የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
رفتن به کانال در Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
نمایش بیشتر4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
4 374
#ከስምዖን_ጫማ_ሰፊው_ጋር_ተራራን_ያፈለሰው_ታላቁ_አባት_አቡነ_አብርሃም_ዕረፍቱ_ነው
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ታኅሣሥ-፮
አቡነ አብርሃም፡- ይኸውም አባት ከስምዖን ጫማ ሰፊው ጋር ተራራን
ያፈለሰ ታላቅ አባት ነው፡፡ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 62ኛው ሲሆን ከምስራቅ
አገር ከደጋግ ክርስቲያኖች ወገን የተገኘ ነው፡፡ እርሱም አስቀደሞ ብዙ
ገንዘብ የነበረው ነጋዴ ሲሆን ብዙ መመጽወት ይወድ ነበር፡፡ ከመነኮሰም
በኋላ ትሩፋቱና ተጋድሎው በተሰማ ጊዜ የእስክንድርያ አባቶች ይሾሙት
ዘንድ ተስማምተው ጵጵስና ተሾመ፡፡ እርሱም በዘመኑ ኤጲስ ቆጶሳቱን
ለክህነታቸው እጅ መንሻ መማለጃ የሚያመጡት እንዳይቀበሉ አወገዘ፡፡
የአሕዛብ ግብር ያላቸውና ብዙ ዕቁባትን የያዙ ሰዎችን ዕቁባቶቻቸውን
እንዲፈቱ በአዋጅ አዘዘ፡፡ ነገር ግን አንድ የንጉሡ ጸሐፊ እምቢ ብሎ
ዕቁባቱን ሳይፈታ ቀረ፡፡ አባታችንም ብዙ ጊዜ ቢመክረው እምቢ አለ፡፡ አባ
አብርሃም አንድ ቀን እቤቱ ሲሄድ ባለ ዕቁባቱ ዐውቆ እንዳላየ ሆኖ በሩን
ዘጋበት፡፡ አባታችንም ከበሩ ላይ ሁለት ሰዓት ያህል ቆመ፡፡ ከዚህም በኋላ
አባ አብርሃም ‹‹የዚህ ሰው ደሙ በራሱ ላይ ነው እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ››
በማለት የእግሩን ትቢያ አራግፎ ሲመለስ ወዲያው የቤቱ መድረክ ለሁለት
ተከፈለ፡፡ ሰውየውም ከሹመቱ ተሽሮ እጅግ ድኃ ሆኖ በክፉ ደዌ ተይዞ
እጆቹና እግሮቹ ተቆራርጠው ክፉ አሟሟት ስለሞተ ለሁሉም ሰው
መቀጣጫ ሆነ፡፡
በዘመኑም ወደ እስልምና ሃይማኖት የገባ አንድ አይሁዳዊ ሰው ነበር፡፡
የጭፍሮች አለቃ የነበረውም ሰው ጓደኛው ስለነበር ከጓደኛውም ጋር አብሮ
ወደ ምስር አገር ንጉሥ ዘንድ እየገባ ከንጉሡ ጋር ይነጋገር ነበር፡፡ አንድ ቀን
የሰለመው አይሁዳዊ ንጉሡን ‹‹ኤጲስ ቆጶሳቱን አምጣውና ልከራከረው››
አለው፡፡ ንጉሡም አባ አብርሃምን አስጠርቶ አከራከራቸው፡፡ አባ አብርሃም
አይሁዳዊውን በንጉሡ ፊት አሳፈረው፡፡ ከዚህም በኋላ ከጓደኛው ጋር ሆነው
አባ አብርሃም የሚወድቅበትን ነገር ይፈልጉ ጀመር፡፡ በወንጌልም ላይ
‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ
ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል የሚሳናችሁ ነገር የለም›› (ማቴ 17፡20)
የሚውን ትእዛዝ ለንጉሡ በመንገር ይህን ግን ክርስቲያኖቹ በፍጹም
ሊያደርጉት አይችሉም አለው፡፡ ንጉሡም ድጋሚ ሊቀ ጳጳሱን አባ አብርሃምን
አስጠራቸውና ‹‹በውኑ እንዲህ የሚል ነገር በወንጌላችሁ አለን?›› ብሎ
ጠየቃቸው፡፡ ሊቀ ጳጳሱም «አዎ ልክ ነው በወንጌላችን ‹እምነት ቢኖራችሁ
ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ ተነቅለህ ሂድ ብትሉት ይፈልሳል› ተብሎ
ተጽፏል» አሉት፡፡ ንጉሡም፡- ‹‹እንግዲያውስ እናንተ ብዙ ስለሆናችሁ
የእናንተና የዚህ ሁሉ ክርስቲያን እምነት ቢደመር ተራራን ያፈልሳልን?
ከእናንተ ውስጥ ይህን አድርጎ የሚያሳየኝ ሰው አምጣልኝ›› አላቸው፡፡ ሊቀ
ጳጳሱም ቀን እንዲሰጣቸው ጠየቁና የሦስት ቀን ዕድሜ ተሰጣቸው፡፡
አባ አብርሃም ጳጳሳቱንና ካህናቱን ሁሉ ሰብስበው ሱባኤ ያዙ፡፡ ወደ
ቤተክርስቲያን ሄደው ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ሥር ተንበርክከው
‹‹የአምላክ እናት ሆይ ብርሃን የሆነ የልጅሽን ኃይል ግለጭልኝ›› እያሉ
እመቤታችንን በጽኑ ተማጸኗት፡፡ እመቤታችንም በሱባኤው ሦስተኛ ቀን
ተገልጣላቸው ‹‹ልጄ ሆይ እንዲህ ያለው ነገር ላንተ ሳይሆን ባለ አንድ
ዐይና ለሆነውና ስምዖን ለሚባለው ጻድቅ ነው የሚደረግለት፤ እርሱ ስለ
ልጄ ትእዛዝ አንድ ዐይኑን አጥቷልና፡፡ እርሱን ሄደህ ‹እመቤታችን ነግራኝ
ነው› ብለህ ንገረው፡፡ እንዲህ ብለህ ካልነገርከው ግን እሺ አይልህም፡፡
ተራ ሰው መስሎ በገበያ ውስጥ እንስራ የተሸከመ ሰው ሆኖ ታገኘዋለህ››
አለቻቸው፡፡ እንደነገረቻቸውም ገበያ ሄደው አቡነ ስምዖንን አገኟቸውና ከኋላ
በኩል ሆነው የልብሳቸውን ጫፍ ቢነኳቸው «ተሰውሮ የኖረው ጸጋዬ
ታወቀብኝ» በማለት በእጅጉ ተቆጧቸው፡፡ ሊቀ ጳጳሱም «እመቤታችን
ልካኝ ነው» በማለት የመጡበትን ጉዳይ ነገሯቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ስምዖን ለአቡነ አብርሃም እንዲህ አሏቸው፡- «ስለ እኔ
ለማንም ቢሆን በፍጹም እንዳትናገር፣ ማንነቴንም አትግለጥብኝ አደራ ነገር
ግን ሄደህ ንጉሡ ይነሳልኝ በሚልህ ተራራ ትይዩ ከካህናቱና ከሕዝቡ ጋር
ሄደህ ቁም፡፡ ክርስቲያኖችን ከተራራው ፊት ለፊት፥ አይሁዳውያንንና
የማያምኑትን ደግሞ ከተራራው ጀርባ እንዲሆኑ አድርግ፤ ካህናቱንም ልብሰ
ተክህኖ አልብሰህ፣ ወንጌል፣ ማዕጠንት፣ መብራትና መስቀል አስይዘህ
ቆየኝ፤ እኔም ማንም ሳያውቀኝ ከሕዝቡ ጋር ተደባልቄ በፊትህ እቆማለሁ፡፡
አንተ እኔ የምሠራውን ሥራ እያየህ ሥራ፣ ሕዝቡ ደግሞ አንተ
የምትሠራውን እያዩ ይሥሩ እኔም ስሰግድ አንተም ስገድ፣ ይህንንም ሦስት
ጊዜ አድርግ በየስግደትህም ሦስት ጊዜ በመስቀልህ አማትብ» አለው።
ሊቀ ጳጳሱም ቀድሞ ሄደው እንደተባሉት አደረጉ። በመጨረሻም አርባ አንድ
ኪርያላይሶን አድርሰው፣ ጸሎት አድርገውና ሰግደው ሲነሡ ተራራው ምድርን
ለቆ ወደ ላይ ተነሣ፣ በተራራው ሥርም በወዲያና በወዲህ ያሉት ሁሉ
እርስ በእርሳቸው ተያዩ፡፡ ይህም ሂደት ለሦስት ጊዜ ያህል ተደጋግሞ
ተከናወነ፡፡ በዚህም ጊዜ ስለ ቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊው ፍጹም እምነት
ሲባል ለሊቀ ጳጳሱና በዚያች ሀገር ለነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ «እውነት
እላችኋለሁ፥ የሰናፍንጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ
ከዚህ ወደዚያ ተነቅለህ ሂድ ብትሉት ይፈልሳል፤ የሚሳናችሁ ነገርም
የለም›› ተብሎ በጌታችን የተነገረው ቃል ተፈጽሞላቸዋል፡፡ ማቴ 17፡20፣
21፡21፡፡ ንጉሡም እጅግ በመደነቅ ወደ አባ አብርሃም ቀርቦ ‹‹ምን
እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹በምስር አገር የቅዱስ
መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን ሥራልኝ›› አሉት፡፡ እንዳሉትም ቤተ
ክርስቲያኑን ሠራላቸው፡፡ ሌሎች አገሮችም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን
ሠራላቸው፡፡ አቡነ አብርሃምም ተጋድሎአቸውን ፈጽመው በሰላም
ዐርፈዋል፡፡
🙏የአባታችን የአቡነ አብርሃም ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን🙏
4 374
፣ ወተትና ማር ወደ አራቱም አቅጣጫ ፈሰሰ፡፡
እርሷና ሌሎቹም 72 ሰማዕታት ከተሰየፉ በኃላ ሥጋቸው ቀምድር ላይ
ተጥሎ ቀረ፡፡ ንጉሡም ጋኔን ተጭኖበት መልኩ ተለውጦ እንደ እሪያ ሆነ፡፡
ከዚያ በፊት የአርማንያውን ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ጎርጎርዮስን ንጉሡ ድርጣድስ
ዕጣን ሊያሳርግ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ አቡነ ጎርጎርዮስን ጠርቶ
ለአማልክት ዕጣን አሳርጉ ቢላቸው እሳቸውም ትእዛዙን አልፈጽምም ባሉት
ጊዜ እጅግ ጽኑ በሆኑ በተለያዩ ሥቃዮች ካሠቃያቸው በኃላ ጥልቅ ጉድጓድ
አስቆፍሮ በዚያ ውስጥ ጣላቸው፡፡ አባታችንም በዚያ ጥልቅ ጉድጓድ
እንደተጣሉ ለ15 ዓመታት ኖሩ፡፡ ስለምግባቸውም እግዚአብሔር አንዲት
እናትን አዘዘላቸው፡፡ በንጉሡ አዳራሽ አቅራቢያም የምትኖረው ይህች ሴት
በእግዚአብሔር ታዝዛ እንጀራን እየጋገረች ወደ ጉድጓዱ ትጥልላቸው ነበር፡፡
ከእርሷም በቀር አባታችን በሕይወት መኖራቸውን የሚያውቅ ሰው የለም፡፡
እንዲህም እያደረገች 15 ዓመት ኖራለች፡፡
ንጉሡ ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ማግባት ፈልጎ ሳለ ፈጽሞ እምቢ
ብትለው በእርሷ ምክንያት ብዙ ደናግል ሴቶችን ገደለ፡፡ ሰይጣን በልቡ
ያደረበት ይህ ንጉሥ ድርጣድስም ደናግሎቹን እና ቅድስት አርሴማን በብዙ
ሥቃይ ከገደላቸው በኋላ ሥጋቸውን በተራራ ላይ ጥሎት ነበር፡፡ ነገር ግን
ምንም ሳይሆን በጌታችን ጥበቃ ኖረ፡፡ የቅድስት አርሴማንም ውበቷን
እያሰበ ስላስገደላት የሚጸጸት ሆነ፡፡ ወገኖቹም ‹‹ከሀዘንህ ታርፍ ዘንድ ወደ ጫካ ሄደን አውሬ አድን›› አሉት፡፡ ንጉሡም በፈረሱ ተቀምጦ ወደ ጫካ
ወጣ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ተዋሃደውና በእነ ቅድስት አርሴማና በአቡነ
ጎርጎርዮስ ላይ በሠራው ግፍ እግዚአብሔር የተፈጥሮ መልኩን ቀይሮት
እንደ እሪያ አደረገው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነጾር ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ
አእምሮው ስቶ ልቡ ተሰውሮ ወደ እንስሳነት እንደተለወጠ ሁሉ (ዳን 4፡
28-37) ንጉሥ ድርጣድስም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ ወደ
እሪያነት ተለወጠ፡፡
ንጉሡ ድርጣድስ ወደ እሪያነት ከተለወጠ በኋላ ያገኘውን ሁሉ የሚናከስ
ሆነ፡፡ በቤተ መንግሥቱም ባሉ ሰዎች ላይ ሰይጣን አደረባቸውና ታላቅ
ጭንቅ ሆነ፡፡ የንጉሡም እኅት በሌሊት ‹‹ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ
ካላወጣችሁት በቀር አትድኑም›› የሚል ራእይ አየችና ለወገኖቿ
ነግረቻቸው፡፡ የሞተ መስሏቸው ስለነበር ይህን ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና
ሄደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን 15 ዓመት ተጥሎ ከኖረበት ጉድጓድ ውስጥ
በገመድ ጎትተው አወጡትና አክብረው ወሰዱት፡፡
እርሱም የእነ ቅድስት አርሴማን ሥጋ ወዴት እንዳደረሱት ሲጠይቅ
በተራራው ላይ እንዳለ ነግረውት ሄዶ ሲያየው ምንም ሳይነካው በደህና
አገኘው፡፡ አንሥቶም ባማሩ ቦታዎች አኖራቸው፡፡ ሰይጣን ያደረባቸውን
የቤተ መንግሥቱንም ሰዎች ፈወሳቸው፡፡ ስለ ንጉሡም ወደ አውሬነት
መለወጥ ነግረውት እንዲፈውሰው ለመኑት፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስም ወደ
ንጉሡ ሄደው በእሪያነቱ ሳለ ‹‹ብፈውስህና ባድንህ ከክፉ ሥራህ
ትመለሳለህ? በእውነተኛው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህ?››
አሉት፡፡ እሪያ የነበረው ንጉሥም ‹‹አዎ›› ቢላቸው ጸሎት አድርገው
ፈውሱት፡፡ አእምሮውና የቀድሞው መልኩም ተመለሰለት፡፡ ነገር ግን አቡነ
ጎርጎርዮስ ንጉሡ ዳግመኛ እንዳይታበይ በማለት ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር
አስቀሩለት፡፡
የቤተ መንግሥንም ሰዎች ሁሉ ከፈወሳቸው በኋላ 8 ቀን እንዲጾሙ
አዘዛቸው፡፡ ሃይማኖትንም አስተምሮ ሥርዓት ሠራላቸው፡፡ እርሱም ክህነት
አልነበረውምና ወደ ሮሜው ንጉሥ ወደ አኖሬዎስና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ
መልአክት ላኩና ጳጳስ ይላኩላችሁ አላቸው፡፡ የሮሙ ሊቀ ጳጳሳትም
ጎርጎርዮስን ሾሞ ላከላቸው፡፡ ንጉሡ አኖሬዎስም በዚህ ተደሰተ፡፡
ጎርጎርዮስም ተሹሞ ከመጣ በኋላ ሁሉንም አጠመቃቸው፡፡ አርማንያም
በቅዱስ ጎርጎርዮስ ትምህርት በክርስትና የምትታወቅ አገር ሆነች፡፡ እርሱም
በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው፡፡ ምእመናንያንም
የሰማዕታቱን ሥጋ ሰብስበው በመልካም ቦታ ካስቀመጡት በኃላ
የመከራው ዘመን ሲያልፍ የተዋበች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው የቅዱሳኑን
በዚያ አኖሩ፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡
የቅድስት አርሴማ ዕረፍቷ መስከረም 29 ነው፡፡ የቤተክርስቲያኗም ቅዳሴ
በአርማንያ አገር፣ በኪልቂያ፣ በሶርያ፣ በአንጾኪያና በግብፅ አውራጃዎች ሁሉ
በታኅሣሥ ወር በ6ኛው ቀን ሆነ፡፡ ጌታችን ከገባላት ብዙ ቃልኪዳን ውስጥ
አንደኛው "... ልጁን በአንቺ ስም የጠራውን በመንግሥተ ሰማያት
የበለጠና የከበረ ስምን እኔ እሰጠዋለሁ" የሚል ነው፡፡
🙏የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን🙏
4 374
ዲያው ሰማዕታቱ ከእሳቱ ውስጥ ሆነው
እግዚአብሔርን በሰላም ሲያመሰግኑ አዩአቸውና እጅግ ተደነቁ፡፡ ቅድስት
አርሴማም በዚያ ላሉት ሁሉ ወደፊት በንጉሡ ላይ የሚሆነውን ነገር
በትንቢት ነገረቻቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ድርጣድስ ቅድስት አርሴማን እንደበቀሉለትና
እንዲያጠፉለት ወደ አማላከቶቹ ቤት ይወስዷት ዘንድ የሠራዊቱን አለቆች
አዘዛቸው፡፡ ወደ አማልክቶቹም ቤት በወሰዷት ጊዜ በዚያ ሆና ስትጸልይ
በወንዶች አምሳል የተሠሩ 77 እና በሴቶች አምሳል የተሠሩ 33 ጣዖታት
ሁሉ ተሰባበሩ፡፡ ከአንገታቸው የተሰበሩ አሉ፣ እግሮቻቸውና እጆቻቸው
የተሰበሩ አሉ፣ ወገባቸው የደቀቁ አሉ፣ እንደትቢያም የተነተኑ አሉ፡፡
በምድርም ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም
እንደመብረቅ ባለ ድምጽ መጥቶ ምድሪቱን መላትና በዚያ ያሉ ጣዖታት
በሙሉ እንደትቢያ ጠፉ፡፡ ቅድስት አርሴማም ይህንን ባየች ጊዜ ደስ
ተሰኝታ የሆነውን መጥቶ ያይ ዘንድ ወደ ንጉሡ ላከችበት፡፡ ንጉሡም በመጣ
ጊዜ ‹‹አምላኬ መልአኩን ልኮ አዳነኝ፣ ጣዖታቶችህንም እንዳልነበሩ
አደረጋቸው እህግዲህስ እፈር›› አለችው፡፡ ንጉሡም ‹‹በምትሃትሽ ይህንን
እንዳደረግሽ ዐውቀለሁ›› አላትና ወደ እስር ቤት ወስዶ ከሰማዕታቱ ጋር
ጨመራት፡፡
ሰማዕታቱም በእስር ቤት ሆነው እህልና ውኃ ከቀመሱ ሰባት ቀን
ሆኗቸዋልና ርሀቡና ጥሙ እጅግ ጠናባቸው፡፡ ያንጊዜም ቅድስት አርሴማ
ተነሡ እንጸልይ አለቻቸውና ቢጸልዩ ብርናኤልና አቅናኤል በሚባሉ ሁለት ቅዱሳን መላእክት እጅ ሰማያዊ ኅብሥትባ የገነት ውኃ መጣላቸው፡፡
ከመካከላቸውም ካህኑ ኢያሴኖስ ባርኮ ለሌሎቹ ሰማዕታት ሰጣቸውና
ተመግበው ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ፡፡ የተረፋቸውም ኅብሥት በመላአክቱ
እጅ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
በማግሥቱም ንጉሡ ወደ ፍርድ አደባባይ ባወጣቸው ጊዜ ሰማዕታቱ
ፊታቸው እንደፀሐይ ያበራ ነበር፡፡ የእሥር ቤት ጠባቂውንም ጠርቶ ‹‹እህል
ያበላሃቸውና የነገሥታትን ልብስ ያለበስካቸው ለምንድነው?› ብሎ
ተቆጣው፡፡ ጠባቂውም ‹‹ጌታዬ ሆይ እነርሱስ ሳይበሉ ሳይጠጡ ይረካሉ
እንጂ የሰጠኃቸው ምንም ነገር የለም›› አለው፡፡ ቃሉንም በመሐላ ካጸናለት
በኋላ ‹‹ነገር ግን ንጉሥ ሆይ በሌሊት እሥር ቤት በብርሃን ተጥለቅልቆ
አይቼዋለሁ፡፡ ዳግመኛም ሃያ ሰባት የብርሃን አክሎችም ሲወርዱ አየሁ››
አለው፡፡ ቀጥሎም ይህ ጠባቂ ‹‹ንጉሥ ሆይ እኔም በእነዚህ ሰማዕታት
አምኛለሁ›› አለው፡፡ ወደ ቅድስት አርሴማም ዞሮ ‹‹እመቤቴ ሆይ በጸሎትሽ
አስቢኝ›› በማለት ሌሎቹንም ሰማዕታት ተመጸናቸው፡፡ ንገሡም በዚህ
እጅግ ተቆጥቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ እርሱም በጣዖት የሚያመልክ
አረማዊ ቢሆንም አምኖ በደሙ ተጠምቋልና የሰማዕትነትን የክብር አክሊል
ተቀዳጀ፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ሰማዕታቱም ይህን አደነቁ ሰማዕትነትን በመፈጸም
ቀድሟቸዋልና፡፡ በድኑንም በምድረ በዳ ጣሉት ነገር ግን አውሬዎችና
አሞራዎች አልበሉትም ቅዱሳን መላእክት ይጠብቁታልና፡፡
ንጉሡም ሰማዕታን በጽኑ ዱላዎች ካስደበደባቸውና ለእያንዳንዳቸው ሌላ
ሦስት ሦስት መቶ ግርፋት ካስገረቸው በኋላ ወደ እሥር ቤት መለሳቸው፡፡
በመግስቱም ቅድስት አርሴማን አስመጥቶ ከእርሱ ጋር ትሴስን ዘንድ
አባበላት፡፡ ‹‹ንግሥት አድርጌሽ በወርቅ ዙፋኔ ላይ ትቀመጫለሽ፣
በአርማንያ ካሉ ሴቶች ሁሉ በላይ አደርግሻለሁ…›› እያለ አባበላት፡፡
ቅድስት አርሴማ ግን ‹‹ልብህ የደነደነ ሰነፍ ሆይ ኃጢአትህን ሁሉ ይቅር
ይልህ ዘንድ ወደ አምላክህ እግዚአብሔር ትመለስ ዘንድ በተሻለህ ነበር
…›› እያለች አስተማረችው፡፡ ስለ ጌታችንም መንገሥት ካስተማረችው
በኋላ ‹‹እኛ ሰማዕታቱ ስለ አንተ እንጸልይልሃለን›› አለችው፡፡ ንጉሡ በዚህ
ጊዜ ‹‹ማመኔን ብትወጂ ግን ከእኔ ጋር ተስማምተሽ እንጋባለን
ለአምላክሽም እገዛለሁ›› ሲላት ወዲያው እርኩስ መንፈስ ፊቱን መታውና
‹‹ከእናትህ መኅፀን ጀምሮ ያሳደኩህና በሥራህ ሁሉ ልብ፣ አፍና ብርታት
ሆኜ በኃይሌም ብርታት የክርስቲያን ልጆችን እንድታስጨንቃቸውና
እንትገድላቸው ያደረኩህን እኔን ለምን ተውከኝ? ስለዚህች ሴት ብለህ
እግዚአብሔር አምላክን ታመልክ ዘንድ ወደድክን! ...›› እያለ በቁጣ ሆኖ
አፉን አጣመመውና ምድር ላይ ጣለው፡፡ ከዚህም በኋላ ለጣዖታቱ ይሰግዱ
ዘንድ ሰማዕታቱን በቁጣ አዘዛቸው፡፡ ነገር ግን የጣዖታቱ ካህናት መጥተው
ጣዖታቱን ቅድስት አርሴማ እንዳጠፋቻቸው ነገሩት፡፡ ዳግመኛም ‹‹እርሷን
ካልገደልካት አገራችን ትጠፋለች፣ መንግሥትህ ተሻራላች›› አሉት፡፡
ከዚህም በኃላ ከቅድስት አርሴማ ጋር ያሉትን 27ቱን ሰማዕታት ስሙ
ጋብጋቦ ወደሚባል ወንዝ ወስደዋቸው አንገታቸውን በሰይፍ ቆረጧቸውና
የሰማዕትነት ፍጻሜአቸው ሆነ፡፡ ከእነርሱም አንደኛውን በቅድሚያ አንገቱን
ሲቆርጡት ሥጋው ወደ ምድር ወደቀ፡፡ ራሱ ግን ለብቻ ለአንድ ሰዓት ያህል
ቆመች፡፡ ቡርክት ቅድስት አርሴማም ሮጣ ሄዳ የሰማዕቱን በርቲኖስን ራስ
ያዘቻትና ወደ አንገቱ መለሰቻት፡፡ እርሱም "ሰማዕት ለመሆን እኔን
ስላስቀደመ አምላኬ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" እያለ ሦሰት ጊዜ
ተነፈሰ፡፡ ለቅድስት አርሴማም "እመቤቴ ሆይ መምጣትን እንዲያፋጥኑ
ከፀሐይ ይልቅ የምታበራ አገርን እንዲያዩ ለወንድሞቻችን ለእኅቶቻችን
ነገሪያቸው" አላት፡፡ እርሷም ወደ ሰማዕታቱ ዞራ "ወንድማችን በገነት
ያየውን ይነግረንና ያሳየን ዘንድ በሕይወት ኖሯል እንጂ አልሞተም"
አለቻቸው፡፡
ከዚህም በኃላ ሰማዕታቱ እግዚአብሔርን አመስግነው "እኔ አስቀድሙ እኔ
አስቀድሙ..." እያሉ ወታደሮቹን ለመኗቸው፡፡ እየተሻሙ በየተራ እየተሰየፉ
ሰማዕትነታቸውን ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ የእነዚህም የ27ቱ
ክቡራን ሰማዕታት ስማቸው ይህ ነው፡- ካህኑ ኢያሚኖስ፣ አፍጢኖስ፣
በርቲኖስ፣ ጢሞና፣ ጢሞዓና፣ ዘኬዎስ፣ እስጢፋኑ፣ አርሞና፣ ኪርያኮስ፣
አንጥያኮስ፣ ያዕቆብ፣ ቡራኬሌስ፣ አስቂርያቆስ፣ አስኪርያኖስ፣ ሚርያኖስ፣
ትትግርጦስ፣ ያስቲኖስ፣ ጥልያኖስ፣ ዑልያኖስ፣ ጴርቅላስ፣ ኬብያኖስ፣
ጴጥሮስ፣ ጳክንዮስ፣ ሐናንያ፣ ሐሊባኖስ፣ ኤስያኖስ እና ኤልያብ ናቸው፡፡
ቅድስት አርሴማም የሰማዕታቱን ራሶቻቸውን ትሰበስብ ነበር፡፡ ወደ
ሥጋቸውም ታጋጥመው ነበር በዚያም ጊዜ እንደመጀመሪያው ይሆናል፡፡
እንዳልተቆረጠም ይሆናል፡፡ ልብሶቻቸውንም ታለብሳቸዋለች፡፡ ይህንንም
ታላቅ ተአምር ያዩ 92 የንጉሡ ወታደሮች ወደ ንጉሡ ሄደው "እኛም
በአምላካቸው አምነን ክርስቲያን ሆነናል" በማለት መሰከሩ፡፡ ንጉሡም
በፈረስ ገመድ ላይ አስሮ ሥጋቸው ተቆራርሶ እስኪወድቅ ድረስ
ካሠቃያቸው በኃላ አንገታቸውን ሰየፋቸውና የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡
ዳግመኛም በእነርሱ ምክንያት ሌሎችም አመኑ፡፡ ከዚህም በኃላ ንጉሡ
ቅድስት አርሴማን ውበቷን እያሰበ ልቡናውን ሳተ፡፡ ድንግልናዋንም
ሊያረክስ ሽቶ እናቷን አጋታን እንድታባብልለት አዘዛት፡፡ እናቷም ሄዳ "ልጄ
ሆይ ስሚ ይህ አረማዊ እንዳያረክስሽ ተጠንቀቂ" አለቻት፡፡ ንጉሡም
ቅድስት አርሴማን "መንግሥቴንና ግዛቴን ሁሉ አወርስሻለሁ" እያለ በመሀላ
ቢለምናትም እሺ እንደማትለው ሲያውቅ ይዞ በግድ ወደ እልፍኙ
ሊያስገበት ሲል ቅድስት አርሴማ ይዛ መሬት ላይ ጣለችው፡፡ በእርሷ ላይ
ያደረ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሞገስ ሆኗታልና፡፡
እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የበረታ ኃይለኛ ስለነበረ አሁን በታናሽ ሴት
ብላቴና ስለተሸነፈ አፈረ፡፡ በዚህም እጅግ ተናዶ ለሥጋዊ ፈቃዱም
እንደተመኛት ሊያገኛት ስላልቻለ ተስፋ ቆርጦ በንዴት አንገቷን ይቆርጧት
ዘንድ አዘዘ፡፡ የቅድስት አርሴማንም ራሷን ቆረጧትና የሰማትነት ፍጻሜዋ
ሆነ፡፡ ከአንገቷም ደም፣ ውኃ
4 374
እግሮቻቸውንና እጆቻቸውን እንዳሠሯቸው ለንጉሥ ድርጣድስ
አስረኩቧቸው፡፡ መኮንኑም ለንጉሡ ‹‹ጌታዬ ሆይ እነሆ አንተ
የምታመልካቸውን ጣዖቶችህን የማያመልኩትን ብዙ ክርስቲያኖችን
ሰቀልናቸው፣ ገደልናቸው፡፡ የቀሩትንም እየገረፍን ይኸው ከፊትህ
አቁመናቸዋል የወደድከውን አድርግባቸው፡፡ አንዲትም ውብ ሆነች ሴት
ልጅ አብራቸው መከራ መቀበልን መርጣ መጥታለች የመልኳንም ማማርና
ደም ግባቷን ባየን ጊዜ ደንግጠን በእርሷ ላይ አንዳች ክፉ ማድረግ
አልተቻለንም›› አለው፡፡ ንጉሡም ያመጧት ዘንድ ሲነግረው መኮንኑ ‹‹ነገር
ግን ጌታዬ ሆይ እርሷ በመልክ የሚስተካከላት የሌለ እጅግ ውብ
ብትሆንም ‹ከሕይወት ይልቅ መሞት ይሻለኛል› ይምትል ናት›› አለው፡፡
ከዚህም በኋላ ሰማዕታቱን ወደ እሥር ቤት በመውሰድ ቅድስት አርሴማን
ግን ይዘው ወደ ንጉሡ ዘንድ አመጧት፡፡ እርሷም ወደ ንጉሡ አዳራሽ
እያማተበች ስትገባ ንጉሡ ባየት ጊዜ ልቡ ታወከ፡፡ ሰማዕቷ ግን
‹‹ከሰማያትና ከምድር ንጉሥ ከእግዚአብሔር አምላኬ ትለየኝ ዘንድ
የወደድክ ሰነፍ ንጉሥ ሆይ! የሰይጣን መልአክተኛና የጥፋት ልጅ የይሁዳ
ወገን ከእኔ ምን ትሻለህ? ከወደድክስ በእጅህ ሰማዕት እሆን ዘንድ
እወዳለሁ›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰማዕቷ በጸለየች ጊዜ ቅዱስ
ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ተገለጡላት ነገር ግን ቅድስት
አርሴማ ‹‹ጌቶች ሆይ! ነፍሰ ገዳይ እንዳልባል በማንም ላይ ጥፋት
አይድረስ›› ብላ ለመነቻቸው፡፡ ሊይዟት የመጡት ሰዎችም ግርማዋን አይተው ፈሩ፡፡ ሰውነቷንም ቀርበው እንዳይነኳት የመለኮት ኃይል
ከለከላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ይህች ሴት አስማተኛ ናት፣ ጥበብና ምትሃት
አላት›› ብለው ለንጉሡ በነገሩት ጊዜ እርሱም ‹‹ዛሬ ያሸነፍሽኝ
እንዳይመስልሽ ነገ ብርቱዎች በሆኑ አማልክቶቼ ኃይል ድል አደርግሻለሁ››
አላት፡፡ እርሷም ‹‹ዛሬም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ይረዳኛል፣ በእኔ
በኃጢአተኛይቱና በደካማይቱ ኃይል አይደለም፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት
የጸሎት ኃይል እንጂ›› በማለት መለሰችለት፡፡ ሰማዕታቱም ከቅድስት
አርሴማ ጋር በእሥር ቤት ሳሉ ‹‹የእግዚብሔርን ኃይል በአንቺ ላይ
አይተናልና በጸሎትሽ አስቢን›› አሏት፡፡ እርሷም ‹‹በገድላችሁ ብርታት ለእኔ
ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ቅድስት አርሴማ ሌሊት ታላቅ ምሥጢርን አየች፡፡
እልፍ አእላፋት የብዙ ብዙ የሚሆኑ ቅዱሳን መላእክት የሥላሴን ዙፋን
ከበው ‹‹የጌትነትህ ምስጋና ሰማይንና ምድርን መላ ፍጹም አሸናፊ
እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ ሲጮኹ ተመለከተች፡፡ ይህንንም
የመላእጅትን ዜማ እንደሰማችና እንዳየች ለሰማዕታቱ ነገረቻቸው፡፡
‹‹ከእነዚህም መላእክት ውስጥ አንዱ ወደ እኔ ተልኮ መጣና በቀኜ ቆሞ
በጥላው ሸሽጎ የሕይወትን እንጀራ መግቦኝ የድኅነትን ጽዋ አጠጣኝ፡፡
ያንጊዜም ሥጋዬ ወደ ምድር ወረደ፣ በላዬም ነፍሴ ተመለሰቸ፡፡ ከእንቅልፍ
እንደሚነቃና የወይን ጠጅ ጠጥቶ ስካሩ እንደተወው ሰው ነቃሁ›› አለቻው፡፡
በነጋም ጊዜ ንጉሡ በፍርዱ ዙፋን ተቀምጦ ሰማዕታቱን ከእሥር ቤቱ
አውጥተው ወደ ፍርድ አደባባይ ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ በፊቱም አቁሞ
ለጣዖታት አማልክቶቹ እንዲሰግዱና እንዲሠው አዘዛቸው፡፡ እነርሱም
‹‹እኛስ የምናመልከው እውነተኛ አምላክ አለን ለረከሱ ጣዖታት አንገዛም››
ባሉት ጊዜ ‹‹ትእዛዜን ካልፈጸማችሁ ሰውነታችሁን በትንሽ በትንሹ
እየቆራረጥኩ እጥለዋለሁ›› አላቸው፡፡ ሰማዕታቱም ‹‹በሚያስፈራ ቃልህና
በቅጣትህ የምንፈራና አምላካችንን ክርስቶስን የምክደው አይደለንም፡፡ ስለ
አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳችንን እንሰጥ ዘንድ ወደ አንተ
መጥተናል›› አሉት፡፡ ያን ጊዜም ንጉሡ ድርጣድስ እጅግ ተቆጥቶ ‹‹ይህችን
ሴት በማስቀደም ጽኑ ቅጣት ቅጧቸው የምታስተምራቸው እርሷ ናትና››
ብሎ አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም ‹‹የሴት ልቧ ደካማ ነውና ቅድሚያ ወንዶችን
አሠቃይተን ብንገድል ሴቶቹ ለጣዖቶችህ ይገዛሉ›› በማለት ወንዶቹን ለብቻ
ወስደው ለተራቡ አንበሶችና ሌሎች አውሬዎች ሰጧቸው፡፡ ቅድስት
አርሴማም አጽናናቻቸውና ተሰነባብተው ወደ ሰማዕትነት ገቡ፡፡ ነገር ግን
የተራቡት አንበሶችና ሌሎችም አውሬዎች ወደ ሰማዕታቱ መቅረብ
አልተቻላቸውም ይልቁንም በሰማዕታቱ ፊት ሰገዱላቸው፡፡ በጅራታቸውም
እየዳሰሷቸው አጫወቷቸው፡፡ የቅድስት አርሴማንም የእግሯን ትቢያ ላሱ፡፡
እርሷም በእጆቿ ዳሰሰቻቸው፡፡ አውሬዎቹም ብረቱን እየበጠሱ ንጉሡ
ከመንግሥቱ ዙፋን እስኪወድቅ ድረስ አባረሩት፡፡ ወታደሮቹንም
ሲያባርሯቸው ከእነርሱ ውስጥ 300 ጭፍሮች ሞቱ፡፡ የተረፉትም ይህንን
ተአምር ሲያዩ እጅግ እያደነቁ ሰማዕታቱ ምትሃተኞች መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ይልቁንም ቅድስት አርሴማን ‹‹እርሷ መመኪያቸውና መሪያቸው ናትና
አስቀድመን እንግደላት›› አሉ፡፡
ከዚህም በኋላ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳትን አንድደው
ሰማዕታቱን ከዚያ ይጨምሯቸው ዘንድ ሲመክሩ ንጉሡ በዚህ ምክራቸው
ደስ ተሰኘ፡፡ እንደምክራቸውም ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳት
አንድደው የተለያዩ ሰውነትን ቆራርጠው የሚጥሉ እንደ ዲን፣ ሙጫ፣
ቅንጭብ ጨምረው የእሳቱ ነጎድጓድ እስኪሰማ ድረስ አንድደው
ሰማዕታቱን ከዚያ እንዲጨምሯቸው ንጉሡ አዘዘ፡፡ ቅድስት አርሴማንም
‹‹አሁን ከዚህ ማን እንሚያድንሽ አያለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹እኛንስ
አምላካችን እንደሚያድነን አሁን ታያለህ አንተ ግን ከዚህ ክፋትህ
ካልተመልስክና ጣዖት ማምለክህን ትተው እውነተኛውን አምላክ
ካላመለክህ በኋላ ከዘላለማዊው እሳት ወዴት ትሸሻለህ? በማስ
ትማጸናለህ? በዕንጨት ነውን ወይስ በድንጋይ? …. ›› በማለት ስለ ዕለተ
ምጽዓት ሌላም ብዙ ነገር አስተማረችው፡፡ በዚህም ጊዜ ከወታደሮቹ አንዱ
ተነሥቶ በኃይል ሲመታት ከአፍንጫዎቿ ደም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡም
‹‹በዚህ የምተውሽ አይደለሽም ሥጋሽን በእሳት አቃጥለዋሁ›› በማለት
ተናገራት፡፡ ያንጊዜም ምድር አፏን ከፍታ ያንን የመታትን ወታደር ዋጠችው፡፡
ይህንንም ያዩ ሁሉ በማድነቅ እጅግ ፈሩ፡፡ ንጉሡም ፈርቶ ከዙፋኑ ላይ ፈጥኖ
ተነሣ፡፡ ቅድስት አርሴማም ፈገግ ብላ በእርሱ ይመጣ ዘንድ ያለውን ነገር
ትንቢት ነገረችው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ስለ እኛ ይበቀልሃል፣ የአጋንንትም
ማደሪያ ያደርግሃል፣ እንደ ጅብ በራስህ ሥጋህን እስከምትበላ ድረስ
ያሳብድሃል፡፡ መልክህና ምሳሌህ ይለወጣል፣ እንደ በረሃ እሪያም
ትሆናለህ፣ የምትናገረውን አታውቅም፣ የእርኩሳን አጋንንት የእግራቸው
መረገጫ ትሆናለህ፡፡ ያንጊዜም የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ ትታመን ዘንድ
አለህ ይህ እንደሚሆንብህ በእውነት እነግርሃለሁ›› አለችው፡፡ ንጉሡም
ይህን ጊዜ ‹‹እናተን በክፉ ቅጣት አሠቃይቼ ከገደልኩ በኋላ ይህን አሁን
ያልሽውን ብሆን አይሳዝነኝም›› አላት፡፡ ይህንንም ሲነጋገሩ ወታደሮቹ
መጥተው የእሳቱ ነበልባል ከሩቅ እስኪታይ ድረስ እንደነደደ ነገሩት፡፡
እርሱም ሰማዕታቱን ከእሥር ቤት አውጥተው በማምጣት ከቅድስት
አርሴማ ጋር በእቶኑ እሳት ውስጥ ይጥሏቸው ዘንደ አዘዘ፡፡ ቅድስት
አርሴማም ሰማዕታቱን ካጽናናቻቸውና ከመከረቻቸው በኋላ በመስቀል
ምልክት አማትባ ማንም ገፍቶ ሳይጨምራት ራሷን ወደ እሳቱ ውስጥ
ወረወረች፡፡ ቀጥሎም ዲያቆን ጤሜልዮስ ወደ እሳቱ ተወርውሮ ገባ፡፡
ታላቃቸው ጌርሎስም እንዲሁ ራሱን ወርውሮ ወደ እሳቱ ውስጥ ገባ፡፡
ሁሉም እንዲሁ በየተራ ራሳቸውን እየወረወሩ ገቡ፡፡ በጎች ወደ ወንዝ ውኃ
እየሮጡ እንደሚገቡ ሁሉም ሰማዕታት ራሳቸውን እየወረወሩ ወደ እቶኑ
እሳት ገቡ፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ያዩአቸው ወታደሮች ሁሉ በሀዘኔታ
አለቀሱላቸው፡፡ ነገር ግን ወ
4 374
#የታላቋ_ሰማዕት_የቅድስት_አርሴማ_ቤተክርስቲያኗ_የከበረችበትና_የሥጋዋ_ፍልሰት_የተከናወነበት_ዕለት_ነው
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
ታኅሣሥ ፮
የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ
ክርስቲያኗ የከበረችበትና የሥጋዋ ፍልሰት የተከናወነበት ነው፡፡ ከእርሷም
ጋር አብረው የተሰየፉ 27 ደናግልም የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ፡፡ (የቅድስት
አርሴማ ዋነኛ በዓሏና ዕረፍቷ መስከረም 29ን ይመለከቷል)
የቅዱስት አርሴማ አባቷ ቴዎድሮስ ከሌዋውያንና ከኃያላን ነገሥታት ወገን
ሲሆን እናቷ አትኖስያ ደግሞ ከጳጳሳት አለቆች ወገን ናት፡፡ ወላጆቿ
በሃይማኖት በምግባር ያጌጡ በበጎ ትሩፋት የተመሰገኑ ደጋግ ቅዱሳን
ናቸው፡፡ በጾም፣ በጾሎት፣ በምጽዋትና ዓሥራት በኩራትን በማውጣት
በመንፈሳዊ ሥራ ሁሉ እየተጉ ቢኖሩም ነገር ግን እስክ እርጅናቸው ዘመን
ድረስ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበር፡፡ እናቷ ቅድስት አትኖስያ እንደ ነቢዩ
ሳሙኤል እናት ሐና ጠዋት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ
በእግዚአብሔር ፊት ታለቅስ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የልቧን ፈቃድ
ይፈጽምላት ዘንድ ወደደና የቂሣርያውን ሊቀ ጳጳሳት ልድዮስን ስለ እርሷ
ይጸልይላት ዘንድ አዘዘው፡፡
ሊቀ ጳጳሳቱም ስለ ቅድስት አትኖስያ ጸለየላት፡፡ እግዚአብሔር አምላክም
የሊቀ ጳጳሳቱንና የቅድስት አትኖስያን ጸሎት ሰምቶ መልኳ እጅግ ያማረችን
ሴት ልጅ ቅድስት አርሴማን ሰጣት፡፡ እናቷም እየተንከባከበች አሳድጋት
ዕድሜዋ ከፍ ሲል አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስም ወደተሠራች
ቤተ ክርስቲያን ታገለግል ዘንድ ሰጠቻት፡፡ ቅድስት አርሴማ ወጣት በሆነች
ጊዜ ወላጆቿ ባል ያጋቧት ዘንድ ወደዱ ነገር እርሷ ይህንን ፈጽሞ
አልወደደችምና ወላጆቿን ‹‹እኔ የሰማያዊው የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ እንጂ
ምድራዊ ሙሽራ አይደለሁም›› አለቻቸው፡፡
ቅድስት አርሴማ ከእርሷ በፊትም ሆነ ከእርሷ በኋላ በመልክና በውበት
የሚመስላት የለም፡፡ ይህን ዓለም እንደትቢያ በመቁጠርና ፍጹም በመናቅ
ጌታችንን ከተከተሉት ቅዱሳት ደናግል አንስት ውስጥ በመልክና በውበት
ቅድስት አርሴማን የሚመስል የለም፡፡ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን
በቀር የሚበልጣት ማንም የለም፡፡ እርሷም በምግባር በሃይማኖት ያጌጠች
በመንፈሳዊ ተጋድሎ የበረታች በትሩፋት የበለጸገች ናት፡፡ ብሉይን ከሐዲስ
አጠናቃ ተማረች፡፡ የአገሮችንም (የሮምያን፣ የጽርዕን፣ የሶርያን፣ የኪልቅያን)
ቋንቋዎች ታውቅ ስለነበር ቅዱሳት መጻሕፍትንም ወደ ተለያዩ አገራት
ቋንቋዎች ትተረጉማለች፡፡
ቅድስት አርሴማ 15 ዓመት በሆናት ጊዜ ከሃዲውን ዲዮቅልጥያኖስን
ሰይጣን አስነሥቶት ነገሠ፡፡ ይኸውም ከሃዲ ንጉሥ ሚስት ያባ ዘንድ
በመልኳ ውብ የሆነች ሴት ልጅን ይመርጡለት ዘንድ በሀገሩ ሁሉ
እንዲሄዱ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ያገኟትንም ውብ የሆነችን ሴት መልኳን ሥለው
ያመጡለት ዘንድ ሠዓሊዎችንም አብሮ ላከ፡፡ የተላኩትም ሰዎች ወደ ሮሜ
አገር በደረሱ ጊዜ ቅድስት አርሴማ ያለችበትን የደናግል ገዳም አገኙ፡፡ ወደ
ገዳሙም ገብተው ቅድስት አርሴማን አይተዋት በመልኳ ማማር እጅግ
ተደስተው ‹‹ለንጉሡ ሚስት የምትሆነው ይህች ናት›› ብለው መልኳን
በሥዕል ቀርጸው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ሥዕሏን በተመለከተ ጊዜ
ፈጽሞ ተደሰተ፡፡ ስለ ሠርጉ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ሕዝቡን ይጠሩአቸው
ዘንድ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ሁሉ ላከ፡፡
በገዳም ያሉ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዝነው አለቀሱ፡፡
ድንግልናቸውን እንደጠበቁ ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመኑት
ከገዳሙ ወጥተው ወደ ንጉሥ ድርጣድስ የግዛት አገር ወደ አርማንያ
ደረሱ፡፡ በዚያም በምድረ በዳ ዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ ቁጥራቸውም 75
ወንዶችና 39 ደናግል ሴቶች ነበሩ፡፡ በዋሻም ውስጥ በረሃብና በጥም
እየተቸገሩ ተቀመጡ፡፡ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ቅድስት አርሴማን ፈልጎ
ባጣት ጊዜ እጅግ ቢያዝንም ነገር ግን ቆይቶ በአርማንያ እንዳለች ሰማ፡፡
እርሷንም ይዞ ይልክለት ዘንድ ወደ አርማንያው ንጉሥ ድርጣድስ መልእክት
ላከ፡፡ ድርጣድስም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይና ጨረቃን የሚያመልክ ነው፡፡
በሰው እጅ የተጠረቡ ዕንጨቶችንና ድንጋዮችንም በቤቱ አስቀምጦ
‹‹አማልክት›› እያለ በመጥራት እንደ አምላክ ያመልካቸው ነበር፡፡
በውስጡም ሰይጣን አድሮበታልና የእርሱን ጣዖታት ሕዝቡም
እንዲያመለኩ ያስገድዳቸው ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም እያሰረ በመግረፍ
ያሠቃይ ነበርና ቅድስት አርሴማ በዋሻ ውስጥ ሆና አንዱ መኮንን
ክርስቲያኖችን በመግረፍ ሲያሠቃይ ታየዋለች፡፡ ስለ ሰማዕታቱም ወደ
እግዚአብሔር ስትጸልይ የብርሃን አክሊል የያዙ ቅዱሳን መላእክት
ሰማዕታቱ ሲሰጧቸው አየች፡፡ ይህንንም ታላቅ ምሥጢር ባየች ጊዜ
‹‹አቤቱ አምላኬ ሆይ ስለስምህ እኔም ሰማዕት እሆን ዘንድ እርዳኝ››
እያለች ለመነች፡፡
ከዚህም በኋላ ወደ ሰማዕታቱ ዘንድ ስትሄድ መኮንኑ አያት ከመልኳ ማማር
የተነሣ ደነገጠና ‹‹እመቤቴ ሆይ እዛው ባለሽበት ሆነሽ ተዋቸው ብትይኝ
ፈትቼ እለቃቸው ነበር አንቺ ከዚህ መምጣት አያስፈልግሽም›› አላት፡፡
ቅድስት አርሴማም ‹‹እኔም የእነዚህን ሰማዕታት መከራ እሸከም ዘንድ
እወዳለሁ፣ የእነርሱንም የክብር አክሊል አገኝ ዘንድ እሻለሁ›› አለችው፡፡
እርሱም ‹‹እመቤቴ ሆይ አንቺስ ከመንግሥት አዳራሽ ውጭ መኖር
አይገባሽምና ለምን ይህን ከንቱ ነገር (ሞትን) ትወጃለሽ?›› አላት፡፡ ቅድስት
አርሴማም ‹‹የጎሰቆልክ ጤልሜዎስ ሆይ ለእኔስ ሰማያዊው ንጉሥ
በመንገሥቱ አዳራሽ አዘጋጅቶልኛል›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ መኮንኑ
ሰማዕታቱን ከእሥር ቤት ጣላቸውና ቅድስት አርሴማን ግን ከአጃቢዎች ጋር
በክብር አስቀምጦ ምግብ መጠጡን አዘጋጀላት፡፡ እርሷ ግን ለሰማዕታቱ
ስለ ሰማያዊው ስጦታቸው ትነግራቸው ነበር እንጂ ምግቡን
አልቀመሰችም፡፡ ከሃዲው መኮንኑም ቅድስት አርሴማን ‹‹እሽ ብለሽኝ
አንቺን ካገባሁ በቤቴ ያሉትን ሚስቶቼን ሁሉ አባርሬ አንቺን ብቻ ሚስት
አድርጌ እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ እኖራለሁ ለዚህም በትላልቅ አማልክቶቼ
ስም እምምልሻለሁ›› ብሎ መልእክተኛ ላከባት፡፡ ቅድስት አርሴማም
መልአክተኞቹን መጻሕፍትን እየጠቀሰች የዓለምን ከንቱነትና የክርስቶስን
ፍቅር አስተማረቻቸው፡፡ እርሷም የእግዚአብሔርን ቃል ስትነግራቸው
ልባቸው እየተቃጠለ ያለቅሱ ነበር፡፡ እነርሱም ‹‹በቃልሽ አምነናል ጸሎትሽ
ኃይል ይሁነን›› አሏት፡፡
መኮንኑም የቅድስት አርሴማን መልስ በሰማ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ
ሰማዕታቱን ይዞ በማሠቃየት የበላዩ ወደ ሆነው ወደ አርማንያው ንጉሥ
ድርጣድስ ዘንድ እንዲወስዷቸው አዘዘ፡፡ የአገሩ ሰዎችም ቅድስት አርሴማ
ሰማዕት ትሆን ዘንድ ፈቅዳ ወደ ንጉሡ ዘንድ እንደሄደች ለእናቷ ለአትኖስያ
ነገሯት፡፡ እናቷም መጥታ ‹‹ልጄ ሆይ ወደሞት ለምን ትሄጃለሽ? ወደ ሞት
መሄድሽን እያየሁ አሁን ልቤ እንዲህ በሀዘን ከሚሰበር መነው መጀሪያውኑ
ባልወለድኩሽ ይሻለኝ ነበር›› አለቻት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን የክርስቶስን
ፍቅር ለእናቷ አስረዳቻት፡፡ በኪልቂያ አጋታ ብለው የሚጠሯት ወላጅ እናቷ
አትኖስያም ‹‹አስተማሪዬ ልጄ አርሴማ ሆይ! እባክሽ እሺ በይኝ…›› እያለች
ብዙ ብትለምናትም ቅድስት አርሴማ ግን እናቷንና የአገሯን ሰዎች
ተሰናብታ ስትሄድ ሁሉም እያለቀሱ ሸኟት፡፡ በመንገድም ሳለች ቅድስት
አርሴማን ወደ ንጉሥ ድርጣድስ የሚወስዷት ጭፍሮች ከሰማዕታቱ ጋር
ሄዳ ሰማዕት ከምትሆን ይልቅ ወደ እናቷ መመለስ ብትፈልግ
እንደሚመልሷት ነገሯት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ከሰው ፍቅር ይልቅ የእግዚአብሔር
ፍቅር ይበልጣል›› አለቻቸው፡፡
ሰማዕታቱም አርማንያ አገር እንደደረሱ ጭፍሮቹ የሰማዕታቱን
4 374
#በእንተ_ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
፩. #በኮከብ_መጽኡ
በኮከብ መጽኡ(፪) ሰብአ ሰገል
ለአማኑኤል(፬) ይስግዱ ለአማኑኤል
፪. #ቤዛ_ኩሉ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፪)
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፬)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፪)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፬)
፫. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል(፪)
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ(፪)
፬. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል ረኪቦሙ ህፃነ ህፃነ(፪)
ዘተወልደ ለነ(፬) ህፃነ ዘተወልደ ለነ
፭. #በቤተልሔም_ተወልደ
በቤተልሔም ተወልደ(፪) አማኑኤል
እምዘርአ ዳዊት (፬) ተወልደ አማኑኤል
፮. #ተወልደ_ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም(፪) ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ(፪) በቤተልሔም
፯. #ወወለደት
ወወለደት ወልደ ዘበኩራ(፪)
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ(፬)
፰. #ለዘተወልደ
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሎ ናስተማስሎለመድኀኒነ
አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ(2) ከራድዮን
፱. #ስብሐት_ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለእግዚአሔር በሰማያት(፪)
ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ ሃሌሉያ(፫)ሃሌ(፪)ሉያ
፲. #አማን_በአማን
አማን በአማን(፪) መንክር(፪)
መንክር ስብሐተ ልደቱ(፬)
እውነት በእውነት(፪) ድንቅ ነው (፪)
ድንቅ ነው የጌታ ልደቱ(፬)
፲፩. #ይትፌስሃ
ይትፌስሃ አድባረ ጽዮን ወይትሀስያ አዋልደ ኢትዮጵያ
እስመ ተወልደ ብኁተ ልደት መድኀኔዓለምበኢየሩሳሌም መድኀኔዓለም
፲፪. #ዮም_ሰማያዊ
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል
ርዕይዎ ኖሎት (፪)አእኮትዎ መላእክት(፪)
፲፫. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል(፪)ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ
ወይቤላ(፪) እስመ ረከብኪ ሞገሰ በሀበ እግዚአብሔር
፲፬. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል/፪/ ወርቀ ወሜላት
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም
፲፭. #ለድንግል
ለድንግልገብርኤል አብሰራ
ሚካኤል/፪/በክነፍ ጾራ/፪/መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
፲፮. #ሊቀ_መላእክት
ሊቀ መላእክት ገብርኤል ዘአብሠራ ለድንግል
ኃያል ኃያል/፬/ ሰዳዴ ሳጥናኤል ኃያል ገባሬ ኃይል
፲፯. #መጽአ_ከመ_ይቤዙ
መጽአ ከመ ይቤዙ ዓለም
የሀበነ ሰላመ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ
፲፰. #በጎለ_እንስሳ
በጎለ እንሰሳ
በጎለ እንሰሳ ተወልደ አማኑኤል
፲፱. #ብርሃን_ዘመፅአ
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፪)
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፬)
፳. #ኢየሱስ_ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ መፅአ ውስተ ዓለም
በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ
፳፩. #መድኀኒነ
መድኀኒነ ተወልደ ነዋ መድኀኒነ ተጠምቀ ነዋ(፪)
ይዕዜኒ ለሰላም ንትልዋ(፬)
፳፪. #ኢየሩሳሌም_በሆን
እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
እንደ እረኞች ወይ ሰብአ ሰገልን በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
፳፫. #በጎል_ሰከበ
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም(፪)ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት(፪) ዛሬ ተወለደ
፳፬. #እም_ሰማያት
እም ሰማያት ወረደ ወእማርያም ተወልደ(፪)
ከመይኩን ቤዛ(፪) ለኩሉ ዓለም ለብሰ ሥጋ ማርያም
ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ
እንዲሆነን ቤዛ(፪)ለዓለሙ ሁሉ ተዋሐደየማርያምን ሥጋ
፳፭. #የምስራች
የምስራች ደስ ይበለን(፪)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
የምሥራች ደስ ይበለን(፪)
ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን(፪)
ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ(፪)
ሰብአ ሰገል እንደታዘዙት
በኮከብተመርተው ህፃኑን አገኙት(2)
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው
ወርቅዕጣን ከርቤውንም ሰጥተው(2)
፳፮. #ይኸው_ተወለደ
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ(3)
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(3)
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ይዘው(3)
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው(3)
ህፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት(3)
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት(3)
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደእነግዳ(3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(3)
፳፯. #ሳርቅጠሉ_ሰርዶው
ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ
የታደሉ እረኞች ያደሩ በትጋት
ብርሃን ሆነላቸው በእኩለሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሰራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት
እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምስራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
የሩቅ ምስራቅ ሰዎችሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢያትም ጠፋ
፳፰. #አንቺ_ቤተልሔም
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
በአንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት
ለአዳም ክብር ሲሻ ቤተልሔም
ለሁሉም ሰላም ”
ዛሬ ተወለደ ”
ከድንግል ማርያም ”
እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም
የምሥራቅ ነገሥታት ”
በከብቶች በረት ”
ተኝቶ ላገኙት ”
እሥራኤል ሕዝቤን ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው ”
ከአንቺ ይወጣል ብሎ ”
እንደ ነገራቸው ”
፳፱. #እሰይ_እሰይ_ተወለደ
እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን ”
መች ትገኝ ነበረ ”
ገነት ምድራችን ”
ብርሃን ወጣላቸውእሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ ”
በጨለማ ጉዞ ”
እንዲያ ሲሰላቹ ”
እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ ”
ወገኖቹን ሊያድን ”
ከኃጢአት ቁራኛ ”
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን ”
እርሱ ወዷልና ”
እንዲሁ ዓለሙን ”
፴. #አዳምን_ያልተወው
አዳምን ያልተወው እንደተሰደደ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ (፪)
አምላካችን መድኃኒታችን
ተወለደ ለነፃነታችን(፪)
አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ (፪)
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ(፪)
ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ
የወይን ጠጅ ሆነ ውሃው ተለውጦ (፪)
እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ (፪)
ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተአምር
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉ ፍጡር (፪)
4 374
በእርጅናዋ ጊዜ መፀነሷን የተመለከቱ ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች
ተገርመው እየመጡ ይጠይቋት ነበር፡፡ እመቤታችን ማርያም በፅንስ እያለች ብዙ
ታምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳባን
ልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መጸነሷን ለማረጋገጥ ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡
እርሷም ሳታስበው ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ እመቤታችንም በተፀነሰች በ9
ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች፡፡ ሦስት ዓመትም
በሆናት ጊዜ እናትና አባቷ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ስዕለታቸውን አስበው
የአምላክ እናት ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ይሰጧት ዘንድ በዚህች ዕለት
ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዷት፡፡
የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ከበዓሏ ረድኤት በረከት ትክፈለን!
👇👇👇👇🙏🙏🙏👇👇👇👇
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾🌾🌾 #በዓታ_ለማርያም 🌾🌾🌾
የብርሃን እናቱ የድንግል ወላዲተ አምላክን የትውልዷን ነገር እንዲህ ነው፡- ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ የከበሩ ደጋግ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው በሕገ እግዚአብሔር ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱም በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ስለነነበሩ የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ቀን ጴጥርቃ ቴክታን እንዲህ አላት፡- ‹‹እህቴ ሆይ! ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? ልጅ የለን የሚወርሰን፣ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወንድሜ ሆይ! አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን?
ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ›› ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ
ላደርገው በልቦናዬም እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ እርሷም‹‹አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም፣ ትላንትና ማታ በህልሜ
ነጭ ጥጃ ከማኅፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ
እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፣ ጨረቃዋም
ፀሐይን ስትወልድ አየሁ›› አለችው፡፡ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሔዶ
የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ ‹‹እግዚአብሔር በምሕረቱ
አይቷችኋል፣ በሳህሉ መግቧአችኀል፣ 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች
ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፤ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ
ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሐይ
ነገር ግን አልታወቀኝም›› አለው፡፡
ጴጥርቃም ሕልም ፈቺው የነገረውን ሁሉ ሔዶ ለሚስቱ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እንጃ
አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል!?›› ብላ ዝም አለች፡፡ ከዚያም
ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ
ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች፣ በስምንተኛ ቀኗም
ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና
አለቻት፣ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፣ ሲካርም እንዲሁ ሴት
ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፣ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት፣
ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን
እመቤታችንን የምትወልደውን ሐናን ወለደች፡፡
ይህቺም ሐና በሥርዓት አድጋ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ
መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት፡፡
እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ እነርሱም
እጅግ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡
ወደ ቤተመቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው
ይለምኑት ነበር፡፡ መብዓ ይዘው ለሊቀ ካህኑ ሲሰጡት ሊቀ ካህኑም እንኳ ሳይቀር
‹‹እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ
የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መብዓችሁን አልቀበልም›› ብሎ በእጅጉ
አሳዝኗቸዋል፡፡ በሊቀ ካህኑ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ
ዛፍ ሥር ተቀመጠው ሳለ እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተው
‹‹ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ
የምትሰጠን?›› ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡
ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት
አይታ ‹‹አቤቱ ጌታዬ ለዚች እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ
ነሳኸኝ?›› እያለች ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው
ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ
ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም
ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ
እንድትኖር እንሰጣለን›› ብለው ስዕለት ገቡ፡፡ ዘካርያስም ‹‹እግዚአብሔር
ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ የልቦናችሁን ሀሳብ
ይፈጽምላችሁ›› ብሎ አሳረገላቸው።
ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር
አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም ‹‹7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ
ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ››
አላት፡፡ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ
ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ
አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል
ነው፡፡ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው ምልአቱ ስፋቱ ርቀቱ
ልዕልናው ናቸው፡፡ ሐናም ‹‹እኔም ደግሞ አየሁ እንጂ›› አለችው፡፡ ‹‹ምን አየሽ?››
ቢላት ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ
አየሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፤ ነጭነቱ
ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ
ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን
በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷን ነው፡፡
ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡
እነርሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ
አልተገናኙም ይልቁንም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን
‹‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት›› ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ ይልክልን
የለምን?›› ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው
ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ‹‹‹ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች
ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ› ብሎሏችኀል ጌታ›› ብሎ
መልአኩ ለቅድስት ሐና ነገራት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምን እና ሳራን
የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሐና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት
የሆነችውን እና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ ትኖር የነበረች
የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጎም ጌታ
የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7
ቀን በ16 ዓ.ዓ ተፀነሰች፡፡
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው
ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ፤ እነርሱም
እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡ ቅድስት ሐናም
የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ
ቆዯአት፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ
ሳይል ብድግ ብሎ ተነሥቶ "ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ
ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ"
ብሎ ሰገደላት፡፡ አይሁድም ይህ ተአምር ሲደረግ ከዚያው ነበሩና "ምነው ሳሚናስ
ምን አየህ? ምን ትላለህ?" ቢሉት "ከዚች ከሐና ማኅፀን የምትወለደው ሕፃን
ሰማይ ምድርን አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ
ሲያመሰግኗት ሰማሁ" አላቸው፡፡ ዳግመኛም "እኔንም ያነሣችኝ የፈወሰችኝ
ያዳነችኝ እርሷ ናት" አላቸው፡፡ አይሁድም "በል ተወው ሰማንህ" ብለው ቅናት
ጀመሩ፡፡ ሐና
4 374
#ኢያቄም_ወሐና
ኢያቄም ወሐና እናት አባትሽ ቤተ እግዚአብሔር ወስደው ስዕለት የሰጡሽ መና ከሰማያት የወረደልሽ እፁብ ድንግል የሆንሽ ማርያም አንቺ ነሽ(፪)
ኦ(፬) እመ ክርስቶስ ማርያም አንቺ ነሽ (፪)
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
" #ልደቱ_ለነቢዩ_ኤልያስ "
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉ታህሳስ 1 ቀን
✞ ኤልያስ ማለት ዕፀ ዘይት ማለት ሲሆን ትውልዱ ከነገደ ሌዊ ነው:: አባቱ
ኢያሴንዩ እናቱ ቶና ይባላሉ ቁጥሩ ከቀደምት ነቢያት ነው ሰውነቱ በጸጉር
የተሸፈነ መልከ ቀና ነው::
በአጽርቅተ እሳት ተጠቅልሎ ነው የተወለደው በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበረ {1ኛ ነገ፡1፥8}
✞ በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከቃል ነቢያት አንዱ የሆነና ንጉሡ አክአብንና
ንግሥቲቱ ኤልዛቤልን በድፍረት የገሰጸና የጣዖት በዓላትንና አምልኮን
በማጥፋት ሰማይን የለጎመ ታላቅ ነቢይ ነው::{1ነገ17:-1}
✞ ጊዜ ዕርገቱ ሲደርስ ኤልሳዕን "ወደ ቤቴል እሄዳለሁ ከዚህ ቆይ" አለው::
"ሕያው እግዚአብሔርን አልለይህም" አለዉ:: ቤቴልም ሲደርሱ "ወደ ኢያሪኮ
እሄዳለሁ ከዚህ ቆይ" አለው "አልለይህም" አለ ኢያሪኮም ሲደርሱ "ዮርዳኖስ እሄዳለሁና ከዚህ ቆይ" አለው:: "አሁንም አልለይህም" ብሎ ተከተለው ዮርዳኖስን በመጎናጸፊያው ከፍሎ ተሻገሩ::
ኤልያስም:-ኤልሳዕን "ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን"
አለው:: ኤልሳዕም "መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ"
አለ::
ኤልያስም:-"አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል ነገር ግን ከአንተ ዘንድ በተወሰድኩ ጊዜ
ብታየኝ ይሆንልሃል አለዚያ ግን አይሆንልህም"አለው::
ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ እነሆ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በሁለቱ
መካከል ገብተው ከፈሏቸው ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ወደ ሰማይ
ወጣ::
ኤልሳዕም:-"አባቴ አባቴ ሆይ" ብሎ ጮኸ ኤልያስም መጎናጸፊያውን ከሁለት
ተርትሮ አንዱን ጥሎለት አረገ:: {2ኛ ነገ፡2፥1-14}
☞ ኤልሳዕ የመምህሩ የኤልያስን ዕፅፍ ድርብ መንፈስ ቅዱስ ተቀበለ
በመጠምጠሚያውም መትቶ የዮርዳኖስን ባህር ከፈለ ፣ የመጥረቢያውንም
ብረት በውሀ ላይ እንዳንሳፈፈው ፣ ብዙውንም ተአምራትን አደረገ ፡፡
ሙት አነሳ በግዮን ውሀም ነምፃሙን ንዕማንን አነፃው፡፡
☞ የነቢዩ ኤልያስ # ዕርገቱ ጥር 6 ቀን ነው፡፡
🙏የነቢዩ ኤልያስ ረድኤት በረከት ምልጃ ጸሎት ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን
ጋር ይሁን አሜን::🙏
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር✝
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
