የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
رفتن به کانال در Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
نمایش بیشتر4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
4 374
✞ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ✞
•••✞✞✞••ማርያም••ማለት••✞✞✞•••
#ማ__ማኅደረ_መለኮት ማለት ነው።
#ር__ርግብየ_ይቤላ ማለት ነው።
#ያ__ያንቀዓዱ_ኀቤኪ_ኲሉ_ፍጥረት ማለት ነው።
#ም__ምስአል_ወምስጋድ_ወምስትስራየ_ኃጢአት ማለት ነው።
#ደግመኛም_ማርያም_ማለት፦ ተፈስሒ ቤተ ይሁዳ ወተሐሰዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው።
#እንድም_ማርያም_ማለት፦ ልዩ ከጣኦት ክብርት እምፍጥረታት ንጽህት እምኃጢአት መልአክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው።
#አንድም_ማርያም_ማለት፦ መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እንሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሷም በፍቅሯ ፤ በጣዕመ ፍቅሯ የሰውን ሁሉ ኃጢአት ክፋት ፍቃ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት፦ ሰረገላ ፀሐይ ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እንሆ ዛሬ በዚህ አለም ፀሀይ በሰለገላ ወጥቶ የረጠበውን ያደርቃል፤የበረደውን ያሞቃል ፤የጨለመውን ያስለቅቃል ፤ የተሰወረውን ሁለ ይገልጣል እንደዚህም ሁሉ ጌታችን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ በስጋወ በደሙ ከአብ ከባህርይ አባቱ ከመንፈስ ቅዱስ ከባህርይ ህይወቱ አስታርቆ ከገሃነመ እሳት አውትቶ መንግስተ ሰማያት የሚያገባ ስለሆነ ስለዚህ ሰረገላ ፀሀይ አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት ፦ተላኪተ እግዚአብሔር ወስብእ ማለት ነው። ይኸስ እንዴት ነው ቢሉ መለኮት ከትስብእት ትስብእት ከመለኮት ተዋህዶ በእመቤታችን በእግዝእትነ ማርያም ማኅፀን አድሮ ነበርና ስለዚህ ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ አላት። አንድም የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወደ ሰው እያመላለሰች በፍቅሯ በጣዕመ ፍቅሯ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ተላኪተ እግዚአብሔር ወስብእ አላት።
#አንድም_ማርያም_ማለት ፦ውህብት (ስጥውት) ማለት ነው። ይህስ እንዴት ነው ቢሉ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም የተወለደች እለት በአባት ተገኝታለች በኋላ የዓለሙ ሁሉ አማለጅ ሁና ሞታለች ስለዚህ ውህብት (ስጥውት) አላት።
ከዚህም በኋላ እርሱም ፀሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በጊዜ ሞቷ ከመከራ ወደ እረፍት፤ ከኀዘን ወደ ትፍስሕት ትሄጅ ዘንድ ሙቺ አላት እርሷም እግዝእትነ ማርያም ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ ያንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት ብትለው እርሱም ፀሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በፈቃዷ እንዳልሞተችለት አውቆ ፱፼ ከ፱ሺሀ ከ፱፻ ከ፺፱ ነፍሳት በአንድ ቀን ተኮንነው ገሃነመ ሲወርዱ አሳያት። እነዚህም ነፍሳት እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ባዩ ጊዜ እናታችን እመቤታችን ሆይ ለዘመዱ የሚያዝን አንጀት ራሱን የማይሸከም አንገት አንጀቱም አንጀት አንገቱም አንገት አይደለም ከልጅሽ አስታርቂን ከገሃነም እሳት አውጭን መንግስተ ሰማያት አግቢን ብለው ቢያለቅሱባት እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ልጄ ሆይ ወጃጄ ሆይ እባክህ ማርልኝ አለችው። እርሱም ጸሀየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ደቂቀ አዳምን ከገሃነመ እሳት አውጥቼ መንግስተ ሰማያት ያገባሁ ተገፍቼ፤ ተገርፌ ፤ተሰቅዬ ፤ተቸንክሬ ፤ሞቼ፤ ተነስቼ አይደለምን? አንቺ ለእነዚህ ነፍሳት በኃጢአታቸው ካልሞትሽላቸው ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ይቀራሉ አላት። እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ ስንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ ልሙት ብላ ሙታለች ኋላም ለፍጥረቱ ሁሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ስለዚህ ውኅብት (ስጥውት) አላት።
#ደግመኛም_ማሪሃም_ይላታል፦ ለአብርሃም ማለት አበ ብዘኃን ማለት እንደሆነ ስለምን የሁሉ እናት አላት ያለ እግዚአብሔር ያለ ክርስቶስ ልጅ አላትን ቢሉ ያንድ የእግዚአብሔር እናት ነኝና ብላ ትንሽ ትልቁ፤ ክፉ በጎው ቢለምናት ልመናህን አልሰማህም አትለውም አትፀየፈውም የሰውን ሁሉ ኃጢአት ክፋት ፍቃ ከልጅዋ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት እምታገባ ስለሆነች ስለዚህ የሁሉ እናት አላት።
•••✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክበቡር ✞✞✞•••
4 374
#ድንግል_ሆይ_ስላንቺ
•••✞•••✞•••✞•••
ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሀሪ
አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ
ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አስቸገረኝ
#አዝ•••••••
ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትዛዙን እንደሻርሁ ህጉን እንደጣስኩኝ
#አዝ•••••••
በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምንሃለሁ ከአሁኑ ይቅርታ
#አዝ•••••••
አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ
አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ
#አዝ•••••••
ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ
#አዝ•••••••
4 374
#6_ቅትለተ_ዘካርያስ፦
~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የካህኑ ዘካርያስ መሞት ፣ መገደል ማለት ነው። የእግዚአብሔር
ካህን የነበረው ዘካርያስ የተገደለው በተልዕኮ ላይ እያለ በቤተመቅደስ ውስጥ በመሠዊያው አጠገብ ነበር። እርሱም የሞተው ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን በግፍ ነው። እንደዚሁም ሁሉ የእግዚአብሔር ዓይኖች (አዕይንተ እግዚአብሔር) የተባሉ
እውነተኞች ካህናት በሐሳዊ መሲሕ ጊዜ አገልግሎታቸው ለእውነተኛው አምላክ
ለኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ መከራ ይደርስባቸዋል ፣ በአገልግሎትም ላይ እያሉ ይገደላሉ። ስለዚህ ይህ የሚያመለክተው የቅዱሳን ካህናትን መከራ መቀበልና በሰማዕትነት ማለፍ ሲሆን እነ ሄኖክና ኤልያስ ሌሎችም የተሰወሩ ቅዱሳን አባቶቻችን ሞት በሰው ልጆች ትክሻ ላይ የተሰየመ ነውና ወደዚህ ዓለም መጥተው በዚህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) ዘመን በሰማዕትነት ያርፋሉ የሞትንም ጽዋ ይቀምሳሉ። ሚል 4፥5 ፣ ማቴ 23፥25-36 ፣ ራዕይ 11፥3-13
--------------------//----------------
#7_ሞተ_ወልደ_እግዚአብሔር፦
~~~~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ንፁህና ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ስለሰው ልጆች ፍቅር እና ሕይወት እንጂ
አንዳች በደል ኖሮበት ወይም ተገኝቶበት አይደለም። ንፁሐ ባህርይ አምላክ ሆኖ
ሳለ እውነተኛ ፍርድ ስለጠፋ ነው በቅንዓተ አይሁድ የሞተው ፤ እንደዚሁም በዚህ ሐሳዊ መሲሕ ዘመን እውነተኛ ፍርድ ትጠፋለች ፣ ፍትህ ትጓደላለች ፣
ክርስቲያኖች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ፣ ይሰቃያሉ ፣ ይገደሉማል። ዮሐ 15፥18-20
፣ ማቴ 10፥16-20
---------------------//----------------
ከዚህ በኋላ ደግሞ ፦ "ዘንዶው ኃይሉንና ዙፋኑንም ትልቅም ሥልጣን ሰጠው"
ይላል ራዕ 13፥2
#ዘንዶ_የተባለው_ማነው?
~~~~~~~~~~~~~~
የዘንዶውን ማንነት ለማወቅና ለመረዳት ደግሞ ወደ ራዕይ 12፥3 ፣7፣ 9
እንመለሳለን። በዚህ በራዕይ 12፥3 "ታላቅ ቀይ ዘንዶ" ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስለዘንዶው ማንነት ይናገራል። ይህም ዘንዶ የተባለው አባታችንን አዳምና እናታችን ሔዋንን ያሳተው ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ነው። ዘፍ 3፥1 ^ታላቅ^ መባሉ የቀድሞውን ተፈጥሮውንና ክብሩን ለመግለፅ ነው፣ የመላዕክት
አለቃ ነበርና! "ቀይ" መባሉ ደግሞ ተፈጥሮው እንደ ሌሎቹ ብርሃናዊያን
እሳታዊያን ቅዱሳን መላዕክት ከእሳትና ከነፋስ ስለሆነ ነው። መዝ 103፥4 ፣ ዕብ
1፥7 ፣ ሕዝ 28፥14 ፣ ኢሳ 14፥12 ።
#ምድር_ሁሉ_አውሬውን_ይከተላል ራዕ 13፥4 መላው ዓለም በአውሬው የተመሰለው ይህ ሐሳዊ መሲሕ በሚያደርገው ምትሐታዊ ተአምር ይሳባል ፣ ይደነቃል "እውነተኛ አምላክ ነው" እያለም ይከተለዋል ማለት ነው። በምትሀታዊ ተአምራቱም ሕዝቡን ሁሉ ያስገርም ዘንድ ሥልጣን ለሰጠው ለዘንዶውም ይሰግዱለታል ፣ ይገዙለታል። አውሬውን "ማን
ይመስለዋል? ማንስ ይስተካከለዋል? ብቸኛ ገናና አምላክ ነው" ብለው
ያመልኩታል ማለት ነው። ዘዳ 13፥1-8 ፣ ማቴ 12፥38-39
#አውሬው_ተሳዳቢ_ነው (ራዕ 13:5-7)
አውሬውም ታላቅንም ነገርንና ስድብ የሚናገርበት አፍ ተሰጠው ፣ አርባ ሁለት
ወርም እንዲሰራ ሥልጣን ተሰጠው" ይላል ራዕይ 13:5
ይህ አውሬ (ሐሳዊ መሲሕ) በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ይሰድባል። "እግዚአብሔር ማን ነው? የትስ አለ? እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አምላክ እኔ ነኝ።"
ይላል። እውነተኛውን አምላክ ሰዎች እንዳይረዱና እንዳያመልኩት ርኩስ መንፈስ በልባቸው ያሳድርባቸዋል ፤ ደግሞም ያስታቸዋል። ዛሬም ቢሆን ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ "ፍጡር ፣ አማላጅ" የሚሉ አሉ። እነዚህ ለአውሬው ጥርጊያ መንገድ የሚያዘጋጁ ናቸው። ምክንያቱም በዮሐ 1፥1 ላይ መጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ቃልም ሥጋ ሆነ" ተብሎ የተነገረለትን እግዚአብሔር ወልድን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አሳንሶ "ፍጡር አማላጅ" ነው ማለት እግዚአብሔር መሳደብ ነው። እግዚአብሔርም ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለምና ፣ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለምና።
አውሬው (ሐሳዊ መሲሕ) ስድቡን በዚህ አያበቃም አርባ ሁለት ወር (ሶስት
አመት ከስድስት ወር) ሙሉ የወደደውን ምትሐታዊ ተአምር እየሰራ ራሱን ብቻ
ከፍ በማድረግ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ይሳደባል። ይላል ሐዋርያው ቅዱስ
ዮሐንስ በራዕይ 13፥6!
#የእግዚአብሔር_ማደሪያ_ማን_ናት?!
የእግዚአብሔር ማደርያ የተባለችው ጌታን ያየንባት በሁለት ወገን ድንግል
የምትሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው እመቤታችን ወላዲተ አምላክ
ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
እንግዲህ ድንግልን ነው ዘንዶውና ተከታዮቹ ማርያም አታማልድም፣ ሞታለች፣ ሌላም ሌላም እያሉ የሚሰናከሉባት። እንግዲህ ትንቢት ነውና ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ! ይማረክም ዘንድ እጁን አይስጥ!!
🙏አቤቱ ወደውና ፈቅደው ከሚጠፋት ጋር አታጥፋን!!🙏
✞ #አሜን_አሜን_አሜን ✞
------------------//----------------
4 374
#7ቱ_ሀገሮች_እና_7ቱ_የኃጢአት_ራሶች
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
➊ ፋርስ
➋ ባቢሎን
➌ ግሪክ
➍ ሜዶን
➎ ግብፅ
➏ ሮም
➐ ኢየሩሳሌም
በመጨረሻው ዘመን እነዚህ ሰባቱ ሀገሮች በሐሳዊው መሲሕ ወይም
በውሸተኛው ክርስቶስ ቁጥጥር ሥር የሚውሉ መላውን ዓለም በክህደት
ትምህርትና በታላላቅ ምትሐታዊ ተአምራት የሚያስቱና የሚያናውጡ ናቸው።
_____________\\____________
#ሰባት_ራሶች፦ የተባሉት በመጨረሻው በሐሳዊ መሲህ ዘመን የሚፈጸሙ
ሰባቱ ዋና ዋና ኃጢያቶች ናቸው። እነዚህም 7ቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ወይም 7ቱ የኃጢአት ራሶች ይባላሉ!
እነርሱም፦
➊ ኃጢያተ አዳም (ወይም የአዳም ኃጢያት
➋ ቅትለተ አቤል (የአቤል መገደል)
➌ ጥቅመ ሰናዖር (የሰናዖር ህንፃ)
➍ ኃጢያተ ሰዶም (የሰዶምና ጎሞራ ሰዎች ኃጢያት)
➎ ኃጢያተ እስራኤል (የእስራኤላዊያን ኃጢያት)
➏ ቅትለተ ዘካርያስ ካህን (የዘካርያስ ካህን መገደል)
➐ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት)
ናቸው።
-------------------//--------------
#1_ኃጢያተ_አዳም፦
~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የአዳም ኃጢያት ማለት ነው። የመጀመሪያው ሰው አዳም
አምላክነትንና ፈጣሪነትን ስለሻተና ስለተመኘ አትብላ የተባለውን "ዕጸ በለስን" በላ። በዚህም ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከክብር ቦታ ከገነት ተባርሮ ወጣ። አሁንም በዚህ በመጨረሻ ዘመን የሚነሳው ይህ ሐሳዊ መሲሕ "እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔ ፈጣሪ ነኝ፤ ለእኔ ስገዱ" እያለ የሚመጣ ሰው ነው። በሞተ-ወልደ
እግዚአብሔር ተደምስሳ የነበረችውም የአዳም ኃጢያት (አምላክነትን መሻት)
በዚህ በሐሳዊው መሲሕ ዘመን ለመጨረሻ ጊዜ አይላ ትፈፀማለች ማለት ነው። ዘፍ 3:1
በምንም የሚያስታችሁ አይኑር ፤ ክህደት ሳይመጣና የአመፅ ሰው እርሱም
የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያቺ ቀን አትመጣምና። ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለሁሉም እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ የሚል በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሚቀመጥ ራሱንም እንደ እግዚአብሔር የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው።" 2ኛ ተሰ 2፥3-5
-------------------//----------------
#2_ቅትለተ_አቤል፦
~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የአቤል መገደል፤ መሞት ማለት ነው። አቤልና ቃየል የአዳምና
የሔዋን ልጆች ናቸው። ዘፍ 4:1-12 ቃየን የገዛ ወንድሙን በግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ገድሎታል። አሁንም በዚህ የአውሬው (የሐሳዊው መሲሕ)
ዘመን መገዳደል እጅግ ይበዛል ፤ ርህራሄ ከሰው ልጆች ዘንድ ትርቃለች።
ወንድም ወንድሙን ይገድላል። እህት እህቷን ትገድላለች ማለት ነው።
ማቴ 10:21-36 "ወንድምም ወንድሙን ፣ አባት ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል።
ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ ፤ ይገድሉዋቸዋልም።"
-------------------//----------------
#3_ጥቅመ_ሰናዖር፦
~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት የሰናዖር ሕንፃ (ግንብ) ማለት ነው። ባቢሎናዊያን በቀድሞ ወቅት
ሰይጣን በልባቸው አድሮ፣ ልባቸው በትዕቢት ተወጥሮ፣ የማይታየውን ረቂቅ
አምላክ እናየዋለን ፣ የማይዳሰሰውን አምላክ እንዳስሰዋለን ፣ በጦርም ወግተን ከዙፋኑ እናወርደዋለን፣ በማለት በእግዚአብሔር ላይ በትዕቢት ተነሳስተው ግንብ መገንባት ጀመሩ። የግንቡም ርዝመት 5532 ክንድ ነበር። በዚህን ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር ሦስትነቱን ገልጦ እንዲህ አለ፦ ንዑ ንረድ ወንከአው ነገሮሙ ለከለዳውያን። ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ
እንደባልቀው" ዘፍ 11:7 ወዲያውኑ ቋንቋቸው ተደበላለቀባቸው። ድንጋይ
አቀብለኝ ሲለው ውኃ ፣ ውኃ አቅብለኝ ሲለው ደግሞ እንጨት ያቀብለው ጀመር
፤ በዚህም ዓይነት ቋንቋቸው ተደበላለቀ። እግዚአብሔርም በትዕቢታቸው ምክንያት በተናቸው። (መዝ 2:5) ዛሬም በእኛ ዘመን የሚያጣላን የዘረኝነት ጉዳይ ነው። አስተውለን ካየነው የቋንቋችን ብዛትና ልዩነት በኃጢአታችን ብዛት እንዳንደማመጥና እንዳንስማማ
የተደበላለቀብን እንጂ የጽድቃችን ምልክት አይደለም። አሁንም በዚህ ሐሳዊ መሲሑ ዘመን ከዚህ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ቴክኖሎጂው ይራቀቃል፣ ይሰለጥናል። ሰዎችም እጅግ ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ መሳሪያዎች
እግዚአብሔር ያለበትን ቦታ ለማግኘት ከጨረቃ አልፈው ይመጥቃሉ ፣
እግዚአብሔርን ግን አያገኙትም ፤ አያዩትም። መዝ 2፥4-5 እንዲህ ይላል፦
"በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል። እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል ፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"
ትንቢተ አብድዩ 1፥1-4 "ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ
መስማትን ሰማሁ ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ ፥'ተነሱ ፤ በላይዋም እንነሳና
እንውጋት። እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ። አንተ እጅግ ተንቀሃል።
በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ እንደሚኖር ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ፤
በልቡም ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል ፥ በልብህ ትዕቢት እጅግ
አኩርቶሃል። እንደንስር መጥቀህ ብትወጣ ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያም አወርድሃለሁ' ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በዚህም ጊዜ ሐሳዊው መሲሕ እግዚአብሔር የት አለ? አምላክ ፣ ፈጣሪ እኔ ነኝ" ይላል። ለዚህም ሙት ያስነሳል። እሳት ከሰማይ ያወርዳል ፣ ታላላቅ ተዓምራትን ያሳያል። በዚህም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እያስነገረ በቤተ መቅደስ ይቀመጣል። በዚህን ጊዜ መላው ዓለም አውሬውን ማን ያህለዋል? ማንስ ይመስለዋል? እያለ ይከተዋል፤ ይሰግዱለታልም። ማቴ 24፥23-27 ፣ 2ኛ ተሰ 2፥4 ፣ ራዕ 13፥4
-------------------//----------------
#4_ኃጢአተ_ሰዶም፦
~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ኃጢያተ ሰዶም ተብሎ የሚጠራው በሎጥ ዘመን በሰዶምና በገሞራ የተፈፀመው የኃጢያት ስራ ነው። ሰዶምና ጎሞራ በአንድ ወቅት ትዕዛዘ-እግዚአብሔርን አፍርሰው ሕጉንም ተላልፈው ለባሕርያቸው የማይስማማውን የማይገባውን እንስሳዊ ግብር በመፈፀማቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ከሰማይ እሳት (ዲን) አዝንቦባቸዋል። ዘፍ 19፥24 ፣ መዝ 48፥12 ፣ ሉቃ 17፥18-30 ፣ 2ኛ
ጴጥ 2፥6-8 ፣ ሮሜ 1፥22-32
ይህ ግብረ ሰዶም በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ላይ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው። በተለይም በሰለጠነው ዓለም ይህ ግብረ ሰዶም ሕጋዊ እንዲሆን ተደርገዋል። በብዙዎችም ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል። ይህ የሚያስረዳን የጊዜው መቃረብና ከዛሬ ሦስት ሺህ ዓመተ በፊት የነበረው ኃጢአት በዚህ ሐሳዊ መሲህ ዘመን እንደ አዲስ መምጣቱንና የግብረሰዶም ኃጢያት በገሀድ እንዲፈጸም መደረጉን ያሳያል። ማቴ 24፥15
------------------//----------------
#5_ኃጢያተ_እስራኤል፦
~~~~~~~~~~~~~~
ይህ ማለት ሀገረ እግዚአብሔር ፣ ህዝቡም "ሕዝበ እግዚአብሔር" ይባሉ
እንደነበር በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሁላችንም የምናውቀው ነው። እስራኤላዊያን ግን በዚያን ጊዜ የአባቶቻቸውን አምላክ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ትተውና ረስተው ሕጉንም ተላልፈው በአሕዛብ ጣዖታት ያመልኩና ለጣኦታቱም ይሰግዱ ነበር። እንደዚሁም ሁሉ በዚህ በሐሳዊ መሲሕ ዘመን ብዙ ሰዎች ከአምልኮተ እግዚአብሔር ወጥተውና ተለይተው ወደ ተለያየ አምልኮተ ጣዖት ይገባሉ። የአውሬው (የሐሳዊው መሲሑ) ስምና መንፈስ ፣ መለያ ቁጥሩ ለሆነው 666 ላለበት ጣዖት ይገዛሉ። ራዕይ 13፥15
------------------//----------------------
4 374
#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ {ለምን እንላለን}? ✞✞✞
—“#ሚስጢሩ ”—
በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ። ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ።
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ
ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ
ሆይ ማረን ማለት ነው ።
አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም
ደግሞ ለሊቱን 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው።
ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦
#1ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል
#አ_ብ_ወ_ል_ድ_መ_ን_ፈ_ስ_ቅ_ዱ_ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
#2ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ።
#ቅ_ድ_ስ_ት_ድ_ን_ግ_ል_ማ_ር_ያ_ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
———✞ “እግዚኦ” ✞———
አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት /በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ።
ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ
ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ።
መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤ በትንሿ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።
———✞ “ብእንተ” ✞———
በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው ።
ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ
ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው።
“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” -
የማቴ፡ 23፥12
ደግሞ የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀ ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር
አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው።
“ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” መዝ፡ 132፥8
ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም
አታደርግም።
4 374
☞✞ ✝ማቴ፡6፥16✝
ስትጦሙም፥እንደ፡ግብዞች፡አትጠውልጉ፤ለሰዎች፡እንደ፡ጦመኛ፡ሊታዩ፡ፊታቸውን፡ያጠፋሉና፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋቸውን፡ተቀብለዋል።
አንተ፡ግን፡ስትጦም፥በስውር፡ላለው፡አባትኽ፡እንጂ፡እንደ፡ጦመኛ፡ለሰዎች፡እንዳትታይ፡ራስኽን፡ተቀባ፡ፊትኽንም፡ታጠብ፤በስውር፡የሚያይ፡አባትኽም፡በግልጥ፡ይከፍልኻል።
#ራስኽን_ተቀባ፦ የተባለውም ፍቅርን፣ ትህትናን፣ ሰላምን፣ ጥሩ ምግባርን ተላበሱ ማለት ነው፡፡
#ፊትህንም_ታጠብ፦ ማለት ራስኽን ከሀሜት፣ ከክፋት፣ ከዝሙት፣ በአጠቃላይ ከመጥፎ ስራዎች ሁሉ ንፃ/አፅዳ ማለት ነው፡፡
---✞መልካም ዕለተ ቅድስት ሰንበት✞---
4 374
#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_በመስቀል_ላይ_ተሰቀለ?
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል
ተሰቅሎ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶልናል፥ ክቡር ደሙን አፍስሶልናል፥ ክብርት
ነፍሱንም በፈቃዱ አሳልፎ ሰጥቶልናል።
ይህንንም ያደረገው በቤዛነቱ እኛን ከእርግማን ሊዋጀን ነው። ምክንያቱም የሰው ልጆች በጠቅላላ በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ ተይዘን ነበርና።
በመሆኑም በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም፥ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ
ተፈርዶብን ከእርግማን በታች ወድቀን ነበር። ይሁን እንጂ ፈጣሪያችን “እንደ ወጡ ሳይመለሱ፥ እንደወደቁ ሳይነሱ ይቅሩ፤” ሳይል እኛን ለመፈለግ ከሰማየ ሰማያት ወረደ። /ማቴ. 18፥12-14/። በመንፈስ ቅዱስ ግብር በማኅፀነ ድንግል ማርያም ተፀነሰ። /ሉቃ. 1፥35/።
✞ ከእመቤታችንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በቤተልሔም በከብቶች በረት ተወለደ። /ሉቃ. 2፥7/።
በተዋሕዶ ሰው አምላክ፥ አምላክ ሰው ሆነ። /ማቴ. 16፥13፣ 1ኛ ዮሐ.
1፥1-2፪፤ 5፥20/። ቀስ በቀስም አደገ። /ሉቃ. 2፥40/። ሠላሳ ዓመት
በሞላውም ጊዜ በፈለገ ዮርዳኖስ በዕደ ዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ገዳመ
ቆሮንቶስ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ጾመ። /ማቴ. 3፥13-17፣ ሉቃ. 3፥21-23፣ ማቴ. 4፥2/። ከዚያም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ሰባ ሁለቱን አርድዕትና ሠላሳ ስድስቱን ቅዱሳት አንስት መረጠ። / ሉቃ. 10፥1፣ የሐዋ. 1፥15/።
✞ አዲስ ሕግ ወንጌልንም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር አስተማረ። በመጨረሻም
ሰለእኛ እርግማን /ኃጢአት/ ተላልፎ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ። /ማር.
15፥23-37/። የሞተውም በፈቃዱ ነው።
/ዮሐ. 10፥11፤ 15፥13/። በዚህም የዕለት ፅንስ ሆኖ በእመቤታችን ማኅፀን
ጀምሮት የነበረውን የማዳን ሥራ በመስቀል ላይ ፈጸመው። /ዮሐ. 19፥30/።
----✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞----
