fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ኑ_በእግዚአብሔር_ደስ_ይበለን,,,MA.3gp2.35 MB

ኢትዮጵያ_ሰላምሽ_ይብዛ_ተጠለይ_በእግዚአብሔር_ታዛ.3gp2.61 MB

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻የሱፍ አበባ የአምላክ እናት🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 👉ጠቢቡ ሰሎሞን በማሕ ፪፥፩‐፪ ላይ በመንፈሰ እግዚአብሔር በመቃኘት የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕና በሱፍ አበባ መስሎ ሲያስተምር፡- “አነ ጽጌ ገዳም ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቈላት፤ ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ከማሁ አንቲኒ እንተ ኀቤየ በማእከለ አዋልድ” (እኔ የዱር ጽጌረዳ፤ የቈላም የሱፍ አበባ ነኝ፤ በእሾኽ መኻከል እንዳለ የሱፍ አበባ እንዲኹ ወዳጄ በቆነዣዥት መኻከል ነሽ) በማለት የተናገረውን ምሳሌያዊ ኀይለ ቃል ሊቁ በድርሰቱ ላይ፡- “ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ከማሃ አንቲኒ ኦ ወላዲተ አምላክ” (በእሾኽ መኻከል እንዳለ የሱፍ አበባ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ አንቺም እንደ ርሷ ነሽ) ሲል ያቺ ሰሎሞን የተናገረላት የሱፍ አበባ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን ተርጒሞታል፡፡ 👉ይኸውም ይቺ የሱፍ አበባ እሾኽ ዙሪያዋን ከቧት ሳለ በሾኽ መኻከል እንደምታብብ እንደምታፈራ ቅድስት ድንግል ማርያምም ኀጢአት እንደ እሾኽ በከበባቸው በአይሁድ መኻከል ሳለች ብቻዋን ከኀልዮ (ከማሰብ)፣ ከነቢብ (ከመናገር)፣ ከገቢር (ከመሥራት) ኀጢአት ተጠብቃ በሃይማኖት፣ በምግባር፣ በንጽሕና፣ በቅድስና፣ በድንግልና ጸንታ የሕይወት ፍሬ ክርስቶስን አብባ አፍርታ ተገኝታለችና ነው፡፡ 👉አባ ጊዮርጊስም ይኽነን የሰሎሞንን ቃል በአርጋኖን መጽሐፉ ሲተረጒመው፡- “ጽጌ ደንጐላት እንከ እሰምየኪ እስመ ጽጌ ደንጐላት ዕዉድ በአሥዋክ... ” (በሱፍ ዕንጨት እመስልሻለኊ፤ የሱፍ አበባ በእሾኽ የተከበበ ነውና፤ አንቺም ከዳዊት ግንድ (ባሕርይ) የተገኘች የንጽሕት አበባ ቅንጣት ኾነሽ ሳለ፤ በጒስቁልናቸው የሚመኩ አንገታቸውን የሚያደነድኑ በዐይኖቻቸው የሚጠቃቀሱ በእግሮቻቸው የሚያሸበሽቡ የልብሶቻቸውን ዘርፎች የሚጐትቱ የሚዘፍኑትን የቆነዣዥት አለቆች የሚኾኑ የጽዮንን ልጆች እግዚአብሔር ያዋርዳቸዋል ያጐሳቁላቸዋል ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት እንደተናገረባቸው (ኢሳ ፫፥፲፮‐፲፯)፤ አንቺም አንገተ ደንዳኖች በሚኾኑ በዕብራውያን ቆነዣዥት መኻከል እንደተቀመጥሽ) በማለት ግዙፉነ ክሣድ በኾኑ ኀጢአት እንደ እሾኽ በከበባቸው በአይሁድ ልጆች መኻከል ሳለች ርሷ ብቻ በንጽሕና በቅድስና ጸንታ የመገኘቷን ምስጢር ከሰሎሞንና ከኢሳይያስ ቃል በመጥቀስ ተንትኖታል፡፡ 👉ሊቁ ቅዱስ አባ ሕርያቆስም ከዚኽ ምስጢር በመነሣት በቅዳሴው ላይ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልህቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ) በማለት ግዙፋነ ክሣድ በኾኑ በዘፈን፣ በቧልት፣ በጨዋታ፣ ኀጢአትን በመሥራት ይኖሩ ከነበሩ ከዕብራውያት ሴቶች ልጆች ተለይታ በቤተ መቅደስ ማደጓን አስተምሯል፡፡ 👉አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ይኽነን የሰሎሞንን ቃል ሲያብራሩ:- “ጽጌ ደንጐላ ዘቈላ ወአኮ ዘደደክ ዘጸገይኪ ጽጌ በማእከለ አይሁድ አሥዋክ ተአምረ ድኂን ማርያም ዘልማድኪ ምሂክ መሀክኒ ለምእመንኪ እምጻዕረ ኩነኔ ድሩክ ተአምኖትየ ኢይኩን በበክ” (በእሾኾች አይሁድ መኻከል የደጋ ያይደለ የቈላ የሱፍ አበባን ያበብሽና ልማድሽ መራራት የኾነ የመዳን ምልክት ማርያም፤ ብርቱ ከኾነ ከጭንቅ የቅጣት ፍርድ ታማኝሽን አድኚኝ፤ በአንቺ ምልጃ መታመኔ ከንቱ ኾኖ እንዳይቀር) በማለት በሱፍ አበባ መመሰሏን አጒልተው ተርጒመዋል፡፡ [🌻የሱፍ አበባ የተባልሽ የአምላኬ የክርስቶስ እናት ሆይ ከማያልቀው በረከትሽ ጥቂቱን በእኔ ላይ አሳድሪ አሜን✞✞✞🌻] ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ 🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share ❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @EOTC2921 👈 👉 @EOTC2921 👈 👉 @EOTC2921 👈 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

አለ ና ሚካኤል.m4a3.19 MB

ኦ ሚካኤል.m4a1.12 MB

ሚካኤል.m4a1.11 MB

ንዓ ንዓ ሚካኤል.m4a1.05 MB

ሚካኤል ነው የደረሰልኝ.m4a1.03 MB

ሚካኤል ወረደ.m4a10.20 KB

ቅዱስ ሚካኤል አጽናኝ.m4a8.66 KB

ሚካኤል ይላል አንደበቴ.m4a8.04 KB

ት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን✞✞✞ ✍✍ @EOTC2921 ✍✍

✞የቅዱስ ሚካኤል ክብር✞ ❖ መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ ስለኾነ የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡ ❖ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ❖ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡ ❖ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የክሕደት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡- “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል፡፡ ❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡- ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡- ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ” (የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡- የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡- ╬ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ” (የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት ለሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘይስእል በእንተ ምሕረት መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት” (የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡ ❖ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡ ❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ ╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ መልአኮሙ ሥዩሞሙ የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ” (ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል ❖ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር። ❖ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ” (መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው) ❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡- ╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ” (የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡- ╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ” (ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡ ❖ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ ሲኾን፤ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት ነቢዩ ዳንኤል፡- “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ…ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርኻለኊ በዚኽም ነገር ከአለቃችኊ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም… በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብኽ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” በማለት አማላጅነቱን መስክሮለታል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡ ❖ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ በመንክር ትሕትናከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ” (በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ) ╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ” (ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡ ╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ዳዊትን ከጎልያድ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፤ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት፣ ሶስናን ከረበናት፤ ቅድስት አፎምያን ከዲያብሎስ እጅ በምልጃው የታደገው፤ አስቀድሞም ዘንዶው ዲያብሎስን ተፋልሞ የጣለው ይኽ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል፤ ራሶቹ ሰባት ቀንዶቹ ዐሥር ከተባለው ዓለምን እየተበተባት ካለው ከዘንዶው ከ666 የሐሳዌ መሲሕ ክፉ አሠራር በቀንም በሌሊትም ተራድቶ ይጠብቀን እላለኊ (ራእ 12፡7፤ ራእ 13፡1-3)፡፡ ❖ ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎ

ይበራል_በክንፉ @EOTC2921.3gp2.39 MB

ዐይኑ_ዘርግብ @EOTC2921.3gp2.20 MB