fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
🎯 🎻 ✝     በገና ክራር መሰንቆ እቤቶ ሆነው መማር ይፈልጋሉ ? ከፈለጉ ቤተ ዝማሬ የYoutube ቻናላችንን Subscribe  በማረግ ቤተሰብ ይሁኑየ ክራር የበገና የመሰንቆ ተከታታይ ስልጠናዎች ✝  የመድረክ ዝማሬዎች ✝  አዳዲስ ዝማሬዎች ✝  ስብከቶች ቆየት ያሉ ዝማሬዎች የሚተላለፍበት ቤተ ዝማሬ የዜማ መሳርያዎች ማሰልጠኛ ተቋም የ Youtube ቻናላችንን የታችኛውን Link ተጭነው Subcribe , ሼር በማረግ ቤተሰብ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ይከታተሉ !                                   👇👇👇👇👇👇👇👇        https://youtu.be/wHiN2TZmkyY?subconfirmation=yes         👆 ይህን ይጫኑት     ይህን ይጫኑት 👆 ̶Promot By ,  ᴇᴏᴛᴛᴄᴘ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ                      ©ᴀʟʟ ʀɪɢʜᴛ ʀᴇsᴇʀᴠᴇᴅ 2018

#ከክፍል_ስድስት_የቀጠለ~~ 🌾✞ #ፍሬ_ቅዳሴ የአጠቃላዩ ሥርዓተ ቅዳሴ የመጨረሻ ክፍል ፍሬ ቅዳሴ ነው፡፡ ይህ ክፍል ኅብስቱና ወይኑ ወደ ሥጋ ወደሙ የሚለወጥበትን ጊዜ የሚመለከት ጸሎትና ቡራኬ የያዘ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው መረሳት የሌለበት ጉዳይ ኅብስቱና ወይኑ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔርና ደመ ወልደ እግዚአብሔር ወደመሆን የሚለወጠው በአንድ ክፍለ ጸሎት ብቻ አለመሆኑን ነው፡፡ የኅብስቱና የወይኑ የክርስቶስን ሥጋና ደም ወደ መሆን መለወጥ የአጠቃላዩ የሥርዓተ ቅዳሴው /ሥርዓተ ጸሎት/ ውጤት ነው፡፡ 🌾✞ #አኰቴተ_ቁርባን (የቁርባን ምስጋና) በቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ላይ የዋሉ ፲፬ ቅዳሴያት አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከወቅቱና ከዕለቱ በዓል ጋር እየመረመረች መጽሐፈ ግጻዌ በሚባል መጽሐፍ ምንባባትንና መዝሙራትን ወጥ አድርጋ ስትሠራ በዕለቱ የሚቀደሰውንም ቅዳሴ ምሥጢር በማስማማት ለይታ አብራ ሠርታለች፡፡ አባቶቻችን ቁርባንን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለአምላካቸው የሚያቀርቡት ምሥጋና መሆኑን ለመግለጥ “አኰቴተ ቁርባን” ብለውታል፡፡ ሁሉም ቅዳሴያት ሲጀምሩ አኰቴተ ቁርባን ዘቅዱስ…………. በረከተ ጸሎቶሙ/ ጸሎቱ ወበረከቱ/ የሃሉ ምስለ…………፤” በማለት ይጀምራሉ። ✤ቅዳሴ እግዚእ “እመጽሐፈ ኪዳን ዘነግሮሙ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቲሁ ንጹሐን…፤ ጌታችንና መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለንጹሐን ሐዋርያቱ የነገራቸው የኪዳን መጽሐፍ…..፡” ብሎ ያስቀድምና ምዕራፍ ፪ ላይ እንደሌሎቹ ሁሉ “አኰቴተ ቁርባን ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በረከተ ሣህሉ የሃሉ ምስለ…….፤” በማለት ይቀጥላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስም “ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት፣ ወአበዊነ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ወአበዊነ ቀሳውስት፣…፤ ስለ አባቶቻችን ጳጳሳት፣ ስለ አባቶቻችን ኤጲስ ቆጶሳት፣ ስለ አባቶቻችንም ቀሳውስት ጸልዩ…፤” የሚለውን ያስቀድምና ቁጥር ፫ ላይ እንደሌሎቹ ሁሉ “አኰቴተ ቁርባን” በማለት ያስተካክላል፡፡ ሌሎቹ ቅዳሴያት ግን ከላይ በገለጽነው መሠረት የሚጀምሩ ናቸው:: ✤ከዚህ በታች የምናየው የፍሬ ቅዳሴ ክፍል ለማሳያ ያህል የአባቶቻችን የሐዋርያትን ይሆናል፡፡ በጥቅሉ የፍሬ ቅዳሴው ክፍል በውስጡ በስማቸውና በአፈጻጸማቸው ልዩ ልዩ የሆነ በዛ ያሉ ንዑሳን ክፍሎችን ይዞ ይገኛል፡፡ ዐሥራ ዐራቱ ቅዳሴያት በዝርዝር ሲታዩ፡- ቅዳሴ እግዚእ፣ ዘሐዋርያት፣ ቅዳሴ ማርያም፤ ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፣ ዘጎርጎርዮስ፣ ዘአትናቴዎስ፣ ዘቄርሎስ፣ ዘሠለስቱ ምዕት፣ ዘባስልዮስ፣ ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ዘኤጲፋንዮስ፣ ዘዲዮስቆሮስ፣ ዘያዕቆብ ዘስሩግ፣ ዘጎርጎርዮስ ካልዕ በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡ ✤ቅዳሴ ሐዋርያት በውስጡ ምሥጋናና ልመና፣ ብዙዎች ትእዛዛትም በብዛት የሚገኙበት ቅዳሴ ነው፡፡ ሌሎቹን ቅዳሴያት ለማጥናት እንደመሠረት የሚሆን በመሆኑ ለምሳሌነት (ለማሳያነት) ተመርጧል፡፡ ሌሎቹ ጥቂት ለውጥ ወይም ጭማሬ ከሚኖርባቸው በቀር በዚህ መሠረትነት የሚጓዙ ናቸው፡፡ ቅዳሴውን አባቶቻችን ሐዋርያት እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው የተናገሩት፣ ያመሰገኑት ምሥጋና፤ የለመኑትም ልመና (ጸሎት) ነው፡፡ አስተጋባዒው (አደራጅቶ የጻፈው) ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው፡፡ ሲጀምርም “አኰቴተ ቁርባን ዘአበዊነ ሐዋርያት በረከተ ጸሎቶሙ የሃሉ ምስለ ፍቁሮሙ (እገሌ) ለዓለመ ዓለም” ይላል፡፡ትርጉሙም “ከልመናቸው የተነሣ የሚገኝ በረከታቸው ይደርብንና ካህናት ሥጋውን በጻሐል፣ ደሙን በጽዋዕ አድርገው ወደ መንበር የሚያቀርቡት አኰቴት፣ የሚለውጡት፣ የሚያከብሩት፤ አንድም በክብር በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ፤ አንድም የሚቀበሉት የሚያቀብሉት አኰቴት ፲፪ቱ ሐዋርያት የተናገሩት ቅዳሴ ይህ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡ ይ.ካ፡- እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ /እግዚአብሔር አድሮባችሁ ይኑር/፤ ይ.ሕ፡- ምስለ መንፈስከ /እንደቃልህ ይደረግልን (ከመንፈስህ ጋር)/፤ ይ.ካ፡- አእኩትዎ ለአምላክነ /ፈጣሪያችንን አመስግኑት/፤ ይ.ሕ፡- ርቱዕ ይደሉ /ምስጋናው እውነት ነው፤ ይገባል፡፡/፤ ይ.ካ፡- ነአኵተከ እግዚኦ በፍቁር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ፤ አቤቱ ልጅህ ወዳጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምስጋናው አብነት ሁኖን፣ በልጅህ በወዳጅህ ባደረግኸው ቸርነት እናመሰግንሃለን፡፡” ↪ #ይቀጥላል~↩ ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯‌‌

🌾✞ #ምሥጢረ_ቁርባንና_አፈጻጸሙ ✞🌾 ~ክፍል ፮~ 🌾✞ #ጸሎተ_ሃይማኖት https://t.me/EOTC2921 💠ጸሎተ ሃይማኖትን በቃልዎ መድገም ይችላሉን? በቃልዎ እያነበቡ በማስታወሻ ደብተርዎ የቻሉትን ያህል ለመጻፍ ይሞክሩ። ✤ጸሎተ ሃይማኖት የሃይማኖት ምስክርነት ነው፡፡ ምእመናን ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ሲቀበሉ ዐዋቂዎቹ (በዕድሜ) ተምረውና አምነው ምስክርነታቸውን የሚሰጡበት፤ ሕፃናት ደግሞ በክርስትና አባቶቻቸው /እናቶቻቸው/ በኩል ተመስክሮላቸው የሚከብሩበት ጸሎት ነው፡፡ ጸሎተ ሃይማኖት አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት ሰብስቦ የያዘ፤ ሊቃውንት አባቶቻችን ምሥጢር አደላድለው፣ አንቀጽ አውጥተው፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አልበው፣ ጉባኤ ሠርተው፣ መናፍቃንን ረትተውና ሃይማኖት አቅንተው የሠሩልን መሠረተ እምነት ነው፡፡ ማንኛውም ምእመን በሕይወቱ ሁሉ የሚጸልየው (የሚያነብበው)፣ በጸሎተ ቅዳሴም አንድ ሆኖ የሚዘምረው የክርስቲያናዊነቱ መታወቂያ ነው፡፡ በዕለቱ የታዘዘው ቅዳሴ የሊቃውንት ከሆነ የሚጸለየው ጸሎተ ሃይማኖት ነው፡፡ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቅዳሴ እግዚእ፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና ቅዳሴ ማርያም ከሆነ ደግሞ “አመክንዮ ዘሐዋርያት” ሕየንተ ጸሎተ ሃይማኖት (በጸሎተ ሃይማኖት ምትክ) ይጸለያል፡፡ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ በመሞከር ራስዎን ይገምግሙ፡፡ 💠ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ “ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል፤ ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል፣ በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብና ዝሙትም ያለበት ቢኖር አይቅረብ፡፡” በማለት የሚያውጀውን ዐዋጅ እንዴት ያዩታል? ✤ጸሎተ ሃይማኖት ከተደገመ በኋላ ካህኑ እጁን ሲናጻ (ሲታጠብ) የሚከተለውን ትእዛዝ ያስተላልፋል፡፡ “ዘኮነ ንጹሐ ይንሣእ እምቁርባን፤ ወዘኢኮነ ንጹሐ ኢይንሣእ ከመ ኢየዐይ በእሳተ መለኮት ዘተደለወ ለሰይጣን ወለመላእክቲሁ፤ ዘቦ ቂም ውስተ ልቡ ወዘቦ ውስቴቱ ኅሊና ነኪር ወዝሙት ኢይቅረብ፤- ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል፤ ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል፤ በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብና ዝሙትም ያለበት ቢኖር አይቅረብ፡፡” በሂደት ለማወቅ እንደተቻለው ይህን አንቀጽ ብዙዎች ምእመናን ይፈሩታል፡፡ አንዳንዶችም “ሰው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዳይቀርብ ካህናት ምእመናንን የሚያስፈራሩበት መሣሪያ ነው፡፡” እስከማለትም ይደርሳሉ፡፡ የዚህ አንቀጽ /ክፍለ ንባብ/ ዋነኛ መልእክት ግን እንደተባለው ሳይሆን ምእመናን ንስሐ ሳይገቡ በድፍረትና በግዴለሽነት ወደ ሥጋውና ደሙ እንዳይቀርቡ ማድረግ ነው፡፡ የተጣሉ ታርቀው፣ የቀሙ መልሰው፣ የበደሉ ክሰውና ንስሐ ገብተው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ እንዲቀርቡ የሚያሳስብ ትምህርት ነው፡፡ በርግጥ ከዚህ ውጪ በድፍረትና በማንአለብኝነት (ንስሐ ሳይገቡ) ተንደርድረው የሚቀርቡ ካሉ መቀጣታቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህም በድፍረትና ባለማወቅ ምእመናን እንዳይጎዱ ለመጠበቅ እንጂ በማስፈራራት ለማራቅ አለመሆኑ መታወቅ አለበት። ✤ካህኑ ከላይ የተናገርነውን እውነት እጁን ተናጽቶ ሲያበቃ በእፍኙ የያዘውን ማይ ወደ ሕዝቡ እየረጨ ይመሰክራል፡፡ እንዲህ ሲል፡- “በከመ አንጻሕኩ እደውየ እምርስሐት አፍአዊ ከማሁ ንጹሕ አነ እምደመ ኵልክሙ፤ በድፍረትክሙ ለእመ ቀረብክሙ ኀበ ሥጋሁ ወደሙ ለከርስቶስ፤ አልቦ ላዕሌየ ትኅላፍ ለተመጥወትክሙ እምኔሁ፤ ንጹሕ አነ እምጌጋይክሙ፣ ኃጢአትክሙ ዳዕሙ ይገብእ ዲበ ርእስክሙ ለእመ በንጹሕ ኢቀረብክሙ፤- እጄን ከአፍአዊ እድፍ ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ፤ ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም፤ በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጂ፣ በንጽሕና ሁናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ፡፡” ✤የተከበሩ አንባቢ ሆይ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው ይህ ምስክርነት አሁንም ቢሆን ማስፈራሪያ ወይም ማባረሪያ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እንወዳለን። ምእመናን ንስሐ ሳይገቡ በድፍረት በመቅረብ ሊመጣባቸው ከሚችል አምላካዊ ቅጣት መጠበቂያ (መከላከያ) ነው እንጂ፡፡ መፍትሔውም ኃጢአትን ለመምህረ ንስሐ በመናገር የሚሰጠውን ቀኖና ፈጽሞ በትሕትና ቀርቦ ሥጋውንና ደሙን መቀበል ብቻ ነው፡፡ ካህኑ እጁን የሚታጠብበት ምክንያትም ከዚህ ወዲያ ወደ ፍሬ ቅዳሴው የሚገባ ስለሆነ ነው። ከዚህ በኋላ ሥጋውና ደሙን ከመባረክና ከመዳሰስ ውጪ ምንም ነገር አይነካምና ነው፡፡ ይህም አይሁድ “ስቅሎ፣ ስቅሎ፤ ስቀለው፣ ስቀለው” ብለው ክርስቶስን ለሞት አሳልፈው በሰጡት ጊዜ መስፍኑ ጲላጦስ “ከደሙ ንጹሕ ነኝ! (በክርስቶስ ሞት አልተባበርኩም)” በማለት በአደባባይ እጁን መታጠቡን የሚያዘክር (የሚያስታውስ) ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ካህኑ እጁን መታጠቡ ንስሐ ሳይገቡ፣ ከበደላቸውም ሳይነጹ የሚቀርቡ ካሉ በደማቸው የማይገባ (የማይጠየቅ)፣ በኃጢአታቸውም (በድፍረታቸው) የማይተባበር መሆኑን መግለጹ ነው፡፡ ዲያቆኑም ከካህኑ ጋር አንድ ሆኖ “ይህን የካህኑን ቃል ሰምቶ ያፌዘ፣ የሣቀ፣ ዋዛ፥ፈዛዛ የተነጋገረ ቢኖር ጌታን እንዳሳዘነው፣ እጁንም በእርሱ ላይ እንዳነሣ ይወቅ ይረዳ፤ በቡራኬ ፈንታ መርገምን፣ በኃጢአት ሥርየትም ፈንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል፡፡” በማለት ገልጦ ያውጃል፤ ያስጠነቅቃል፡፡ 🌾✞ #ጸሎተ_አምኃ_ቅድሳት ይህ ጸሎት በጊዜ ቅዳሴ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ካህናትና ምእመናን በየጾታቸው ማለትም ካህናት ከካህናት ጋር፤ (ቀሳውስት ከቀሳውስት፣ ዲያቆናት ከዲያቆናት ጋር) ወንዶች ከወንዶች ጋር፤ ሴቶችም ከሴቶች ጋር፤ ከይሁዳ ሰላምታ በተለየች (በተቀደሰች ሰላምታ) ሰላም እንዲባባሉ (እጅ እንዲነሳሱ) ዲያቆኑ የሚያውጅበት ክፍል ነው፡፡ ዲያቆኑ “ተንሥኡ ለጸሎት” ብሎ ሕዝቡ ተሰጥኦውን ከመለሰ በኋላ ካህኑ “እግዚአብሔር ዐቢይ ዘለዓለም…፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ታላቅ /ከፍ ከፍ ያለ/ ነው…፤” የሚለውን ጸሎት ይጸልያል፡፡ በማስከተልም ቅዱሳን መላእክት ጌታችን በተወለደ ጊዜ ያቀረቡትን ምስጋና “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” የሚለውን በዜማ ያቀርባል፡፡ ሕዝቡም እንደካህኑ ይዘምራሉ፡፡ ከዚያም ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተአምኁ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድሳት፤ በፍጹም ሰላምና ፍቅር እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ” በማለት ያዝዛል፡፡ ሕዝቡም “ክርስቶስ አምላክነ ይረስየነ ድልዋነ ከመ ንትአማኅ በበይናቲነ በአምኃ ቅድሳት፤ ክርስቶስ አምላካችን በተቀደሰች (ልዩ በሆነች) ሰላምታ እርስ በርሳችን ሰላም እንድንባባል (ለመባባል) የተዘጋጀን ያድርገን፤” እያሉ እጅ ይነሳሳሉ። (ሰላም ይባባላሉ)፡፡ ↪ #ይቀጥላል~↩

🌾✞ #ልደቱ_ለቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ ✞🌾 ⛪️ ሰኔ ፴ 🌾✞ በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ። ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤ በዚያን ጊዜም በፍርሃት ተሞላ፤ መልአኩም እንዲህ አለው፤ 🌾✞ ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› 🌾✞ ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳) ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩) 🌾✞ በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡ (ሉቃ.፩፥፶፪-፷፬) 🌾✞ ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤ ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ። ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡››(ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱) 🌾✞ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ሄሮድስ ጌታችን ኢየሱስን ለመግደል ይፈልገው ስለነበር የተወለደ ወንድ ሁሉ እንዲገደል በወሰነው መሠረት ሕፃኑ ዮሐንስን እንዲገድሉት ጭፍሮችን ወደ ካህኑ ዘካርያስ ላከ፤ በዚህም ጊዜ አባቱ በትክሻው ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በመሠዊያው ጠርዝ ላይ ካኖረው በኋላ ወታደሮቹን መውሰድ ከቻሉ ከዚያ እንዲወስዱት ነገራቸው። ከመቅጽበትም የእግዚአብሔር መላክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው፡፡ ወታዳሮቹም ሕፃኑን ባጡት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት፡፡ ዮሐንስም አድጎ በሀገረ እስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ በበረሀ ኖረ፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም›› ብሎ የመሠከረለት ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት ነው፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ ፴ ገጽ ፬፻፸፱- ፬፻፹) 🙏የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤ አሜን።🙏 ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯‌‌

🎯 🎻 ✝     በገና ክራር መሰንቆ እቤቶ ሆነው መማር ይፈልጋሉ ? ከፈለጉ ቤተ ዝማሬ የYoutube ቻናላችንን Subscribe  በማረግ ቤተሰብ ይሁኑየ ክራር የበገና የመሰንቆ ተከታታይ ስልጠናዎች ✝  የመድረክ ዝማሬዎች ✝  አዳዲስ ዝማሬዎች ✝  ስብከቶች ቆየት ያሉ ዝማሬዎች የሚተላለፍበት ቤተ ዝማሬ የዜማ መሳርያዎች ማሰልጠኛ ተቋም የ Youtube ቻናላችንን የታችኛውን Link ተጭነው Subcribe , ሼር በማረግ ቤተሰብ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ይከታተሉ !                                   👇👇👇👇👇👇👇👇        https://youtu.be/wHiN2TZmkyY?subconfirmation=yes         👆 ይህን ይጫኑት     ይህን ይጫኑት 👆 ̶Promot By ,  ᴇᴏᴛᴛᴄᴘ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ                      ©ᴀʟʟ ʀɪɢʜᴛ ʀᴇsᴇʀᴠᴇᴅ 2018

🎯 🎻 ✝     በገና ክራር መሰንቆ እቤቶ ሆነው መማር ይፈልጋሉ ? ከፈለጉ ቤተ ዝማሬ የYoutube ቻናላችንን Subscribe  በማረግ ቤተሰብ ይሁኑየ ክራር የበገና የመሰንቆ ተከታታይ ስልጠናዎች ✝  የመድረክ ዝማሬዎች ✝  አዳዲስ ዝማሬዎች ✝  ስብከቶች ቆየት ያሉ ዝማሬዎች የሚተላለፍበት ቤተ ዝማሬ የዜማ መሳርያዎች ማሰልጠኛ ተቋም የ Youtube ቻናላችንን የታችኛውን Link ተጭነው Subcribe , ሼር በማረግ ቤተሰብ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ይከታተሉ !                                   👇👇👇👇👇👇👇👇        https://youtu.be/wHiN2TZmkyY?subconfirmation=yes         👆 ይህን ይጫኑት     ይህን ይጫኑት 👆 ̶Promot By ,  ᴇᴏᴛᴛᴄᴘ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ                      ©ᴀʟʟ ʀɪɢʜᴛ ʀᴇsᴇʀᴠᴇᴅ 2018

👩‍ ✈️ 😭 ✝    " በስደት ላይ ሆኖ እግዚአብሔርን በተለያዮ መንገዶች ማመስገን  እንዴት ደስ ይላል "     👩 በዚህ የ Youtube ቻናሌ ለእናተ ያስተምራል ያልኩት የቤተክርስቲያን ይዘት የጠበቀ የመንፈሳዊ ስራዎችን ይዤ መጥቻለሁ !‍ ሴት ልጅ ከመሆኔ አንፃር እንዲሁም ካለውበት የስደት ሀገር እንፃር ብዙ ፈተናዎችን ተቆቁሜ የራሴን ዝማሬዎችንም ለመስራትም በቅቺያለው በእግዚሐብሔር ፍቃድ እና ቸርነት ! ከዚህ በላይ እንድሰራ የእናንተ አብሮነት , ማበረታታት  ያስፈልገኛል  የ Youtube ቻናሌን Subscribe , Share በማረግ እንድታበረታቱኝ በእግዚሐብሔር ስም ጠይቃለው  ! 🙏❤ ️ መንፈሳዊ መዝሙሮች 🙏❤️  የሃይማኖታዊ ጥያቄና መልሶች 🙏❤️  የመንፈሳዊ ግጥም ፣ ወግ ፣ ትረካዎች 🙏❤️  የበጎ አድራጎት ስራዋች የሚዳሰሱበት 🙏❤️ ለእስልምና ተከታዮች በኢየሱስ ክርስቶስ  አምላክነት ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ በቂ መልስ የምሰጥበት      እንዲሁም በርካታ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች  የማቀርብበት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ቻናሌ ነው ! ከታች ያለውን Link ተጭነው Marakiye የሚለውን የ Youtube ቻናሌን Subscribe እንድታረጉልኝ በእግዚሐብሔር ስም ጠይቃለው ! 🙏  👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇                ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት . ❎█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█❎ ❎█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█❎ ❎█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█❎ ❎█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█❎ 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 .

#ከክፍል_አምስት_የቀጠለ ✤በማስከተልም ቀሪ የጸሎተ ወንጌሉ አካላት ተጸልየው ሠራኢው ዲያቆን ወንጌል ከመነበቡ በፊት “ሃሌ ሉያ ቁሙ ወአጽምኡ ወንጌለ ቅዱሰ ዜናሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነኢየሱስ ክርስቶስ፤ የንጉሥን ዐዋጅ ወንጌለ መንግሥትን ቁሙና አድምጡ፤ እርሱም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራን የሚያበስር የምስራች ነው፡፡” በማለት በማስቀደስ ላይ ያሉትን ሁሉ ያነቃቸዋል፡፡ ካህኑም “እግዚአብሔር ምስለ ኩልክሙ፤ እግዚአብሔር በረድኤት አይለያችሁ” በማለት ወንጌሉን በሚሰሙበት ጊዜ ጸጋ እግዚአብሔር እንዳይለያቸው ይባርካቸዋል፤ (ይመርቃቸዋል)፡፡ ከዚህ በኋላ በዐቢይ ድምፅ “ወንጌል ቅዱስ ዘዜነወ (ዘሰበከ) …” እያለ ለዕለቱ እንደታዘዘው የወንጌሉን ስም እያከለ (እየጠራ)ያዜማል፡፡ ሕዝቡም በበኩሉ “ስብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኵሎ ጊዜ፤ ይህን ቅዱስ ቃል የምታሰማኝ ጌታዬና አምላኬ ክርስቶስ ሁልጊዜም ለአንተ ምስጋና ይገባል፡፡” በማለት የክርስቶስን ውለታ እያስታወሰ ያመሰግናል፡፡ ✤ወንጌል ከመነበቡ በፊትና በኋላ እንደየጊዜው ሁኔታና እንደወንጌሉ ዓይነት በዜማ የሚቀርብ ልዩ ልዩ መርገፍ አለው፡፡ ይህም ምስጋና፣ የትምህርተ ሃይማኖት ምስክርነትን የያዘ ነው፡፡ “ወንጌል ቅዱስ” ብሎ ወደ ቅድስት ከወጡ በኋላ በመጀመሪያ ሠራኢው ካህን “ነዋ ወንጌለ መንግሥት” ጌትነቱን የምትናገር ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል ይህቺ ናት::” በማለት ለንፍቁ ካህን ይሰጠዋል፡፡ ንፍቁ ካህን ደግሞ “መንግሥቶ ወጽድቆ ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ፤ ጌትነቱን ቸርነቱን የምትናገር ቄሱ የሰጠኝን ወንጌልን ሰጠሁህ” እያለ ለዲያቆኑ ይሰጣል፡፡ ዲያቆኑ ደግሞ “ነስሑ ወእመኑ እስመ ቀርበት ይእቲ መንግሥተ ሰማያት፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በማወጅ ለካህኑ አመቻችቶ ይይዝለታል፡፡ ይህም ለጊዜው “ወንጌል የምትነገርበት ጊዜ ቀርቧልና ነቅታችሁ÷ ተግታችሁ ስሙ፤” ማለት ሲሆን ለፍጻሜውም “ልጅነት፣ መንግሥተ ሰማያት የምትሰጥበት ጊዜ ቀርባልና ንስሐ ግቡ፤” ማለት ነው:: ሠራኢው ካህን ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ የዕለቱን ወንጌል ጎላ ባለ ድምፅ ያነባል፡፡ ✤ወንጌል ተነቦ ሲያበቃ አስቀድመን እንደተናገርነው መርገፉ በዜማ ከቀረበ በኋላ አማናዊውን ሰላም የምትሰብክ ወንጌል ናትና ሰላማውያን ክርስቲያኖች ከካህናቱ ጀምሮ ምእመናኑ ሁሉ ይሳለሟታል፤ ይስሟታል፡፡ 💠የተከበሩ አንባቢ ሆይ አሁን ደግሞ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክሩ በቅዳሴ ጊዜ (መሐል) ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ እንዴት ሆነው ነው የሚያዳምጡት? (ምን ያህል ትኩረት ይሰጡታል?) ✅ስለ ክብረ ወንጌልና ስለጠቅላላው ጸሎተ ቅዳሴ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያስተላለፉልን ቃለ ምዕዳን የሚለውን እስኪ እንስማ! “በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃላት ሲነበቡ የሰማያውዊን ንጉሥ የተከበረ የወንጌሉን ቃል ለመስማት ከመጀመሪያቸው እስከ መጨረሻቸው ድረስ ከማመስገንና ከመቀደስ በቀር ማድነቅና ጸጥታ ሊሆን ይገባል። የምድራዊ ንጉሥ ደብዳቤ ሲነበብ አንድ ሰው እንኳን ለመናገር የማይደፍር ከሆነ፤ ቢናገርም ግርፋትና ቅጣት የሚያገኘው ከሆነ፤ የሰማያዊ ንጉሥ ደብዳቤ የምትሆን ወንጌል ስትነበብማ ቢናገር እንደምን ያለ ቅጣት (ፍዳ) ያገኘው ይሆን?” ✤ወንጌል ከተነበበ በኋላ ካህኑ የተነበቡትን መጻሕፍተ ሐዲሳትና ምስባኩን በማብራራት አጠር አድርጎ ለአስቀዳሹ ሕዝብ ያስተምራል። በዕውቀት እንዲታነፁና በእምነት እንዲጸኑ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በቅኔ ማኅሌቱ በተፈቀደላቸው ቦታ ሆነው ያዳምጡ የነበሩ ንዑሰ ክርስቲያኖች “ጻኡ ንዑሰ ክርስቲያን፤ የክርስቲያን ታናናሾች ውጡ” ተብሎ ሲታወጅ ይወጡና በተሰጣቸው በአት ይቆያሉ፡፡ የፍሬ ቅዳሴ መጀመሪያው ነውና ምሥጢረ ቁርባንንም ሊቀበሉ ገና አይችሉምና፣ ተምረው፣ መስክረውና ተጠምቀው ከምእመናን አንድነት እስኪቆጠሩ፥ ምሥጢራትንም ለመቀበል እስኪፈቀድላቸው ድረስ ፍሬ ቅዳሴውን አይሳተፉም፡፡ 🌾✞ #ጸዋትው ይህ ጸሎት ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ካህናትና፣ ስለ ማኅበረ ምእመናን ካህናት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡት ነው፡፡ ጸዋትው ማለት የምእመናን ወገኖች ማለት ነው፡፡ ስለ ጾታ ምእመናን ስለሚጸለይ ጸዋትው ተብሏል፡፡ ስለ አንዲቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም ሰላምና አነድነት፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ ስለ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን ሕይወት፣ ጤንነትና ሰላም፣ አንድነት ሠራኢው ካህንና ዲያቆኑ እያስተዛዘሉ ወደ እግዚአብሔር ምልጃ የሚያቀርቡበት ክፍል ነው፡፡ ካህኑ “ኵሎ ሕዝበ ወኵሎ መራእየ ባርኮሙ፤ ሕዝቡንና መንጋውን ሁሉ ባርክ” እያለ የሚባርክበት፣ ሕዝቡም ኪሪያላይሶን (አቤቱ ይቅር በለን!) እያለ የሚማፀንበትና ቡራኬውን የሚቀበሉበት የሥርዓተ ቅዳሴ አንዱ አካል ነው፡፡ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ ዘውስቴታ፤ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጧም ስለሚገኙ ማኅበር (ስለ ምእመናን አንድነት) ጸልዩ” ባለ ጊዜም ሕዝቡም “ማኅበረነ ባርክ ዕቀብ በሰላም፤ ማኅበራችንን ባርክልን፣ በሰላምም ጠብቅልን” በማለት እምነቱን፣ ፈቃዱንና ፍላጎቱን የሚገልጽበት ጸሎት ነው፡፡ ↪ #ይቀጥላል~↩ ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯‌‌

🌾✞ #ምሥጢረ_ቁርባንና_አፈጻጸሙ ✞🌾 ~ክፍል ፭~ 🌾✞ #ጸሎተ_ፍትሐት_ዘወልድ https://t.me/EOTC2921 💠ከላይ እንደገለጽነው ይኽ ጸሎት ምእመናን ሰግደው ሳለ ንፍቁ ቄስ ለሥርየተ ኃጢአት እንዲሆን የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ ቡራኬ በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ ሠራዒው ቄስ በመስቀል ምልክት ይባርካል፡፡ በመቀጠልም በእንተ ቅድሳትን ዲያቆን (ቄስም ቢሆን) እያነበበ ምእመናን “አሜን ኪሪያላይሶን” ወይም “አሜን እግዚኦ ተሠሃለነ” እያሉ ይማጸናሉ፡፡ 🌾✞ #ጸሎተ_ዕጣን ይህ ጸሎት ካህኑ ዕጣኑን ለማክበርና ለመባረክ በዕጣኑ ላይ የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ አምስት ቆቀር ዕጣን ተመርጦ ይቀርብና ካህኑ በዕጣኑ ላይ ጸሎቱን አድርጎ ይባርከዋል፡፡ ሦስቱን ቆቀር ዕጣን ወዲያው እንደባረከው በማዕጠንቱ ውስጥ ይጨምረዋል። አንዱን በጸሎተ ወንጌል ጊዜ፤ አንዱን ደግሞ “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን፤” በሚባልበት ወቅት ይጨምረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰግደው የነበሩ ሁሉ ይነሣሉ፤ ጳጳስ ካለ ጳጳሱ ከሌለም ቀዳሹ ቄስ ዕጣኑን ይባርካል፤ ያከብራል፡፡ ይህንንም ጸሎት የሚያደርግ ካህን ሌሊቱን፣ መዓልቱን፣ ዕለቱን፣ ወርኁን፣ ዓመቱን፣ ወንጌላዊውን ቀምሮ (አስልቶ) ማውጣት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ በመቀጠል ባለው ጸሎት ውስጥ “እማሬ” ሲል በጥንቃቄ እያመለከተ፤ “ቡራኬ” ሲልም እየባረከ ይጸልያል፡፡ ሠራዒ ቄስና ዲያቆን ከንፍቅ ዲያቆን ጋር ሁነው መንበሩን ይዞራሉ። ከዚያ በኋላ “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን …” የሚለውን ጸሎት ዲያቆኑ አሰምቶ ከጸለየ በኋላ “ንስግድ” የሚለውና ቀሪ ጸሎታት በቅደም ተከተላቸው ይቀርባሉ፡፡ 🌾✞ #የሐዲስ_ኪዳን_ምንባባት ውድ የዚህ ጽሑፍ ተከታታይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማስተዋል መርምረው ይመልሱ፡፡ 💠በቅዳሴ ጊዜ ከልዑካኑ መካከል፦ ወንጌልን ፣የሐዋርያት ሥራን፣ የቅዱስ ጳውሎስን መልእክትና ሌሎቹን መልእክታት የሚያነባቸው ማነው? ✅በዚህ ክፍል ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንባባት በልዑካኑ በየተራቸው፣ በየአባባላቸውና በየቦታቸው ሆነው ይነበባሉ፡፡ ገባሬ ሠናይ ዲያቆን የቅዱስ ጳውሎስን፣ ንፍቅ ቄስ የሐዋርያት ሥራን፣ ገባሬ ሠናዩ ካህን ወንጌልንናንፍቅ ዲያቆን ቀሪውን መልእክት ያነባሉ። ሁሉም በዜማ የሚደርስ የራሳቸው የሆነ የመግቢያና የመሰናበቻ ምስጋና (መርገፍ) ስላላቸው ከንባብ በፊትና በኋላ በዜማ ይቀርባሉ፡፡ እነዚህም መርገፎች ራሳቸውን የቻሉ ሃይማኖታዊ ምስክርነት ያላቸው ናቸው፡፡ በየመሐሉ “ተንሥኡ ለጸሎት” የሚለውና “ሰላም ለኵልክሙ” በማለት የሚቀርበው የበረከት ቃል በየቦታቸው በቅብብሎሽ ይባላሉ፡፡ “ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት..፤ ይኽ የቡራኬ (ምስጋና) ጊዜ ነው…፤” የሚለውን፤ በበዓለ ሃምሳ ከሆነ ደግሞ “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት…፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ ሞቶ ሞትን ቀማው…፤” የሚለውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ 🌾✞ #ጸሎተ_ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዕለተ ዓርብ ያስተማረው ወንጌል፣ ከትንሣኤው እሰከ ዕርገቱ ያስተማረው ደገሞ ኪዳን ይባላል፡፡ ይህም ጸሎት የዚሁ አካል የሆነ በመጽሐፈ ኪዳንም ሰፍሮ የሚገኝ ነው፡፡ ለጸሎት የተለዩ ሰባት ኪዳናት ሲኖሩ አንዱ ይህኛው ነው፡፡ የኪዳን አዳራረስ ሥርዓት በሦስቱ ጊዜያት ማለትም በሌሊት፣ በነግህና በሠርክ የተከፋፈለ ሲሆን በሥርዓተ ቅዳሴ የሚደረሰው የነግሁ በነግህ፣ የሠርኩም በሠርክ ነው፡፡ “ቅዱስ” ተብሎ የሚጀምረው ጳጳስ ካለ ጳጳስ ከሌለም ሠራኢው ካህን ነው፡፡ የሚቀርብበት ዜማ በአራራይ ነው፡፡ ሕዝቡም ኪያከ ንሴብህ (ንዌድስ)እግዚኦ፤ አቤቱ አንተን እናመሰግናለን” እያለ በየክፍሉ ከካህናት ጋር አብሮ ተሰጥዖውን በመቀበል ያመሰግናል፡፡ 🌾✞ #ጸሎተ_ወንጌል የኪዳን ጸሎት ተፈጽሞ አቡነ ዘበሰማያት ከተደገመ በኋላ ቀጣዩ የቅዳሴ ሥርዓት ወንጌል የሚነበብበት ክፍል ነው፡፡ ጸሎተ ወንጌል ደግሞ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ሆነው የወንጌልን ቃል በንቃት የሚያዳምጡበትና የሚያስተውሉበት ኃይል እንዲያገኙ ቅድመ ወንጌል የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ ጸሎቱ እንደተለመደው ዲያቆኑን፣ ሕዝቡንና ካህኑን የሚያሳትፍ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ #ዲያቆን፡- ፊቱን ወደ ሕዝቡ መልሶ “ጸልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ፤ ስለ ቅዱስ ወንጌል ጸልዩ” በማለት ያዝዛል፡፡ #ሕዝቡ፡- በያለበት በንቃት ቆሞ በአንድ መንፈስና ድምፅ “ረስየነ ድልዋነ ለሰሚዓ ወንጌል ቅዱስ፤ ቅዱስ ወንጌልን ለማዳመጥ (ለማስተዋል) የተዘጋጀን (የተገባን) አድርገን” በማለት እግዚአብሔርን ይለምናሉ፡፡ #ካህኑ፡- ከቅዱሳት መጻሕፍት እያውጣጣና እየመሰከረ የሚነበበው ወንጌል ከሰሚዎቹ ጋር እንዲዋሐድ ሰሚዎቹም እንዲዘጋጁ እንዲህ በማለት ይጸልያል፤ አምላካችንና መድኃኒታችን ሰውንም የምትወድ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱሳን የሚሆኑ ደቀመዛሙርትህንና አገልጋዮችህን ንጹሐን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዳርቻ የሰደድሃቸው አንተ ነህ፡፡ የመንግሥትህን ወንጌል ይሰብኩና ያስተምሩ ዘንድ በሕዝብህም ውስጥ ያለውን ደዌውን ሁሉ በሽታውንም ሁሉ ያድኑ ዘንድ፤ ከዓለም አስቀድሞ የነበረውን የተሰወረውን ምሥጢርህንም ያስተምሩ ዘንድ፤ አሁንም ጌታችን አምላካችን ሆይ ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክልን፤ ያሳባችንንና የልቡናችንን ዓይኖች አብራልን፤ የከበረ የወንጌልን ቃል በመጨከን እንሰማ ዘንድ የበቃን አድርገን፤ የምንሰማ ብቻ አይደለንም እንደሰማን ልንሠራም ነው እንጂ። ስለ አንዱ ፈንታ ሠላሳና ስልሳ መቶም ያማረ ፍሬ በላያችን ያፈራ ዘንድ የወገኖችህን ኀጢአት ታስተሠርይ ዘንድ በመንግሥተ ሰማያትም የበቃን እንሆን ዘንድ።” ✤ከዚህ በኋላ ዲያቆኑ ከቅዱስ ዳዊት መዝሙር ለዕለቱ የተወሰነውን አባቶቻችን በመጽሐፈ ግጻዌ ቀምረው ባዘጋጁት መሠረት ሦስቱን ስንኞች በዐቢይ ዜማ ያዜማል (ያቀርባል)፡፡ ሕዝቡም ተሰጥኦውን እየተቀባበሉ ሁለት ሁለት ጊዜ፤ ሦስተኛውን ደግሞ በጋራ (በኀብረት) ይዘምራሉ (ያቀርባሉ)፡፡ ካህኑ በዚህ ጊዜ አራቱን መዓዘን “እግዚአብሔር ልዑል ይባርክ ላዕለ ኵልነ ወይቀድሰነ በኵሉ በረከት፤ እግዚአበሔር ልዑል ሁላችንንም ይባርከን፤ በመንፈሳዊ በረከትም ያክብረን” እያለ ይባርካል፡፡ ✤ከዚህ በማስከተል አብሮ (ተያይዞ) የቀረበውን ጸሎት ከጸለየ በኋላ በመሠዊያው ዙሪያ እያጠነ አብሪ ዲያቆን ከፊት፣ ንፍቅ ካህን ወንጌሉን ይዞ አብሪውን ዲያቆን እየተከተለው መሐል ላይ ሠራኢው ካህን፣ ከኋላውም ሠራኢው ዲያቆን መስቀሉን ይዞ፣ በመጨረሻም ጥላ (ድባብ) የያዘው ዲያቆን ሆነው በመሠዊያው (በመንበሩ) ዙሪያ ዑደት ያደርጋሉ፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፤ ንፍቅ ዲያቆን (አብሪ) የነቢያት፣ ንፍቅ ቄስ የመጥምቁ ቅ/ዮሐንስ፣ ሠራኢው ካህን የጌታ፣ ሠራኢ ዲያቆን የቅ/እስጢፋኖስ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ↪ #ይቀጥላል~↩