fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
“ወጣትነህ ? “ ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2 ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ፤ ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን ወይስ በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን እንዲህም ቢሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም ነገር ግን በጽድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና›› #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ገጽ 134 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ምጽዋት ብዛት ወይስ ጥራት? የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ። የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ። አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው ። የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፤ ታድያ ለወንድምህስ የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነውን? መሆን የለበትም። ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው። ከምትለብሳቸው ሁለቱ ልብሶች አንዱን ስጠው። የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው። ለአንተ የምትመኝውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 ያለውን ቃል መለስ ብለህ አስብና የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ። አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋእት እንዴት እንደነበረ አሰብ። "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋእቱ ተመለከተ።"ዘፍ 4፥4 ለምን መረጠለት? ብትል አቤል ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ስላቀረበ ነው። በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሰፍሮ የሚገኝውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 #ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

☀️☀️☀️☀️ኅሊና🌟🌟🌟🌟 ኅሊና ማለት በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ግብረገባዊ የስሜቶች አካል ነው። ለምሳሌ ከሰውነታችን የአካል ክፍሎች አንዱ የሆነው ዓይናችን አንድን ነገር ከሌላው የመለየት ችሎታ ያለውን ያህል እንዲሁም ኅሊናችን ክፉና ደግ አድራጎቶችን የመለየት ችሎታ አለው። ስለዚህ ሰው በኅሊናው አነሳሽነት መልካም ስራ ይሠራል ከክፉም ይርቃል የኅሊናውን ምክር ተላልፎ ቢሠራም እንዲጸጸት ያስገድደዋል፤ ይወቅሰዋል ማለት ነው። ይህም በመሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ላላነበበ ሰው እንኳን ቢሆን ኅሊናው የእግዚአብሔርን መኖር ይገልጻል ማለት ነው። እንዴት ቢባል አንድ ሰው ክፉን ማየትና መስማት ባልወደደ ጊዜ አይኑን እንደሚጨፍን ጀሮውንም እንደሚይዝ እና ሊሰማው እና ሊያየው ካለው ነገር እንዲከለከል፣ ሰው ከኅሊናው ምክር ተከልክሎ ክፉ ቢያደርግ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጨነቃል። ዓይኑን ጨፍኖ አላይም እንደሚል ኅሊናውን ግን ሊያዘው እንደወደደ ሊያደርገው አይቻለውም። በሰውነት ውስጥ ያለ ነገር ግን በሰውየው ፈቃድ ሕግን የማይታዘዝ ኅሊናችን ስለምንድነው? ከኛም ሆኖ የሚመራን ማነው ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ጊዜ ሁሉን የፈጠረ ከእኛ በላይ ሆኖ የሚመራ አምላክ እንዳለ እንረዳለን። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ሮሜ ም፪ ፦፲፬ ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕሪያቸው ትእዛዝ ሲያደርጉ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳን ለራሳቸው ሕግ ናቸውና እነርሱም ኅሊናቸው ሲመሰክርባቸው አሳባቸውም እርስ በርሱ ሲካሰስ ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። ፨ከዚህ የምንረዳው ለደጉም ሆነ ለክፉ ፡ እንደሥራው ዋጋ የሚከፍልና ሳያዳላ የሚፈርድ ከሁሉ በላይ የሆነ አንድ አምላክ እግዚአብሔር መኖሩን በኅሊና ማረጋገጥ ነው። 👉ሰለዚህ የልዑል እግዚአብሔር ልጆቹ ሁሉም ሰው መጥፎ ስራ ስርቶ ሊሰወር ሊጠፋ ይችል ይሆናል ነገር ግን ከ ህሊናው ወዴትም ሊስወር ሊሸሽ አይችልም የልባችንን በኅሊናችን ውስጥ ያለውን የማቅ የሚመረምር ልዑል እግዚአብሔር ነው ሁላችንም ከህሊናችን መሰወር አንችልም እና ህሊናችን የማይፈልገውን ያሎደደውን መጥፎ ነገር አናርግ ከምድራዊ እስር ልናመልጥ እንችል ይሆናል ነገር ግን ከህሊና ባርነት እስር አኖጣም ሰውን በሰውነቱ እናክብር ሲቸገር እንርዳ ሲታመም እናስታም ሲታሰር እንጠይቀው በገሃድ የሰራናውን በጎ ስራ በገሃድ ይክፈለናል እልና ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

መልካምነት ለራስ ነው (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት) አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ። ፍርድ ቤት የተባለው የሰው ልጅ ይችን ዓለም ተሰናብቶ የሚኖርባት የዘላለም ቤቱ ሲሆን 1-የመጀመሪያው አልችልም ያለው ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ። 2-ሁለተኛው ፍርድ ቤቱ አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም። 3- ሶሰተኛው እሰከ መጨረሻው አንተ ጋ ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡ ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ትሑት እና ትዕግሥተኛ ሁን በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል / ዘኁ 12:3/ ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር ሐዋርያው " ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ ..ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ..." /ሮሜ 12*17-19/ብሏልና ። እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ " ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ " / ሮሜ 12*21/ በማለት ይጠይቀናል ። በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው ። ለዚህ ነው ሐዋርያውም " እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል ። " / ሮሜ 15*1/ ያለው። @Abbuneshinoda ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ ። ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል ። ወቅቶችን ዝናባማ ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል ። ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ ። ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም ። ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው ። ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው ። ከንነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው ። ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው ። አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

.....ክፍል ፮ የመጨረሻው ክፍል.... በጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ኤፍ ኬነዲ ግን በኮሚቴው ሃሳብ አልተስማሙም፡፡ የአንድ ዓለም አንድ መንግስት አስተዳደር የሚለውን የኮሚቴውን እቅድ ‹‹ቅዠት›› እና ‹‹የማይረባ›› መሆኑን በይፋ በመቃወም ገልጸው ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ መጽሐፍቶችን ለንባብ ያበቁ ፀሃፊያን እንደሚሉት ከሆነ ለጆን ኤፍ ኬኔዲ መገደል ምክንያቱ ከሚስጥር ማህበራቱ ጋር አለመተባበራቸው ነው፡፡ ዓለማችን በአንድ መንግስት አንድትመራ የሚፈልጉና ለዚህ ሃሳባቸው መሳካት ሌት ከቀን የሚተጉ ሚስጥራዊ ቡድች (Secret societies) መቀመጫቸውን በተለያዩ ሃገራት አድርገው በብዛት እንዳሉ የተለያዩ ፀሀፊዎች አስነብበውናል፡፡ እነዚህ የሚስጥር ማህበራት ረዥም ዘመናትን ያስቆጠሩ ሲሆን ታዋቂና በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስራን ያበረከቱ ስመጥር ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው ብየመዝናኛው የሚመሩ ማህበራት ናቸው፡፡ በዓለማችን ላይ በርካታ የሚስጥር ማህበራት እንዳሉ ቢነገርም በዋናነት የሚታወቁትና በጉልህ የሚንቀሳቀሱት ፍሪማሰንስ፣ ኢሉሚናቴ፣ የቢልድበርግ ቡድንና ስከል ኤንድ ቦንስ የሚባሉት ናቸው፡፡ ዝነኛና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉት የፖለቲካውና የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ታላላቅ ሰዎች የነዚህ ማህበራት አንቀሳቃሾች ናቸው፡ ፡ የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ሰዎች በኢሉሚናቴ የፖለቲካው ዓለም ሰዎች ደግሞ በፍሪማሰንስና በቢልድበርግ ማህበራት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ አላቸው ይባላል፡፡ ሚስጥረኞቹ ዝነኞች ከአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች መካከል ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ሞንሮ አንድሪው፣ አንድሪው ጃክሰን፣ ጀምስ ጋሪፊልድ፣ ቴዎዶር ሩዝቬልት፣ ሀሪ ትሩማንና ሊንደን ጆንሰን ፍሪማሰንስ በተባለው የሚስጥር ቡድን ውስጥ አባል የነበሩና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችንም ያደረጉ ናቸው፡፡ ዊንስተን ቸርችል፣ ሲሞን ቦሊቫር፣ ቶኒ ብሌየር፣ ያሲር አረፋትና ይሳቅ ራቢንን የመሳሰሉ የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ፖለቲከኞችም የዚህ ማህበር አባላት እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ውስጥ ከነበሩ እንደ መካከል ሞዛርት፣ ቬትሆቨን፣ ዋልት ዲዝኔይ፣ ሊኦናርዶ ዳቬንቺ፣ ዊልያም ሼክስፒርና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ አሁንም በዚህ ማህበር ውስጥ ታላላቅ የፖለቲካና የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ሠዎች የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ ይነገራል፡፡ እ.ኤ.አ በ1776 በደቡብ ምስራቅ ጀመርን በምትገኘው ባቫሪያን የተባለች ቦታ እንደተመሠረተ የሚነገርለት ኢሉሚናቴ የተባለውሙዚቃና ማህበር የጊዜው መነጋገሪያና የብዙ ታዋቂ ሰዎች ነው፡፡ ራሳቸውን (The Enlighted Ones) መሰባሰቢያ(የተገለጠላቸው) አድርገው የሚቆጥሩት ኢሉሚናቴዎች ዓለምን ለመቆጣጠር የሚያስችሏቸውን የተለያዩነገሮች ያደርጋሉ፡፡ ዓለምን ለመቆጣጠር የእያንዳንዱን ሠው አዕምሮ መቆጣጠር (Mind Control ) አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ለዚህም ሲባል ሙዚቃና ፊልሞችን ዋነኛ መሳሪያቸው አድርገዋል፡፡ በአብዛኛው የዚህ ሚስጥራዊ ማህበር አባላትም በፊልሙና ሙዚቃው ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ግለሰቦች ናቸው፡ አሊሺያ ኪይስ፣ አዴል፣ አንጀሊና ጆሊ፣ ቢዮንሴ ኖውልስ፣ ቦብ ዲለን፣ ብሪትኒ ስፒርስ፣ ሴሌንድዮን፣ ክሪስ ብራውን፣ ኤሚኒየም፣ ጄዚ፣ ኬቲ ፔሪ፣ ጀስቲን ቢበር፣ ሌዲ ጋጋና ሪሃና በዋናነት የሚጠቀሱ የኢሉማናቲ አባላት እንደሆኑ ይነገራል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ተጫዋች ክርስቲያ ሮናቪዲዮ የአለማችን ሃብታም ዋረን በፌት ሳይቀሩ የዚህ ማህበር አባላት ስለመሆናቸው ይነገራል፡፡ ኢሉማናቲዎች ለሰይጣን የተገዙ ናቸው፡ ፡ ከላይ ስማቸውን ከጠቃቀስናቸው ዘፋኞች መካከል ኢሚኒየም፣ ኬቲ ፔሪ፣ ቢዮንሴና ጄይዚ በሙዚቃዎቻቸውና በተለያዩ ቃለ ምልልሶች ወቅት ይሄን አረጋግጠዋል፡፡ ነፍሳቸውን ለሰይጣን ሸጠው ዝናና ሃብት ማግኘት እንደቻሉ ገልጸዋል፡ ፡ በሚሠሩት የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ የኢሉሚናቴ ምልክቶች ናቸው የሚባሉትን ፒራሚድና የአንድ ዓይን ምልክትን በተደጋጋሚ አሳይተዋል፡፡ The Biggest Secret የተሰኘውን መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ዴቪድ አይክ እንደሚለው ኢሉሚናቴዎችና ሌሎች የሚስጥር ማህበራት ዓለምን በአንድ መንግስት ስር ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ እንደደራሲው ገለጻ ነጩ ቤተ መንግስት (CapitolHill) የፓለቲካ አላማ ማስፈጸሚያ ቤት ሳይሆን የሰይጣን ወንድማማቾች መሰባሰቢያ ቦታ ነው፡፡ ዓለምን ወደ አንድ መንግስትነት ለመቀየር የህዝብ ቁጥሮቿን መቀነስ እንደሚያስፈልግ የሚያምኑት የሚስጥር ማህበራቱ አሁን ያለውን ከ7 ቢሊዮን በላይ የሚሆን የህዝብ ቁጥር ወደ ግማሽ ቢሊዮን እንዲቀንስ ፍላጎት አላቸው ይባላል፡ ፡ ለሶሪያ ብጥብጥ፣ ለእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት፣ ዓለም ላይ ለሚከሰቱት ጦርነቶችና የተለያዩ አደጋዎች እንዲሁም ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ ለሚፈጠሩ ሌሎች ቫይረሶች ዋና ተዋናይ እነዚህ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት እንደሆኑ ፀሀፊዎቹ ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያን ያሰጋታል? ይሄንን ጥያቄ ‹አዎ› ብለው የሚመልሱና ይህ ስሜት የተጋባባቸው የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ፀሐፊዎችና የቤተክርስቲያን ሰዎች ስለ ሚስጥራዊ ማህበራቱ የሚያስገነዝቡ መጽሐፎችንና ቪሲዲዎችን በአማርኛ አዘጋጅተው ለገበያ አቅርበዋል፡፡ ሁሉም ጉዳዩ የኢትዮጵያም ስጋት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ በሚስጥራዊ ማህበራቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ሠዎች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ብለዋል፡፡ በመንግስትና በህዝቡም ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የኢሉሚናቲ አባላት መካከል ቢዮንሴና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ይገኙበታል፡፡ ከታዋቂ የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢዋና ራሷም ኢሉሚናቲ እንደሆነች ከሚነገርላት ኦፕራ ዊንፍሬይ ጋር በቅርቡ ባደረገችው ቃለ ምልልስ ወቅት ኢሉሚናቲ መሆኗን ያመነችው ቢዮንሴ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በመንግስትና በወቅቱ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የተደረገላት አቀባበል ደማቅ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በነበራት ቆይታም የኢሉሚናቲ ምልክቶቹን በኮንሰርቷ ላይ ከማሳየቷ በተጨማሪ በገጠር ለሚኖሩ ህፃናት ስታሳያቸውና እሷ የምታደርገውን እንዲያደርጉ ስታስተምራቸው ታይቷል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዝነኛ ሰዎች የሚያስተላልፉት መልዕክትና ሙዚቃዎቻቸውና ፊልሞቻቸው በወጣቱ ትውልድ ያገኘው ተቀባይነት ለሚስጥራዊ ማህበራቱ ዓላማ መሳካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ ስለሚስጥራዊ ማህበራቱ የሚገልጽ ሁለት ቪሲዲዎችን ለእይታ ያበቁት ኢትዮጵያውን ወጣቶች ይናገራሉ፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ደቀመዝሙር ሜሎስ ተሾመ እና ዲያቆን እዮኤል ጌታቸው እንደሚሉት ወደሃገራችን ብቅ ያሉ የውጭ ሀገር ድምጻዊያን የሰይጣን አምልኮታቸውንና የኢሉሚናቲ ምልክቶችን በተለያ መንገድ ሲያሳዩ ነበር፡፡ በሃገራችንም ‹የሰይጣን መጽሀፍቅዱስ› በአማርኛ ተተርጉሞ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በብዛት እንደሚነበብ ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡ እንደወጣቶቹ ገለጻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ተማሪዎች እጅ መጽሐፉን በተደጋጋሚ ተመልክተውታል። ♦ወስብሐት ለእግዚአብሔር♦ ♦ወለወላዲቱ ድንግል♦ ♦ወለመስቀሉ ክቡር♦ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

......... ክፍል ፭................ 👉አሜሪካ ና ተከታዮቿ እንዲሁም ምዕራብ አውሮፖዎች በጋራ የአትላንቲክ ህብረት (Atlantic Union) የሚባልና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(NATO) የተባለውን ተቋም በበላይ ሆኖ የሚመራ የዓለሙ ሁሉ ገዥ የሆነ ተቋም ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ስቶለር ያስረዳል፡፡ ያ ጥረታቸው ደግሞ የአውሮፓ ህብረት የተባለውን ተቋም እውን አድርጓል፡፡ የአንድ ዓለም አስተዳደር አራማጅ ከነበሩ ሠዎች መካከል በ1930ዎቹ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበረው ክላረንስ ስትሬት ይገኝበታል፡፡ የኒውዮርክ ታይምስ መጽሔት ጋዜጠኛ የነበረው ስትሬት የሊግ ኦፍኔሽንን ስብሰባዎችና ሌሎችንም የተቋሙን ስራዎች በተለየ ሁኔታ የሚዘግብ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በወቅቱ ጋዜጠኛው እንደገለጸው የአሜሪካን መገለልና የአውሮፓውያንን የፋሽሽት እንቅስቃሴ ማቆም የሚቻለው ዓለም ወደ አንድ ስትመጣ እንደሆነ በተለያዩ ጽሁፎቹ ላይ ገልጾ ነበር፡፡ በተለይ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኒውዝላንድ፣ አውስትራሊያ፣የሩሲያ ደቡብ አፍሪካና አብዛኞቹ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ለስኬታማነቱ ዋነኛ ቁልፎች መሆናቸውን አስቀምጧል፡፡ ማት ስቶለር እንደሚገልጸው እ.ኤ.አ በ1971 በአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከፍተኛ ሁኔታ ሲወያይባቸው ከነበሩት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው የአትላንቲክ ህብረትን የማቋቋም ሀሳብ ነበር፡፡ አሜሪካንና የአውሮፓ ሀገራትን በአንድ አስተዳደር የመምራት እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ አመቱን ሙሉ ውይይት ተደርጓል፡፡ ይሁንና እምቢ ባይነትና በጉዳዩ ፍላጎት አልባ መሆን አሜሪካዊያኖቹ ያሰቡትን ነገር እንዳያሳኩ አድርጓል የሚሉ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ የአንድ ዓለም አንድ መንግሥት አስተሳሰብ ዓለም አንድ መንግስት አስተሳሰብን ወደ ተግባር ለመቀየር ሲተጉ የነበሩትና አሁንም ጥረቶችን እያደረጉ ነው የሚባሉት አሜሪካዊያኑ ስርዓቱን አበጅተው ጨርሰዋል፡፡ የወደፊቱ የዓለማችን አስተዳደር እስራኤልን ዋና ከተማ ያደርጋል፡፡ አሁን ያሉት ሀገራት የራሳቸውን መገበያያ ገንዘብ፣ የጦርሃይል፤ የንግድ ህግና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን እንደየፍላጎታቸው ማስኬድ ቢችሉም የሚመሩት ግን በአንድ አስተዳደር ይሆናል፡፡ በአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከነበሩትና በ1971 ስለ አንድ ዓለም አንድ መንግስት ሰርዓት ሲወያዩና አዋጅ ሲያረቁ ከነበሩት ሰዎች መካከል የሜኒሶታው ሴናተር ዶናልድ ፍሬዘር ይገኙበታል፡፡ ዶናልድ በወቅቱ እንደተናገሩት የዚህ ሰርዓት ተግባራዊ መሆን ለዓለም ሠላምና ዲሞክራሲ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡ ፡ ‹‹ዓለም አቀፍ ስምምነት ተደርጎ አዋጅ በማጽደቅ ይሄን ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ ተፈላጊው ዲሞክራሲ በዓለማችን ላይ ይሰፍናል›› ብለው ነበር ሴናተሩ......... ይቀጥላል...... ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

................ክፍል ፬............ 👉 ሆኖ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ አውሮፕላን እምጥ ይግባ ስምጥ አለመታወቁ አዕምሯችን በብዙ ጥያቄዎች እንዲሞላ የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ በድንገት ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የቀረውና የገባበት ያልታወቀው የማሌዥያ አውሮፕላን ሚስጥራዊነት አንዱና የቅርብ ጊዜ ማሳያ ሆነ እንጅ ፔርሙዳ ትሪያንግል በተባለ የባህር ሰርጥ ውስጥ ጠፍተው ቀርተዋል የተባሉ መርከቦችና አውሮፕላኖችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ 👉 ስለዚህ ቦታ ምንነትና ለምን ለአውሮፕላንና መርከቦች መቃብር እንደሆነ ሚስጥሩን ፈትቶ ያስረዳ አካል የለም፡። ‹‹ፔርሙዳትሪያንግል›› ሚስጥራዊ ቦታ ነው ከማለት ባለፈ በውስጡ ምን እንደሚገኝና በምን ምክንያት አውሮፕላኖቹ እንደሚሠወሩ የሚገልጹ እውነታዎችን አልተረዱም፡፡ 👉 ወይም ተረድተው እንኳ ቢሆን ለኛ ግን አልነገሩንም፡፡ ያልታወቁ በራሪ አካላት (UFO) ስለሚባሉትና ወደፊት ዓለምን ሊቆጣጠሩ ይችላሉ የሚሉ መላምቶች ስለ ሚሠነዘሩባቸው ፍጡራን ሳይንቲስቶቹ ገብቶናል ያሉትን መረጃ በተለያየ መንገድ ቢገልጹም አሁንም ግልጽ ያልሆኑ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ 👉 እስካሁን ከላይ የጠቃቀስናቸው የአለማችን ሚስጥሮች በተፈጥሮ ሃይል የሚንቀሳቀሱና ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆኑ ናቸው ማለት እንችላለን፡፡ ሰው ሰራሽ የሆኑትስ? ሰው ሠራሽ ሚስጥሮች የሰው ልጅ አዕምሮ በቁልፍ ተከፍቶ ቢመረመር እንኳ ሊደረስበት የማይችል ብዙ ሚስጥራትን ይዟል። አንድ ግለሠብ ለራሱ ብቻ የሚያውቀው ወይም ደግሞ በራሱ ልክ ለሚያምናቸው ሰዎች ብቻ የሚያጋራው ሚስጥር ይኖረዋል፡፡ 👉 ያ ሚስጥር እስከሞት ድረስ የሚዘልቅም ይሆናል፡፡ ከግለሰቦች አልፎ በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ህልውናውን ያደረገ ሚስጥር ደግሞ አለ፡፡ የዚህ ጸሁፍ ዋነኛ ትኩረትም በዚያ ላይ ያጠነጠነ ነው፡፡ የሚስጥር ማህበራት (ድብቅ ማህበራት) ወይም ደግሞ በእንግሊዝኛው አጠራር (Secret Societies) ስለሚባሉት አንዳንድ ነጥቦችን እናነሳለን፡፡ በተለያየ ጊዜ ድብቅ ማህበራት ስለሚባሉት ቡድኖችና በነዚህ ማህበራት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ስለሚያደርጉ ታላላቅና ዝነኛ ሰዎች በርካታ ጽሁፎችና የቪዲዮ መረጃዎች ሳይቀሩ ቀርበዋል፡፡ 👉 ማህበራቱ አብዛኞቹ ዓለምን ወደ አንድ ሀገር የመቀየር (One World government) አላማ ያላቸውና ያንን አላማቸውን ለማሳካት ሲሉ በርካታ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ እንደሆኑ ሚስጥሩን ደርሰንበታል የሚሉ ፀሐፊዎች ያስረዳሉ፡፡ በማስረጃነትም የተለያዩ ነገሮችን ያቀርባሉ፡፡ የአንድ ዓለም አገዛዝ (አስተዳደር) ፈረንጆቹ New World Order የሚሉት ፅንሰ ሃሳብ የመጣው እ.ኤ.አ በ1920 መሆኑን የሚገልጹ ጽሁፎች አሉ፡፡ 👉 በወቅቱ ፍሬድሪክ ቻርለስ ሂክስ የተባለ ደራሲ New World Order የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅቶ ነበር፡፡ ይህ ደራሲ ከሚስጥር ማህበራቱ አባላት አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ማት ስቶለር የተባለ ታዋቂ የዘመናችን ጦማሪ(Blogger) በቅርቡ በጻፈው አንድ አነጋጋሪ ጽሁፍ ላይ እዳሰፈረው ደግሞ ዓለምን በአንድ መንግስታዊ አስተዳደር ስር የማድረግ ሃሳብ እየተንሰራፋ የመጣው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነው....... ይቀጥላል..... ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

...............ክፍል ፫.............. 👉 1፡የግብረ ሰዶማዊያን የጋብቻ መብት 2፤ ህጋዊ ፅንስ የማስወረድ መብት (ውርጃ) ሜሪስቶፕስ ክሊኒክ 3፤ ነጻ ገበያ 4፤የሃይማኖት ነጻነት በሚል ሽፋን ቀደምት ሃይማኖቶችን በሲስተም በማፈራረስ አዳዲስ ሰይጣናዊ (መናፍቃዊ ሀይማኖቶችን ማቆቆም) 5፤ ነፃ ፕሬስ የሚል ሽፋን በመያዝ ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ማሰራጨት፡፡ 👉የሰይጣን አምላኪዎች ማህበር በኢትዮጵያ? የሚስጥር ማህበርተኞች - ኢሉሚናቲ - ሰይጣን አምላኪዎች ዘመናትን ያስቆጠሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች - እውን አለማችን በአንድ መንግስት የምትመራበት ጊዜ ተቃርቧል? 👉 የዓለምን ህዝብ ቁጥር ወደ 500 ሚሊዮን የመቀነስ አላማ አለ? - የኤች አይ ቪ ቫይረስን ማን ፈጠረው? - የጦርነቶች ሁሉ ምንጭ ምንድነው? - ከሀብት፣ ስልጣንና ዝና ጀርባ ያለው ድብቅ ሚስጢር? - ጉዳዩ ኢትዮጵያን ያሰጋታል? 👉 ቁምነገር መፅሄት ቁጥር 183 ለሶደሬ የ ምንኖርባት ዓለም በብዙ እንቆቅልሾች የተሞላች ናት፡፡ እንቆቅልሾቹ ‹ሀገር ስጡኝ› ተብለው የሚመለሱ አይደሉም፡፡ ሳይገቡንና ሳንረዳቸው ዘመናት አልፈዋል፤ ያልፋሉም፡፡ በየጊዜው በመገናኛ ብዙሃኑ፣ በፊልሞች፣ በሙዚቃዎችና በመጽሐፍት አማካኝነት የሚደርሱን እውነታዎች ስለምንኖርባት ዓለም ያለን እውቀትና ግንዛቤ ቁንጽል መሆኑን የሚያስረዱ ናቸው። 👉 ሳይንቲስቶቹ ደርሰንበታል ከሚሉት የአለማችን ሚስጥራት ይልቅ ያልደረሱበት በእጅጉ የላቀ እንደሆነ ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ የሚከራከሩባቸውና እምነታቸውን የሚያስቀምጡባቸው እንጅ በማስረጃ አስደግፈው በአሳማኝ ሁኔታ ማቅረብ የማይችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ 👉 ስለሠው ልጆች አመጣጥ፣ የወደፊት ህልውናና የምድራችን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ጉዳይ የእምነት ተቋማትና አስተሳሰቦችና መጽሀፍቶቻቸው በእርግጠኝነት የሚያስቀምጧቸው አስተምህሮዎች አሉ፡፡ 👉 ( እነዚያ አስተምህሮዎች እውነት የሚሆኑት ግን ለሚያምንባቸው ብቻ ነው፡፡) ሳይንሱ ግን በመንታ መንገድ ላይ ነው፡፡ በእምነት ተቋማቱ አስተሳሰብና አስተምህሮት የማይገዛና እርግጠኛ የሆነ ሌላ የራሱ መንገድ የሌለው ነው፡፡ 👉 በየዘመናቱ የሚመጡ ሳይንቲስቶችም ሆኑ የላቀ እውቀት ባለቤት ነን የሚሉ ተመራማሪዎች የተለያዩ ‹‹እውነታዎችን›› በዓለም ማህበረሰብ ውስጥ ለማስረጽ ቢደክሙም የነሱ ሀሳብ በሌሎች ይተካል እንጅ ዘላለማዊነት ያለው አይደለም፡፡ የዓለማችን ሚስጥር የገዘፈ ነው፡፡ 👉 ከምናውቀው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው፡፡ ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ከሆነ ከ99 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለማችን ሚስጥር አይታወቅም፡፡ 👉 በቅርቡ የዓለማችን መነጋገሪያ የነበረው የማሌዥያው አውሮፕላን የገባበት አለመታወቅ የሚስጥሩ አንድ አካል ተደርጎ እየተወሰደ ነው፡፡ ከ230 በላይ ሠዎችን ጭኖ ከኳላላምፑር የተነሳው ቦይንግ አውሮፕላን የገባበት ሳይታወቅ መቅረቱ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን ለማመን በእጅጉ የሚከብድም ነው፡፡ አሁን አለ በሚባለው የቴክኖሎጂ እድገት ደረጃ በቀላሉ በራዳር እይታ ውስጥ...... ይቀጥላል....... ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

......................ክፍል ፪✝✝✝✝✝ 👉 1፤ ኦርጋኖፓስፌት በተባለ መርዝ የተቀቀለ የእርዳታ (ዮኤስኤ) ስንዴ 2፤የሚረጋ #የዘንባባ ዘይት (በውስጡ ፓልሚክ አሲድ የተባለ ኬሚካል የያዘ) 3፤ #ኮካኮላ (የሚስጢር መጠጥ) የኮካኮላ ካምፓኒ ባለቤት የኢሉሚናንቲ ማህበር ቁልፍ ሰው ሲሆን እፀ በለስ እና ሞርፌን የተባለውን መድሃኒት በማቀላቀል የኮካኮላን ድፍድፍ ማሰራት የቻለ ሲሆን ይህን የሰራለትን ፋርማሲስትም ስራውን ከጨረሰለት በኋላ ሚስጥሩን እንዳያወጣ በማሰብ በሚስጥር እንዲገደል አድርጎል፡ 👉 የኮካኮላን ሚስጥር የሚያውቁት ሰወች ፪ብቻ ሲሆኑ እነሱም ከማንኛውም ሰው ጋር ዕንዳይገናኙ ጥበቃ ይደረግባቸዋል፤ 👉 ተራውን የአለም ሕዝብም የኮካ ኮላን ቅመማ የማንነግርው ለኮፒ ራይት ደህንነት ነው በማለት ያተልሉታል፤ 👉 በአለም ሀገራት ሁሉ የሚጠመቀው የኮካ ኮላ ድፍድፍ ከ1 የዋናው ፋብሩካ በሚስጥር ከተሰራ በሆላ በበርሚል እና በቦቲ በማሸግ ለየሃገራቱ ቅርንጫፎች የሚሰራጭ ሲሆን ቅርንጫፎቹም ይሄንኑ የማያውቁትን ጥቁር ድፍድፍ ውሃ በመጨመር እና በማሸግ ለገበየ ያቀርቡታል፡፡ 👉 በሀገራችን ኢትዮጵያም ይሄው የሚስጢር ድፍድፍ በጅቡቲ ወደብ በኩል በቦቲ ተጭኖ የሚገባ ሲሆን በውሃ ተበርዞ እና ታሽጎ ለገበያ ይቀርባል፡፡ 👉 ኢሉምናንቲወችም ኮካኮላን የጠጣ ማንኛውም ሰው በውስጡ በያዘው ዕፀ በለሰስ ምክንያት የማስታወስ ቸሎታውን ስለማጣ ለሰይጣን ይገዛልናል፡ የትራፊክ አደጋ ያደርሳል፡ ለከፍተኛ የወሲብ ፍላጎት ስለሚዳረግ ዝሙት ይፈፅማል፡ አባት ልጁን ይደፍራል ብለው ያስባሉ፡፡ 👉 #የኢሉሚናንት ፀረ ሐይማኖታዊ #ህጎች..... ይቀጥላል......... ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ኢሉሚናንቲ (አለም አቀፍ የሰይጣን ማህበር) ምንድነው? #የኢሉሚናንቲ የሚስጥር መጠጥ ( #ኮካኮላ Coca Colla) ምንድነው? ኢሉሚናንቲ የተባለው የሚስጢር ማህበር በ1776 አ.ም በአዳም ዊሻፕት የተመሰረተ ሲሆን ኢሉሚናንቲ ማለት የበራለት ሌላው ሰው ማወቅ የማይችለውን ጥበብ ማወቅ የሚችል ጭንቅላት ከሰይጣን የተሰጠው ማለት ነው፡፤ የኢሉሚናንቲወች አላማ ፡ በአለም ላይ ያሉትን ሁሉንም ሃይማኖቶች እና መንግስታት በማፈራረስ አለምን በአንድ የሰው ሳይጣን (666 አውሬው) መንግስት ማስተዳደር ነው፡፡ በኢሉሚናንቲወች የተቀነባበሩ ሽብሮች እና ጦርነቶች፡ 1፤ የመስከረም 11 የአሜሪካ የሽብር ጥቃት 2፤ የቦከሃራም የጫካ ቡድን 3፡ 1ኛው እና ሁለተኛው የአለም ጦርነቶች 4፤የደቡብ አፍሪካው ዜኖፖቢያ 5፤የአይ እስ አይ ኤስ ቡድን 6የሳውዲ አረቢያው የውጭ ዜጎችን የማፈናቀል ሴራ #የኢሉሚናንቲ ታዋቂ ሰው 1፤ ከአሜሪካ ፕሬዜዳንቶች 70 በመቶ ( ጆ. ቡሽ. ክሊንተን ….) 2፡ቶፓክ. ማዶና. ሲሊንዲወን 3፤አውሮፓ ህብረት. የአለም ባንክ. ክሊንተን ፋውንዴሽን. ሜሪ ስቶፕ . ኮካኮላ #የኢሉሚናንት የሚስጥር መጠጦች / ምግቦች እነዚህ የአለምን ህዝብ አእምሮ በማደንዘዝ ተጠቃሚውን ለሃይማኖቱም ሆነ ለራሱ ቸልተኛ እንዲሆን የሚያደረጉ ፡ ለዘላቂ መሀንነት ለስኳር በሽታ ለደም ጊፊት ህመም የሚዳርጉ ሲሆኑ እነሱም........ ይቀጥላል ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝ የግእዝ ቁጥሮች በፊደል የዐረብኛ ቁጥር - አልቦ =0 ፩ አሐዱ =1 ፪ ክልኤቱ =2 ፫ ሠለስቱ =3 ፬ አርባዕቱ =4 ፭ ሐምስቱ =5 ፮ ስድስቱ =6 ፯ ስብዓቱ =7 ፰ ስመንቱ 8 ፱ ተሰዓቱ 9 ፲ አሠርቱ 10 ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11 ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12 ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13 ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14 ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15 ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16 ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17 ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18 ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19 ፳ እስራ 20 ፳፩ እስራ ወአሐዱ 21 ፳፪ እስራ ወክልኤቱ 22 ፳፫ እስራ ወሠለስቱ 23 ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 24 ፳፭ እስራ ወሐምስቱ 25 ፳፮ እስራ ወስድስቱ 26 ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 27 ፳፰ እስራ ወሰመንቱ 28 ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 29 ፴ ሠላሳ 30 ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31 ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32 ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33 ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34 ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35 ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36 ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37 ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38 ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39 ፵ አርብዓ 40 ፶ ሃምሳ 50 ፷ ስድሳ 60 ፸ ሰብዓ 70 ፹ ሰማንያ 80 ፺ ተሰዓ 90 ፻ ምዕት 100 ፻፩ ምዕት ወአሐዱ 101 ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 102 ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 103 ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104 ፻፭ መዕት ወሐምስቱ 105 ፻፮ ምዕት ወስድስቱ 106 ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107 ፻፰ ምዕት ወስመንቱ 108 ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109 ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 110 ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111 ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112 ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113 ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114 ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115 ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116 ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117 ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118 ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119 ፻፳ ምዕት ወእስራ 120 ፻፴ ምዕት ወሠላሳ 130 ፻፵ ምዕት ወአርብዓ 140 ፻፶ ምዕት ወሃምሳ 150 ፻፷ ምዕት ወስድሳ 160 ፻፸ ምዕት ወሰብዓ 170 ፻፹ ምዕት ወሰማንያ 180 ፻፺ ምዕት ወተሰዓ 190 ፪፻ ክልኤቱ ምዕት 200 ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201 ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202 ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203 ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204 ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205 ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206 ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207 ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208 ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209 ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210 ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211 ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212 ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213 ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214 ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215 ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216 ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217 ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218 ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219 ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220 ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230 ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240 ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250 ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260 ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270 ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280 ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290 ፫፻ ሠለስቱ ምዕት 300 ፬፻ አርባዕቱ ምዕት 400 ፭፻ ሐምስቱ ምዕት 500 ፮፻ ስድስቱ ምዕት 600 ፯፻ ስብዓቱ ምዕት 700 ፰፻ ስመንቱ ምዕት 800 ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 900 ፲፻ አሠርቱ ምዕት 1000 ፳፻ እስራ ምዕት 2000 ፴፻ ሠላሳ ምዕት 3000 ፵፻ አርብዓ ምዕት 4000 ፶፻ ሃምሳ ምዕት 5000 ፷፻ ሳድስ ምዕት 6000 ፸፻ ሰብዓ ምዕት 7000 ፹፻ ሰማንያ ምዕት 8000 ፺፻ ተሰዓ ምዕት 9000 ፻፻ እልፍ 10,000 ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000 ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000 ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000 ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000 ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000 ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000 ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000 ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000 ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000 ፳፻፻ እስራ እልፍ 200,000 ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000 ፵፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000 ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000 ፷፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000 ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000 ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000 ፻፻፻ አእላፋት 1,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000 ፻፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ወርኃ ጽጌ - (ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6) እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡ በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡ የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንንለጓደኞቻችን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ፍቅር ከእግዚአብሔር ቤት መራቅ ስትጀምር ፍቅር ካንተ ትርቃለች። ከምታየው ነገር ጋር ሁሉ ትጣላለህ። የምትጣላውም ከሰዎች ጋ ብቻ አይደለም። ካገኘከው ነገር ጋ እና ከራስህም ጋ ጭምር እንጂ። ከራስህ ጋ ተከራክረህ እራስህን መርታት ከማትችልበት ጭንቀት ውስጥ ትወድቃለህና የምትሞትበትን ጊዜ ታመቻቻለህ። እንደ ይሁዳ ታንቆ ለመሞት አልያም እንደ ሌሎቹ በሌላ ምክንያት እራስህን እስከማጥፋት ድረስ ማንነትህን ትጥላለህ። እራስህን እንደ ሰው መቁጠር ከማትችልበት ከባድ ሙግት ውስጥ ትወድቃለህ። በዚህም ከአምላክህ ጋ እና ከሰዎች በፍቅርና በሰላም መኖር አልችል ትላለህ። ሁልጊዜ ከሰዎች ጋ ክርክርና ጥላቻ ይሆንብሀል። ጠላትን የምታጠፋበት ትልቁ መሳሪያ ፍቅር ብቻ መሆኑን ትዘነጋለህ። ይህን የከበሩ እንቁዎች የማይተካከሉትን ልዩ ፀጋ ማጣት ማለት ሰው ሁኖ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ አለመገኘት ነው። የሰውነት መመዘኛው ትልቁ ሚዛን ፍቅር ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ንሀስ ወይንም እንደሚንሿሿ ፅናፅል ሁኛለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ፣ ሚስጥርንም ሁሉና፣ እውቀትንም ሁሉ ባውቅ፣ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፣ ስጋዬን ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋ ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሳል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይፀናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም። እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ። ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ቆሮ 13፥1-13 ፍቅር በሰዎችና በመላእክት ልሳን ከመናገር በላይ ነው። ድሆችንም ከመመገብና ስጋችንም ለእሳት አሳልፈን ከመስጠት የላቀ ነው። እውነተኛ ፈቅር የሚታገስ፣ ሁሉን የሚያምን፣ ከእውነት ጋ ደስ የሚለው፣ የማይቀና፣ ቸርነት የሚያደርግ የማይመካ፣ በደልን የማይቆጥር፣ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ ነው። ይህንን ፍቅር የምናገኘው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋ በመሆን ብቻ ነው። ምክንያቱ ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው እራሱ እግዚአብሔርም ደግሞ ፍቅር ነውና። ሐዋርያው ዮሃንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል:-ወዳጆቼ ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ የሚወደው ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ እግዚአብሔርም ስለሚያውቅ እርስ በራሳችን እንዋደድ።1ኛ ዮ 4፥7 ለዚህም ነው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሔርን ስትርቅ ፍቅር ደግሞ ከአንተ የምትርቀው። ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ በመሆኗ ትልቁ ገንዘብ ናት። ፍቅርን የምንገልፀው ሰውን እግዚአብሔርን እንዲሁም ሀገርን በመውደድ ነው። እኛም እንደታማኙ አገልጋይ ጌታ የሰጠንን መክሊት ልናተርፍበት ይገባል። በመክሊታችን ትርፋማ ለመሆን ደግም ፍቅር ትልቁን ሚና ይጫወታል። ስለዚህ ፍቅርን ለብሰን ትህትናን ተጫምተን በማስተዋል መጓዝ አለብን። የፍቅር አምላክ ፍቅርን ያድለን! የአብ_ፀጋ_የወልድ_ፍቅር_የመንፈስ_ቅዱስ_አንድነት አይለየን አሜን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንንበየቀኑ አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ኃጥያትን ስትሠራ፦ መዝሙረ ዳዊት ፶፩(51) አንብብ፣ ☞ኣደጋ ሲያጋጥምህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፺፩(91) አንብብ፣ ☞ሰዎች ቢያሳዝኑህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፳፯(27) ኣንብብ፣ ☞እግዚአብሔር ከአንተ የራቀ ሲመስልህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፻፴፩(131) አንብብ፣ ☞እምነትህ ማነቃቂያ ሲያስፈልጋት፦ ዕብራውያን ፲፩(11) አንብብ፣ ☞ብቻህን ስትሆንና ስትፈራ፦ መዝሙረ ዳዊት ፳፫(23) አንብብ፣ ☞ስትጨነቅ፦ ማቴዎስ ወንጌል ፰፡፱–፴፬(8:9–34) አንብብ፣ ☞ስትቀየምና ነቃፊ ስትሆን፦ 1ኛ ቆሮንቶስ ፫(3) አንብብ፣ ☞ስለክርስትና ግራ ሲገባህ፦ 2ኛ ቆሮንቶስ ፭፡፲፭–፲፰(5:15– 18) አንብብ፣ ☞ያልተፈለክ መስሎ ሲሠማህ፦ ሮሜ ፰፡፴፩–፴፱(8:31–39) ከንብብ፣ ☞ሠላምን ስትሻ፦ ማቴዎስ ወንጌል ፩፡፳፭–፴(1:25–30) አንብብ፣ ☞ዓለም ከእግዚአብሔር የበለጠ ሲመስልህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፺(90) አንብብ፣ ☞ክርስቶስን እንደ መታመኛህ ስትሻው፦ ሮሜ፰፡፩–፴(8:1–30) አንብብ፣ ☞ለጉዞ ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድ፦ መዝሙረ ዳዊት ፻፳፩ (121) አንብብ፣ ☞ለምትሠራው ስራ ብርታት ሲያስፈልግህ፦ ኢያሱ ፩(1) አንብብ፣ ☞የኑሮ ውድነት ባለፀጋነት ሀሳብህን ሲያጠብቡት፦ የማርቆስ ወንጌል ፲፡፲፯–፴፩(10:17–31) አንብብ፣ ☞የጭንቀት ሐሳብ ሲያስቸግርህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፳፯(27) አንብብ፣ ☞የባንክ ሂሳብህ ባዶ ሲሆን፦ መዝሙረ ዳዊት ፴፯(37) አንብብ፣ ☞በሰው ልጅ ላይ አመኔታ ስታጣ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ ፲፫(13) አንብብ፣ ☞ሰዎች የወዳጅነት ስሜት ያላሳዩህ ሲመስልህ፦ የሐንስ ወንጌል ፲፭(15) አንብብ፣ ☞ተስፋ ስታጣ፦ መዝሙረ ዳዊት ፻፳፮(126) አንብብ፣ ☞አለም ከአንተ ጋር ሲነፃፀር ትንሽ መስሎ ሲሠማህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፲፱(19) አንብብ፣ ☞ፍሬ ማፍራት ስትፈልግ፦ የዮሐንስ ወንጌል ፲፭(15) አንብብ፣ ☞የጳውሎስ የደስታ ሚስጥር፦ ቆላሲስ ፫፡፲፪–፲፯(3:12–17) አንብብ፣ ☞ከሌሎች ሰዎች ጋር በሠላም ለመኖር፦ ሮሜ ፲፪(12) አንብብ፣ ☞ሙስና ለመስራት ስታስብ፦ ትንቢተ ዕንባቆም ፪፡፮(2:6) አንብብ፣ ☞ንስሃ መግባት ስትፈራ፦ ሲራክ ፩፡፭(1:5) አንብብ፣ ☞ስለ አስራት ቦክራት ግር ካለህ፦ ሲራክ ፲፬፡፲፩(14:11) አንብብ። ፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌿🌿🌿 ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል? 🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌿🌿🌿 ሸር ሸር ሸር አድርጉ እንማማር የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ። ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን። ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት እንዲህ ነው... አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው። እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና ነው ወንጌል፦ የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን ናቸው። ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው። ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!! ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አያናውጧትም ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም! ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) ለሌሎች እንዲዳረስ SHARE እና LIKE እንዲያደርጉ በሚጠፉትና በሚድኑት መሀል የክርስቶስ መአዛ በሆኑት በቅዱሳን ስም እንጠይቃለን! ቤተክርስቲያን.... መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

«ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።" 1ኛ ዮሐ. ፬፥ ፳-፳፩ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑየበረከት ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌿🌿🌿 #የስምዎትን_ትርጉም_ያውቃሉ? 🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌿🌿🌿 1. ሆሴዕ - እግዚአብሔር ያድናል 2. ሐና - ጸጋ 3. ሔዋን - የሕያዋን ሁሉ እናት 4. ሕዝቅኤል - እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል 5. ሕዝቅያስ - እግዚአብሔር ኃይል ነው 6. መልከ ጼዴቅ - የጽድቅ ንጉሥ 7. ሚልክያስ - መልእክተኛየ 8. ሚክያስ - እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው 9. ምናሴ - ማስረሻ 10. ሣራ - ልዕልት 11. ሩሐማ - ምህረት 12. ሮቤል - እነሆ ወንድ ልጅ 13. ሰሎሞን - ሰላማዊ 14. ሳሙኤል - አምላካዊ ስም (የአምላክ ስም) 15. ሳኦል - ከእግዚአብሔር የተለመነ 16. ሴዴቅያስ - የእግዚአብሔር ጽድቅ 17. ሶፎንያስ - እግዚአብሔር ሰውሯል 18. ቃዴስ - ቅዱስ 19. በርተለሜዎሰ - የተለሜዎስ ልጅ 20. በንያስ - እግዚአብሔር አዳነኝ 21. ባሮክ - ቡሩክ 22. ቤተልሔም - የእንጀራ ቤት 23. ቤተል - የእግዚአብሔር ቤት 24. ብንያም - የቀኝ እጄ ልጅ (የደቡብ ልጅ) 25. ቶማስ - መንታ 26. ናሆም - መጽናናት 27. ናታን - እግዚአብሔር ሰጥቷል 28. ንፍታሌም - የሚታገል 29. አልዓዛር - እግዚአብሔር ረድቷል 30. አማኑኤል - እግዚአብሔር ከእኛጋር 31. አርኤል - የእግዚአብሔር ምድጃ 32. አሴር - ደስተኛ 33. አስቴር - ኮኮብ 34. አብርሃም - ታላቅ አባት (የብዙዎች አባት) 35. አቤሴሎም - አባቴ ሰላም ነው 36. አቡ - አባት 37. አብዱዩ - የእግዚአብሔር አገልጋይ 38. አቢያ - እግዚአብሔር ወንድሜ ነው 39. ኢሳይያስ - እግዚአብሔር ደህንነት ነው 40. አቤኔዘር— እግዚአብሔር እረድቶኛል 41. ኢዩኤል - እግዚአብሔር አምላክ ነው 42. ኢያሱ - እግዚአብሔር አዳኝ ነው 43. ኢይዝራኤል - እግዚአብሔር ይዘራል 44. ኢዩሣፍጥ - እግዚአብሔር ፈርዷል 45. ኢዩራም - እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ 46. ኢዩርብአም - ሕዝቡ እየበዛ ሄደ 47. ኢዮስያስ - እግዚአብሔር ይደግፋል 48. ኢዮአስ - እግዚአብሔር ሰጥቷል 49. ኢያቄም - እግዚአብሔር አቆመ 50. ኢዮአብ - እግዚአብሔር አባቴ ነው 51. ኢዮአታም - እግዚአብሔር ፍጹም ነው 52. ኢዮአካዝ - እግዚአብሔር ይዟል 53. ኤሊዔዘር - እግዚአብሔር ረዳቴ ነው 54. ኤልሳዕ - እግዚአብሔር ደህንነት ነው 55. ኤልያቄም - እግዚአብሔር ያስነሳል 56. ኤርምያስ - እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል 57. እስማኤል - እግዚአብሔር ይሰማል 58. ኬልቅያስ - እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ነው 59. ኤድን - ደስታ 60. ኬብሮን - ኅብረት 61. ዘካርያስ - እግዚአብሔር ያስታውሳል 62. ይሳኮር - ዋጋየ 63. ይዲድያ - በእግዚአብሔር የተወደደ 64. ዮሐናን - እግዚአብሔር ጸጋ ሰጭ ነው 65. ዮናስ - ርግብ (የዋህ) 66. ዮናታን - እግዚአብሔር ሰጥቷል 67. ዮአኪን - እግዚአብሔር ያቆማል 68. የካብድ - እግዚአብሔር ክብር ነው 69. ዮዳሄ - እግዚአብሔር ያውቃል 70. ዮፍታሔ - እግዚአብሔር ይከፍታል 71. ጋድ - መልካም ዕድል 72. ጎዶልያስ - እግዚአብሔር ታላቅ ነው ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

😭😭😭😭😭😭😭😭 …✞… #ወዴት_እንታደስ? ...✞… 😭😭😭😭😭😭😭😭 o ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ወደ የቱ ሐይማኖት? o ከቀደመዉ መንገድ ወደ የትኛዉ ህይወት? o ከአባቶቻችን ሐይማኖት ወደ እነማን እምነት? o በክርስቶስ ደም ከተዋጀች ቤተ ክርስቲያን ወዴት? ///….. ነዉ ወይስ ….. //// o ከጾም ወደ መብል ብቻ? o ከጥምቀት ወደ አለመጠመቅ? o ከቁርባን ወደ አለመቁረብ? o ከስርዓት ወደ ስርዓት የለሽነት? o ከቤተ ክርስቲያን ወደ አዳራሽ? o ከቅዳሴ ወደ ጩኸትና ሁከት? o እግዚአብሔርን ከማምለክ ፈላስፎችን ወደ መከተል? o የክርስቶስን ክብር ከፍ ከማድረግ ዝቅ ወደ ማድረግ? o ፈራጁን ጌታ አማላጅ ነዉ ወደ ማለት? o ቅዱሳኑን ከመቀበል ወደ አለመቀበል? o ቅዱሳኑን ከማክበር ወደ መቃወም? o ቅዱሳኑን አማላጅ ከማለት ምንም ቦታ የላቸዉም ወደማለት? o ጸበልን እንደ ተራ ዉኃ ወደ ማየት? o ከበሮን በጊታር ወደ መቀየር? o ጸናጽልን በኦርጋን ወደ መለወጥ? o ዕጣኑን በዓለማዊ ሽታ ወደ መተካት? o እምነት ብቻ ብሎ ሥራን ወደ መርሳት? ////…….. እሽ ወዴት እንታደስ? …..../// o ራስን ለካህን ወደ አለማሳየት? o መጽሐፍትን እንደ ራስ ፈቃድ ወደ መተርጎም? o መዝሙርን ዘፈን መሰል ወደ ማድረግ? o 365 ቀን ራስን ለሆድ ወደ ማስገዛት? o የሉተርን ፍልስፍና ወደ መከተል? o የእግዚአብሔርን ታቦት ጣዖት ነዉ ወደ ማለት? o በቅዱሳን ስም ምጽዋትና ዝክርት ማድረግን ወደ መርሳት? ///……ነዉ ወይስ……..//// o ሴቶች ራሳቸዉን ሳይሸፍኑ ወደሚጸልዩበት? o ሐሰተኛ ነቢያት ወዳሉበት? o ነገረ ሥራቸዉ ሁሉ ተቃዉሞ ብቻ ወደሆነበት? o ስግደትን በዝላይ ወደ መቀየር? o ጸሎትን ወደ መተዉ? o ገዳምን ንቀዉ የስጋን ዓለም ወደመረጡት? ብሉይ ኪዳን ተሽሯል ወደሚል ክህደት? o ንዋየ ቅድሳትን እንደ ተራ ዕቃ ወደ ማሰብ? o ማዕተብን ወደ መበጠስ? o መንፈሳዊ በረከት ከሚገኝበት ብርና ዶላር ወደሚቸረቸርበት? o የጌታ እናት ወላዲተ አምላክን እንደ ማንም ፍጡር ወደ መመልከት? o የቅዱሳን ተጋድሎ እንደ ተራ የሕይወት ጉዞ ወደ መቁጠር? o መስቀሉን ተራ እንጨት ነዉ ወደሚል ንቀት? o በትዕቢት ተነፍቶ እኔ ቅዱስ ነኝ ወደማለት? o ከካህን ወደ ፓስተር? o የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸዉን መጻሕፍት ወደ አለመቀበል? o የቅዱሳንን መታሰቢያ ዘላለማዊነት ጊዜያዊ ወደ ማድረግ? o ከህይወት ወደ ሞት? ///…… ተሃድሶ ስትሉ ወዴት? ……..//// o በዓላትን ወደ አለማክበር? o ከምንኩስና ወደ ዓለም ናፋቂነት? o ወንጌልን ወደ ማጣመም? o ሴት ልጅ በድፍረት የወንድ ልብስ ለብሳ አስተማሪ ነኝ ወደምትልበት? o ከእዉቀት ወደ ምንምነት? o ከእዉነተኞቹ ነቢያትና ሐዋርያት ወደ ሐሰተኞቹ? o ከምሉዕነት ወደ ባዶነት? o ከቅድስና ወደ ርኩሰት? o ከነጻነት ወደ ባርነት? o ከንግስተ ሳባ እምነት ወደ ዘመኑ ፈላስፎች? o ከኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ ክርስትና ወደ ምንፍቅና? o ከመንፈሳዊነት ወደ ዓለማዊነት? o ከክርስትና ወደ ፍልስፍና? ///……. እሽ ተሃድሶ ስትሉ ወዴት እንታደስ? ……..// እንንቃ ጓደኞቼ!!! 👇👇👇✝✝✝✝✝✝✝👇👇👇 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ስምሽን_ጠርቼ_@EOTC2921.3gp2.59 MB