cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አስገራሚ ታሪኮች👌👌👌👌

በዚህ ቻናል ፦ ♦ አስገራሚ ታሪኮች ♦ ወጎች ♦ ግጥሞች ♦አነቃቂ መልዕክቶች እና ቪዲዮዎች Join us .............@asegeramiTarikoch.............. ለአስተያየት : @bekibinibot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
611
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" (ኢሳይያስ 9:6) ________________________ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! በዓሉም የሰላም እና የደስታ በዓል ይሁንላቹ እንመኛለን! 🔆 መልካም የገና በዓል 🔆
نمایش همه...
👍
❤️
ስለ ቡሔ(ቡሄ!) ሀሙስ 12/12/14 “መጣና ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ ክፈትልኝ በሩን የጌታዬን ሆያ-ሆዬ-ሆ…” ቡሄ! ወይንም ደብረ ታቦር በመላው ሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ (ዋና) በዓላት አንዱ ነው። የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው። የማቴዎስ ወንገል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር ፩ እስከ ፭ ” ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።” ዓቢይ መሠረቱ ይሄ ሲሆን፣ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት ‘ቡሄ’ የሚለውን ስያሜ አገኘች። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታዲያ ያንን ማስታወሻ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ መልካም የቡሄ በዓል ይሁንላችሁ!!!!
نمایش همه...
ትንሽ ዘና በሉ ሰዎች 😂
نمایش همه...
card ተሳስቼ ልኬ ነው.mp33.43 KB
ራስን መገምገም! ፈጣሪ በህይወት ዘመናችን ሙሉ ልንጠቀመበት ከምንችል በላይ ድንቅ አቅምና ስጦታ ሰጥቶናል፣ ይህ የፈጣሪ ስጦታ ለኛ ነው፡፡ ፈጣሪ ልንሰጠውም ባንችል አንዱ ልናመሰግንበት ከምንችልበት መንገድ የተሰጠን አቅምና ችሎታ በህይወት ዘመናችን እስከምንችለው ድረስ መጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ የተሰጠን ድንቅ አቅምና ችሎታ እንዴት እየተጠቀምንበት እንዳለን ራሳችን እንፈትሽ፡፡ ልክ እንደኛ የሆኑ የሰው ልጆች በዉስጣችን ያለ ድንቅ አቅም በመጠቀም ብዙ ተዓምር ሰርተዋል፡፡ እኛስ ይህ እፁብ ድንቅ የሆነ አቅማችን በመጠቀም ምን እየፈጠርን፣ ምን እየሰራንና ምን ዓይነት ህይወት እየኖርን ነው የምንገኘው? አሁን የምንፈትሸው ድንቅ አቅማችንን አይደለም ምክንያቱም በአቅምና በአፈጣጠራችን ደረጃ ሁላችንም የሰው ልጆች ድንቅ ነን፡፡ አሁን የምንፍተሸው በህይወታችን በምን ያክል ፈተና እና ችግር እየተፈተንን እንዳለንም አይደለም። ምክንያቱም ድንቅ ሰዎች በየትኛውም አይነት ፈተና ወይም መከራ ውስጥ ቢገቡም ሁሌ የሚያሸኑፈበት መንገድ በመፈለግና በማሸነፍ ነው የሚታወቁት፡፡ ድንቅ የሆነ አቅማችንን በመጠቀም ምን እየሰራን፣ ምን እየፈጠርን፣ ምን እያሻሻልን እንገኛለን? አሁን የምንኖረዉ ያለን ህይወት፤ የምናገኘዉ ገቢ፤ የምናደረገው እንቅስቃሴ፤ የምንፈጥረው መፍትሄ፤ በህይወታችን የምናፈራው ያለን ውጤት ስንፈትሽ ድንቅ አቅማችንን የምንጠቀመበት መንገድ ድንቅ ነዉ ወይስ ተራ? እባክዎ አንዴ ረጋ ብለዉ ድንቅ አቅሞትን የሚጠቀሙበት ደረጃ የት እንደሆነ እራሷን ይፈትሹ፡፡ (ከዳዊት ድሪምስ "ትልቅ ህልም አለኝ" መጽሐፍ የተወሰደ
نمایش همه...
ጆርዳን የተባለው ደራሲና የሥነ ልቦና ባለሙያ የሰው ልጆች ከተዛባ አመለካከት ወደ ቅን አሳቢነት የሚያሸጋግሩና መልካምነትን የሚያጎናፅፉ #ዘጠኝ አስተሳሰቦች ብሎ ያስቀመጣቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል። 1. ለሰዎች መልካም ሁን፦ መልካምነት ለተረጋጋ ህይወት መጀመሪያ ነው። መልካምነት ካንተ ጋር ከሆነ ሁሉም ነገር አብሮህ ይኖራል። ለሰዎች መልካም ነገር ባደረክ ቁጥር የተረጋጋ ህይወትን ለመምራት የሚያስችልህን መንገድ እየጠረክ ትሄዳለህ። የመልካምነትን መንገድ መከተል የጀመረ ሰው ለተሳሳቱና ላልጠሩ አመለካከቶች የሚሆን ቦታ ስለማይኖረው፤ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በተለየ አቅጣጫ እየተመለከተ ለመፍታት ይሞክራል። 2.ማገዝ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተወዳጅ፦ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ብቻ የሚፈልጉት የስኬት ጫፍ ላይ ለመድረስ ሲታገሉ እንመለከታለን። በተለይ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን እገዛ መጠየቅ የውድቀት መጀመሪያ መስሎ ይታያቸዋል። በዙሪያ የሚያግዙ ሰዎች መኖር ጥንካሬና ብርታትን ይሰጣል። ስለዚህ የሚያግዝህና ሃሳብህን የምታጋራው አስተዋይ ወዳጅ ይኑሩህ። 3. ኃላፊነቶችን ለመወጣት ዝግጁ ሁን፦ ኃላፊነትን ለመቀበል ዝግጁ መሆን የተሳሳተ አመለካከትን አሽቀንጥሮ ለመጣልና ቀና አመለካከት ለማካበት ከሚረዱ ነገሮች አንዱ ነው። ኃላፊነትን በተሸከምክ ቁጥር ስለ ሌሎች ሰዎች ማሰብና ራስህን በሌሎች ቦታ አስቀምጦ ፍርድ የመስጠት ልምድ ማግኘት ይቻላል። ለሰዎች ማሰብ መቻል ደግሞ ለቀና አመለካከት እንደ ማሳያነት ይቀርባል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት በነገሮች ላይ የነበረህን የተሳሳተ ግንዛቤ እያጠራልህ ይሄዳል። ቀስ በቀስ አመለካከትህ ተቀይሮ ሁኔታዎችን የመለወጥ አቅም እንዳለህ ማመን ትጀምራለህ። 4. ይቅር ባይ ሁን፦ በይቅርታ ማመን መቻል ሌላኛው ቀና አመለካከት ያለው ሰው መገለጫ ባህሪ ነው። አንድን ሰው በሆነ አጋጣሚ ቢያስቀይምህና ከቀናት በኋላ የሠራው ሥራ ትክክል እንዳልነበረ ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅህ ይቅርታህን አትንፈገው። ቀና አመለካከት ያለው ሰው ይቅርታ ለጠየቁት ሰዎች ምህረት ከማድረግ ባለፈ በጥፋቱ ይቅርታ የመጠየቅ ልምድ አለው። 5. ሙሉነት ይሰማህ፦ የሙሉነት ስሜት በሥነ ልቦና ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በህይወትህ ብዙ ነገሮች ሊያጋጥሙህና እንዳልነበሩ ሆነው ልታገኛቸው ትችላለህ። ለራስህ ግን ሁሉም ነገር ሙሉ እንደሆነና ዘወትር መልካም ነገር ላይ እንዳለህ አስብ። አብዛኛውን ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በራሳቸው ሙሉነት አይሰ ማቸውም። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ግን የተዘበራረቁ የህይወት መስመሮች ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እንዳልተዘበራረቁ አድርገው ማሰብ ይችላሉ። የጎደለ ነገር ሁሉ ባዶ አይሆንምና ሁል ጊዜ በራስህ ሙሉነት ይሰማህ። ሰዎች ዛሬ የምታሳልፈው ቀን ደስ የማይል እንደሆነ አስረግጠው ቢነግሩህ እንኳን ፍፁም ደስተኛ ሆነህ ማሳለፍ እንደምትችል ውስጥህን አሳምነው። 6. ከመጠን ያለፈ አታስብ፦ ሁሉም ነገር በተፈቀደለት ጊዜ መሆኑ አይቀሬ ነው። አእምሮህ ከሚችለው በላይ በሃሳቦች መወጠር ቀና አመለካከት እንዳይኖር ያደርጋል። ስለአንድ ነገር አብዝተህ የምትጨነቅ ከሆነ ትኩረትህን ሁሉ ጉዳዩ ላይ ይሆንና በዙሪያህ ስላሉ ሰዎች ማሰብ ታቆማለህ። ያኔ ከሰዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ትገባለህ። 7. ደስታ አይራቅህ፦ አብዛኛውን ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ፍፁም ደስታ የራቃቸው ናቸው። ነገሮች ላይ አብዝተው ስለሚጨነቁ፣ በይቅርታ ስለማያምኑና ሙሉነት ስለማይሰማቸው ለራሳቸው ደስታን መፍጠር ይሳናቸዋል። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ግን ሁል ጊዜ ሙሉ እንደሆኑ ስለሚሰማቸውና አርቀው ስለሚያስቡ ደስታቸው በእጃቸው ነው። 8. ለዋዛ ፈዛዛ ነገሮች ቦታ አለመስጠት፦ ለሚረባውም ለማይረባውም ነገር ቦታ መስጠት የተዛባ አመለካከት እንዲኖር ከማድረጉም በላይ መንፈስን ላላስፈላጊ ጭንቀት ይዳርጋል። በመሆኑም ትኩረት መስጠት ለሚያስፈልገው ጉዳይ ብቻ ትኩረት በመስጠት የቀና አመለካከት ጎዳናን ማስፋት ይቻላል። 9. ግርማ ሞገስ መላበስ፦ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትንና ተወዳጅነትን ለማግኘት የሰዎችን ቀልብ መሳብ መቻል ተገቢ ነው። ማድረግ የምትፈልጋቸው ድርጊቶች ሁሉ ግርማ ሞገስን የተላበሱ ቢሆኑ መልካም ነው።  ጸሐፊ መሰረት ተስፋዬ (አዲስ ዘመን ጋዜጣ መዝናኛ አምድ)
نمایش همه...
👉አቅምህን ምታውቀው ከአቅመኞች ተርታ ስትሰለፍ ነው! 👉ታላቅነትህን ምትረዳው ከታላቅ ነገር ጋር ስትጋፈጥ ነው! ጠንካራ የዱር አውሬ በሐሪው እንደ ቤት እንስሳ ሲመስል አይተን እናቅ ይሆናል፤ ያም የሆነው እንደቤት እንስሳ አድርገው ስላሳደጉትና እሱም የፍጥረቱን በሐሪ ስለረሳ ነው። አንተነትኽ ልክ በሚሆንበትና ካሸናፊዎች ተርታ ካልተገኘኽ አቅሙን እንዳላወቀው ጠንካራ ያራዊት ፍጥረት ውሎሕ እና ኑሮህ እንዳይመስለው ስጋ!!!
نمایش همه...
ወዳጄ ሆይ:- * በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። * ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። * የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። * ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ። * የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
نمایش همه...
የተገለጠ ዓይን ሁሉ አያይም የተዘጋ ዓይን ሁሉም አይተኛም።
نمایش همه...
✝ ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
نمایش همه...
crazy kids😂😂😂😁😁😁😁
نمایش همه...
5.39 KB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.