fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
07 Track 7 - 07 Track 7.mp42.06 MB

06 track 6 - 06 track 6.mp43.24 MB

05 track 5 - 05 track 5.mp41.88 MB

04 Track 4 - 04 Track 4.mp42.34 MB

03 track 3 - 03 track 3_2.mp44.64 MB

02 Track 2 - 02 Track 2.mp42.04 MB

01 Track 1 - 01 Track 1.mp42.24 MB

#ልብ_ብለህ_አስተውል 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ዘፍጥ 3÷1-8 #አትቅና፦ እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላለህ፡፡ ዘፍጥ 4÷1- #አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷30-38 #ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷22-23 #በአባትህ አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ ዘፍጥ 9÷20 #እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡ ዘፀ 14÷28 #በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ፡፡ መጽ.አስቴ 7÷1 #ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ 2ነገ:19÷35 #ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡ መጽ.መሳ 16÷15 #አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡ 1ነገ 11÷1-8 #ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም #በአባትህ ላይ ትነሣለህ፡፡ 2ነገ ሳሙ 15÷13-17 #ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡ ማቴ:26÷14-16 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

#ልደተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ወሥርዐተ_ማኅሌት ፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 (ከሰንበት ትምህርት ቤታችን የሰሌዳ መጽሔት ተለቅሞ የተዘጋጀ፡፡) # ልደቱና_ብሥራቱ አባቱ ዘካርያስ (ከአብያ ምድብ የኾነ ሊቀ ካህን ነው)፤ እናቱ ዘካርያስ (ከአሮን ነገድ ነበረች)፤ ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፡፡» /ሉቃ.1÷5-7/፡፡ ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር በጸሎት ይጠይቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዐት / ዘጸ.3ዐ÷6-8/ ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት /ዕጣ ወጥቶለት/ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው / ከዕጣን መሥዋዕት ማቅረቢያው/ በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ በፍርሃት ተዋጠ፡፡ መልአኩ ግን «ዘካርያስ ሆይ አትፍራ ጸሎተህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ ብዙዎቹም በእርሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና» በማለት ብሥራት ከነገረው በኋላ ስለሚወለደው ልጅ አራት ነገሮችን ነገረው /ሉቃ.1÷13-17/፡፡ ሀ. የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፡ ለ. በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡ ሐ. ከእስራኤል ወገን ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል፤ መ. ለጌታ የሚገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኃይል በጌታ ፊት ይሔዳል፡፡ ዘካርያስ ይህንን ከመልአኩ በሰማበት ወቅት እርሱ ሸምግሎ፥ ሚስቱም አርጅታና የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ በዚያም ላይ መካን ነበረችና «ይህን በምን አውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች» በማለት ጥርጣሬውን በጥያቄ መልክ አቀረበ፡፡ በዚህን ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለው «እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬያለሁ፤ እነሆ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም» አለው፤ በዚህም መሠረት ዘካርያስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ መስማትም ሆነ መናገር አልቻለም ነበር፡፡ መልአኩ እንደነገረውም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ይህ ከሆነ ከስድስት ወር በኋላ የቅዱስ ዮሐንስን መፀነስ ለዮሐንስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችንን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት ኤልሳቤጥ መፀነስዋንም ነግሯት ነበር፡፡ «... እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወራት ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና» ብሏት ነበር፡፡ እመቤታችንም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ የነገራትን ለማየት በዚያው ሰሞን ፈጥና ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች፡፡ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ስታቀርብላት እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ተከሰተ፤ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማኅፀኗ ያለው ጽንስ ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- «አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሏልና፡፡... »፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን አስመልክቶ በድጓው ላይ ባስተማረው ትምህርት «አእሚሮ እምከርሠ እሙ ሰገደ ወልደ መካን ለወልደ ድንግል» «ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ አውቆ የመካኒቱ /የኤልሳቤጥ/ ልጅ ለድንግሊቱ /ለእመቤታችን/ ልጅ ሰገደ» ብሏል፡፡ # የቅዱስ_ዮሐንስ_ልደት (ሉቃ.1÷67-80) ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ በስምንተኛውም ቀን ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ እናቱ ግን ለዘካርያስ በቤተ መቅደስ «የሕፃኑ ስም ዮሐንስ ይባላል» ብሎ ያናገረ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት «ዮሐንስ መባል አለበት» አለች፡፡ ዘካርያስን ለልጁ ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ «ስሙ ዮሐንስ ነው» ብሎ ጻፈ ወዲያውም አንደበቱ ተፈታ፡፡ (ዮሐንስ ማለትም ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ማለት ነው፡፡)፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ይናገር ጀመር፡፡ በዚህም ምክንያት ጎረቤቶቹ ሁሉ በፍርሃት ተመሉ፡፡ ነገሩም በይሁዳ አውራጃ ሁሉ ተወራ፡፡ የሰሙትም ሁሉ «ይህ ሕፃን ምን ይሆን?» እያሉ በመገረም ጠየቁ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ስለ ሕፃኑ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትንቢት ተናገረ /ሉቃ.1÷67-79/ «አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና፤ እንደዚሁም የኃጢአታቸው ሥርየት የሆነውን የመዳን ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ» በማለት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆን ማለትም ከእርሱ ቀድሞ የሕዝቡ ልብ ጌታችንን እና ትምህርቱን እንዲቀበል የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያስተምር ተናገረ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መንገድ ጠራጊነት በቅዱስ ገብርኤልና በአባቱ በዘካርያስ ብቻ ሳይሆን ቀድሞም በሌሎች ነቢያት ትንቢት የተነገረለት ነበር፡- ነቢዩ ኢሳይያስ «የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል «የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ...» /ኢሳ.4ዐ ÷3/ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡

#የዮሐንስ_ወንጌል_ምዕራፍ_14 1፤ልባችኹ፡አይታወክ፤በእግዚአብሔር፡እመኑ፥በእኔም፡ደግሞ፡እመኑ። 2፤በአባቴ፡ቤት፡ብዙ፡መኖሪያ፡አለ፤እንዲህስ፡ባይኾን፡ባልዃችኹ፡ነበር፤ስፍራ፡አዘጋጅላችኹ፡ዘንድ፡ እኼዳለኹና፤ 3፤ኼጄም፡ስፍራ፡ባዘጋጅላችኹ፥እኔ፡ባለኹበት፡እናንተ፡ደግሞ፡እንድትኾኑ፡ኹለተኛ፡እመጣለኹ፡ወደ፡እኔም፡እወስዳችዃለኹ። 4፤ወደምኼድበትም፡ታውቃላችኹ፥ መንገዱንም፡ታውቃላችኹ። 5፤ቶማስም፦ጌታ፡ሆይ፥ወደምትኼድበት፡አናውቅም፤እንዴትስ፡መንገዱን፡እናውቃለን፧አለው። 6፤ኢየሱስም፦እኔ፡መንገድና፡እውነት፡ሕይወትም፡ነኝ፤በእኔ፡በቀር፡ወደ፡አብ፡የሚመጣ፡የለም። 7፤እኔንስ፡ብታውቁኝ፡አባቴን፡ደግሞ፡ባወቃችኹ፡ነበር።ካኹንም፡ዠምራችኹ፡ታውቁታላችኹ፡አይታችኹትማል፡አለው። 8፤ፊልጶስ፦ጌታ፡ሆይ፥አብን፡አሳየንና፡ይበቃናል፡አለው። 9፤ኢየሱስም፡አለው፦አንተ፡ፊልጶስ፥ይህን፡ያኽል፡ዘመን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ስኖር፡አታውቀኝምን፧እኔን፡ያየ፡አብን፡አይቷል፤ እንዴትስ፡አንተ፦አብን፡አሳየን፡ትላለኽ፧ 10፤እኔ፡በአብ፡እንዳለኹ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡አታምንምን፧እኔ፡የምነግራችኹን፡ቃል፡ከራሴ፡አልናገረውም፤ነገር፡ግን፥በእኔ፡የሚኖረው፡አብ፡ርሱ፡ሥራውን፡ይሠራል። 11፤እኔ፡በአብ፡እንዳለኹ፡አብም፡በእኔ፡እንዳለ፡እመኑኝ፤ባይኾንስ፡ስለ፡ራሱ፡ስለ፡ሥራው፡እመኑኝ። 12፤እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥በእኔ፡የሚያምን፡እኔ፡የማደርገውን፡ሥራ፡ርሱ፡ደግሞ፡ያደርጋል፤ከዚህም፡የሚበልጥ፡ያደርጋል፥ 13፤እኔ፡ወደ፡አብ፡እኼዳለኹና፤አብም፡ስለ፡ወልድ፡እንዲከበር፡በስሜ፡የምትለምኑትን፡ዅሉ፡አደርገዋለኹ። 14፤ማናቸውንም፡ነገር፡በስሜ፡ብትለምኑ፡እኔ፡አደርገዋለኹ። 15-16፤ብትወዱኝ፡ትእዛዜን፡ጠብቁ። እኔም፡አብን፡እለምናለኹ፡ለዘለዓለምም፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንዲኖር፡ሌላ፡አጽናኝ፡ይሰጣችዃል፤ 17፤ርሱም፡ዓለም፡የማያየውና፡የማያውቀው፡ስለ፡ኾነ፡ሊቀበለው፡የማይቻለው፡የእውነት፡መንፈስ፡ነው፤ነገር፡ግን፥ከእናንተ፡ዘንድ፡ስለሚኖር፡በውስጣችኹም፡ስለሚኾን፡እናንተ፡ታውቃላችኹ። 18፤ወላጆች፡እንደ፡ሌላቸው፡ልጆች፡አልተዋችኹም፤ወደ፡እናንተ፡እመጣለኹ። 19፤ገና፡ጥቂት፡ዘመን፡አለ፡ከዚህም፡በዃላ፡ዓለም፡አያየኝም፤እናንተ፡ግን፡ታዩኛላችኹ፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እናንተ፡ደግሞ፡ሕያዋን፡ትኾናላችኹ። 20፤እኔ፡በአባቴ፡እንዳለኹ፡እናንተም፡በእኔ፡እንዳላችኹ፡እኔም፡በእናንተ፡እንዳለኹ፡በዚያን፡ቀን፡ታውቃላችኹ። 21፤ትእዛዜ፡በርሱ፡ዘንድ፡ያለችው፡የሚጠብቃትም፡የሚወደኝ፡ርሱ፡ነው፤የሚወደኝንም፡አባቴ፡ይወደዋል፡ እኔም፡እወደዋለኹ፡ራሴንም፡እገልጥለታለኹ። 22፤የአስቆሮቱ፡ያይደለ፡ይሁዳ፦ጌታ፡ሆይ፥ለዓለም፡ሳይኾን፡ራስኽን፡ለእኛ፡ልትገልጥ፡ያለኽ፡እንዴት፡ነው፧አለው። 23፤ኢየሱስም፡መለሰ፥አለውም፦ የሚወደኝ፡ቢኖር፡ቃሌን፡ይጠብቃል፤ አባቴም፡ይወደዋል፡ወደ፡ርሱም፡ እንመጣለን፡በርሱም፡ዘንድ፡መኖሪያ፡እናደርጋለን። 24፤የማይወደኝ፡ቃሌን፡አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም፡ቃል፡የላከኝ፡የአብ፡ነው፡እንጂ፡የእኔ፡አይደለም። 25፤ከእናንተ፡ዘንድ፡ስኖር፡ይህን፡ነግሬያችዃለኹ፤ 26፤አብ፡በስሜ፡የሚልከው፡ግን፡መንፈስ፡ቅዱስ፡የኾነው፡አጽናኝ፡ርሱ፡ዅሉን፡ያስተምራችዃል፥እኔም፡የነገርዃችኹን፡ ዅሉ፡ያሳስባችዃል። 27፤ሰላምን፡እተውላችዃለኹ፥ሰላሜን፡እሰጣችዃለኹ፤እኔ፡የምሰጣችኹ፡ዓለም፡እንደሚሰጥ፡አይደለም።ልባችኹ፡አይታወክ፡አይፍራም። 28፤እኔ፡እኼዳለኹ፡ወደ፡እናንተም፡እመጣለኹ፡እንዳልዃችኹ፡ሰማችኹ። የምትወዱኝስ፡ብትኾኑ፡ከእኔ፡አብ፡ይበልጣልና፥ወደ፡አብ፡በመኼዴ፡ደስ፡ባላችኹ፡ነበር። 29፤ከኾነም፡በዃላ፡ታምኑ፡ዘንድ፡አኹን፡አስቀድሞ፡ሳይኾን፡ነግሬያችዃለኹ። 30፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ብዙ፡አልናገርም፥የዚህ፡ዓለም፡ገዢ፡ይመጣልና፤በእኔ፡ላይም፡ አንዳች፡የለውም፤ 31፤ነገር፡ግን፥አብን፡እንድወድ፡ዓለም፡ሊያውቅ፥አብም፡እንዳዘዘኝ፥እንዲሁ፡አደርጋለኹ።ተነሡ፤ከዚህ፡እንኺድ።

•✞ #በዓለ_ጰራቅሊጦስ ✞• 🌻🌾🌻🌾🌻🌾🌻🌾🌻🌾 ☞✞ በሐዋርያት ሥራ ምዕ ፩፥፲፬ ላይ እንደተጻፈ የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በተነሣ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ በማውጣት “እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ብሎ ሰማያዊ ሀብትን ሰማያዊ ዕውቀትን ገንዘብ እስኪያደርጉ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ አዝዞ በምስጋና ዐረገ፡፡ ☞✞ ስለምን እንዲኽ አዘዛቸው ቢሉ መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላቸው በፊት ፈሪዎች ነበሩና ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ባልተቀበለ ሰውነታቸው አይሁድ መከራ አጽንተውባቸው ሃይማኖታቸውን እንዳይክዱ፡፡ ☞✞ ዳግመኛም ኅሊናቸውን በተመስጦ ለማቆየት፡፡ ሌላው መንፈስ ቅዱስ የሚወርደው በጽርሐ ጽዮን ነውና ከአንዱ ወደ አንዱ ሲዘዋወሩ እንዳይቀርባቸው ነው፡፡ ☞✞ 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስት በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ኹነው በይሁዳ ምትክ ማትያስን አስገብተው፤ ሰማይ ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማሕፀኗ የተሸከመች የድንግልና ጡቶቿን ያጠባች ቅድስት ድንግል የሌለችበት ጉባኤ ከጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተለየ ነውና የመስቀል ሥር ስጦታቸውን “የኢየሱስ እናት ማርያምን” ይዘው በአንድ ልብ ኾነው በጸሎት መትጋት እንደዠመሩ ሉቃስ ጽፏል (የሐዋ ፩፥፲፬)፡፡ ☞✞ ከዚያም ልክ በሦስት ሰዓት “መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምፅ ከመ ድምፀ ነፋሰ ዐውሎ” ይላል ከወደ ሰማይ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ነጒዶ ተሰምቶ ያሉበትንም ቤት መላው ይኽም የሚያስተምረን ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ የኾነች እመቤታችን ያለችበትና የምትጠራበት ጉባኤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንዳለበት ያሳየናል፤ ይኽም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አስቀድሞ በኤልሳቤጥ ሲታወቅ ገና እመቤታችን ደርሳ ሰላምታን ስትሰጣት ቅዱስ ወንጌል “በኤልሳቤጥ ላይ መንፈስ ቅዱስ መላባት” በማለት እንደመሰከረ እናያለን (ሉቃ ፩፥፵፩)፡፡ ☞✞ ጌታ በዐረገ በ10ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ስለምን ወረደ ቢሉ፡- ➊ኛ10ሩን ሕዋሳት 10ሩን ቃላት በእውነት ብንጠብቅ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጠን ለማጠየቅ፡፡ ➋ኛ ከ10ኛው መዐርግ የገባን እኛ ነበርንና ከጥንተ ቦታችን ክብራችን እንደተመለስን ለማጠየቅ ነው፡፡ ☞✞ ይኸውም ለሐዋርያት በአምሳለ ነፋስ የተገለጸው መንፈስ ቅዱስ ነው ለምን በነፋስ አምሳል ተገለጸ ቢሉ መተርጉማነ መጻሕፍተ ሐዲሳት ያመሰጥሩታል፦ ✔ነፋስ ረቂቅ ነው መንፈስ ቅዱስም ረቂቅ ነውና፤ ✔ነፋስ ኀያል ነው መንፈስ ቅዱስም ኀያል ነውና፤ ✔ነፋስ ፍሬውን ከገለባው ይለያል መንፈስ ቅዱስም ጻድቃንን ከኃጥኣን ይለያልና፤ ✔ነፋስ በምላት ሳለ አይታወቅም ባሕር ሲገሥፅ ዛፍ ሲያናውፅ ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስም በምላት ሳለ አይታወቅም ቋንቋ ሲያናግር ምስጢር ሲያስተረጒም ነውና፤ ✔ነፋስ መንቅሂ ነው መንፈስ ቅዱስም መንቅሂ ነውና፤ ✔ነፋስ መዐዛ ያመጣል መንፈስ ቅዱስም መዐዛ ጸጋን ያመጣልና ነው፡፡ ከዚያም “ወአስተርአይዎሙ ልሳናተ እሳት ክፉላት ከመ እሳት ዘይትከፈል” ይላል እንደ እሳትም የተከፋፈለ ልሳን ኹኖ በያንዳንዳቸው ላይ ተቀምጦባቸዋል፤ ☞✞ ይኸውም ልሳን ላንቃ ማለት ቋንቋን ማውጫ መነጋገሪያ እንደኾነ ኹሉ ሰዎች የሚግባቡበት ትክክለኛ መግባቢያ የኾነ፤ ሊጻፍ ሊሰማ ሊያግባባ የሚችል የቋንቋ ሀብትን መንፈስ ቅዱስ በእሳት ላንቃ አምሳል አሳድሮባቸዋል፡፡ ☞✞ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል መውረዱ ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኸውም እሳት ምሉእ ነው መንፈስ ቅዱስም ምሉእ ነውና፤ ✔እሳት በምላቱ ሳለ ቡላድ ካልመቱ አይገለጽም መንፈስ ቅዱስም ቋንቋ ሲያናግር ምስጢር ሲያስተረጉም እንጂ ዐድሮ ሳለ አይታወቅምና፤ ✔እሳት ከቡላዱ ሲወጣ በመጠን ነው ኋላ በዕንጨት እያቀጣጠሉ ያሰፉታል መንፈስ ቅዱስም በ፵ በ፹ ቀን በጥምቀት ሲሰጥ በመጠን ነው ኋላ በሥራ ያሰፉታልና፤ ✔እሳት ጣዕምን መዐዛን ያመጣል መንፈስ ቅዱስም ጣዕመ ጸጋን መዐዛ ጸጋን ያመጣልና፤ ✔እሳት በመጠኑ የሞቁት እንደኾነ ሕይወት ይኾናል ከመጠን ዐልፎ ቢሞቁት ያቃጥላል መንፈስ ቅዱስም በሚገባ በተጻፈው የመረመሩት እንደኾነ ሕይወት ይኾናል በማይገባ ከተጻፈው ወጥተው የመረመሩት እንደኾነ ይቀሥፋልና፤ ✔እሳት ያቀረቡለትን ያቃጥላል መንፈስ ቅዱስም የጸለዩትን ጸሎት ያቀረቡለትን መሥዋዕት ይቀበላልና፤ ✔እሳት ውሃ ገደል ካልከለከለው ኹሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል መንፈስ ቅዱስም ቸርነቱ ካልከለከለው ኹሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋልና፤ ✔እሳት ዱር ይገልጻል መንፈስ ቅዱስም ምስጢርን ይገልጻልና፤ ✔እሳት የበላው መሬት ለእኽል ለተክል ይመቻል መንፈስ ቅዱስም ያደረበት ሰውነት ለገድል ለትሩፋት ይመቻልና ርሱ ባወቀ በእሳትና በነፋስ አምሳል ወርዷል፡፡ ☞✞ ከዚያም በኹሉም መንፈስ ቅዱስ መልቶባቸው ዓለም በሚሰማው ኹሉም በሚረዳው በ፸፪ቱ ቋንቋ ተናግረዋል፤ በሐዋርያት 72 ቋንቋ አልተከፈለባቸውም፤ የቀሩት ግን ከ15 በታች የወረደ የለም እንጂ 20ም 30ም 40ም 50ም 60ም የተገለጠላቸው አሉ፡፡ ☞✞ እስራኤል ከምርኮ መልስ በኋላ በወደዱት ሀገር በሕጋቸው ይኖራሉ፤ ለበዓለ ፋሲካ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤ በዓለ ፋሲካን አክብረው ከዚያ አያይዘው ሰባት ሱባዔ ቈጥረው በ50ኛዪቱ ዕለት በዓለ ሰዊትን ያከብሩ ነበርና በዓለ ፶ን ለማክበር ከየዓለማቱ የመጡት በእጅጉ ተገርመው:- “እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?፤ የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች በኹለት ወንዝም መኻከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን” በማለት በእጅጉ ተደነቁ፡፡ ☞✞ ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነሥቶ ነቢዩ ኢዩኤል በምዕ 2፡28-29 ላይ “ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ” ብሎ የተናገረው መፈጸሙን ጠቅሶ ሰፋ አድርጎ ነገረ ክርስቶስን ቢያስተምራቸው ቃሉን ተቀብለው ሦስት ሺሕ ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ☞✞ ሊቃውንትም ይኽነን በመያዝ በተለይ እነቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዕለቷን “የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን” ብለዋታል፡፡ ☞✞ እመቤታችን በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በማርቆስ እናት ቤት በሰገነት ላይ በመስቀል ሥር በአደራ የተቀበለቻቸው በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የሚያምኑ የአደራ ልጆቿን ሐዋርያትን ይዛ እንደተገኘች ዛሬም በልጇ ደም በተመሠረተችው ሐዋርያዊት በኾነችው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን የልጇን የባሕርይ አምላክነት የርሷን ወላዲተ አምላክነት በመመስከር እንኖራለን፡፡ ☞✞ “ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማሕየዊ ዘሠረጸ እምአብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት” (ጌታ ማሕየዊ በሚኾን ከአብ በሠረጸ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፤ በነቢያት ዐድሮ የተናገረ ለርሱ ከአብ ከወልድ ጋር እንስገድለት እናመስግነው) አሜን፡፡ [ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ] Channel @EOTC2921 Group @Ethio_Orthodox1 •✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞•

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌍ስርዓተ በዓል ወጾም ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን🌍 ❀☞ ጰራቅሊጦስ🌾🌾🌾 ሰኔ ፱ ❀☞ ጾመ ሐዋርያት🌾🌾🌾ሰኔ ፲ ❀☞ ጾመ ድኅነት🌾🌾🌾 ሰኔ ፲፪ 👇•✞•👇•✞•👇•✞•👇 Channel @EOTC2921 Group @Ethio_Orthodox1

ይህን የማያምኑ እንዲሁም የእናቱን የእመቤታችንን ዕርገት የሚክዱ እንደ ይሁዳ አንጀታቸው ተዘርግፎ ንዋየ ውስጣቸው ወጥቶ ይሞታሉ! የጌታን ዕርገት ያመነ የእኛን ዕርገት ያረጋግጣል፣ የእኛን ዕርገት ያመነ ደግሞ የእናቱን ዕርገት እንዴት ይክዳል??? እኛ ግን "ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም" (የሙታንን መነሣትና ዕርገት እናምናለን፤የሚመጣውንም የዘለዓለም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን) እያልን በቅድስቲቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን እየተባረክን !!! #በትንሣኤው_ላነሣን_በእጆቹ_ለባረከን_በዕርገቱ_ላሳረገን_የማታልፍ_ዘለዓለማዊት_ርስቱን_ለሚያወርሰን_ጌታችንና_አምላካችን_ክብር_ምስጋና_ይድረሰው!አሜን!!!

•✞✞✞ #የዕርገት_በረከቶች ✞✞✞• #እንኳን_ለብርሃነ_ዕርገቱ_አደረሳችሁ!!! ጥንቱ ግንቦት 8 ቀን ዕለቱ ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ያረገበት ዕለት ነው። ☞✞በቀመረ ድሜጥሮስ በሊቃውንት ውሳኔ መሠረት ዕለቱን (ሐሙስን) ሳይለቅ በግንቦት 5 (ኢይወርድ/ታሕታይ ቀመር) እና በሰኔ 9 (ኢየዐርግ/ላዕላይ ቀመር) መካከል እየተመላለሰ የሚከበር ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት ዋናውና የመጨረሻውም ነው፤በዚህም መሠረት ዘንድሮ ግንቦት 29 ቀን በዓለ ዕርገትን እናከብራለን። ☞✞ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት መጽሐፈ ኪዳንን እያስተማረ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያሳየ፣ ለነፍሳት ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን እየገለጠ ለ 40 ቀናት መቆየቱን ቅዱስ ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት ጽፎልናል ፦ "ሕማማትን ከተቀበለ በኋላ ብዙ ተአምራትን በማሳየት አርባ ቀን ሙሉ እየተገለጠላቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸውና እያስተማራቸው ሕያው ሆኖ ራሱን ገለጠላቸው" እንዲል፣ ሐዋ 1÷3። የጌታችን የዕርገት ታሪክ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 24 ÷50 ጀምሮ የተጻፈ ሲሆን ደቀመዛሙርቱ በዓይናቸው እያዩት እየባረካቸው ከዓይናቸው መሠወሩ ተገልጧል፣ሐዋርያትም ለረጅም ሰዓታት ዓይኖቻቻውን የሥጋ ዓይን ማየት ማብቂያ የሆነው ግዙፍ መጋረጃ ሰማይ ላይ ተክለው የቆዩ ሲሆን ነጫጭ ልብስ የለበሱ መላእክት መጥተው "ዳግመኛ ይመጣል" በማለት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አሰናብተዋቸዋል። ሐዋርያትም የተደረገላቸውንና የሚደረጉላቸውን አራት ነገሮች እያሰቡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። {ቡራኬ ፣ ሹመት ፣ ተስፋ ፣ ቀጠሮ!} #ቡራኬ "አንሥአ እዴሁ ወባረኮሙ" እንዲል እጆቹን በላያቸው ላይ ጭኖ በረካቸው፣ "እየባረካቸውም ራቃቸው፣ ወደ ሰማይም ዐረገ" ይላል (ወንጌል፣ቅ.ያሬድ)። ይህ ቡራኬ ለሐዋርያት በመዋዕለ ሥጋዌው ከሆነው ሁሉ የመጨረሻው ቡራኬ ነው ፤ ይህንን ቡራኬ መቀበል እስከዚህ ተራራ ድረስ መጽናትንና መታገሥን የሚጠይቅ ነው፤ይህ ዕለት ደግሞ በክርስቶስ የጸኑት የተባረኩበት ፣ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ብለው እንደተራ ሰው እና እንደ እቃ በወርቅና በብር የሸጡና የለወጡ ሰዎች አንጀታቸው ተዘርግፎ የሞቱበት ዕለት ነው፣ ቡራኬው ዛሬም የማይቋረጥ መሆኑን ሲያረጋግጥልን ደግሞ "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኀቆሙ ወዐርገ ሰማየ" (እየባረካቸው ራቃቸው ፤ወደ ሰማይም ወጣ) በማለት ይነግረናል (ሉቃ 24÷51)። ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴ ፍጻሜ ላይ ካህኑ እጆቹን አመሳቅሎ "እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን " በማለት ያን የ"ዕርገት" በረከት/ቡራኬ ለምእመናን ስታድለውና ስታከፋፍለው ትኖራለች፤ ይህም ደግሞ "እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ " (ማቴ 28÷20) በማለት የገባልን ኪዳን ማረጋገጫ ቡራኬ ነው። በዚህም ቡራኬና ኪዳን ቤተክርስቲያን ጸንታበት፣ አስከ ዓለም ፍጻሜ ሳትፈርስ ሳትናወጥ ተማምናበት ትኖራለች። #እሊያ_አዳምን_ውብና_ድንቅ_አድርገው_አከናውነው_የፈጠሩ_ኋላም_ልዩ_ልዩ_ድውያንን_የፈወሱ_ሙታንን_ለማስነሣት_የተዘረጉ_ለቤተ_ክርስቲያን_መስቀል_ላይ_የተቸነከሩላት_እጆች_በተዘጋ_ቤት_ውስጥ_በፍርሃትና_በድንጋጤ_ለነበረች_የመጀመሪያዋ_ቤተ_ክርስቲያን (ጉባኤ ሐዋርያት) "ሰላም ለኩልክሙ" በማለት የተዘረጉላት እጆች ፣በዕርገት የማያልቅ በረከትን ለመስጠት የተመሳቀሉላት እጆች እንደጣራ እንደ ጒልላት ሆነው ከድነዋት ምሕረትና ይቅርታ እየዘነበላት ትኖራለች። #ሹመት ቡራኬው በውስጡ ከያዛቸው ታላላቅ ምሥጢራት አንዱ "ሢመት መንፈሳዊ" ነው፤ ሐዋርያት እስከዚህ ቀን ድረስ የተሰጣቸው ሹመት ሁሉ በቡራኬ የተረጋገጠበትና የመጨረሻውን የክህነት ሥልጣን/ፕትርክናን የተቀበሉበት ዕለት ዕለተ ዕርገት ነው፤ መተርጒማነ ወንጌል ሊቃውንትም "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኃቆሙ ወዐርገ ሰማየ" ያለውን ሲተረጒሙ "ሾሟቸው የርቀት(ቀ ፊደል ጠብቆ ይነበብ) ያይደለ የርኅቀት ተሠውሯቸው ወደ ሰማይ ዐረገ" ብለዋል (ትር . ወን)። ዛሬም እነዚህ ተመሳቅለው እየባረኩን ተዘርግተው ያረጉ እጆች በርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት፣በሊቃነ ጳጳሳትና፣በጳጳሳት አማካይነት ካህናትን እየሾሙ ይኖራሉ። #ተስፋ የጌታችን ዕርገት ያለ ተስፋ የሆነ ዕርገት አይደለም የኤልያስ ዕርገት በመጎናጸፊያው በኩል ለኤልሳዕ ተስፋ ከሆነው በላይ የጌታ ዕርገት ለቤተ ክርስቲያን በተዘረጉት የይቅርታ እጆች በኩል የተላለፈው ቡራኬ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰማይ ወደዙፋኑ የተጠራችበት ተስፋ ነው፣ ኤልሳዕ በመምህሩ በኤልያስ መጎናጸፊያ ከተሰጠው እጥፍ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በእጅጉ የበለጠ ስጦታ በጌታችን ዕርገት ጊዜ ተቀብለናል፤ #የመጀመሪያው_ተስፋ_የመንፈስ_ቅዱስ_ወደዚህ_ዓለም_መምጣት_ሲሆን (ዮሐ 15÷26፣ሉቃ24÷49) #ሁለተኛው_ደግሞ_የእኛ_ዕርገት_ነው_የእርሱ_ዕርገት_የእኛ_ዕርገት_ነውና፣ ሊቃውንቱም "ዐርገ እግዚአብሔር ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን " (የንጹሐን ጻድቃንን ዕርገት ያረጋግጥ ዘንድ እግዚአብሔር ወልድ ዐረገ) በማለት ነግረውናል፤ ትንሣኤው ለትንሣኤያችን ማረጋገጫ እንደሆነ ዕርገቱም እንዲሁ ነውና ፤ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ይላል :— "በቀኜም ተቀመጥ አለው ይህ ሥጋ ቀድሞ አንተ መሬት ነህ ወደ መሬትነትህም ትመለሳለህ የሚል አዋጅን ሰምቶ ነበር ዛሬ ግን ስለዚህ ሥጋ ከሰማያት በላይ መሆን ብቻ አልበቃውም በመላእክት ቦታ አልተወሰነም።ይህም ክብር አልበቃውም፤ከመላእክት በላይ ከሆነ ከሱራፌልም በላይ ከፍ አለ ወጥቶ ከሊቃነ መላእክት በላይ ሆነ እንጂ ወደላይ መውጣት ብቻ አልበቃውም ወደ መንግሥት ዙፋን ወጥቶ በላዩ እስከመቀመጥ ደረሰ እንጂ…………የእኛን ባህርይ ከዚህ ከፍተኛ ያህል የርኅቀት መጠን በላይ አውጥቶ አኖረው፣ ቀድሞ ሰውን ካወረደበት ቦታ በታች ምንም የለም ዛሬም ሰውን ካወጣበት ቦታ በላይ ምንም የለምና።" በማለት የመጨረሻውን ስፍራችንን ይነግረናል (ሃይ . አበ 88÷23—27)፤ ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስም "ወአንሥአነ እግዚአብሔር አብ ምስሌሁ ወአንበረነ በየማኑ በየማኑ በሰማያት በኢየሱስ ክርስቶስ" (እግዚአብሔር አብ ከእርሱ ጋር ለመኖር አስነሥቶ በኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በክብር አኖረን) ብሏል (ሃይ . አበ) ፤ይህም ደግሞ እርሱ ባለቤቱ "እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስኅብ ኲሎ ኀቤየ" (ከምድር ከፍ ያልኩ እንደሆነ ሁሉን ወደኔ እስባለሁ, ዮሐ 12÷31) ዳግመኛም "እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ " (ዮሐ 14÷3) በማለት የሰጠን የመጨረሻ ተስፋ የተረጋገጠበት ነው። #ቀጠሮ ይህም ቀጠሮ ዕርገታችን የሚከናወንበት ፤ ተስፋችን የሚጨበጥበት ቀጠሮ ነው እርሱም ዳግም ምጽአቱ ነው። ይህንንም ቀጠሮ ለቤተ ክርስቲያን አስይዘው የሄዱት ብሥራተ ትስብእቱን/ሥጋዌውን ለእመቤታችን ፣ብሥራተ ትንሣኤውን ለቅዱሳት አንስት የተናገሩ መላእክት ናቸው ፤ነጫጭ አልባሳት ለብሰው "………ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል" (ሐዋ 1÷11) በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፣ አቡቀለምሲስ ዮሐንስም "እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል ፤ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል……" (ራእ 1÷7) በማለት በዕርገቱ ያየነውን ደመና በዳግም ምጽአቱ እንደምናየው አስተምሮናል(የጥምቀት፣የደብረ ታቦር፣የዕርገት፣የምጽአት ደመና የባህርይ ክብሩ/ክበበ ትስብእት/ሥጋ ማርያም ነው ብለዋል ሊቃውንት)። እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ልጅነታችን ጠብቀንና አስጠብቀን የመንግሥቱን መሰጠት እየተጠባበቅን እንኖራለን። ዕርገቱ ዕርገታችን ነው ብለን በፍጹም እምነት እናምናለን!!!

💚 @EOTC2921 💚 💛 @EOTC2921 💛 ❤️ @EOTC2921 ❤️
💚 @EOTC2921 💚 💛 @EOTC2921 💛 ❤️ @EOTC2921 ❤️

#የሱራፊ_ማዕጠንት_የአምላክ_እናት ☞✞በቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢር የተራቀቁ ቀደምት ሊቃውንት ቅድስት ድንግል ማርያምን ዮሐንስ ባያት በመላእክት እጅ በተያዘች የወርቅ ማዕጠንት መስለዋት አስተምረዋል (ዮሐ ፰፥፫‐፬)፡፡ ☞✞ይኸውም የሥነ ፍጥረት መጻሕፍት እንደሚያስረዱን ልዑል እግዚአብሔር ከሰራዊተ ሩፋኤል ኻያ አራት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ መንግሥት ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ አያይዞ አቁሟቸዋል፤ “ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት ዘሕብሩ መብረቅ” ይላል እነዚኽን ስማቸውን “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት ወርቅ ጽና አስያዛቸው፤ የብርሃን አክሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው፤ ማኅተሙ መስቀል የኾነ የብርሃን ዘንግን አስያዛቸው፤ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ የብርሃን ካባ ላንቃ አልብሷቸዋል። ☞✞ዮሐንስም በራእ ፬፥፬‐፭ ላይ “በዙፋኑ ዙሪያም ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ኻያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር” ብሏል፡፡ ☞✞ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወይወፅእ እምውስተ ማዕጠንቶሙ መብረቅ ወነጐድጓድ ወፀዓዕ ዘመዐዛሁ ሠናይ ወይቤሎሙ እግዚአብሔር ለካህናቲሁ ጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን ይኩን ውስተ ማዕጠንትክሙ ከመ ይዕርግ ኀቤየ” እንዳለው፤ እነዚኽ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፤ ድምፁ ነጓድጓድ፤ መዐዛው መልካም የኾነ ሲኾን የጻድቃን ጸሎት፣ የሰማዕታት ገድል፣ የደጋግ ሰዎች ምግባር በእናንተ ማዕጠንት እየታጠነ ወደኔ ይድረስ ብሏቸዋል፤ “ወይገለብቦ ለሰማይ ወለአርያም ጢሰ ዕጣኖሙ ዘመዐዛሁ ሠናይ” ይላል ዛሬ በክረምት ተራራውን ኮረብታውን ጉም እንደሚሸፍነው እንደሚጋርደው ኹሉ ካህናተ ሰማይም የሚያጥኑት ማዕጠንት ጽርሐ አርያምን መንበረ መንግሥት ይሸፍናል፡፡ ☞✞ዮሐንስ በራእዩ “እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ ኻያ አራቱ ሊቃናት በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ ጌታችንና አምላካችን ሆይ አንተ ኹሉን ፈጥረኻልና ስለ ፈቃድኽም ኾነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባኻል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ” በማለት እንደተናገረ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ካህናተ ሰማይ ዝቅ ብለው ክንፍ ለክንፍ ገጥመው ቁመው አምላካቸውን ያመሰግናሉ (ራእ ፰፥፱-፲፩)፡፡ ☞✞ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ የቅዱሳንን ጸሎት መልአኩ በወርቅ ማዕጠንቱ በርሱ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዳወጣው በምእ ፰፥፫-፬ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” በማለት ምዕራገ ጸሎት የሚደረግባት የጥናዋን ምስጢር ገልጽዋል፡፡ ☞✞በመኾኑም የቅዱሳኑ ኹሉ ጸሎት በመልአኩ እጅ በወርቅ ጥናዋ አማካይነት ቅድመ እግዚአብሔር እንደደረሰ ኹሉ በተመሳሳይ ፍሕመ መለኮትን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ በተሸከመች አማናዊት ማዕጠንት በኾነች በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የጸለይነው ጸሎት ኹሉ እውነተኛ ፈራጅ ወደኾነው ወደ አምላካችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚቀርብ ነውና ሊቃውንት ቅድስት ድንግል ማርያምን ዮሐንስ ባያት በመላእክት እጅ በተያዘች የወርቅ ማዕጠንት መስለዋታል፡፡ ☞✞ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከዚኽ ተነሥቶ በአንቀጸ ብርሃን መጽሐፉ ላይ፦ “ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ በማዕጠንት ዘወርቅ ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ካህናት ሰማያውያን እለ ይከውኑ ጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን ወመሃይምናን እምዲበ ምድር በውስተ ማዕጠንቶሙ ከማሁ በስእለተ ስምኪ ያዐርጉ ስእለቶሙ ለደቂቀ ዕጓለ እመ ሕያው ውስተ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወታስተስርዪ ኀጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም” ☞✞(እመቤታችን ሆይ የቅዱሳንና የምእመናንን ኹሉ ጸሎት በማዕጠንታቸው ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች እጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን፤ እንዲኹም ስምሽን በመጥራት የሰው ልጆችን ልመና ወደ ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሳርጋሉ፤ የወገኖችሽን ኀጢአት ታስተሰርዪ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተፈቅዶልሻል፤ ለሰው ልጆች የዘላላም ሕይወት ድልድይ ትኾኚ ዘንድ) በማለት በምልጃዋ በተሰጣት ቃል ኪዳን ጸሎታችንን ኹሉ ወደ ሥላሴ የምታደርስልን አማናዊት ማዕጠንትነቷን መስክሯል፡፡ ☞✞ከሊቃውንት ውስጥ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ማዕጠንተ ሱራፊነቷን ሲገልጹ፦ ☞✞“ዐቢይ ውእቱ ተአምር ጸግዮትኪ በድንጋሌ ወፈርዮትኪ በንጽሕ ቊርባነ አምልኮ መጥለሌ ማዕጠንተ ሱራፊ ዘወርቅ ወጽዋዐ ኪሩብ ዕንቈ ቢረሌ አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌኪ ማርያም ዘየዐርግ ሉዓሌ” (በድንግልና መፅነስሽ በንጽሕናም የሚያለመልም የአምልኮ ቊርባንን መውለድሽ ታላቅ ድንቅ ተአምር ነው፤ የሱራፊ የወርቅ ማዕጠንት ቢረሌ የሚባል የኪሩብ የዕንቊ ጽዋ ማርያም ያላንቺ ወደላይ ወደ ፈጣሪ የሚያርግ ልመናም ምልጃም የለም) በማለት በርሷ ምልጃ እውነተኛ ፈራጅ የኾነው ልጇ ልመናችንን የሚቀበልልን እውነተኛዋ የሱራፊ ማዕጠንት መኾኗን ሲመሰክሩ፤ ☞✞ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፋቸው ላይ፦ “ከመ ጼና ልብስኪ ወጼና አንፍኪ ወመዐዛ አፉኪ ቦኑ እምነ ጽጌያት ዘገነት ዘበውስተ ገዳም ይጼኑ ተአምረ ቊርባን ማርያም ለኪሩብ ጢሰ ዕጣኑ ማየ ልብንኑ ሰሊኆትኑ መዐዛ ዚኣኪ ዘይመስል መኑ” (እንደ ልብስሽ እንደ አፍንጫሽ እንደ አፍሽ መዐዛ በገነት በበረሓ ከአሉት አበባዎች እንደዚያ የሚኾን አለን? የለም፤ ኪሩብ የሚያቀርባት የዕጣን ጢስ ማርያም፤ የነጭ ዕጣን ልባንጃ ውሃ ነውን? ወይስ ሰሊኆት የተባለ ሽቱ? የአንቺን መዐዛ የሚመስል ማንኛው ነው?) በማለት የመዐዛ ንጽሕናዋን ነገር መዐዛቸው በሚያስደንቅ ነገራት በመመሰል “ኪሩብ የሚያቀርባት የዕጣን ጢስ ማርያም” በማለት የምልጃዋን ነገር አስተምረዋል፡፡ "ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ" 🙏ምዕራገ ጸሎት ማዕጠንተ ሱራፊ ድንግል ሆይ ጸሎታችንን ኹሉ ወደ ልጅሽ መንበር አሳርጊልን፡፡🙏

ድንግል ሆይ ስላንቺ @EOTC2921 .mp31.67 MB

ነይ ነይ እምዬ ማርያም @EOTC2921.m4a1.10 MB

መመኪያዬ_እርስቴ_የሆነች.m4a9.71 KB