን ናት ። ሄዋን ልጁን መታው ከመሄዷ በፊት አንድ ቃል ተናግራለች ። "እኔ ሄዋን ነኝ እሺ የምሽኮርመምልህ ወይም የምፈራህ እንዳይመስልህ ። በጭራሽ እንዳትሳሳት.. ቀና ብለህ እንዳታየኝ ። ተግባባን !! ብላ አስጠንቅቃዉ ነበር ። በጣም ገርመችኝ... ወኔዋ በእራስ መተማመኗ እና ሁሉ ነገሯ አስገረመኝ ። ለፍቅር ያጨኋት ማለቴ በአይነ ህሊናዬ የሳልኳት አይነት ሰው ሳትሆን ግን ልቤን እና ሁሉ ነገሬን በአንድ ጊዜ ተቆጣጠረችው ።" አለ አዳም ። ፈገግ እያለ ነበር የሚያወራው ። " በቃ የቀረውን ደግሞ ሌላ ጊዜ" አላት የእጅ ሰአቱን እየተመለከተ ። " ኧር አለስማህም... ልቤን እንደዚህ አንጠልጥለኸዉ ወልፈት የለም ። በቃ እንደውም ዛሬ ሆስፒታል ነው የማድርው።" አለችው ። አዳም በአግራሞት እያያት "ዛሬ እረፍት አደለሽ እንዴ " አላት "አዎ ነኝ ግን የእረፍት ጊዜዬን ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ በመስማት ላሳልፍው ወስኛለሁ" አለችው ። የመድሀኒት መደብሩ ጋር ደርሱና መድሀኒቱን ገዙ ። መድሀኒቱ በጣም ውድ ነው ። ቢሆንም ግን የገንዘብ ችግር የለበትም ። ገዛና ወደ ሀኪም ቤቱ ተመለሱ ። ከመድሀኒት ቤቱ እስከ ሆስፒታሉ ምንም ነገር አላወሩም ነበር ። ሆስፒታሉ በር ላይ ሲደርሱ ዲና "በቃ አሁን ቤቴ ሄጄ እርፍት ላድርግ..አመሻሹ ላይ መጥቼ የጀመርክልኝን ትጨርስዋለህ። እንገናኛለን" ብላዉ ተሰናበተችዉ ። ባይኑ ሽኛትና ሄዋን ወደተኛችበት ክፍል አመራ ። ሄዋን አሁንም ኮማ ውስጥ ናት ። ግን ደግሞ ልትነቃ ትንሽ ለሊት ማታ እና ቀን ወይም ሰአት ነው የቀረው ። "ሄዋኔ " አለ በለሆሳስ ደምፅ ... "አንቺን አለማፍቀር ይቻላል...? እእ አንቺን አለመውደድስ ...? አይ በጭራሽ አይቻልም ። አዎ አይቻልም.. የኔ አስተዋይ .. የእኔ ጩኸታም.. የኔ አኩራፊ ንቂ ...ንቂልኝ ። ሄዋኔ ሄዋኔ አንቺ ነሽ ሰላሜ እናቴ ልበልሽ በቃ ነሽ አለሜ የፍቅርሽ ወላፈን ከአድማስ ባሻገር ልቤን አሳመመሙ ለኔ ሳይናገር ። ኮማ ውስጥ ያለሽው ፍቅሬ ተይ ንቂልኝ ጨርቄን ጥዬ ሳላብድ ባክሽ ድርሽልኝ ። እያለ አጠር ያለችውን የግሉን ግጥም በውስጡ አዥጎረጎርው ። በተመስጦ እሷን በማየት ግጥሙን ቀጠለዉ... ትነቂያለሽ ብዬ በተስፋ ልጠብቅ አትነቂም ብሎ ውስጤ እንዳይጨነቅ። እያለ በሀዘን ፊት ያያት ጀመር ። "ትነቂያለሽ ውዴ" አለ በለሆሳስ.... እዚህ ሀስብ ውስጥ ሆኖ ጠና ያለው ዶክተር ትካሻውን ለመጣራት እና ለማፅናናት ያክል መታ አደረገው። "ከአንድ ሰአት በኋላ ቢሮ ና" ብለውት ሄዱ... "ምን ሊሉኝ ነው...? አትተርፍም ትሞታለች ሊሉኝ ነው...? ለምን እንዲህ አዘኑ..? እእእ " ይቀጥላል... ✎ ክፍል 4 ከ 20 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 🌹 @couple_goal2 🌹 @chel1905 T.me/couple_goal2
نمایش همه...
❤️ 1
.😘 አለሜ ነሽ 😘 ❤️‍🔥 ክፍል 2 . . የዚህችን ሴት ምንነት ለመግለፅ ምን ይሆን የከበደው..? የሚለውን ጥያቄ ሲጮኽ የሰሙት ሰዎች በውስጣቸው ያለ ማቋረጥ እያሰቡት ነው ። አለሙ ማን ናት ህይወቱስ ማን ናት? ድቅደቁ ምሽት ተገፎ ወደ መነጋጋቱ ወስዶታል ። ብርሀን እየመጣ ነው ። ጨለማው ለውጦ ፀሀይ ቦታዉን ተረክባለች። ኮማ ውስጥ ያለችው ሴት ቀኑን እና ለሊቱን ያለ ልዩነት በስቃይ ውስጥ ነች። ማታ ሆስፒታሉን ሲቀውጠው ያደረው ያ ለግላጋ ስውም በእንባ እና በእንቅልፍ አብጦ አይኑን እያሻሽ ተነስቶ ኮማ ውስጥ ወዳለችው ሴት አመራ ። በጉጉት እና በናፍቆት ሲከንፍ ሄዶ አያት ። ምንም የተነቃነቀም ሆነ የተለወጠ ነገር የለም ። ዛሬ ከትላንት ለእሱ የተለየው መሽቶ መንጋቱ ብቻም አይደለም። የሚሳሳላት ሴት በህይወት መኖሯም ተመስገን አስኝቶታል ። ሰላም ስላሳደራት...ሰላም እንዲያውላት እና እንዲያኖራት ወደ ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዉን ሊያመስገን ፤ ሊማፀን ሄደ ። በሃሳብ ሩቅ ስለነጎደ ረዥሙ መንገድ አልታወቀውም ። በስተመጨርሻ እራሱን ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ላይ አገኘዉ። ሰማይ እና ምድርን..ሙት እና በህይወት ያሉትን ነገሮችን በሙሉ የማንቀሳቀስ እና የማዘዝ መብት ላለው ፈጣሪ ስላምታውን አቀርበ ። ወደ ግቢው ዘልቆ ገባና አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ። ግማሹ ቁሞ ሌላው ተቀምጦ ከፊሉ ደግሞ ተንበርክኮ ምልጃውን ያደርሳል ። በጉልበቱ ተንበርክኮ አለሙ የሆነችውን.. እስትንፋሱ የሆነችውን ሴት እንዳይወስድበት ተማፀነው ። ቀጥሎ ዝም ብሎ ቆየ ። ከራሱ ጋርም እንዲ ሲል ሙግት ገጠመ "ቆይ ፈጣሪ ቂም ያዉቃል እንዴ..? ለምንድነው አዳምና ሄዋንን ይቅር ያላላቸው። አይ..አይ ለነገሩ አታድርጉ የተባለውን ነገር ስላደረጉ ነው ። ቆይ ታድያ ፈጣሪ ሀጢያት እንደሚሰሩ ካወቀ ለምን አላስቆማቸውም..? ለነገሩ ማሰቢያ አእምሮ ሰጥቷቸዋል.. ማስብ የእነሱ ድርሻ ነው ። ልንሞት ነገርስ ለምን ተፈጠርን..? ምን ሆኜ ነው ...ፈጣሪ የፈጠርንኮ ለመግደል ብሎ አይደለም ። እሱማ ያረገው ነገር ቢኖር ነፃነትን ከእውቀት ጋር መስጠት ነው ። ፈጣሪን ከምወቅስ አታድርጉ ተብሎ ላረግነው እኛ ለምን ክስ አላቀርብም..? ምን እየሆንኩኝ ነዉ!! ፈጣሪ ፍቅር ነው ። ጥላቻን እንድናውቅ ያረገን የፍቅርን ሀያልነት ሊያሳየን ስለፈለገ ነው ። አዳም ብቻውን ቆዝሞ ከራሱ ጋር ያወጋል ። ስለማንም ግድ አልሰጠውም ። የእሱ ሄዋን አሁን አጠገቡ የለችም ። ወደ ራሱ ተመለሰ በሀዘኑ ምክንያት የተንጨበረረ ፀጉሩን እና ፂሙን በተራ እየዳበሰ ተንጠራርቶ ተነሳ ። ወደ ሀኪም ቤት ተመለሰ። በጣም ርቦታል መብላት ፍልጓል። ያለ እሷ መብላቱን ሊለምደው አልቻለም ። ከትላንት ጀምሮ ምግብ በአፉ አልዞረም ። ለመብላት በማስብ ወደ ሀኪም ቤቱ ካፌ ሄደና ተቀመጠ ። ቀጫጫ ረዘም ያለ አስተናጋጅ ቀልጠፍ ብሎ " ምን ይምጣ ወንድሜ " አለው "እእ ቀለል ያለ ቁርስ ባንተ ምርጫ ይሁንልኝ" አለው ። አስተናጋጁም ሲከንፍ ሄዶ ምርጥ ዱለት ከውሀ ጋር አመጣለትና መልካም ምግብ ብሎት ሄደ ። እጁን ታጥቦ ዱለቱን በፍጥነት በልቶ ጨርሰ ። የራሱን ሆድም በጣም ታዘበው ። "ለካስ ስጋና ነብስ የተለያዩ ናቸው ።" አለ በውስጡ "እሷ ተኝታ እኔ ግን በላሁ" አለ ምግብ መቅመሱ በትንሹ ያረጋጋው ይመስላል ። ከበላ በኋላ አረፍ ማለት ቢፈልግም አልቻለም ። ልቡ እና ሀሳቡ ሄዋኑ ጋር ነው ። እርሷ ጋር ሲደርስ ብቻዋን አልነበርችም ። አጭሯ ነርስም ነበረች ። በውስጡ "ይህቺ ነርስ ቀንና ለሊት ነው እንዴ የምትሰራው" ሲል እያሰበ ተጠጋት ። በስስ ፈገግታ ስላም ተባባሉ። ነርሷ አተኩራ እያየችው " ትላንት ግን" አለችና ፀጥ አለች "ትላንት ምን..?" አላት "አይይይ በጣም ጮኸክ በስላም ነው..?" አለችው የትላንቱ ትዕይንት በአይነ ህሊናዋ እየታያት ። "ልብሽን አሞሽ ወይም ልቡን የታመመ ሰው አጋጥሞሽ ያዉቃል ..?" አላት " ዉይ አዎ !! ይገርምሃል ጎረቤቴ ልቡን አሞት ነበር ። ማለቴ የልብ ድካም አለበትና በቃ ሊሞት ለጥቂት ነው የተረፈው " አለችው ። አዳም ትንሽ ሊስቅም ቃጣው ። ሌላ ጊዜ ቢሆን በደንብ ይስቅ ነበር ። አሁን ግን የሚስቅበት አንደበት የለውም ። ፈገግ ብሎ እያያት " እሱኛውን የልብ ህመም አደለም ያልኩሽ ። በፍቅር ምክንያት ሰለሚታመም ልብ ነው የጠየቅኩሽ ። ልክ እንደኔ በፍቅር መስቃየት የሚወዱትን.. የሚያፈቅሩትን ስው በቅርብ በአይን እያዩት በእጅ የማይነኩትን ነዉ የምልሽ..የሚወዱትን ሰው ትንፋሽ ካጠገቡ ሳትርቂም እስትንፋሱን አለመስማት... ድምፁን መራብ በጣም ያማል ። ቅስምን ይስብራል ። ይህንን ህመም . .. ይህንን ስቃይ ነው ያልኩሽ" አላት አሳዘናት... ያላትን ነገር ተረደተዋለች። እጇን ወደእሱ ሽቅብ እየዘረጋች "እንተዋወቅ ዲና እባላለው... ቅር ካላለህ የሁለታችሁንም ስም ብትነግርኝ " አለችው ። ዳግመኛ ስለ ስሟ ስጠይቀው እንደ ማታው እንዳይጮኽ በመፍራት... የጨበጣትን እጁን ከእጇ አላቀቀና " እኔ አዳም እባላለሁ። እሷ ደግሞ" አለ አልጋዉ ላይ ዟ ብላ ወደተኛችው ልጅ እየጠቆመ "ሄዋን ትባላለች" ብሎ ሌላ ወሬ ሊያወራ ሲል ተናዳ "አትቀልድ ባክህ ትክክለኛ ስማችሁን ንገረኝ" አለችው ... "ማለት?" አላት "ማለትማ ስማችሁን በስርአት ንገረኝ" " ነገርኩሽኮ" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ አንድ ጠና ያለ ዶክተር ሄዋን ክፍል ገብቶ ካያት በኋላ ወደ አዳም ዞረና "አቶ አዳም ለወይዘሪት ሄዋን መድሃኒት ያስፍልጋታል ። ነገ ማታ ትነቃለች የሚል ግምት አለኝ "ብሎት ሄደ ... ነርስ ዲናም እንዳልቀለደ ገባት ። አዳም እና ሄዋን መገጣጠም ነው ወይስ ለእራሳቸው አውጥተውት ነው..? ብላ ተገረመች ። አዳም በደስታ ጮቤ ረገጠ ። መቼም የሚያየው ያልመስለውን አይን ሊያይ ቀጠሮ ተስጥቶታል ። ሮጥ ሮጥ እያለ መራመድ ጀመረ... ዲና "የት ልትሄድ ነው አለችው" "መድሃኒቱን ልገዛ ነዋ " ፊቱ ላይ ደስታ ይነበባል ። "አብርን እንሂድ " አለችው ፈገግ ብላ ... "ስራሽስ? " "ፈረቃዬን ጨርሻለው። ከመውጣቴ በፊት ላያችሁ ነበር የመጣሁት ። "እሺ እንሂድ" አላት አዳም እየተጣደፈ እስታፍ ልብሷን ቀይራ መጥታ መንገድ ጀመሩ ። መንገድ ላይ "አለሜ ልትነቃ ነው። አዎ ልትነቃ ነው ። እናትዬ ልትነቃ ነው " አለ ጮኽ ብሎ... ዲና ግራ ገባት ። እንደመሳቅም እየቃጣት " አረ ባክህ ዝም በል..ቆይ ይህቺ ሴት ምን አይነት እድለኛ ብትሆን ነው እንዲህ ያለ አፍቃሪ የሰጣት። ... አይ ሄዋን " አለች በውስጧ ስለሁለቱ ታሪክ ለመስማት እየጓጓች.... ይቀጥላል... ✎ ክፍል 3 ከ 20 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ​ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share 🌹 @chel1905 🌹 🌹 @couple_goal2 𓤄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌
نمایش همه...
❤️
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.